Thursday 10 March 2016

ጥቂት ስለ ቃሊቲ የሴቶች መቆያ እና ማረሚያ ቤት – በማሕሌት ፋንታሁን

የማይቻል ነገር እንደሌለ በተግባር ለማየት ከሚያስችሉ ሁኔታዎች አንዱ የእስር ቤት ሕይወት ነው። እስር ቤት እንገባለን የሚል እሳቤ በአይምሯችን ውስጥ ስለማይኖር በአብዛኛው ከተለመደው የኑሮ ዑደት (መወለድ፣ ማደግ፣ መማር፣ መሥራት፣ ማግባት፣ መውለድ፣ ማደርጀት እና መሞት) እና ተያያዥ ጉዳዮች ተነስተን ነው የግል አቋማችንን የምንቀርፀው። “ከሰው ጋር መተኛት አልወድም/አልችልም፤ እንቅልፍ አይወስደኝም”፣”ስፕሪስ ሳልጠጣ መዋል አልችልም”፣ “የቀዘቀዘ ምግብ አልወድም”፣ “ሲጃራ ሳላጨስ መኖር አልችልም”፣ “በቀን ቢያንስ ሁለት ፊልሞችን ካላየሁ አልደሰትም”፣ “እከሊትን/እከሌን ሳላይ መዋል አልችልም”፣ “ጨለምለም ካላለ ወደ ቤት መግባት አልወድም”፣ “መብራት ካልጠፋ እንቅልፍ አይወስደኝም”እና የመሳሰሉ የማይለወጡ የሚመስሉን አቋሞቻችን ፈተና ውስጥ የሚወድቁት የእስር ሕይወትን ‹ሀ› ብለን ስንጀምር ነው። ብዙ አልችልም ብዬ የማስባቸውን ነገሮችን ችዬ ስለወጣሁበት ስለ ቃሊቲ የሴት እስረኞች ግቢ ጥቂት ልበላችሁ።
Compiled
በቃሊቲ እስር ቤት ግቢ ውስጥ ከሚገኙት8 ዞኖች ሁለቱ የሴት እስረኞች የሚኖሩበት ነው። በአንደኛው ዞን በቀጠሮ ላይ የሚገኙ ሴቶች በሌላኛው ደግሞ የተፈረደባቸው ሴቶች ይኖሩበታል። ልዩ ጥበቃ ወይም የቅጣት ቤት የሚባሉ ቤቶች አሉ። ወይም በተፈለገበት ሰዓት ይሠራሉ። ለምሳሌ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ከማንም እስረኛ ጋር እንዳትገናኝ 5ት ሰው ብቻ የሚኖርበት የቅጣት ቤት ውስጥ ነበር የምትኖረው። ISISን በመቃወም ከተጠራው ሰልፍ ጋር በተያያዘ ሚያዚያ ወር 2007 የታሰሩ ሴቶች ከሌሎች ጋር እንዳይገናኙ ለብቻቸው በተሠራላቸው ቤት ይኖሩ ነበር።
በቀጠሮ ዞን ደግሞ 5 ቤቶች ያሉ ሲሆን በፍርደኛ ግቢ 6 ቤቶች አሉ።አንድ ቤት ውስጥ ከ 40 እስከ 120 እስረኞች ይኖራሉ። ቀጠሮ ግቢ ከአንዲት አነስተኛ ሱቅ በስተቀር ሌላ ምንም ስለሌለ የተለያዩ ነገሮችን ለመገበያየት እና ፀጉር ቤት ለመጠቀም ፍርደኛ ግቢ መሄድ ግድ ይላል። ቤተሰብ መጠየቂያ ቦታው የፍርደኛ ግቢን አቋርጦ የሚገኝ ቦታ በመሆኑ፤ በቤተሰብ መጠየቂያ ሰዓቶች (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:00 ከሰዓት ከ7:30 እስከ 10:00 እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ጠዋት ከ2:30 እስከ 6:00)፤ ቀጠሮ ክልል የሚገኙ እስረኞች ከፍርደኛ ክልል ማግኘት የሚፈልጉትን ነገር ማግኘት ይችላሉ። በቀጠሮ እና ፍርደኛ ክልል መሐል 200 ሜትር ገደማ ርቀት ያለው ሲሆን በየግቢዎቹ በር እና ማማዎች ላይ ጠባቂ ፓሊሶች አሉ። ዞኖቹ (ቤቶቹ) ከአስተዳደር ጀምሮ በእስረኞች በተመረጡ የእስረኛ ኮሚቴዎች ይመራል። በየቤቱ ለሊት የሚደረግ ጥበቃ አለ። ሮንድ ይባላል። እያንዳንዷ እስረኛ ተራዋ በደረሰ ቀን ለሁለት ሰዓት ከሌላ አንድ እስረኛው ጋር ይጠብቃል። ከለሊቱ 5:00 ሰዓት እስከ 7:00 እና ከ7:00 ሰዓት እስከ 9:00 ሮንድ ተረኞች የሚጠብቁበት ሰዓት ነው። የእስረኞች ቆጠራ በቀን ሁለቴ ይካሄዳል። የጠዋት ገቢ ፓሊሶች ከጠዋቱ12:00 ላይ፤ 11:30 ላይ ደግሞ የማታ ገቢ ፓሊሶች ቆጥረው ይረከባሉ።
የስድስት ሰዓት ተጠያቂዎች
ከላይ የጠቀስኳቸው የእስረኛ”መብቶች” እኛ የስድስት ሰዓት ተጠያቂዎች ጋር ሲደርስ ቅንጦት ይሆናሉ። እንኳን በውናችን በሕልማችንም አናስበውም።”ይቺም ቂጥ ሆና ለሁለት ተከፈለች” ዓይነት ነገር ነው። ያም መብት ተብሎ ተሸራርፎ ሲሰጠን እና ስንከለከል “All animals are equal but some are more equal” የሚለው አባባል ትዝ ይለኛል። የስድስት ሰዓት ተጠያቂዎች ማለት በሽብር ወይም በአመፅ ማነሳሳት የሚል ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸውን በቀጠሮ ክልል ሆነው የሚከታተሉ ወይም ተፈርዶባቸው ፍርደኛ ክልል ያሉ ሴቶች ማለት ናቸው። ስያሜው የመጣው ከቤተሰብ ጋር ከምንገናኝበት ሰዓት የተወሰደ ነው። የምንጠየቀው 6 ሰዓት ላይ ብቻ ሲሆን እኔ በቆየሁባቸው ጊዜያት ከ10 ደቂቃ እስከ 30 ደቂቃ ለሚሆን ቅፅበት ነበር። የመጀመሪያዎቹ የስድስት ሰዓት ተጠያቂዎች ለ5 ደቂቃ ብቻ ይገናኙ እነደነበር ሰምቻለሁ። ከዚህ በተጨማሪም የምንጠየቀው በቅርብ ቤተሰቦች ብቻ ነው። ያለንበት ዞንም ሆነ ቤት በኮሚቴነት መመረጥም መምረጥም አንችልም። ሮንድ ጥበቃ እኛን አያካትትም። ፍርደኛ ግቢ ሄዶ መገበያየት ይናፍቀናል። ቢበዛ የ6 ሰዓት ተጠያቂ ያልሆነ(ኖርማል) እስረኛ እንድንልክ ቢፈቀድልን ነው። ሆኖም ግን አስጠጪ እስረኞች ሰበብ ፈልገው የሚላኩትን ኖርማል እስረኞች ለአሸባሪ ይላላካሉ የሚል ክስ ስለሚያቀርቡባቸው፤ የሚላክልን ማግኘት እስቸጋሪ ነው።
ክሊኒክ እና ፀጉር ቤት ለመሄድ ስንፈልግ ለብቻችን አጃቢ ተመድቦልን ነው። የምትመደብልን አጃቢ ፀጉር ቤት ውስጥ ገብታ ተሰርተን እስክንጨርስ ጠብቃ ይዛን ትመለሳለች። ይሄ ሲገርመን የሆነ ጊዜ ላይ ፓሊሶች የሚሰሩበት ፀጉር ቤት እንድንጠቀም መመሪያ ተላለፈ። ይህ መመሪያ ከተላለፈ በኋላ የሆነ ቀን ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ ፀጉር ቤት ለመሄድ ጠይቃ፤ አጃቢዋ እየወሰደቻት የተላለፈውን መመሪያ ስትነግራት “እኔ እስረኛ ነኝ። ለምንድነው የፓሊስ ፀጉር ቤት የምሰራው? ይቀራል እንጂ!” ብላ ፀጉሯን መሠራቱን ትታ ተመለሰች። እስክትወጣ ድረስም በአቋሟ እንደፀናች ነበር። ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬም የሚደርስብንን መገለል በመቃወም ፀጉሯን በመላጨት መልዕክት አስተላልፋአለች።
ስድስት ሰዓት ላይ ቤተሰብ ልንጠይቅ ስንወጣ እና ስንገባ በአጃቢ ነው። ቤተሰብ ስናወራም የምናወራውን የሚሰሙ ከኛም ከቤተሰባችንም በኩል ፓሊሶች ይቆማሉ። ቤተሰብ ለማገናኘት ከሚወስዱን አጃቢ ፓሊሶች በማይሰሙት ቋንቋ ከቤተሰብ ጋር ማውራት አይቻልም። ከግቢያችን ስንወጣም ሆነ ወደ ግቢያችን ስንገባ ከኖርማል እስረኞች በተለየ ብርበራ ይካሄድብናል። ቤተሰብ ልንገናኝ ስንሄድ ፍርደኛ ክልል ያሉ የሚያቁን እስረኞችን ጋር በዓይን እንኳን ሰላም መባባል አይቻልም። እነሱም ሰላም ካሉን የተለያየ ቅጣት ይደርስባቸዋል። እኛ በምናልፍበት ሰዓት ከቤት እንዳይወጡ መከልከል፣ በካቴና መታሰር እና በአጃቢ መንቀሳቀስ የተለመዱት ዓይነት ቅጣቶች ናቸው። ባስ ሲልም እስከ አመክሮ መከልከል ይደርሳል። ማንኛውም ዓይነት ጽሑፍ የተጻፈባቸው ማስታወሻ ደብተሮቻችን በፍተሻ ወቅት ይወሰዳሉ። ፍተሻዎች እኛ ላይ እና ከኛ ጋር ይቀራረባሉ የሚባሉ እስረኞች ላይ ይበረታል። በፍተሻ ወቅት እራሳቸው ሳንሱር አድርገው ያስገቡት መጽሐፍ ሳይቀር ይወሰድብናል። መጽሐፍት ሳንሱር ሰበብ እንዳይገቡ/እንዲመለሱ ይደረጋል። ከሚገቡልን መጽሐፍት የሚመለሱት ይበልጡ ነበር። ሌሎች እስረኞችን በማይመለከት “ሕግ” በመተዳደራችን የተነሳም፤ በእስረኞችም ሆነ በፓሊሶች ዘንድ እንደ ልዩ ፍጡር ነው የምንታየው።
ቤተሰቦቻችንም ሊጠይቁን ሲመጡ የሚደርስባቸው እንግልት ከሁሉ የከፋ ነው። እኛ እስረኞች በመሆናችን የመጠየቂያ ሰዓታችን መቼም ሆነ መቼ ለውጥ የለውም። ጠያቂዎቻችን ግን ከ6ሰዓት በፊት ግቢ ውስጥ መድረስ አለባቸው። አንድ ደቂቃ እንኳን አሳልፈው በር ላይ ቢደርሱ የሚሰማቸው የለም። በዚህ ምክንያት ቤተሰቦቻችን በር ደርሰው ሳያዩን የሚመለሱባቸው ቀናት ጥቂት አይደሉም። በ6ሰዓት ተጠያቂዎች እና ጠያቂዎች ላይ የሚደርሰው በደል ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም።
በሕገ መንግሥታችን አንቀፅ 21 ላይ በጥበቃ ስር እና ተፈርዶባቸው በእስር ስላሉ ሰዎች መብት ሲያስቀምጥ ምንም አይነት ልዩነት አላስቀመጠም። ወንዶች ጋር ከታዋቂ ጋዜጠኞች፣ የፓርቲ አመራራት እና የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በስተቀር የስድስት ሰዓት ተጠያቂ የሚባል ነገር የለም። ከተመሳሳይ ወንጀል ከተከሰሱ/ከተፈረደባቸው ወንዶች ጋር እንኳን በእኩል አይደለም እንታይ የነበረው። በዚህም በሕገመንግስቱ አንቀፅ 35 የተደነገገውን የሴቶች ከወንዶች ዕኩል የመታየት መብት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር መጣሱን ማየት ይቻላል። እነዚህ በሕገ መንግሥት የተደነገጉ መብቶች፤ በማረሚያ ቤቱ አስተዳደር እየተጣሰ እንዳለ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ብናሰማም ተገቢውን ምላሽ አናገኝም። ወይ በማረሚያ ቤት አስተዳደር ጉዳይ አያገባኝም ይላሉ፣ ወይም የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ምላሽ እንዲሰጥበት ያዛሉ። የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ኃላፊዎች በአካልም ተገኝተውም፤ በጽሑፍም የስድስት ሰዓት ተጠያቂ የሚባል ነገር እንደሌለ እና ከሌሎች እስረኞች በተለየ አናያቸውም ብለው ዓይን ያወጣ ውሸት ይዋሻሉ። እነዚሁ ኃላፊዎች ወደ ግቢ ሲመለሱ የስድስት ሰዓት ተጠያቂዎች ብለው በማስታወቂያ አስጠርተው ይሰበስቡንና ፍርድ ቤት መናገራችን ለውጥ እንደማያመጣ ይነግሩናል።
ታዲያ እራሱ መንግሥት ለሴቶች አስከበርኩ ያለውን መብት እራሱ እየጣሰ፤ ግን ደግሞ በየዓመቱ የሴቶች ቀን እያለ ስለ ሴቶች መብት መደስኮር በፍፁም የማይጣጣም እና የኢሕአዴግን መንግሥት ግብዝነት የሚያሳይ ነው።
በቃሊቲ የስድስት ሰዓት ተጠያቂ የነበሩ እንዲሁም አሁንም እዛው ያሉ ሴት እስረኞች* ዝርዝር የሚከተሉት ናቸው።
  1. እማዋይሽ ዓለሙ– በ2001 ሚያዚያ ወር ጀምሮ በእስር ትገኛለች። መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ተንቀሳቅሳችኋል በመባል በእነ ብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ ከተከሰሱት ውስጥ አንዷ ስትሆን የዕድሜ ልክ ፍርድ ተፈርዶባት በቃሊቲ የምትገኝ ነች።
  2. ሒሩት ክፍሌ -ከ2003 ሰኔ ወር ጀምሮ በእስር ትገኛለች። በነኤልያስ ክፍሌ መዝገብ ከተከሰሱት 5 ሰዎች አንዷ ናት። የሽብር ክስ ተመስርቶባት 14 ዓመት ተፈርዶአባት በቃሊቲ የምትገኝ ነች።
  3. ጫልቱ ታከለ – ትውልዷእና ዕድገቷ ምስራቅ ወለጋ ነው። ከኦነግ ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው በ2000 ከታሰሩ በርካታ ኦሮሞዎች መሃከል አንዷ ናት። የተፈረደባት 12 ዓመት ሲሆን፤ ከ7ዓመት በላይ በእስር አሳልፋለች። አሁን በቃሊቲ ትገኛለች።
  4. ባጩ መርጋ -የ18 ዓመት ፍርድ ተፈርዶባት በቃሊቲ የምትገኝ።
  5. ቢፍቱ -የ18ዓመት ፍርድ ተፈርዶባት በቃሊቲ የምትገኝ።
  6. ድርቤ (ቦንቱኢታና -በ2002 በራሷ ሥም በተከፈተው መዝገብ (እነ ድርቤ ኢታና) ከተከሰሱት 7 ሰዎች አንዷ ስትሆን የሞት ፍርድ ተወስኖባት በቃሊቲ የምትገኝ።
  7. ኡርጌ አበበ -በ2002 እነ ድርቤ ኢታና መዝገብ ከተከሰሱት 7 ሰዎች አንዷ ስትሆን የሞት ፍርድ ተወስኖባት በቃሊቲ የምትገኝ።
  8. ሃዋ ዋቆ – የቦረና ልጅ ናት። በ2003 በነበቀለ ገርባ መዝገብ ከተከሰሱት 9 ሰዎች አንዷ ናት። በሽብር ተከሳ 5 ዓመት ተፈርዶባት የነበረ እና በ2007 ግንቦት ወር አካባቢ ፍርዷን ጨርሳ የወጣች።
  9. ሂንዲያ ኢብራሂም – የሶማሌተወላጅ ስትሆን በሽብር ወንጀል ተከሳ 6 ዓመት ተፈርዶባት የነበረ። ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር አካባቢ ፍርዷን ጨርሳ የወጣች።
  10. ኡሜማ አሕመድ -የሶማሌ ተወላጅ ስትሆን በሽብር ወንጀል ተከሳ 6 ዓመት ተፈርዶባት የነበረ። ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር አካባቢ ፍርዷን ጨርሳ የወጣች።
  11. አበራሽ ኢቲቻ -በ2000 ላይ ለኦነግ የገንዘብ ዕርዳታ በማድረግ እና የኦነግ አባል ናችሁ ተብለው በነኢንጂነር መስፍን አበበ መዝገብ ከተከሰሱት 16 ሰዎች ውስጥ አንዷ ናት። አስር ዓመት ተፈርዶባት በ2007 ሰኔ ወር ላይ ፍርዷን ጨርሳ ከእስር ተለቃለች።
  12. ህደያ ከድር -በ2006 ነሐሴ ወር በረመዳን ፆም ወቅት ተቃውሞ በነበረባቸው ጁምአ ቀናት በአንዱ ቀን ከመንገድ ላይ ተይዛ ከእህቷ ራቢያ ከድር ጋር የታሰረች። 5ወር ተፈርዶባት የነበረ ሲሆን ፍርዷን ጨርሳ የወጣች።
  13. ራቢያ ከድር -በ2006 ነሐሴ ወር የረመዳን ፆም ወቅት ተቃውሞ በነበረባቸው ጁምአ ቀናት በአንዱ ቀን ከመንገድ ላይ ተይዛ ከእህቷ ህደያ ከድር ጋር የታሰረች። 5ወር ተፈርዶባት የነበረ ሲሆን ፍርዷን ጨርሳ የወጣች።
  14. ሃያት አሕመድ – ከሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ጋር በተያያዘ ከአዳማ ከተማ ከተያዙ ሙስሊሞች አንዷ ናት (በእነ አብዱላዚዝ መዝገብ)። በ2005 የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስዳ ውጤቷን በመጠባበቅ ላይ እያለች ነው የድንገቴ እስር የገጠማት። በእስር ሆና ክሷን ለዓመት ከስምንት ወር ስትከታተል ቆይታ በነፃ ተለቃለች። (ማእከላዊ 4 ወር ቆይታለች)
  15. ፈቲያ መሐመድ – ከሙስሊምመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጋር በተያያዘ ከአዲስ አበባ እና ከሌሎች ዩንቨርስቲ እና ኮሌጅ ተይዘው ከታሰሩት ውስጥ ናት። ለዓመት ከስድስት ወር ያክል ክሷን በእስር ሆና ስትከታተል ቆይታ 6 ወር የተፈረደባት ሲሆን ከተፈረደባት የፍርድ ልክ በላይ በእስር በመቆየቷ በጥቅምት ወር 2007 ከእስር ወጥታለች። (ማእከላዊ 4 ወር ቆይታለች)
  16. መርየም ሐያቱ -ከሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጋር በተያያዘ ከአዲስ አበባ እና ከወልቂጤ ኮሚቴውን ለመተካት ሲንቀሳቀሱ ነበር ተብለው ከተያዙት (እነ ኤልያስ ከድር) ውስጥ አንዷ ናት። መርየም በ2005 መጨረሻ አካባቢ ከወልቂጤ ነው የተያዘችው። ከሁለት ዓመት አራት ወር የፍርድ ቤት መንከራተት በኋላ በታኅሳስ ወር 2008፣ 7ዓመት ተፈርዶባት ቃሊቲ የምትገኝ። (ማእከላዊ 4ት ወር ቆይታለች)
  17. ሃያተልኩብራ ነስረዲን – ከ5ት ወር የማዕከላዊ ቆይታ በኋላ ‹የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ› የተባለ ‹የሽብርተኛ ድርጅት› ጋር ግንኙነት በማድረግ በሚል ሐምሌ ወር 2007 ላይ ክስ ከተመሰረተባቸው 20 ሰዎች ውስጥ አንዷ ሆና ቃሊቲ እስር ቤት ገባች። ከወራት በፊት ችሎት እንዲቀየርላቸው ያመለከቱ ሲሆን፤ እስካሁን አቤቱታቸው ባለመመለሱ የዐቃቢ ሕግ ምስክሮችን መሰማት አልተጀመረም።
  18. 18ኤዶምካሳዬ(ጋዜጠኛ) – በሚያዚያ 17/2006 ተይዛ ማዕከላዊ ለሦስት ወራት ከቆየች በኋላ ክስ ተመስርቶባት ቃሊቲ እስር ቤት ገባች። የኅብረተሰቡን ደኅንነት አደጋ ላይ ለመጣል አሲራችኋል፣ አቅዳችኋል ተብለው በነሶሊያና ሽመልስ መዝገብ ከተከሰሱት 3 ጋዜጠኞች አንዷ ስትሆን ለዓመት ከሦስት ወር በእስር ሆና ክሷን ከተከታተለች በኋላ ክሱ ተቋርጦላት በነፃ ወጥታለች።
  19. ማሕሌት ፋንታሁን -በሚያዚያ 17/2006 ተይዛ ማዕከላዊ ለሦስት ወራት ከቆየች በኋላ ክስ ተመስርቶባት ቃሊቲ እስር ቤት ገባች። የኅብረተሰቡን ደኅንነት አደጋ ላይ ለመጣል አሲራችኋል፣ አቅዳችኋል ተብለው በነሶሊያና ሽመልስ መዝገብ ከተከሰሱት 6 ጦማሪ አክቲቪስቶች አንዷ ስትሆን ለዓመት ከሦስት ወር በእስር ሆና ክሷን ከተከታተለች በኋላ ክሱ ተቋርጦላት በነፃ ወጥታለች።
  20. ርዕዮት ዓለሙ (ጋዜጠኛ እና መምህርት) – በ2003 ሰኔ ወር ላይ ተይዛ ማዕከላዊ ገባች። በነኤልያስ ክፍሌ መዝገብ በሽብር ወንጀል ከተከሰሱት አምስት ሰዎች አንዷ ናት። ከፍተኛ ፍቤት የ14ዓመት ፍርድ ከበየነባት በኋላ ይግባኝ ብላ ክሶች ተሰርዘውላት ቅጣቱ ወደ 5ዓመት ዝቅ አለላት። በደንቡ መሠረት በአመክሮ ጥቅምት ወር 2007 ላይ መለቀቅ ሲገባት፤ በጥፋቷ መፀፀቷን አምና ካልፈረመች አመክሮ አይሰጥሽም ተባለች። የማላምንበት ነገር ላይ አልፈርምም በማለትም ያለአመክሮ ፍርዷን ለመጨረስ ወሰነች። ባልተጠበቀ እና ባልታሰበ ወቅት ከአራት ዓመት እስር በኋላ ሐምሌ 1፣ 2007 ከእስር ተለቀቀች። የመጨረሻዎቹን ሁለት የእስር ዓመታት አምስት የእሷን ሁኔታ የሚከታተሉ እስረኞች ያሉበት ብቻ በቅጣት ቤት ውስጥ ነበር ያሳለፈችው፤ ከእናት እና አባቷ ውጪም በማንም እንዳትጎበኝ ተከልክላ ነበር። በእስር ሆና ‹የኢሕአዴግ ቀይ እሰክብሪቶ› የሚል የቀድሞ ጽሑፎቿ ስብስብ ታትሞላታል፡፡
  21. ረዳት ኢንስፔክተር አዜብ ተክላይ -ለኤርትራ የስለላ ቡድን የሃገሪቱን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል መረጃ አቀብለሻል ተብላ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ማዕከላዊ ገባች። ከአራት ወር በላይ እዛ ከቆየች በኋላ ምንም ማስረጃ ሳይገኝባት በስለላ ወንጀል ክስ ተመሥርቶባት ቃሊቲ እስር ቤት ገባች። ክሷን በእስር ሆና ስትከታተል ቆይታ በዚህ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ ጥፋተኛ ተብላ የ7ት ዓመት ፍርድ ተበይኖባታል። ጥፋተኛ መባል አይገባኝም ስትል ጠቅላይ ፍቤት ይግባኟን አቅርባ ተከራክራለች። ለመጋቢት 16/2008 ለብይን ተቀጥራለች።
  22. አበበች ጣሙ –የጎንደር ተወላጅ ናት። በጥር ወር 2006 ላይ ተይዛ ማዕከላዊ ገባች። በእነአበበ ካሴ መዝገብ ከተከሰሱት ውስጥ ስትሆን መሳሪያ ደብቀሻል የሚል ክስ ነው የተመሰረተባት። 1 ዓመት ከአምስት ወር በእስር ቆይታ በ2007 ሰኔ ወር ላይ በዋስ ወጥታ ክሷን ስትከታተል ከቆየች በኋላ ጥር ወር 2008 ላይ በነፃ የተሰናበተች።
  23. እየሩሳሌም ተስፋው -የሰማያዊ ፓርቲ አባል የነበረች። በየካቲት ወር 2007 በሰላማዊ ትግል ተስፋ ቆርጣ ሰማያዊ ፓርቲን በመልቀቅ በኤርትራ በኩል ግንቦት 7 ልትቀላቀል ስትል ማይ ካድራ የተባለ ቦታ ላይ ተይዛ ወደ ማዕከላዊ የገባች። ከዛም የሽብርተኛ ድርጅት አባል መሆን የሚል ክስ ተመስርቶባት በቃሊቲ የምትገኝ። እሷ ያለችበት መዝገብ (እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ) መከላከያ ምስክሮችን ለማሰማት ለመጋቢት 22/2008 ተቀጥረዋል።
  24. እየሩስ አያሌው– የ2007ን ሃገራዊ ምርጫ ተከትሎ “ትግሬ አይገዛንም” ብለሻል የሚል ክስ ተመስርቶባት ዓመት ከአራት ወር ተፈርዶባት ግንቦት ወር 2007 ላይ ቃሊቲ ገባች። ከፍተኛ የአይምሮ ጭንቀት ሕመም የነበረባት ሲሆን ምግብም አትበላም ነበር። በየካቲት ወር መጀመሪያ 2008 ላይ በእስር ላይ እያለች እራሷን አጥፍታ ሕይወቷ ያለፈ።
  25. ቀለብ ስዩም -ከአራት ወር በላይ ይሆናታል ከታሰረች። ከጎንደር ነው የመጣችው። በሽብር ወንጀል ተከሳ ጉዳይዋን በቃሊቲ እስር ቤት ሆና እየተከታተለች የምትገኝ።
26 ሃዊ ጎንፋ -በሽብር ወንጀል ተከሳ ሦስት ያልተገቡ ዓመታትን በእስር አሳልፋለች። ለሦስት ዓመታት ክሷን በእስር ሆና ስትከታተል ከቆየች በኋላ በነፃ ተሰናብታለች። በማዕከላዊ እና ቃሊቲ የታዘበችውን የሚተርክ RIRRIITTAA የተሰኘ መጽሐፍ እና ሌሎች ሁለት ተጨማሪ መጽሐፍቶችን (HIREE GALGALAA እናCANCALA QABSOO) አበርክታለች።
  1. አየለች አበበ -ካጋሞ ጎፋ ዞን ተይዘው አራት ወር ማዕከላዊ ከቆዩ በኋላ የሽብርተኛ ቡድን አባል ናችሁ በመባል በሚያዚያ 27 ቀን 2008 ክስ ከተመሠረተባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት (እነ ሉሉ መሰለ) ውስጥ ናት።
የISIS ቡድን በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን ግድያ በመቃወም በሚያዝያ ወር 2006 በተጠራው ሰልፍ ጋር በተያያዘ “ስብሰባ በማወክ”፣ “ሁከት በመፍጠር”፣ እና በመሳሰሉ ክሶች የተመሠረተባቸው በርካቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ ጭራሽ ሰልፉ ላይ ያልነበሩ (እቤታቸው ወይም ሥራ ገበታቸው ላይ የነበሩ) ይገኙበታል፡፡ በነጻ የተሰናበቱት እንዲሁም ስምንት ወር ፍርድ ተወስኖባቸው የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ቅጣታቸውን ጨርሰው ከእስር ወጥተዋል፡፡ ቃሊቲ ገብተው የነበሩት የሚከተሉት ናቸው፡፡
  1. ብሌን መስፍን – (የሰማያዊ ፓርቲ አባል)
  2. ቤተልሔም አካለወልድ
  3. ወይንሸት ሞላ (የሰማያዊ ፓርቲ አባል)
  4. ዝናሽ አንከላ
  5. ዝናሽ ምትኩ
  6. ማሕሌት ኤርሳዶ
  7. እኑኪ ኃይሉ
  8. ቤዛዊት ግርማ (ጋዜጠኛ)
  9. ራሕሙ ጀማል
  10. ፍቅር
  11. መስከረም ወንድማገኝ (አርቲስት)
  12. ዮዲት ኃይለማርያም
  13. ሔለን ነዋይ
  14. ሜሮን አስማማው
  15. ንግሥት ወንዲፍራው (የሰማያዊ ፓርቲ አባል)
—-
*በመረጃ እጦት የተገደፉ ጥቃቅን ስህተቶች እና ያላካተትኳቸው እስረኞች ሊኖሩ ይችላሉ።

የማንነት ጥያቄ በሃይል አይገታም” – በሰሜን አሜሪካ ከሚኖሩ የጠለምት ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ




Telemet
የካቲት 30 ቀን 2008 ዓ/ም ኢትዮጵያን በማፈራረስ፣ ሃብቷን በመዝረፍ፣ ሕዝቧን በማሳደድ፣ በማፈናቀልና በማሰቃየት ለ 25 ዓመታት ያህል በመሳርያ
ሃይል አስገድዶ በመግዛት ላይ ያለው ጠባብ በሄርተኛው ወያኔ፣ በሕዝብና በአገር ላይ እየፈፀመ ያለው ግድያ፣ እስራት፣ እንግለት፣ሰቆቃና ግፍ በቀላል ቋንቋ ለመግለጽ ያዳግታል።
ገና ጫካ እያለ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ቃለ መሃላ አድርጎ የመጣው ዘረኛው ወያኔ በሕዝብና በሃገር ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት መቆምያ አጥቶ እጅግ አሳሳቢና አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።
ታላቋን ትግራይ ለመመሥረት በሚል ፀረ ኢትዮጵያ አቋም የተመረዘው ወያኔ(ህውሃት) በለምነታቸዉ፣ በተፈጥሮ ሃብት ጠቃሚነታቸው ዉብ በሆኑ ወንዞችና ጅረቶች የተከበቡና እስትራቴጅካዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ቦታዎች ለትግራይ ክ/ሃገር አጎራባች ከሆኑት ክፍላተ-ሀገራት ወደ ትግራይ ክልል ማስገባቱን ይታወቃል።
ወያኔ ኢትዮጵያን በጠመንጃ ሃይል ስልጣን ከተቆጣጠረበት ከ1983 ዓ/ም ጀምሮ የታላቋን ትግራይ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ለምና ወሃ-ገብ የሆኑትን የጎንደር ወረዳዎች፣ ወልቃይት፣ ጠገዴንና ጠለምትን ከወሎ ክ/ሃገር ደግሞ ወደ አራት የሚሆኑ ወረዳዎችን በትግራይ ክ/ሃገር ሥር እንዲሆኑ አድርጓል;
ጠለምት፣ በረጅሙ የኢትዮጵያ ታሪክ በጎንደር ክ/ሃገር የሚገኝ አማራ፣ የአማራ ባህልና ወግን የሚከተል ሕዝብ ለመሆኑ ታሪክ ያረጋገጠው ሃቅ ነው። የጠለምትን መልከዓ-ምድር አቀማመጥን ስንመለከት፤ በሰሜን ተከዜ ወንዝን ተከትሎ ትግራይ፤ ክ/ሃገርን በምሥራቅ እንዲሁ ተከዜን ወንዝን ተከትሎ ተንቤን አውራጃ(ትግራይ) እና ዋግ አውራጃ(ወሎን)፤ በምዕራብ ወልቃይትና ጠገዴ፤ በደቡብ በተፈጥሮ ሃብት የበለጸጉ በጎንደር ክፍለ-ሃገር የሚገኙ የሰሜን ተራራዎች ስንሰለት ያዋስናል።
የተለያዩ የውጭ ወራሪ ጠላቶች በተለያዩ ጊዜያት አገራችን ኢትዮጵያ ለመውረር ሲመጡ፤ ጀግናው የጠለምት ሕዝብ የአገሩን ነፃነትና ዳር ድንበር ለማስከበር በተለያዩ የጦር ሜዳዎች በቆራጥነት በመዝመት በኢትዮጵያ ታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ታላቅ አንጸባራቂና አኩሪ ታሪክ የሠሩ፤ በ5 ዓመት የጣሊያን ወረራ ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ጀብዱ የፈፀሙ እውቅና ስመ ጥር አርበኞችን ያፈራ ሕዝብ ነው።
የጠለምት ሕዝብ ልክ እንደ ወገኖቹ ወልቃይትና ጠገዴ ሕዝብ ከትግራይ ሕዝብ ጋር የሚያዋስነው ተፈጥሮአዊ ድንበር የማይሞተውና የማይዋሸው የተከዜ ወንዝ ሲሆን ረጅሙ ገናናው የኢትዮጵያ ታሪክም የሚመሰክረው ይኸኑን ዕውነታ ነው። ለግንዛቤ ያህል፤ ሩቅ ሳንሄድ፤ በዘመነ መሳፍንት ጊዜ የአማራ ተወላጆች የነበሩ መሪዎች እንደ ራስ ወልደሩፋኤል፣ ልጃቸው ራስ ገብሬ፣ ራሰ ኃይለማርያም እና ደጃዝማች ውቤ ይገዙት የነበረው ግዛት ከባንብሎ (ከጎንደር ከተማ በስተሰሜን በኩል በግምት 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝው ጉርድ መሬት) እስከ ተከዜ ወንዝ ያለውን ሠፊ ግዛት ነበር። ይኸም ሠፊ ግዛት አሁን የምናውቀውን ወገራ አውራጃ (ወገራ፣ ዳባት፣ ጠገዴ፣ ወልቃይትና ሰቲት ወረዳዎች) እና ሰሜን አውራጃ (ደባርቅ፣ ድብባሕር፣ ጠለምት፣ ጃናሞራና በየዳ ወረዳዎች) የሚጠቀልል ነበር። እንድያውም ታላቁ መሪ ደጃዝማች ውቤ ይገዙት የነበረው ግዛት ይህ ብቻ ሳይሆን፤ ትግራይንና ባሕረ-ነጋሽን (ኤርትራን) ጨምሮ ነበር።
ዘመነ መሳፍንት አክትሞ፤ ታላቁና ገናናው የኢትዮጵያ መሪ በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት፤ እንዲሁም በአፄ ዮሐንስ አራተኛ፤ በአፄ ምንሊክ፣ በአፄ ኃይለሥላሴ እና በኮሎኔል መንግሥቱ ዘመናት የትግራይና የጎንደር አማራ ሕዝብ ተፈጥሯዊ ድንበር ተከዜ ወንዝ እንደሆነ ታሪክ ያረጋገጠው ሃቅ ከመሆኑም ባሻገር የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት መስራች አባል የነበሩት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ ኢንጅነር ግደይ ዘራዓፅዮን፣ አቶ ገብረመድህን አርአያ፣ አቶ አስገደ ገብረስላሴና የትግራይ ጠቅላይ ግዛት አገረ ገጅ የነበሩት የተከበሩ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ያረጋገጡት ነው።
TPLF(ወያኔ) የትግራይ አገዛዝ ተከዜን ወንዝ የተሻገረው “ታላቋን ትግራይ” ለመመሥረት ባቀደው እቅድ መሠረት፤ ለምና ወሃ-ገብ የሆኑትን የጎንደር ወረዳዎችን ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምትን በተቆጣጠሩበት በ17 ዓመት የሽፍትነት ጊዜና ከ25ዓመት በፊት መላ ኢትዮጵያን በሃይል በመዳፉ ሥር ባሰገባበት ወቅት፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ይወያኔ ታጋይዮች የነበሩና ደጋፊዎቻችወን አምጥቶ በወልቃይት፣ በጠገዴና በጠለምት አስፍሮ ለዘመናት በጋራ አብሮ ይኖር የነበረን ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭና እንዲጠላላ አደረገ።ወደ። የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) ከላይ የተገለፁትን ወረዳዎች ተቆጣጠሮ ወደ ትግራይ ክልል ካስገባቸው ከጥቂት ወራት በኋላ ወደ 1983 ዓ/ም መጨረሻ አካባቢ፤ አንድ የወያኔ ባለሥልጣን ታማኝ ካድሬውን ወደ አዳርቃይ ከተማ ልኮ ነበር። ካድሬውም በከተማው የሚገኙትን ታላላቅ አዛውንቶች ስብስቦ በማናገር ላይ እያለ “ የትግራይን ድንበር” እስከየት እንደሆነ ታውቃላችሁ ወይ? ብሎ ሲጠይቅ፤ ንግግሩን በጽሞና ይከታተሉ የነበሩት የአገሬው ሰመ ጥሩ አዛውንት “ ልጄ! የትግራይ ድንበር አልፈህ የመጣኸው ተከዜ ወንዝ ነው” ብለው ነበር የመለሱለት።
TPLF(ወያኔ) ካለፉት 25 ዓመታት ጀምሮ፤ የጠለምትን ሕዝብ በመዳፉ ሥር ካስገባ በኋላ፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን እንዲሁም የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት ባለው እቅድ መሠረት፤ በጠለምት ያሠፈራቸውን ቅጥረኞችን በማስታጠቅ፤ በጠለምት ሕዝብ ላይ ወደር የሌለው ጭፍጨፋ (genocide) እና የዘር ማጥፋት (ethnic cleansing) በማያቋርጥ ሁኔታ አካሂዷል። እያካሄደም ነው። ይኽ ሁሉ ዘግናኝ ግፍ የተካሄደውና በመካሄድ ላይ ያለው ፤ የጠለምት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በማንሳቱና እኛ አማራ፤ ቋንቋችን አማርኛ ነው፤ ክልላችንም ከላይ በታሪክ ተደግፎ እንደተገለፀው ጎንደር ነው ብሎ ስለጠየቀ ነው።
የጠለምት ሕዝብ የደረሰበትንና የሚደርስበትን ጭፍጨፋ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ለኢትዮጵያ ሕዝብ በተቀናጀ መንገድ ለመግለጽና ለማስረዳት፤ በመታገል ላይ ካለው ወገናችን አጋርነታችን ለማሳየትና ብሎም ለነፃነት፣ ለፍትህና ለዴሞክራሲ ከሚታገልው ስፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመቆም አስከፊዉንና ዘረኛዉን የወያኔ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨርሻ አሽቀንጥሮ እንዲጥል ለመቀስቀስ እንዲረዳ በማስብ፤ እኛ በሰሜን አሜሪካ የምንኖር የጠለምት ተወላጆች አስቸኳይ ስብሰባ አድርገን የሚከተለውን የአቋም መግለጫና ሕዝባዊ ጥሪ አቅርበናል።
1. የአማራ ሕዝብ አካልና የጎንደር ክ/ሃገር ክልል የነበሩት ወረዳዎች(ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት) እና የወሎ ለም 4ቱ ወረዳዎች ያለሕዝብ ውሳኔና ፈቃድ በወያኔ አስገዳጅነትና ያለ አግባብ ወደ ትግራይ ክልል እንዲጠቃለሉ መደረጉን እናወግዛለን።
2. በፀረ-ኢትዮጵያው የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) ከፍተኛ ጭፍጨፋ (genocide) እና የዘር ማጥፋ ( ethnic cleansing) የተካሄደበትና የሚካሄድበት ጀግናው አማራው የወልቃይትና የጠገዴ ሕዝብ ከወያኔ አስከፊና ዘግናኝ አገዛዝ ለመውጣት የሚያካሂደውን ትግልና የአማራ ማንነት መብት ጥያቄ ሙሉ በሙሉ እንደግፋለን፤ እስከ መጨረሻው ድረስ ከጎኑ እንቆማለን።
3. የተቀደሰውና ታሪካዊው ዋልድባ ገዳም በትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) መደፈር፣ መዘረፍ፣ምፍረስ፣ የአረጋዊ አባቶች መንገላታት፣ መሰደድና መገደል በጥብቅ እናወግዛለን። የወያኔ ጣልቃ ገብነትን እያወገዝን በቅዱስ ገዳምት ያሰፈረዉን ወታደራዊ ሃይል እንዲያነሳና እኩይ ተግባሩን እንዲያቆም እናሳስባለን።
4. እርዝመቱ 1600 ኪ/ሜትር የጎን ስፋቱ ከ20 እስከ 60 ኪ/ሜትር የሆነውን ለም ወሃ-ገብ የአገራችን ዳር-ድንበር መሬት የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) በገጸ-በረከት መልክ ለሱዳን መስጠቱ አጥብቀን እናወግዛለን።
5. በኦሮምያ ክልል በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ላይ እየተፈፀመ ያለዉን ግድያ፣ ጭፍጨፋ፣ እስራትና እንግልት በጥብቅ እያወገዝን ገዳዮቹን ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን።
6. የጠለምት ሕዝብ ሆይ! የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) አገዛዝን አሽቀንጥረህ በማጣል የአማራ ማንነትህንና የመሬት ባለቤትነትህን ለማስመለስ የጀምርከውን ትግል አጠናክረህ ቀጥል፤ እኛም ልጆችህ እስከመጨረሻው ድረስ ከጎንህ መሆናችን እናረጋግጣለን።
7. በአገር ውስጥና በውጭ የምትኖሩ የጠለምት ተወላጆች በሙሉ በያላችሁበት በመሰባሰብና በመደራጀት፤ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) በወገናችን የጠለምት ሕዝብ ላይ የሚያካሂደውን ጭፍጨፋ (genocide) እና የዘር ማጥፋት (ethnic cleansing) በማጋለጥና፤ ከወያኔ ጨቋኝ አገዛዝ ቀንበር ነፃ ለመውጣት የሚያደርገውን ትግል በማንኛው መልክ እንድትድግፉ፤ ጥሪ እናቀርባለን።
8. የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ቅጥረኛ የሆነውን ፀረ-ኢትዮጵያው የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) እና ተላላኪዎቹን በመራራ ትግላችን አስወግደን፤ እኩልነት፣ ፍትህና የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ስርዓት ለመመሥረት እንደ ሰደድ እሳት በመቀጣጠል ላይ ያለውን ሕዝባዊ አመጽና ትግል በማጠናከር በጋራ እንድትታገል አገራዊ ጥሪ እናቀርባለን።
ያለ አግባብ ከጎንደር የተወሰደው መሬት በመራራው ትግላችን ይመለሳል!
የወልቃይት፤ የጠገዴና የጠለምት ሕዝብ የአማራ ማንነት መብት ጥያቄ በቆራጥ ትግላችን እውን ይሆናል! ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

Breaking: የኢቢሲ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ስርዓቱን ከድተው አሜሪካ ቀሩ



Breaking News zehabesha
(ዘ-ሐበሻ) በመንግስት 100% ቁጥጥር ሥር የሆነው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ጨምቤሳ አሜሪካ ለሥራ መጥተው በዚሁ መቅረታቸው ታወቀ::
የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳስታወቁት በአሁኑ ወቅት ሥርዓቱን በመክዳት በሁለት ዲጂት የሚቆጠሩ ባለስልጣናት እና ወታደሮች ወደ ተለያዩ ሃገራት በመኮብለል ላይ ይገኛሉ::
የኢቢሲ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ጨምቤሳ አሜሪካ ከመጡ በኋላ በአሁኑ ወቅት ሚኒሶታ በተሰኘችው ግዛት ውስጥ እንደሚገኙ ጨምሮ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያሳያል::

ህወሓት የወልቃይትን ህዝብ ጉሮሮ ፈጥርቆ እስትንፋሱን ሊያቋርጠው ተግቶ እየሰራ ነው – ከትግራይ ህዝብ አጓጉዞሊያሰፍር ዝግጅቱን አጠናቋል

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)  “ህወሓት መሬታችንን እንጂ እኛን አይፈልገንም…” የሚሉት የወልቃይት ነዋሪዎች ዛሬ ዛሬ የሚፈፀምባቸው መከራ ከመቸውም ጊዜ በላይ በርትቷል፡፡ ግፍና በደሉ ምድሪቷን አጥለቅልቋል፡፡ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሰዎች በህወሓት ደህንነቶችና የታጠቁ ቡድኖች እየታፈኑ ደብዛቸው እየጠፋ ነው፡፡ በስውር እየተገደሉ ነው፡፡ የህወሓቶች ሰፋፊ እስር ቤቶች በወልቃይት ነዋሪዎች ተጨናንቀዋል፡፡
Wolqite News
የወልቃይት ህዝብ ይህ ሁሉ መከራ፣ ግፍና ሰቆቃ እየተፈፀመበት የሚገኘው “ትግሬ አይደለሁም አማራ ነኝ” በማለቱ ብቻ ነው፡፡ የወልቃይት ህዝብ ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ተደራድሮ ለመፍታት ያቋቋመው ኮሚቴ አባላት በህወሓት እየተሳደዱ ነው፡፡ አቶ በለጠ ታደሰ እና አቶ ማሩ ሽፋ የተባሉት የኮሚቴው አባላት የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም በደህንነቶች ታፍነው “የህዝቡን ሃሳብ አስቀይራችሁ ትግሬ ነኝ እንዲል ካላደረጋችሁ በስተቀር በምድር ላይ አትኖሩም…” የሚል ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው በኋላ ተለቀዋል፡፡ ከየካቲት 29 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ሁለቱ ኮሚቴዎች የት እንደተወሰዱ ሳይታወቅ ከአካባቢው ተሰውረዋል፡፡
የወልቃይትን ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ለማፈን የህወሓት ቡድን ከግድያው፣ አፈና እና እስሩ ባሻገር የተለያዩ ሸፍጦችን እየፈፀመ ይገኛል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ከትግራይ አጓጉዞ በወልቃይት ምድር ላይ በአራት ሰፈራ ጣቢያዎች ለማስፈር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በሁመራ እና በሌሎች የወልቃይት ከተሞች የሚገኙትን ሆቴሎች፣ ህንፃዎችና የንግድ ቦታዎች የስርዓቱ ታማኝ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች እንዲከራዩዋቸው እየተደረገ ነው፡፡
በመሆኑም ወልቃይቶች ተዕግስታቸው እንደተሟጠጠና ጠብመንጃቸውን በመወልወል ላይ መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡ “በግንቦትና ሰኔ አንዱ ይለያል” በማለት ቆርጠው መነሳታቸው ተሰምቷል፡፡

ከጠመንጃ ‘ነፃነት’ ወደ ስኳር ባርነት! (ታሪኩ አባዳማ)

ታሪኩ አባዳማ – የካቲት 2008
ለስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎች ማስፋፊያ በሚል ሰበብ መጠነ ሰፊ መሬት ከዜጎች እየተዘረፈ መሆኑን ስንሰማ ቆይተናል። የታሪክ እና እምነት መናኸሪያ ዋልድባ ገዳም በይዞታው ስር የሚገኘውን ርስት በዚህ ምክንያት መቀማቱንም እንደ ዋዛ ሰምተን ነበር። ሰሞኑን በምናገኘው ወሬ ደግሞ የኦሞ ሸለቆ ልዩ ልዩ ብሔረሰብ ኢትዮጵያውያን ከክልላቸው ጭካኔ በተመላበት የወያኔ አስገድዶ ማፈናቀል ዘመቻ ከቄያቸው ሲጋዙ መክረማቸውን ተረድተናል። መሬታቸው ለሸንኮራ እርሻ ማምረቻ እና ስኳር ፋብሪካ ስለተመረጠ እነሱ ወዳልመረጡት አካባቢ በጠመንጃ አፈሙዝ ተገደው ተወስደዋል።INVESTORS, WELCOME TO ETHIOPIA
እንደ እንሰሳ በገመድ ተጠፍሮ ካሚዮን ላይ የተጫነውን ወገናችንን አተኩራችሁ ካስተዋላችሁ በስኳር ገበያ የጎመዘዘው የኦሞ ሸለቆ ክልል ህዝቦች ህይወት ስዕል ቁልጭ ብሎ ይታያችሁዋል። ስኳር የሚልሱ ጉልበተኛ ገዢዎች በዜጎች ጉሮሮ እንቆቆ እያንቆረቆሩ ስለመሆኑ በማያሻማ ሁኔታ ትገነዘበላችሁ። ለም የተባለ ያገሪቱ ምድር እንደ ጠላት ወረዳ ወረራ እየተፈፀመበት የይዞታው ባለቤት የሆኑ ነዋሪዎቹ ወደ ዘቀጠ ኑሮ እየተወረወሩ ይገኛሉ። በዚህም የወያኔ እውነተኛ ተፈጥሮ ይበልጥ ግጥጥ ብሎ ወጥቷል።
በመሰረቱ የዚህ አይነቱ ጭካኔ በወያኔ ወህኒዎች በታገቱ ንፁሀን ዜጎች ላይ ሲፈፀም የቆየ በመሆኑ ለብዙዎቻችን እንግዳ ነገር አይደለም። ምናልባት ይህን የተለየ የሚያደርገው በጠመንጃ አፈሙዝ ብሔረሰባዊ ነፃነታችሁ ተረጋግጧል የተባሉት ኢትዮጵያውያን በስኳር ኢንቨስተሮች ጡንቻ እውነተኛ ባርነት ተጭኖባቸው ማየታችን ሊሆን ይችላል –
ወያኔ በስኳር ገበያ ሊከብር ፣ ሊናጥጥ ፤ የወያኔ ጀሌ በስኳር ህይወቱን ሊያጣፍጥ ሌላው ዜጋ አያት ቅድም አያቱ ከተከሉት ከገዛ መሬቱ ላይ በወታደር ተገዶ ይጋዛል – እንደ ከብትም ታስሮ ፣ ተወግሮ እና ተዋክቦ ፤ ስብእናው ተክዶ እና ተዋርዶ የህይወት ተስፋው ጨልሞ ደብዛው እንዲጠፋ ሲደረግ ቆይቷል።
ስኳር መራራ የሆነበት ዜጋ ሆነን የመገኘታችን ምስጢር መፍትሔ ያሻዋል።
የኦሞ ሸለቆ ሰላማዊ ዜጎች ለም መሬታቸውን መቀማታቸው አልበቃ ብሎ በቁማቸው አሳር እንዲቀበሉ በመደረግ ላይ ነው። ወልቃይት ላይ የተፈፀመውን አይን ያወጣ ወረራ ስናስብ ፣ በኦሮሞ ክልል የተፈፀመው የመሬት ዘረፋ እና ማፈናቀል ፣ ጋምቤላ አፅመ ርስቱን የተቀማው ህዝብ – ይህ ሁሉ ድርጊት አፈፃፀሙ ወጥነትና እና ተመሳሳይነት እንዳለው መገንዘብ አያዳግትም። የዚህ እርምጃ ግብ አንድ ጠገብኩ የማይል ስግብግብ ጎጠኛ ሀይል መጠነ ሰፊ ሀብት አግበስብሶ አገዛዙን አለገደብ ማራዘም እንዲበቃ ማስቻል ነው።
ወያኔ የስልጣንና ሀብት ጥሙን ለማርካት ሲል ይሉኝታ የማያውቅ ፣ ስለ ዜጎች ደህንነት ቅንጣት ሀላፊነት የማይሰማው ፣  የሚሊዮኖች ህይወት ቢናጋ ፣ ሰብአዊ ክብራቸው ቢዋረድ… ብሎም ኢትዮጵያ ራሷ ከገፀ ምድር ብትጠፋ ቅም የማይለው መሆኑን በወሬ ሳይሆን በተግባር ሲያሳየን ቆይቷል። ይኼ ዛሬ ያየነው  ድርጊት ሌላ ተጨማሪ ኤግዚቢት ነው። የብሄረሰቦችን እኩልነት አውጃለሁ ብሎ ዘገር የነቀነቀው ባለ ቁምጣ የብሄረሰቦችን ለም መሬት በዘገር እየቀማ ለባርነት እየዳረጋቸው ነው።
የኦሞ ሸለቆ በሞላሰስ አተላ ሲበከል አናይም ያሉ ዜጎች ደማቸው እንደ ጅረት እየፈሰሰ ነው። በወያኔ ወታደር ተገደው ካሚዮን ላይ የተጫኑትን ወገኖቻችንን አካል አስተውሉት ፣ እርቃን ገላቸውን በህሊናችሁ ዳሱት ፣ የፊታቸውን ገፅ አንብቡት ፣ አይናቸውን እዩት – ከግንባራቸው የሚፈሰውን ላብና ደም አስተውሉት… – አንገታቸው ላይ የተሸመቀቀውን ገመድ ፣ ክንዳቸው የፊጥኝ ተሰትሮ መተንፈሻ እንኳ ተነፍገው በጨካኝ ወታደር እርግጫ የሚደርስባቸውን ሰቆቃ አሰላስሉት… እዚህ ፎቶ ላይ ያየናቸው ዜጎች በጥይት ተገድለው በየስርቻው ከተጣሉት የተረፉት መሆናቸውንም አስቡት… ።
አንድ ህዝብ በገዛ አገሩ ይህ ሁሉ ሰቆቃ በቁሙ የሚፈፀምበት ለስንት ስኳር ላሾች ምቾት ሲባል ይሆን?
በማህበራዊ መገናኛ አውታሮች የተለቀቁትን ምስሎች ሳስተውል እስከ አጥንቴ ዘልቆ የሚወጋ ህመም ተሰምቶኛል። ወያኔ ወደ አስራስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመሳፍንት ዘመን ይዞን የሄደው በፖለቲካ ብቻ ሳይሆን በዚያው በጥንታዊው ዘግናኝ የባሪያ ንግድ ዘዴ አፍሪካውያን የደረሳባቸውን ሰቆቃ በመድገም ጭምር መሆኑን ተገነዘብኩ። ይሄ ነጮቹ barbaric (አረመኔ) የሚሉት ባህርይ ነው። በኔ እምነት ወያኔ በተፈጥሮው barbaric ብቻ ሳይሆን beast (አውሬ) መሆኑን ተገንዝቤያለሁ።
አንድ ኢትዮጵያዊ በገዛ ቄየው እንዲህ እርቃኑን እንደ ከብት ተጠፍሮ ሲንገላታ በአይንህ ብሌን ከመመስከር በላይ ወያኔን የሚገልፅ ምን ትጠብቃለህ። ወደድንም ጠላንም የሚካሄደው ትግል ይህን የባርነት ቀንበር ለመስበር የሚደረግ ተጋድሎ ነው። ይህን ለአፍታ የሚጠራጠር ካለ ሌላ ከዚህ የባሰ ተጨማሪ የዜጎች ውርደት እስኪመጣ ለመጠበቅ የመረጠ ብቻ ነው። ይህም ባርነትን ወዶ እንደ መቀበል ይቆጠራል።
አውሬ ህሊና የለውም – ወያኔ ህሊና የለውም!
ኦሮሞ መሬት ላይ ህፃን ከአዛውንት ፣ ነብሰጡር እናቶች ፣ ለጋ ወጣት ተማሪዎች እና አርሶ አደሮች… ማንም አልቀረውም – ሁሉንም በአውሬ ተፍጥሮው ፣ በመርዛም ጥርሱ ነክሷል… እየነከሰ ነው። ያየናቸው ምስሎች ሀፍረታቸው እንኳ በወጉ ሳይሸፈን በገመድ የፊጥኝ ታስረው በካሚዎን ላይ የታጨቁ ምሬት የተላበሱ ኢትዮጵያውያን በወታደር ሀይል እየተዋከቡ ወደማይውቁበት ስፍራ እየተጋዙ መሆኑን ነው። እነኝህ ዜጎች ምናልባትም በታሪካቸው ከዚህ ቀደም ደርሶ የማያውቅ ጭካኔ እየተፈፀመባቸው ነው። መላ የሰው ዘር ባርነትን በተጠየፈበት በሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ነፃነቱን ለምዕተ ዓመታት አስከብሮ የኖረ ህዝብ መልሶ ወደ ባርነት ስርአት ሲገባ ከማየት በላይ ህሊናን የሚያቆስል ጉዳይ የለም።
ኢትዮጵያውያን በባርያ ፈንጋይ እጅ ወድቀናል። ትግላችንን የነፃነት ጥያቄ የሚያደርገውም ይኸው ነው።
ወገኖቻችን በባርነት ቀንበር ስር እየማቀቁ ሳሉ አንዳችንም ከባርነት ነፃ ነን ማለት አንችልም። እንዲህ  አይነቱን አሳፋሪ እና ፀያፍ አውሬአዊ ድርጊት ከምድራችን ለመፋቅ ባለን አቅም እና መንገድ ሁሉ መታገል አማራጭ የለውም።
ተንበርክኮ መኖር ያሳፍራል። የዜጎች ክብር የተዋረደባት ፣ አሳፋሪ አገር ለዛሬውም ሆነ ለነገው ትውልድ አያሻንም። በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለሁ እያልን ዜጎቿ ከተራ ሰብአዊ ፍጡር በታች ተዋርደው መሳለቂያ ሲሆኑ ማየት ትልቅ የህሊና ቁስል ነው። ምኑ ነው የሚያኮራን ፣ የኩራታችን ምንጭ የዜጎቻችን ክብር ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?

ዘ-ህወሀት በኢትየጵያ የታክሲ ሾፌሮች ላይ የከፈተው ጦርነት! (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
በአሜሪካ “ባለሶስት-ጥፋት ሕግ“ እያሉ ይጠሩታል፡፡ ወንጀለኞች ሶስት ከባድ ወይም ደግሞ አስከፊ ወንጀሎችን የሰሩ ከሆነ ከ25 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት የሚያደርስ ቅጣት ይበየንባቸዋል፡፡Addis-Ababa-Taxi-STRIKE4
ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ላይ ጦርነት አውጇል!
በኢትዮጵያ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላየዘራፊ ቡድን ስብስብ (ህወሀት) ለሶስት ወር ተራዝሟል የሚል ሽንገላ ያስቀመጠለትን እና አንድ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌር ሶስት ተከታታይ ጥፋቶችን ከፈጸመ ከታክሲ ማሽከርከር ስራው የመንጃ ፈቃዱን ተነጥቆ ይሰናበታል በማለት ከእጅ ወደ አፍ በሆነች ገቢ ኑሯቸውን በመግፋት ትግል እያደረጉ ባሉት አሽከርካሪዎቸ ላይ የሚተገበር “ሕግ” አውጥቷል፡፡ የትራፊክ ሕግ ደንብን በመጣስ 20 ወይም ከዚያ በላይ ነጥብ የተያዘባቸው የታክሲ አሽከርካሪ ሾፈሮች ለዘላለሙ ከታክሲ አሽከርካሪነት ሙያው ይሰናበታሉ፡፡
እንደ አዲስ ስታንዳርድ ድረ ገጽ ዘገባ ከሆነ “የዘ-ህወሀት አዲሱ የትራፊክ ቁጥጥር ደንብ ስድስት የቅጣት ደረጃዎችን አካትቶ የያዘ ሲሆን የትራፊክ መብራት ጥፋትን ጨምሮ ሁለት ነጥብ በመቀነስ ይጀምር እና ተሽከርካሪን አለአግባብ ማቆም እና ከታክሲው የመጫን አቅም በላይ ተሳፋሪን ጭኖ የመገኘት በመሳሰሉት ጥፋቶች ላይ የቅጣት ዝርዝሩን አቅርቧል፡፡ ደንቡ ቀደም ሲል ከ14 – 16 የጥፋት ነጥቦች  የተያዘባቸውን አሽከርካሪዎች የመንጃ ፈቃድ በመንጠቅ ለስድስት ወራት ከስራ ገበታ ውጭ እንዲሆኑ የሚያደርግ እንደሆነ ይጠበቃል፡፡ ከ17 – 19 ነጥብ የተያዘበት/ባት አሽከርካሪ መንጃ ፈቃዱ/ዷ ለአንድ ዓመት ያህል እንዲነጠቅ ይደረጋል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ማንኛውም አሽከርካሪ 20 እና ከዚያ በላይ ነጥብ የተያዘበት ከሆነ መንጃ ፈቃዱ ለዘላለሙ ይነጠቅ እና ውሳኔው ከተሰጠበት ከሁለት ዓመታት በኋላ እንደ አዲስ እንደገና መንጃ ፈቃድ ለማግኘት ሊያመለክት ይችላል” ይላል፡፡
ዘ-ህወሀት 500 ወይም ከዚያ በላይ ብዛት ላላቸው የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ስለአዲሱ የትራፊክ ቁጥጥር ደንብ ገለጻ ካደረገ በኋላ ያንን ሕግ “ወይም ሌላ” እንዲከተሉ እና ተግባራዊ እንደሚያደርግ ይፋ አድርጓል!
“ወይም ሌላ” የሚለው ተቀጽላ ቃል የቀረበው አሽከርካሪዎቹ ወደዱም ጠሉ አዲሱ ሕግ በዘ-ህወሀት ጉሮሯቸውን ተይዘው በግድ ተግባራዊ እንደሚደረግ ለተሰባሰቡ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ሲናገር እና ሲያስፈራራ በነበረው በስም አሰፋ መዝገቡ በተባለ የዘ-ህወሀት ታዛዥ ሎሌ ነው፡፡ ዛቻዉን ሲጥል አሰፋ መዝገቡ  ዓይኑንም አላሸም!
በታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ የተደረገው የመዝገቡ የጦርነት እወጃ ቅጽበታዊ የሆነ ግጭትን አስከትሏል፡፡ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች እጅግ በጣም ተቆጥተው ነበር፡፡ እ.ኤ.አ የካቲት 22/2016 የስራ ማቆም አድማ መቱ፡፡ የከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ሽባ ሆኖ ውሏል፡፡ በዕለቱ የአዲስ አበባ ኗሪዎች በየቦታው በእግር ሲቋትኑ/በእግር ጉዞ ሲውተረተሩ ተስተውለዋል፡፡ ዘ-ህወሀት አዲሱ ሕግ ለ90 ቀናት ያህል ተግባራዊ ሳይደረግ እንደሚቆይ አሳውቋል፡፡ በሚቀጥለው ዕለት የታክሲ አሽከርካሪዎች ወደ መደበኛ ስራቸው ተመለሱ፡፡
እንደ አንድ ዘገባ ከሆነ አዲስ አበባ በ7,500 ሰማያዊ እና ነጭ ቅብ ባላቸው ሚኒባስ ታክሲዎች፣ በዘ-ህወሀት ቁጥጥር ስር ባለው እና በአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ስር በሚተዳደሩ በ800 አውቶብሶች፣ በ500 ሀይገር መካከለኛ አውቶብሶች፣ በአሊያንስ የትራንስፖርት አገልግሎት ኩባንያ ባለአክሲዮኖች የግል ንብረትነት በሚተዳደሩ በ25 አውቶብሶች፣ በ4,000 ነጭ ሚኒ ባሶች እና በ400 ሀገር አቋራጭ አውቶቶብሶች እየታገዘ የሚካሄድ አገልግሎት አላት፡፡
እጅግ በጣም የተቆጣ  አንድ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌር እንዲህ የሚል ቃለመጠይቅ ሰጥቷል፡
“የስራ ማቆም አድማው ቅጽበታዊ መነሻ ምክንያቱ አዲሱ የትራፊክ ሕግ ቢሆንም ቅሉ ዋናው እና ቁጥር አንድ የሆነው ምክንያት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ በተለያዩ አጋጣሚዎች የመንግስት ባለስልጣኖች ስልጣናቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ በመጠቀም የተሳሳቱ ሕጎችን እየተገበሩ የታክሲ ሾፌሮችን የተጎጅነት ሰለባ እንዲሆኑ እያደረጉ በመምጣታቸው ምክንያት ነው፡፡ ለዚህም ነው ህብረተሰቡ የእኛን የስራ ማቆም አድማ ደግፎ የወጣው፡፡ ህብረተሰቡ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ችግር እንዳለ ያውቃል፡፡ የፍትህ እጦት ተንሰራፍቷል፡፡ የመልካም አስተዳደር እጦት ችግር ህዝቡን እጅ ከወርች ጠፍንጎ ይዟል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ማንኛውም የህወሀት አባል የፈለገውን ነገር ማድረግ ይችላል፣ አንድን የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌር በቁጥጥር ስር ማዋል እና ማሰር ይችላል፡፡ የታክሲ ሾፌሩን ወደየትም ወደሚፈልገው ቦታ እንዲያሽከረክር ሊያዝዘው ይችላል፡፡ ይህ የስራ ማቆም አድማ እንቅስቃሴ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች መብታቸውን ለመጠየቅ ያደረጉት ሙከራ ነው፡፡ ህወሀት እና ኢህአዴግ(እውነተኛውን የህወሀትን ማንነትለመደበቅ ሲባል ለህወሀት መጠቀሚያ ሲባል የተቋቋመ ግንባር) የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮችን በማስፈራራት የስራ ማቆም አድማውን ለማጨናገፍ ጥረት አድርገዋል፡፡ በአዲሱ ሕግ አንድ ጥፋት 7 ነጥቦችን ያስይዛል፣ እናም አንድ ሾፌር 20 ነጥቦች ከተቆጠሩበት ሙሉ በሙሉ ህልውናውን እንዲያጣ በማድረግ ከስራው ይታገዳል፡፡ እነርሱ [ህወሀቶች] የአሽከርካሪ ሾፌሮችን መንጃ ፈቃዶች መንጠቅ እንደሚችሉ፣ የታክሲዎቻቸውን ሰሌዳዎች በመፍታት እና ከዚህም አልፎ ተሸከርካሪዎችን ለመቀማት እንደሚችሉ ለማስፈራራት ሙከራ አድርገዋል፡፡ ሆኖም ግን የፈለገውን ያህል ለማስፈራራት ጥረት ቢያድርጉም 99.9 በመቶ የሚሆኑት የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ያለምንም ፍርሀት የስራ ማቆም አድማውን ተቀላቅለዋል…“ ብሏል፡፡
ዘ-ህወሀት የግል የትርንስፖርት ዘርፉን ለማሽመድመድ ሲያደርገው የቆየው ይህ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም፡፡
እ.ኤ.አ ነሐሴ 2014 መኪና ወደ ሀገር ውስጥ በሚያስገቡት እና በሚያከፋፍሉት ሰዎች ላይ (በእርግጥ የዘህወሀትአጫፋሪዎች ከግብር ጫናው ነጻ ናቸው) ከፍተኛ የሆነ ግብር ቆለሉባቸው፡፡
አንድ መኪና አከፋፋይ የሆነ ነጋዴ በድንገት በወጣው የጉምሩክ ሕግ መሰረት ልክ በድንገት ቅጽበታዊ በሆነ መልኩ እንደወጣው የትራፊክ ደንብ ሁሉ ቀደም ሲል በተከታታይ በ5 ዓመታት ውስጥ በአንድ መኪና ላይ ይጣል የነበረው ሁሉም ግብሮች/sundry tax 134,000 ብር የነበረ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2014 ለተመሳሳይ ግብይት በ183.6 በመቶ በማሳደግ ብቻ ሳይሆን በመቆለል ብር 380,000 እንዲከፍል ዱብ ዕዳ ሆኖ ተጣለበት፡፡ መኪና አከፋፋዩ 35 በመቶ የጉምሩክ ግብርን ጨምሮ፣ 10 በመቶ የሱር ታክስ ግብር፣ 100 በመቶ የኤክሳይስ ታክስ ግብር፣ 15 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር እና 3 በመቶ ዊዝሆልዲንግ ታክስ ግብር በመክፈል እንደዚህ ያሉትን በርካታ የግብር ዓይነቶች እንዲከፍል በመዳረጉ ቅሬታውን ለዘ-ህወሀት አቀረበ፡፡
ዘ-ህወሀት በሕገወጥ መልክ የሚሰበስበውን እና ግብር እያለ በሚጠራው በዜጎች ሊከፈል በማይገባው ሕግን ያልተከተለ የገንዘብ ዘረፋ ላይ እጅግ ከመጠን በዘለለ መልኩ ደስታ እና ሀሴትን ተጎናጽፎ ይገኛል፡፡
የዘህወሀት የባለሶስት ጥፋት እና ከታከሲ ማሽከርከር ስራ ላይ የማባረር ሕግ በእርግጠኝነት ዓላማው ስለምንድንጉዳይነው?  
የዘ-ህወሀት የባለሶስት ጥፋት እና የታክሲ ስራህን በማቆም ከንግድ ዘርፉ ዘወር በል ቻው በማለት ዘ-ህወሀት በአሁኑ ጊዜ እየፈጸመ ያለው ሕገ ወጥ ድርጊት ዘ-ህወሀት ቀደም ሲል ጀምሮ በህዝቦች ላይ ሲሰራ የቆየው የረቀቀ ሸፍጥ እና ደባ አንዱ ተቀጽላ አካል እንደሆነ እገነዘባለሁ፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ዘ-ህወሀት የሕክምና ቱሪዝም/Medical tourism የሚል የወሲብ ቱሪዝምን የሚያስፋፋ አስፈላጊ ያልሆነ ውሳኔ ለማስተላለፍ ሞክሯል፡፡
አዎ፣ ዘ-ህወሀት በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ እና የወሲብ ስራ ሀራራ ከሚያናውዛቸው በዘ-ህወሀት አጠራር አልሚ ተብየ አጥፊዎች ከካታር ጋር በኢትዮጵያ ውስጥ ግዙፍ የሆነ የዝሙት ማሳደጃ ማዕከል እና እንደዚሁም ደግሞ የሕክምና ቱሪዝም/Medical tourism ገንቢዎች እያለ ከሚጠራቸው ጋር የውል ስምምነት አድርጓል፡፡
የዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች እኛን ሊያታልሉ እንደሚችሉ አድርገው ያስባሉ፣ ሆኖም ግን ሳይሳካላቸው ቀርቶ ሙሉ በሙሉ ከስረዋል፡፡ እኛ ነቂቶ ካልን ቆይተናል፣ እናም ከንቱ ድካም እና የተበላ እቁብ ነው፡፡
የዘ-ህወሀትን ሸፍጠኛ የቡድን መንግስታዊ ማሽንን የሚያንቀሳቅሱት በጣም ጥቂት ስብስቦች ቡድንን ያካተተ እጅግ በጣም አታላዮች፣ ድብቆች፣ አጭበርባሪዎች፣ ተደጋጋሚ ሸፍጥ ሰሪ መሰሪዎች፣ ሰይጣናዊ ድርጊት ሰሪዎች፣ ጨካኝ እና አረመኔዎች፣ አውዳሚዎች፣ አደገኞች፣ ጽልመተኞች እና የማኪቬሌያንን የፖለቲካ ፍልስፍና የሚያራምዱ በዓለም ላይ በሁሉም ቦታ የሚገኙ ሰው መሰል ሰይጣኖች ያሉበት መሆኑን ሁልጊዜ ስናገር ቆይቻለሁ፡፡ በሁሉም አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ጡንቻማ ሸፍጠኞች ናቸው፡፡
የዘ-ህወሀት ሸፍጠኞች እንደገና ለማታለል፣ የበለጠ ለማጭበርበር፣ ለማሞኘት፣ ለማጦዝ፣ የበለጠ ለማታለል እና ተቃዋሚዎቻቸውን ለማጥፋት ብቅ ያሉ ለመሆናቸው አምናለሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን የጥፋት በትራቸውን ለማሳረፍ እየታገሉ ያሉት በታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ላይ ነው!
ለመናገር የምጠላው ነገር ቢሆንም በእርግጥ ለእኔ አብዛኞቹ የስራ ማቆም አድማ የመቱት የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች በጫካው ውስጥ ያለውን እያንዳንዱን ዛፍ ለመመልከት አይችሉም፡፡
ትልቁን ስዕል እያዩት አይደለም፡፡
በዘ-ህወሀት “አዲሱ የትራፊክ ደንብ”  እየተባለ በሚጠራው የድብብቆሽ ጨዋታ ሀሳባቸው እንዲቀለበስ ተደርጓል፡፡
የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች በዘ-ህወሀት የውሸት የማስመሰያ ወጥመድ ውስጥ ወድቀዋል፡፡
የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ተታለዋል፣ እናም ተጭበርብረዋል፣ ሆኖም ግን ነገር በግልጽ አይታያቸውም፡፡ ምን ዓይነት አሳዛኝ ድርጊት ነው እባካችሁ!!!
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እያሉ የሚጠሩትን እንዛዝላ በአዲስ አበባ ዙሪያ አካባቢ በሚገኙ አርሶ አደሮች ላይ በመጫን ለማታለል ሙከራ አድርገዋል፡፡
አሁን በቅርቡ ባዘጋጀሁት ትችቴ በግልጽ ለማመላከት እንደሞከርኩት የአዲስ አበባ ሳይሆን የዘህወሀት ማስተርፕላንነበር፡፡ የዘ-ህወሀት ሆዳሞች እና የመሬት ዘረፋን በማካሄድ የማይረካ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ሌት ቀን የሚቋምጡት ወሮበላ ዘራፊዎች ለዕኩይ ዓላማቸው ስኬታማነት በድብቅ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እያሉ በሚጠሩት ስም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ዘ-ህወሀት በከተማዋ ዙሪያ ያለውን እያንዳንዷን ስንዘር መሬት ከወሰደ በኋላ በቀጣይነት ደግሞ ከከተማዋ በመውጣት የተለመደ እና ተመሳሳይ ዘረፋውን ይቀጥላል፡፡
ሆኖም ግን በደፋር ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት እና ተጋድሎ የዘ-ህወሀት ቀልደኛ/ኮሚኮች ገሀነም እንዲገቡ እና በዚያው እንዲቆዩ በማድረግ ታግደዋል፡፡ የዘ-ህወሀት ቦቅቧቆች እንደዚህ ያለ ዕቅድ አልነበረም፣ እንዲያው ስለዚያ ነገር የሚብላላ ሀሳብ ብቻ ነበር ያለው በማለት ዓይኔን ላፈር በማለት ቅጥፍናቸውን ለቀውታል፡፡ ወቼ ጉድ፣ ወይ ነዶ!
በአሁኑ ጊዜ ደግሞ መልኩን በመቀየር የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮችን የጥቃት ሰለባ ለማድረግ ተመሳሳይ ሸፍጡን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ደፋር በሆኑ ኢትዮጵያውያን የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች አማካይነት የዘ-ህወሀት ፈጣጣ ኮሚኮችን ገሀነም ግቡ ብለዋቸዋል፡፡ ዘ-ህወሀት የአዲሱን የትራፊክ ደንብ ተግባራዊነት ለ90 ቀናት አራዝሜዋለሁ ብሏል፡፡ ሆኖም ግንሾፌሮች እንዳትሞኙ አንዳተኙ ፡፡ ህወሀት ለጊዜው ጸጥ ያለ መስሎ ይቆይ እናእንደ ቀሳፊው የድርቅ አደጋ ተመልሶዘው ብሎ ይመጣል፡፡
እኔ ባለኝ መረጃ መሰረት እና እንደማስበው ከሆነ ዘ-ህወሀት አዲሱ የትራፊክ ደንብ እያለ የሚጠራው ደንብ የትራፊክ ሁኔታውን ለማሻሻል አስቦ አይደለም፡፡
መጨናነቅን ለመቀነስ ታስቦ አይደለም፡፡
እንደዚሁም ደግሞ የትራንስፖርት ዘርፉን ቅልጥፍና ለማሻሻል ታስቦም አይደለም፡፡
Addis-Ababa-Taxi-STRIKE3
በተጫባጭ ማስረጃ እና በመረጃ ላይ ተደግፎ የቀረበው የእኔ ትንታኔ አዲሱ ሕግ የትሮጃን ፈረስ ነው፡፡ በጥንት ዘመን ግሪኮች እጅግ ግዙፍ የሆነ የእንጨት ፈረስ ሰሩ እና በውስጡ ወታደሮች እንዲደበቁ በማድረግ የሚዞር ለማስመሰል ሞከሩ፡፡ ያልጠረጠሩት ትሮጃዎች ፈረሱን ወደከተማው በማምጣት በጨለማው ተታለው እንደነበር ተገነዘቡ፡፡ የግሪክ ወታደሮች ከፈረሱ ሆድ ውስጥ ወጡ እና ውጊያ በመክፈት ከውጭ ያሉ ወታደሮች እንዲገቡ አደረጉ፡፡ ትሮይ ወደቀች ፡፡ ስለዚህ ገለጻው እንዲህ ይላል፣ “የግረክ መሳይ ስጦታዎችን ተጠንቀቁ“፡፡
ዘ-ህወሀት አዲሱን የትራፊክ ደንብ ለአዲስ አበባ ከተማ እና ለሌሎች ከተሞች በስጦታነት አቅርቧል፡፡ በአዲሱ ሕግ ውስጥ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮችን የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እውንነትን እና የፖለቲካ አጋርነትን በማጥፋት የከተማውን ኗሪ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የተዘጋጁ፣ ፈቃደኛ የሆኑ እና የሰለጠኑ ወታደሮች አሉ፡፡
የዘህወሀት አዲሱ የትራፊክ ሕግ””  አራት ዓላማዎች አሉት የሚል እምነት አለኝ፡፡ እነርሱም፣
አንደኛ፡  “አዲሱ የትራፊክ ሕግ” በዘ-ህወሀት እጅ ዘንድ ያለ ጠንካራ የሆነ የፖለቲካ መሳሪያ ነው፡፡ የሕጉ ዋናው ዓላማ የኢትዮጵያ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች በቀጣይነት የዘ-ህወሀት የኢኮኖሚና የፖለቲካ የስጋት አደጋዎች እንዳይሆኑበት አስቀድሞ በሕግ ሽፋን ሽባ ለማድረግ እና ስለዕለት በዕለት ኑሮ ላይ ብቻ ተጠምደው በፍርሀት እና በቆፈን ተጠፍንገው ለአገዛዙ እያጎበደዱ እና እየሰገዱ እንዲኖሩ ለማድረግ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ለታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ግልጽ ሆኖ ላይታያቸው ይችላል፡፡
የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች እንደ አንድ የኢኮኖሚ ስብስብ ቡድን ትስስር ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ኃይል እንደሚኖራቸው ዘ-ህወሀት አሳምሮ ያውቃል፡፡ በየዕለቱ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡት ባለው በሚሊዮን በሚቆጠር ህብረተሰብ የደም ስር ላይ ጣቶቻቸውን አስቀምጠዋል፡፡ እምቅ የሆነ የፖለቲካ ኃይል አላቸው፡፡ ይኸ እውነታ ለበርካታ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ሊታያቻው የሚችል አይሆንም፡፡ እምቅ የፖለቲካ ኃይል ስል በመቶ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኝ ዒላማ ላይ በማነጣጠር በደጋኑ ውስጥ የተጠራቀመውን ኃይል በመጠቀም ዒላማውን ለመምታት እንደሚቻል ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮችም በታመቀው የፖለቲካ ኃይል ዒላማውን መምታት ይችላል ለማለት ነው፡፡
ዘ-ህወሀት የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮችን እምቅ የፖለቲካ ኃይል በህልዮት፣ በተግባር እና በታሪክ አሳምረው ያውቃሉ፡፡
እ.ኤ.አ በ1973 የነዳጅ ዋጋ በኢትዮጵያ በአራት እጥፍ በጨመረ እና አውዳሚ ረኃብ በተከሰተበት ጊዜ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች የነዳጅ ዋጋ ጭማሪውን በመቃወም በንጉሳዊው አገዛዝ ላይ የስራ ማቆም አድማ በመምታት ህዝባዊ አመጹ እንዲቀጣጠል ወሳኝ ሚና ተጫውተው ነበር፡፡ እንደዚሁም እነርሱ ለሌላው አርዓያ በመሆን መምህራን፣ የባቡር ሰራተኞች እና ጫኝ እና አውራጅ ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ በማንሳት የስራ ማቆም አድማ እንዲመቱ ምሳሌ ሆነዋል፡፡ ተማሪዎች የተከሰተውን ረኃብ በመቃወም ህዝባዊ እንቅስቃሴ ያደረጉ ቢሆንም ወታደሮች ህዝባዊ አመጹን በመንጠቅ አምባገነናዊ ወታደራዊ መንግስት አቋቋሙ፡፡
ሆኖም ግን የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች እ.ኤ.አ በ1973 የተከሰተውን ህዝባዊ አመጽ የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ያቀጣጠሉት ለመሆናቸው የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም፡፡
እ.ኤ.አ የካቲት 22/2016 የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች የስራ ማቆም አድማውን ውጤታማ በሆነ መልኩ የሚተገብሩት ከሆነ ድባቅ ለመምታት የሚያስችል ኃይል እንዳላቸው ለዘ-ህወሀት በግልጽ አሳይተዋል፡፡
የዘ-ህወሀት ስልት ነዳፊዎች የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ከፍተኛ የሆነ እምቅ የፖለቲካ ኃይል እንዳላቸው እና በእነርሱ ላይ ለሚደረግ ህዝባዊ አመጽ ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ አሳምረው ያውቃሉ፡፡ ስለሆነም የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮችን ስልታዊ በሆነ መልኩ ማዳከም እና የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ስብስብ ትስስራቸው እንዲበጠስ እና እንዲበታተን ለማድረግ አጥንክሮ መስራት የዘህወሀት አዲሱ የትራፊክ ሕግ ዋና መርህ ነው፡፡
ዘ-ህወሀት የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች የኢትዮጵያ የከተማ ኢኮኖሚ እና የትራንስፖርት ስርዓቱን ኦክሲጂን ተሸካሚ ቀይ የደም ሕዋሳት/hemoglobin መሆናቸውን አሳምሮ ያውቃል፡፡
የታክሲ አሽከከርካሪ ሾፌሮች የኢኮኖሚ እና ትራንስፖርት ስርዓቱን ትስስር አጠናክረው በመያዝ ዘ-ህወሀትን ከጉልበታቸው ስር የማንበርከክ ኃይል አላቸው፡፡ እ.ኤ.አ የካቲት 22/2016 የተደረገውም ይኸው ነው፡፡
ዘ-ህወሀት ሁሉንም የፖለቲካ ተቃናቃኞቹን እና የፖለቲካ ፓርቲዎችን አጥፍቷል፡፡ ይፋ በሆነ መልኩ 79 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አንድ ፓርቲ ብቻ (የህወሀትን ማንነት ለመደበቅ ሲባል የበግ ለምድ ለብሶ ለማስመሰያየተቀመጠው ኢህአዴግ) በይስሙላው የዝንጀሮ ፓርላማ ስር ያሉትን መቀመጫዎች መቶ በመቶ ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡
የዘ-ህወሀት አዲሱ የትራፊክ ሕግ ለወደፊቱ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ አደጋ ስጋት ይሆኑብኛል ብሎ የሚያስባቸውን የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ህልውና ለማሳጣት ሲባል ዓላማ አድርጎ የተዘጋጀ ለመሆኑ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡
ሁለተኛ፡  ዘ-ህወሀት የእራሱን የፖለቲካ ዓላማ ለማሳካት በማሰብ ስልታዊ በሆነ መንገድ አሁን በሾፌርነት ደረጃ እያገለገሉ ያሉትን የታክሲ ሾፌሮች ከታክሲ ገበያው በማስወገድ የዘ-ህወሀት፣ ታዛዥ ሎሌዎች፣ ደጋፊዎች፣ ጓደኞች፣ አገልጋዮች እና ሌሎች ታማኞች የታክሲውን ገበያ በብቸኝነት ጠቅልለው እንዲይዙ ለማስቻል እንደሆነ አምናለሁ፡፡
ማንም ሰው ቢሆን የአዲሱን የትራፊክ ሕግ የቅጣት ደረጃዎች በጥሞና በማገናዘብ ይህንን ስልት በግልጽ ማየት ይችላል፡፡ ባለ 20 ነጥብ የነጥብ አሰጣጥ ስርዓት ዋና ዓላማ ተደርጎ የወጣው በአሁኑ ጊዜ በታከሲ ሙያ ላይ ተሰማርተው የሚገኙትን የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከታክሲ ገበያው ስራ ውስጥ ለማስወጣት የታቀደ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል አንድ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌር በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 7 ነጥብ የሚያሰጥ ቅጣት ሊሰጠው ይችላል፡፡ ለምሳሌም የእንዝህላልነት አነዳድ፣ የመሳሪያ ያለመኖር፣ በቂ ያልሆነ የትራፊክ ቁጥጥር መሳሪያዎች ያለመኖር፣ አደጋዎች፣ ህዝብ የሚበዛባቸው ሰዓቶች ላይ የሚፈጸም ጥፋት፣ ወዘተ፡፡ በቀናት ወይም ደግሞ በሳምንታት ውስጥ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌር 20 ወይም ከዚያ በላይ ነጥቦችን በመስጠት ከታክሲ ገበያው ለዘላለሙ ማባረር ይችላል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ያሉት የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች በነጥብ አሰጣጥ ስርዓት ከሙያቸው በግዳጅ እንዲለቁ በማድረግ ዘ-ህወሀት ሕግን የጣሱ ናቸው በማለት የነጠቃቸውን ጥቂት የመንጃ ፈቃዶች ለእርሱ ታዛዥ ሎሌዎች፣ ደጋፊዎች፣ ጓደኞች እና አገልጋዮች እንደሽልማት (ለዋና ደጋፊዎቻቸው ነጻ ስጦታ) በማድረግ በደስታ ያድላሉ፡፡ ዘ-ህወሀት በከፍተኛ  የተረፈዉን ፈቃዶች በከፍተኛ ዋጋ ይሸጠዋል ፡፡ ቀስ በቀስም የዘህወሀት ደጋፊዎች፣ ታዛዥ ሎሌዎችእና ጫማ ላሾች የታክሲገበያውን በበላይነት በመቆጣጠር የዘህወሀትን ፍላጎት ለማሳካት ጥረት ያደርጋሉ፡፡
ከዚህም አልፎ የፓርቲ ሰላዮች በመሆን የህዝቡን መንፈስና እና አስተሳሰብ ቀን በቀን እየሰለሉ እና እየለኩ ዘገባ በማቅረብ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
የዘህወሀት አዲሱ ሕግ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ 80 – 85 በመቶ የሚሆኑትየታክሲአሽከርካሪ ሾፌሮች ከታክሲ ማሽከርከር ገበያው ውስጥ እንዲወጡ በማድረግ በዘህወሀት ደጋፊዎች፣ እናታዛዥ ሎሌዎችእንዲተኩ ይደረጋሉ፡፡
እድለኛ የመሆን አጋጣሚ ካገኙ ደግሞ ጥቂቶች የኢህአዴግ አባል በመሆን የመንጃ ፈቃዳቸው ሊመለስላቸው ይችላል፡፡ ከዚያ ውጭ ያሉት ደግሞ ሌላ ስራ መፈለግ ይኖርባቸዋል ወይም ደግሞ መምገድ ላይ ለመለመን ይገደዱ ይሆናል፡፡ (ወደ እውነታነት የሚመጡ ነገሮችን በመተንበይ ረገድ በጣም ጥሩ የሆነ ምዝገባ እንዳለኝ አምናለሁ፡፡)
እንግዲህ የኢትዮጵያ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ይህንን መራር እውነታ መጋፈጥ አለባቸው፡፡
የዘ-ህወሀት የተበላሸና ወንጀለኛ የፈቃድ አሰጣጥ፣ የመንግስት ኮንትራት ስምምነቶች፣ የግብር እዳ ቅነሳ ሙስና እና የህግ ውጤቶች በየጊዜው የመቀያየር ሁኔታን በማስመልከት የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ በ2012 በኢትዮጵያ ላይ ባደረገው መጠነ ሰፊ የሙስና ጥናት ላይ ይፋ ተደርጎ ተመዝግቦ ተቀምጧል፡፡
ዘ-ህወሀት አዲሱን የትራፊክ ሕግ በመጠቀም ጠቅላላ የከተማውን ኢኮኖሚ በቀጥጥሩ ስር በማድረግ ለእራሱ አጎብዳጅ ሁኔታን ለመፍጠር እያደረገ ካለው እውነታ ጋር በተያያዘ መልኩ ያለው ምላሽ ከሚከተሉት ጥያቄዎች ከሚገኙ ምላሾች የሚገኝ ይሆናል፡
1ኛ) በአሁኑ ጊዜ ማንም ኢትዮጵያዊ የዘ-ህወሓት (ኢህአዴግ የማችበርበሪያ የማጭበርበሪያ ሰሙ) አባል ሳይሆን በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ በእርግጠኝነት ስራ ፈልጎ መቀጠር ይችላልን?
2ኛ) ማንም ሰው ቢሆን ለዘ-ህወሓት ታማኝነትን ሳይሳይ እና አጎብዳጅ ታዛዥ ሎሌ ሳይሆን በያዘው የመንግስት ስራ ላይ በነጻነት ያለምንም ችግር ሊቀጥል ይችላልን?
3ኛ) በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የዘ-ህወሓት  አባል ሳይሆን በተሻሉ የከፍተኛ የትህምህርት ተቋማት በመመዝገብ ትምህርቱን መከታተል ይችላልን? ወይም ደግሞ ዓለም አቀፍ የምግብ እርዳታ ማግኘት ይችላልን?
ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት “ልማት ካለነጻነት፡ እርዳታ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት ለመጨቆኛ መሳሪያ እየዋለ እንደሆነ“ በሚል ርእስ ያዘጋጀውን እና ዘ- ህወሀት በለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍ የሚያገኘውንሀብት እና እርዳታ እንዴት አድርጎ ስልጣኑን ለማጠናከር እየተጠቀመበት እንደሆነይፋ የሆነውን ባለ105 ገጽ ዘገባ መመልከት ብቻ በቂ ነው፡፡
4ኛ) ዘ-ህወሀት የተራቡ አርሶ አደሮችን ከጉልበቱ ስር እንዲንበረከኩ የሚያደርግ ከሆነ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮችን አጥንታቸው እስኪታይ ቢግጣቸው የሚያስገርም ነገር ሊሆን ይችላልን?
እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ የዘ-ህወሀት የቁጥጥር አባዜ ደህንነት እንዲሰማው ከተፈለገ ሁሉንም ነገር መቆጣጠር አለበት፡፡
የታክሲ አሽከርካሪዎች ዘ-ህወሀቶችን ገሀነም እንዲገቡ እና ደህንነት እንዳይሰማቸው አድርገዋል፡፡ ዘ-ህወሀት በማንኛውም መንገድ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮችን መቆጣጠር በሺታ አለበት፡፡
ሦስተኛ፡ የዘህወሀት አዲሱ የትራፊክ ሕግ በሸፍጥ ወረቀት የተጠቀለለ ድብቅ የታክሲ ግብር ልመናን አቅርቧል፡፡ገንዘቡን ተከተል፡፡
ዘ-ህወሀት ተስፋቢስ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ዘ-ህወሀት እንደ ደም መጣጭ ሰይጣን ደምን ለመጠጣት ተስፋቢስ ሆኗል፡፡
ዘ-ህወሀት ገንዘብን ለማግኘት ሲል ያለ የሌለ አቅሙን ሁሉ በማድረግ ጥረት ያደርጋል፡ መሬትን በመቀራመት ይሸጣል፣ ከሀገሪቱ ጥንታዊ ቤተመጽሐፍት ታሪካዊ መጽሐፍትን በማውጣት ይሸጣል፣ የስነ አጽም ቅሪቶችን እና ሌሎችንም በዓይን የሚታዩ ነገሮችን ይሸጣል፡፡
ከዚህም ባለፈ መልኩ ዘ-ህወሀት የወሲቡን ቱሪዝም  የህክምና ቱሪዝም እያለ በሚጠራው ማደናገሪያው የሴት እህቶቻችንን ገላ በመሸጥ ገንዘብ ለማግኘት በመቋመጥ ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት አገልግሎት በአብዛኛው በትክክለኛው አካሄድ ስለማይመራ የውጭ ምንዛሬ ጥቁር ገበያዎች (ኮንትሮባንድ) እንደ አሸን እንዲፈሉ አድርጓል፡፡
ዘ-ህወሀት ወደ ውጭ ሀገር በመዞር ዶላርን እና ኢውሮን በመለመን ወደ ግል ባንካቸው ለማጨቅ ይቋምጣሉ፡፡
ባለፈው ወር በአፍሪካ ህብረት እና በቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት በታቦ ኢምቤኪ ሊቀመንበርነት የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በተካሄድ ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ ከአፍረካ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር በአብዛኛውም ወደ አደጉ ሀገሮች በሚወጣ ገንዘብ ቀዳሚ ሆና ተገኝታለች፡፡
ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት እ.ኤ.አ በ2011 እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፣ “የኢትዮጵያህዝቦች አጥንታቸው እስኪታይ ድረስ ተግጠዋል፡፡ ከአስከፊ እጦት እና ድህነት ማጥ ውስጥ ለመውጣት የቱንም ያህል ጊዜ ጥረት ቢያደርጉም እንኳ በአሁኑ ጊዜ ባለው ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት በወንዙ ወደ ላይ አቅጣጫ በመዋኘት ላይ ይገኛሉ“ ብሏል፡፡ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)
የዘህወሀት አዲሱ የትራፊክ ሕግ የኢትዮጵን የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች አጥነታቸው እስኪታይ ለመጋጥ የተሰላስሌትነው፡፡ የታክሲ ማሽከርከር ሙያ እስከ አሁን ድረስ በአንጻራዊ መልኩም ቢሆን ነጻ ነው እየተባለ የሚጠራ እና በዘ-ህወሀት ብቸኛ ቁጥጥር ስር ያልዋለ የንግድ ስራ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ በዘ-ህወሀት ያልተያዘ፣ በቁጥጥር ስር ያልዋለ፣ የማይተዳደር ወይም ደግሞ ከዘ-ህወሀት መዳፍ ውስጥ ያመለጠ ገቢ የሚያስገኝ ስራ ከቶውንም የለም፡፡ በፍጹም!
ዘ-ህወሀት የማያነፈንፈው አትራፊ እና አዳጊ የሚመስል ቢዝነስ እንደሌለ የሚክድ ሰው አለን? ምንም ዓይነት ቢዝነስ! እነርሱ የማይወስዱት ቢዝነስ ከሆነ በአንድ ምሽት ሊያጠፉት አይችሉምን?
ዘ-ህወሀት ኢኮኖሚውን፣ ወታደራዊ ኃይሉን፣ ፖለቲካውን፣ የሲቪል ተቋማትን፣ ወዘተ አይቆጣጠርምን? ዘ-ህወሀት የመጨረሻውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በስንት መቶኛ ነው ያሸነፈው? በዚህ ጉዳይ ላይ ማንም ምንም ዓይነት ሀሳብ ሊኖረው ይችላልን?
የዘ-ህወሀት አዲሱ የትራፊክ ሕግ ከፍተኛ የማጭበርበር ሸፍጥን በተላበሰ መልኩ ተዘጋጅቶ የቀረበ የተደበቀ ግዙፍ ህገወጥ ግብር የተቆለለበት የሸፍጥ አሰራር ዕቅድ ነው፡፡
እ.ኤ.አ የካቲት 22/2016 እራሱን “ለሁሉ” እያለ የሚጠራ የንግድ ተቋም እንዲህ የሚል መግለጫ አወጣ፡
“በዛሬው ዕለት (ሰኞ የካቲት 22/2016) የትራፊክ ደንቡን የሚጥሱ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም ሾፌሮች ቅጣታቸውን “በለሁሉ” በመቅረብ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ለሁሉ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝ የትራፊክ ቅጣት ክፍያን ለመሰብሰብ የተቋቋመ ብቸኛ ድርጅት ነው፡፡“
እኔ እስከማውቀው ድረስ የትራፊክ ቅጣትን በአንድ የግል ኩባንያ እስከፋይነት ገቢ እንዲደረግ የሚለው መሰረተ ሀሳብ ከፍተኛ ደረጃ የሙስና ግማት ሽታን ይጋብዛል፡፡
በዘ-ህወሀት የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች የልመና ሸፍጥ ውስጥ ያለው “ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ” እየተባለ የሚጠራው እና ለሁሉ እየተባለ በሚጠራው የክፍያ አሰራር ስርዓት ውስጥ የዘ-ህወሀትን ቦርሳ የተሸከመ ጽልመታዊ ተቋም አለ፡፡
ይገማል! ይጠረናል! የዘህዋሃትና ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ መሞዳሞድ ፡፡
በለሁሉ ውስጥ ከዘ-ህወሀት ጋር ስምምነት የምታደርግ ግዙፍ፣ ወፍራም እና ዓይኗ የፈጠጠ አይተ ሞገጥ አሸታለሁ፡፡
ያች የሙስና አይጥ ገና ከ10 ሺ ሜትሮች ርቀት ላይ ትሸተኛለች፡፡ (ቅርናት!  ቅርናት! …ኡፍ፤ ኤዲያ እቴ…)
ግን “ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ” ምንድን ነው?  “ለሁሉ” ምንድ ነው?
**** ”ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ“ የሚለውን አየመረመርን ሳለን የእርሱ ድረ ገጽ በአስቸክዋይ ተዘጋ : እንዲህ የሚል ጽሁፍ አስቀምጧል፡፡ **** አስፈላጊ የሆነው ድረ ገጽ ጫን በሚደረግበት ጊዜ መልዕክቱ እንዲህ ይላል፣ “ይኸ ድረ ገፅ አይገኝም፡፡“
ለጉግል መዛግብት ምስጋና ይግባና ማስረጃው እስከ አሁንም ድረስ አለ፡፡ (1) እዚህ፣ (2) እዚህ (3) እዚህ የሚሉትን የግንኙነት መስመሮች ተመልከት፡፡
እንደ newbusinessethiopia.com “ለሁሉ“ በኮሙኒኬሽን እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና በክፍያፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መካከል እና በፌዴራል የትራንስፖርት ባለስልጣን እና በአዲስ አበባ የመንገዶች ባለስልጣን ተባባሪነት የተደረገ የግል እና የመንግስት ስምምነት ነው፡፡
ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ እንዲህ የሚል ራዕይ አስቀምጧል፣ “ራዕይው ግብይቶችን ቀላል በማድረግ፣ አቅምን ያገናዘበ እና ሊደረስበት የሚችል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የህዝቦችን ህይወት በማሻሻል የእራሱን አስተዋጽኦ ማድረግ“ ይላል፡፡ ተልዕኮው ደግሞ እንዲህ ይላል፣ “ቀጣይነት ያላቸውን ቴክኖሎጂዎች እና የማሰራጫ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ፋይናንስ ነክ ለሆኑት እና ላልሆኑት ተደራሽነትን በመፍጠር የተቀናጀ እና ሊያድግ የሚችል አገልግሎትን ማቅረብ ነው፡፡“
ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ አጋሮች የኮሙኒኬሽን እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ኢትዮ-ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ባለስልጣንን  ያካትታል፡፡
ሆኖም ግን ከዘ-ህወሀት ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ጋር አጋሮች (እውነተኛ ስሞች) እነማን ናቸው?
ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂን በባለቤትነት የያዘው ማን ነው?
ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ጀርባ ማን አለ? ስላቅ ያበዛ የነበረው እና አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በአንድ ወቅት በስሩ ያለውን አጎብዳጅ ድርጅት በስም ኦህዴድ በሚባለው ድርጅት ላይ ተቆጣ እና አሁን ልባችሁ እንደፈጣን ሎተሪ ቢፋቅ ኦነግ ሆናችሁ ትገኛላችሁ እንዳለው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ አሁንም የክፍያፋይናንሻል ቴክኖሎጂልብ እንደ ፈጣን ሎተሪ ቢፋቅ ማን ሊሆን ይችላል? ውስጡን ለቄስ ነው፣ ሆድ ይፍጀው!
በእራሱ ድረ ገጽ ላይ ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ እንዲህ ይላል፣ ኩባንያው የተመሰረተው .. 2010ሲሆንበኢትዮጵያ ውስጥ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ልምድ ባለውድርጅትመስራችነት ነው፡፡“ (አጽንኦ ተጨምሯል፡፡)
ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ድረ ገጽ ወይም ደግሞ በሌሎች የመንግስት ምንጮች ላይ ስለባለቤቶቹ ማንነት የትም ቦታ መረጃ ስለመኖር አለመኖሩ፣ ስለጋራ ባለቤትነት፣ ስለአጋርነት ወይም በኩባንያው ውስጥ ስላሉት ባለድርሻ አካላት ሁኔታ የሚገልጽ ምንም ነገር የለም፡፡
ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ባለቤቶች ማንነት ሆን ተብሎ እና ፍጹም በሆነ መልኩ በሚስጥር እንዲያዝ እና እንዳይታወቅ ተደርጓል፡፡
እኮ ለምን?
ከኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጋር እውቅና ያላቸውን ግለሰቦች በግል እና በመንግስት ዘርፎች ስለ ክፍያፋይናንሻልቴክኖሎጂ ቢጠየቅ ማንም የሚያውቅ ሰው የለም ፡፡
በኢትዮጵያ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጁው ዘርፍ  ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ እነማን ባለቤቶች፣ ባለድርሻ አካሎች፣ አጋሮች፣ ወዘተ እንደሆኑ አይታወቅም፡፡ በክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ውስጥ እነማን ታቅፈው እንደሚገኙ ለይቶ ለማወቅ ያለመቻሉ ጉዳይ ግልጽ አይደለም!
ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ በእራሱ ድረ ገጽ በደርዘን ስለሚቆጠሩት “ለሁሉ ማዕከሎች” ከፍ ከፍ እያደረገ ይናገራል፣ ሆኖምግን ዋና መስሪያ ቤት እንደሌለው መዝግቧል፡፡
ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ድረ ገጽ የግንኙነት መስመር ክፍያ ለዋና መስሪያ ቤቶች የመዘገበው አድራሻ የለም፡፡ ይህም በርካታ ደንበኞች አሉኝ እያለ ለሚናገር ድርጅት እና ከመንግስት ጋር ስላለው አጋርነት ጉራ እየቸረቸረ ላለ ድርጅት እንግዳ የሆነ ነገር ነው፡፡ እንደመገናኛ ነጥብ የፖስታ አድርሻ እና የኢሜይል አድራሻውን ብቻ መዝግቧል፡፡ (አንዴ ሙስና ሙስና ይገማል ይጠረናል!)
በአጠቃላይ 1.92 ቢሊዮን ብር ገቢ የሚያስገኝ ኩባንያ info@email አድራሻ ብቻ የሚገናኝ መሆኑሲታሰብጭንቅላትን የሚበጠብጥ ነገር ነው፡፡
ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ በእያንዳንዱ ወር 2..1 ሚሊዮን ግብይቶችን ከ1.1 ሚሊዮን ከፋይ ደንበኞች ጋር እንደሚያካሂድ ግልጽ አድርጓል፡፡ እንደዚሁም 450 እና ከዚያ በላይ ሰራተኞችን እንደሚቀጥር እና በ31 ለሁሉ ማዕከሎች በቅርቡም 26 እንደሚጨመሩ ዕቅድ በመያዝ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ኩባንያው በፕሮጀከቱ ማጠናቀቂያ 1.92 ቢሊዮን ብር እንደሚያስገኝ ይጠብቃል፡፡
ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በድረ ገጹ ላይ የእርሱ ባለቤቶች የአስር ዓመታትልምድንያካባቱ IT ባለሙያዎች እንደሆኑ ጉራ አሰምቷል፡፡
እንደዚህ ባለ ሁኔታ ጉራ እየተቸረቸረባቸው ያሉ የክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እነማን ናቸው? ለመሆኑ ስም አላቸው? ምናልባትም ቅጽል ስም? ተቀጥላ ስሞችስ? ሌላም ነገር? በእውን ህልውና አላቸውን?
የአስርት ዓመታት ልምድ አላቸው እየተባለ ስለሚነገርላቸው የIT ባለሙያ ባለቤቶች ምንም የሚታወቅ ነገር የለም!በድረገጾቻቸው ላይ ስለእነርሱ ማንነት ድበቅ ስራ የሚሰሩ ከሆነ ሊደብቁት የሚፈልጉት አንድ ነገር አለ ማለትነውን?
በግልጽ ለመነጋገር ባለፉት ቀናት የክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂን ባለቤቶች ማንነት ለማወቅ ከፍተኛ የሆነ ምርመራ የተደረገ ቢሆንም ለማረጋገጥ አልተቻለም ወይም ደግሞ ከኩባንያው በስተጀርባ ያሉትን መስራች ባለቤቶች ወይም ግለሰቦች ማወቅ አልተቻለም፡፡ ለማወቅ ዕድሉ ያላቸው እንኳ ስለክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ባለቤቶች፣ አጋሮች እና ባለድርሻ አካላት የሚያውቁት ምንም ዓይነት ነገር የለም፡፡
እዚህ  አንድ አፍታ ቆም በሉምን እንዳሰባችሁ አውቃለሁ!
ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ በባለቤትነቶች፣ በአጋርነቶች እና በባለድርሻ አካላት ማንነት ላይ ጭጋጋማ ሚስጥራዊነት እና ጠቅላላ የሆነ ድብቅነት የሚታይበት ሁኔታ የመኖሩ ምክንያት ሊባል ይቻል ይሆናል፣ እኔ ግን የሸፍጥ የይስሙላየዝንጀሮየቢዝነስ ማችበርበር ስራ አለ ብዬ አላልኩም !
እባካችሁ በኮምፒውተር መክፈቻ ቁልፎቼ ላይ ቃላትን አታስቀምጡልኝ!
ይህንን ጉዳይ ግልጽ ላድርገው!
ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በዘ-ህወሀት አባላት፣ ደጋፊዎች እና በታማኝ ግብረ አበር ሎሌዎች የተያዘ፣ የሚንቀሳቀስ እና የሚመራ ነው እያልኩ አይደለም፡፡
የዘ-ህወሀት አለቆች ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂን በእርግጠኝነት በባለቤትነት በመያዝ ኩባንያውን ልክ የኢህአዴግን ፓርቲ ለዘ-ህህወሀት ጭንብልነት እንደሚጠቀሙበት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ይህንን ኩባንያም በጭንብልነት እየተጠቀሙበት ነውእያልኩ አይደለም፡፡
የዘ-ህወሀት አለቆች ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂን በአጋርነት በድብቅ በመያዝ እየተጠቀሙበት ነው እያልኩአይደለም፡፡
ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ኩባንያ ባለቤቶች (ማንም ይሁኑ ማን) ከትርፋማው ስምምነት ትርፍን በመዛቅ ወይም ደግሞ እንደዚህ ያለውን የማትነጥፍ ላም ስምምነት ከዘ-ህወሀት ጋር በመፈጸም ወይም ደግሞ ከታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች እና ከሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ገንዘብን እያለቡ ለዘ-ህወሀት ክፍያ ይፈጽማሉ እያልኩ አይደለም፡፡
በክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ባለቤቶች፣ በአጋሮች እና በባለድርሻ አካላት ዙሪያ ያለው ሚስጥራዊነት እና ድብቅነት ማለት ማንም ማየት የሚችል ዓይን ያለው ሰው ሁሉ ህወሀት በክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ላይ ያለውን የእጅ አሻራ እና የእግር ኮቴውን በግልጽ ይመለከታል እያልኩ አይደለም፡፡
ዘ-ህወሀት ሁሉንም ዓይነት የንግድ እንቅስቃሴዎች እና የሸፍጥ ስራዎች ለማካሄድ ቀደም ሲል እንደ ማረት/EFFORT የመሳሰሉ ግንባር ድርጅቶችን ይጠቀም እንደነበር እና አሁን ደግሞ ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂንበተለመደው መንገድ እተጠቀመበት ነው እያልኩ አይደለም፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ ናቸው እያልኩ አይደለም፡፡ ስለሆነም ቃላትን በአፌ ላይ ወይም ደግሞ የበለጠ ግልጽ ለማድረግ በኮምፒውተር መክፈቻ ቁልፎቼ ላይ አታስቀምጡልኝ፡፡
እኔ እንደዚህ አላልኩም፡ ለልበ  እርግ ብ ነኝ!
በአጠቃላይ እያልኩ ያለሁት እንዲህ የሚል ቀላል ነገር ነው፡ “ብዙ ውጣ ውረድ ሳይደረግበት በቀላሉ ህገወጥ ገንዘብ እንደ አሸዋ የሚዛቅበትን ግዙፍ የፋይናንስ ተቋም እና 1.2 ቢሊዮን ብር የማመንጨት አቅም ያለውን ድርጅት ባለቤቶች፣ አጋሮች እና ባለድርሻ አካሎችን ማንነት መሰወር እና መደበቅ ለእኔ ሊታመን እና ሊታሰብ የማይችል አስደናቂ ነገር ነው፡፡“
ለኢትዮጵያ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች መናገር የምፈልገው እንዲህ የሚል አንድ ነገር ብቻ ነው፡ ገንዘቡን ተከተሉ!የክፍያፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ባለቤቶች ማን መሆናቸዉን ስታውቁ ለዘህዋሃት የሚታለቡ ላሞች እና ለዘ-ህወሀት የወርቅ እንቁላል የሚጥሉትን ዳክየዎች አንዴት አንደሆናችሁ ታውቃላቸሁ፡፡
በክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ   ውስጥ የዘ-ህወሀትን ሚስጥራዊ የባለቤትነት ይዞታ ለማወቅ በዘ-ህወሀት የይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ቀርባችሁ ትግል አድርጉ፡፡
ፍትሕን እንደማታገኙ እርግጠኞች ብትሆኑም ዝንጀሮዎችን በዝንጀሮው ፍርድ ቤት በመገኘት ላብ በላብ አድርጓቸው፡፡
አራተኛ፡ የዘ-ህወሀት አዲሱ የትራፊክ ሕግ  ለዘ-ህወሀት የትራፊክ ፖሊሶች ነፋስ አመጣሽ ከሰማይ የወረደ መና ነው፡፡
አዲሱ የትራፊክ ሕግ በሙስና ስለተዘፈቁት የዘ-ህወሀት የትራፊክ ፖሊሶች ሾፌሮችን በማስፈራራት ስለሚዘርፉት ጉቦ ምንም ያለው ነገር የለም፡፡ የዘ-ህወሀት የትራፊክ ፖሊሶች በሕጉ መውጣት ምክንያት ለሀጫቸውን እያዝረበረቡ እና የእጆቻቸውን መዳፎች እያፋተጉ እንደሚሽከመከሙ ጅቦች በመፈንደቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮችን ለማጥቃት የመቆየት እንኳ ትዕግስቱ የላቸውም፡፡ አዲሱ የትራፊክ ሕግ የታክሲ ሾፌሮች በትራፊክ ፖሊሶች አንደ ዱር አራዊት የሚታደኑበትንመድረክ ይከፍታል፡፡
የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ በዘ-ህወሀት የፖሊስ ሙስና ዝቅጠት ላይ ስላወጣው መረጃ እስቲ እንመልከት፡፡
የዓለም ባንክ እ.ኤ.አ በ2012 “በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር“ በሚል ርዕስ ካወጣው የሙስና ጥናት ዘገባ ውስጥ ከገጽ 214 – 215 በግልጽ እንደተመለከተው የዘ-ህወሀት ፖሊሶች እየፈጸሟቸው ያሉትን የሙስና ልምዶች በዝርዝር አስቀምጧል፡፡
የጥናት ሰነድ ዘገባው የዘ-ህወሀት ፖሊሶች የተዘፈቁባቸውን የሙስና ልምዶች ዝርዝር መዝግቦ ይፋ አድርጓል፡፡
በዓለም ባንክ የጥናት ሰነድ ዘገባ ውስጥ ከቀረቡት በደርዘን ከሚቆጠሩት የሙስና ልምዶች መካከል የሚከተሉት ይካተቱበታል፡
  • በትራፊክ ፖሊሶች የሚወሰድ ጉቦ፣
  • ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ መጠቀም ወይም ደግሞ ከመጠን ያለፈ ኃይልን መጠቀም- አብዛኛውን ጊዜ ሙስና ነው ባይባልም አንዳንድ ጊዜ በማስፈራራት በሀሰት በቁጥጥር ስር ማዋል ወይም ደግሞ የሀሰት ማስረጃ ማቅረብ፣
  • ማስረጃዎችን ለማስቀየር ጉቦ መስጠት፣
  • ምስክሮች እንዳይመሰክሩ ማስፈራራት እና ጉቦ መስጠት ወይም ደግሞ ከሕጋዊ እርምጃ አንጻር የፖሊስ የስራ ጓደኝነትን ለመርዳት ጥረት ማድረግ፣
  • ዋጋ ያለው ሆኖ ሲገኝ ማስረጃን መስረቅ፣
  • ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስራ ላለማቆየት ወይም ደግሞ በቁጥጥር ስር አድርጎ ለማቆየት ጉቦ መቀበል- አንዳንድ ተጠርጣሪዎች እስከ ሰኞ ድረስ በቁጥጥር ስር ሆነው እንዲቆዩ የመጠየቅ ሁኔታ እና ሳምንቱን ሙሉ በእስር ቤት እንዳይቆዩ ወይም ደግሞ ዋስትና በማስያዝ ሙሉ በሙሉ እንዲለቀቁ የማድረግ.
  • ጉቦ በመቀበል፣
ሀ) ተከላካዩ በክስ መስሚያው ዕለት እንዳይገኝ/ትገኝ ማድረግ ወይም ደግሞ
ለ) በምስክርነት መስሚያው ዕለት ምስክሮች እንዳይቀርቡ ማድረግ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የዘ-ህወሀት ፖሊሶች የማፊያ ዓይነት ስራዎችንም ይሰራሉ፡፡ በማፊያ ቤተሰብ ውስጥ ካለ “ወታደር” ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ (አስገዳጆች፣ ጡንቸኞች፣ የዘ-ህወሀትን ቆሻሻ ስራ የሚሰሩ እና በሙያው ጥልቅ እውቀት የሌላቸው ግልቦች ናቸው)፡፡
ግልጽ በሆነ መልኩ የልመና ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ የኢትዮጵያ ሞተረኞች ለዘ-ህወሀት የትራፊክ ፖሊሶች ጉቦ የሰጡበት ግላዊ የሆነ የስልክ ቪዲዮዎች በዓይኔ አይቻለሁ፡፡ በማንኛውም አጋጣሚ ሁሉ የዘ-ህወሀት ፖሊስ ጉቦ የሚጠይቅበት በደርዘን የሚቆጠሩ ማስረጃዎች አሉኝ፡፡ በአንድ ልዩ አጋጣሚ አዲስ አበባን በመጎብኘት ላይ የነበረ ሞተረኛ የአውሮፕላን በረራ ዕድሉን ላለማጣት ሲል 500 ብር ጎቦ ከፍሏል፡፡ ያ ሞተረኛ በኋላ በጓደኞቹ መሳቂያ እና መሳለቂያ ሆኗል፣ ምክንያቱም ሞተረኛው ሙሉ በሙሉ ተታሏል፡፡ 50 ብር ብቻ በመስጠት ከችግሩ መገላገል ይችል ነበር፡፡ በጉቦ ተቀባዩ ዓይን አውጣ ጉቦኛ ፖሊስ በደረሰበት ውርደት ምክንያት ሞተረኛው ኢትዮጵያን ዞር ብሎ ላለማየት እና ላለመመለስ ምሎ ተገዝቷል፡፡ የትራፊክ ፖሊሱ 500ውን ብር ከገሸለጠች  በኋላ የዋቱሲን ዳንስ እንደምታስነካው  እርግጠኛ ነኝ፡፡ ከማይጠረጠረው ሞተረኛ፡፡ (ትራፊክ ፖሊሷ ፋስካዋ ነበር )
ግሎባል ኢንቴግሪቲ እንደሚባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት ዘገባ “የኢትዮጵያ መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ትክክል ያልሆነ የአሽከርካሪዎች መንጃ ፈቃድን በመስጠት እና ዓመታዊ የተሸከርካሪዎችን ምርመራ ከማድረግ ጋር በተያያዘ መልኩ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት በሙስና ከተዘፈቁ መንግስታዊ ተቋማት መካከል አንዱ ነው፡፡ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣንም (ፌትባ) እንደዚሁ በርካታ ለሙስና በር የሚከፍቱ አሰራሮችን በመተግበር ለሙስና የተጋለጠ ድርጅት ነው“ ብሏል፡፡
የውጭ ሀገር ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያፈስሱትን መዋዕለ ንዋይ እ.ኤ.አ ጥር 2014 በተደረገው ጥናት መሰረት የዘ-ህወሀት ትራፊክ ፖሊሶች ከሌሎች መስሪያ ቤቶች ሰራተኞች የበለጠ ጉቦ በመጠየቅ የቀዳሚነቱን ስፍራ እንደሚይዙ ይፋ አድርጓል፡፡
አዲሱ የትራፊክ ደንብ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮችን ሙልጭ አድርጎ ለመጋጥ የተሸረበ የሸፍጥ ዕቅድ ነው፡፡ የትራፊክ ሕግ በሚል ማታለያ የታክሲ ሾፌሮች ላይ ለመቆለል የታሰበ የግብር እዳ ነው፡፡
ክፈል እና እንጫወት ዓይነት ሸፍጥ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ከዘ-ህወሀት የታክሲ ማሽከርከር ጨዋታ ጋር ለመጫወት ከፈለጉ ላለቆቻቸው በሚያስተላልፉ የትራፊክ ፖሊሶች አማካይነት ለዘ-ህወሀት ህገ ወጥ ገንዘብ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡
የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ለመክፈል እና ለመጫወት የማይፈልጉ ከሆነ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ፡፡
የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች የታክሲ ማሽከርከር ጨዋታውን ለመጫወት መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
ይኸ ሁሉ ነገር ለታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ምን ማለት ነው?
የዘ-ህወሀት የትራፊክ ፖሊስ በኢትዮጵያ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ላይ የሞት እና የሽረት ያህል ኃይል እና ስልጣን አለው፡፡
አንድ በሙስና የበከተ የዘ-ህወሀት የትራፊክ ፖሊስ ማንኛውንም የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌር አቅም ለማሽመድመድ ሲፈልግ ከእርሱ የሙስና ተባባሪ አጋሮቹ እና አለቆቹ ጋር በማበር በጥቂት ቀናት ውስጥ የማባረሪያ የሸፍጥ ሰነዶችን በማዘጋት ከታክሲ አሽከርካሪነት ሙያው ለዘላለሙ ለማሰናበት ይችላል፡፡ እንግዲህ አዲሱ የትራፊክ ሕግ (ካልተሻረ በስተቀር) ሊሰራው የሚችለው ነገር ይህንን ነው፡፡
የዘ-ህወሀት አዲሱ የትራፊክ ሕግ ከጅ አፍ በሚታገሉ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ላይ የትራፊክ ፖሊሶችን ትንሹ አምላክ የሚያደርግ ነው፡፡
ይኸ ሊካድ የማይችል ሀቅ ነው!
የፌዴራል ትራንስፖርት ቢሮ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች የስራ ማቆም አድማ በመቱበት ዕለት የአዲሱ ደንብ ተግባራዊነት በሶስት ወራት ተራዝሟል የሚል መግለጫ ሰጠ፡፡ ወቼ ጉድ፣ እንዴት ተቀለደ!
የፌዴራል የፈለገውን ማንም ተብሎ ቢጠራ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላንን ጨምሮ ሞቷል፡፡ በእርግጥ መቸውንም ቢሆን ሊኖር አይቸልም፡፡ ሆኖም ግን መቸውንም ቢሆን የሚኖር ባይሆንም ሞቷል፡፡ ቀጣፊዎች!
እንግዲህ ከዘ-ህወሀት ጋር ያለው ችግር ይኸ ነው፡፡ እነዚህ ወሮበላ ዘራፊ ሸፍጠኞች እነርሱ በጣም ብልጦች እና ሌላው ምንም የማያውቅ ደደብ እንደሆነ አድርገው በመቁጠር ልያታለሉ ይሞክራሉ፡፡
ዘ-ህወሀት ከ90፣ ከ180 ቀናት ወይም ከሁለት ዓመታት በኋላ (እስከዚያ እድሜውን የሚሰጣቸው ከሆነ) በአዲሱአሮጌየታክሲ አሽከርካሪ ሕግ እንደገና ብቅ ይላሉ፡፡
ዘ-ህወሀት ከ90፣ ከ180 ቀናት ወይም ከሁለት ዓመታት በኋላ (እስከዚያ እድሜውን የሚሰጣቸው ከሆነ) በአዲሱ አሮጌ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንደገና ብቅ ይላሉ፡፡
የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ማድረግ ያለባቸው ምንድን ነው?
ዘ-ህወሀት የስልጣን ህልውናውን ለማቆየት ሲል በመንገዱ ላይ የሚያገኘውን ማንኛውንም ነገር ሁሉ የሚጨፈልቅ ደም የሚመጥ  ኃይል ነው፡፡
የታክሲ ማሽከርከር ሙያ በኢትዮጵያ ውስጥ በተነጻጻሪ መልኩም ቢሆን ትንንሽ የንግድ ቡድኖች በኢኮኖሚ ተደራጅተው የሚሰሩበት ብቸኛ ነጻነት ያለበት የኢኮኖሚ ዘርፍ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ እንደምንመለከተው ዘ-ህወሀት የታክሲ ማሽከርከር ሙያውን ለማውደም ማንኛውንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ አይልም፡፡
የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮችን የመብት ማስከበር ትግል ለማኮላሸት በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት የትግሉን መሪዎች እናየአደራጆችንስም ዝርዝር በመልቀም ጥቃት ለማድረስ እና የበቀል እርምጃ ለመውሰድ እየመረመረው እንደሆነእርግጠኛ ነኝ፡፡
ዘ-ህወሀት በታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ላይ የከፋፍልህ ግዛን መርህ ለመተግበር ጥረት በማድረግ ሙከራ ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ የስራ ማቆም አድማውን መሪዎች በገንዘብ ለመግዛት ሙከራ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ የስራ ማቆም አድማውን መሪዎች እና እያንዳንዱን የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌር ያስፈራራሉ፡፡ በታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች መካከል ስምምነት እንዳይኖር እና ክፍፍል እንዲፈጠር አጠንክረው ይሰራሉ፡፡ በጎሳ እና በኃይማኖት እንዲከፋፈሉ ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ የሽብር ተጠርጣሪዎች በማለት ወደ ማጎሪያው እስር ቤት እንዲገቡ ያደርጋሉ፡፡ አሸባሪዎች ብለው በመፈረጅ ጉዳያቸው ወደ ይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ቀርቦ ማለቂያ በሌለው የቅጥፈት የተንዛዛ የጊዜ ቀጠሮ በማጉላላት ሊበቀሏቸው እንደሚችሉ ያስፈራራሉ፡፡ በጓደኞቻቻው ላይ ሰላይ እና መረጃ አነፍናፊዎች ሆነው ለእነርሱ ቆሻሻ ዓላማ እንዲያገለግሉ ለማድረግ ይሞክራሉ፡፡ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮችን የማድረግ ብቃት፣ ጽናት እና የትግል መንፈስ ለመግደል ማንኛውንም ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡
ያም ሆነ ይህ እንዲህ በማለት ትንበያ እሰጣለሁ፣ ዘ-ህወሀት ይወድቃል፣ ይወድቃል፣ ይወድቃል…
ሆኖም ግን የኢትዮጵያ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች እራስን በማተለል ደህነነት ከዋናው ዓላማቸው ለአፍታም ቢሆን ጸጥ ማለት የለባቸውም፡፡ አዲሱ የትራፊክ ሕግ 90 ቀናት ተራዝሟል ለሚለው ማታለያ እና ማደናገሪያ ጆሮሊሰጡ አይገባም፡፡በምንም ዓይነት መልኩ ለዘህወሀት ቃል ፍጹም፣ ፍጹም፣ ፍጹም እምነት መስጠትየለባቸውም፡፡ TPLF በሚለው ቃል ውስጥ LF የሚሉት ፊደሎች የውሸት ፋብሪካ/Lie factory የሚለውን ይወክላሉ፡፡
ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያ የታክሲ አሽከርካሪዎች የኢኮኖሚ ህልውናቸው መረጋገጥ ለዘላለማዊ ህይወታቸው ዋስትና መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
ዘ-ህወሀት ሌላ የትራፊክ ሕግ በማውጣት ጥሩ ስም ይሰጥ እና ወደ ሾፌሮቹ እንደገና ይመለሳል፣ አስፈላጊ ሆኖ ባገኘው ጊዜ ሁሉ እንደገና ለበርካታ ጊዚያት ይመላለሳል፡፡ ይኸ ነገር ጸሐይ ነገ ትወጣለች የማለትን ያህል እርግጠኛ  ነገር ነው፡፡
የኢትዮጵያ ታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ዘ-ህወሀት ደም መጣጭ አጋንንት ድርጅት መሆኑን ማወቅ እና እምነት ሊያድርባቸው ይገባል፡፡
በስልጣን ለመቆየት ስልዘህ ዋሃት በአካባቢው ያለውን ማንኛውንም ኢኮኖሚያዊ ደም ሁሉ ይመጥጣል፣ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮችን የትግል ደም ጭምር፡፡
ማረት (ኤፎርት)  የዘ-ህወሀት ደም መጣጭ የኢኮኖሚ አገዛዝ ልብ እና መንፈስ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች እ.ኤ.አ በ1776 የአሜሪካንን ነጻነት የሚያውጀውን አዋጅ ከመፈረማቸው በፊት የአንድ አሜሪካውያንን መስራች የተናገሩትን ቃል ማስታወስ ይኖርባቸዋል፡፡ ቤንጃሚን ፍራንክሊን በዚያን ጊዜ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ሁላችንም እጅ ለእጅ መያያዝ አለብን፣ አለዚያም በተናጠል እየተያዝን እንሰቀላለን፡፡“
ከዓመት በኋላ በፓሪስ ፍራንክሊን እንዲሀ በማለት ጻፋ፣ “የእኛ ትግል ለሰው ልጆች ሁሉ በሰላም መኖር መረጋገጥ ትግል እንደሆነ የተለመደ እይታ ነው፣ እናም የእራሳችንን እየተካለከልን ለእነርሱ ነጻነት መዋጋት አለብን፡፡“
የኢትዮጵያ ታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች እጅ ለእጅ ተያይዘው በመጓዝ ሊበጠስ የማይችል ሰንሰለት መስራት እና ልብ፣ አእምሮ እና መንፈስ የጋራ ጥቅሞችን ከጨቋኝ አምባገነን ወሮበላ ዘራፊዎች ለማስከበር በጋራ በጽናት አንድ ሆነው መቆም አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ጨቋኞች እና ወሮበላ ዘራፊዎች እያንዳንዱን ሾፌር እየነጠሉ ይሰቅሉታል፡፡
የኢትዮጵያ ታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች የእነርሱ ጉዳይ የእነርሱ ብቻ አይደለም፣ ጉዳዩ የኢትዮጵያውያን በሙሉ ጭምር እንደሆነ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለነጻነታቸው በሚዋጉበት ጊዜ ለኢትዮጵያውያን ነጻነቶች ሁሉ እየተዋጉ መሆኑ ሊጤን ይገባል!
የኢትዮጵያ ታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ጠንካሮች እና ህብረት የሌላቸው ከሆኑ ትልቁ መጥፎ አስቀያሚ ተኩላ አውሬ ዘ-ህወሀት እየተባለ የሚጠራው በእያንዳንዷ መንገድ ማዕዘን ላይ በመቆም እያንዳንዳቸውን ተራ በተራ ለመዋጥ ለሀጩን እያዝረበረበ በመቋመጥ ይጠብቃችኋል፡፡
የኢትዮጵያ ታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች፡ አንድነት ኃይል ነው፡፡ አንድነት በተፈጠረ ቁጥር ሁልጊዜ ድልን መቀዳጀትአለ
የኢትዮጵያ ታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ከተባበሩ ፍጹም ሊሸነፉ አይችልምበርቱ እንዳትሸነፉሌሊቱ እየነጋ ነው !  
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
የካቲት 29 ቀን 2008 .