Sunday, 9 November 2014

የቁርሾ ቋሳ – አለቅት ዝቅጠት። (ሥርጉተ ሥላሴ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 09.11.2014 /ዙሪክ – ሲዊዘርላንድ።/
በቅድሚያ ዬጸሐፊ አቶ ጌታቸው ሽፈራው “ጥቁሩ አብዮት›› እንዲሁም ዬጸሐፊ ዮፍታሔ „ስምንት ዋና ነጥቦች ከእስራኤላውያን“ ጭብጦቹ በሚሉ እርእሰ ጉዳዮች የተጻፉት የፍላጎታችን ፍሬ ነገር፤ የመንፈስ መርህና መሪ ከመሆናቸውም በላይ መንገድ ጠራጊም ናቸው። አስፈላጊነታቸውም የዓይን ያህል ናቸው። እንደዚህ መስል ጹሑፎች ናቸው „የአሻም ፈሎች“ ሆነው በቃኝን አምርተው ድምጽ የሚመራት የርትህ ሀገር የሚፈጥሩት። ስለሆነም አመሰግናለሁ ከልብ – ጸሐፍትን። ለነገሩ የጸሐፊ ጌታቸው ሽፍራውን ጹሁፍ ሌላ መጻፍ ሳያስፈልግኝ በ07.11.2014 በነበረኝ የቅኔው ልዑል የጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራም /Radio Tesgaye/ ሙሉን ተጠቅሜበታለሁ። የጸሐፊ ዮፍታሄም ለቀጣዩ ዝግጅት ታጭቷል። በተያያዘ ሁኔታ ስለ ኢቦላ ባይረስና ስለ ህዝብ ጉዳይ ግድ ስለማይሰጠው የወያኔ አስተዳደር „ጀብደኝት ..“ የተጻፈውም ወርቅ ነበር – እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)
ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
ሰሞኑን አዲስ ዜግነት ደግሞ ተስጥቶናል ሰምታችኋል አይደል የእኔ ውዶች  „የአፍሪካ ቀንድ ዜጎች“ ወይ ማላገጥ። እንዴት ተቀለደ …  ከአፍሪቃ ቀንድ ዜጎች ጋር በአካባቢያችን የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ፣ እንዲሁም በስነፅሁፍ ነክ ርእሰ ጉዳዮች፣ ካደረግሁዋቸው ውይይቶች እጅግ ብዙ ትምህርት ቀስሜያለሁ።”
የዛሬው ጸሐፊ  ገዳ ገብራብ ነገ ደግሞ ተሰፋዬ አክራም በመባል ወደ ሳውዲ ወይንም ተስፋዬ ሮቬርቶ በመባል ወደ ጣሊያን እንደ ሽንብራ ቂጣ መገላበጡን እንጠብቃለን። እንዲህ በሚጸዬፈውና ግማሽ ዕድሜውን በጨረሰበት የጥላቻ መግል ውስጥ ሆኖ ስለምን በተገፋውና በተረገጠው፤ በተገለለውና በተናቀው አማርኛ ቋንቋ መጻፍ እንዳስፈለገውም ፈጽሞ አልገባኝም። ለነገሩ እኔ ለወደቀ እንጨት ብዙም ቁብ ስለማይሰጠኝ ሰው ከፍቅር ሃፍትነቱ ወደ መፏከት ሲያሰኘው እምለው አልነበረኝም። ለቡጀሌ ለምን ጊዜ ይቃጠል?! ነገረ ግን ዛሬ የተጠላውና አጥብቆ በጥርሱ በያዘው – በተፀዬፈውም የኢትዮጵያዊነትን ሰንደቅን ከፍ ባደረገው ዬምልዕተ ቤት በዘሃበሻ  የካህዲ ጹሑፍ አቅም አግኝቶ ገልባጤን እንዲህ ሲያቀናጣ በማዬቴ ዝም ብዬው ማለፍን መንፈሴ አላስቻለውም።
በቅድሚያ እጅግ የማከብራችሁ የፁሁፌ ታዳሚዎች እና እንዲሁም ልጅነቱን ፈቅደው ለተቀበሉት „አባወራ ኦቦ ሉቤ“ የቤት ሥራ መስጠቱን ወሰንኩ። እናንተም ውዶቼ ብታነቡት አይከፋም። እርእሱ ብቻ ይበቃል። አንዲት የትውልድ ዕንቁ ብቻ አይደለም ብልህ ወጣት መሪ ክብርት ዳኛ ብርቱካንን „ከባህር የወጣች አሳ“ ሲል ቅብጥ ሲል ያዛላጠውን ጨቀጨቅ እሳቤ ለኩት … እንሆ በትሁት ቅናዊ መንፈስ ሊንኩንhttps://www.facebook.com/ethiopiazare/posts/535876466438109
http://www.ethiopiazare.com/art-56/short-story/2565-birtukan-mideksa-by-tesfaye-gebreab ጹሑፉን ከማንበባቸሁ በፊት ግን የክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዲቅሳ ዬለጠፈውን ፎቶውን እንዴት አበልቆ እንዳወጣው ተመልከቱት። በወቅቱ እኔ እንዲነሳ እጅግ ለማከብረው ወንድሜ ጽፌለት ነበር። ከዚህ በኋላም ነበር በአንድ ቀን ሌሊቱን አክዬ በጉጉት አንብቤ የጨረስኩት „ዬጋዜጠኛው ማስታወሻ“ ክፍል አንድ መጸሐፉ ብዕርና የእኔ ፍቅር ተምሶ የተቀበረው። ለማንኛው ውስጡን በሚገባ ጎብኘት አድርጋችሁ ከእነብልቱ – ፈትሹት። ጠረኑም ጠጋ አድርጋችሁ አሽቱት። በተረፈ ቀጣዩ የህሊና ፍርዱን ለክብረቶቼ ለአንባብያን ትቼ ልጅነቱን የተቀበሉለትን „አባወራ ኦቦ ሉቤ“ ከክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዲቅሳ እና ከጸሐፊ ገዳ ገብረመድህን የትኛው ለደማቸው እንደሚቀርብ እራሳቸውን ይለኩት ዘንድ በአጽህኖት አሳስባለሁ። እንዲህ የተረገጠ – የተጠቀጠቀ – የተወቀጠ – የተናቀ – የተጣለ – የተቃለለ – የተሳለቀበት አካላዊ እትብትና ሥጋ እንደ ገና ደጅ ጥናት ተሄዶለት እውቅና ሰጠኝ አስብሎ በአታሞ ያሳዳከረው ይሄው ገማና ነው። ብልሃት የሌለው ቅላት።
„ከአሜሪካ መልስ እነሆ! በህግ ኦሮሞ ሆኛለሁ። ኦሮሞ መሆን “ኢትዮጵያዊ መሆን” ማለት ግን አይደለም። ወደፊት የኦሮሞ ህዝብ ስለማንነቱ በነፃነት ሲወስን ያን ጊዜ የሚታይ ይሆናል። ኢትዮጵያዊነትን በመተው ኦሮሞ ብቻ ሆኖ መቆየት እንደሚቻል ግን ቀደም ሲል በሞጋሳ ባህል ኦሮሞነትን ከወሰዱ ግለሰቦች ተረድቻለሁ።“
ጸሐፊ ተስፋዬ ጥሩ አብሾ ተጎንጭቶ ብቻ ሳይሆን አብሾው መሥራቱን ያመለከተው መሰረታዊ ነገር የኢትዮጵያ ጠላትነቱን ዝርግፍግፍ አድርጎ ቄጤማ ማድረጉ ነው። እንዲህ ይልናል በግልጽና በስውር ሴራ በገደል ለተወረወሩ፤ ለተገደሉ፤ በስለት ለታረዱ፤ አድራሻቸው ሳይታወቅ ለቀሩ ለተፈናቀሉ ሚሊዮኖች ሥቃይ፤ ለጥላቻ አምራችነቱ፤ ተጠያቂነቱን ብዕሩ ቁማ እንሆ መሰከረች። የተከደነው ተዘሎ እንዲህ አለን ግማሽ የህይወቱን ክፍል የታገለለት አላማ በመጨረሻ በኦሮሞ ህዝብ ፊት ዋጋና ሞገስ ማግኘቱ በትክክለኛው መስመር ላይ ሲጓዝ እንደቆየ ማረጋገጫ ሆኖለታል።”የስለላ ተግባሩ፤ በ6ቢላዋ መብላቱ፤ ደም እዬተጎነጨ በደም ሰብቶ መኖሩን፤ ፍንትው አድርጎ ከነመግሉ አሳይቶናል።„ኢትዮጵያዊነት“ ሲገፋ እንዲህ ያንደፈድፋል። እንዲህ ያስቃዣል። እንዲህ ቅብጥብጥ ያደርጋል። ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ሥነ ህይወት ነው። ኢትዮጵያዊነት ልዕቅናው ሆነ ልዕልናው ዕውቅናው ጥበቡ የመረቀው የአባቱ የአደኖይ ነው። አሁን እንኳን ከሃብቱ ለመውጣት ጋዳ ሆኖ አማርኛ ቋንቋ አስጎንብሶ ያስደገድጋል። ተመስገን!
ስለነገው ቀለበጡሊ ትረካ ደግሞ „አዳማ ላይ ከብቶችን አርብቶ ለመኖር መቋመጡን“ አንብበናል። ሲያምርህ ይቀራል እንላለን። ወንዱ ቀበቶ ከሌለው አንስቶች እምናደርገውን እናውቃለን። በተረገጠና በተናቀ መሬት መልሶ መፈንጨት አይፈቀድም። „ኢትዮጵያዊነቴን ማንም ሊሰጠኝ ወይንም ሊነሳኝ አይችልም“ ባልክበት አንደበት ደግሞ ዛሬ „በህግ ኦረሞ ሆኛለሁ“ ትለናለህ። ያልሆንከውን ልትሆን እንደማትችል ታውቃዋለህ – ጌታው። እንግዲህ በሞጋሳ ስርአት መሰረት ኦሮሞነትን በኩራት የተቀበልኩ በመሆኑ በኦሮሚያና በአካባቢያችን ጉዳዮች ላይ የመፃፍ ብቻ ሳይሆን፣ የመሳተፍ ጭምር ግዴታ አለብኝ።„ አባ አዋጉ ያው ለማንኮር። ያው ለማተራመስ – ዬአረም አጥሚት። ኦሮሞ ሲከበር ልጁንም ነው። ሲወዱ እስከ ንፍጥ ልጋጉ …  ብርቴ ከዬት የመጣች መሰለችህ? የቅኔው ልዑል ጸጋዬ ገ/መድህን ምንጩ ማን መሰለህ? ለልዑሉ አክብሮት ካለህ ለእትብቱም …. „ትንሽ ሥጋ በመርፌ ትውጋ“ ይህን ለአቶ በረከት ንገራቸው – ከኑዛዜያቸው በፊት__ ያው በመስመራችሁ እዬተገናኛችሁ የሰብዕና ዘረፋችሁን አና ብላችሁት የለ። ለማንኛውም አራባና ቆቦ እዬረገጡ አምታቶ መኖር – አላጋጦ መኖር፤ በደም ቋንጣ ንግድ እንዲሁም መዘባነን ህልም ነው።
ሌላው የተነሳው ነገር የእኛን ልቦና ፈታሽና ነገር አዋቂ ሆነህ መገኘትህ ደግሞ የሚገርም ገደል ነገር ነው። ኢትዮ አማሮች ደግሞ ከወያኔ በከፋ ደረጃ የኦሮሞን ህዝብ መብቶች ለማፈን ጊዜ የሚጠብቁ መሆናቸውን የኦሮሞ ህዝብ ጠንቅቆ ሊረዳው ይገባል። በመሆኑም ከወያኔ መውደቅ ቀጥሎ የኦሮሞ ህዝብ ከባድ ፈተና የሚገጥመው ከእነዚሁ እላዩ ላይ መጥተው ቁጭ ካሉበት ሰፋሪዎች ነው።” ቃሬዛ የዋኘበት ዝልቦ ትንተና …..
እንዲህ ለዛቀጠ ለወረደ ሰብዕና፤ ተፈጥሮ ለሚያረግርግ እንዳንተ ላለ ሊሆን ይችላል። ይህ ስንጥቅና ትርትር ፈት ግልቢያ። ለጥንቁቁ የኢትዮጵያ ህዝብ አካል ለሆነው አማራ ግን የሚበልጥበት እናት ሀገሩና ሰንደቅዓላማዋ ነው። በእኔ ውስጥ ያለው ነገር እኔን እንጂ ሌላውን ሊወክል አይችልም። ትናንትም ዛሬም ማንነት ችግር ያለበት በወደቀ በተነሳ – በፈረጠ በዘለለ ቁጥር ማተባችን አንበጥስም። ተግባባን?! መስመራችን አፈራችን መሆኑን ስለምናወቅ እንደማተባችን ኖረን እንደ ማተባችን እናልፋለን። እኔን ለመተርጎም ኢትዮጵያዊነትን የማንበብ ሆነ የመተርጎምና የማመሳጠር አቅም የተሰጠው ብቻ ይሆናል ስለ እኔ ስለ ሥርጉተ ስሜት ፍላጎት ራዕይ የውስጥ አዋቂ ሊሆን የሚችለው። …. ስለዚህ የእኛን ለእኛ ተወው። አንተ የተፈጠርክበትን በደም አላባ ተዘፍቆ ውሎ ማደር፤ በሴራና በተንኮል በክቶ ቁርሾን ታቅፎ ለቂም ሰግዶ በቋሳ ዘልቦ መኖሩን ለመረጠከው ስለራስህ እንዲህ ዘርግፍ …. ዝርግፍ —-
ግን ክብሮቼ የእኔዎቹ የሀገሬ ልጆች ደሞቼ „አለቀት“ ታውቃላችሁን? አለቀት ውሃን ተግን አድርጎ ውሃን መስሎ የሚኖር ተውሳክ ነው። ከብቶች ውሃ ሲጠጡ ሰለል ብሎ ውሃን ተመሳስሎ ገብቶ ወይ አይወጣ ወይ ወደታች አይወርድ ጉሮሮ ላይ ተሰንቅሮ ከብቶችን አሰቃይቶ ይገድላል። ለዚህ ሙያ የተካኑ ሀገረሰብ ሃኪሞች አሉ። ከብቱ ከመሞቱ በፊት የባህል ሃኪሞች ከደረሱ አለቅቱ ሲወጣ ደም ጎርሶ ነው የሚወጣው። ከወጣ በኋላ ደግሞ እንደ ቅል ተነፍቶ በደም ተቀብሮ ይገኛል። የዘመናችን አለቅት ለዛውም የቁርሾና የቋሳ ቀንዳሙ ደግሞ ፀሐፊ ገብረ ጉንዳን ነው።
ሌላው ደግሞ ምንድን ነው የተባለነው? „ጉዳይ ሳይኖረኝ ወደ ምጽዋ ሄድኩ። ሰላምታ ላቀርብ“ አዬ ትዕቢት። ትናንት ወደ ምፅዋ ሄጄ ነበር። ምፅዋ የሚያስኬድ ምንም ጉዳይ አልነበረኝም። የተጓዝኩት ለቀይባህር ደረት የሞቀ ሰላምታ ለማቅረብ ብቻ ነበር። የቀይባህር የምሽት ማእበል ናፍቆኝ ነበር። የምፅዋ ሙቀት በጣም ናፍቆኝ ነበር። የጀበና ቡና እና ፈንዲሻ – ባህሩ ዳርቻ ናፍቆኝ ነበር።” …. ድንቄም ቡና “ወደሽን ቆማጤ ንጉሥ ትመርቂ” አሉ …
አላስችልህ አለህ? ግን ለመሆኑ የጤፍ ጠላ ጠጥተህን ታውቃለህ? ታቅፈው ወይንም አሽኮኮ አድርገኸው ዙር። አባቶቻችንና ወንድሞቻችን እንደ ክረምት እንጨት አካላቸው ተደርድሮ በበቀል – ታጭደው – የተቃጠሉበት – የነደዱበት – አመድ የሆኑበት ነው። የሰው ልጅ የማገዶ መሬት ነው። የአካላችን ጢሱ ከመንፈሳችን ውስጥ አለ። ለአንተ ግን እንኳን ለዚህ አበቃህ ክክክክክክክከ —- ከውስጡ ገብተህ ብትጠመቅ ምን አልባት መላ አሳጥቶ የሚያስለፈልፍ ጉድህ ይለቅህ ይሆን? እስኪ ሞክረው?
ሌላ ምን ነበር የተደስኮረልን ደጎስ ያለውን ልበወለድ ትልም „የአሜሪካ ቆይታዬን በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቄ ቀጣዩን ዳጎስ ያለ ታሪክ ቀመስ ልቦለድ ድርሰት ለመፃፍ ወደ ኤርትራ ተመልሻለሁ።” ሪፖርቱ ለዬትኛው ታዳሚህ ነው? ጉብራህን የተረገጠኽ ከቶ ይኖር ይሆን? ማን ጠዬቀኽ?! ከተሳካልህ ለአማርኛ ተነጋሪዎች ሳይሆን ለመረጥከው ቋንቋ አወራርደው … አይመስልህም? ይመስለህ።  …. „ስለክብርት ዳኛ ብርቱካን የጻፍከው እርእስ ለአንተ ነበር እኮ የተነበይከው? „ከባህር የወጣ አሳ“ ይህ የሚስማማው እንደ አንተ ላሉ ማንነታቸው ጠፍቶባቸው በበታችንት ስሜት ለሚወዛወዙ ዝልቦች ይመስለኛል። የችግርህ ቁንጮው በለው ጅራቱ ማንነትህን የሚመልስልህ መንፈስ አላገኘህም ምን አልባት ብትተረተር ልታገኘው ትችል ይሆናል። ተሰንጠቅ እና እስኪ የቀረህ ይኸው ነውና እዬው —–
„ኢትዮጵያዊ ነኝ“ ያልከን አንተው። እኛ የትኛውን አማላጅ ይሆን ዬላክንልህ? ናልን እባክህ ብለን ደጅ አልጠናነኽ? ዛሬ ደግሞ ከረፋኝ የምትለን አንተው ነህ። ትዋዥቃለህ ማህለቋ እንደተሰበረ መርከብ። ቀድሞ ነገር ለጥበብ ሰው „ሰው መሆኑ ብቻ ይበቃው በነበር“ ጥበብ የሰማይ ሥጦታ ስለሆነ ድንግልናው ቅድስናው ቤተ መቅደስ ነው። ጥበብ ታቦት ነው። የሚወደድ የሚከበር ለሥነምግባሩ በፍቅር ፈቅደው የሚገዘሉት ድንበር ወሰን ያልተሰራለት ፍጥረት ለተባለ ቀርቶ ለድንጋይ ቅሬቶች ለግዑዛን ሳይቀር እንደ ተፈጥሯቸው ብርቱ ጥንቃቄ የሚያድርግ የሰብዕና ልዩ መለያ ሰማያዊ ጸጋ ነበር። አዳካርከው … አንቦጨራቅከው …. ይብላኝላት አንተን አግብታ ለምትኖር ብዕርና ብርና …. መጥኔ! ….. ፈርዶባት … ያተረፈቸውን ፍቅር በቤንዚን አርክፍክፎ ከሚያቃጥል ግልብ ተጠግታ መለመላዋን ቀረች ….
አንተ በገዢው ፓርቲ ውስጥ ሆነህ የሰራኸው ደባ፤ ዛሬም አንተን አምነው የተጠጉትን የበላህ የቀን ጅብ ነህ። ስለላና ጥበብን እንዴት አድርገህ አጋብታሃቸው ኖርክ ከቶ … ?! ይገርማል አካልህን መክሊትህ ተሸክሞት መኖሩ … እራሱ አንድየጨለማ መጸሐፍ ያጽፋል። ዳፍንት ነህና —
ሌላው ድሉም ቅርብ እንደሆነ ተንብዬሃል። ዘለልክ …. የፈጣሪንም ሥልጣን ቀማኸው። ልክ ይኑርህ። በእጅህ ምን እንዳለ እናውቃለን። ግን እሳቱ ከዚህም አለ። የምትፎክርበት ይህ ከንቱ ዓለም በሰው ሰራሽ ጥበብ ሰክኖ አያውቅም። የፈጣሪ ታምር ብቻ ነው ደምን አርግቶ ሰውን አቁሞ የሚያስኬደው፤ መሬትን ካለ ካስማ ሰማይን ካለባላ ያቆመ አምላክ አላት … ክብርት ልዕልት ኢትዮጵያ ….  አይመስለህ ወድቃ የማትወድቅ ደክማ የማትደክም አላዛር ናት።
አሁን ግራ ቀኙ እሳት ነው። የአባ ገብርህይወትና የእማማ ብሬ ልጅ ጠ/ሚሩ እሱ ነው ያው እትብትህ። … ጽጌ መልስ ይኖራታል ብዬ ነበር …  አቮይም ተዛው ናቸው ዘሃ ግራው ተጀምሮ እስኪጨርስ ድረስ በጠላት የታጠረች ሀገር ናት ጥንታዊቷ ቀደምት ሀገር ንግሥት ኢትዮጵያ። … ግን አምላክ አላት። የማያንቀላፋ – የማይተኛ … ከቶውንም የማይረሳት …. 90 ሚሊዮን ህዝብ ከተነሳ ደግሞ የግራ ቀኙን ትዕቢቱን ሁሉ ያስተነፍሳል። የቆመ የሚመስለው ሁሉ በቁሙ ነቅዞ … ከንቱነት ይጨፍርበታል ….
ሽልማት ደግሞ ሰጠህ። ተቀናጣህ – ካለልክህ ተወጣጠርክ – ተወራጨህም። እራስህ በምናብህ በምትፈጥረው ጥያቄ ተጠይቀህ መልስ እንደሰጠኽበት ታወራለህ። „ወሎ …. ምን?“ መብቱ ያለን ሰዎች ነው የመናገር መብት ያለን። ሰባራ ገል ለምን ነበር አገልግሎት የሚውለው? እቴ አምጡልኝ እባካችሁ? ኣህ መጣልኝ  … ለእሳት መጫሪያነት … አዎን የአግልግሎት ጊዜህ መጠናቀቁን እወቀው …. ደሙ አስክሮ እራሱ ይደፋሃል … መጣፊያ – መለበጃ የድሪቶህ ማግኘትህ እያወሩ ብቻን ከመሄድ ይታደግኽ ይሆን?!
መቋጫ ለዳርቻ —- ከገለባ ጋር። እንደራስህ ኖረህ አፈር ለመሆን ያብቃህ ልበልህ ወይንስ ማንነትህን ሳታገኝ እንደባዘንክ ስንብት ይሁንልህ? የተሻለህን ውስድ። ከዜሮ በታች —
ውዶቼ የሞተ ውይብ መንፈስ ሊንክ ካስፈለጋችሁ ይኼው ነው።http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35970
ለእኔዎቹ ብቻ … አብረን በመቆዬታችን ደስ አለኝ። መለዬቴ ደግሞ ጊዜያዊም ቢሆን ከፋኝ። በሌላ ጉዳይ እስንገናኝ ድረስ ሁሉንም ውስጤን በልግስና ሸልሜ ልሰናበት። መሸቢያ ሳምንት።
ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

Zone 9 Case Sees 11th Court Delay

By: Siobhan Hagan, IPI Contributor
The International Press Institute


zone_9_blogger_101405801474
VIENNA – An Ethiopian court this week delayed proceedings for an 11th time against six bloggers and three independent journalists, who were arrested in April in connection with their activities as part of the Zone 9 collective.
The court at a hearing on Tuesday adjourned the case until Nov. 12, 2014. The nine defendants, who were arrested in Addis Ababa on April 25 and 26, have now been in pre-trial detention for over six months.
The bloggers and journalists are being held on charges of alleged terrorism and inciting violence as a result of their contact with foreign human rights organisations and opposition political parties. They are being prosecuted under Ethiopia’s controversial, 2009 anti-terrorism law.
After a joint mission to Ethiopia with the World Association of Newspapers and News Publishers (WAN-IFRA) last year, IPI called on Ethiopian authorities to release all journalists convicted under the legislation and urged that the law be amended in a way that does not inhibit constitutionally guaranteed freedom of expression rights.
IPI Senior Press Freedom Adviser Steven M. Ellis said: “The Zone 9 case not only illustrates the stifling press environment in Ethiopia, but the severely impeded judicial proceedings in this case also interfere with the defendants’ due process rights.”
The Zone 9 Trial Tracker blog calls the 11th delay a “record” in a case that has been stalled since the April arrests and marked by repeated delays.
The first delays were a result of police requests for more time to conduct investigations. The defendants were not formally charged until July 17, when they were brought to the Lideta High Court for a hearing without legal representation. When they refused to be tried without a lawyer, the case was adjourned until the next morning. At a July 18 hearing, the trial was adjourned until Aug. 4.
2014-07-22-Zone9_Collage4_1200-thumbThe Trial Tracker blog reported that at Tuesday’s hearing there was confusion regarding changes in the courtroom venue. The blog said that the hearing was pushed back as a result of two presiding judges in the case being replaced with new judges, who were unprepared to make a ruling.
Before last year’s joint IPI/WAN-IFRA mission, African Union Special Rapporteur on Freedom of Expression and Access to Information Pansy Tlakula told IPI: “[F]ollowing the 2005 general elections in Ethiopia, freedom of expression and media freedom [have] been continuously deteriorating.”
In a report released on Jan. 14 following the mission, IPI said that Ethiopia’s use of sweeping anti-terrorism law to imprison journalists and other legislative restrictions were hindering the development of free and independent media in the country.
– See more at: http://www.tadias.com/11/08/2014/defendants-in-ethiopia-zone-9-case-see-11th-court-delay/#sthash.MobBVsuQ.dpuf
- See more at: http://www.zehabesha.com/zone-9-case-sees-11th-court-delay/#sthash.guQfJpVp.dpuf

ክህደትን ክህደት፣ የካደንም ከሀዲ ለማለት ድፍረት ይኑረን ከጣሰው አንተነህ ከስዊድን

”ፕሮፌሰር መስፍንን ለቀቅ” ለሚለው ለአቶ አንተነህ መርዕድ ጽሁፍ መልስ፣ ቁ. 1
ዛሬ ኦክቶበር 8/2014 ምሳ ሰዓት ላይ አንድ ጓደኛዬ ደውሎ ”ፕሮፌሰር መስፍንን ለቀቅ” የሚለውን ጽሁፍ አንብቤው እንደሆን ጠየቀኝ። ይህ ሰው በፕሮፌሰር መስፍን ማንነት ላይ ይቅርታ ጠይቄው ስለነበር ”ቢጤህ የጻፈውን እየው” ለማልት ማሾፉ ነበር። ለፕሮፌሰር መስፍን ከወጣትነት በተለይም የትግራይ ብሄረተኞች ስልጣን ላይ ሊመጡ አጥቢያ ጀምሮ በየአደባባዩ ድምጼን ከፍ አድርጌና በጽሁፍ ጠበቃ ሆኜ ቆሜላቸዋለሁ። ሆኖም አልፎ አልፎ በሚጽፉትና በሚናገሩት ብደነግጥም የራሴን ቅን ትርጉም እየፈጠርሁለት እራሴን ሸንግዬ ስኖር በሸገር ሬዲዮ ጣቢያ ያደረጉትን ቃለ መጠየቅ ደጋግሜ ካዳመጥሁ በሗላ ግን በቅርብ የማገኛቸውን ወዳጆቼን ስለ ፕሮፌሰር መስፍን ቀደም ሲል የነበረኝ መረዳታ የተሰሳተ እንደነበር ገልጬ ይቅርታ ጠይቄአለሁ።
”ፕሮፌሰር መስፍንን ለቀቅ” የሚለው የአቶ አንተነህ መርዕድ ጽሁፍ ማስተላለፍ የፈለገው ምን እንደሆን ከመገመት ያለፈ ባላውቅም ከራሴ መረዳት፤
1ኛ/ አቶ አንተነህ ፕሮፌሰር መስፍንን ካለማወቅ በየዋህነት የጻፉት
2ኛ/ ፕሮፌሰር መስፍንን በማወቅ፤ ግን አቶ አንተነህ ስለሳቸው መናገር ፈርተው የፕሮፌሰሩን ማንነት የሚያውቁ ግለሰቦች ፕሮፌሰሩን በማጋለጥ ከነማስረጃቸው እንዲመጡ ለመጋበዝ
3ኛ/ ከ23 ዓመት በሗላ በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ዘመቻ የሚያጋልጥ ሞረሽ ወገኔ የሚባል ሲቪክ ድርጅት ተፈጥሮ ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በካናዳና በአውስትራሊያ በተጠናከረ መልክ ከመደራጀቱ ተጨማሪ አባሎቹና ደጋፊዎቹ ግልጽ ያለመሆናቸው በህዝብ መካከል የፈጠረው መጠራጠር አስደንግጧቸው፤
4ኛ/ ወይም የፕሮፌሰር መስፍንን ቃል ልጠቀምና ”ልፋጭ አንጋጣጮች” እንደሚሏቸው የሞረሽ ወገኔን ሊቀመንበር በመስደብ ከትግራይና ከሌሎች አክራሪ ብሄረተኞች በልፋጭ አንጋጣጭነት
5ኛ/ ወይስ አቶ አንተነህ እንዳሉት ፕሮፌሰር መስፍን ጃጅተዋል እና ክደዋል መባላቸው አስቆጥቷቸው፣ ከሆነስ ለምን የሞረሽን ሊቀመንበር መዝለፍ ተፈለገ?
ለሁሉም አቶ አንተነህ አስቆጣኝ ያሉትን ”ጃጄ እና ከዳ” ለዛሬ ጽሁፌ በመንደርደሪያነት ልውሰድ፣ የአቶ አንተነህን ጽሁፍ ከማንበቤ ቢያንስ ከ10 ቀን በፊት ”ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን” በ 24/10/2014 ”በአርባ ጉጉ እና አካባቢው በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል መካድ አይቻልም” ሲል ባወጣው ጽሁፍ ለምን እንዳልቀጠለ ጠይቄአቸው፤ በአንድ አካባቢ በተፈጸመ ዘር ማጥፋትና በአንድ ሰው ንግግር ማተኮሩ በጊዜው በተከሰተብን የጊዜ እጥረት ላይ በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል እየተከታተሉ የማጋለጫ ጊዜያችንን ከመሻማቱም ተጨማሪ በተለይ በግለሰብ ላይ የማተኮር ፍላጎት እንደሌላቸውና ጉዳዩን ለግለሰቦች እንደተውት ነግረውኝ፤ እኔንም አሳምነውኝ፤ ስለፕሮፌሰር መስፍን ያለኝን ቅሬታ እኔም እንደነሱ ቸላ ብዬ ትቸው ነበር።
ፕሮፌሰር መስፍንን ለነቀፋ የዳረጋቸው በተከታታይ በሸገር ሬዲዮ ጣቢያ የሰጡት ቃለ መጠየቅ ነው። በዚህ ቃለ መጠየቅ አንዳንድ እሳቸውን በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ”እናንተ የምታደንቁትን ሰው የተደበቀ መልኩን በጨረፍታ ያሳየ ቃለ መጠይቅ ነው” ሲሉ ሌሎች ደግሞ ”መስፍን ቀባሪ አጣ፣ የአውስትራሊያ ጉዞውም ለመስፍን ነፍስ ለመዝራት ነው” ይላሉ። ሌሎቹ ደግሞ ቃለ መጠየቁን በደንብ ሳያዳምጡና ፕሮፌሰሩን ሳይከታተሉዋቸው ቀርተው ሊሆን ይችላል አሁንም ቢሆን ለፕሮፌሰር መስፍን የላቀ አክብሮት አላቸው። ሆኖም ከፕሮፌሰሩ ወገን ሆኘ ሳየው ያን ቃለ መጠየቅ ባላደረጉ ኖሮ እላለሁ። ለኔ ግን፣ ቃለ መጠየቁ ባይኖር ኖር ፕሮፌሰሩን ሳላውቃቸው እቀር ነበር ብዬ በዚህ የፕሮፌሰሩን ማንነት በጨረፍታም ቢሆን ባስደመጠን ቃለ መጠየቅ እደሰታለሁ።
ፕሮፌሰር መስፍንን አንዳንዶቹ እንደሚያደንቋቸው፣ እንደሚሸልሟቸው፣ እንደሚጽፉላቸው ሳይሆን ከቃለ መጠየቁ በሗላ ያ የሰጠናቸው ክብርና ካባ ተገፎ እርቃናቸውን የቆሞ ናቸው የሚል መረዳት አለኝ። ከእንግዲህ በሗላ በቁም እያሉም ሆነ ከዚህ ዐላም እንደማነኛውም ሰው ከተለዩ በሗላ ታሪክ የሚያስታውሳቸው ከዚህ በፊት ከነበራቸው ስምና ክብር በተቃራኒው መሆኑን በተከታታይ ለማውጣት በማስበው ጽሁፍ ለማሳዬት እሞክራለሁ። በዚህም ጽሁፌ አቶ አንተነህ መርዕድ ከቻሉ በውይይቱ ቢካፈሉ አንባቢ በነቃፊና በደጋፊ መካከል በሚደረግ ውይይት አንባቢም ሆነ እኔና አቶ አንተነህ የምንማረው ነገር ይኖራል የሚል ግምት አለኝ።
ፕሮፌሰር መስፍን ከመለሰ ዜናዊ ጋር ባደረጉት የቴሌቪዥን ውይይት ”አማራ የለም” ሲሉ ውነታቸውን ነው ብዬ በአደባባይና በጽሁፍ ነቃፊዎቻቸውን ተሟግቻለሁ። ምክንያቱም፣ በዚያን ጊዜ የሳቸው አማራ የለም የገባኝ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ነው ከሚል የግል እምነቴ በመነሳት የራሴን ትርጉም በመስጠት ነበር።
የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት በጦርነትም ሆነ በህዝብ መፍለስ ባደረገው ከቦታ ቦታ መዘዋወር አንድነቱን በመፍጠሩ ዛሬ ህዝብን እያጋጩ በስልጣን ላይ ለመቀመጥ ካልሆነ በቀር የኢትዮጵያን ህዝብ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ቆቱ፣ ከንባታ፣ ሀዲያ ወዘተ ብሎ መለየት አይቻልም። ሌላው ቀርቶ ዛሬ ትግሬዎች ነን ብለው ስለሚኮፈሱ ትግሬዎች አንድ የታሪክ ተመራማሪ ”ትግሬዎች፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በሰሜን በኩል ሀገርን ከውጭ ወራሪ ለመከላከል ባደረገው ዘመቻና ጦርነት ስንት ነፍጠኛ በናቶቻቸው ጭን እንዳለፈ አያውቁም” እንዳሉት፣ የዛሬ የትግራይ ብሄረተኝነት አክራሪዎች እናቶቻቸውን እንጂ አባቶቻቸውን የሚያውቁ አይመስለኝም። ለዚህም ነው መለሰ ዜናዊ ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር ባደረገው ውይይት አማራ የለም ሲሉ የተቃውሞ ምልክት፣ አሁን ካድኸኝ አይነት ነገር ያሳየው። ታዲያ ያን የቴሌቪዥን ውይይት ዛሬ ጋ ሆኜ ሳዬው፣ ፕሮፌሰር መስፍን የኢትዮጵያን ህዝብ እንደኔ አንድ ህዝብ ነው ብለው ከማመን ሳይሆን እሳቸው ካላቸው ስር የሰደደ የአማራ ህዝብ ጥላቻ አስበው፣ አልመውና አቅደው የሰጡት መልስ ይመስለኛል። ይሄንን ጥላቻቸውን ከራሳቸው ንግግርና ጽሁፍ በቀጣይ ጽሁፎቼ ለማሳየት እሞክራለሁ። በዚህ የቴሌቪዠን ውይይት አድናቂያቸው አቶ አንተነህ መርዕድ ያለተረዱት የመሰለኝ፣ ይህ ውይይት ከመደረጉ በፊት ፕሮፌሰር መስፍን ከመለሰና ከኢሳያስ ጋር ተወያይተውና ተማምነው፣ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ የተሻለ ለውጥ ያመጣል ብለው አምነውና ደግፈውት እንዲሁም የጋራ መግባባት ላይ ደርሰው ስለነበር፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ውይይት እንዲሆን የተፈለገው ፕሮፌሰር መስፍንን የኢትዮጵያ ህዝብ ስለሚያከብራቸው መለስ ዜናዊን የኢትዮጵያ ህዝብ በሳቸው መልክ እንዲያየው የተቀነባበረ ቲያትር መሆኑንና፣ ፕሮፌሰር መስፍን ከመለሰ ዜናዊ ጋር ያላቸው ወዳጅነትና መግባባት ለህዝብ ለማሳየት መሆኑን አቶ አንተነህ የተረዱት አይመስለኝምና በድጋሚ ቃለ መጠየቁን እንዲያዳምጡት እጠይቃለሁ።
ከላይ እንዳልሁት ለዛሬው አቶ አንተነህ ሁለት ወር አስበው፣ ከወዳጅና ከጓደኛ መክረው በድፍረት ለፕሮፌሰር መስፍን ጠበቃ ለመቆምና ለመጻፍ ያነሳሳቸው ፕሮፌሰር መስፍን ጃጁና ካዱ መባላቸው ነው። እኔ ጃጄ የሚለውን ቃል የምረዳው፣ አንድ ሰው በእድሜው መግፋት ምክንያት ነገሮችን መርሳት ጀመረ ማለት ሆኖ ነው። ይህ የመርሳት ነገር ደግሞ አሁን እንዲያውም አንድ ሰው በወጣትነት እድሜ ላይ እያለ የሚጠቃበት በሽታ ሆኖዋል። ታዲያ ሞረሽ ወገኔ ፕሮፌሰር መስፍንን ጃጁ ሲል ከስድብነቱ ይልቅ እንዲያውም በአንድ ህዝብ ላይ ክፋት አስቦ ነገር ከጀርባው ላዘለ ንግግራቸው በእድሜያቸው ምክንያት አድርጎ ህዝብ ይቅርታ እንዲደረግላቸው የሚጠይቅ ”ይቅርታ ልመና” ሆኖ ነው ያገኘሁት። ካዱ የሚለው ቃልም ቢሆን፣ አንድ ሰው በቃል፣ በጽሁፍና በድምጽ እንዲሁም የሰው ምስክር ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ ብዙ ሰው በሚያዳምጠው ራዲዮ አልሆነም፣ አልተደረገም፣ አልነበረም ብሎ ሲናገር ካደ ከማለት የተለየ ቃል እንዳለው አቶ አንተነህ አማራጩን አልሰጡንም። አንድ ሰው የሆነን አልሆነም፡ የተደረገን አልተደረገም፣ የተፈጸመን አልተፈጸመም ካለ፣ ካደ ይባላል። ሰውየውም ሌላ አዲስ ቃል ካልተፈጠረለት በቀር ከሀዲ ይባላል። ፕሮፌሰር መስፍን በቃለ መጠይቃቸው በአርባ ጉጉው የአማራውን ህዝብ እልቂት አልካዱም? ክህደታቸውስ ከሀዲ አያሰኛቸውም? ወይስ በአርባ ጉጉ አማራው የኢትዮጵያ ህዝብ ቤት ተዘግቶበት፣ ቤተክርስቲያንን ሙጥኝ ያለ ከነቤተክርስቲያኑ ተከቦ በሞርተር አልነደደም?
ፕሮፌሰር መስፍንን ከሀዲ ያሰኛቸው ንግግር በሸገር ሬዲዮ ጣቢያ የአርባ ጉጉን ጭፍጨፋ አስመልክቶ በተጠየቁት ጥያቄ ”በአርባ ጉጉ የሞተው ኦሮሞው ነው፡ አማራ የሚባል ህዝብ የለም” ማለታቸው ነው”
በዚህ ንግግራቸው ፕሮፌሰሩ፣ እስላም ኦሮሞዎች ክርስቲያን ኦሮሞዋችን ገደሉ፤ እስላም ኦሮሞዎች የክርስቲያን ኦሮሞዎችን ቤተ ክርስቲያን አቃጠሉ፤ ለማለት ይሆናል። ምክንያቱም በግንቦት ወር 1984 በኦህዲድ ሰራዊት፣ በጉልበት የደከሙና መሸሽ ያልቻሉ በቤታቸው እያሉ መንደሮች በላውንቸር ሲወድሙ፣ ሰውና ከብት እንዳይወጣና እንዳይሸሽ ሆኖ ከቤቱ ጋር አብሮ ነዶዋል፤ ወደ ቤተክርስቲያን ሸሽተው ቤተክርስቲያን አጥር ጊቢ የገቡ ህጻናት፣ እናቶችና አዛውንት እንዲሁም ካህናት መስቀል ይዘው እግዞ እያሉ አብረው ከነቤተ ክርስቲያናቸው እንዲነዱ ለሁሉም ወንጀሎች ትእዛዝ ሰጪና አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ሀሰን መሀመድ የኦህዲድ ተወካይ የመንግስት ምክር ቤት አባል በመሆናቸው፣ ፕሮፌሰሩ ሊሉን የፈለጉት አቶ ሀሰን መሀመድ እስላም በመሆናቸው እስላም ኦሮሞሞቹ ክርስቲያን ኦሮሞዎችን ገደሉ ከሆነ በቀጣይ ጽሁፌ ስለ አርባ ጉጉ እልቂት ሳነሳ ግልጽ የሚሆን ይመስለኛል።
በዚያው ቃለ መጠየቃቸው አማራ ማለት ክርስቲያን ማለት ነው ስለሚሉ፣ ክርስቲያን ኦሮሞ የለም? ለማለት ከሆነ በጊዜው በዋናነት ትእዛዝ ሰጪ የነበሩት ሰው ስለሀይማኖታቸው እርግጠኛ ባልሆንም አቶ ኩማ ደመቅሳ ክርስቲያን ይመስሉኛል። በአሩሲ ውስጥ ስላለው የኦሮሞ እስላሞችና ክርስቲያኖች ጉዳይ ከተነሳ ደግሞ የፕሮፌሰር መስፍን ንግግር ከጅዋር መሀመድ ንግግር ጋር የሚቀራረብና አንድ መልክት የሚያስተላልፍ ሆኖ እናገኘዋለን።
ፕሮፌሰሩ ”የወንድ በር መውጫ” በሚሉት ጽንሰሀሳባቸው እነማንን ነጻ ለማውጣት አስበው ነው? የሚለውም ሌላ ጥያቄ ሆኖ የሚቀርብ ጉዳይ ነው። እንዲሁም ፕሮፌሰር መስፍን በአማራ ህዝብ ላይ ባላቸው ጥላቻ በአርባ ጉጉ በተደረገውን ጭፍጨፋ ተጠያቂ እንዳይኖር ለማድረግ ከሆነም፣ የሚያዛልቅ አይመስለኝም። ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖረው የአማራው ህዝብ ለመጨረሻ ጊዜ ”በቃ ብሎ” ሞረሽ ወገኔ የሚል ሲቪክ ድርጅት አቋቁሞ በአማራው ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ዘመቻን በሚቻለው መንገድ ሁሉ ለመታገል የሚያደርገውን ትግል፣ የፕሮፌሰር መስፍን አድናቂ የሆኑት አቶ አንተነህ መርዕድ ድርጅቱን ከመንቀፍ አልፈው ድርጅቱ ሊቀ መንበር አድርጎ የመረጣቸውን ሰው መዝለፍ፣ በአማራው ህዝብ ላይ ለሚፈጸመው ግፍ ተባባሪነትን ከማሳየት ያለፈ ሆኖ አይታየኝም። በችኮላ ለተጻፈው ጽሁፌ ይቅርታ እየጠየቅሁ በሚቀጥለው ጽሁፌ እንገናኝ።
ከጣሰው አንተነህ ከስዊድን (tasewanete@gmail.com)
ይቀጥላል

The day Ethiopian protestors shut a busy street in Brussels By Robele Ababya

I had the privilege to watch, with tears choking my eyes, the stunning demonstration, in front of the EU Headquarters, by heroic Ethiopians that shut a busy street in Brussels. Ethiopians converging in a display of colorful unity from all over Europe and probably beyond made history by their unique act of patriotism.


The mammoth demonstration was no doubt necessitated by the complete denial of fundamental freedom of expression and gross violations of human rights by the brutal TPLF regime in Ethiopia during its dictatorial rule of the last 23 years and counting. These heinous crimes of the ruling regime are well recorded by respectable international organizations – and even by those powers in the Western industrialized democracies such as the United Kingdom and the United States that nevertheless keep the genocidal regime afloat with generous all round support including military, security, and direct financial assistance at the expense of the taxpayers of their citizens.
It was inspiring to watch our brave Ethiopians young and old holding the beautiful true flag colored Green, Yellow, and Red without the eye-soar satanic epigram. It was enlightening to hear the hard-hitting powerful slogan “One country Ethiopia; one people Ethiopians” voiced by the enthusiastic protestors. It was glorifying to see the demonstrators demanding for the immediate and unconditional release of all political prisoners, journalists and bloggers calling the names of the victimized heroes and heroines.
TPLF colonizes Ethiopia on the watch of AU
The TPLF militia with direct support of radical Arab states such as Libya made its way to Addis Ababa walking on the blood and leaping over the corpses of fighters of both sides recruited from mainly peasant parents toiling in a feudal society. The TPLF fighters were brain-washed to overthrow the Derg and replace it with a classless society where citizens are rewarded with fair share of the national economic output according to the precept: “To each according to his needs; from each according to his ability”. Ironically, the injured or fallen combatants on both sides were victims of internecine carnage inflicted by their respective leaders professing communist Marxist – Leninist ideology.
The first evil act of Meles Zenawi regime to dismantle Ethiopia was to desecrate the Green, Yellow and Red original flag as well as remove the statute of Emperor Menilik II – the illustrious victor of the famous Battle of Adwa that became a beacon of hope in the liberation of oppressed black people on a global scale.
The following facts prove beyond any doubt that the TPLF was a puppet collection of thugs with a mission to destroy Ethiopia:-
The tyrant finally died leaving us with the legacy of: sellout of Ethiopia’s vital national interests such as active support for the separation of Eritrea; grisly heinous crimes including genocide, victims of torture, incarceration of peaceful protesters en masse; extra judiciary execution of peaceful protesters, the wailing of mothers, the agony of bereaved families, filthy jails in which hundreds of political prisoners are cruelly kept, toiling peasants in serfdom, interethnic hatred, daylight robbery of votes, pervasive corrupt practices, culture of pathological lies, demised free media, government monopoly of all pillars of democracy, blocked freedom of expression, poor educational standard, forbidden academic freedom in tertiary institutions, a land-locked country, fertile farmland ceded to the Sudan; leasing large chunks of fertile farmlands to unscrupulous foreign investors at tiny price; massive unemployment largely affecting the youth; demoralized youth addicted to psycho-thermal drugs; abject poverty; embezzlement of national treasure and diverting donor fund; rampant breach of the constitution; regional instability et al.
All in all it was a tragedy that befell Ethiopia bringing her to the precipice of catastrophe that will require divine guidance, visionary leadership and hard work in a democratic environment in order to nullify the gruesome legacy of tyrant Zenawi whom Ambassador Rice calls her friend she truly misses.
Strategy to defeat the TPLF regime
The brutal EPRDF regime is spewing its propaganda of accelerated economic growth in a ‘developmental state’. It is therefore proposed to enrich and advance the arguments provided in the following few paragraphs in order to isolate and defeat the regime.
The GERD is foremost in the propaganda of the ruling regime. But the rivers tributaries to the Blue Nile originate from the Amhara, Oromia, and Gambella regions of Ethiopia. The three regions are sitting on abundantly fertile lands and mineral resources that are usurped by TPLF leaders, their cronies and unscrupulous foreign investors. And yet it is the people of these regions that are victims of genocide, heinous crimes, and exploitation perpetrated by the TPLF regime for the last 23 years and counting! The trio should there act in unison to dethrone the TPLF corrupt warlords.
The rank-and-file members of Woyane defense and security establishment bellow the rank of Lt. Colonel or equivalent civilian ranks unaffected by corruption are indispensable in bringing change at minimum cost. This is obvious in that experience has shown that it is practically impossible to avoid their participation in the lofty struggle for regime change. It also will make sense to woo as many as possible of the 6 million cadres of the regime to join the opposition.
The OPDO and ANDM leaders should be persuaded to end their coalition and with sincere apology join other democratic opposition forces and thereby make history. I wish most sincerely that the OLF and other opposition forces wearing a tribal acronym discard their ethnic garb and join the national movement to dethrone the EPRDF brutal regime and on its grave build a strong, united, democratic and prosperous Ethiopia where compassion and the supreme rule of law are prevalent.
The greedy corrupt TPLFites leave no stone unturned to divide the Amhara and Oromo ethnic groups, just like the Fascist Italian invaders did in order to make the two numerically dominant people economically poor and politically impotent. These two major groups should emphatically say no to the intrigue of the TPLF. Furthermore the Woyane leaders falsely accuse Emperor Menilik II for ordering to cut breasts of Oromo women in Arsi. Dismiss this shameful and unfounded blatant lie meant to tarnish the image of the magnanimous victor of the famous Battle of Adwa that even his enemies. That victory at Adwa stands monumental forever for it became a beacon of hope for all black people on our globe fighting for freedom.
Let me bring to the attention of my fellow Ethiopians that a minority parochial segment of the great Oromo people had in its culture that an adult male had to cut and show the private part of mainly an Amhara male in order to get a bride. Is this not a gruesome act of savagery? Why didn’t the ruling TPLF regime bring this atrocity to light in its ongoing political indoctrination?
In closing,
Let the soul of Emmeye Meinilik rest in eternal peace. The time now is to vanquish the EPRDF at the polls in just the same way as it was convincingly done in the election of 2005. This time however denying the EPRDF daylight robbery of votes!
In a nutshell, it is of paramount importance to paralyze and dethrone the repressive ruling regime and take power in order to create a conducive environment in which to manage Ethiopia’s national resources for the benefit of all of its mosaic ethnic groups living in harmony.
I subscribe to the motto: “One country, Ethiopia; one man one vote!”
It is my ardent hope and fervent prayer that all political prisoners and prisoners of conscience in Ethiopia including:- Andualem Aragie, Eskinder Nega, Andargachew Tsige, Abraha Desta, Bekele Gerba, Reeyot Alemu, Haptamu Ayalew Daniel Shibeshi, Yeshiwas Assefa, Leaders of the Ethiopian Muslims, the 9 bloggers and 3 Journalists, Temesgen Desalegn et al are released immediately and unconditionally!
LONG LIVE ETHIOPIA!!!
rababya@gmail.com