Saturday, 2 January 2016

የዕምነት ቤቶች ምን እየአደረጉ ናቸው?

ቁምላችው መኩሪያ
የዕምነት አባቶች በዕኩይ መሪዎች ምክንያት ፍትህ ሲጓደል፤ ድሀ ሲበደል እና መንገጋው ሲበትን ብሎም በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ፍጡር ሲገድል፤ ሲሰደድ እና በረሃብ አለንጋ ሲገረፍ በዳዩን የመገሠፅ የሞራልም ሆነ የዕምነት ግዴታ አለባቸው።For Ethiopian muslims and chrstians
አሁን ግን በዕምነት ቤቶች አከባቢ ይህ ሲደረግ አይታይም። ይባስ ብሎም ስለ ተበደለ ህዝብ መናገር ፖላቲካ ነው ወይም ከዕምነት አሥተምህሮት ውጪ ነው አሊያም ሁለቱንም ናቸው በማለት ውኃ የማይቆጥር ምክንያቶች ሲደረድሩይ ይደመጠሉ።
በትልቁ መጽሐፈችን በመጽሐፍ ቅዱስ ግን (እርግጠኛ ነኝ በቅዱስ ቁራኑም ቢሆን ሰለ ፍትህ እና ስለ ሰው ልጆች ደህንነት ሳያወሳ አቀይርም ብዬ አምናለሁ) የሚከተሉት ተፅፈዋል በዕምነተት ቤቶችም ተሰብካዋል።
ሙሴ፡ ፋርዖንን ገስጿል ህዝብንም ከባርነት አውጥቷል።
ነብዩ ናታን፡ ንጉሥ ደዊትን ግስጾል፡ ደዊትም ዕንባ አውጥቶ አልቅሷል።
ቅዱስ ዮሐንስ፡ ሔሮዶስን ገሥጿል።
የመይሞተው እየሱስ ክርስቶስ የሞተው የሰውን ልጅ ከባርነት እና ከመካራ ለመታደግ ነው። ምሣሌነቱም የሰው ልጅ በአርዕየ ክርስቶሰ ለተፈጠረው ወንድሙ በመካራ ቀን ከጎኑ ቁሞ መስዋዕት መክፈል እንደአለበት ለማሳየት ነው።
አባታችን ብፁ ወቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ መንጋውን ሊበትን የመጠን ወራሪ በጎቼን አትንካብኝ ብለው ደረታቸውን ለአሩር ሰተዋል። አሁን ግን አባቶቻችን ያቆሙላቸው ሀውልት የትም ሲጣል ዝምታን መርጠናል።
አባቶቼ ሆይ!!፦ እንደ እናተ አሰተሳሰብ ቢሆን እኒህ ሁሉ ከለይ የተዘረዘሩት ፖላቲካኞች ናቸው ማለት ነው? የሠሩት ሥራስ ከዕምነት አሥተምህሮ ውጪ ነው ማለት ነው? ለእናንተ ፖላቲካ ማለት ምን ማለት ይሆን? ፖላቲካኞች እንኳ እያሉ ያሉት፦ ፍትህ ተጓደለ፡ ድሃ ተበደለ፡ ሀገር በዘውግ ተሸነሸነ፡ ህዝብ በራሃብ አለንጋ ተገረፈ። ወገን ተሰደደ ነው። ይህ የዕምነት ቤቶች ሥራ ካልሆነ ሥራችሁ ንግድ እና ውትድርና ነው ማለት ነው?
የዕምነት አስተምህሮትስ ቢሆን ጥሬ ቃሉ እንኳ የሚለው ድሓ ሲበደል ጩህ፡ ባልንጃራህን እንደ ራስህ ውደድ ነው። ታዲያ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንዲህ ስታናባ ህዝቦቾ በጥይት እና በራሃብ ሲቆሉ ካላዘነችሁ ችግራቸውን ካልተናገረችሁ እረኝነቱ እና ባልንጀራን እንድ ራስ መውደድ ምኑ ላይ ነው? በዚህ አጋጣሚ በስደት ለይ ያለውን የኢትዮጵያ ህጋዊ ሲናዶስ እና ዋሺንግተን ዲሲ ያለውን ፈርስት ሂጅራን የኢትዮጵያ እስልምና ምህበርን አመሰግናለሁ። በሥሩ የሚገኙት አድባራት እና ካህናት እንዲሁም አጥባቂ ምዕመናን ግን ዝምታቸውን መሥበር አለባቸው እላለሁ። የእስልምናውም ቢሆን እንዲሁ።
በርግጥ ሀገርን በየፊናው የሚያገለግሉ አራት በአዘውንት ዘንድ “ቀአነተ” በሚል ምህፀረ ቃል የሚተውቁ መሰረተዊ አውታሮች ማለትም” ቀዳሽ(ኃይማኖት)፡ አራሽ(አምራች)፡ ነጋሽ(አስታዳዳሪ)፡ ተኮሽ(ወተደር)” የስፈልጓታል። ይህ ማለት ግን መነኩሴውም ሆኑ ጰጰሱ፡ ሼኪውም ሆኑ ቄሱ፡ ዘመሪውም ሆኑ ፓስተሩ ሀጂውም ሆነ ደብታራው በፖላቲካ እና በእስተምህሮ ቆፈን ተሸብበው በዝምታ ይቆዝሙ ማለት አይደለም። ኃይማኖት መልኩን ሲቀይር ሀገርም ደብዛው ሲጠፋ ህሊናቸውን ሊጎሽማቸው ይገባል።
ሌላው አሳዛኙ “ሀገራችን በሰማይ ነው ስለ ምድር አታስቡ” የሚባለው መፈክር ነው። በርግጥ ስለ ሰማይ ቤታችን ማሰቡ ጥሩ ነው ። ዕውነተኝውን የሰማይ ቤት የምናገኘው እኮ በምድር ለይ ሆነን በሰራነው በጎ ሥራ ነው። በምድር ለይ ሆነን የወገንን ሥቃይ ለመታደግ ላበረከትነው ለቅሶ ነው። በምድር ለይ ሆነን ወገንን ከባርነት እና ከሞት ለመታደግ ላደረግነው መልካም ሥራ ነው።
ይህንን ምድር ሆነን ካልሰራን የትኛው ሰማይ ነው ሀገራችን የሚሆነው?
ያ የሰማዩ መንግሥት(ቦታ) እኳ እንደ ወየኔ መንግሥት በዘመድ ወይም በአገር ልጅነት ወይም እንደ ኮንደሚኒያም በማጎብደድ አይተደልም። እባካችሁ ወገኖቼ ዕምነትን በትክክል እንተርጉም።
ወገኖቼ ሆይ!!፦ ሀገር በመንታ መንገድ ላይ ናት። ወያኔ በፈጠርው ጦስ ወገን በጥይት እና በራሃብ አላንጋ እየተገረፈ ነው። መሬት እዬተቆረሰ ለሱዳን፤ ለሳውዲ ዓረቢያ፧ ለቻይና፤ ለህንድ፤ ለግብፅ፤ ለኩዬት እና ለቤልጂየም እየታደለ ነው። ሀገሬቷን የዘር ፖላቲካ እያናወጣት ነው። ኢትዮጵያን የመሰለች ትልቅ ሀገር ወደብ አልባ ሆናለች። ውርደትና ረሃብ መለያችን ሆነዋል። ዝም ብለን ካየናቸው እነዚህ የጣሊያን ቡችሎች ሀገራችንን በጥቂት ጊዜ ውስጥ ያጠፏታል። ስሟንም ይቀይሯታል።
የትግራይ ወጣቶች ሆይ!! ከሌሎች ኢትዮጵያውኖች ጎን ቁሙ። ራሳችሁን ከታሪክ ተጠያቂነት አድኑ። የትግራይ አባት እና እናቶች ሆይ!! ልጆቻችሁን ሀይ በሏቸው። ከአብራካችሁ የወጡ ልጆቻችሁ ሀገር አያጥፉ፡ ወገንም እይጨርሱ ነው።
አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቅ!!!
“ኢትዮጵያ ታበፅህ እደዊሃ ሀበ ኢግዚአብሔር”!!!!!!

አቶ በቀለ ነጋ ተደበደቡ — በቁም እስር ላይም ይገኛሉ

አቶ በቀለ ነጋ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሀፊ ሁኔታውን እንዲህ በማለት ገልጸውታል፣
———————–
ወዳጆቼ
ዛሬ ማለዳ ወደ ስራ እያመራሁ ሲቪል የለበሱ 4 ሰዎች ስሜን ጠርተው ሰላምታ ካቀረቡልኝ በኋላ ፖሊሶች መሆናቸውን ነግረውኝ እኔን ካስቆሙበት ቦታ አጠገብ ወደሚገኘው መኪናቸው እንድገባ ጠየቁኝ።ፈቃደኛ አለመሆኔን ስነግራቸውም እጆቼን ይዘው እየጎተቱኝ በመኪናቸው የኋላ መቀመጫ ላይ እንድቀመጥ አድርገውኝ መንዳት ጀመሩ።
Bekele Nega of Oromo Federalist Congress
አቶ በቀለ ነጋ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሀፊ
መኪናው መንቀሳቀስ እንደጀመረም መማታት ጀመሩ፣ በቀኝና በግራዬ የተቀመጡት ሁለት ሰዎች ሲደበድቡኝ ጋቢና የተቀመጠው ወደኋላ ዞሮ በመሳሪያው ፊቴን ይነካ ነበር።
እየደበደቡኝ ይህንን የሚያደርጉት ማስጠንቀቂያቸውን ችላ ብዬ ለሚዲያ መረጃ በመስጠቴ እንደሆነ ይነግሩኝ ነበር ።ድብደባቸውን እንዳቆሙም መሳሪቸውን እንደደገኑ ስልኬን ወሰዱብኝ ።የሚሉኝን ካላደረግኩም ለእኔና ለቤተሰቦቼ እንደሚመጡ አስፈራርተውኛል።
“ከዛሬ ጀምሮ ከቤትህ ብትወጣ ወይ ሚዲያ ብታናግር በአንተም ሆነ በቤተሰቦችህ ላይ ለሚሆነው ነገር ሃላፊነቱ ያንተ ነው” ብለውኛል።
የእኔ ብቻ ሳይሆን የቤተሰቦቼ ህይወት አደጋ ውስጥ እንደሆነ በመንገርም ከመልቀቃቸው በፊት የሚሉኝን ካላደረኩ እንደሚገሉኝ ዝተውብኛል።
“ከእንግዲህ ወዲህ እናንተን የምናስርበት ቦታ የለንም:: ወይ እንገድልሃለን ወይ በመኪና ገጭተን ፓራላይዝ እናደርግሃለን ”ብለውኛል።
የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ብዙዎች እያቀረቡለት ለሚገኘው አቤቱታ ጆሮውን ደፍኖ ሰላማዊውን ጥያቄ በኃይል ለማፈን እየሰራ በመሆኑ ያለምንም ኃላፊነት ዜጎችን እያሰረ፣እያዋረደና እየገደለ ይገኛል።
በቀለ ገርባ፣ ደጀን ጣፋ፣ አዲሱ ቡላላና ደስታ ዲንቃን ጨምሮ 4.000 የሚደርሱ የፓርቲያችን አባላት በግፍ ታስረዋል።
መንግስትና ሁኔታውን በፀጥታ እየተመለከቱ የሚገኙ አካላት ንፁሃንን ማሰርና መግደል የሚልዮኖችን ህጋዊ ጥያቄ ለማፈን መፍትሔ እንደማይሆንና ኦሮሞውንም ይህ ድርጊት እንደማያስቆመው ይገነባሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
እስከዛው ግን እንደግለሰብና እንደ ኦፌኮ አባልነቴ በሰላማዊ አግባብ የኦሮሞ ህዝብ አንደበት መሆኔን እቀጥላለሁ ።ምክንያቱም ለነፃነትና ለህዝባችን ክብር ስንል በምንከተለው ሰላማዊ ትግል እኔና ሚልዮን ኦሮሞዎች ህይወታችንን ጭምር ለመክፈል ተዘጋጅተናል።
ከአክብሮት ጋር
በቀለ ነጋ
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሀፊ