Friday 21 March 2014

UDJ to call a “Day of Vociferation” demo in Addis Abeba

The opposition Unity for Democracy and Justice (UDJ) party is to call a vociferation demonstration in Addis Abeba to oppose to the social service problems in Addis Abeba.
The fact that roads constructed with a large amount money have broken few days after they were inaugurated, lack of alterative roads during construction, lack of public transport, stagnation of work in the city, the dysfunctional state of EthioTelecom, which the government calls a “cash cow”, the constant power and water blackout and cuts that has forced children to go distant places to fetch water instead of attending schools are some of the reasons that necessitated the call for a “Day of Vociferation.”
UDJ on its press release stated that EPRDF, which is administering the city now, is responsible for the difficult life that city dwellers are leading and it is incapable of administering the City. The Addis Abeba Council of the Party has said that the “Day of Vociferation” will be held within one month.
It has also called the residents of Addis Abeba to come out en masse and voice their opposition against the regime.
Ethiopians often complain that they are grappling huge problems of power and water cuts, high cost of living, telecommunication service and network disruptions and social issues. The government of EPRDF claims that the economy has been growing at 11% every year.

ለነፃነት የምናደርገው ትግል በህገ ወጥ እስርና ማስፈራሪያ አይደናቀፍም! (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ)

‹ማርች-8›› የሴቶችን ነጻነትና እኩልነት እንዲሁም ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ የሚከበር የሴቶች ቀን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህን በዓል አስመልክቶ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፈው ዕሁድ የካቲት 30/2006 ዓ.ም ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት የጎዳና ላይ ሩጫ ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ የሐገራችንም ሆነ የዓለም ሴቶች የነጻነት ቀናቸውን በሚያከብሩበት ዕለት እንደሌሎች ሴቶች ሁሉ የሰማያዊ ፓርቲ አአባላትም አላማውን ደግፈው በዕለቱ ቀኑን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በዚህ በሴቶች የነጻነት ቀን በስርዓቱ ላይ የሚነሱ ብሶቶችን ካሰሙት ተሳታፊዎች ውስጥ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሚገኙበት ሲሆን፣ በተለየ መልኩ በእነዚህ አባላቶቻችን ላይ ያነጣጠረ የአፈሳ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡
Semayawi wetatoch
ሰማያዊ ፓርቲ እንደዚህ አይነት ህዝባዊ መድረኮችን ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ህዝብ ላይ የሚደርሰው በደል በማጋለጥ መብት እና ለአገራችን ብሄራዊ ጥቅም በመቆም በገዥው ፓርቲ ተደጋጋሚ ህገ ወጥ እርምጃ ሲወሰድበት ቆይቷል፡፡ የተደረገው ህገ ወጥ ድርጊት ከዚሁ ፓርቲው ለህዝብና ለአገር መቆሙን ተከትሎ እየደረሰበት ያለው የከፋ የጭቆና አካል ነው፡፡
ህገ ወጥ ድርጊቱን የበለጠ አስገራሚ የሚያደርገውም አባላቶቻችን የታሰሩበት ምክንያት ‹‹የጣይቱ ልጅ ነን ፣ ህወሓት /ኢህአዴግን ምን ያህል ከታሪክ ጋር የተጣላ መሆኑን ከማሳየቱም በተጨማሪ አባላቶቻችን ለማስር እንግልት ወቅት በአባላቶቻችን ላይ የደህንነት አካላት ነን በሚሉ ግለሰቦች ማስፈራሪያና ዛቻ ተፈፅሞባቸው፡፡ አንዳንዶቹ አባላቶቻችን በሌሊት ጭምር ከእስር ክፍላቸው ወጥተው ቃል እንዲሰጡ ተከልክለዋል፡፡ ሙከራ ተደርጎባቸዋል፡፡ ከጠያቂ ቤተሰቦቻቸውና የትግል ጓደኞቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ተከልክለዋል፡፡ የተጠረጠሩበት ክስ የማያስከስስና በነፃ የሚያስለቅቃቸው መሆኑ በየካ ክፍለ ከተማ ፍትህ ፅ/ቤት አቃቤ ህጎች ከተገለፀላቸው በኋላም በድጋሚ ፍርድ ቤት በማቅረብ እያንዳንዳቸው 1300 ብርና የመታወቂያ ዋስ በዋስትና እንዲቀርቡ ተጠይቀዋል፡፡
ፓርቲያችን ይህ እርምጃ በአባላቱ ላይ የተወሰደው ሰማያዊ ፓርቲ በመላው አገሪቱ መዋቅሩን እያደራጀና ህዝብን ከጎኑ እያሰለፈ ባለበት ወቅት መሆኑ፣ የህዝብ ድጋፍ የሌለው ገዥው ፓርቲ በስበብ አስባቡ ሰማያዊ ፓርቲን ከወዲሁ ለማዳከም የወሰደው ነው ብሎ ያምናል፡፡ በተለይ የምርጫ ወቅት እየቀረበ መሆኑን ተከትሎ ይህን ህገ ወጥ እርምጃ መውሰዱ አሁንም ቢሆን የአገራችን የፖለቲካ ምህዳር ምን ያህል እየጠበበ እንደሄደ ያሳያል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ መቼም ቢሆን ይህንና መሰል የአገዛዙን አፈናዎች አጥብቆ የሚያወግዛቸውና የሚታገላቸው መሆኑን እየገለጸ በሴቶች የነጻነት ቀን ያለአግባቡ ታስረው ህገወጥ እርምጃ በአባላቶቻችን ላይ የወሰዱትን የፖሊስ አካላት በህግ የምንጠይቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በተጨማሪም ይህን መሰሉ የህገ ወጦች እርምጃ ሳይገታን ትግላችንን አጠናክረን የምንቀጥል መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በአዲስ አበባ “የእሪታ ቀን” በሚል ስያሜ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ ወሰነ!! ከአዲስ አበባ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ!!

ከአዲስ አበባ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ!
ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!!
ሌሎች አገሮች ለዋና ከተሞቻቸው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የየአገሮቻቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ማሳያ በማድረግ አለም አቀፍ ተቋማትንና ጎብኝዎችን በመጋበዝ የከተሞቻቸውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ግን በብዙዎች የአፍሪካ አገራት የአህጉሪቱ መዲና ተደርጋ የምትጠቀሰው አዲስ አበበባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ኋላ አየተጎተተች ለኑሮ ምቹ ከሆኑ ከተሞች ምድብ መቀላቀለ ተስኗት ለነዋሪዎቿ የማትመች የፈተና ምድር ሆናለች፡፡
ኢህአዴግ ራሱን ልማታዊ መንግሥት በማድረግ ከሰየመበት ቅጽበት አንስቶ በልማት ሰበብ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ቤተሰቦቻቸውን ከሚያስተዳድሩበት የንግድ ቦታ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ በከተማይቱ እንዲነሱ የተደረጉት የንግድ ሱቆች በአብዛኛው በኪራይ ቤቶችና በቀበሌ ስም የተመዘገቡ በመሆናቸውም በሱቆቹ በመነገድ ይተዳደሩ የነበሩ ቤተሰቦች ባዶ አጃቸውን እንዲቀሩ ተደርገዋል፡፡
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን የመንገድ ዝርጋታ የተነሳ የተጠና ሥራ ባለመሰራቱ ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ የወጣባቸው መንገዶች ለምረቃ በበቁ በጥቂት ቀናት ልዩነት እንዲፈርሱ ተደርገዋል፡፡ የከተማው ነዋሪ ለሚጠቀምባቸው የመጓጓዣ አውታሮች ተለዋጭ መንገድ ባለመዘጋጀቱም ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል፡፡ ትራንስፖርት ማግኘት በሁሉም አካባቢዎች አስቸጋሪ በመሆኑ የከተማይቱ የሥራ እንቃስቃሴ ተዳክሟል፡፡ መንግሥት ‹‹የምትታለብ ላም›› በማለት የሚጠራው የኢትዮ ቴሌ ኮም አገልግሎት የለም የሚባልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ጭምር በኢትዮጵ ቴሌኮም የተንቀራፈፈ አገልግሎተ የተነሳ ባንኮችና የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለደምበኞቻቸው ተገቢውን ግልጋሎተ ማበርከት አልቻሉም፡፡
የከተማይቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር የተወሰኑ ሠራተኞች ችግር እንደሆነ ተጠቁሞ ሠራተኞች ለስንብት ቢዳረጉም የኤሌክትሪክ መቆራረጥና ለረጅም ግዜ መጥፋት የከተማይቱ ኢንዱስትሪዎች ፤ንግድ ተቋማትንና ነዋሪውን እያማረረና ህይወቱን እያመሰቃቀለ ከመሄድ ውጭ ምንም አይነት ለውጥ አልታየበትም፡፡ በከተማይቱ ውሃ ማግኘት እንደ ትልቅ እድል መቆጠር ጀምሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የከተማይቱ 75% ነዋሪ ውሃ እንደሚያገኝ ቢናገሩም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን በተቃራኒው ሆኗል፡፡ ጊዜያቸውን በትምሀርት ገበታቸው ላይ በመገኘት ማሳለፍ ይገባቸው የነበሩ ተማሪዎች ውሃ ለመቅዳት ረዥም መንገድ ለመጓዝ በመገደዳቸው የትምህርት ጊዜአቸው እየተበደለ ይገኛል፡፡
በአጠቃላይ ከተማይቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የከተማይቱ ነዋሪ ለሚገፋው አስቸጋሪ ህይወት ተጠያቂ ነው፡፡ ድርጅቱ አገሪቱን የመምራት ብቃት እንደሌለውም የወቅቱ የአዲስ አበባ ሁኔታ አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከተማይቱ ነዋሪ እየገፋው የሚገኘውን ፈታኝ ህይወት በማጥናት ህዝቡን በተለይም የከተማውን እና የዙሪያ አካባቢዋን ነዋሪ በማደራጀት በቅርቡ ‹‹የእሪታ ቀን›› በማለት ሰይሞ በ1ወር ጊዜ ውስጥ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ የወሰንን መሆኑን እየገለፅን የአዲስ አበባና አካባቢዋ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፉ በሚደረግበት ቀን በነቂስ በመውጣት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለፅ እንዲዘጋጁ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ድል የህዝብ ነው
መጋቢት 11 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም
አዲስ አበባ1920578_827198673963262_1874916504_n

Wednesday 19 March 2014

ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ስነምግባር ደንብ እንደማይፈርም አስታወቀ

በ2002ቱ ጠቅላላ ምርጫ መቃረቢያ ላይ ከ60 ያላነሱ ሀገር አቀፍና ክልል አቀፍ ፓርቲዎችም እንገዛበታለን ብለው ከፈረሙበት በኋላም ሕግ ሆኖ የወጣው የስነ-ምግባር ደንብ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደማይፈርም አስታወቀ። የፓርቲው ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለሰንደቅ እንደተናገሩት፤ የምርጫ ስነ-ምግባር ደንብ በሀገሪቱ ፓርላማ ሕግ ሆኖ እስከወጣ ድረስ ፓርቲው እንደገና የሚፈርምበት ምክንያት የለም ብለዋል።
Yilkal Getnet
ኢህአዴግን ጨምሮ ዘጠኝ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች በሚሳተፉበት የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለመግባት እንደ ቅድመ ሁኔታ እየቀረበ ያለው የምርጫ የስነ-ምግባር ደንብ በቅድሚያ ፈረሙ የሚባለውን “እኛ እንደቁምነገር አንቆጥረውም” ሲሉ የመለሱት ኢንጂነሩ ከኢህአዴግም ጋር የሚደረግ ማናቸውም ውይይት በቅድመ ሁኔታ ላይ መመስረት እንደሌለበት ገልፀዋል። በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ውይይትም ሆነ የጋራ ምክር ቤት የምክር ቤቱን ነፃነት ጥያቄ ላይ የሚጥል ስለሆነ ለመነጋገርና ለመወያየት የምርጫ ስነ-ምግባር ደንብ ፊርማ እንደቅድመ ሁኔታ መቅረብ የለበትም ብለዋል።
“አሁን ተቋቁሟል የሚባለው የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በራሱ ብዙ ችግር ያለበት፣ ኢህአዴግና ደጋፊዎቹ ተሰብስበው የሚቀልዱበት እንጂ ሐቀኛ ሆኖ በነፃነት ውይይት የሚደረግበት ም/ቤት አይደለም” ሲሉ ኢንጂነር ይልቃል ተናግረዋል። ስለሆነም ፓርቲያቸው ለጊዜው በፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት የመሳተፍ ፍላጎት የለውም ብለዋል።
ከኢህአዴግ ጋር ለመነጋገርም ሆነ ተቀራርቦ ለመወያየት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መሆን እንዳለበት የጠቀሱት ኢንጂነሩ ሕጋዊ ፓርቲዎች ሆነን በምርጫውም እንደምንሳተፍ ሰለሚታወቅ ሌላ የተለየ ቅድመ ሁኔታ አያስፈልግም፣ ወደፊርማ የሚያስገባ ሕጋዊ መሠረት የለም ብለዋል።
ኢንጂነር ይልቃል ወደፊርማ የሚያስገባ ሕጋዊ መሠረት የለም ቢሉም፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የምርጫ ስነ-ምግባር ለመደንገግ በወጣው አዋጅ 662/2002 ዓ.ም አንቀጽ 21(6) እና (7) ላይ አዋጁ እንዲወጣ ተስማምተው በፈረሙ ፓርቲዎች እንደሚቋቋምና የስነ ምግባር ደንቡ ሲቀርፅ በልዩ ልዩ ምክንያት ያልተሳተፉ ሌሎች ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤቱ የሚያወጣውን የስምምነት ሰነድ መፈረም እንዳለባቸው ያስገድዳል።
ይሁን እንጂ፤ “የምንፈርመው ነገር የለም” ያሉት ኢንጂነር ይልቃል ፓርቲያቸው በዚህ ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎት እንደሌለው አረጋግጠዋል። በምርጫውም የሚኖራቸው ተሳትፎም ደንቡን በመፈረምና አለመፈረም ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በአጠቃላይ ገዢው ፓርቲ የፖለቲካውን መድረክ ጨምድዶ በያዘበት ሁኔታ ነው ብለዋል። አሁን ባለው ሁኔታም ምርጫው ፍትሐዊ ይሆናል ብለው እንደማያስቡ ነገር ግን መብቱን የማስከበር የሕዝቡ እንጂ የኢህአዴግ መልካም ፈቃድ አይደለም ሲሉ አስረድተዋል።
blue party
በቅርቡ ኢህአዴግ በመወከል ወደ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት አባልነት የተዛወሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ደስታ አስፋው በበኩላቸው ማንኛውም ፓርቲ የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ለመግባት በማመልከቻ መጠየቅ እንዳለበት ሀገር አቀፍ ፓርቲ መሆንና በጥር ወር 2002 ዓ.ም የወጣውን የፖለቲካ ፓርቲዎችን የምርጫ ስነ-ምግባር ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 662/2002 ዓ.ም መፈረም አለበት ብለዋል። ፓርቲዎቹ ወደ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሲመጡ የስነ-ምግባር ደንቡን እንዲፈርሙ የሚያስገድደው በፓርቲዎች ስምምነት ሕግ ሆኖ የወጣው አዋጅ እንጂ ኢህአዴግ አለመሆኑንም አያይዘው ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ተተኪ ሴቶች ትውልድ መነሳሳት!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል!”
ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ እንደገና ወኔ የተሞላበት የትግል መንፈሱን በማደስ ጥንካሬውን አሳየ !
Semayawi Women  Demonstrationእ.ኤ.አ ማርች 9/2014 የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጀቶ በነበረው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶችም ተሳትፎ አድርገው ነበር፡፡ ከዴሞክራሲያዊ ምርጫ ባፈነገጠ መልኩ በኃይል በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጠው ስልጣንን የሙጥኝ በማለት ከህግ አግባብ ውጭ በህዝብ ላይ ደባ በመፈጸም ላይ የሚገኙትን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ዕኩይ ምግባር የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘበው በማሰብ ወጣት ሴቶቹ እውነታውን ያለምንም መሸፋፈን በማጋለጥ እምቢ አሻፈረኝ በማለት ተቃውሟቸውን ለዓለም በይፋ አሰምተዋል፡፡ እንዲህ በማለትም ተቃውሟቸውን አጠናክረዋል፣
“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል! ተርበናል! ነጻነት እንፈልጋለን! ነጻነት እንፈልጋለነ! እስክንድር ይፈታ! አንዷለም ይፈታ! አቡባከር ይፈታ! ርዕዮት ትፈታ! የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ! ፍትህ እንፈልጋለን! ነጻነት! ነጻነት! ነጻነት! አትከፋፍሉን! ኢትዮጵያ አንድ ነች! አንድ ኢትዮጵያ! ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል! ውኃ ናፈቀን! መብራት ናፈቀን! ተርበናል!…“
ለሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች ባርኔጣዬን ዝቅ በማድረግ ከወገቤ ጎንበስ በማለት ያለኝን አድናቆት ልገልጽላቸው እፈልጋለሁ፡፡ በእነርሱ እጅጉን ኮርቻለሁ፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ሰማያዊ ፓርቲን ለምን እንደደገፍኩ እና በጽናትም ከፓርቲው ጎን ለምን እንደምቆምኩ በርካታ ሰዎች ጥያቄዎችን አቅርበውልኝ ነበር፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ቁጥር አንድ አድናቂ (አንደኛ ቲፎዞ) ለምን እንደሆንኩ ማንም ቢሆን ጥያቄዎች ካሉት/ካሏት ይህንን ቪዲዮ (እዚህ ይጫኑ)  እንዲመለከቱት እጋብዛለሁ፣ እናም መልሱን ከእዚያው ያገኙታል፡፡
አረመኔው ገዥ አካል በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያን ወጣት ሴቶች እና ወንዶች በዱላ እየደበደበ እና እንደ እባብ እየቀጠቀጠ ሁሉንም የጭቆና ዓይነቶች በእነርሱ ላይ እየተገበረ ባለበት ሁኔታ ከዳር ቆሜ ለመመልከት ህሊናዬ ሊፈቅድልኝ አይችልም፡፡ የመናገር መብታቸውን ተጠቅመው ሀሳባቸውን ለመግለጽ በመሞካራቸው ምክንያት ብቻ የኢትዮጵያ ወጣቶች ሲታሰሩ፣ ሲደበደቡ፣ ሲሰቃዩ እና ግፍ ሲፈጸምባቸው በዝምታ አልመለከትም፡፡ በወጣቶቹ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እና ስቅይት የእነርሱ ድምጽ በመሆን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እናገራለሁ፡፡
ወጣት ሴቶቹ ተቃውሟቸውን የገለጹት በሰላማዊ መንገድ ነው፡፡ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በማሰማታቸውም በጨካኙ የገዥ አካል ማሰቃየት ተፈጽሞባቸዋል፡፡ በሰላማዊ እና ከአመጽ በጸዳ መልኩ በአገሪቱ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ሲሉ ነው በአሁኑ ጊዜ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በመሰቃየት ላይ የሚገኙት፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች እና አባላት እንደማንኛውም ሰው ሁሉ የ5 ኪ/ሜ ሩጫውን ተቀላቀሉ፡፡ በሰላማዊ መንገድ እሮጡ እና ከማጠናቀቂያ ቦታው ደረሱ፡፡ ምንም ዓይነት ህግ አልጣሱም፡፡ አንድም ጠጠር አልወረወሩም፡፡ በማንም ላይ ጥቃት አልፈጸሙም፡፡ ምንም ዓይነት ሁከትን በሚያመጡ ተግባራት ላይ አልተሳተፉም፡፡ ከአንድ ሺህ በላይ ሯጮች በተሳተፉበት በዚያ ሩጫ ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች እና አባላት በመሳተፋቸው (ወይም በሌላ ምክንያት) በአንድም ሰው ላይ ጉዳት አልደረሰም፡፡ ቅንጣት ያህል ንብረት ላይ ጉዳት አልተፈጸመም፡፡ አንድም ባለስልጣን ማስፈራሪያ አልደረሰበትም ወይም ደግሞ የጥቃት ሰለባ አልሆነም፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች ምንም ዓይነት የዘለፋ ቃላት እንኳ አልተጠቀሙም፡፡ ሁሉምን ነገር በሰላማዊ መንገድ፣ ሞገስን በተላበሰበ መልኩ እና በሚያስደምም ሁኔታ ነው ያከናወኑት፡፡ እነዚያ ጀግና ወጣት ሴቶች የምርጥ ተደናቂነት ተምሳሌት ቀንዲል ናቸው! በእነዚህ ወጣቶች እጅግ ኮርቻለሁ እናም ባርኔጣዬን ዝቅ በማድረግ አድናቆቴን ልገልጽላቸው እፈልጋለሁ፡፡
በዕለቱ የተከበረውን በዓል ኃላፊነት በመውሰድ ያዘጋጀው የገዥው አካል የሴቶች፣ የህጻናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ነበር፡፡ የገዥው አካል የዕለቱ መፈክር “የምርጥ ሴቶች የመጀመሪያው ዙር የ5 ኪ/ሜ ሩጫ“ የሚል ነበር (ምን ለማለት እንደተፈለገ ግልጽ ባይሆንም)፡፡ ገዥው አካል ዕለቱ ከ10,000 በላይ ሴቶችን እና ልጃገረዶችን ያሳትፋል በማለት ዲስኩር አድርጎ ነበር፡፡ ገዥው አካል በበዓሉ ዕለት ሴቶች እንዲሳተፉ በስፋት የጥሪ ማሳሰቢያ ሲያደርግ ጠንካራዎቹ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣት አመራሮች ማሳሰቢያውን ሊሰሙት እንደሚችሉ እረስቶት ኖሯል፡፡ መንፈሰ ጠንካራዎቹ ወጣት ሴቶች ግን ማድረግ ያለባቸውን ነገር በሚያስደምም ሁኔታ አደረጉት፡፡ ወጣት ሴቶቹ ለገዥው አካል ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሳይሆን ብጫ ካናቴራ በመልበስ ተልዕኳቸውን ሲፈጽሙ ታይተዋል፡፡ እዚያ የተገኙት ለመሮጥ ነበር፣ ለነጻነታቸው ለመሮጥ፣ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ለመሮጥ፣ የኢትዮጵያ እስረኞች እንዲፈቱ ለመሮጥ፣ በመሰቃየት ላይ ላለው እና ተስፋ ለራቀው ህዝብ ትኩረት በመሳብ  ለመሮጥ፡፡ ወጣቶቹ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች አረመኒያዊ እና ጨካኝ እየተባለ በሚታወቀው ገዥው አካል ፊት ደፋርነታቸውን ማሳየት መቻላቸው ብቻ አይደለም አስደናቂ የሚሆነው ሆኖም ግን የእራሳቸውን የብልህነት ፈጠራ በመጠቀም የስርዓቱን ዕኩይ ምግባር በማጋለጣቸው ጭምር እንጅ፡፡
የአምስት ኪሎ ሜትሩ ሩጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ሰባት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፣ ተደብድበዋል እንዲሁም ለእስር ተዳርገዋል፡፡ የሰብአዊ መብት እረገጣው ሰለባ ከሆኑት ውስጥ፡ ሜሮን ዓለማየሁ፣ ምኞቴ መኮንን፣ መታሰቢያ ተክሌ፣ ወይኒ ንጉሴ፣ ንግስት ወንድይፍራው፣ ወይንሸት ሞላ፣ እና እመቤት ግርማ ይገኙበታል፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ የሚገኙ  ጌታነህ ባልቻ (የድርጅተ ጉዳይ ኃላፊ)፣ ብርሀኑ ተክለያሬድ (የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ) እና አቤል ኤፍሬም (የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባል) የተባሉ ሌሎች ሶስት ወጣት ወንዶች ደግሞ እስረኛ ሴቶች ያሉበትን ሁኔታ ለመጠየቅ  በሄዱ ጊዜ በቁጥጥር ስር ውለው እነርሱም ለእስር ተዳርገዋል፡፡
የጣይቱ እና የምኒልክ ልጆች በይስሙላው/በዝንጀሮዎች (ካንጋሩ ኮርት) ፍርድ ቤት፣
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የይስሙላ ፍርድ ቤት ስርዓት በአገሪቷ ዘርግቶ በመተግበር ላይ ይገኛል በማለት ሁልጊዜ ስናገረው የቆየሁት ጉዳይ ነው፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የተመሰረቱት “ክሶች” የገዥው አካል የይስሙላ ፍርድ ቤቶች እንዴት ባለ ሁኔታ እየተካሄዱ እንዳሉ ከምንም ጥርጣሬ በላይ በግልጽ ያመላክታሉ፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ የተመሰረቱት ክሶች በባዶው የትወና መድረክ ላይ ብቻ የሚከናወኑ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የይስሙላው ፍርድ ቤት  እ.ኤ.አ ማርች 14/2014 ያደረገው የሁለተኛው ቀን “የችሎት” ትወና በሳሙኤል በኬት፣ ኢጀን ኔስኮ፣ ጂን ገነት ወይም ካፍካ ላይ የተደረገ ያለቀለት የትያትር ትወና ይመስል ነበር፡፡ የህጋዊነት ትወናው በምግባር የለሾች፣ በስም የለሾች፣ የማስተዋል ብቃት በሌላቸው፣ በህሊና የለሾች፣ በሀሳብ የለሽ ደነዞች፣ታማኝነት በሌላቸው ፖለቲከኞች እና ዋናው ተግባራቸው ህዝቡን ማሰቃየትን እና መከራ ማሳየትን እንደመርሀ የሚከተሉ አስመሳዮች በግልጽ በማይታይ መልኩ የሚጦዝ የውሸት የህጋዊነት ሽፋንን ተላብሶ እየተተገበረ ያለ ኃላፊት የጎደለው እና የተዋረደ የመድረክ ተውኔት ነው፡፡ ፍትህ ፊት የሌላት እና ቅርጿ የተበላሸ የይስሙላ ስርዓት ዘርግታ ትገኛለች፡፡ ፍትህ በሚያስገርም ሁኔታ በመደምሰሷ ምክንያት አካል የላትም፡፡ በኢትዮጵያ የፍትህ ፊት እና አካል በይስሙላው ፍርድ ቤት በርቀት በቁጥጥር ስልት መጠቀሚያ መሳሪያ ተይዞ የሚመራ እና በጌቶቹ ትዕዛዝ እንዲያደርግ የተሰጠውን ብቻ ያለምንም ኃፍረት ተቀብሎ እንደበቀቀን የሚደግም የሮቦት ዳኛ (አንደየተሞላ አሻንጉሊት) የተሰማራበት ሆኗል፡፡ የፍትህ አካሉ በዘራፊዎች ቁጥጥር  ስር ዉሎአል፡፡
በ “ችሎቱ” ክፍል እንደ አንድ ተመልካች ዘገባ ከሆነ “የማታ” በሚል ስም የሚታወቅ “የፖሊስ መርማሪ” የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች የጣይቱ ልጆች ነን (የ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንግስት የነበሩት) እና የእምዬ ምኒልክ ልጆች ነን (በ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንጉስ እና የንግስት ጣይቱ ባለቤት የነበሩት) በማለት በአደባባይ በመጮህ በሽብር ተግባር ላይ ተዘፍቀው ታይተዋል በማለት የምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ “መርማሪው” በተጨማሪም ተከሳሾቹ እየተራቡ ያሉ መሆናቸውን እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ማለትም ርዕዮት፣ እስክንድር፣ አንዷለም እንዲሁም ሌሎች እንዲፈቱ” እያሉ በአደባባይ ጩኸት እያሰሙ ነበር ብሏል፡፡ እንግዲህ ይኸ ነው በሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች ተፈጸመ የተባለው “የሽብር ተግባር” ይዘት፡፡
የችሎት ስነስርዓቱ ከታቀደለት በአንድ ሰዓት ዘግይቶ ነው የተጀመረው፣ ምክንያቱም የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች በሰልፉ ላይ ለብሰዋቸው የነበሩትን ካናቴራዎች ወደ ችሎቱ ሲቀርቡ እንዲቀይሯቸው ቢጠየቁም ለመቀየር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነበር፡፡ ፖሊሱ እስረኞቹን ከነካናቴራቸው ወደ ፍርድ ቤቱ እንዲቀርቡ መፍቀድ የፖለቲካ እምቢተኝነትን አምኖ እንደመቀበል ያስቆጥራል የሚል እምነት አደረበት፡፡ እንደ ዘገባው ከሆነ ሴቶቹ ወደ “ፍርድ ቤቱ” ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት የለበሷቸውን ካናቴራዎቻቸውን በማስገደድ እንዲቀይሩ ለማድረግ ፖሊ ሁከት ፈጥሮ እንደነበሩ ታውቋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች እስከሚወሰዱ ድረስ በተያዙበት ቦታ እንዲቆዩ ተደርገዋል፡፡ “የፍርድ ቤቱ” ክፍል በተመልካች ተጨናንቋል፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችም በሙሉ ተገኝተው ነበር፡፡
የፌዴራል አቃቤ ህግ ጉዳዩን ለመመርመር እና መረጃ ለማሰባሰብ ተጨማሪ የ14 ቀናት ጊዜ እንዲሰጠው ሴት እስረኞችም በእስር እንዲቆዩ ጠየቀ፡፡ (በቁጥጥር ስር የማዋል ልምድ እና ተጠርጣሪን በእስር ቤት አውሎ ለጥፋተኝነት መረጃዎችን ለመፈለግ መሞከር የገዥው አካል የይስሙላው ፍርድ ቤት አሰራር ዋናው መለያ ባህሪው ነው፡፡ አንድ ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት የሚደረገው አሳፋሪ ዘዴ በእያንዳንዱ ከፍተኛ የወንጀል ጉዳይ ከሁለት ደርዘን ወይም ከዚያ በላይ በሚሆኑ በቀድሞዎቹ ባለስልጣኖች እና ባለፈው ዓመት ደግሞ በንግዱ ማህበረሰብ አባላት ላይ ሙስና በሚል ሰበብ የተደረገው እስራት ሲታይ ገዥው አካል ካለፉት አስርት ዓመታት በላይ ሲፈጽመው የቆየ ተግባር መሆኑን ነው፡፡ አቃቤ ህጉ እስከ አሁንም ድረስ ለሙስናው መረጃ ፍለጋ በሚል ሰበብ ጊዜ እየነጎደ በሄደ ቁጥር እነርሱ በእስር ቤት ተረስተዋል፣ ገዥው አካል ጉዳዩን ለሁለት ዓመታት ያህል ምርመራ እየተካሄደበት ነው በማለት በይፋ የገለጸ ቢሆንም)፡፡
የይስሙላ አቃቤ ህጉ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የዋስትና መብት መሰጠት እንደሌለበት ተከራክሯል፣ ምክንያቱም “ዋስትናው ከተሰጠ አሁን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ያሉት ታሳሪዎች መረጃዎችን ያጠፋሉ፣ እናም ምስክሮች የምስክርነት ቃላቸውን እንዳይሰጡ በማንገራገር እና በማስፈራራት እንዳይመሰክሩ ሊያደርጉ ይችላሉ” ብለዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ መከላከያ ጠበቃ አቶ ዓለሙ ጎቤቦ (በእስር ቤት የምትገኘው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናን ያተረፈችው ርዕዮት ዓለሙ አባት) ጉዳዩ የፖለቲካ ባህሪ ያለው ስለሆነ ልጆቹ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከውጭ ሆነው እንዲከራከሩ እንዲደረግ በማለት የክርክር ጭብጣቸውን አቅርበዋል፡፡ ቀጥለውም እንደ ህጉ ከሆነ ደንበኞቼ የዋስትና መብት እንዲያገኙ ይፈቅዳል፣ እናም ይህንን ላለማድረግ እየተከናወነ ያለው የዳኞቹ ተቃውሞ ተጠርጣሪዎቹን በእስር ቤት ለማማቀቅ የተደረገ ደባ ነው ብለዋል፡፡ “ዳኛው” የዋስትና ጥያቄውን አልተቀበሉትም፣ እናም የዳኝነት ሂደቱን ቀጠሉ፡፡ (ባለፉት በርካታ ከፍተኛ የሆኑ የፍርድ ቤት ጉዳዮች የፍርድ ሂደት ላይ እ.ኤ.አ የ2006 የቅንጅት ፓርቲ አመራሮችን “የፍርድ ሂደት” ጉዳይ ጨምሮ ገዥው አካል ምስክሮችን በማስፈራራት፣ ጉቦ በመስጠት፣ በሙስና አማልሎ ተጽዕኖ በማሳደር እና ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ መልኩ ቃለመሃላን በመጣስ የውሸት የምስክርነት ቃል እንዲሰጡ በማድረግ ዕኩይ ምግባር ላይ ተዘፍቆ ይገኛል)፡፡
እንደ ፍርድ ቤት ተመልካች ታዛቢዎች ከሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች በእስር ቤቱ ውስጥ በቁጥጥር ስር ሆነው እያለ ከህግ አግባብ ውጭ በፖሊስ እና በደህንነት ኃላፊዎች አካላዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው እንዲሁም የማስፈራራት ሰለባ እንዲሆኑ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ለይስሙላው ፍርድ ቤት ተናግረዋል፡፡ በሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ላይ ቅጥረኛ እና ሰላይ እንዲሆኑ ብዙ ገንዘብ ቀርቦላቸዋል፡፡ ከተከሳሾቹ መካከል ትዕግስት ወንድይፍራው የተባለችው ባለፈው እኩለ ሌሊት ላይ ሶስት ወንድ ፖሊሶች እርሷ ወደታሰረችበት ክፍል መጥተው እንድትወጣ ትዕዛዝ እንደሰጧት “ለፍርድ ቤቱ” ተናግራለች፡፡ ከኃላፊዎች መካከል አንደኛው ዱላ በማንሳት በማወዛወዝ ካልተባበረች በስተቀር እስክትሞት ድረስ እንደሚደበድቧት ማስፈራራታቸውን ገልጻለች፡፡ ሌሎችም ሴቶች ተመሳሳይ የማስፈራሪያ ዛቻ እንደተፈጸመባቸው ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ ሴቶቹ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የሚያደርጉትን ንቁ የአባልነት ተሳትፎ እና ጓዳዊ የትግል መንፈስ እንዲተው እና ከድጊታቸው እንዲታቀቡ በመደብደብ እንዳዋረዳቸው እና እንዳስፈራራቸው ያላቸውን ምሬት ገልጸዋል፡፡ በተመልካቾች ዕይታ “ብቃት የለሽ” ተብሎ የተፈረጀው የዕለቱ የችሎት ዳኛ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቅቆ እ.ኤ.አ ለመጋቢት 18/2014 እንዲቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት አሰናብቷል፡፡
በይስሙላው ፍርድ ቤት ያለውን ኃይል መገዳደር፣
የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶችን በቁጥጥር ስር የማዋል እና የፍርድ ሂደታቸው እንዲታይ ማድረግ እ.ኤ.አ በ2015 ይካሄዳል ተብሎ በሚታሰበው አገር አቀፋዊ ምርጫ ሰማያዊ ፓርቲ እንዳይሳተፍ እና ለመዝጋት በደጋኑ የተተኮሰ የመጀመሪያው ቀስት ነው፡፡ ገዥው አካል ለሰማያዊ ፓርቲ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልጽ እና ግድፈት ሊደረግበት የማይችል ሀቅ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ በአንክሮ ሲታይ በቅርቡ ባረፉት በአቶ መለስ ዜናዊ የተጻፈው የባለ ሶስት ድርጊት የረዥም ጊዜ ተውኔት ተከታይ ነው፡፡ እነዚህ የተውኔት ድርጊቶችም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ ድርጊት አንድ፡ “ምርጫው” ከመድረሱ በፊት የሰማያዊ ፓርቲ, አመራሮችን እና አባላትን የይስሙላውን ፍርድ ቤቶች በመጠቀም ማሰቃየት፣ ማስፈራራት፣ ሽባ እና አቅመቢስ ማድረግ፡፡ በዚያ መንገድ ሌላ ተጨማሪ የኃይል እርምጃዎች ቢወሰዱ በህዝቡ ዘንድ የተለመደው አካሄድ እንጅ የበቀል እርምጃ አይደለም የሚል እንደምታ እንዲኖር ከመሻት የመነጨ ነው፡፡ ድርጊት ሁለት፡ ምርጫው ከመድረሱ ጥቂት ወራት በፊት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን ሰብስቦ በእስር ቤት ማጎር፡፡  ይሄም የይስሙላውን ፍርድ ቤት አንደውነት የፍርድ ሸንጎ የሚሰራ ለማስመሰል ነው፡፡ ድርጊት ሶስት፡ ከምርጫ በኋላ እ.ኤ.አ በ2005  (1997 ምርጫ) የተደረገውን  ጭፍጨፋ ድርጊት መድገም ነው፡፡!
የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን የህግ ሂደት እና ጥቃት በተመለከተ ሁለት አማራጮች አሉ፡፡ 1ኛ) በይስሙላው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ላይ ተስፋ በመቁረጥ እራስን መነቅነቅ እና በመሰላቸት ጥሎ መሄድ 2ኛ) እንደ ኪልኬኔ አገር ድመቶች ከይስሙላው ፍርድ ቤት ጋር ጎሮሮ ለጉሮሮ መተናነቅ እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን መብት ማስከበር፡፡
ገዥው አካል ኢትጵያውያን እና ሌሎች በይስሙላው ፍርድ ቤት የውሸት ማስመሰያ ምክንያት እራሳቸውን በመነቅነቅ ሁሉንም ነገር ይተውታል ወይም ደግሞ ትችት በመስጠት ብቻ ጥለው ይሄዳሉ የሚል እሳቤ ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ ገዥው አካል በጊዜ ሂደት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችም እንደ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ አንዷለም አራጌ፣ አቡባከር አህመድ እና ሌሎችም  በእስር ቤት ታጉረው “ይረሳሉ” የሚል ስሌት አለው፡፡ ገዥው አካል የይስሙላው የፍርድ ቤት ማስፈራሪያ ዘመቻ በከፍተኛ ውጤታማነት እና ብቃት ላይ ተመስርቶ የሚቀጥል ላለመሆኑ ትንሽም እንኳ ቢሆን ጥርጣሬ የለዉም፡፡
የሰላማዊ ትግል ዋና ዓላማው የጨቋኙን አካል ተቋማት እና ህጎች በመጠቀም በጨቋኙ አካል ላይ ትግሉን በሰላማዊ መልኩ በማፋፋም መቀጠል ነው፡፡ በአጠቃላይ መልኩ ሲታይ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያለው ምንም ዓይነት የተፈጸመ ስህተት የለም፡፡ በገዥው አካል የይስሙላው ፍርድ ቤቶች ዘንድ የፍትህን ጥላ እንኳ ማግኘት እንደማይችል ማንም መገመት ይችላል፡፡ ማንም ቢሆን በውሸት እምነት ላይ በተመሰረተው የይስሙላው ፍርድ ቤት ፍትህ ሰበብ መሰቃየት የለበትም፡፡ ወደፊት ምን ሊከሰት እንደሚችል በእርግጠኝነት እናውቃለን፡፡ የክስ ሰነዱ ቀደም ሲል ተጽፎ ተዘጋጅቷል፣ በግልጽ ለመናገር ቀደም ሲል የነበረዉን የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ክስ ስማቸውን በመለወጥ፣ በማደስ እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን በማካተት የክስ ሰነዶቹ እነዚህን ለመዳኘት በስራ ላይ ይውላሉ (በግልጽ አባባል ለማጥቂያነት ይውላሉ)፡፡
ያንን ትያትር ቀደም ሲል አይተነዋል፡፡ ክስ የቀረበባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት በየጥቂት ሳምንታት ልዩነት ከማጎሪያ እስር ቤቶች ወደ የይስሙላው ፍርድ ቤት እንዲመላለሱ ይደረጋል፡፡ የገዥው አካል አቃቤ ህግ ማስረጃ ለመፈለግ (የሩጫው ዕለት የተጠናቀቀ ስለሆነ እና ሌላ ተጨማሪ ማስረጃ ማግኘት የተሳሳተ እና ውኃ የሚቋጥር ባይሆንም) በሚል ስልት ብዙ የማዘግየት ስራዎችን በመስራት የተለመደውን የገዥውን አካል የበቀልተኝነት የሱስ ጥማት ለማርካት ጥረት ያደርጋል፡፡ የዋስትና መብት ጥያቄዎች ተከልክለዋል፣ ሺህ ጊዜ የሚጠየቁ ቢሆንም፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች ይደበደባሉ፣ ህግወጥ አያያዝ ይፈጸምባቸዋል፣ እናም በእስር ቤት የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ይፈጸምባቸዋል፡፡ እርስ በእርሳቸው ላይ መተማመን እንዳይኖርም ጫና ይፈጸምባቸዋል፡፡ ህሊናቸውን እንዲሸጡ ገንዘብ እና ሌላ ሌላም ነገር ይሰጣቸዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲን ከፍተኛ አመራሮችን እንዲክዱ ላቅ ያለ ዋጋ የሚያወጡ ጌጣጌጦችን ይሰጧቸዋል፡፡ በጓደኞቻቸው፣ በፓርቲ አባላት እና አመራሮች እንዳይጎበኙ ክልከላ ሊጣል ይችላል፡፡ ለብቻ በአንድ ክፍል ውስጥ ሊታሰሩ ይችላሉ፡፡ የህክምና እርዳታ እንዳይደረግላቸው ክልከላ ሊደረግ ይችላል፡፡ በገዥው አካል በተቀጠረ ባለሙያ እንደተገለጸው እነዚህ እስረኞች  “በሚከረፋው እስር ቤት” የገሀነም ህይወት እንዲገፉ ሊደረግ ይችላል፡፡ ይህ ጉዳይ ለብዙ ጊዜ ማለትም እ.ኤ.አ በ2015 እስከሚደረገው አገር አቀፍ “ምርጫ” ድረስ ቀጣይነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ዘዴው ቀላል ነው፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ሃሳብ ማስቀየስ፣ ማሸማቀቅ፣ ማስፈራራት፣ ከመሰረታዊ ዓላማቸው እንዲርቁ ማድረግ እና በአጠቃላይ መልኩ ደግሞ ምርጫ እየተባለ ከሚጠራው የይስሙላ ምርጫ ተሳትፏቸውን ሽባ ማድረግ ነው፡፡
ገዥው አካል የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ያለምንም ውይይት በፍጥነት ወደ እስር ቤት የመውሰዱን ሁኔታ በተመለከተ በእራሱ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች ለምን ሊጠየቅ እና ሊሞገት እንደሚገባው አራት አሳማኝ ምክንያቶች አሉ፡፡ በመጀመሪያ የጅምላ ሰብአዊ መብት ረገጣው ተግባራዊ እንዲሆን የሚያግዙት የገዥው አካል ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች (በተለይም የምራብ መንግሥታት) እነርሱ በሚያደርጉት ልገሳ ድርጊት እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ በተጨባጭ እንዲያዩት ይገደዳሉ፡፡ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲስፋፋ እና ሰብአዊ መብት እንዲጠበቅ ደንታ አንደማይሰጣቸው የታወቀ ነው፡፡ ሁለተኛ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የይስሙላ የፍርድ ሂደት በእራሱ በይስሙላው ፍርድ ቤት ላይ አንዲፈረጅበት ማድረግ ያስፈለጋል፡፡ ገዥው አካል እራሱ ለይስሙላው የፍርድ ቤት ሂደት መቅረብ አለበት፡፡ ሶስተኛ የይስሙላው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ዛሬ በፍትህ ወንበር ላይ ተቀምጠው (እና ሌሎች ከመጋረጃ ጀርባ ተቀምጠው በዳኝት ወንበር ላይ የተሰየሙትን ዳኞች ጣቶች የሚጠመዝዙ) በእራሳቸው ዳኝነት ነገ እንደሚዳኙ በመገንዘብ ከፍተኛ ተቃውሞ መኖር አለበት፡፡ ዛሬ ከህግ አግባብ ውጭ ለመፍረድ በወንበር ላይ የተቀመጡት ሰዎች ከፍትህ ረዥም ክንድ ሊያመልጡ እንደማይችሉ የኑረምበርግ የፍርድ ሂደትን፣ የካምቦዲያ ፍርድ ቤት ልዩ የፍርድ ቤት ሂደትን፣ የሩዋንዳ የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደትን፣ የደቡብ አፍሪካ የእውነት እና የዕርቅ ኮሚሽንን፣ የቻርለስ ቴለር የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደትን እና የቦካሳን እና ሌሎች የአገር ውስጥ የፍርድ ሂደቶች ሊያስታውሱ ይገባል፡፡ ሁኔታዎች ሁልጊዜ ይገለባበጣሉ፡፡ ስለ ሁኔታዎች መገለባበጥ ጉዳይ እስቲ ደጋግማችሁ አስቡ፡፡ ሁልጊዜ ይገለባበጣሉ!
ከደቡብ አፍሪካ ታሪክ ብዙ ቁም ነገሮችን ልንማር እንችላለን፡፡ እ.ኤ.አ በ1964 የአፓርታይድ ገዥ አካል የአፍሪካ ኮንግረስ መሪዎችን እና ሌሎች የጸረ አፓርታይድ ተሟጋቾችን ኔልሰን ማንዴላን፣ ዋልተር ሲሱሉ፣ ጎቫን ኢምቤኪ፣ ራይሞንድ ሃላባ፣ አህመድ ካትራዳ፣ ኤሊያስ ሞሶሌዲ እና ቢሊ ኔይር ሰብስቦ በይስሙላው የአፓርታይድ የፍትህ ችሎት ፊት ገተራቸው፡፡ እነዚህ ሰባት አመራሮች እንደ “ጣይቱ ሰባት” የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሁሉ በአፓርታይድ የይስሙላ ፍርድ ቤቶች ፍትህን እናገኛለን የሚል እምነት አልነበራቸውም፡፡ ሆኖም ግን መሰረተ ቢስ ክሱን አጥብቀው ተቃውመውታል፡፡ ይህንንም በማድረጋቸው  ለደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላው ዓለም ታሪክ ሰርተዋል፡፡ የሰባቱ የጸረ አፓርታይድ መሪዎች የሪቮኒያ የፍርድ ሂደት ለዛሬዋ ደቡብ አፍሪካ ፍትህ መስፈን መሰረትን የጣለ ነው፡፡
አራተኛው እና ምናልባትም በጣም ጠቃሚው ነገር የይስሙላውን ፍርድ ቤት አጥብቀን መዋጋት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በህግ የበላይነት ለሚያምኑ ሁሉ ለህጉ ተገዥ ላልሆኑት ወንጀለኞች የህይወት እና የመተንፈስን ያህል ጠቃሚ መሆናቸውን ሊያስተምሩ የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ በህግ የበላይነት ላይ እምነት ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው ስለወንጀለኞች ማስተማር እና መጮህ ያለባቸው፡፡ እራሱ ያወጣቸውን እና ያጸደቃቸውን ህጎች የሚደፈጥጥ ወሮበላ መንግስት በእራሱ እና በህግ የበላይነት ላይ ንቀትን የሚፈለፍል ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ  የህግ የበላይነትን ለመያዝ እና ለመንከባከብ ከማንም የተሻለ መሆን አለበት፡፡
“የጣይቱ ሰባት የህግ ጥበቃ ፈንድን (ድጎማ/ዝክር)” እንደግፍ፣
Semayawi Party Legal Defense Fund 2ሁሉንም አንባቢዎቼን “ለጣይቱ ሰባት የህግ ጥበቃ ፈንድ (ድጎማ/ዝክር)” እንድታዋጡ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ የሰኞ ትችት መጣጥፌን ለበርካታ ዓመታት ስታነቡ የቆያችሁ በርካታ ወገኖቼ እንዳላችሁ እገነዘባለሁ፡፡ የሰኞ ትችት መጣጥፌ አሁን ስምንተኛ ዓመቱ መሆኑ ነው፡፡ አንዳንዶች ከእኔ ጋር በሁሉም ነገር በሀሳብ የማይግባቡ እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ እንደዚሁም በርካታ ለመቁጠር የሚያስቸግር ብዛት ያላቸው አንባቢዎቼ ደግሞ ቢያንስ በጥቂት ነገሮች ላይ ከእኔ ሀሳብ ጋር እንደሚስማሙ እገነዘባለሁ፡፡ የእኔ አቤቱታ የቀረበው ለእነዚህኛዎቹ ወገኖቼ ነው፡፡  በኢትዮጵያ በገዥው አካል የይስሙላው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት እየተሰቃዩ ያሉትን “የጣይቱ ሰባት” ጀግኖችን በመርዳቱ ጥረት እያንዳንዳቸው ማገዝ እንዲችሉ ያቀረብኩትን ሀሳብ በመደገፍ በተግባር እንዲያሳዩ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ እርዳታ እንዲያደርጉም በአጽንኦ እማጸናለሁ፡፡ ምንም ትንሽም ቢሆንም እንኳን ስጋት አይደርባችሁ፣ ትልቅ ጋን በትንሽ ጠጠር ይደገፋል ነውና፡፡ ባለፉት ዓመታት ምን ለመስራት እንዳቀድኩ አድናቆታቸውን የገለጹልኝ በርካታ ኢትዮጵያዊያን/ት ወገኖቼን በተለያዩ ጊዚያት አግኝቸ ነበር፡፡ ምንም ይሁን ምን ለሰራሁት ሁሉ ምስጋናን አልሻም፣ በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብት ያለመሻሻል ሁኔታን ስመለከት ካሁን የበለጠ ሺ አጥፍ መሆን የሆነ ስራ መስራት ነበረብኝ በማለት አራሴን ወቅሳለሁ፡፡
የዛሬ ሰባት ዓመት በዚሁ ወር “ትንሿ ወፍ እና የጫካው እሳት: የዲያስፖራው ማህበረሰብ የሞራል ትረካ” በሚል ርዕስ ስር በትችት መጣጥፌ ላይ ምን ለመስራት እንዳሰብኩ ለአንባቢዎቼ ተናግሬ ነበር፡፡ በዚህም መሰረት ማድረግ የምችለውን ሁሉ እያደረግሁ ነው፡፡ አሁን አንባቢዎቼን መጠየቅ የምፈልገው ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ ነው፡፡ እስቲ በጥሞና አስቡት ወገኖቼ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ትናንሽ ወፎች አንድ ላይ ተባብረው በመስራት የጫካን እሳት መግታት ይችላሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የ”ጣይቱ ሰባት” ጀግኖች በአረመኔው ገዥ አካል የእሳት ማቀጣጠያ ጉድጓድ ውስጥ ናቸው፡፡ ሲቃጠሉ መመልከት አለብን ወይም ደግሞ ከእነርሱ ጎን በመቆም ታግለን ለድል መብቃት አለብን፡፡ “ለጣይቱ ሰባት የህግ ጥበቃ ፈንድ(ድጎማ/ዝክር)” እርዳታችሁን እንድታደርጉ እማጸናለሁ፡፡ ለወደፊቱ የኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች ተቆርቋሪነታችሁን አሁኑኑ በተግባር አሳዩ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲን ሴት ጠይቁ…
Free the Taitu Seven Amharicከቀድሞዋ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ማጊ ታቼር ጋር በብዙ ነገሮች ላይ እንደማልስማማ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሯ በሴቶች የፖለቲካ አመለካከት ላይ በነበራቸው እምነት ምንም ዓይነት ያለመስማማት አዝማሚያ አልነበረኝም፡፡ “በፖለቲካው ዓለም የተነገረ ምንም ነገር በፈለጋችሁ ቁጥር ወንድን ጠይቁ፡፡ የተሰራ ምንም ነገር በፈለጋችሁ ጊዜ ግን ሴትን ጠይቁ“ ነበር ያሉት፡፡ ሰለሆነም ለእነዚህ ወጣት ሴት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት አንድ ነገር እናድርግ፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሴቶች እሩጡ፣ እሩጡ…! ለነጻነት የምታደርጉትን ሩጫ በጽናት ቀጥሉበት…

stop arresting semayawi party women's

on this year,The international women's day theme was" equality for women is progress for all" celebrated on march 8 ,2014. on this day thousands of event held all world to mark the economic, political and social achievement of womens.

It is obviously that empowered women contribute to the health and productivity of whole families and communities.more over the achievement of full equality between womens and men is very important for the advancement of the society.

As we know, the young innocent womens of semayawi party have been arrested during 5km run that is held in addis ababa on the international womens day celeberation. during the day of march 8 the young semayawi party members and supporters demand their rights,justice and equalty in a peaceful way but the TPLF cruel and oppressive regime have been subjected to sever beatings and arresting semayawi party members and supporters.

TPLF party has been one of the most evil organization that accused  innocent civilians. I am proud of what has been contribute for freedom, justice and equalty on the day. Finally we need to come together to defeat this oppresive regime.free all political prisoners and innocent civilians in ethiopia.
we ethiopians never stop our struggle until we get freedom.

justice for all

Berhanu taye
 

Monday 17 March 2014

TPLF Security Agent Points Gun at Arrested Female Activist

March 17, 2014
Semayawi Party (Blue Party) updated its supporters and the world about the arrested party leaders and female activists prison experience.
Semayawi Party- Ethiopia
Lets share you some of the news from the prison we are disgusted with!
A day before one of the girls called out late at night, the security guard took her to a room where there was a man namely Sami (Samson I think) who claim to be from security force and ordered her to sit. The talk was started with threatening and tricking. She reported to us that he told her they cannot be successful with peaceful struggle and asked what the Blues are trying to do if that does not work.Emebet Girma, turned 18 this year is on of the arrested female activists
Emebet Girma, turned 18 this year was quite smart one, she explained to him “all the Blue members and supporter would not do such an act and we stand and struggle peacefully all the way till we are all arrested or killed for freedom with love and truth that for sure will set them free”… the replay that he got from the young girl irritates him and took out his gun and put it on the table… “I wasn’t disturbed,” she said.
After a pause he pointed the gun at her and threatened her. She said, “he asked me what if he shoots me, and I told him to go ahead.” The brave young women told us this in the narrow window that ables visitors communicate with while the guards are watching every move and hear every word. While we talk one of the police was looking at us repulsively trying to warn us to stop with a scary facial expression. Yet she remained still and continued.
“After some filthy threatening he started to talk to me as young girl who must act like the rest of the girls out there,” she said… and added he even asked her phone number after trying to sweetly talk to her.
Past the drama she was returned to her cell hearing partially begging and somehow threatening speeches behind her, followed by the so called security force member ‘Sami’ and the same guard that took her out.
We will keep you updated for more!

የጠፋውን የማሌዥያ አውሮፕላን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፤ (ከዚህ በፊት 5 አውሮፕላኖች ጠፍተው እንደነበር ያውቁ ኖሯል?)

ከአትላንታው አድማስ ራድዮ
ስለ ማሌዢያው የበረራ ቁጥር 370፣ የተሰወረ አውሮፕላን መዘገብ እጅግ ከባድ ነው። ምክንያቱም ነገሮች በየደቂቃው ይቀያየራሉና። ገና ሲጀመር፣ አውሮፕላኑ ለመጨረሻው ጊዜ ድምጽ ያሰማበት ሰአት ልክ አልነበረም፣ ከዚያ ቀጥሎ ሁለት ጥቁሮች በሃሰት ፓስፖርት ተሳፍረዋል ተባለ፣ ጥቂት ቆይቶ ጥቁር አይደሉም፣ ኢራናውያን ናቸው ተባለ፣ .. ከዚያ በኋላ 6 ሰዎች አውሮፕላኑ ውስጥ ሊገቡ ካሉ በኋላ ሃሳባቸውን ቀይረዋል ተባለ፣ ጥቂት ቆይቶ ስድስት አይደሉም 2 ናቸው፣ እነሱም ገና ከቤታቸው ሳይወጡ ሃሳባቸውን የቀየሩ ናቸው ተባለ ….፣ ከዚያ ደግሞ አውሮፕላኑ ከጠፋ ከ 48 ሰአት በኋላ የአንዳንድ ተሳፋሪዎች ስልክ ይጠራል ተባለ . ጥቂት ቆይቶ ፣ ውሸት ነው የማንም ስልክ አይጠራም ተብሎ ተነገረ …፣ ከዚያ በኋላ ቻይናዎች በአንድ የቻይና ባህር ላይ የአውሮፕላኑ ስባሪን አይተናል አሉ ተባለ ..፣ ጥቂት ቆይቶ ውሸት ነው አላዩም በሚል ተስተባበበለ።

እያንዳንዱ የሚነገር ጉዳይ ልብ የሚያንጠለጥል ቢሆንም፣ በዚህ በዓለማችን የበረራ ታሪክ እጅግ ውስብስብና አሰገራሚ የሆነ መሰወር ጉዳይ ሁሉም መላምቱን ለመስጠት ቢቸኩል የሚፈርድ አልነበረም። እንደተባለው አውሮፕላኑ በቴክኒክ ችግር አይደለም ድምጹን ያጠፋው፣ እንደተባለው ካቅሙ በላይ የሆነ ነገር ገጥሞትም አይደለም።
ምናልባት ያለፉትን ሰባት ቀናት የተለያዩ ነገሮችን ሰምታችሁ ይሆናልና ቀጥታ ወደፊት በመፈናጠር ዛሬ ጉዳዩ ከደረሰበት ነገር እንጅምር። ከዚያ በኋላ ከዚህ በፊት የጠፉ አውሮፕላኖችን ታሪክ እናሳያችኋለን።
ዛሬ ጠዋት የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአየር ሃይል ሃላፊያቸው ያሉበትን ደረጃ ለመናገር ብቅ ብለው ነበር። በነሱ መረጃ መሰረት ዛሬ የተነገረው ትልቁ ነገር አውሮፕላኑ በቴክኒካል ችግር ሳይሆን ሆን ተብሎ ድምጹን ማጥፋቱንና ፣ ምናልባትም የመጨረሻውን ግንኙነት ከተቆጣጣሪዎች ጋር ካደረገ በኋላ ቢያንስ 7 ሰአት ያህል ሳይበር እንዳልቀረ መናገራቸው ነው፡፡ ያ ማለት አውሮፕላኑ ተጠልፏል ወይም ታግቷል። ይህ የሆነው ደግሞ ወይም ከተሳፋሪዎች መካከል በአንዱ ወይም ደግሞ እንደ ኢትዮጵያው አየርመንገድ በራሱ ፓይለት ተጠልፎ ነው ማለት ነው።
ይህ የዛሬው ውጤት እስካሁን አውሮፕላኑ ሲፈለግ የነበረባቸውን ቦታዎች ሁሉ ፉርሽ እንደነበሩ የሚያሳይ ነው። ለመሆኑ አውሮፕላኑ ከምድር ተቆጣጣሪዎች ጋር እንዳይገናኝ፣ ሆን ብሎ መገናኛውን የነቀለው ሰው ማነው? ይህ ሊሆን የሚችለው እንደ አቪየሽን ሃላፊዎች ወይ በራሱ በፓይለቱ ነው፣ ወይም ደግሞ በጣም ጥሩ የሆነ የፓይለትነት ችሎታ ባለው ጠላፊ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ አውሮፕላኑ ቢያንስ ለሰባት ሰአት ያህል በምዕራብ አቅጣጫ ከተጓዘ ሊደርስ የሚችለው ሁለት ቦታ ነው፣ አንዱ አንዳማን ደሴቶች ሲሆን ሁለተኛው ህንድ ውቂያኖስ መካከል ነው። እንደ ማሌዥያ ባለሥልጣኖች ገለጻ አውሮፕላኑ የያዘው ነዳጅ ቢያንስ ሰባት ሰአት ያህል ያስኬደዋል። ያ ማለት ከዚያ በላይ መሄድ ስለማይችል፣ ወይም አንዱ የተደበቀ ደሴት አርፏል፣ ወይም ህንድ ውቂያኖስ መካከል ተከስክሷል። አሁን ያለው መላ ምት ይህ ነው።
ይህም ቢሆን እንቆቅልሹን የሚፈታው አይደለም። ለመሆኑ ከአየር መንገዱ ጋር ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ የቆየው ፓይለት፣ የቤተሰብም የሆነ የሌላ ችግር ያልታየበት፣ .. ጥሩ ምግባር እንዳለው የተመሰከረለት፣ በትዳሩ ከ20 ዓመት በላይ የቆየው ፓይለት እንዴት ሆን ብሎ አውሮፕላኑን ይዞ ይሰወራል? ይህ አንዱ ጥያቄ ነው፡ በሌላ በኩል የ 27 ዓመቱ ረዳት ፓይለት አብዱል ሃሚድ፣ ከአየር መንገዱ ጋር ለ7 ዓመት ሰርቷል፣ የተከበረና ምንም አይነት የሚያጠራጥር ነገር የለሌበት ነው። ርግጥ ከዓመታት በፊት ከተሳፋሪዎች መካከል ሁለት ሴቶችን ውስጥ ድረስ ጋብዞና አጠገቡ አስቀምጦ መጓዙ ቢነገርና ይህም የአየር መንገድ ህግን መተላለፍ ቢሆንም፣ በጉርምስና ተሳብቦ ከመቅረቱ በቀር ሌላ እንዲህ ያደርጋል ተብሎ የሚያስገምት ነገር ምንም አልተገኘም።
ከመንገደኞች መካከል ከሆነስ የአውሮፕላን እገታው የተደረገው ማን አደረገው? ለምንስ አደረገው? ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው። ከመንገደኞቹ አብዛኞቹ ቻይኖች እንደመሆናቸው አልቃይዳና ታሊባን በዚህ ድርጊት ይኖራሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው። ርግጥ አንዳንድ ተንታኞች ከቻይና አንድ ግዛትን ለመገንጠል የሚታገልና ከዚህ በፊት አንድ የቻይና አውሮፕላን ለመጥለፍ የሞከረ አንድ ድርጅት እንዳለ በማስታወስ ይመዝገብልን እያሉ ነው። አስገራሚው ነገር ግን፣ ይህ ከሆነ ጠላፊዎቹ ወይም አጋቾቹ ወይም ድርጊቱ የፈጸመው ማንም ይሁን ማን፣ እንዴት ምክንያቱንና የሚፈልገውን አልተናገረም? እንዲሁ ዝም ብለን እንሙት፣ ድምጻችንን እናጥፋ ብሎ እንዴት ይወስናል? ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው።
ነገር ግን አሁን ባለው የነገሮች ግጥምጥም አውሮፕላኑ የቴክኒክ ብልሽት አልገጠመው ይልቁኑ ሆን ተብሎ ታግቶ ወይም ፓይለቱ ራሱ አግቶት የሆነ ቦታ ወስዶታል ወይም ውቂያኖስ መካከል ከስክሶታል። ይህ ደግሞ በቅርብ ከሆነውና የራስን አውሮፕላን ጠለፈ ከተባለው የኢትዮጵያው ሃይለመድህን ታሪክ ጋር ለማመሳሰል የሞከሩም ነበሩ።
ከዚህ በፊት የጠፉ አውሮፕላኖች ተገኝተዋል? የጠፉስ አሉ?
አዎ አሉ።
- ለምሳሌ በሜይ ወር 2003 ዓ.ም የኡጋንዳ ንብረት የሆነው ቦይንግ 727 ድንገት ሳይፈቀድለት ከአየር ማረፊያው ተነስቶ በመብረር ያልታወቀ ቦታ ሄዷል – እስካሁንም የት እንደገባ አልተገኘም። ፓይለቱና ረዳቱ ብቻ እንጂ ተሳፋሪ አልነበረውም።
- የፈረንሳይ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 447 በ2009 ዓ.ም ድንገት ጠፍቶ ፣ ስብርባሪው ህንድ ውቂያኖስ ላይ የተገኘው ከሁለት ሳምንት በኋላ ነበር።
- የትራንስ ዎርልድ አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን በበረራ ቁጥር 800 ጉዞ ከጀመረ በኋላ አየር ላይ በመፈንዳቱ 230 ሰዎች አልቀዋል። ይህ የሆነው በ1996 ዓም. ነው።
- የታይገር አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ፣ በበረራ ቁጥር 793 ጉዞ ከጀመረ በኋላ 106 ሰዎችን እንደጫነ የት እንደገባ አልታወቀም ፣ ይህ ይሆነው በ1962 ዓ.ም ቢሆንም፣ ዛሬም ድረስ ምን እንዳጋጠመው የሚያውቅ የለም።
- በ1957 ዓ.ም የፓን አሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላን ቦይንግ 337 44 ሰዎችን እንደጫነ አየር ላይ ጠፋ፣ከአንድ ሳምንት በኋላ ስብርባሪው ውቂያኖስ ላይ ተገኘ።
እነዚህ ሁሉ አስገራሚ ታሪኮች ናቸው። አንዳንዶቹ ምናልባት ቴክኖሎጂ በጣም ባልዳበረበት ወቅት ሊሆኑ ይችላሉ። አሁን 43 መርከቦች፣ 58 አውሮፕላኖች፣ 14 አገሮች ፍለጋውን እያጣደፉ ቢሆንም፣ የመጥፋቱ እንቆቆልሽ ግን ፣ አገር ስጠኝ ብለን የምንፈታው አልሆነም።

Hiber Radio: የወቅቱን የኢትዮጵያውን አገዛዝ ጨምሮ ምዕራባውያን ለአምባገነኖች የሚሰጡት ድጋፍ ተገቢ አለመሆኑን አንድ አሜሪካዊ ምሁር ገለጹ

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 7 ቀን 2006 ፕሮግራም
<<...የኢትዮጵያ ሕዝብ በውስጥም በውጭም ያለው ወያኔ በምስጢር ለሱዳን የሰጠው ድንበራችን ከመካለሉና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰነድ ከመስፈሩ በፊት የተቃውሞ ድምጹን ያሰማ...>>
አቶ አገኘሁ መኮንን የድንበር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የም/ቤት አባል ለሱዳን ስለተሰጠው የአገራችን መሬት ለህብር ከስዊዘርላንድ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ(ሙሉውን ያዳምጡት)
<...የሚሊዮኖች ድምጽ ሁለተኛ ዙር እንቅስቃሴንም በውጭ ያለው በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብት መከበር የሚታገለው አገር ወዳድ ወገን ሁሉ መደገፍ አለበት ይሄ የአንድነት ፓርቲ ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆን የአገር ጉዳይ ነው...>
አቶ ግርማይ ግዛው የአንድነት የሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ማህበር ሊቀመንበር ስለ አዲሱ የሚሊዮኖች ድምጽ ሁለተኛ ዙር እንቅስቃሴ ከሰጡን ቃለ ምልልስ የተወሰደ
<...በቬጋስ የሚጘኙ ኢትዮጵያውን በየጊዜው በአገራቸው ያለውን ትግል ይደግፋሉ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነትም የአዲስ አበባውን እንቅስቃሴ በገነዘብ እንደግፋለን ስንል ከዚያ የተለየ አይደለም...>
አቶ ሰለሞን በቀለ በቬጋስ የአንድነት የድጋፍ ቻፕተር ሰብሳቢ
<...አባቶቻችን በአድዋ አንድ ላይ ሆነው መገዛት ባርነት የሚያመጣውን ውድርደት በመረዳት በአድዋ ታሪክ ሰርተዋል ይሄ ትውልድ ግን...>>
አቶ ኤልያስ ረሺድ በስዊዘርላንድ የአድዋ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ትላንት ስላደረጉት በጄኔቭ የአድዋ በዓል አከባበር አስመልክቶ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ
<<...ኢትዮጵያውያን ብንተባበር አባቶቻችን እናቶቻችን በአደዋ ካስመዘገቡት ድል በላይ ዛሬ ማምጣት እንችላለን...>>
አቶ ኦባንግ ሜቶ ከጄኔቭ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ(ሙሉውን ያዳምጡት)
የሩሲያና የዩክሬን ውዝግብና የቀረው ምዕራብ አለም ከሩሲያ ጋር የገባበት ፍጥጫ(ልዩ ዘገባ)
<<...በኦባማ ኬር የጤና ሽፋን ኢንሹራንስ ስንገዛ በተለይ ኢንሹራንሱ የሚሰጠንን ሽፋንና የምንከፍለውን መጠን በደንብ ማወቅ ያስፈልጋል..ያልተመዘገቡ የጤና ሽፋን የሌላቸው መመዝገብ አለባቸው...>>
ዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ከአትላንታ ስለ ኦባማ ኬር ከሰጡት ማብራሪያ
ሌሎችም ዝግጅቶች
ዜናዎቻችን
የወቅቱን የኢትዮጵያውን አገዛዝ ጨምሮ ምዕራባውያን ለአምባገነኖች የሚሰጡት ድጋፍ ተገቢ አለመሆኑን አንድ አሜሪካዊ ምሁር ገለጹ
ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ካልተከበረ ልማት የሚባለው ዘለቄታ እንደሌለው ገለጹ
ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ አንድ ሺህ ቀናቶች በእስር ቤት አሳለፈች
ኤርትራ ህገ ወጥ ብላ ካሰረቻቸው የመናውያን አሳ አስጋሪዎች የተወሰኑትን ለቀቀች
ከሳውዲ የኢትዮጵያውያንን ሰቆቃ እየተከታተለ የሚዘግበው የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በአገሪቱ የደህንነት ሰዎች መታሰሩ ተሰማ
አንድነትና መኢአድ ሐሙስ የቅድመ ውህደት ፊርማ ለማድረግ ወሰኑ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ

[ውንብድና ካርቱም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ] – ሁዳ የሚባል እስር ቤት 35 ጠያቂ የሌላቸው እስረኞች ይማቅቃሉ – አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

በዓለም ዉድድር አለ። ዉድድሩ በህዝቦች መካከል ነው። ህዝቦች ዉድድሩን ለማሸነፍ አብሮነትን ይፈልጋሉ። በአብሮነት የራሳቸው ደህንነትና ጥቅም ማስከበር ይሻሉ። ደህንነታቸውንና ጥቅማቸው ለማስከበር ሀገር ይመሰርታሉ። ሀገር መስርተው በመንግስት ይወከላሉ። የመንግስት ተግባር ታድያ የህዝቡን ጥቅምና ደህንነት መጠበቅ ነው። በዚሁ መሰረት መንግስት የህዝቦች ተወካይ ጠበቃ መሆን ይጠበቅበታል።የህዝቦች ወኪል (ጠበቃ) ለመሆን መንግስት በተለያዩ ሀገሮች ኤምባሲ ይከፍታል። የኤምባሲው ሰራተኞች የሚወክሉትን ህዝብ ጥቅምና ደህንነት ይጠብቃሉ፣ ያስጠብቃሉ። ለዚሁ ተግባራቸው ሲባል ህዝብ ደሞዛቸውን ይከፍላቸዋል። ደሞዛቸው የሚከፈላቸው ከመንግስት ካዝና ነው። የመንግስት ገንዘብ የሚሰበሰበው ከህዝብ ነው፤ በግብር መልክ። 
የኢትዮጵያ መንግስትም (መንግስት ልበለው) ከህዝብ ኪስ የሚከፈሉ የኤምባሲ ሰራተኞች አሉት። በተለያዩ ሀገሮች ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች በህዝብ ገንዘብ እየተዳደሩ የሚከፍላቸውን ህዝብ የሚበድሉ መሆናቸው እናውቃለን። ዛሬ ትኩረቴ የሳበ ግን በካርቱም ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው።
ካርቱም የሚገኙ ጓደኞቼ እንደላኩልኝ ከሆነ የኢትዮጵያ ኤምባሲ (በካርቱም) ሰራተኞች በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር ተሰማርተው ኢትዮጵያውያንን አደጋ ዉስጥ እየጣሉ ይገኛሉ። የሰዎች ደህንነት ከመጠበቅ ይልቅ ሰዎችን አደጋ ዉስጥ ማስገባት ምን ይሉታል? የመንግስት አካላት ወንጀልን ከመከላከል ይልቅ ቁማርተኞች ሲሆኑ ምን ማድረግ ይቻላል?!
የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች ሱዳን ዉስጥ የሚቸገሩ ዜጎቻችንን ደህንነት ከመከታተል ይልቅ ከሱዳን መንግስት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያውያን እስርቤት ይከታሉ። እስካሁን ድረስ በሱዳን ብዙ ኢትዮጵያውያን ያለ ምንም ጠያቂ በወህኒቤቶች እየማቀቁ ነው። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች በሱዳን ሀገር የሚደርስባቸው ችግር፣ እስር፣ እንግልት እያወቁ በሰዎች ንግድ መሰማራታቸው ይገርማል። የኤምባሲው ሰራተኞች በሀገራቸው ሰዎች ንግድ ነው የተሰማሩ።
በሱዳን ያሉ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንደሌላቸው (መንግስት አልባ እንደሆኑ) ነው የሚቆጠረው። “ሑዳ” በሚባል ወህኒቤት 35 ጠያቂ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን አሉ። እነዚህ እስረኞች ያለ ምንም የፍርድቤት ዉሳኔ የተያዙና ከ8-12 ዓመት በወህኒቤቱ የቆዩ ናቸው። ተሰቅለው የተገደሉም መዓት ናቸው። በሱዳን የኢትዮጵያውያን ህይወት ርካሽ ነው። መስከረም አያሌው የተባለችም በሰባት ሱዳናውያን መደፈሯ ይታወሳል።
ኢትዮጵያውያን መንግስት አልባ (stateless) ሁነው ሲሰቃዩ የኤምባሲው ሰራተኞች ግን ሰዎች እየገዙና እየሸጡ (በሰዎች ንግድ ተሰማርተው) ገንዘብ ይሰበስባሉ። ዘመናዊ መንግስታዊ የንግድ ባርያ መሆኑ ነው።
ኢትዮጵያውያን ክብራችንን የምናስመልስበት ግዜ ሩቅ አይሆንም። አቶ መሐመድ ቱፋና አቶ በላቸው ግን ተግባራቹሁ ሁሉ እየተከታተልነው እንገኛለን።