Saturday 13 December 2014

አገር ውስጥ እየኖሩ መሞት፣ በስደት ጉዞ መሞት፣ በስደት እየኖሩ መሞት! “መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው!”

“መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው!”
ethiopians and their plight

* አገር ውስጥ “ባርነት”፤ ከአገር ተሰድዶ “ባርነት”

ከጥቂት ቀናት በፊት በአገራቸው መኖር ያቃታቸው 70 ኢትዮጵያዊያን ቀይ ባህርን በጀልባ አቋርጠው ወደ የመን ሲያመሩ በደረሰ አደጋ ሁሉም መሞታቸው ተገልጾዋል። ኢህአዴግ እነዚህ በእርግጥ ኢትዮጵያውያን ለመሆናቸው ማስረጃ እንደሌለውና “እያጣራ” መሆኑን በቃል አቀባዩ በኩል ተናግሯል፡፡
በዚህ ዓይነት ሁኔታ ከአገራቸው እየተሰደዱ ለባህር፣ ለአውሬ፣ … የተዳረጉት ወገኖቻችን ብዛት ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ ይህንን ሁሉ አልፈው ወዳሰቡት የደረሱት ደግሞ በስደት የሚኖሩባቸው በተለይ የአረብ አገራት ይህ ነው የማይባል ሰቆቃ ይደርስባቸዋል፡፡ ይህንን ሁሉ የሚሰማው ወገን አሁንም በየኤምባሲው ቪዛ ለማስመታት በተገኘው ቀዳዳ ከአገሩ ለመውጣት ይጥራል፡፡ በዚህ በኩል ያልተሳካለት ድንበር በማቋረጥ አስጨናቂውንና አስፈሪውን ጉዞ ይጀምራል፡፡
“አገር እየለማች” ነው ለሚለው ኢህአዴግ ይህ ምንም ዓይነት ምላሽ የሚሰጥበት ባይሆንም አሁንም “ለጊዜው የምጠብሰው ትልቅ አሣ አለና ጊዜ የለኝም” በማለት መስማት የተሳነው መሆኑን ይናገራል፡፡ አሽቃባጭ ካድሬዎቹም በየማኅበራዊ ድረገጾችና መገናኛ ብዙሃን “መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው” ይሉናል፡፡“አገር እየለማች” ነው ለሚለው ኢህአዴግ ይህ ምንም ዓይነት ምላሽ የሚሰጥበት ባይሆንም አሁንም “ለጊዜው የምጠብሰው ትልቅ አሣ አለና ጊዜ የለኝም” በማለት መስማት የተሳነው መሆኑን ይናገራል፡፡ አሽቃባጭ ካድሬዎቹም በየማኅበራዊ ድረገጾችና መገናኛ ብዙሃን “መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው” ይሉናል፡፡
በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የስደት ህይወት ለመምራት እየወሰኑ የሚሄዱት ወገኖቻችን ከሚያስቡበት አገር ሲደርሱ ስለሚሆነው ሰሞኑን የወጣው የ2014 “የባርነት መለኪያ ዘገባ” በዘመናዊ ባርነት ውስጥ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 390ሺህ እንደሚገመት ተናግሯል፡፡ (የጎረቤት ኬኒያ65ሺህ እንኳን አልደረሰም)
ከአረመኔ የባህር ላይ አስተላላፊዎች ያመለጡት ወይም “በልማት እየተመነደገች” ካለችው አገራቸው ኑሮን ማሸነፍ እያቃታቸው ወደ አረብ አገራት “በቪዛ” የሚወጡት በ“Global Slavery Index” መለኪያ መሠረት ለዘመናዊ ባርነት የሚጋዙ ናቸው፡፡
አገር ውስጥ ያለው “ዘመናዊ ባርያ” ኑሮን ማሸነፍ ያቃተውና የሰው ልጅ ሊሰራው የማይገባውን ሥራ የሚሠራ እንደሆነ ዘገባው ጠቆሟል፡፡ ከገጠር ወደ ከተማ የሚሰደደውና እዚያም በኑሮ ስቃይ ውስጥ የሚገባው ወላጅ ልጆቹን ለጎዳና ተዳዳሪነት፣ ለልመናና ለወሲብ ንግድ አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ወደ ት/ቤት መላክ የሚገባቸው ህጻናት ሊሠሩት ቀርቶ ሊያስቡት የማይገባ እጅግ ዘግናኝና ሰቅጣጭ ሥራዎችን እንዲሰሩ ይገደዳሉ፡፡refugees and their boat
በአፍሪካ ቀዳሚውን ሥፍራ የያዘው የመርካቶ አካባቢ የመሸታና የሴተኛ አዳሪ ቤቶች ክምችት እንደሆነ የጠቆመው ዘገባ የዘመናዊ ባርነቱን ሁኔታ ይዘረዝራል፡፡ በዚህ ሁኔታ ከአገር ውስጥ “ዘመናዊ ባርነት” ያመለጡት ወደ አረብ አገራት “ለውጭ አገር ዘመናዊ ባርነት” ገንዘባቸውን እየከፈሉ ራሳቸውን በፈቃደኝነት ይሰጣሉ፡፡
በዚህ የባርነት ንግድ ያልጠገበው ኢህአዴግ በቅርቡ በሳውዲ የሆነውን የወገን ሰቆቃ ቸል በማለት የተቋተረጠበትን ገቢ እንደገና ለመጀመር “ሕግ እያረቀቀ” መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ባርነቱን በመቀጠል ሽያጩን ለማጧጧፍና ትርፉን ለማጋበስ ረቀቅ ባለ ሁኔታ ዝግጅቱን አድርጓል፡፡ ባለሥልጣናቱም የአረቡን አገራት ጎብኝተው “በባርነት ንግዱ” ላይ ተስማምተው መጥተዋል፡፡ ይህንን “መልካም ዜና” የሰሙት “ተስፈኛ ዘመናዊ ባሪዎችም” ዓይናቸውን ጨፍነው ወደ ጭለማው ለመግባትና ህይወታቸውን ለባርነት አሳልፈው ለመስጠት ሙሉ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ እስከዚያው ለመጠበቅ ያልቻሉትና “ከአገር ውስጥ ዘመናዊ ባርነት” ሞትን የመረጡት አሁንም ድንበር እያቋረጡ ወደ ባህር ይጓዛሉ፡፡
ባለፉት የመጋቢትና የሚያዚያ ወራት ቁጥራቸው ከመቶ የሚያልፍ በተመሳሳይ አደጋ ሰጥመዋል፤ ለቀብር ሳይበቁ በውሃ ተበልተዋል፡፡ ያገራቸው “ህዳሴና ልማት” ሊያኖራቸው ያልቻለው አውሮጳን አልመው እስከዚያው የአረቢያ ምድርን ተስፋ አድርገው በምድርና በባህር የሚሰደዱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ ከመሄድ በቀር የመቀነስ ሁኔታ አይታይበትም፡፡ አውሮጳን ሳያልሙ “ለዘመናዊ ባርነት” ወደ አረቢያ የሚሰደዱት ምንም ተስፋ በሌለበት ሁኔታ እንኳን ከእነርሱ በፊት ሄደው የተሳካላቸውን ሰዎች በማሰብ እነርሱም ከእነዚያ መካከል እንደሚሆኑ በመገመት ጉዞ ያደርጋሉ፡፡ ከደረቁ ምድር ገና ለመሳፈር ሲነሱ ለባህር ወንበዴዎች ገንዘባቸውን ይከፍላሉ፤ ከዚያም ሲያልፍ የአካል ክፍላቸውን እያወጡ ይሸጣሉ፤ እዚያው በኢንፌክሽን ይሞታሉ፤ ከዚህ ያመለጡትና “ባርነትን” ተስፋ ያደረጉት ደረቅ ምድር ሳይደርሱ በባህር ይሰጥማሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ የተረፉት ጥቂቶች ከባህርና ከአጓጓዥ አውሬዎች አምልጠው “ለዘመናዊ ባርነት ብቁ” ይሆናሉ፡፡ በባርነት “ያተረፉትን” ገንዘብ ወዳገራቸው ይልካሉ፤ ያገራቸውን “ኢኮኖሚ በድርብ አኻዝ” ያሳድጋሉ፤ “በልማቱ መስክ” ይሳተፋሉ፤ … “መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው!”

የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና – ተመስገን ደሳለኝ (ከዝዋይ እስር ቤት)

መሐሙድ የሱፍ የተወለደው በ1980ዓ.ም ከሶማሌ ክልል ርእሰ-መዲና ጅጅጋ 500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውዶሀን ከተማ ነው፡፡ ለቤተሰቡ ሰባተኛ ልጅ ሲሆን፤ አምስት እህቶችእና ሦስት ወንድሞች አሉት፡፡ በጅጅጋ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ አስረኛ ክፍል ድረስ መዝለቁቢሳካለትም፤ ከዚህ በላይ ግን ሊቀጥል አልተቻለውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኢትዮጵያመንግስት የደህንነት ሠራተኞች የ1999ዓ.ም የግንቦት ሃያ በዓል በጅጅጋ ከተማ ስታዲዬም በተከበረበት ዕለት፣ የኦጋዴን ነፃአውጪ ግንባር (ኦብነግ) በሰነዘረው የቦንብ ጥቃት ተሳትፈሃል በሚል ለእስር በመዳረጉነው፡፡ ይህንን ተከትሎምከምድራችን አስከፊ ማሰቃያዎች መካከል ግንባር ቀደም በሆነውና የክልሉ ነዋሪ “ጄል-አዳብ” (የገሃነም እስር ቤት) እያለ በሚጠራው ማጎሪያ ውስጥ እጅግ በጣም የከፋ ምድራዊ መከራ እንደተቀበለሀዘን በተጫነው ድምፅ ይናገራል፡፡ በሠውነቱ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እንደ ፍም ቀልተው የሚታዩት ጠባሳዎቹም ያሳለፈውንሥቃይ አፍ አውጥተው ይመሰክራሉ፡፡ ለአራት ወራት ያህል አንድ ክፍል ውስጥ ለብቻው ተቆልፎበት፤ ሃያ አራት ሠዓታትሙሉ እጆቹ በካቴና ተቀፍድደው፣በቀን ከአምስት ጊዜ በላይ ለምርመራ እየተጠራ ያለዕረፍት ከባድ ስቅየት (ቶርቸር)ሲፈፀምበት ቆይቷል:፡ በመጨረሻም ለአንዲትም ቀን የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጥ፣ ለኦብነግ አባላት አንድ ፓኬት ሲጋራሲያቀብል እጀ-ከፈንጅ ተይዟል በሚል ክስ የጅጅጋ ዞን ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን እዛው እስር ቤት ሆኖከኢትዮጵያ ሬዲዮ የዜና እወጃ እና ከቪኦኤ ሶማሊኛ ፕሮግራም ሠምቷል፡፡
ከፍርዱ በኋላም በተመሳሳይ ወንጀል ከተከሰሰ አንድ እስረኛ ጋር በካቴና ተጠፍሮ በቀን አንድ እንጀራ ለሁለት ተካፍሎእንዲበላ እንደ ውሻ እየተወረወረለት 60 ቀናትን አሳልፏል፡፡ መሐሙድ በተለይም በእንቅልፍ ወቅት እርሱ ወይምየሰንሰለት ደባሉ የተገላበጠ እንደሆነ ካቴናው የሚያደርስበትን የመለብለብ ቃጠሎ ሲያስታውስ ዓይኖቹ በእንባ ይሞላሉ፡፡በአሁኑ ወቅት በዝዋይ ማጎሪያ ከባድ ጥበቃ ለሚደረግባቸው ብቻ በተመደበ ‹‹ዘጠነኛ ቤት›› ውስጥ አስራ አንድ ሶማሊኛተናጋሪዎችን ጨምሮ በድምሩ ሰላሳ አራት ሰዎች ጋር ከዛሬ ነገ የግፍ ፍርዱ ተፈጻሚ ሊሆንብኝ ይችላል በሚል ሰቀቀንእየባነነ በስጋት ተጠፍንጎ መኖር ከጀመረ እነሆ ሰባት ዓመት ሊደፍን ሦስት ወራት ብቻ ቀርተውታል፡፡
የተዋረደው የፍትሕ ሥርዓት!. . .
ርግጥ ነው ይህ በጨረፍታ ያቀረብኩት አሳዛኝ ታሪክ የመሐሙድ የሱፍ ብቻ አይደለም፡፡ ሌሎች ሰባት ‹‹አባሪዎቹ››ስቃዩንም ሆነ የሞት ፍርዱን ይጋሩታል (በነገራችን ላይ በአንድ መዝገብ የተወነጀሉት እነዚህ ስምንት የሞት ፍርደኞች፡-መሐድ ኢብራሂም፣ አረብ ሰዋኔ ዱልባንቲ፣ ሐሰን መሐመድ ዑስማን፣ ሐሰን መሐመድ ዓሊ፣ ሙክታር መሐመድ ዓብዱላሂ፣ከድር ሽኩር ሙሳ እና ካሚል ዓብዱልናስር እንኳን በጋራ መንግሥት ላይ ሊያሴሩ ቀርቶ እርስ በርስም የተዋወቁት እስር ቤትውስጥ ነው፡፡ ከጅጅጋ ወደ ዝዋይ ‹‹ዘጠነኛ ቤት›› ተዘዋውረው በርካታ ዓመታትን ያሳለፉትም በጭካኔው ወደርእንደማይገኝለት የሚነገረው የክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ በአደራ እንዲቀመጡ በመተላለፋቸው መሆኑን ነግረውኛል፡፡) እንደ መሐሙድ ሁሉ እነርሱም ፍርድ ቤት ቀርበውአያውቁም፤ ምንም ዓይነት የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ አልተቆጠረባቸውም፡፡ እዚህ ጋ የማነሳው አሳዛኝ ገጠመኝከመካከላቸው አንዳቸውም ራዲዮ ስላልነበራቸው የተጣለባቸውን የሞት ፍርድ ውሳኔ የሠሙት፣ ዜናው ከተላለፈ ከበርካታቀናት በኋላ ሬዲዮ ካላቸው እስረኞች መሆኑ ነው፡፡ ይህ እጅግ አሳፋሪና አስደንጋጭ መንግሥታዊ ውንብድና በደንብ ይብራራ ዘንድ ለተከሳሶቹ ከተሰጣቸው ባለ አንድገፅ የክስ ቻርጅ የሁለቱን ብቻ በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡-
‹‹በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ፍትሕቢሮ በሶማሌ ክልላዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጅጅጋ
የዐ/ሕግ/መ/ቁ 90/2000
ከሳሽ፡- ዐ/ሕግ
ተከሳሽ፡- ሐሰን መሐመድ ዑስማን (ሐንን መድቤ)
ዕድሜ፡- 21
ሥራ፡- ተማሪ
አድራሻ፡- ጅጅጋ ከተማ፡- 06 ቀበሌ
ወንጀልበ1996ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ.መ.ሥ.ሥ.ህ.ቁ. 240(3) እና 251(መ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣
የወንጀል ዝርዝር
ተከሳሽ ከመስከረም 1999 ዓ.ም. ጀምሮ እራሱን ኦ.ብ.ነ.ግ. እያለ ከሚጠራው ተቃዋሚና አሸባሪ ድርጅት ጋር በራሱፈቃድ
በዚሁ በጅጅጋ ከተማ ከላይ በተጠቀሰው ዓመተ-ምህረት አባል በመሆን በጫካ በዚሁ አካባቢ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋርበከተማም
ሆነ በጫካ በመገናኘት በኢኮኖሚ ረገድ የሚያስፈልጋቸውን፡- ጫማ፣ ልብስ የመሳሰለውን እዚያው ድረስ ሄዶ በማቀበልአብሮ
ሲንቀሳቀስ በመቆየቱ ተከሶ ቀርቧል፡፡››
ሁለተኛው የክስ ቻርጅ ደግሞ እንዲህ ይነበባል፡-
‹‹በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ፍትሕ ቢሮ
በሶ/ክ/መ/ ጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ጅጅጋ
የዐ/ሕ/መ/ቁ 90/2000
ከሳሽ፡- ዐ/ሕግ
ተከሳሽ፡- መሐድ ሼክ ኢብራሂም
ዕድሜ፡- 28
ሥራ፡- የለውም
አድራሻ፡- ጅጅጋ ከተማ፡- ቀበሌ 05
1ኛ ክስ
ወንጀሉ

በ1996 ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ/መ/ህ/ ቁ. 241 እና 251(መ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝርተከሳሹ በ1998 ዓ.ም. ወራትና ቀኑ በውል ካልታወቀ ጊዜ ጀምሮ እራሱን ኦ.ብ.ነ.ግ. እያለ ከሚጠራው ተቃዋሚ የፖለቲካ
ድርጅትና አሸባሪ ጋር በራሱ ፈቃድ አባል በመሆን ከዚህ ሕገ-መንግሥቱን ከሚፃረር ድርጅት በቀጥታ ፌዴሬሽኑእንዲከፋፈል፣ ክልሉን
የመገንጠል ዓላማ ለማሳካት ይህንኑ ድርጅት ከዚሁ በጅጅጋ ከተማ ለጊዜው ካልተያዘ ግብረ-አበሩ ጋር በመሆን ይህንኑአሸባሪ ድርጅት
በሚያስፈልገው ማቴሪያል ሁሉ፡- ጫማ፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ፣ መድሃኒት. . . የመሳሰለውን በማቀበሉ፡፡
2ኛ ክስወንጀሉበ1996ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ/መ/ህ/ ቁ. 36 (ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ የተለያዩ መ/ቤቶች ማለትም፡- የክልሉ ት/ቢሮን፣ የቀብሪ-ደሐር ት/ቢሮን፣ እንዲሁም የMSF
እና የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችን እና የትምህርት ተቋማትን ማህተም በማስመሰል አትሞ እና የኃላፊዎችን ፊርማ ዓይነትአስመስሎ
በማስፈር ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ በመገኘቱ ተከሶ ቀርቧል፡፡››
(ሁሉም የክስ ቻርጆች ማኅተም እና አንጋው አፈወርቅ ምንተስኖት የተባለ የክልሉ ዐቃቤ ሕግ ፊርማ አላቸው)
እነሆም ያለአንድ ምስክር፣ ያለምንም የሰነድ ማሰረጃ፣ አንድም ቀን ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃል ሳይጠየቁ እና ሳይከራከሩ (ያውም የዞን ፍርድ ቤት) በነዚህ በስም በጠቀስኳቸው በስምንቱ ኢትዮጵያውን ላይ የሞት ቅጣትን የመሰለየመጨረሻ ውሳኔ እንደቀልድ አስተላልፎባቸዋል፡፡ (በነገራችን ላይ ሌሎች 13 የኢትዮጵያ-ሶማሌ ተወላጆችም በተመሳሳይ የሐሰትውንጀላ የዕድሜ
ልክ እስር ተፈርዶባቸው ዝዋይ ይገኛሉ፡፡ የሚገርመው ጉዳይ ደግሞ ም ቢሆኑ መጀመሪያ ተጠርጥረው በተያዙበት ወንጀልአይደለምየተጠየቁት፡፡ ጉዳዩ ጭራሽኑ በምርመራም ወቅት አልተነሳም) መቼም በዚህ መልኩ በተቀናበረ የውሸት ክስ ከ20-27 ዓመት የሚገኙ ወጣቶችን በሲኦላዊ እሳተ-ነበልባል ስቅየት ውስጥ እንዲያልፉ ከማድረግም በዘለለ፣ ብሩህ ቀናቸውን አጨልሞ ላይመለሱወደመቃብር
የሚሸኝ ቅጣት ሲጣል ከመመልከት የበለጠ የትኛውንም ዜጋ የሕሊና ስቃይ ውስጥ ከትቶ፣ አንገት አስደፍቶ፣ በቁጣ ቀስቅሶ ወደአደባባይ የሚያወጣ ገፊ-ምክንያት አለ ብዬ አላምንም፡፡
ማነው ተጠያቂው?
በእነዚህ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ‹በጄል-አደብ› የደረሰባቸው በነውረኝነት የታጀለ ኢ-ፍትሐዊ ፍርድ እና ስቅየት፣ የሥርዓቱን እውነተኛ ማንነት ገሃድ የሚያወጣ ተጨባጭ ተግባር መሆኑ ባይካድም፡ ይህንን አረሜናዊ ድርጊት በፊት-አውራሪነት የመሩት፡- ኮሎኔል ሞኒ መንገሻ በጊዜው የክልሉ የፀረ-ሽብር ግብረ-ኃይል ዋና ኃላፊ የነበረ አሁን ወደአዲስ አበባ ተቀይሮ‹ሕገ-ወጥ የሠው ዝውውር ወንጀል መከላከል› ኃላፊ፣ ቢኒያም የተባለ የክልሉ የደህንነት ኃላፊ፣ ሻለቃ ዘገየ በክልሉ የፌዴራል ፖሊስኃላፊ፣ ወልደአራዌ የክልሉ ፖሊስ ም/ኮሚሽነር፤ እንዲሁም ሻለቃ ወንድሜ፣ ሻለቃ በለጠ እና ታሰረ የተባሉ ኃላፊነታቸውንለይተው የማያስታውሷቸው ግለሰቦች መሆናቸውን ግፉአኖቹ በተሰበረ ልብ፣ ምሬት በሞላው ድምፅ፣ ተስፋ በቆረጠ ስሜት ሲተርኩልኝ ዓይኖቼ ላይ የተቋጠረው የእንባ ከረጢት ገንፍሎ እንዳይፈስ ብርቱ ትግል ማድረጌን አልሸሽግም፡፡
የሆነው ሆኖ እነዚህ የሥርዓቱ ሹማምንት የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጡ፣ የሞት ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ባደረጓቸው ምስኪኖች ላይ የማሰቃያ ጥበቦቻቸውን በሙሉ ከሞከሩባቸው በኋላ፡- ‹‹ሞት እንፈርድባችኋለን!!›› እያሉ ያስፈራሯቸውናይዝቱባቸው ነበር፤ እነርሱም፡- ‹‹እናንተ ፍርድ ቤት ናችሁ እንዴ?›› ብለው በግርምትና ባለማመን ሲጠይቋቸው፣ ማናአህሎኝነትያሳበጣቸው የፀጥታ ኃላፊዎች እንዲህ በማለት አስረግጠው መልስ መስጠታቸውን ሰምቻለሁ፡-
‹‹አዎን! ፍርድ ቤት ማለት እኛ ነን!!››
በርግጥ ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ የተላለፈባቸው ውሳኔ፣ ያውም በሞት እንዲቀጡ የሚል መሆኑን ስናስተውል የዛቻውን መነሾ መረዳቱ አዳጋች አይሆንብንም፡፡ በአናቱም በምርመራ ወቅት ዕድል ፊቷን ያዞረችበትን ተጠርጣሪ እዛው እስረኛ ፊትበሽጉጥ ግንባሩን በርቅሰው እንደ መናኛ ነገር ሜዳ ላይ ይዘረጉት እንደነበረ የዓይን እማኞች ይመሰክራሉ፡፡ በጥቅሉ ይህ ሁነት በሀገሪቱ አለቅጥ የተንሰራፋውን የፍትሕ እጦት፣ የሠብአዊ መብት ጥሰት፣ ዳኞች ከሕግ ይልቅ ከቤተ- መንግሥት በሚላክላቸው የፍርድ ውሳኔ ንፁሃኑን ለምድራዊ ስቃይ ከመዳረግም አልፈው ተርፈው በጭካኔሕይወታቸውንም እንደሚነጠቁ በቂ ማስረጃ ይመስለኛል፡፡
‹‹ጄል-አዳብ››
የክልሉ ኗሪዎች ‹‹ጄል-አዳብ›› (የገሃነም እስር ቤት) እያሉ የሚጠሩት የጅጅጋው ማሰቃያ ቤት ክፍሎች የተሠሩት አራትመቶ ታሳሪዎችን እንዲይዙ ታስቦ ቢሆንም፣ አብዛኛውን ጊዜ ከአራት ሺህ በላይ ታሳሪዎች እንደሚታጎሩበት አረጋግጫለሁ፡፡ይህም አንድ ሰው ከአንድ ሰዓት በላይ በእንቅልፍ ማሳለፍ እንዳይችል አድርጎታል፡፡ ምክንያቱም ቦታውን ለተረኛው የመልቀቅ ግዴታአለበትና፡፡ ምናልባት እንቅልፍ ቢጥለው እንኳ ተረኞቹ ቀስቅሰው (ጎትተው) ያስነሱታል፡፡
ከ‹‹ጄል-አዳብ›› በሕይወት ተርፎ የሚወጣ ሰው ዕድለኛ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ በዚህ ቦታ ከቤተሰብ ጋር መገናኘት ጭራሽ አይሞከርም፡፡ ማሰቡ እንኳ እንደ ቅንጦት ነው የሚታየው፡፡ በእስር ቤቱ አጥር ሦስት መቶ ሜትር ክልል ርቀት ዙርያ ውስጥመገኘትም ለከባድ ስቃይ (አንዳንዴም ለሞት ቅጣት) ይዳርጋል፡፡ በሃያ አራት ሰዓት አንዴ፣ አንድ እንጀራ ለሦስት እየተቃመሱለአምስት ዓመት በዛ እስር ቤት ያሳለፈ ምስኪን አጋጥሞኛል፡፡ ይህ ወጣት በ2004ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ሦስት ዓይነት ተላላፊ በሽታ(ተቅማጥ፣ ሰውነትን የሚያሳክክና ጉሮሮን አሳብጦ ለአዕምሮ መቃወስ የሚዳርግ) ተከስቶ በቀን እስከ አስራ አራት ሰው ድረስ ይሞትእንደነበር ያስታውሳል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕክምና ብሎ ነገር አልነበረም፡፡ እንዲያውም በግልባጩ የክልሉ አስተዳዳሪዎችጭካኔያቸውን (ኢ- ሠብአዊነታቸውን) ወለል አድርገው የሚያሳብቁ ድርጊቶች መፈፀማቸውን አላቋረጡም፡፡ ለማሳያ ያህልም እስረኛው ከሌሊቱስድስት ሰዓት ላይ በአንድ ድምፅ እንዲህ የሚል መፈክር እንዲያሰማ መገደዱን እዚህ ጋ መጠቀስ ይቻላል፡-
‹‹መለስ ዜናዊ ሐኖላዶ!›› (መለስ ዜናዊ ለዘላለም ይኑር!)
‹‹አብዲ ሑመድ ዑመር ሐኖላዶ!››
‹‹ኢትዮጵያ ሐኖላዶ!››
ኦብነግ ሐዳኦዶ!›› (ኦብነግ ይውደም!)ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ቤተሰብ ታሳሪ ልጁ በሕይወት ይኑር ይሙት የሚያውቀው ከማጎሪያው በስንት ጊዜ አንዴ የሚፈታ ሰው ሲገኝ ብቻ የመሆኑ እውነታ ነው፡፡ እናም ድንገት በአንዲት ‹ዕድለኛ› ቀን አንድ ታሳሪ ከ‹‹ጄል-አዳብ›› የተለቀቀእንደሆነ ወሬው ከመቅጽበት ይዛመትና ለሳምንታት አሊያም ለወራት የእስረኛው ቤት በእንግዶች እስከ አፍ-ገደፉ ጢም ብሎ ይውላል፡፡የተለመደ ነውና እሱም ያለመታከት የቀረበለትን ጥያቄ በሚከተለው መልኩ ሲመልስ ይከርማል፡-
‹‹ኦ!… እገሌ ከሞተ እኮ ሁለት ዓመት አለፈው›› ፤ “እገሌማ ሲያሳዝን! ካረፈ ገና አንድ ወሩ ነው”፤ “ኦ! እገሌ ለወደፊቱ እግዜር ይጠብቀው እንጂ እስካሁን በሕይወት ይገኛል…” ወዘተ ወዘተ.394711_184013551696255_1365830121_n . .
Source:: Zehabesha

The US Government Must Implement Congress’ Stance Against Forced Evictions in Ethiopia

Oakland, CA – The Oakland Institute applauds the US Congress for adopting language in the 2015 Omnibus Appropriations Bill that ensures US funding to Ethiopia will not be used to support forced evictions in the country.
This provision in the bill acknowledges the ongoing crisis of human rights abuses resulting from forced evictions and land grabbing in Ethiopia and prevents US assistance from being used to support activities that directly or indirectly involve forced displacement in the Lower Omo and Gambella regions. Furthermore, it requires US assistance to be used to support local community initiatives aimed at improving livelihoods and be subject to prior consultation with affected populations. The bill also opposes US funding to international financial institutions such as the World Bank for programs that could lead to forced evictions in Ethiopia.
Several reports from the Oakland Institute have exposed the scale, rate, and negative impacts of large-scale land acquisitions in Ethiopia that will forcibly displace over 1.5 million people. This relocation process through the government’s villagization scheme is destroying the livelihoods of small-scale farmers and pastoralist communities. Ethiopian security forces have beaten, arrested, and intimidated individuals who have refused to relocate and free the lands for large-scale agricultural plantations.
Ethiopia’s so-called development programs cannot be carried out without the support of international donors, particularly the US, one of its main donors. Oakland Institute’s on-the-ground research has documented the high toll paid by local people as well as the role of donor countries such as the US in supporting the Ethiopian policy.
With this action, the US Congress clearly sends a message to both the Ethiopian government and the US administration that turning a blind eye to human rights abuses in the name of development is not acceptable. The new Bill reiterates provisions already contained in the 2014 Appropriations Bill, however, to date no evidence has been made available to demonstrate how US agencies and International institutions have implemented the provisions of the previous Bill. As the oversight authority of the State Department, Congress must ensure that the law is fully upheld and implemented. This warrants thorough scrutiny of USAID and World Bank programs to Ethiopia and their role in the forced resettlements and human rights abuses.Other human rights abuses – including the unlawful extradition and detainment of two Ethiopian-born individuals holding citizenship in Britain and Norway – abound, making strong action by the US Government imperative.
Thus, while the Oakland Institute applauds the US Congress for continuing its commitment to funding meaningful development work in Ethiopia, we believe that more needs to be done. We are calling on members of the Congress to demand that monitoring and reporting from the US State Department, Treasury, USAID, and other involved institutions begin immediately.

Wednesday 10 December 2014

የቅሊንጦ አንበሶች (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)


lion
ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ቅሊንጦ የሚባል ጫካ አለ እዚያ ጫካ ውስጥ በርካታ ጥቁር አንበሶች አሉ፡፡ ለጥቂት ቀናት እዚያ ጫካ ውስጥ ከትቸ ነበር፡፡ በገባሁ በዐሥረኛ ቀኔ ትቻቸው ወጣሁ፡፡ እዚያ በነበርኩበት ወቅት ካገኘኋቸው አናብስት የሁለቱን ታሪክ ብቻ በአጭር በጭሩ ላጫውታቹህ፡፡
አንደኛው አበበ ካሴ ይባላል፡፡ ተወልዶ ያደገው ጎንደር ነው፡፡ አምና 2006ዓ.ም. ጥር 12 ቀን ነበር የተያዘው፡፡ ወደዚህ ጫካ ከመምጣቱ በፊት በተለያዩ ሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የማሰቃያ ቦታዎች ሰቆቃ ሲፈጸምበት ቆይቶ በመጨረሻ ነው እዚህ ጫካ ውስጥ የታሰረው፡፡ አበበ ካሴ የግንቦት 7 ቆራጥ ታጋይ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ከ1981-1993ዓ.ም. ድረስ የቀድሞው ኢሕዴን የአሁኑ ብአዴን ታጋይ ሆኖ ለ12 ዓመታት አገልግሏል፡፡ ከዚያ በኋላ እሱና ጓዶቹ ታግለው ለዚህ ያበቋቸው መሪዎቹ ከዚህ በስተቀር የማይባል ሁለንተናዊ ድጋፍ እየሰጠ ባበቃቸው ሕዝብ ላይ የሚፈጽሙት ገደብ የለሽ ግፍና በደል አንጀቱን ሲቆርጥበት፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ የፍትሕ ጥያቄ የመመለስ ብቃቱ ወኔው ፍላጎቱ ጽናቱ እንደሌላቸው ባረጋገጠ ጊዜ ጥሏቸው በረሀ ገባ፡፡ በረሀ ሆኖ ለሦስት ዓመታት ያህል በግሉ ሲንቀሳቀስ ቆይቶ በኋላ እንደሱ የከፋቸው ቢጤዎቹህ ተቀላቀለ ከዚያም ወደ ግንቦት 7 ተቀላቅሎ ድርጅቱ ላዘዘው ተልእኮ አምና ጎንደር ላይ እስከተያዘበት ቀን ድረስ ለ9 ዓመታት ያህል ነፍጥ አንሥተው ከሚታገሉ ወገኖች ጋራ ሲታገል ቆይቷል፡፡
ለአበበ ካሴ አምና ጥር 12 ገደኛ ቀን አልነበረችም፡፡ ያች ቀን የተሰጠውን ወታደራዊ ተልእኮ (mission) በዚህ አገዛዝ ባለሥልጣናት ላይ የሚፈጽምባት ቀን ነበረች፡፡ ለዚህ ለሚወስደው እርምጃ ከአጋሩ ጋራ ቅድመ ዝግጅት በሚያደርጉበት ሰዓት በጥቆማ ተያዙ፡፡
አበበ ጎንደር ከመግባቱ በፊት ከሁለት ጓዶቹ ጋራ ሆኖ ሙሉ ትጥቃቸውን እንደያዙ ከኤርትራ ተነሥተው የሱዳንን በረሀ ለ13 ቀናት በእግራቸው ተጉዘዋል፡፡ ወደ ሀገራቸው ምድር ገብተው እየገሰገሱ እንዳሉ ከወያኔ ካምፕ በቅርብ ርቀት ላይ በሆኑበት ሰዓት ከሁለቱ ጓዶቹ አንደኛው መሬት ላይ በመቀመጥ እንደደከመውና መንቀሳቀስ እንደማይችል ተናገረ፡፡ አበበም እንደ አለቃነቱ ያሉበት ቦታ ከወያኔ ወታደሮች ካምፕ ቅርብ ርቀት በመሆኑ አደገኛ መሆኑን አስገንዝቦ እንደምንም ተጠናክሮ ቦታውን ከመልቀቅ ውጭ ምንም አማራጭ እንደሌለውና እንዲነሣ አዘዘው፡፡ ጓዱ ግን ጨርሶ መንቀሳቀስ እንደማይችል ተናገረ፡፡ ይሄኔ ነበር አበበ ይህ ባልደረባው በእርግጥም የወያኔ ሰላይ እንደነበረ አልነሣም ያለውም ስለደከመው ሳይሆን ሆን ብሎ እንደነበር ያረጋገጠው፡፡
አበበ በዚህ ልጅ ላይ ጥርጣሬ አድሮበት የነበረው ሱዳን በረሀ ላይ እንዳሉ ያሉበትን ሁሌታ ለአለቆቹ ለማስታወቅ ከሁለቱም ነጠል ብሎ ስልክ ለመደወል በሚሞክርበት ሰዓት ድንገት ወደጓዶቹ ዞር ሲል ይህ አሁን ተቀምጦ አልንቀሳቀስም ያለው ጓዱ መሣሪያውን የማቀባበል እንቅስቃሴ ሲያደርግ ያየው ይመስለውና ስልኩን አቋርጦ ይመለስና መሣሪያውን ተቀብሎ ሲመለከተው በእርግጥም ተቀባብሎ አገኘው፡፡ ማን አዞት ለምን እንዳቀባበለው ሲጠይቀው “ሰው ከርቀት ያየሁ መስሎኝ ነው” ይለዋል ከዚያ በኋላ አበበ ይሄንን ልጅ በጥርጣሬና በጥንቃቄ ነበር የሚመለከተው፡፡ ሁኔታውን ለአለቆቹ ለማሳወቅ ስልክ ለመደወል በተደጋጋሚ ሞክሮ ሊሳካለት አልቻለም በግሉ ወስኖም ርምጃ መውሰድ አልፈለገም፡፡ ይህ ልጅ መሣሪያውን ያቀባበለው የነበረው እነ አበበን ለመግደል አስቦ ነበር፡፡
አበበ ይህ ጓዱ አልነሣም እንዳለው መሣሪያውን ይቀበለውና ሰላይነቱን እንዳወቀበትና ሊያደርግ የሚፈልገውንም ነገር ማድረግ እንዲችል ወደፈለገበት ቦታ እንዲሄድ ይፈቅድለታል፡፡ ይሄኔ ልጁ ይደናገጥና እንዲገለው አበበን ይጠይቀዋል፡፡ አበበም “እኔም ሆንኩ ድርጅቴ ሰው የመግደል ዓላማ የለንም አንተን ጨምሮ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትሕና ነጻነት እራሳችንን መሥዋዕት ማድረግ እንጅ” የሚል መልስ ይሰጠውና ልጁን እንዲሔድ ያዘዋል ልጁ ከአሁን አሁን ተኩሶ ገደለኝ በሚል ጥርጣሬ ዐሥሬ እየዞረ በመመልከት ወደ ካምፑ አቅጣጫ ተጓዘ፡፡ አበበ እነኝህ አብረውት ያሉት ሁለቱ ጓዶቹ የተሰጣቸው ወታደራዊ ተልእኮና የትና ምን እንደሆነም ስለማያውቁ የዚህ ልጅ ከእነሱ መለየትና ሔዶ ለወያኔ ስለነሱ መናገሩ አላሳሰበውም፡፡ አበበና አንዱ ጓዱም በተቻለ ፍጥነት አካባቢውን ከለቀቁ በኋላ ሌሊት ሌሊት እየተጓዙ ጎንደር ከተማ ገቡ፡፡ ጎንደር እንደገቡም ሰዓቱ ሲደርስ ለጓዱ የሚወስዱት እርምጃ ምን እንደሆነና በማን ላይ እንደሆነም ከነገረው በኋላ በቦታው ላይ ቅድመ ዝግጅት በሚያደርጉበት ሰዓት ይሄ ከአበበ ጋር ያለው ጓዱ ቀደም ሲል ኤርትራ እያሉ አብሯቸው ለመታገል ግንቦት ሰባትን ተቀላቅሎ ከነበረ በኋላ ግን ድንገት ከተሰወረ ሰው ጋር ፊት ለፊት ዐይን ለዐይን ይጋጠማሉ፡፡ ይህ ሰው የሬዲዮ መገናኛ ይዟል ልጁ ተደናገጠ መለስ በማለት ቀጥ ብሎ አበበ ወዳለበት ቦታ ሔደ ይሄንን ሁኔታ ለአበበ እየነገረ ባለበት ቅጽበት አካባቢው በሦስት ካሚዮኖች በመጣ የፌዴራል ፖሊስ ተወረረ እነ አበበም በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ይህ እነ አበበን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሰው የወያኔ ደኅንነት ነው፡፡ ኤርትራ ሔዶ የአንድነት ፓርቲ አባል ነኝ በማለት ስሙ ተስፋዬ እንደሚባል ሁለት ዲግሪ እንዳለው አውርቶ የበረሀ ስሙን ታይሰን በሚል ሰይሞ እዚያ ታይሰን በሚባል ስም እየተጠራ ታማኝነት አግኝቶ ከተማ ድረስ እየተላከ ድንገት ተሰውሮ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በድርጅቱ ውስጥ የነበረ ሰው ነው፡፡
አበበ ከዚያች ቀን ጀምሮ ወደዚህ ወደ ቅሊንጦ እስከወረደበት ጊዜ ድረስ አስቀድሞ በጎንደር በኋላም እዚህ አዲስ አበባ በማእከላዊ የግንቦት 7ን አንዳንድ ምስጢሮችና እዚህ ሀገር ውስጥ ያሉ የግንቦት 7 የስለላ መዋቅር ሰንሰለትና አባላትን፣ እጃቸው ላይ የተገኙትን ሊወስዱት አስበውት ለነበረው እርምጃ የሚያገለግሉ ሰነዶችን ማን እንደሰጣቸው እንዴት እንዳገኙት እንዲናገር ተጠይቆ ለመናገር ፈጽሞ ፈቃደኛ ባለመሆኑ የሰው ልጅ የጭካኔ ደረጃ የተለካበት ሰቆቃ (ቶርቸር) ሲፈጸምበት ነበር የቆየው፡፡ የመጀመሪያዋና ቀላሏ እራቁቱን እጅና እግሩን አስረው የጉንዳን አሸን ላይ ነበር የጣሉት በዚህ አልሆን ሲላቸው እያገላበጡ አንጠልጥለው ገረፉት አሁንም አልሆነላቸውን ሰቆቃውን እያከበዱት መጡ ውኃ የተሞላ የፕላስቲክ ጠርሙዝ ብልቱ ላይ አንጠለጠሉበት በዚህ ሁሉ መከራ ወይ ፍንክች ያለው አበበ ደረቱላይና ውስጥ እግሩ ላይ ኤሌክትሪክ አያይዘው አቃጠሉት አበበ ግደሉኝ እንጅ ምንም ዓይነት ኢሰብአዊ የጭካኔ ድርጊት አይበግረኝም ብሎ እንቅጩን ነገራቸው፡፡ ርሕራሔ ያልፈጠረባቸው አውሬዎቹ የአበበን የእጆቹንና የእግሮቹን ጣቶች ጥፍሮች እያንዳንዳቸውን በተራ በተራ እየገሸለጡ እየቦጨቁ እየፈነቀሉ ጣሏቸው ቆራጡ ጨካኙ ጀግናው አበበ ግን ጽናቱ ወደር አልነበረውምና ጨርሶ ሊፈታላቸው አልቻለም፡፡ አውሬዎቹ ተስፋ ቆረጡ ከአበበ ምንም እንደማያገኙ ሲገባቸው ማእከላዊ ጨለማ ክፍል ውስጥ ወርውረውት ከቆዩ በኋላ ከዚያ አውጥተው እሱን ወዳገኘሁበት ቦታ ወደ ቅሊንጦ አመጡት ከዚህ በኋላ የሚቀራቸው እሱን ለመበቀል መግደል ብቻ ነው፡፡ እስከአሁን ይሄንን አላደረጉም፡፡ ሲመስለኝ ይሄንን እንዳያደርጉ ያደረጋቸው ይህ ሥርዓት ሰቆቃ (ቶርቸር) በዜጎች ላይ እንደማይፈጽም በኢትዮጵያ ውስጥ ይደረግ የነበረው ሰቆቃ በደርግ ሥርዓት እንደቀረ ለሰብአዊ መብት ድርጅቶችና ለምዕራባዊያን መንግሥታት ሳያሰልስ ስለሚደሰኩር አበበ ደግሞ በእነዚህ አካላት በወያኔ እጅ እንዳለ መታወቁ ይኔንን የመጨረሻ እርምጃ እንዳይወስዱ አድርጓቸዋል፡፡
አሁን አበበ ከሌሎች ወንድሞችና እኅቶች ጋር የግንቦት ሰባት አመራር ተብሎ ክስ ተመሥርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ነው፡፡ በዚህ አገዛዝ ሳንባ የሚተነፍሰውና የሀገርንና የሕዝብን ጥቅሞች ሳይሆን ከሀገርና ሕዝብ ጥቅሞች ጋራ የማይጣጣመውን የሥርዓቱን ጥቅም ለማስጠበቅ ከሚሠራ “ፍርድ ቤት”፤ የሀገርና የሕዝብ ጥቅም ሳይሆን የሀገርና የሕዝብ ጥቅም ተጎድቶ የቡድን ጥቅም በሚጠበቅበት በሚከበርበት በወያኔ ፓርላማ ሰላማዊ አማራጮች ፈጽሞ ስለተዘጋባቸውና የዜግነት ግዴታቸው የታሪክ አደራ አላሳርፍ ብሏቸው ለሀገርና ሕዝብ ፍትሕ ነጻነትና እኩልነት በመታገላቸው፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከግፍ አገዛዝ ነጻ አውጥተው የሥልጣን ባለቤት ለማድረግ ይህ አገዛዝ የተወላቸውን ብቸኛ አማራጭ በመጠቀማቸው በዚሁ ምንም ዓይነት የሕዝብ ውክልና በሌላቸው በወያኔ ቡድን ስብስብ ፓርላማ ተብየ በወጣ ሰብአዊ መብቶችን ዓለማቀፋዊ ድንጋጌዎችንና የገዛ ሕገ መንግሥታቸውን በቀጥታ በሚጻረር ሕግ አላግባብ አሸባሪዎች ስለተባሉ ብቻ ግንቦት ሰባትንና የአርበኞች ግንባርን አሸባሪ ናቸው ብሎ ከሚያምንና ከተቀበለ ፍርድ ቤት ፍትሕ ባይጠበቅም ፍርድ ቤት አቅርበዋቸዋል፡፡
አበበና ሌሎች ወገኖች ፍርድቤት በቀረቡ ጊዜ በተለይም በአበበ ካሴ ላይ የተፈጸመበትን ኢሰብአዊ የግፍ ዓይነቶች ለፍርድ ቤቱ በሚያስረዱበት ጊዜ ዳኛው እሱ ራሱ ይናገር እናንተ ምንድን ናቹህ? በማለቱ በሰው ተደግፎ የቆመው ቆፍጣናው ጎንደሬ አበበ ካሴ ዳኛው ያልጠበቀውን መብረቃዊ ቃላቶች በዳኛው ላይ አወረደበት ዳኛው ደነገጠ “ነገሩህ እኮ!” አለ አበበ “ምኑን ነው የምነግርህ?” ሲልም ጠየቀ “ለመሆኑ አንተ ዳኛ ነህ? ዳኛ ነኝ ብለህስ ራስህን ትቆጥራለህ? ለዜጎች የፍትሕ ጥያቄ ፍትሕ የመስጠት ነጻነቱና ብቃቱስ አለህ? ለመሆኑ በዚህች ሀገር ፍርድ ቤት አለ? የማናውቅ መሰለህ አንተ ዳኛ ሳትሆን ካድሬ ነህ፡፡ ቀን ቀን ዳኛ ነኝ ብለህ ካባ ደርበህ ትውላለህ ሌት ሌት ፋቲክ ለብሰህ ሕዝብ ስታሰቃይ ስትቀጠቅጥ የምታድር የሕዝብ ጠላት ነህ” አለ አበበ፡፡ አበበ ወኔውና ጽናቱ ዳርቻ የለውም፡፡
ይሄንን የአበበን ታሪክ መጀመሪያ ከሌሎች በኋላም ከራሱ ስሰማ ትውስ ያለኝ የነ አቶ መለስ ጀግና አሞራው ነበር፡፡ በእርግጥ አሞራው በአበበ ዐይን ሲታይ ትንኝ ነው፡፡ የሰማይና የምድር ርቀት አላቸው፡፡ ይሄም ልዩነታቸው መሰለኝ እንዳስታውሰው ያደረገኝ፡፡ ለነአቶ መለስ ግን አሞራው የጀግናና የጽናት ምሳሌ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከአሞራው ጋራ ያደረገውን ቃለ ምልልስ ዐይታቹህታል፡፡ በቃለ ምልልሱ አሞራው ምንም እንኳን ደርግ እንዲናገርለት የፈለገውን ነገር ባይናገርለትም አቀራረቡ ግን ምን ያህል የተለሳለሰ እንደነበር ታስታውሳላቹህ፡፡ “ሕወሀት ደርግ ከያዛቹህ እንዲህ ያደርጋቹሀል እንዲህ ያደርጋቹሀል” እያለ የሕወሀት ካድሬዎች ምን እያሉ እንደሚሰብኳቸው ተንትኗል፡፡ ያውም እንግዲህ ይሄ የቀረበው አሞራውን ለትዝብት ሊዳርጉ የሚችሉ ብዙ ነገሮች ከመሀሉ ተቆራርጦ እንደቀረበ የቀረበው ቪዲዮ (ምስለ ትዕይንት) ያረጋግጣል፡፡
ቆፍጣናው አቤ ግን ቀድሞ ነገር መቸ ፊት ሰጣቸውና እንኳን እንደ አሞራው እንዲህ ነው እንዲህ እያለ ሊቀበጣጥር ይቅርና! ለምርመራ በመጡበት ቁጥር ተናግሮት የማያልቀውን እንደ መብረቅ የሚያነዱ ካላቶቹን ያዘንብባቸዋል፡፡ የምርመራ ሥራቸውን ለመሥራት ዕድል ባይሰጣቸው ከሱ ጋራ ስድብና ብሽሽቅ መግጠሙን ሥራ አድርገው ይዘውት ነበር፡፡
ከዚያ ሁሉ መከራው በኋላ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች የቪዲዮ ካሜራቸውን (መቅረጸ ምስለ ትዕይንታቸውን) ተሸክመው አበበ እንደማያውቃቸው ሁሉ ልክ ነጻና ተቆርቋሪ ጋዜጠኛ በመሰለ አቀራረብ ቀርበውት ነበር አልተሳካላቸውም፡፡ እነሱም ቅመሱ ብሏቸው አይደል ሲያከለፈልፍ ያመጣቸው? አጠጣቸዋ እስኪበቃቸው! ፀረ ኢትጵያነታቸውን ፀረ ሕዝብነታቸውን እየዘከዘከ አንባረቀባቸው፡፡ ካልደመሰሱት ወያኔ አሞራውን እንዳሳየ ሁሉ ነገ ሀገር ነጻ ስትወጣ አበበን ዕናይ ይሆናል፡፡ የዛ ሰው ይበለንና ፈጣሪ፡፡
ዛሬ አበበ በዛ በተፈጸመበት ዘግናኝና አረመኔያዊ ጭካኔ የተሞላበት የግፍና ሰቆቃ ዓይነቶች የተነሣ ከጭንቅላቱ እስከ እግሩ ድረስ የግራ ጎን ሰውነቱ በድን ሆኖ ደርቋል፡፡ ብልቱ ያዣል ፈሳሽ አለው ጥፍሮቹ ግን እንደገና በቅለዋል፡፡ በእነዚህ ህመሞች እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ ቀይ መስቀል መጥቶ በጎበኘው ሰዓት በራሱ ወጪ ሙሉ ሕክምና እንዲያደርግለት አገዛዙን ፈቃድ ሚጠይቅም አገዛዙ ሊፈቀድለት አልቻለም፡፡
አቤ በውጭ ጋዜጠኞችም ተጎብኝቷል ቃለ መጠይቅም አድርገውለታል ቆፍጣናው መብረቁ አቤ ለነሱስ ቢሆን መቸ ተመለሰ? ለዚህች ሀገር ውድቀት ለዚህ ሕዝብ ስቃይና መከራ መንግሥቶቻቸው ተጠያቂዎች መሆናቸውን እስኪደነግጡ ድረስ ነግሯቸዋል፡፡ ወንድሜ አበበ ካሴ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ባለህበት ይጠብቅህ፡፡ አበበ አንዱ ምሳሌ ነው ገድሎቻቸውን ሰው ሳያውቅላቸው ሳይሰማ ሳያይላቸው ከዓላማቸው ፈቀቅ አንልም እያሉ ከሀቃቸው ጋር በመጽናት፤ አጨካከናቸው ግድል አድርገው ሊገላግሏቸው እየቻሉ በሰቆቃ ብዛት ነፍሳቸው ሳይወጣ በወደቁበት ገምተው ተልተው ተጠራሙተው እንዲሞቱ ያደረጓቸው በርካታ ዕንቁ ጀግና አንበሳ ዜጎች እንዳለፉ በእነዚህ የማሰቃያ የምድር ሲዖል ቦታዎች ለቶርቸር (ለሰቆቃ) ገብተው ከወጡ ሰዎች የዐይን ምስክሮች ተረድቻለሁ፡፡
አንድ የገረመኝ ነገር ቢኖር እነኝህ ጀግኖች ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ከገበሬው ማኅበረሰባችን የወጡ መሆናቸው ነው፡፡ በእርግጥ አንድ ግልጽ ነገር አለ የሀገር ፍቅር ስሜት ከከተማ ሰው ይልቅ በገጠር ሰው ይጠናል፡፡ የዚህም ምክንያቱ የሚመስለኝ ሀገር ማለት በድንበር ተከልሎ ያለው መሬትና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ ማለት ነውና የገጠር ሰው ደግሞ ሕይዎቱ የተመሠረተው በግብርና ስለሆነና ከአፈሯ ከውኃዋ ከእጽዋቷ ከአዕዋፋቷ ከእንስሳቷ ከሁለመናዋ ጋር ያለው ግኑኝነት ቅርብና ቀጥተኛ በመሆኑ የመሬቷ የውኃዋ የሌሎች ሀብቶቿ ዋጋ ስለሚገባው ጋራ ሸንተረሯን በእግሩ ስለሚወጣ ስለሚወርድባት ወዙ ከወዟ ላቡ ከላቧ ጋር ስለሚሞጋሞግ ስለሚሻተት ስለሚቀዳ በክረምቱ ከመኸሩ በበጋው በጸደዩ የተለያየ ዓይነት ማራኪ ውበት ገጽታዋ በዐይነ ሥጋውና በዐይነ ሕሊናው ላይ ታትሞ ስለሚቀረጽበትና በእነዚህ ምክንያቶች ፍቅሯ የግዱን በልቡ እንዲያድርበት ስለሚያደርገው ይመስለኛል፡፡
የከተማ ሰው ግን ግፋ ቢል የበዓልና የበዓል ግርግሩ ካልሆነ በስተቀር እንደ ገጠሩ ሰው ስለሀገሩ በተለየ እንዲያስታውስ እንዲናፍቅ የሚያደርገው ጠንካራ ትስስር ስለሌለው የሀገር ነገር ብዙም የሚደንቀው አይደለም፡፡ ይሄንን ነገር ምሁራን በሚባሉትና ባልተማሩት ወገኖች መሀከል ብናየውም ውጤቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ ምሁራን የሚባሉት የፈለገ ነገር ቢሆን ግፋ ቢል “የተጠየቀውን በመጠኑ ለመቀነስ” ወይም “ሁሉንም ከማጣት ጥቂት ለማግኘት” እንደራደር ይላሉ እንጅ ያልተማረው እንደሚለው “እሞታለሁ እሠዋለሁ እንጅ የሀገሬን ጥቅምማ አሳልፌ አልሰጥም” አይሉም፡፡ ምሁራን ነፍሳቸውን ይወዳሉ ጥቅመኛም ናቸው ለሚጨበጠው ለቁሳዊ ነገሮች ያላቸው ግምትና ዋጋ ከፍተኛ ነው ለማይጨበጠው ለመንፈሳዊ ሀብቶች ግድ የላቸውም፡፡ እንደ መሥዋዕትነት የሚፈሩት ነገር የለም በተቻላቸው መጠን መሥዋዕትነትን በሚጠይቅ ጉዳይ ዙሪያ አይደርሱም፡፡ በዚህም ምክንያት ነው የዜግነት ግዴታቸውና መማራቸው የጣለባቸው ኃላፊነት ሆኖ እያለ መሥዋዕትነት በሚጠይቅ ቦታ ሁሉ ላይ ምሁራኖቻችንን የማታዩዋቸው፡፡ በፖለቲካው(በእምነተ አሥተዳደሩ) ብቻ ሳይሆን በሰብአዊ መብቶች ጥበቃና ግንዛቤ ፈጠራ ዙሪያ በሚሠሩ ድርጅቶችም በመሳተፍ ሲሠሩ የማታዩዋቸው፡፡
ሳይበላ ሳይጠጣ ሳይለብስ ሳይጫማ ሳይማር ግብሩን ከፍሎ ለዚህ ያበቃቸውን ወገንና ሀገር ውለታቸው አለብኝ ዕዳ አለብኝ ብለው ቅንጣትም እንኳን የባለዕዳነት ስሜት ሳይሰማቸው የግል ቁሳዊ ጥቅማቸውን ብቻ በማሰብ ሀገር አስተዋጽኦዎቻቸውን እጅግ እየፈለገች እያለች “ስትፈልጊ ለኔ ስትይ አራት እግርሽን ንቀይ!” እያሉ እየጣሏት የሚሔዱት፡፡ ያልተማረ ገበሬ ብለን የምንንቃቸው ግን በሀገር ጥቅምና ክብር በመጣ ነገር ያለማወላወል ዐይናቸውን ሳያሹ አንዲት ነፍሳቸውን ለመስጠት ሲሰለፉ ነፍሳቸው መተኪያ የሌላት እንደሆነች እንኳን አያስመስሏትም፡፡ ይህ ከሕዝባችን ቁጥር 85 % ይይዛል የሚባለው የገጠር ሰው ባይኖር ኖሮ እኮ እንደከተሜውና ምሁር ተብየው አስተሳሰብ ቢሆንማ ይህች ሀገር ዛሬ ላይ በታሪክ እንደሁ እንጅ በእውን ባልተገኘች ነበር፡፡
ወደ ሁለተኛው አንበሳ አጭር ታሪክ ልለፍ ኦኬሎ አኳዬ ኡቸላ ያባላል የጋምቤላ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሆኖ እያገለገለokello እያለ 1996ዓ.ም. ይህ የአገዛዝ ሥርዓት በአኙዋክ ጎሳ ላይ የፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያጋለጠ ጀግና ነው፡፡ ኦኬሎ እንደነገረኝ ያ የዘር ማጥፋት ወንጀል በተፈጸመበት ወቅት መጀመሪያ ላይ 550 የአኙዋክ ተወላጆች ነበሩ እንዲጨፈጨፉ ትእዛዙን ላስፈጸመው በወቅቱ የክልሉ የጸትታና የደኅንነት ክፍል ኃላፊ ለነበረው ከአቶ ኦኬሎ በኋላ ደግሞ ርእሰ መሥተዳድር ሆኖ የቆየውና በኋላ ላይ አገዛዙ ይሄንን በአኙዋኮች ላይ የፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰውየው እንዳስፈጸመው አድርጎ ሲወነጅለው “እኔ የታዘዝኩትን ነው የፈጸምኩ ትእዛዙን ያዘዙኝ አቶ መለስ ናቸው እኔ የምጠየቅ ከሆነ ይህ ክስ በቅድሚያ እሳቸውን ተጠያቂ ያድርግ” ላለው ለአቶ ኡመድ ኡቦንግ የስም ዝርዝራቸው ተሰጥቶት የነበረው፡፡ ቀጥሎና በሁለተኛው ዙር ደግሞ የ250 ሰዎች ዝርዝር መጣ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ እኔ ነበርኩ ይላል አቶ ኦኬሎ፡፡
አቶ ኦኬሎ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ (ዶቸቬሌ) ጋዜጠኛ የነበረችውን ወ/ሮ አሰገደች በርታን አመስግኗት አይጠግብም፡፡ ነፍሴን ያተረፈችልኝ እሷናት ይላል፡፡ አቶ ኦኬሎ ምንም በማያውቀው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሐሰተኛ ዜና ለቆ ምንጩንም አቶ ኦኬሎን አድርጎ ስለነበር አንጋፋዋ በሳል ጋዜጠኛ ወ/ሮ አሰገደች በርታ ወደ አቶ ኦኬሎ ደውላ የዜናውን ትክክለኝነት ስትጠይቅ አቶ ኦኬሎ ፈጽሞ ሐሰት እንደሆነና ግጭቱ በአኙዋክና ኑዌር ጎሳዎች መሀከል የተፈጸመ ሳይሆን የመከላከያ ሠራዊቱ በአኙዋኮች ላይ የፈጸመው እንደሆነ ስለነገራት ወ/ሮ አሰገደች ይሄንን ዘገባ በጀርመን ድምፅ ራዲዮ ለቀቀችው፡፡ ያ ዜና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲለቀቅ አቶ ኦኬሎን ምሽቱን ሁሉ በስብሰባ ወጥረውት ስለ ነበረ አላየውም ነበር፡፡
ይህ ትክክለኛ ዜና በጀርመን ድምፅ ራዲዮ እንደተሰማ በማግስቱ አገዛዙ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን ጋዜጠኞች አምጥቶ ለጀርመን ራዲዮ የሰጠኸውን ቃል አስተባብልና መግለጫ ስጥ ይሉታል፡፡ እሱም የተናገረው ያየውንና የሚያውቀውን እንደሆነ በመግለጽ ይሄንን እንደማያደርግ ሲናገር በቅርብ ክትትል ስር አድርገውት እያለ ባገኛት ክፍተት ተጠቅሞ ወደ ሱዳን ተሰደደ ለ6 ቀናት በእግሩ ተጉዞም ሱዳን ድንበር ላይ ደረሰ ሱዳን ገብቶ ከዲፕሎማቲክ አካላት ጋራ ግንኙነት በማድረግ ወደ ኖርዌይ ወጣ ብዙም ሳይቆይ የኖርዌይ ዜግነትን ያዘ ባለቤቱንና ልጆቹንም አወጣ፡፡ አቶ ኦኬሎ እነኝህን ነገሮች ማሳካት ቢችልም አገዛዙ አርፎ አልተኛለትም ነበር፡፡ አቶ ኦኬሎ እንደነገረኝ ለአደጋ የሚዳርጋቸውን ከባድ ምስጢር ይዞባቸው እንደወጣ የተረዱት አቶ መለስ ዜናዊ አቶ ኦኬሎን እዚያ በሚኖርበት ሀገር ለአንዲት የዩኒሴፍ ሠራተኛ 10.5 ሚሊዮን ዶላር በመክፈል ሊያስገድሉት ሞክረው እንደነበር ይናገራል፡፡ ይህ ሙከራ ከከሸፈ በኋላም ወ/ሮ አዜብ መስፍን ለማፍያ ቡድን 6 ሚሊዮን ዶላር ከፍለው ልጀንና ሚስቴን ሊያስገድሉብኝ ሞክረው ነበር በማለት ይሄም እንደከሸፈ ይናገራል አቶ ኦኬሎ፡፡
አቶ ኦኬሎ በወገኖቹ ላይ በ21 መቶ ክ/ዘ በጠራራ ፀሐይ የተፈጸመው ግፍ እረፍት ስለነሳው ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ሆኖ በ2004ዓ.ም. GDM (Gambella Democratic Movement) የተሰኘ ፓርቲ አቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ እያለ ሌሎቹ የፓርቲው አባላት ዓላማችን መገንጠል ነው በማለታቸውና እሱ ደግሞ መገንጠልን ባለመፈለጉና መፍትሔም አይሆንም ብሎ በማመኑ በተፈጠረ የዓላማ ልዩነት ምክንያት ትቶ በመውጣት አምና ሊያዝ አካባቢ GDAM (Gambella Democratic Alliance Movement) የሚልፓርቲ መሥርቷል የኦኬሎ ሕልም ራስገዝ (self determination) ማለትም ወያኔ እያደረገው እንዳለው የውሸት ፌዴራሊዝም ሳይሆን ትክክለኛ ፌዴራላዊ አወቃቀር ያላት ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡ መገንጠል መፍትሔ እንዳልሆነ ጠንቅቆ ያውቃል እነ ደቡብ ሱዳንና ኤርትራን እየጠቀሰም ያስረዳል፡፡ የፌዴራሉ የክልል መንግሥታት የክልል አወቃቀር የብሔረሰቦችን አሰፋፈር መሠረት ማድረጉ ችግር ይኖረዋል ብሎ ስለሚያስብ ብሔረሰቦች እራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር እስከቻሉ ጊዜ ድረስ የክልል አቀወቃቀሩ የደርግ ዘመኑ ክፍላተ ሀገራት ቢሆን ችግር እንደሌለበትና ድንበርን መንስኤ አድርጎ ዘወትር የሚቀሰቀሰውን አሰልቺ የብሔረሰቦችንና የጎሳዎችን ግጭቶችን እንደሚያስወግድና ግጭቶቻችን ለማስወገድ መፍትሔ እንደሚሆንም ያምናል፡፡ 80 ብሔረሰች አሉ ተብሎ 80 ድንበር ያላቸው የክልል መንግሥታት ይኑሩ ማለት የማይታሰብና ሊተገበር የማይችል እንደሆነም በሚገባ ይረዳል፡፡ ከዚህም የተነሣ ነው ከከሸፈውና ወያኔም በአፉ ከማውራት በስተቀር አስተካክሎ ሊፈጽመው ካልቻለው ብሔርን መሠረት ያደረገ ከሚለው የወያኔ 9 የክልል መንግሥታት አወቃቀር ይልቅ ታሪክንና መልክአምድርን መሠረት ያደረገው 14ቱ ክፍላተ ሀገራት ጥሩ መፍትሔ ነው የሚለው፡፡
አቶ ኦኬሎ ፓርቲውን ከመሠረተ በኋላ ሱዳንና ኬንያ እየተዘዋወረ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ባገኘው አጋጣሚና መድረክ ሁሉ እያጋለጠ ፓርቲውንም እያስተዋወቀ ሲንቀሳቀስ እንዳለ አምና 2006ዓ.ም. ደቡብ ሱዳን በነበረበት ወቅት የደቡብ ሱዳን የደኅንነት ሰዎች በቁጥጥር ስር አዋሉት፡፡ የደቡብ ሱዳን የደኅንነት ሰዎች እኔንና ላገኛቸው እየፈለኳቸው የነበሩትን አራት ሰዎች እንዲሁም ሌሎች ሦስት ወያኔ የሚፈልጋቸውን አኙዋኮች አድርገው ለወያኔ በ23 ሚሊዮን ዶላር ሸጡን፡፡ የወያኔ ደኅንነቶች ወዲያውኑ ባዘጋጁት የጭነት አውሮፕላን (በረርት) ጭነው ጋንቤላ ከጋምቤላም ደብረ ዘይት አመጡንና ለመግደል ዝግጁ አድርገው እኔን ለብቻየ ሌሎቹን ሰባቱን አንድ ክፍል አሰሩንና ሄዱ፡፡ ከሰዓታት በኋላ አንድ የደኅንነት ሰው መጥቶ አቶ ኦኬሎ ስሕተት ሰርተናል የኖርዌይ ዜጋ መሆንህንም አናውቅም ነበር በማለት ከጓዶቹ ጋር ወደ ማዕከላዊ እንዲዛወር አደረጉት፡፡
እነ ኦኬሎን እግዚአብሔር ትረፉ ሲላቸው የደቡብ ሱዳን የደኅንነት ሰዎችና የወያኔ የደኅንነት ሰዎች ሸጠዋቸው አውሮፕላኑ ላይ ሲቀባበሏቸው ፎቶ ያነሡ ሰዎች ስለነበሩ ፎቷቸው (ምስለአካላቸው) ወዲያውኑ በተለያዩ መካነ ድሮች ተለቆ ስለነበርና ጉዳዩን ዓለም ስላወቀው እንዳሰቡት በስውር ገድለው ሊጥሉን ሳይችሉ ቀሩ በማለት ይናገራል ታጋይ ኦኬሎ፡፡ አቶ ኦኬሎ በማዕከላዊ ቆይታው ሦስቱንም ማጎሪያዎች አይቷል ለ17 ቀናት ጨለማ ክፍል ብቻውን ታስሯል ከዚያም ወደ ሳይቤሪያ ከሳይቤሪያም ወደ ሸራቶን ከሸራተንም አሁን እሱን ወዳገኘሁበት ቦታ ወደ ቅሊንጦ አዛውረውታል፡፡
አስቀድሞ ከሌሎች እስረኞች በኋላም ከራሱ እንዳረጋገጥኩት አንዴ ምን ሆነ መሰላቹህ የወሕኒ ቤቱ ኃላፊዎች እስረኞቹን ስለ ሽብርተኛነት ለማወያየት ሰብስቦ በነበረበት ወቅት የወሕኒ ቤቱ ኃላፊዎች ስለ ሽብርተኛነት ገለጻ ሲያደርጉ አንበሳው ኦኬሎ ይነሣና “ሽብርተኛ እናንተ ብቻ ናቹህ! ከእናን በስተቀር በዚህች ሀገር ሌላ ሽብርተኛ የለም! ጨፍጫፊም እናንተ ናቹህ!” እያለ በኃይል በስሜት ሲናገር እስረኛውም አብሮት በመጮህ ኦኬሎን በመደገፉ የወሕኒ ቤቱ ኃላፊዎች ጥለው እንዲወጡ አድርጎ ነበር፡፡ በዚህ ያቄሙት የወሕኒ ቤቱ ኃላፊዎች ኦኬሎን ወስደው እንደ እባብ ቀጥቅጠውታል በድብደባው ምክንያትም ሁለቱ ጣቶቹ እንደማይንቀሳቀሱ ስብራት እንደደረሰባቸው አሳይቶኛል፡፡ እኔ የታሰርኩት የነበረው እነኝህ ሁለት አንበሶች ባሉበት ክፍል ነው፡፡ ነገሩ ሆን ተብሎ ለተንኮል ይሁን ያጋጣሚ አላውቅም ሆን ተብሎ “ቢንጎ” ለማለት ከሆነም ለወያኔ ደኅንነቶች እሱውላቹህ ደስ ይበላቹህ ልላቸው እወዳለሁ፡፡
የዋና ዋናዎቹህ አናብስት ላጫውታቹህ ብየ ነው እንጅ ቅሊንጦ ጫካ ውስጥ ስንት ጀግኖች ስንት አንበሶች አሉ መሰላቹህ! ባሉበት አምላክ በሰላም በጤና ይጠብቃቸው፡፡ ጨለማው ነግቶ ለብርሃኑ እንዲያበቃቸው በጸሎታቹህ አስቧቸው፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

አሳዛኙ ብሔራዊ ውርደታችን

ኢትዮጵያ መንግስት አላት ወይ? የአሜሪካ አምባሳደር ለኢትዮጵያ መንግስት በቀይ ባህር ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሃዘን መግለጫ ላኩ።ኢህአዲግ/ወያኔ እስካሁን አንዳች አልተነፈሰም።Statement by Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia
Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia
በያዝነው ሳምንት መጀመርያ ላይ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች በየመን የባህር ዳርቻ፣ በቀይ ባህር ውስጥ ከሰባ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መስመጣቸው መሰማቱ ይታወቃል።ጉዳዩ በሀገር ቤት እና በመላው ዓለም በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ሃዘን አስከትሏል።
ከእዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያውያንን ልብ ያደማው ጉዳይ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ የዜና አውታሮች የተቀባበሉትን ጉዳይ ላይ አንዳች የሃዘን መግለጫ አለማሰማቱ ነው።በትናንሽ አደጋ ለሞቱ ለሌላ ሀገር ዜጎች የሃዘን መግለጫ በማውጣት እና በመላክ የሚታወቀው ኢህአዲግ/ወያኔ ለኢትዮጵያውያን ሞት አንዳች አልመተንፈሱ ሌላው የብሔራዊ ውርደታችን መገለጫ ነው።በሳውዲ ጉዳይ መንግስት እንደሌለን አውቀን ነበር።ዘንድሮም በቀይ ባህሩ አደጋ አረጋገጥን።በፌስቡክ ገፃቸው የእየእለቱን ውሎ የሚለጥፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሰሞኑን ከ 300 ሚልዮን ብር በላይ ወጣበት ስለተባለው በአሶሳ ስለነበረው ብሔር ብሄርሰቦች በዓል ማውሳታቸው ኢትዮጵያ መንግስት አላት ወይ? ብለው ብዙዎች እንዲጠይቁ ማስገደዱ አልቀረም።
ከእዚህ በታች በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ከሰባ በላይ ለሚሆኑት በቀይ ባህር ሕይወታቸው ላለፈው ኢትዮጵያውያን የሃዘን መግለጫ አወጣ።የኢትዮጵያ መንግስት ስለጉዳዩ እስካሁን ድረስ ምንም አላለም።
”ትናንት በየመን የባህር ዳርቻ ቀይ ባህር ውስጥ በሰጠመችው ጀልባ ሕይወታቸው ባለፈው ኢትዮጵያውያን የተሰማኝን ትልቅ ሃዘን ለኢትዮጵያ መንግስት እና ለሟቾች ቤተሰብ እገልፃለሁ።ልባችን ከሟቾች ቤተሰቦች እና ወዳጆች ጋር ሁሉ ነው” በኢትዮያ የአሜሪካ አምባሳደር ወ/ሮ ፓትሪሽያ ሃስላች
Source – US EMBASSY ADDIS ABABA
”I would like to offer my condolences to the government of Ethiopia and the families of the many victims, including Ethiopian citizens, who drowned in the tragic sinking of a boat off the coast of Yemen in the Red Sea yesterday. Our thoughts are with the families and friends of those who died.”Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia
ከእዚህ በታች ያለው ቢቢሲ አደጋውን አስመልክቶ የዘገበው ነው።

Yemen migrant boat carrying Ethiopians sinks killing 70

Source - BBC
A boat carrying African migrants has sunk off Yemen’s western coast, killing 70 people, Yemeni officials say.
The boat, carrying mostly Ethiopian migrants, sank off Yemen’s al-Makha port due to strong winds and rough waves, security officials said.
Tens of thousands attempt to cross the Red Sea into Yemen every year, often in rickety, overcrowded vessels. Hundreds have died making the journey.
Yemen is viewed by many migrants as a gateway to the Middle East or Europe.
The latest sinking occurred on Saturday, with reports of the incident emerging on Sunday.
The Red Sea crossing between the Horn of Africa and Yemen is one of the world’s major migration routes, BBC Arab affairs editor Alan Johnston says.
Migrants dream of finding jobs and better lives in rich places like Saudi Arabia – but they are in the hands of unscrupulous people smugglers and, too often, never reach the Yemeni shore, our correspondent adds.

In October, the UN refugee agency said that more than 200 people had died at sea in 2014 while attempting to reach Yemen.
“There have been frequent reports of mistreatment, abuse, rape and torture, and the increasingly cruel measures being adopted by smuggling rings seem to account for the increase in deaths at sea,” the UN said at the time.

ልማታዊ ሙስና? ለአንድ ካሬ ሜትር መሬት 305 ሺሕ ብር

ለአንድ ካሬ ሜትር መሬት 305 ሺሕ ብር
305
ባለፈው ዓርብ በተከፈተው የመሬት ሊዝ ጨረታ በአንድ ካሬ ሜትር 305 ሺሕ ብር ቀረበ፡፡ ይህ ዋጋ በከተማው ታሪክ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ የሊዝ ጨረታን የወቅቱ አነጋጋሪ ክስተት አድርጓል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ በርበሬ አካባቢ 449 ካሬ ሜትር ቦታ ለጨረታ ቀርቧል፡፡ በካሬ ሜትር የቀረበው ገንዘብ ሲሰላ ይህ አነስተኛ ቦታ 136.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ሆኗል፡፡ 20 በመቶ ብቻ የተከፈለበት ይህ መሬት ከነወለዱ እስከ 300 ሚሊዮን ብር በ30 ዓመት ሊደርስ እንደሚችል ባለሙያዎቹ ገልጸዋል፡፡ ይህ ክስተት ለአዲስ አበባ ሊዝ ሥሪት ባለሙያዎች እንዲሁም በጨረታው ለታደሙ ባለሀብቶች የቀረበው ዋጋ ብዥታን ፈጥሯል፡፡ በጨረታው ላይ ሁለተኛ ሆኖ የቀረበው ዋጋም ከዚህ ቀደም ቀርቦ የማያውቅ ሲሆን፣ የቀረበውም በካሬ ሜትር 288 ሺሕ ከ90 ሳንቲም ነው፡፡ “በአዲስ አበባ የሊዝ ዋጋ ላይ ቆም ተብሎ ካልታሰበ አደገኛ ውጤት ሊኖረው ይችላል፤” ሲሉ የአዲስ አበባ አስተዳደር የሊዝ ባለሙያ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
መርካቶ በርበሬ ተራ ለሚገኘው ለዚህ 449 ካሬ ሜትር ቦታ በካሬ ሜትር 305 ሺሕ ብር ያቀረበው ዝዋይ ኢንተርናሽናል የተባለ ኩባንያ ነው፡፡ ይህ ኩባንያ ቀደም ሲል ከዚህ ቦታ አጠገብ መሬት በሊዝ ገዝቶ የንግድ ማዕከል ያቋቋመ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ለዚሁ ቦታ በካሬ ሜትር 288 ሺሕ ከ90 ሳንቲም ያቀረበው ደግሞ ኤንኤስኤ የተባለ ኩባንያ ነው፡፡ ይህ ኩባንያም ቦታውን ማሸነፍ ባይችልም ያቀረበው ገንዘብ ግን በከተማው ታሪክ ቀርቦ የማያውቅ ነው፡፡ በከተማው ታሪክ ክብረ ወሰን ሆኖ የቆየው ከወራት በፊት በስምንተኛው ዙር ሊዝ ጨረታ ቦሌ አካባቢ ከኤድናሞል ወረድ ብሎ የሚገኝ ቦታ ነበር፡፡ ቦታው 158 ካሬ ሜትር ስፋት ሲኖረው፣ ለዚህ ቦታ በካሬ ሜትር 65 ሺሕ ብር ያቀረበው ኤስኤንአይ ትሬዲንግ ነው፡፡
በ11ኛው ሊዝ ጨረታ በካሬ ሜትር የቀረበው 305 ሺሕ ብር ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቦ ከነበረው 65,000 ብር በ4,692 በመቶ ብልጫ አለው፡፡ በርካታ የመሬት ሥሪት ባለሙያዎች ይህ ዋጋ ምናልባት ለዓመታት ክብረ ወሰን ሆኖ ይቆያል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸው፣ ነገር ግን በከተማው የሚገኙ አንዳንድ ነጋዴዎች የሚወስዱትን አደጋ መገመት የሚያስቸግር በመሆኑ በቅርቡ አይሻሻልም ማለት አይቻልም ብለዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ ገንዘብ በማንኛውም መመዘኛ ጤነኛ ኢኮኖሚያዊ አካሄድ አይደለም ካሉ በኋላ፣ ሁኔታው ቆም ተብሎ ሊታሰብበት የሚገባ ነው ይላሉ፡፡
አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለጨረታ የቀረበው ይህ ቦታ ብቻ ነው፡፡ ቦሌ ክፍለ ከተማ ላይ ደግሞ 57 ቦታዎች ለጨረታ ቀርበዋል፡፡ ሚሊኒየም አዳራሽ ጀርባ የወጡ ሁለት ቦታዎች ከፍተኛ ዋጋ ቀርቦላቸዋል፡፡
በዚህ ቦታ ለወጣ 400 ካሬ ሜትር ቦታ ቤተልሔም ብርሃን የተባሉ ባለሀብት፣ በካሬ ሜትር 55,244 ብር አቅርበዋል፡፡ ወ/ሮ መኪያ የተባሉ ባለሀብት ደግሞ ለ403 ካሬ ሜትር ቦታ በካሬ ሜትር 51,111 ብር አቅርበዋል፡፡
ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ሁለት ቦታዎች ለጨረታ የቀረቡ ሲሆን፣ 12,000 እና 15,000 በካሬ ሜትር ቀርቦላቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቦሌ ክፍለ ከተማ በብዛት ኮንዶሚኒየም ቤቶች እየተገነቡበት ባለው ቀጠና በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሠራተኞቹ መኖሪያ ቤት እየገነባ ባለበት አካባቢ 52 ቦታዎች ለጨረታ ቀርበዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ቦታዎች እስከ 15,000 ብር የቀረበላቸው ሲሆን፣ ራሕማ ጀማል የተባሉ ባለሀብት በዚህ አካባቢ በካሬ ሜትር 15,221 ብር ሲያቀርቡ ከዚሁ ቦታ አጠገብ ዘገየ ዘመዴ የተባሉ ባለሀብት 2,489 ብር አቅርበዋል፡፡
በዚህ አካባቢ ብዙም ጨረታ ወጥቶ የማያውቅ በመሆኑ የቦታውን ዋጋ ለመስጠት ባለሙያዎች ተቸግረው ነበር፡፡ በሁለቱ ባለሀብቶች መካከልም የቀረበው ዋጋ ልዩነቱ ከዚህ መነሻነት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ በዚሁ አካባቢ በተነፃፃሪ ዝቅተኛ ዋጋ አቅርበው አሸናፊ የሆኑ አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ውብነሽ ሀብቴ በካሬ ሜትር 3,189 ብር፣ አሰፋ ታምሬ በካሬ 2,689 ብር፣ ብርቄ መለስ 1,805 ብር ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ እንዲሁ የዋጋ መነሳት የታየበት ሲሆን፣ በካሬ ሜትር 18,000 ብር ቀርቧል፡፡
የአዲስ አበባ የመሬት ዋጋ ንረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄድ ላይ ሲሆን፣ ለዚህ ምክንያቱ አስተዳደሩ እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ በቅርብ ከኢብኮ ጋር ባደረጉት ቆይታ የመሬት ዋጋ እንዲንር መንግሥት እንደማይፈልግና አልሚዎች ያላቸውን ካፒታል መሬት በመግዛት ሳይሆን፣ ለልማቱ በማዋል ማደግ እንደሚኖርባቸው አስታውቀው ነበር፡፡ ነገር ግን የከተማው የመሬት ዋጋ በየጊዜው እየጨመረ በመሄድ ላይ መገኘቱ ለበርካታ ኢኮኖሚያዊ ችግሮ ሊዳርግ እንደሚችል በመግለጽ ባለሙያዎች ማሳሰቢያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ (ምንጭ: ሪፖርተር)

በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት እናወግዛለን !!! – ግንቦት 7

g7 logoበአብዛኛው በወጣት ወንዶችና ሴቶች የተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነበት የዘጠኝ ፓርቲዎች ኅበረት፣ “ነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ” የተሰኘ የአንድ ወር መርሀ ግብር አውጥቶ፤ ችግሮችን ተጋፍጦ አብዛኛውን ተግባራዊ አድርጓል። የመርሀ ግብሩ አቢይ አካል የነበረውና በህዳር 27 እና 28 ሊከናወን ታድቆ የነበረው የ24 ሰዓት የአደባባይ ተቃውሞ ግን በአገዛዙ የኃይል እርምጃ ምክንያት በታቀደው መንገድ ሊከናውን አልቻለም። የህወሓት ቅልብ የሆኑት ሲቪል የለበሱ ሰላዮችና የፌደራል ፓሊስ በተቃውሞው ተሳታፊዎች ላይ ኢሰብዓዊ የሆነ ጥቃት ፈጽመዋል።
ከጅምሩ፣ የፓርቲዎቹ ኅበረት የተቃውሞ ማሳወቂያ ደብዳቤውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለማስገባት የገጠመው ችግር የህወሓት አገዛዝ የመንግሥትን መዋቅር ለፓርቲ ሥራ፤ የመንግሥት ተቀጣሪዎችን ደግሞ እንደ ህወሓት አገልጋዮች የሚጠቀምባቸው መሆኑ አንዱ ማሳያ ሆኗል። ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ማሳወቅ የፈለጉት ፓርቲዎች ህወሓት የዘረጋውን አፋኝ ሥርዓት የሚታገሉ በመሆናቸው ብቻ ደብዳቤዓቸውን የሚቀበል እንኳን አጥተው ተጉላልተዋል። ለሰልፉ ቅስቀሳ ማድረግም በራሱ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ወጣቶች ተንገላተዋል፣ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል። ያም ሆኖ ውጣ ውረዶች ታልፈው ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ. ም. ደረሰ።
የኅበረቱ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና ጥሪውን የሰማ ሕዝብ ወደ መስቀል አደባባይ ማምራት ሲጀምር ሲቪል የለበሱ የአገዛዙ ታጣቂዎች እና ፌደራል ፓሊሶች ከሰንደቅ ዓላማዎችና መፈክሮች ባለፈ አንዳች ነገር ያልያዙትን እድሜያቸው ከሃያዎች ያልዘለሉ ውድ የኢትዮጵያ ልጆችን ደብድበዋል፤ ብዙዎቹም አፍነው በአሰቃቂ ሁኔታ እያንገላቱ ወደ እስር ቤቶች ወስደዋል። ወጣቶች ተወልደው ባደጉበት አገር፤ ስሜታቸውን በነፃነት ለመግለጽ በመድፈራቸው ብቻ በጭካኔ ተረግጠዋል፤ ተፈንክተዋል፤ እጅና እግሮቻቸው ተሰብሯል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ይህ የህወሓትን ፋሺስታዊ እርምጃ አጥብቆ ይቃወማል። ግንቦት 7፣ ህወሓት ከስልጣን እስካልተወገደ ድረስ እንዲህ ዓይነቱን ፋሺስታዊ ተግባር መፈፀሙን የማይተው እኩይ ኃይል እንደሆነ ያውቃል፤ በዚህም ምክንያት የትግላችን ግብ ህወሓትን ማስወገድና በምትኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት መመሥረት መሆን ይኖርበታል ብሎ ያምናል፤ ለዚህም ይታገላል።
ግንቦት 7፣ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ.ም. “መብቶቻችንን በህወሓት ዘረኛ አምባገነኖች አናስነጥቅም” በማለት አደባባይ የወጡ ወጣቶችን ጽናት ያደንቃል። ህወሓት የሚለውን ሳይሆን የይስሙላ ህጉ የፈቀደላቸውን ለማድረግ በመድፈራቸው በህወሓት የህግ ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ የሚደረገውን ትግል አንድ እርምጃ ወደፊት አራምደውታል።
እያንዳንዱ የፓለቲካ ድርጅት ከዚህ ኩነት የሚወስዳቸው ተጨማሪ ትምህርቶች ቢኖሩም የሚከተሉትን ነጥቦች ብዙዎችን ያስማማሉ ብለን እናምናለን።
1. ህወሓት በምንም ዓይነት ቢሆን የያዘውን ስልጣን ለሕዝብ ፈቃድ ማስገዛት አይፈልግም፤
2. ህወሓት አገራችን ወደ ትርምስ እየገፋት እንደሆነ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፤
3. ስልጣኑን የሚያሳጣው ከመሰለው እና አቅሙ እስካለው ድረስ ዘግናኝ እርምጃዎችን ከመውሰድ አይመለስም፤
ከህወሓት አገዛዝ መገላገል የሚቻለው ተገዶ ሲወገድ ብቻ ነው። ህወሓት እንዲወገድ ደግሞ የመጨቆኛ አቅሙ መዳከም ይኖርበታል። ህወሓትን የማስወገጃ አማራጭ መንገዶች ብዙ ሲሆኑ ተቀናጅተው ቢሠሩ የበለጠ ውጤታማ ይሆናሉ ብለን እናምናለን፤ “ሁለገብ ትግል” የምንለው የትግል ስልት ጭብጥ ይህ ነው። “እምቢ ለነፃነቴ” ብሎ የተነሳ ሕዝብ ህወሓትን ምን ያህል እንደሚያስደነግጥ በተደጋጋሚ ታይቷል። ህዳር 27ን መንደርደሪያ አድርገን በመውሰድ ከዚህ በተሻለ ለተደራጀ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና አመጽ ራሳችን እናዘጋጅ።
በዚህ አጋጣሚ ግንቦት 7፣ ለመከላከያ ሠራዊት እና ፓሊስ አባላት ተደጋጋሚ ጥሪዎችን ማድረግ ይሻል። የመከላከያ ሠራዊት እና ፓሊስ አባላት እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ በህወሓት ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ የተበደላችሁ መሆኑን እናውቃለን። የህወሓት ሹማምንት ከሆኑ አዛዦቻችሁ መላቀቅና ራሳችሁን ነፃ የማውጣት ኃላፊነት የወደቀው በእናንተው በራሳችሁ ላይ ነው። ሠራዊቱ ራሱን በራሱ ነፃ ማውጣት ይኖርበታል። የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ህወሓት መወገዱ የማይቀር በመሆኑ ሠራዊቱ ራሱን ነፃ አውጥቶ ከሕዝብ ጋር ካልወገደ እጣ ፈንታው የተሸነፈ ሠራዊት መሆን ነው። ከዚህ በላይ የሠራዊቱ አባል እየደበደበ ያለው የራሱን ልጅ፣ ወንድሙን ወይም እህቱን እንደሆነ ይወቅ። ይህ ወሳኝ ጊዜ ነው እያንዳንዱ የሠራዊቱ አባል በግል ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ሊሰማው ይገባል።
በሁሉም ዓይነት የትግል ዘርፎች የኢትዮጵያ ወጣቶች በስፋት እየተቀላቀሉ መሆኑ ተስፋ ሰጪ ነው። ጊዜው የለውጥ ነው። የተለያዩ ስትራቴጂዎች ተደጋግፈው እንዲሄዱ መደረግ ያለበት ወቅት ላይ ነን። በህዳር 27 ቀን በህወሓት ቅልብ ሰላዮችና የፌደራል ፓሊሶች አማካይነት የደረሰው ጉዳትና የፈሰሰው ደም ለፍትህና ለነፃነት የተከፈለ ዋጋ ነው። ህመማችሁ ህመማችን፤ ትግላችሁ ትግላችን ነው። የተለያዩ መንገዶች ወደ ነፃነት አደባባይ እያመሩ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!