Friday 8 May 2015

መልዕክተ ሎንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን

May 4, 2015
ከለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት
የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን እና አማራን በጠላትነት በመፈረጅ አከርካሪውን ሰብረነዋል በማለት በእብሪት ሲለፍፉ የነበሩት የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ወያኔ) ባለሥልጣናትና ደጋፊዎች በአሁኑ ወቅት ደግሞ የኦርቶዶክስ እምነት ተቆርቋሪና አሳቢ ነኝ በማለት በለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፋፋይ የጥፋት ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
London Ethiopian Orthodox Church
ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን
በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ከመንስዔው በቤተ ክርስቲያኑ መተዳደሪያ ደንብና በሃገሪቱ የቻሪቲ ሕግ መሠረት ሕግና ሥርዓትን ጠብቆ መፈታት ሲችል የቤተ ክርስቲያኗ አባላትም ሆኑ ሕግና ደንብ አይገዛንም ያሉ ጥቂት ካህናት ሕዝብን ከድተው ለወያኔ ሹመኞች በባንዳነት አደሩ።
በለስ ቀናኝ ያለው ወያኔም ሕዝብን የከዱትን ባንዳዎች በመጠቀም ስደተኛው ሕዝብ በሃብቱና በጉልበቱ ገዝቶ ያቆመውን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በመውረስ የራሱና የደጋፊዎቹ ለማድረግ በሁሉም ዘርፍ እንቅስቃሴ ጀመረ።
በእነ አባይ ፀሐዬ ትዕዛዝና ቁጥጥር የሚንቀሳቀሱ ጳጳሳትን ወደ ውጪ በመላክ ቤተ ክርስቲያኗን ከነንብረቷ በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንዲንቀሳቀሱ አደረገ።
አልበገሬዎቹ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት ግን ለሁለት ዓመት በዓላማቸው ጸንተው በመታገል ጉዳዩን ለፍርድ ቤት በማቅረብ የመጀመሪያው ምዕራፍ የሆነውን ቤተ ክርስቲያኗን በእኩል የመጠቀም መብታቸው እንዲጠበቅላቸው አስፈረዱ።
በዚህ የተደናገጡት የወያኔ ሹማምንቶች የእንግሊዝን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ባለመቀበል የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ የሚቀለበስ መስሏቸው የወያኔው ጳጳስ ሳይቀሩ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት መሳቂያና መሳለቂያ ሆኑ።
በዚህም አላበቃም በሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚመራው መንግሥት የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም አስነዋሪውን ሰላማዊ ሰልፍ ግንባር ቀደም ዜና በማድረግ አቀረበው።
ይህም ወያኔ በለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባቱን ለማመን ያዳግታቸው ለነበሩ አንዳንድ ግለሰቦች ተገቢ ማረጋገጫ ነበር።
የኢትዮጵያው ቴሌቪዥን ስለ ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ያሰራጨውን ዜና የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ።
በቅጥፈትና በክህደት የቆሸሸው የሃሰት ቋቱ ወያኔ፤ ሃገር ያወቀውን፤ ፀሐይ የሞቀውን ጉዳይ ዓይኑን በጨው ታጥቦ
• የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቀረበለት ከእውነት የራቀ አቤቱታ ላይ ተመርኩዞ ፈረደ ይላል፤
• በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩትን የቤተ ክርስቲያኑን አባላት የተለየ ዓላማ የያዙ ጥቂት አባላት ናቸው ይላል፤
• ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተጣሰ፤ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ፈረሰ ይላል፤ (እግዚአብሔር ያሳያችሁ ወያኔ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተቆርቋሪ ሆኖ)
• ቤተ ክርስቲያኗ ከዓላማዋ በእጅጉ ለተለየ ተግባር ልትውል ነው ይላል፤ (ወያኔን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጉዳይ በእጅጉ አሳስቦት)
ውድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮችና ወዳጆች። ለሃይማኖታቸው፤ ለቤተ ክርስቲያናቸውና ለመብታቸው ጸንተው የታገሉት የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት ሃሰት የተጠናወተው ወያኔ እንደሚለው ሳይሆን እውነቱ ሌላ ስለሆነ አባላቱ በፍርድ ቤት ፍትሕ ካገኙ በኋላ ቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ በመግባት የሆሳዕና በዓልን ሲያከብሩ የሚያሳየውን ቪድዮ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ተመልከቱና ወያኔ የአጸያፊ ውሸትና ቅጥፈቱ ማሰራጫ ካደረገው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ካስተላለፈው ነጭ ፕሮፓጋንዳ ጋር በማነጻጸር እውነታውን ተረዱ። http://londondebretsion.org/
ከዚህም በማስከተል የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (TPLF) ሹማምንቶችና ወኪሎች የለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አባላትን ከድተው ለወያኔ በባንዳነት ያደሩ ጥቂት ካህናትን በመያዝ የሚነዙት የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ፋይዳ ቢስ ስለሆነባቸው በአሁኑ ወቅት ደግሞ በወያኔ ወኪሎች የሚመሩ አብያተ ክርስቲያናትን በማስተባበር በለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አባላት ላይ እንዲዘምቱ ለማድረግ አስተባባሪ ግብረ ኃይል አቋቁመው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን በየ አብያተ ክርስቲያኑ በሚያሰሙት አዋጅ ለማረጋገጥ ተችሏል።
ቀጥሎ የተመለከተውን ሊንክ በመጫን የወያኔውን ሹመኛ ሙሉ ቃል ያድምጡ።
ከዚህ በማስከተልም ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መራሹ መንግሥት የዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ ትግል ለማዳከም ወደ ውጪ ሀገራት የሚልካቸው ካድሬዎቹና ባለሥልጣናቱ ምንም ሳይፈይዱ ተዋርደው እየተመለሱ ስለተቸገረ በአሁኑ ወቅት የተያያዘው ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳትንና የቤተ ክርስቲያን ሹማምንትን በማሰማራት በሃይማኖት ሽፋን እነሱ ያቃታቸውን ተግባር እንዲያከናውኑለት ማድረግ በመሆኑ በዚህ መሠረት በአሁኑ ወቅት አቡነ ገብረኤልና አቡነ ቀውጦዎስ የተባሉ ሁለት ጳጳሳት የወያኔ ባለሥልጣናትና ካድሬዎችን ሥራ ለማከናወን ለንደን ዩናትድ ኪንደም ገብተው ይገኛሉ።
St, Mary of London Deber Tsion latest
እንደ እግዚአብሔር ትዕዛዝና እንደ ክርስትና ሃይማኖት ቢሆን ኖሮ “የሚያስታርቁ ብፁአን ናቸው፤ የእግዚአብሔርም ልጅ ይባላሉና” (ማቴ፡ 5:9) ተብሎ እንደተገለፀው በክርስቲያኖች መካከል ችግር ሲፈጠር እነዚህ ሁለት ጳጳሳት ሰላምና እርቅን ለማምጣት በጸሎትና በልመና በአማላጅነትና በአስታራቂነት በደከሙና በጣሩ ነበር።
እነሱ ግን በፁእ የሚለውን ማዕረግ ከመያዝ ባለፈ ተግባር የለባቸውምና ለንደን ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ከዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማሳካት ወደሚያመቿቸው የገብሬኤል እና የሥላሴ ቤተ ክርስቲያናት በመሄድ ከወያኔ ሹማምንቶች ጋር እጅና ጓንት በመሆን ሃይማኖትንና መንፈሳዊ አገልግሎትን በሽፋንነት በመጠቀም የሁለቱን ቤተ ክርስቲያናት አባላት በማስተባበር ላለፉት 24 ዓመታት ከማንኛቸውም የወያኔ ሥርዓት ተጽዕኖ ነጻ ሆና በኖረችው የለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን እላይ የጥቃት ዘመቻ ከፍተው ይገኛሉ።
አቡነ ገብረኤልና አቡነ ቀውጦዎስ ለንደን ከሚኖሩ የወያኔ ካድሬዎችና የኤምባሲ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን ካከናወኗቸው ወያኔያዊ ተግባራት ውስጥ፡
1ኛ) የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ህንጻ ተከራይተው ጳጳሳቱ በተገኙበት በሊቢያ በረሃ መስዋዕት ለሆኑት ኢትዮጵያኖች ጸሎተ ፍትሐት ይካሄዳልና ሃዘኑ የተሰማው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይገኝ በማለት የማታለያ ጥሪ አሰራጩ።
በወገኖቹ ላይ የተፈጸመው አረመናዊ ድርጊት ያሳዘነውና ያስቆጨው ኢትዮጵያዊ ሃዘኑን ለመግለጽ በቦታው ላይ ሲገኝ እነሱ ግን የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አምባሳደር እና ሌሎች የወያኔ ባለሥልጣናትን የክብር እንግዳ በማድረግ በግፍ የፈሰሰውን የወገኖቻችንን ደም ስደትን በኢትዮጵያ አንግሶ ወገኖቻችንን የአረመኔዎችና የባህር ሰለባ በማድረግ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የአለም መዛበቻ ያደረገው የወያኔ አገዛዝ የፖለቲካ መጠቀሚያ መድረክ ሊያደርጉት ችለዋል።
በግፍ የፈሰሰው የኢትዮጵያውያንን ደም ጳጳሳቱ ከወያኔ ካድሬዎች ጋር በመሆን ለፖለቲካ ፍጆታ ካዋሉበት ሂደት የተወሰድ ምስል።
St, Mary of London Deber Tsion latest issueበዚህ ምስል ውስጥም ወያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን በግፍ ሲገድልና ሲጨፈጭፍ፤ ሰብዓዊ መብታቸውን ገፎ በአረመኔነት ሲያስርና ሲገርፍ፤ ከዚህም አልፎ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ ሲገደሉ፤ ሴቶች ሲደፈሩና እንደውሻ ሲሳደዱ አንድም ነገር እንዳልተደረገ በማስተባበልና በኢትዮጵያም ውስጥ ነጻነትና ዲሞክራሲ ሞልቶ ተትረፍርፏል እያለ ለንደን ላይ ተቀምጦ የሚወሸክተው ሆድ አደሩ አምባሳደር ብርሃኑ ከበደ ለኢትዮጵያውያን ያዘነ መስሎ ከጳጳሳቱ ጎን በክብር ተቀምጦ ታዩታላችሁ።
2ኛ) አቡነ ገብረኤልና አቡነ ቀውጦዎስ በለንደን የሚገኙ በሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወኪሎችና ካድሬዎችች የሚመሩ አብያተ ክርስቲያናትን በማስተባበር በስደት ሃገር የመሠረትናትን ቤተ ከርስቲያናችንን ለወያኔ አሳልፈን አንሰጥም በማለት በመታገል ላይ የሚገኙትን የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን አባላት ለማጥቃት የሚያስችል ገንዘብ ለማሰባሰብ ከ02/05/15-እስከ 05/05/15 የሚዘልቅ የፈንድ ሬዚን መርሃ ግብር በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
3ኛ) እነዚሁ ሁለት ጳጳሳት ከዚህ ሁሉ በማለፍ የክርስቶስን መስቀል ተሸክመው የክርስቶስ መንገድ ከሆነው የሃይማኖቱ ሕግ የሰላም፤ የፍቅር፤ የእርቅና የይቅር ባይነት መንገድ ጨርሰው በመውጣት ውግዘትን ለፖለቲካ መሣሪያነት ለመጠቀም በመጣር ላይ ይገኛሉ።
ስለ ውግዘት ከተነሳ እነሱ ራሳቸው በስደት ላይ በሚገኘው ሕጋዊው ሲኖዶስና ቀደምት አባቶች እጅግ በጠነከረና በከረረ ውግዘት መወገዛቸውን ሁሉ ክርስቲያን የሚያውቀው ጉዳይ ነው። አሁን ላይ ግን ራሳቸው እንዳልተወገዙና እነሱም መልሰው እንዳላወገዙ ሁሉ የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ አገዛዝ ተጽዕኖን አንቀበልም ያሉ የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትን እኛ የምንለውን ካልተከተላችሁና በወያኔ ጫና ሥር ካልዋላችሁ እናወግዛችኋለን በማለት ውግዘትን የጎሰኝነት ፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ በመጣር ላይ ይገኛሉ። ይህ እግዚኦ የሚያሰኝ ነገር አይደለም?
ይህ ሁሉ ግርግር እውነትን ከቦታዋ ባያነቃንቃትም ሆኖም ግን ጳጳሳቱ በዚህ ክርስቲያናዊ ያልሆነ ድርጊታቸው ተዋርደውና ተንቋሸው ሃይማኖታችንም ሆነ ቤተ ክርስቲያናችን መሣለቂያ ከምትሆን የማይሳነው እግዚአብሔር ልቦና ሰጥቶአቸው ከዚህ ተግባራቸው ይታቀቡ ዘንድ ልንጸልይላቸው ይገባል።
ወስብሓት ለእግዚአብሔር!!
ከለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት።

የተቀዳደደዉ የዜጐች ነጻነት በኢትዮዽያ (በመሃመድ አሊ)

May 5, 2015
በመሃመድ አሊ
በግንቦት 1983 በኢትዮዽያ አቆአጣጠር ሕ.ወ.ሀ.ት መራሹ ጦር የመንግስት ወንበር ከተቆጣጠረ በኋላ ግዜዉ የሚያሥገድደዉንና በምዕራባያዉያንም ተፅእኖ ጭምር አዲሥ ሊባል የሚችል ሕገመንግስት ማርቀቁ ይታወሳል፡፡
በ1985 የፀደቀዉ የኢትዮዽያ ሕገመንግስት ቀድሞ ከነበሩት የደርግና የዘዉዳዊ መንግስት በብዙ መልኩ እንደሚሻል በሃገር ዉስጥም በዉጭ መንግስትም ችሮታ ተለግሶት ነበር፡፡ ሆኖም የበግ ለምድ የለበሰዉ ተኩላ ባሕሪዉ የመንግስት ስልጣንን ላለመልቀቅ ራሱ ያፀደቀዉን ሕገመንግስት በየግዜው እየሸረሸለዉ ይገናል፡፡ ከቶም እየናደዉ ካሉት ሕጎች መካከል የዜጐች የመናገር፣ የመፃፍና የመደራጀት መብት ዛሬ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ተሸርሽፘል፡፡
በ1997 በዜጎች የመደራጅት መብት ተጠቅመዉ ሕብረብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ መብትን በተግባር ለማዋል ተቀናጀተዉ የነበሩ ፓርቲዎች በሐገሪቱ ሕዝብ ንቃተ ሕሊና ማዳበራቸዉ ስልጣን ላይ የተቀመጠዉን የወያኔ መንግስት አስደምብሮት አዉሬያዊ ባሐሪዉ እንዲገነፍል አድርጐታል፡፡በወቅቱ ተከስቶ የነበረዉ አዲስ የዴሞከራሲ ጅምር ሕብረተሰቡ መቅመሱ በሰዉ ልጅ ላይ ድርድር አለመኖሩን አሳይቶ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ነገሮች ሁሉ መገልበጣቸዉ በይፋ መታየት ጀመፘል፡፡
ዛሬ ኢትዮዽያዊ በሐገሩ የዜግነት መብት በነፃነት የመናገር ፣የመፃፍም ሆነ መደራጀቱ በጥርጣሬ እንዲታይና ወህኒ ማደርያዉ እንዲሆን እያስደረገዉ ይገኛል፡፡ ሐገራችን የዜጐች መብት የተጨፈለቀበት በመሆኑ ሰዉ እርስ በርሱ መተማመን እያቃተዉ በጥርጣሬና በመፈራራት እየኖረ ገዢዉ ፓርቲ አንባገነንነቱን ከመቼዉም ግዜ በላይ በማናር አንዱን ከሌላናዉ ጋር በማጋጨት ዜጐች ተግባብተዉ እንዳይኖሩ እያደረገ ይገኛል፡፡በኢትዮዽያ እስር ቤቶች ከጋዜጣና መፅሔት ስራ ጋር የተገናኙ አዘጋጆች፣ ሪፖርተሮች፣ የጋዜጣና መፅሔት ባለቤቶች ስለ ነፃነት በመፃፋቸዉ ብቻ የመከራ ግፋትን እንዲቀምሱ ተደርጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በ1997 በብዛት ይታዩ የነበሩ ጋዜጣና መፅሔቶች ዛሬ ለዐይን አይታዩም፡፡በከተማዋ በመንግስት የሚደጐሙ ጥቂት የፓርቲ ልሳን የሆኑ ነፃ መሰል ጋዜጦች እንጂ አንድም ነፃ ፕሬስ አይገኝም፡፡ እስከ ቅርብ አመት ስለ ነፃነትና ስለ ዜጐች መብት ሲዘምሩ የነበሩ ጋዜጦች ወይ ከሐገር ተሰደዋል አልያም እጅና እገሮቻቸዉ ተጠፍሮ ወህኒ ገብተዋል፡፡እስር ላይ ከሚገኙ ዜጎች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት የዜጐች መብት ላይ ጥያቄ የሚያቀርቡ የነቁና የተማሩ ኢትዮዽያዊያን ናቸዉ፡፡ በመንግሰት ወንበር ላይ ከተቀመጡት ባለሥልጣናት በላይ በኢትዮዽያ እስር ቤቶች ሐገሪታን መምራት የሚችሉ የነቁ ሙሑራን ወህኒ ታጉረዋል፡፡
በኢትዮዽያ በአሁኑ ግዜ በየትኛዉም የዜጎች መብት ላይ በነፃነት ሚናገሩ ዜጎችን ማግኘት አይቻልም፡፡ ከአምስት በላይ ሰዎች አንድ ቦታ ላይ ተሰብስበዉ መነጋገር ካለባቸዉ ለመንግስት ማሳወቅ እንዳለባቸዉ ይፋ ባልሆነ መንገድ እየተገለፀ ይገኛል፡፡ በቅርቡ አንድ ጋደኛዬ በትምህርት ጉዳዮች ላይ ባዘጋጅዉ አጫጭር ዉይይቶች በተደጋጋሚ ከደህንነቶች ማስፍራሪያና ዛቻ ገጥመዉታል፡፡በሐገራችን ዉስጥ መብት ላይ የሚፅፉ ሰዎች ስልካቸዉ ሊጠለፍ፣የግል ምስጢር ሳጥኖቻቸዉ ሊሰበሩ፣ የፌስቡክና የዌብ ሳይት አድራሻቸዉ መንግስት ባቃቃመዉ INSA በተባለ ድርጅት ሊሰበር ይችላል፡፡ በ24 አመታት የአገዛዝ ዘመን ወያኔ የባለስልጣናትን ኪስ ከማደለብና ንቅዘትን በሰፊዉ ከመዘርጋት ውጭ የሚታዩ ተጨባጭ ለዉጥ ሰዎች ላይ አይታይም፡፡ ሐገሪቱ እያስመዘገበች ነዉ ሚባለዉ እድገት በዜጎች ሕይወት ላይ ለዉጥ አላመጣም፡፡ መብትን የጣሰ እድገት ከቶም ሊኖር አይችልም፡፡
በአጭሩ ኢትዮዽያ ዉስጥ የዜጎች መብት ከላይ የተጠቀሰዉን ይመስላል ፡፡ለአብነት ያክል የታዩትን ነገሮችን ማስተዋል ለቻለ ሰዉ ዜጎች እንዴት ያለ በግፍ ስርዐት ዉስጥ ህይወታቸዉን እየገፉ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህንን ለዉጥ ለማምጣት ሁሉም ሊረባረብና አለምአቀፍ ጫና እንዲኖር ሀያላን መንግስቶች፣ ለዜጎች መብት ዴሞክራሲ መከበር የሚጮሁ ሁላን ኢትዮዽያ ዉስጥ የዜጎችን መብት ለሚደፈጥጥዉ የወያኔ አፋኝ ሥርዐት የብድርና የመሳሰሉትን ድጋፍ እንዲያቆሙና ሥርዐቱ እንዲወገድ ሁላችንም ልንረባረብ ይግባል እያልኩ ፅሁፌን በዚሁ አበቃለዉ፡፡

በየመን የሚታየው ምስቅልቅል እየሰፋ ሰለመጣው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጥረት ምን ያሰተምረናል?

በአክሊሉ ወንድአፈረው ሜይ 5፣ 2015 በተለያዩ ሀገሮች የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ያለፉባቸውን ጥምዝምዞች፣ የገጠማቸውን ደጋፊና አደናቃፊ ሂደቶች መመርመር ባንድ ሀገር ውስጥ ለሚካሄደው ትግል ታላቅ ጠቀሜታ አለው። በዚህ አንጻር በ2011 የአረብ ስፕሪንግ ካምባገነናዊ ስርአት ወደ ዴሞክርሲ ልትሸጋገር ነው ተብላ ተስፋ የተጣለባት የመን፣ እነሆ ዛሬ በእርስ በርስ ጦርነት ተናውጣ እንኳንስ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ልትሸጋገር ከራሷም አልፋ አካባቢውን ለማመስ የቻለ ሁኔታ ውስጥ ገብታለች። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ብሎ መመርመር ለሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ትግልም ሆነ ባካባቢው መረጋጋት ላይ ሊኖ ረው ለሚችለው እንደምታ ታላቅ ትምህርት ይሰጣል። በዚህ አኳያ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የየመንን ተመክሮ በመመርመር ለኢትዮጵያ ሁኔታ የሚኖረውን ትምህርት አመለክታለሁ። በርግጥ ይህ ጽሁፍ ሰፊ የሆነውን የሁለቱን ሀገሮች ውስብስብ የታሪክ፣ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ ኑሮ፣ ወዘተ እውነታ ሙሉ ለሙሉ በዝርዝር መሽፈን እንደማይችል ግልጽ ቢሆንም፣ ለቀጣይ ገንቢ ውይይት አስተዋጽኦ ያበረክታል ብዮ ተስፋ አደርጋለሁ። የየመን ምስቅልቅል መሰረቶች ለ150 አመታት ያክል ለሁለት ተከፍላ የቆየችው የመን በ1990 እንደገና ተዋሀደች ። ምንም እንኳ የተዋሀደችው የመን ህገመንግስት የብዙሀን ፖርቲዎች ስርአትን እንደሚቀበል የደነገገ ቢሆንም፣ የመን ከውህደት ቀኗ ጀምሮ አብደላሂ ሳሊህ ከስልጣን እስከተወገዱበት ጊዜ በእርሳቸው ፕሬዚደንትነት እና በፓርቲያቸው በየመን አጠቃላይ ህዝባዊ ኮንግረስ ፓርቲ (The General People's Congress የበላይነት ነው ስትገዛ የኖረችው። አብዲላህ ሳሊህ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደስልጣን የወጡት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በጁላይ 17፣1978 በዚያን ጊዜዋ ሰሜን የመን ሲሆን፡የመሪነት ምሳሌነታቸውን ሀ ብለው የጀመሩትም ስልጣን ከያዙ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 30 የሰራዊቱ ባለስልጣኖችን እንዲገደሉ ትእዛዝ በመስጠት ነበር። የሟቾቹም ጥፋት “ስልጣኔን ለመጋፋት አሲረዋል” የሚል ነበር። ይህ ሁኔታ ያመላከተውና በቀጣይም የተረጋገጠው የአብዲላሂ ሳሊህ ራእይ ተቃዉሞን ጨፍልቆ ስልጣንን ለብቻ ጠቅልሎ መኖር እንደሆነ ነበር። መልእክቱ ገና ከጠዋቱ ግልጽ ነበር፡፡ ውህዷ የመን በመጀመሪያው ጥቂት አመታት ከየመን ሲሻሊስት ፓርቲ እስከ እስላማዊው ኢስላህ (Islaah) ፓርቲ ድረስ ያሉት ሁሉ የተሳተፉበት የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች የተሰተናገዱበት ህገመንግስት በሜይ 1991 አጸደቀች፡፡ በ1993 በተካሄደ ምርጫም ሕዝባዊ ኮንግረስ 143 ፣ የየመን ሶሻሊስት ፓርቲ 69 ኢስላህ የተሰኝው የእስልምና ፓርቲ 63 የባአዝ አመለካከት ተከታይ ፓርቲ 6፣ የናስር ርእዮትን የሚከተለው ፓርቲ 2፣ አል ሀቅ 2 እና ከምንም ፓርቲ ያልወገኑ ግለሰቦች 15 ወንበር ይዘው ነበር፡፡ በበበየየየመመንንን የየየሚሚሚታታታየየየውውው ምምምስስስቅቅቅልልልቅቅቅልልልናናና IIIትትትዮዮዮጵጵጵያያያ ፖፖፖለለለቲቲቲካካካ ውውውጥጥጥረረረትትት፤፤፤ AAAክክክሊሊሊሉሉሉ ሜሜሜይይይ 222000111555 2 በዚህ ምርጫ ምንም እንኳ መሰረቱ በዋናነት የቀድሞዋ ደቡብ የመን የሆነው ሶሻሊስት ፓርቲው ሁለተኛውን ብዛት ያለውን የፓርላማ መቀመጫ ያሸነፈ ቢሆንም ባዲሱ የትብብር መንግስት ውስጥ ግን ፣ ህዝብ በብዛት ከሌለበት አካባቢን የሚወክል ነው በማለት፣ የሚገባውን ቦታ ሳያገኝ በምትኩ የእስላማዊው ፓርቲ (ኢስላህ ) መሪ አብዲላሂ ቢን ሁኔይን ከአሊ አብዲላህ ሳሊህ እና በፓርቲያቸው በየመን አጠቃላይ ህዝባዊ ኮንግረስ ፓርቲ ጋር የጋራ መንግስቱን እንዲመሰርቱ ተደርጎ አብዲላሂ ቢን ሁኔይን የፓርላማው አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ። ይህ ጉዳይ የደቡብ የመንን ህዝብ እና የሶሻሊስቱን ፓርቲ ቅሬታ እንዲገባቸው ማድረግ ጀመረ። በመቀጠልም ሀድረመውት (Hadhramaut ) እየተባለ በሚጠራው ደቡብ የመን ክፍል ሰፊ የነዳጅ ዘይት ማምረት ሲጀመር፤ መሬታችንንና ሀብታችንን ያላግባብ በሰሜናውያኑ ተዘረፈ የሚል ከፍተኛ የቅሬታ ስሜት በደቡቡ ነዋሪዎች መሀል ተቀሰቀሰ። በመቀጠልም በትብብሩ መንግስት ውስጥ የበለጠ ቅሬታና መፍረክረክ የተከተለው ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የመናውያን፣ መንግስታችሁ የገልፉን ጦርነት እልደገፈም በማለት ከሳውዲ አረቢያ ተባረው ድንገት ወደየመን ሲመለሱ ነበር። እነዚህ እጅግ ብዙ ገንዘብ ወደሀገራቸው በመላክ የሀገሪቱን እኮኖሚ ያግዙ የነበሩ ሰዎች ድንገት ከሳውዲ ሲባረሩ ወደሀገሪቱ የሚገባው የውጭ ምንዛሬ ባንድ ጊዜ ደረቀ። ለተመላሾቹም ቤት፣ ስራ ወዘተ ማመቻቸት ለመንግስቱ እጅግ ከባድ ሆነ። ይህ ሁኔታ የፈጠረው ጫና በትብብሩ መንግስቱ ውስጥ አለመግባባትና ቅራኔውን አፋፋመው። ቀጥሎም፣ የሀገሪቱ ምከትል ፕሬዚደንት አሊ ሳሊም አል በይደር ስልጣናቸውን ለቀው ወደ ደቡቧ ከተማ ወደ ኤደን ተሰደዱ። የቀድሞው የደቡብ የመን ፕሬዚደንት የውህዷ የመን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሁነው ቢቀጥሉም በአጠቃላይ በተለያዩ ፓርቲዎች ውስጥ በተፈጠረው አለመተማመን እና ንትርክ ምክንያት ፕሬዚደንቱ ስልጣናቸው ዋጋቢስ ሆነ። በዚህ ሁሉ መሀል ጎሳ ነክ የሆኑ አመለካከትን የሚያራምዱ ድርጅቶች በሰሜንም በደቡብም የሀገሪቱ ክፍል ራሳቸውን ማጠናከሩን ቀጠሉበት፡እያደርም በተለያየ የፖለቲካ ክፍሎች መሀል የሚታየው አለመግባባትና ግጭት እየሰፋ ሄደ። ሁኔታው ተባብሶም በሜይ 21፣ 1994 ደቡብ የመን ተገንጥላ የየመን ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ብላ ራሷን እንደ ነጻ ሀገርና መንግስት አወጀች። ይህች አዲስ ሀገር በአለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅናን ያላገኘች ሲሆን፣ ባብዛኛው በሰሜን የመን ባለስልጣኖችን ያካተተው መንግስትም የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ አካሂዶ በጁን 7፣ 1994. ኤደንን ተቆጣጠረ። ደቡቡና ሰሜኑ ሲዋሀዱ ቀደም ሲል በሁለቱም በኩል የነበረው ሰራዊት ሙሉ ለሙሉ ስላልተዋሀደ በድርጅቶች መሀል አለመግባባት ሲፈጠር በሁለቱም በኩል ያለው ሰራዊት በገለልተኛነት ቆሞ ሀገራዊ የማረጋጋት ሀላፊነት ከመወጣት ይልቅ፣ ከየክልሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ወግኖ ግጭቱን እጅግ ወደመረረ ደም መፋሰስ አናረው። ሁለቱም የውህዷ የመን አካሎች (ሰሜኑም ደቡቡም) ቀደም ሲል እንደመንግስት የተደራጀ ሰራዊት ስለነበራቸው የደቡብ አማጽያንና በዋናነት ከሰሜን የመን በመጣው የመንግስት ሰራዊት መሀል የተካሄደው ውጊያው በታንክ እና ባይሮፕላን ጭምን ነበር። በበበየየየመመንንን የየየሚሚሚታታታየየየውውው ምምምስስስቅቅቅልልልቅቅቅልልልናናና IIIትትትዮዮዮጵጵጵያያያ ፖፖፖለለለቲቲቲካካካ ውውውጥጥጥረረረትትት፤፤፤ AAAክክክሊሊሊሉሉሉ ሜሜሜይይይ 222000111555 3 የሰሜኑ ጦር ኤደንን መቆጣጠሩን ተከትሎም በሽዎች የሚቆጠሩ የደቡብ የመን የፖለቲካ ሰዎችና ወታደሮች ሀገር ለቀው ተሰደዱ። የደቡብ የመን ህዝብ እምርሮ በሰሜኑ ነዋሪዎች ተረግጠናል፣ የሚለው ሰሜት እጅግ እየሰፋ ሄደ። ከሰሜኑ የመን ተገንጥሎ ነጻ የደቡብ የመን መንግስትን ለመመስረት የሚደረገው ትግልም ከፖለቲካ ተቃውሞ እስከ ትጥቅ ትግል ደረሰ። ይህ ሁኔታ በዚሁ በደቡብ የመን ውስጥ ተጠናክሮ ለቀጠለው አልቃይዳም አመች ሁኔታን ፈጥሮለታል። ከላይ ከተጠቀሱት ሌላ አብድላሄ ሳላህ የስልጣን ተቀናቃኝ የበዛባቸው የያዙትን ስልጣን መደላድል የሚያጠናክር ህገመንግስታዊ ማሻሻያ በተከታታይ በመውሰድ ስልጣናቸውን ለማንም፣ ሳያካፍሉ እርሳቸው፡ቤተሰቦቻቸው እና ድርጅታቸው በዘላቂነት ለመግዛት የሚያስችላቸው እርምጃወችን ይወስዱ ሰለነበረ ነው:፡ ለምሳሌ በ2000 አመተ ምህረት ልጃቸውን የስልጣናቸው ወራሽ ለማድረግ የወሰዱት እርምጃ የቅርብ አጋሮቻቸው ሳይቀሩ እንዲርቋቸው አድርጓል። በዚህም ምክንያት የቅርብ አጋሮቻቸው ሳይቀሩ ከ2009 ጀምሮ አብድላሄ ሳላህ ስልጣን መልቀቅ እንዳለባቸው በግልጥ ይናገሩ ነበር፡ አብደላሂ ሳላህ የውህዷ የመን ፕሬዚደንት ከሆኑ በኋላ በደቡብ የመን የነበረውን የመገንጠል ስሜት ሊያስወግዱ ባለማቻላቸው ብዙዎችን የመሪነት ብቃታቸውን እንዲጠራጠሩ አድርጓቸዋል፡ እንዲሁም በሰሜን በኩል እያደር የመጣውን የሁቴዎችን እንቅስቃሴ ሊገቱ ባለመቻላቸው የሺዓዎችን መጠናከር እና የኢራንን ጣልቃ ገብነት የሚፈሩ ሁሉ አብድላሄ ሳላህ ላይ ታላቅ ቅሬታ እንዲያድርባቸው ሆኗል። በመቀጠልም በማርች 18፣ 2011 51 ሰላማዊ ሰልፈኞች በጸጥታ ሀይሎች ከተገደሉ በኋላ እጅግ የቅርብ ወዳጆቻቸው ሳይቀሩ ፕሬዚደንት ሳላህ ከስልጣን መውረድ እንዳለባቸው ይናገሩ ነበር፡ Charles Schmitz፣Yemen’s National Dialogue ፣ a policy paper serious, PP 8 , Middle east Institute, February 2015. http://www.mei.edu/content/yemens-national-dialogue Charles Schmitz ይህ ሁሉ ሲሆንም ቀስ በቀስ ባንድ ወቅት በመካከለኛው ምሰራቅ በዴሞክራሲያዊ ጅምሯ ውዳሴን ያገኝችው የመን፤ ህዝቧ ከማዕከላዊም መንግስት ጋር ሆድና ጀርባ እየሆነ ፤መጣ። በዚህ ውስብስብ የቅራኔ ሂደት ውስጥ የአልቃይዳ ተዛማጅ የሆነው እንቅስቃሴም ስር እየሰደዱ የቅራኔው አደገኛነቱም እየጨመረ ነበር የመጣው። ለማጠቃለል የየመን የፖለቲካ ምስቅልቅል መስረቶች • አያደር እየጠበበ በመጣው የፖለቲካ ምህዳር ምክንያት በስርአቱ ውስጥ ሀሳብን በነጻ ማራመድ አይቻልም የሚለው አመለካከት በተቃዋሚውም በህዝቡም አመለካክት ውስጥ በመስረጹ • ስርአቱ በተለያየ ማጭበርበሪያ በመጥቀም ለውጥን ለማገትና ራሱን ዘላለማዊ ገዥ ለማድረግ በመሞክሩ የተለየ ራዕይ ያላችው በህጋዊነት በመታገሉ ላይ ተስፉ መቁረጣቸው • ስርአቱ በሀገሪቱ ውስጥ ለሚነሱ ጥያቈዎች አና ግጭቶች መፍትሄ ሊሰጥ ስላልቻለ በአንድ በኩል ችግሩን ለመፍታት ቅንነት የለውም በሌላ በኩል ችሎታ/ብቃት የለውም የሚለው አስተሳሰብ መስፈኑ • የስራ አጥነት መጠን አጅግ ክፍ ብሎ በወጣቱ ላይ ያሳደረው ተስፋ መቁረጥ በበበየየየመመንንን የየየሚሚሚታታታየየየውውው ምምምስስስቅቅቅልልልቅቅቅልልልናናና IIIትትትዮዮዮጵጵጵያያያ ፖፖፖለለለቲቲቲካካካ ውውውጥጥጥረረረትትት፤፤፤ AAAክክክሊሊሊሉሉሉ ሜሜሜይይይ 222000111555 4 • በጎሳ ላይ ያተኮረ ማህበራዊ ግንኝነትን ትልቅ ቦታ የሚስጥው የህብረተሰብ አደረጃጀት የገዥውን ቡድን አግላይነት በቀላሉ የጎሳ ትርጕም በመስጥት እኛ እና እነሱ ለሚለው አደገኛ አመለካለት ስፊ አድል በመክፈቱ • ደቡብ አና ስሜን የመን ሲዋሀዱ ሰራዊቱ በጊዜ ከአንድ አካባቢ ወይም ድርጅት ታማኝነት አንዲወጣና በሀገራዊ ራዕይ አንዲዋሀድ ባለመደረጉ።(ሌሎችም የታጠቁ ሀይሎች እንዲሁ ወደሀገራዊ ሰራዊትነት እንዲቀላቀሉ ሳይደረግ የፖለቲካ ድርጅቶች መሀል ግጭት ሲከሰትም ከሀገሪቱ ይልቅ ለየጎሳው ወግኖ እንዲነሳ ተመቻችቶ መገኘቱ • ከሁሉም በላይ ደግሞ አብደላሂ ሳሊህ እና ድርጅታቸው በተለያየ ደረጃ መቻቻልን እንዲያሰፍኑ፤ ስልጣንን እንዲያጋሩ፣ ንቅዘትን እንዲያሰወግዱ መብት እንዲያከብሩ፣እርቅ አንዲያወርዱ ቢለመኑም ነገሩን ሁሉ በማሳነስ በውጭ ድጋፍ ላይ እጅግ በመመካት በትምክህት የተፈጠረውን እድል ሁሉ ሊጠቀሙበት አለመቻሉ ጥቂቶቹ ነበሩ። የጸደይ አብዩት በየመን (አረብ ሰፕሪንግ)ና የዲሞክራሲ ሀይሎች ንቅናቄ የአብድላሂ ሳሊህ እና ፓርቲያቸው ህዝባዊ ኮንግረስ ፓርቲ (The General People's Congress በሚያካሂደው ያላቋረጠ የመብት ረገጣ የተነሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከህዝብ እየተነጠሉ፣ አዳዲስ ተቃዋሚወችንም በሰፊው እያፈራ በውስጡም እየተፍረከረከ ነው የተጓዘው፡፡ ባንድ ወቅት ተከፋፍላ ለነበረችው ሰሜንና ደቡብ የመን መዋሀድ ባለውለታ በመሆኑ የተወሰነም ቢሆን አክብሮት የነበራቸው አሊ አብዲላህ ሳሊህ እና ፓርቲያቸው አጠቃላይ ህዝባዊ ኮንግረስ ፓርቲ (The General People's Congress) ቀስ በቀስ በሕዝብ አክ እንትፍ ተባሉ። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2011 ሰሜን አፍሪካንና መካከለኘው ምስራቅን ያናወጠው ሕዝባዊ አመጽ ወደ የመን የደረሰው ብዙም ሳይዘገይ ነበር። እንደ ቱኒዝያና ግብጽ፣ በየመንም ህዝብ በየከተማው በነቂስ በመውጣት አሊ አብዲላህ ሳሊህና ፓርቲያቸው የያዙትን መንግስት ከስልጣን እንዲለቁ ጠየቁ። የአጠቃላይ የህዝባዊ እንቅስቃሴ ሞተር በመሆን ይህን ሕዝባዊ አመጽ የመሩት ወጣቶች ስርአቱን አስወግዶ በምትኩ መቻቻል የሰፈነባት ፣ ዴሞክርሲያዊት የመንን እውን ለማድረግ ቆርጠው ተነሱ:፡ የየመን ወጣቶች እንቅስቃሴ “civil state,” በማለት የሰየሙት ስርአት እንዲመሰረት ነበር ትኩረት አድርገው የሚጠይቁት። ይህ ሲቪክ መንግስት (“civil state ) በወጣቶቹ አገላለጥ በህግ የሚገዛ፣ ባስተዳደር ችሎታ ቴክኒካዊ ብቃት ያላቸውን ያቀፈ እና ከሙስና የጸዳ ስርአት ነው። ባጭሩ፣ የለውጥ ፈላጊወቹ ወጣቶቹ ፍላጎት ገዥውን ቡድን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን በምትኩ የዴሞክራቲክ ስርአትን መመስረትም ነበር። http://www.mei.edu/content/yemensnational-dialogue Charles Schmitz ትግሉ እየጠነከረ የተቃዋሚው ጎራም እየሰፋ ቢመጣም አሊ አብዲላህ ሳሊህ እና ፓርቲያቸው ግን ቀደም ባሉት አመታት እንዳደረጉት ሁሉ ይህንንም ተቃውሞ ጨፍልቆ ማለፍ ይቻላል በሚል ግምት ስልጣንን የሙጥኝ ብለው ተቀመጡ። ይህም በመሆኑ በአሊ አብዲላህ ሳሊህ እና ፓርቲያቸው ላይ ተጽእኖ ለማድረግ እና ትግሉን ለማፋፋም ፤ ከተለያየ ህብረተሰብ ክፍሎች እና የፖለቲካ ድርጅቶች ህብረት በኦገስት 2011 በበበየየየመመንንን የየየሚሚሚታታታየየየውውው ምምምስስስቅቅቅልልልቅቅቅልልልናናና IIIትትትዮዮዮጵጵጵያያያ ፖፖፖለለለቲቲቲካካካ ውውውጥጥጥረረረትትት፤፤፤ AAAክክክሊሊሊሉሉሉ ሜሜሜይይይ 222000111555 5 ተመሰረተ ። ይህ ብሄራዊ የምክክር ካውንስል (the National Council) ተብሎ የተሰየመው አካል 143 አባላት ያሉት ነበር።http://main.aol.com/2011/08/17/yemen-oppositionnational-council-_n_929503.html ይህ ትብብር የተለያየ የፖለቲካ አቋም እና ፍላጎት የነበራቸውን ድርጅቶች ወደአንድ መግባቢያ እንዲደርሱ በማድረግ በተፍረከረከችው ሀገራቸው ህዝብ ላይ እንደገና የተስፋ ብርሀን ብልጭ እንዲል አደረገ። በፎቶው ላይ የሚታዩት ከመሀል መሀመድ ባሲንደዋህ (Mohammed Basindwah) አዲስ የተመሰረተው የተቃዋሚወች ትብብር ፕሬዚደንት፡ በግራ በኩል አብደል ዋሂብ አል አነሲ (, Abdul Wahab Al-Anesi) የ እስላማዊው ኢስላህ ፓርቲ ( Islah Party ) ዋና ጸሀፊ በቀኝ በኩል ደግሞ የየመን ሶሻሊስት ፓርቲ ዋና ጸሀፊ ያሲን ሰኢድ ኑማን (Yasin Said Numan,) ናቸው። http://main.aol.com/2011/08/17/yemenopposition-national-council-_n_929503.html ተቃዋሚው ራሱን አሰባስቦ ተከታታይ ሰላማዊ ግፊትን በማድረግ አሊ አብዲላህ ሳሊህ ከስልጣናቸው እንዲለቁ ጥሪውን ቀጠለ። ከፖለቲካ ድርጅቶች እና የወጣቱ መሪዎች በተጨማሪም ብዙ ታዋቂ ግለሰቦችም በህዝባዊው እንቅስቃሴው አሊ አብዲላህ ሳሊህን ከስልጣን በማስወገድ በምትካቸውም ሁሉን አቀፍ ዴሞክራሲያዊ ስርአትን ለመመሰረት ለሚደረገው ትግል ድጋፋቸውን ሰጥተው ነበር። ከነዚህም ውስጥ ከዚህ በታች ምስላቸው የሚታየው በ2012 የኖብል ሽልማት አሸናፊ የሆኑት ተዋኩል ካርማን (Tawakul Karman) አንዷ ናቸው። የኖብል ሽልማት አሸናፊ የሆኑት ተዋኩል ካርማን በበበየየየመመንንን የየየሚሚሚታታታየየየውውው ምምምስስስቅቅቅልልልቅቅቅልልልናናና IIIትትትዮዮዮጵጵጵያያያ ፖፖፖለለለቲቲቲካካካ ውውውጥጥጥረረረትትት፤፤፤ AAAክክክሊሊሊሉሉሉ ሜሜሜይይይ 222000111555 6 የየመን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ከሞላ ጎደል እጅግ በሚያሰገርም መረጋጋት ትግሉን ሁሉ በሰላማዊ መንገድ ቢያካሂድም ፣ ጽንፈኛ የሆነው የአልቃይዳ እና ከእሱም ጋር የተባበሩ ታጣቂዎች በሰላማዊ ትግሉ ውስጥ አየተቀላቀሉ አልፎ አልፎ ንቅናቄውን የመሳሪያ ሀይል የተጨመረበት ሲያደርጉት ታይቷል። በወቅቱ አሜሪካኖች “ተቃዋሚውን ከሳላህ መንግስት ጋር በመሆን በኃይል ያጠቃሉ” እየተባለ ይነገር ለነበረው ተቃውሞ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካን ባለስልጣን ሁኔታውን እንዲህ ሲሉ ገልጸውታል “ የአልቃይዳ ስርጎገቦች ከሌሎች ጸረ መንግስት ሀይሎች ጋር ተቀላቀቅለው ስለሚንቀሳቀሱ አሜሪካን በየመን የሚገኙ ያልቃይዳ አማጽያን ላይ የሚወሰደው የሀይል እርምጃ ለመንግስቱ የወገነች ሳትመስል መንቀሳቀስ እጅግ ከባድ ነው” http://www.nytimes.com/2011/06/09/world/middleeast/09intel.html የሳላህ መንግስትና የሀያላኑ ግንኙነት የመን ከምእራቡ ሀገር በተለይም ከአሜሪካን እና ከሳውዲ አረብያ ጋር የቅርብ ግንኑነት ያላት ሀገር ናች። ያሜሪካን ዋና ትኩረት በየመን ውስጥ መሽጎ የሚገኘውን የአልቃይዳ ድርጅት መደምሰስ ነው፡፡ በሌላ በኩል የሳውዲ አረብያ (እንዲሁም የሌሎቹ የጎልፍ ሀገሮች) ዋና ፍላጎት ደግሞ በየመን ሺዓ ሙስሊሞች በኩል ሊደርስብኝ ይችላል ብላ የምትሰጋበትን የኢራን መንግስት ግፊት መቋቋም ነው። የኢራን የኃይማኖት መሪዎች ለሳውዲ ንጉሳዊ ቤተሰብ ፍቅር እንደሌላቸው ብቻ ሳይሆን ስራቸው ሁሉ ከእስልምና ህግጋት ጋር የተጻረረ ስለሆነ መወገድ አለባቸው ብለው በይፋ በተደጋጋሚ ተናግረዋል። ኢራኖች በተለይም የሺዓ እምነት ተከታይ የሆኑትን የሁቱ ነገድ ሙስሊሞችን ተከታታይ የመነሳሳት እንቅስቃሴ ስለሚደግፉ ይህ እንቅስቃሴ እንዳያድግ እና እናዳይጠናከር ሳውዲዎችም ሆኑ ሌሎች የገልፍ መንግስታት አጥብቀው ይጥራሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ በየመን ውስጥ እነሱ የሚቆጣጠሩት ወይም ለነሱ ታማኝ ያልሆነ መንግስት እንዳይመሰረት እጅግ ይሰጋሉ። የመን ከሳውዲ ጋር ባላት የድንበር አዋሳኝነት የተነሳ በየመን ውስጥ የሚደረግ ነገር ሁሉ ሳውዲን ይነካል ብለው ስለሚሰጉ ፣ የሳውዲ ባለስልጣኖች የመንን ባይነቁራኛ መመልከት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ አካሄዷን ለመቆታጠር ሁልጊዜም ይጥራሉ። የሳላህ መንግስት ለአሜሪካንም ይሁን ለሳውዲ የነበረው ታማኝነት 100% በላይ ነበር ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህም በመሆኑ ህዝበዊ ትግሉ እጅግ በተፋፋመበት እና በለውጥ ፈላጊው የዴሞክራሲአዊ ሀይሎች ላይ ስርአቱ ታላቅ ጭፍጨፋ ያካሂድ በነበረበት በ 2011 መጨረሻ ሳይቀር አሜሪካ ለሳላህ መንግስት የ 120 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ፣ ባብዛኛው ወታደራዊ ሰጥቶ ነበር። በማርች 2012 ዘ ኔሽን በተሰኝው ጋዜጣ ላይ የቀረበ አንድ ሪፖርት እንዳለውም በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ1980ቹ ከተጀመረው ሶቭየት ህብርትና ከአፍጋኒስታን የማስወጣት ጦርነት ጀምሮ ከዚያም የ 9/11 ን ሽብር ተከትሎ የሳላህ መንግስት አልቃይዳንና ጸረ ሽብርተኛነትን እንደማሰፈራሪያ በመጠቀም ካሜሪካኖች እና ከሳውዲ አረብያ ስልጣኑን ለማጠናከር እና ተቃዋሚወቹንም ለማዳከም የሚያስችለው ከፍተኛ ድጋፍን አካብተውበታል http://www.thenation.com/article/166265/washingtons-war-yemen-backfires በበበየየየመመንንን የየየሚሚሚታታታየየየውውው ምምምስስስቅቅቅልልልቅቅቅልልልናናና IIIትትትዮዮዮጵጵጵያያያ ፖፖፖለለለቲቲቲካካካ ውውውጥጥጥረረረትትት፤፤፤ AAAክክክሊሊሊሉሉሉ ሜሜሜይይይ 222000111555 7 በውጭ ግንኙነት ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚንቀሳቀሰ አንድ ድርጅት (ካዉንስል ፎር ፎሬን ሪሌሽን ) በቅርቡ እንደዘገበው አሜሪካ ለፕሬዚዳንት አሊ ሳሊህ መንግስት ያደረገችው እርዳት ከአመት ወደ አመት እጅግ ፈጣን በሁነ መልክ ሲየድግ ነበር የቆየው፡ http://www.securityassistance.org/yemen የምእራቡ አለም እና ያካባቢው መንግስታት ነጠላ ጥቅም ላይ ያተኮረ አካሄድ በዴሞካራሲ እንቅስቃሴው ላይ ያሳደረው እንደም የየመን ህዝባዊ እንቅስቃሴ እያደገ ቢመጣም አሜሪካኖች ከሳላህ በኋላስ ምን ይሆናል ለሚለው በቂ ዝግጅት አላደረጉም ነበር። ሳውዲዎችና የጎልፍ መንግስታትም ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ነበር:: ከሳላህ በኋላ የሚመጣው መንግስት ከቁጥጥራቸው ውጭ ቢሆንስ የሚለው እጅግ አሰጨቋቸው ነበር ። በተቃዋሚው እና በምእራቡ መንግስታት መካከል የተወሰነ ግንኙነት ቢደረግም፣ የአብዳላሂ ሳላህ ቢወገዱ ባልካይዳ ላይ ለሚያካሂዱት ጥቃት ተቃዋሚው ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ይስጥ ይሆናል ወይ ለሚለው ጥያቂ ባሜሪካኖች በኩል በተወሰነ ደረጃ እርግጠኞች አልነበሩም። ተቃዋሚው የብዙሀን ፓርቲ ስርአትን፣የምእራቡን የሚመስል ዴሞክራሲ ፣ አሰፍናለሁ ቢልም ላሜሪካኞች ይህ ቅድሚያ የሚሰጡት አልሆነም፡፡ ስለዚህ ሙሉ በሙሉ የስርአት ለውጥን ከመደገፍ ይልቅ ሳላህን አስወግዶ ስርአቱን ግን ማስቀጠሉን ስራዬ ብለው ተያያዙት። የሳውዲ አረብያና ሌሎችም የጎልፍ መንግስታትም በተመሳሳይ መንገድ ያቀረቡት የውሳኔ ሀሳብ አብደላሂ ሳላህን አስወግዶ በቦታው ምክትል ፕሬዚደንቱን አብዱ ረቡ ማንሱር ሃዲ ( Abdu Rabbu Mansour HadI) ወደስልጣን ማምጣት ነበር። በዚህም መሰረት ያሜሪካውኑ ፕሬዚደንት የተከበሩት ባራክ ኦባማ የጸረ ሽብር አማካሪና በኋላም የሲአይኤ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ጆን ብረናን (John Brennan), ፕሬዚደንት ሳላህን በሳውዲ አረብያ ከሚገኙበት ሆስፒታል ከጎበኙዋቸው በኋላ ስልጣናቸውን እንዲለቁና ለምክትል ፕሬዝደንቱ እንዲያስተላልፉ ነገሯቸው፡፡ http://www.aljazeera.com/news/middleeast/2011/07/201171016636884366.html የተቃዋሚዎች ህብረትም ሆነ ለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ይህንን የሳውዲና ያሜሪካ እቅድ ፈጽሞ አልተቀበሉትም ፡ የህዝቡን እንቅስቃሴ ለማምከን የሚደረግ ሴራ ሲሉ ነበር ያወገዙት። ተቃዋሚው በስርአቱ ውስጥ ሙሉ ተሳታፊ መሆን እንዳለበት አበክሮ ቢያሳሰብም የገልፍ መንግስታትም ሆኑ አሜሪካ አልደገፉትም። የሽግግር እቅድ ተብሎ ባሜሪካና በገልፍ መንግስታት (ሳውዲ፣ ኳታር፣ ባህሬን ) የቀረበውም ሁሉን አቀፍ መንግስት መመስተረትንም ሆነ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወዲያውኑ ማካሄድን ያካተተ አልነበረም። የተፈለገው የሳሊህን ምክትል ወደ ፕሬዚደንትንት አምጥቶ መቀጠል ነበር። ይህ ከህዝቡና ከአክቲቭስቶች ፍላጎት ጋር የተቃረነና ዴሞክራሲያዊ አካሄድን የሳተ ቢሆንም በወቅቱ ያሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሰራቅ ሀላፊ የነበሩት ሚስተር ጀፍሪ በበበየየየመመንንን የየየሚሚሚታታታየየየውውው ምምምስስስቅቅቅልልልቅቅቅልልልናናና IIIትትትዮዮዮጵጵጵያያያ ፖፖፖለለለቲቲቲካካካ ውውውጥጥጥረረረትትት፤፤፤ AAAክክክሊሊሊሉሉሉ ሜሜሜይይይ 222000111555 8 ፌልትማን (Jeffrey Feltman, the Assistant Secretary of State for Near Eastern Affairs,) ይህንኑ እቅድ እንደሚደግፉ አስታወቁ ። http://foreignpolicy.com/2012/05/02/where-democracy-is-americas-second-choice/ ያሜሪካን መንግስት የወሰደውን አቋም እንዲያስተካክል የኖቤል ሽልማት አሽናፊዋ የመናዊት ተዋኩል ካርማን (Tawakul Karman) እንዲህ ሲሉ ተማጸኑ “ዩናትድ ስቴትስ አሜሪካንን በሽብርትኛነት ላይ ያላትን ጭንቅ እንገነዘባለን። ያሜሪካን ደህንነት ለመጠበቅ ከየመን ጋር አሜሪካ ያላትን ስምምነት ማክበርን በተመለከተ ምንም ችግር የለንም ። እኛ የምንጠይቀው አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት መለኪያወችን እንድትከተሉና የየመንንም ህዝብ ለነጻነት፣ ለስብአዊ መብቱና ፣ ለፍትህ መስፈን ፡ያለውን ፍላጉቱን እንድታከብሩለት ብቻ ነው። በሸዎች በሚቆጠሩ የየመን ወጣቶች ስም ከእናንተ ጋር በሙሉ ሽሪክነት አብረናችሁ ለመቆም ዝግጁነታችንን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ ከእናንተ ጋር በጋራ፣ ሆነን ጽንፈኛነት እንዳይቀፈቀፍ አመች ሁኔታ የሚፈጥረውን መደላድሎች ፣ ልማትን ተጋባራዊ በማድረግ እና ነጻ የሲቪክ ማህበራትን በመመስረት እናስወግዳለን፣፡ መረጋጋትንም እውን እናደረጋለን። ለዚህም ለውጥ ፈላጊወችን እንድትደግፉና ከሽብርተኞች ይልቅ ንጹሀን የመናውያንን የሚገድለውን ስርአት መደገፍ እንድታቆሙ እማጸናለሁ”፡፡ http://www.nytimes.com/2011/06/19/opinion/19karman.html?pagewanted=all&_r=0 ያም ሆኖ ግን ሰሚ አላገኙም። በወቅቱ የለውጥ ፈላጊዎቹ ወጣቶች መሪ ከነበሩት ውስጥ አንዱ ኻሊድ አለ አኒስ (Khaled al-Anesi) ትግላችን እና አብዮቱ ከጀርባ ነው በጩቤ የተወጋው ነበር ያለው "This revolution has been stabbed in the back." http://news.antiwar.com/2012/02/27/reform-minded-youth-movement-marginalized-in-postsaleh-yemen/ ባሜሪካን ነዋሪ የሆኑ ትውልደ የመኖችም ተመሳሳይ የለውጥ ፍላጎታቸውን ለአሜሪካ ባለስልጣናት አሰምተው ነበር። አብዱላሂ ሳላሀ አርፈውበት በነበረው በኒውዮርክ ሪትዝ ካርልተን (Ritz-Carlton ) ሆቴል ፌት ለፌት የተቃውሞ ስልፍ ካካሄዱት ውስጥ ጥቂቶቹ (ፎቶ ከኒው ዮርክ ታይምስ 2012) በበበየየየመመንንን የየየሚሚሚታታታየየየውውው ምምምስስስቅቅቅልልልቅቅቅልልልናናና IIIትትትዮዮዮጵጵጵያያያ ፖፖፖለለለቲቲቲካካካ ውውውጥጥጥረረረትትት፤፤፤ AAAክክክሊሊሊሉሉሉ ሜሜሜይይይ 222000111555 9 ይህ ሁሉ የህዝብ ተቃውሞ እያለ በተጻራሪው መንገድ እንዲጓዝ በመደረጉ ህዝባዊ ንቅናቄው በተጀመረው መልክ ቢቀጥል የሚፈለገው ነጻነት፣ የመብት መከበር፣ ዴሞክራሲ ወዘተ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል የሚለው አመለካከት በጥርጣሬ መታየት ጀመረ። ሌሎች አማራጮችንም የመመርመር ጉዳይ ትልቅ ቦታ ያዘ። አቡበከር አልሸማሂ የተባለ አንድ በትውልደ የመናዊ የሆነ እንግሊዛዊ ጋዜጠኛ የምእራቡ አለም የስርአት ለውጥ እና የዴሞክራሲ እንቅስቃሴውን በመደገፍ በዋናነት የሚፈሩትን አላቃይዳን ለማዳከም እንደሚቻል ይህ ሳይሀን ቢቀር ግን ቀጣዩ ሁኔታ ለየመንም ላካባቢውም መልካም ነገርን እንደማያመጣ ልብ ያለው ልብ ይበል ሲል የማስጠንቀቂያ ደወል አስምቶ ነበር:: http://www.aljazeera.com/indepth/opinion/2011/08/2011847134790380.html የዚህ ወጣት ጥሪ፣ የኖቤል ሽልማት ተሸላሚዋ፣ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ህብረትም ሆነ ለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ድምጽ ግን አድማጭ አላገኘም። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው አልቃይዳና ሌሎችም ኃይሎች “ብለናችሁ ነበር፣ የምንፈልገውን ለማገኝት የራሳችንን ጉዞ መጀመር ነው የሚያዋጣን” በማለት ወጣቱን ከሰላማዊ የትግል ጎዳናው ወጥቶ ለሚፈልጉት ግብ እንዲሰለፍ ሰፊ የመመልመያ መሳሪያ ያገኙት። የየመን ህዝባዊ ትግል መደናቀፍና ለየት ያለ ተቃውሞው መበራከት የዴሞክራቲክ ሂደቱ መደናቀፍ የሳላሀ መንግስት ደጋፊወች፣ምእራባውያንና የገልፍ መንግስታት እንደተመኝት ሳይሆን ለገዝው ፓርቲ መንኮታኮት ለፕሬዚደንቱ ሰደት፡ በየመን ውስጥ ላክራሪዎችና ለቀጣይ ምስቅልቅል የተመቻቸ ሁኔታን ነው የፈጠረው። በቅርቡ የቀረበ ጥናት እንዳሳየውም፣ ሀገሪቱ ምስቅልቅል ውስጥ መግባት አልቃይዳን ተጠቃሚ አድርጎታል። http://www.cfr.org/yemen/yemencrisis/p36488?cid=nlc-publicthe_world_this_week-highlights_from_cfr-link16 20150501&sp_mid=48567537&sp_rid=YWRtaW5AYWlnYWZvcnVtLmNvbQS2 ባሜሪካን ጸረሽብር ሀይሎች እና በሰው አልባ አይሮፕላን ጥቃት በተከታታይ በደረሰበት ጥቃት እጅግ ተዳክሞ የነበረው አልቃይዳ በ ኤፕሪል 2015 ሙላካ (Mukallah) በተሰኘችው ከተማ የሚገኝ እስር ቤት ሰብሮ በመግባት በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቹን አስለቅቋል። http://www.longwarjournal.org/archives/2015/04/aqap-storms-yemeni-prison-frees-al-qaedaleader.php በመቀጠልም በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ አምስት ኬላዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። http://english.alarabiya.net/en/variety/2015/04/05/AL-Qaeda-makes-itself-at-home-in-Yemenpalace.html በኤፕሪል 17፣ 2015 እንደተዘገበውም፣ በሀገሪቱ ምስራቃዊ ግዛት የሚገኝ የመንግስት ኃይል አሸንፎ፣ እጅግ ሰፊ የሆነ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ተቆጣጥሯል http://www.dailystar.com.lb/News/Middle-East/2015/Apr-17/294823-al-qaeda-takes-keyyemen-army-camp-heavy-weapons-official.ashx በበበየየየመመንንን የየየሚሚሚታታታየየየውውው ምምምስስስቅቅቅልልልቅቅቅልልልናናና IIIትትትዮዮዮጵጵጵያያያ ፖፖፖለለለቲቲቲካካካ ውውውጥጥጥረረረትትት፤፤፤ AAAክክክሊሊሊሉሉሉ ሜሜሜይይይ 222000111555 10 መሰረቱን ጎሳ ያደረገው የየመን ፖለቲካ አሁንም ተጠናክሮ ሀገሪቱን ወደተወሳሰበ አሳዛኝ ክፍፍል ይዟት በመጓዝ ላይ ይገኛል። http://www.al-monitor.com/pulse/originals/2013/10/yemen-tribesrevolution-politics-saleh.html# የሀሽድ (Hashid ) ጎሳ ተዋጊወች በሰንአ (Sanaa, ) ከተማ ውስጥ ጎዳናወችን ሲቆጣጠሩ (ፎቶ በ ካሊድ አብደላሂ፣ ሮይተር፣ ዲሰምበር 2011) አሊ ሳላህን፣ የተኳቸው ፕሬዚደንት ሃዲና ፓርቲያቸው ከስልጣን ተባረው እነሆ ዛሬ የስደት ፕሬዚደንት ሆነዋል። ባጠቃላይ የፕሬዚደንት አሊ ሳላህ መንግስት የዲሞክራሲ እንቅስቃሴውን ለማጨናገፍ ቀና ደፋ ሲል እና ባለው ኃይል ሁሉ ሲሯሯጥ አልቃይዳ፣ የሁቲ አካራሪዎችና ሌሎችም ጎሳ ነክ ኃይሎች እጅግ ተጠናከሩ። የፕሬዚደንቱ የስልጣን ጥም ፣ ግትርነትና እኔ ያልኩት ብቻ ካልሆነ ብሎ ድርቅ ማለት መጨረሻው የዴሞክራሲያዊ ኃይሎች መዳከም፣ የስርአቱ ሀገሪቱን ሊገዛ አለመቻል፣የሀገሪቱ አንድነት መናጋት፤ የአልቃይዳ መጠናከር፣የተገንጣዮች እንቅስቃሴ መጠናከር፡ ሀገሪቱ የሰፊ ጦርነት አውድማ መሆን እና ከራሷም አልፋ ላካባቢው ሁሉ አደጋን መጋረጧ ጥቂቶቹ ናቸው። በበበየየየመመንንን የየየሚሚሚታታታየየየውውው ምምምስስስቅቅቅልልልቅቅቅልልልናናና IIIትትትዮዮዮጵጵጵያያያ ፖፖፖለለለቲቲቲካካካ ውውውጥጥጥረረረትትት፤፤፤ AAAክክክሊሊሊሉሉሉ ሜሜሜይይይ 222000111555 11 አፍቃሪ ኢራን የሆኑት የሁቴ አማጽያን ሰንአ (Sanaa ) ከተማን ከተቆጣጠሩ በሐላ በሳውዲ አረቢያ የሚመራውና ባሜሪካ የሚደረፈው የአየር ጥቃት እንደማይበግራቸው በሰልፍ ሲገልጽ ( ፎቶ በሀና ሞመመድ፣ ዐሶሽየትድ ፐረስ 2015) የየመን ምስቅልቅል ሰለባ፤ በደም የተነከረ የወገኑን ልብስ ሲያሳይ (ፎቶ በ ቢቢሲ አፕሪል 2015) እእእኛኛኛስስስ??? የየመን ሁኔታ የህዝብን መብት ረግጦ፣ ሌሎችን አግልሎ፣ ተለጣፊ ድርጅቶችን ሰብስቦ መግዛት ይዋል ይደር አንጂ በዘላቂነት ሊቀጥል እንደማይችል በርግጠኛነት ያሳያል። የውጭ መንግስታት ድጋፍ፤ ጊዚያዊ ጥንካሬን አንጂ ዘለቄታ ያለው በህዝብ ዘንድ ከበሬታን እና ፍቅርን ሊያሰገኝ እንደማይችልም ያመለክታል፡ በጎሳ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ መዘዙ እጅግ ሰፊ እንደሆነም ያሳያል። በበበየየየመመንንን የየየሚሚሚታታታየየየውውው ምምምስስስቅቅቅልልልቅቅቅልልልናናና IIIትትትዮዮዮጵጵጵያያያ ፖፖፖለለለቲቲቲካካካ ውውውጥጥጥረረረትትት፤፤፤ AAAክክክሊሊሊሉሉሉ ሜሜሜይይይ 222000111555 12 በሀገራችን ፖለቲካ መድረኩን ለብቻ ሙጭጭ ብሎ መያዙ ፤ የመብት ረገጣው፣ ህዝብን ተስፋ የሚሰጥ ሁኔታ እየተሟጠጠ መምጣቱን ከገዥው ወያኔ/ኢህአዴግ በስተቀር የሚክድ የለም። በሀገሪቱ ውስጥ የሚታየው ውጥረትም የተለያየ መልክ እየያዘ፣ እጅግ እየተካረረ እንጂ እየረገበ መፍትሄም እያገኘ አይደለም የመጣው። በገዥው ቡድን በህጋዊነት የሚንቀሳቀሱትን ፖለቲካ ድረጅቶችንም ሆነ የሲቪክ ድርጅቶች ሰበብ እየፈለገ በፍጹም እነዳይንቀሳቀሱ እያደረገ ስለመጣ፤ በዚች ሀገር ውስጥ በዚህ ስርአት ውስጥ መብትን በህግ ስር ሆኖ ለማስከበር መሞከር ከንቱ ሙከራ ነው የሚለው ስሜት እጅግ ፈጣን በሆነ መልክ እየተስፋፋ ይገኛል፡ የምእራብ መንግስታትን በተመለከተም በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ታላቅ ድጋፍ ሊያበረክቱ እንደሚችሉ ግንዛቤ ቢኖርም ፣ በተግባር እንደታየው ግን ዴሞክራሲን ፣ እኩልነትን ፣ ፍትህን ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ለእነርሱ በዋነኛነት ቅድሚያ የሚሰጡት እንዳልሆነ ነው። ሀገራችን ሁሉን አቀፍ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ከሚፈልጉ ጀምሮ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር መቀጠል የለባትም እስከሚሉ ድርጅቶች የተለያየ አይነት ትግል በውስጥም በውጭም የሚያካሂዱባት ሀገር ነች። የጎሳ መርዝ እጅግ ስር ሰዷል፡ በሰራዊቱም በፖሊሱም ውስጥ የጎሳ ቅኝት ሰፊ ነው። ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ እንደሻቢያ ያሉ እና ሌሎችም ጠላቶች ኢትዮጵያን ከበዋት ይገኛሉ። በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አልቃይዳ፣ አሁን ደግሞ ኢሰላሚክ ሰቴት በአይነ ቁራኛ ከሚያዩዋቸው ሀገሮች አንዷ ለመሆኗ በየጊዜው በአልሸባብ የተነገረውን እና በኤፕሪል ወር ደግሞ በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን አንገት መቅላት እና በጥይት ደብድቦ መግደል ማገናዘቡ ይበቃል። ይህ ሁሉ የሀገራችንን አደጋ እጅግ ሰፊና ውስብስብ እንደሆነ ያሳያል። በሀገሪቱ የሚታየው ውጥረት ገንፍሎ እንደሚፈነዳ በርግጠኛነት መናገር ይቻላል ፤ ጥያቄው መቼ እና በምን መልክ የሚለው ብቻ ይሆናል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉትን አደጋዎች ለማስወገድ ካልተቻለም ለመቀነስ ምን መደረግ አለበት የሚለው እጅግ አስቸኳይ መፍትሄን የሚሻ ሁሉንም ሊያስጨንቅ ሊያስጠብብ የሚገባ ጉዳይ ነው። ማማማጠጠጠቃቃቃለለለያያያ ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጎቿ ሀገር ነች። ለኢትዮጵያ አንድነት አንድ ድርጅት ብቻ ሳይሆን እጅግ ብዙ ዜጎች ያሰባሉ፡ ለብሄር ብሄረሰቦችም እኩልነት እንዲሁ። በዚህ አኳያ የሁሉም አመለካከከት በክብር ሊስተናደግ የሚችልበት በጠንካራ እሴቶቻችን ላይ በማተኮር በኢትዮጵያዊነት በጋራ የመኩራት ሄደት ተጠናክሮ የሚወጣበትን መደላድል መፍጠር ግድ ይላል። የተለያዩ ቅሬታዎችና አዳዲስ አመለካከቶች በሰላማዊ መንገድ በሙሉ ቅንነት ሊስተናገዱ የሚችሉበት መድረክ ሊፈጠር ይገባል። ወጣቶች አዛውንቶች ;የተማረ ያልተማረ፣ ሁሉም ዜጎች ሀገራቸውን ጥለው በባሌም በቦሌም እንዲሰደዱ የሚያደርጓቸው የፍትህ መጥፋት፣ የህግ የበላይነት በበበየየየመመንንን የየየሚሚሚታታታየየየውውው ምምምስስስቅቅቅልልልቅቅቅልልልናናና IIIትትትዮዮዮጵጵጵያያያ ፖፖፖለለለቲቲቲካካካ ውውውጥጥጥረረረትትት፤፤፤ AAAክክክሊሊሊሉሉሉ ሜሜሜይይይ 222000111555 13 መጥፋት፣ የተስፋ ማጣት ወዘተ ሁኔታዎች ሊስተካከሉ የሚችሉበት ስርአት እውን መሆን አለበት። ለዚህም ችግሩን በጋራ በቅንነት ለመፍታት በቁርጠኛነት መነሳት ያሰፈልጋል። የፖለቲካ ድርጅቶች የማምንበትን ራእይ ተግባራዊ ለማድረግ ከውጭ ጠላትም ጋር ቢሆን እሰለፋለሁ የሚያሰኛቸው የፖለቲካ ድባብ እንዲወገድ የሚያስችል መተማመን፣ መፈጠር ይኖርበታል። በስልጣን ላይ ያሉ ፖለቲካ መሪዎች መጨረሻቸው፣ እስርቤት፣ ስደት ወይም ክብር የሌለው ሞት የሆነበትን ስርአት እንዲያከትም ማድረግ የግድ ነው። በምትኩም በፖለቲካ ራእይ ልዩነት የተነሳ እንደጠላት መተያየት የሚወገድበትን መሰረት መጣል፣ ያመጽ አዙሪትን መሰረት ማፍረስ ያሰፈልጋል። ለዚህም አሳታፊ ፣እውነተኛ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ስርአት መስረት መጣል፡ የግድ ይላል። ባለንብረቶች አንዱ ፖለቲካ ፓርቲ ከስልጣን ሲወርድ ንብረታቸው የሚነጠቅበት፣ የጦር መኮንኖች እና ሌሎች ባለስልጣኖች የውርደት ኑሮ እንዲኖሩ የሚገደዱበት ስርአት ማብቃት አለበት። ይህንን ለማድረግ ደግሞ መመካከር የግድ ነው፡፡ የተቃዋሚው ባስቸኳይ ማበር አስፈላጊ ነው። የብሄራዊ መግባባትና እርቅ መሰረትን መጣል የግድ ነው። የዚህ ጉዳይ ተግባራዊ መሆን የረፈደ ቢመስልም እጅግ ሳይዘገይ አሁኑኑ ሊሆን ይገባዋል። የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑ መንግስታትም ሆኑ በዚች ሀገር ደህንነት ተጠቃሚ ነን የሚሉ ሁሉ ለዚህ ተግባር መደናቀፍ ሳይሆን መሳካት ነው ድጋፍ ሊሰጡ የሚገባው። የነርሱም ጥቅም በዘላቂነት የሚጠበቀው በተረጋጋ፣ህግ በሰፈነበት፣ መብት በተረጋገጠበት መቻቻልና ነጻነት በሰፈነበት ስርአት ውስጥ ብቻ እንደሆነ የመን ምስክር ነች። ቀደም ብየ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የጠቀስኩት አቡበከር አልሸማሂ የተባለው የየመን ትውልድ ያለው እንግሊዛዊ ወጣት በ 2011 ሀገሩን በተመለከተ ካሰማውን የአደጋ ደውል እና ካቀረበው ጥሪ ጋር የሚመሳሰል መልእክት እኔም ለማሰማት እፈልጋለሁ። የኢትዮጵያ ሁኔታ እጅግ አሳሰቢያ እጅግ ፈታኛና አጣዳፊ መፍትሄን የሚሻ ነው። በሀገሪቱ ላይ ጥቁር ደመና አንዣቧል። ጭንቀት ሰፍኗል። ውጥረት በዝቷል። ተስፋ ማጣት ተስፋፍቷል። አሁንም ቢሆን ይህን ጭንቅ ለማስወገድ አደጋውን ለማስወገድ የተወሰነ እድል አለ፡ ይህ ደግሞ ደፈር ያለ አዲስ እርምጃን ይጠይቃል። ይህን እውነታ በመካድ ወይም በማድበስበስ ለማለፍ መሞከር ለኢትዮጵያም ለአካባቢውም መልካም ነገርን እንደማያመጣ ልብ ያለው ልብ ይበል። ላስተያየት ethioandenet@bell.net 

ግብጾች ለኢትዮጵያዉይን ሲቆሙ ሕወሃቶችስ ? – ናኦሚን በጋሻው

የዙሉ አክራሪዎች በኢትዮጵያዉያን እና ሌሎች የአፍሪካ ዜጎችን ላይ ኢሰብዓዊ ጥቃት በሚፈጽሙበት ጊዜ፣ እንደ ናይጄሪያ ያሉ አገሮች በዙማ መንግስት ላይ ጠንካራ አቋም ወሰዱ። ዙማ ተጽኖ ሲበረታባቸው፣ አስቸኳይ እርምጃዎች ለመዉሰድና ነገሮችን ለማረጋጋት ተገደዱ። ከነናይጄሪያ በደረሰው ግፊትና ጫና በደቡብ አፍሪካ ያለው ሁኔታ ለጊዜውም ቢሆን መረጋጋት ታየበት። በዚሁ ሁሉ ግን ሕወሃት/ኢሕአዴጎች የተከሰተዉን ቀውስ አሳንሰው በማቅረብ፣ ለኢትዮጵያዉያን ጥብቅና የቆሙ ሳይሆን፣ የዙማ ቃላ አቀባይ ነበር የመሰሉት።
ብዙም አልቆየም፣ እሁድ ሚያዚያ 11 ቀን በሊቢያ ወገኖቻችን አንገታቸው ተቀላ። ኢትዮጵያ በትልቅ ሐዘን ተመታች። የዚያኑ ቀን ቢቢስ፣ አል ጃዚራ፣ ሲ.ኤን.ኤን የመሳሰሉ ታላላቅ ሜዲያዎች ኢትዮጵያዉያን ክርስቲያኖች እንደተገደሉ መዘገብ ጀመሩ። ሰኞ ሚያዚያ 12 ቀን የአሜሪካ መንግስት በይፋ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለሕወሃት/ኢሕአዴግ የሐዘን መግለጫ አቀረበ። ሆኖም ሕወሃት/ኢሕአዴግ ዜናውን አሳንሶ በማቅረብ፣ እንደ ሶስተኛ ተራ ዜና «በሊቢያ ስደተኞች በአይሰስ ተገደሉ። አንዳንድ ሜዲያዎች ኢትዮጵያዉይን ናቸው ይላሉ። ግን ኢትዮጵያዊ ስለመሆናቸው ምንም አይነት ማረጋገጫ የለም» ሲል ኢትዮጱያዉያን መሆናቸውን በኢቢሲ/ኢቲቪ ካደ። የሚያስብና የሚጨነቅ መንግስት እንደሌለ በመገለጽ ሕዝቡ በራሱ አነሳሽነት ተቃዉሞዉን እና ሐዘኑን፣ ሀሙስ ሚያዚያ 15 ቀን እንዲገልጽ የሐዘን እና የተቃዉሞ ቀን በሚል፣ በሶሻል ሜዲያ ዘመቻዎች ተከፈቱ።ሰልፎችና የሥራ ማቆም አድማዎች ተጠሩ።
በነጋታው ማክሰኞ ሚያዚያ 13 ቀን ከሶሻል ሜዲያ ፎቶዎችን በማየት ልጆቻቸው እንደሞቱ ያረጋገጡ ወላጆች፣ በጨርቆስ አካባቢ ድንኳን ጣሉ። ያኔ በጨርቆስ ያሉ ሰላዮች መረጃዎች ለጌቶቻቸው አቀረቡ። ብዙም አልቆየም ሰበር ዜና ብሎ፣ ኢቢሲ/ኢቲቪ የተገደሉት ኢትዮጵያዉይን መሆናቸውን ፣ ፓርላማው በነጋታው ተሰብስቦ የሶስት ቀን የሐዘን ቀን እንደሚያወጅ ገለጸ። የዚያኑ ቀን በጨርቆስና ሌሎች በርካታ ቦታዎች፣ ሐሙስን ሳይጠበቁ፣ የተለያዩ የተቃዉሞና የሐዘን ሰልፎች ተደረጉ።
ሕወሃት/ኢሕአዴግ የሐሙስን ሰልፍ ለማጨናገፍ ሲል፣ ቀድሞ፣ ረእቡ ሚያዚያ 14 ቀን ሰልፍ ጠራ። በሰልፉ ህዝቡ ሐዘኑን ገለጸ። ተቃዉሞዉን አሰማ። ሆኖም ዜጎች በአደባባይ በግፍና በጭካኔ ተደበደቡ። ከአንድ ሺህ በላይ ታሰሩ። በሰልፉ ወቅት «እኛን ከምትደበድብ፣ አይሰስን ደብድቡ» ነበር ያላቸው። ሆኖ ሕወአት/ኢሕአዴጎቭ አይሰስ ላይ ሳይሆን ጡንቻዉን ሰላማዊ ዜጎች ላይ አሳዩ። ሴቶች ሁሉ ሳይቀሩ ተደበደቡ።
ሕወሃት/ኢሕአደግ አገር ቤት ያሉትን በማሰርና በመደብደብ ተጠምዶ ባለበት ሁኔታ፣ በሊቢያ ቁጥራቸው እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ ኢትዮጵያዉያን ችግር ላይ እንዳሉ በኢሳትና በአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ መስማት ጀመርን። ሕወሃት/ኢሕአዴግ፣ ግብጽ ባሉት አምባሳደሩ በኩል «በሊቢያ በአይሰስ እጅ ዉስጥ የገቡ ኢትዮጵያዉይስን የሉም። በሊቢያ ያለውም ሁኔታ በአንጻራዊነት ሰላም ነው» በሚል ለጉዳዩ ክብደት ሳይሰጡበት ቀረ። ሕወሃት/ኢሕአዴግ ፣ ከወዲሁ የዉሸት የሆነው ምርጫ ላይ እና አገር ቤት ያሉ ሰላማዊ ዜጎችን ማሳደዱ ላይ ጊዜና ጉልበት ማጥፋቱን ቀጠለ።
በዚህ መሐል ከሁለት ሳምንታት በኋላ ፣ የግብጽ ወታደሮች ወደ ሰላሳ የሚሆኑ ኢትዮጵያዉይንን ከአይሰስ እጅ ነጻ እንዳወጡ ተዘገበ። ኢትዮጵያዉያኑ ከሊቢያ ወደ ግብጽ ሲመጡም ፕሬዘዳንት አሲሲን ጨምሮ በርካታ የግብጽ ባለስልጣናት አቀባበል አደረጉላቸው። ኢትዮጵያውያኑ፣ መንግስታቸው ረስቷቸው፣ በግብጽ መንግስት እርዳታ ከሞት አመለጡ።
የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶር ቴድሮስ አዳኖም ኢትዮጵያዉይን ከሊቢያ ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ እንደሆነ በመናገር መንግስታቸው ጥረቱን እንደሚቀጥል በፌስ ቡካቸው ገልጸዋል። ሆኖም ሮይተርስ ፣ ኢትዮጵያዊያንን የማስወጣቱ ሥራ 100% በግብጽ እንደተሰራ ነው ያሳወቀው። በዘገባው ምንም አይነት የኢትዮጱያ መንግስት አስተዋጾ እንዳለ የገለጸበት ሁኔታ የለም። ኢትዮጵያዊያንን ይዞ የመጣውም አይሮፕላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን ሲሆን፣ ኢትዮጵያዉያኑንም ለመቀበል ዶር ቴዶርስም ሆነ ሌሎች የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባልስልጣን አልተገኙም።
እዉነቱ እንደዚያ ሆኖ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ፣ በማጭበርበር ፖለቲካ የተካነ እንደመሆኑ፣ ጅብ ከሄደ ዉሻ ጮኸ እንደሚባለው፣ «ዜጎቼን ከሊቢያ አወጣሁ» የሚል የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሊያደርግ እንደሚችልም ይገመታል።
ኢትዮጵያዉያኑ ከቤንጋዚ አካባቢ መምጣታቸው ለኢትዮጵያዉያን ሁሉ ትልቅ አስደሳች ዜናና የጸሎታችን መልስ ቢሆንም፣ አሁን በተለይም በትሪፖሊና በሚስራታ አካባቢ እጅግ በጣም በርካታ ኢትዮጵያዉያን አሉ።ትሪፖሊና ቤንጋዚን የሚቆጣጠረው ኃይል፣ ቤንጋዚን እንደሚቆጣጠረው ኃይል ከግብጽ ጋር ወዳጅነት ያለው ኃይል አይደለም። ይህ ዜና አስደሳች ቢሆንም ከፊታችን ገና ብዙ ይጠብቀናል። ላመለጡ ወገኖቻችን ጌታን እያመሰገንን፣ ገና አደጋ ላይ ላሉት ጸሎታችንን አናቋርጥ። እግዚአብሄር ጸሎትን ይሰማል። ግብጾች በዚህ መልኩ ይረዱናል ብሎ ማን ጠበቀ ?
ኢትዮጵያዉይን ግብጾችና ናይጄሪያኖች ሁልግዜ ይቆሙልናል ብለን መጠበቅ የለበንም። አሁን ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ህዝብን የሚያሸብር ሳይሆን፣ ሕዝብን የሚያገለግልና ለሕዝብ የቆመ እንዲሆን ለማድረግ ግፊታችንን ከመቼዉም ጊዘ እየበለጠ ፣ማጠናከር አለብን። በተቃዋሚ ጎራ ያለነውም ከስልጣን እና መርዛማ ከሆነው የድርጅት ፍቅር ተላቀን፣ በአገራችን ለዉጥ እንዲመጣ መሰባሰብ አለብን። አሁን ካልተነሳን መቼ ? እኛ ካልተነሳን ማን ?
(በነገራችን ላይ ህወሃት/ኢሕአዴግ የተወሰኑትን ከግብጽ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ አድርጓል። ለዚህ ምስጋና ካስፈለጋቸው መስጠት ይቻላል)11193405_818245314927071_2869514135485100463_n

Tuesday 5 May 2015

ወላይታ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ ተከለከለ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
• ‹‹ወላይታ ውስጥ መንግስት የለም›› አቶ ስለሽ ፈይሳ
blue partyበወላይታ ዞን ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ እንደተከለከለ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ በመኪና ላይ ቅስቀሳ እያደረጉ እንደነበር የገለጹት አቶ ስለሽ ሆኖም የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች በሞተር ብስክሌት በመከታተል የመኪናውን ጎማ በሚስማር በማስተንፈስ እንዲሁም የምርጫ ዘመቻ አባላቱን በመደብደብ ቅስቀሳውን ማስተጓጎላቸውን ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ ወረቀት የሚቀበለውን ህዝብ እየተከታተሉ እንደሚያስፈራሩና እንደሚደባደቡ አቶ ስለሽ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ጌትነት በሱፍቃድ የተባሉ ዕጩና ሌላ የሰማያዊ ፓርቲ አባልን ሞባይሎች በመቀማት ከፍተኛ ድብደባ እንደፈፀሙባቸው ተገልጾአል፡፡
የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ስም፣ የሚጠቀሙበትን መኪና ታርጋና ሌሎችም የፈፀሙትን ድርጊት በዝርዝር በማቅረብ ለፖሊስ ቢያቀርቡም ፖሊስ ‹‹ይህ ማስረጃ ሊሆን አይችልም›› በሚል ለተፈፀመባቸው በደል ምንም አይነት ትኩረት እንዳልሰጠው አቶ ስለሽ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠቱ ለዞኑ የምርጫ ኃላፊ ቢያመለክቱም፣ የምርጫ ኃላፊው ‹‹ይህንማ ሊያደርጉ አይችሉም፡፡ ከዞኑ የኢህአዴግ የድርጅት ጉዳይ ጋር እንነጋገርበታለን›› እንዳሉ ገልጸው ምርጫ ቦርድም ከኢህአዴግ የድርጅት ጉዳይ ጋር ተነጋግሮ ነው ውሳኔ የሚሰጠው ብለዋል፡፡ ለሚፈፀምባቸው በደል መፍትሄ የሚሰጥ አካል እንደሌለ የገለጹት አቶ ስለሽ ‹‹ወላይታ ውስጥ መንግስት የለም›› ሲሉም በፓርቲው ላይ ስለሚደርሰው በደል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ቁጣ – VOA

የትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ቁጣ – VOA




  • 87
     
    Share

60167F0B-2C9A-46FD-A63D-B03C1534AF37_w640_r1_sትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ይደርስብናል የሚሉትን የዘረኝነት መድልዎህ የፖሊስ ጭካኔ የሚያጣራ የመንግሥት ኮሚቴ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ተቋቁሟል፡፡
ትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ይደርስብናል የሚሉትን የዘረኝነት መድልዎህ የፖሊስ ጭካኔ የሚያጣራ የመንግሥት ኮሚቴ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ተቋቁሟል፡፡
የቤተ-እሥራኤላዊያኑ ችግር መድኃኒት ሊፈለግለት የሚገባ “ክፍት ቁስል” ነው ሲሉ የእሥራኤል ፕሬዚዳንት ሩቨን ሪቭሊን ዛሬ አስታውቀዋል፡፡
ትናንት በሺሆች የሚቆጠሩ እሥራኤላዊያኑ የኢትዮጵያ አይሁድ በማዕከላዊ ቴል አቪብ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተው ዋናውን አውራ ጎዳና ለረዥም ሰዓት ዘግተዋል፡፡
የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ማኅበረሰብ አባላት ጋር ዛሬ ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡
እሥራኤላዊያኑ የኢትዮጵያ አይሁድ በማዕከላዊ ቴል አቪብ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተው ዋናውን አውራ ጎዳና ለረዥም ሰዓት ዘግተዋልእሥራኤላዊያኑ የኢትዮጵያ አይሁድ በማዕከላዊ ቴል አቪብ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተው ዋናውን አውራ ጎዳና ለረዥም ሰዓት ዘግተዋል
ፕሬዚዳንት ሪቭሊን በዛሬው መግለጫቸው “አላስተዋልንም፤ በቅጡ አላዳመጥንም፡፡ እኛ’ኮ እርስ በራሣችን ባይተዋር አይደለንም፤ ወንድማማች ነን፡፡ በኋላ ሁላችንም ወደሚያሳዝነን ወይም ሊቆጨን ወደሚችል ደረጃ ልንዘቅጥ አይገባንም” ብለዋል፡፡
ችግሮቹና በደሎቹ እንዳይደገሙ ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎችም ዛሬ የተቋቋመው ኮሚቴ ይተልማል ተብሏል፡፡
የተቃውሞ ሰልፎቹ የተጀመሩት ባለፈው ሣምንት የእሥራኤል ፖሊሶች አንድ የደንብ ልብስ የለበሰ የኢትዮጵያ ዝርያ ያለውን የራሣቸውን ወታደር ክፉኛ ሲደበድቡ የሚያሣይ ቪዲዮ ከወጣና ከተሠራጨ በኋላ ነው፡፡
እሥራኤል ውስጥ ከ135 ሺህ በላይ ትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ይኖራሉ፡፡

ጠ/ሚኒስትር ናታኒያሁ የተቃውሞው መነሻ የሆነውን ወታደር ደማስ ፈቃደማስ ፈቃደን አነጋገሩ





  • 692
     
    Share

natanyahu 2
netanyahu
ኢሳት ዜና :-በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተእስራኤላውያን ዘረኝነትን በመቃወም ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፍ እሁድ ተጠናክሮ ከቀጠለ በሁዋላ፣ የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ቤንጃሚን ናታኒያሁ ፣ የተቃውሞው መነሻ የሆነውን ወታደር ደማስ ፈቃደን አነጋግረውታል።
ወታደር ደማስ በእስራኤል ፖሊሶች መደብደቡ በአገሪቱ የሚኖሩትን በተእስረኤላውያንን በእጅጉ አበሳጭቶ ለተቃውሞ አደባባይ አስወጥቶአቸዋል። ቤተእስረኤላውያኑ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ዘረኝነት እጥብቀው የተቃወሙ ሲሆን፣ ቁጣቸውንም የተለያዩ ጠርሙሶችና ፕላስቲኮችን በፖሊሶች ላይ በመወርወር ገልጸዋል። በፖሊሶችም በቤተእስረኤላውያን ላይ ጉዳት መደርሱን መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
እሁድ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በቅርብ የእስራኤል ታሪክ ያልታየ ነው ተብሎአል። ተቃውሞውን ተከትሎ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያውያኑ በአግባቡ አለመያዛቸውን፣ ቁጣውም ለአመታት የተጠራቀመ መሆኑን በመግልጽ ይቀርታ ጠይቀዋል።
ጠ/ሚኒስትሩም ችግሩን እንደሚፈቱ ቃል በመግባት ሁኔታውን ለማረጋጋት እየሞከሩ ነው።
ኢሳት ያነጋገራቸው ቤተእስራኤላውያን እንደሚሉት የአሁኑ ተቃውሞ የ30 አመታት የዘር መድሎ የወለደው ነው። ቤተእስረኤላውያኑ ተቃውሟቸውን የሚቀጥሉ ከሆነ፣ ሁኔታው ሊቀየር እንደሚችል ተስፋቸውን እየገለጹ ነው።
የአለም የመገናኛ ብዙሃን ቤተእስረኤላውያኑ ያደረጉትን ተቃውሞ ሰፊ የዜና ሽፋን ሰጥተውታል።

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየታደኑ እየታሰሩ ነው:: ‪

ሰማያዊ ፓርቲ የአፍሪካ ህብረት ምርጫውን እንዳይታዘብ እንደሚፈልግ ገለጸ
•የህብረቱ ታዛቢ ቡድን ፓርቲዎችን አነጋግሯል
• በየ ክፍለ ሀገሩ የሚገኙ አባላት ላይ የሚፈፀመው ድብደባ ቀጥሏል
• ‹‹የተጀመረውን የሀሰት ክስ እውነት ለማስመሰል የታቀደ ነው››

ethiopia-blue-party-300x164የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ሰበብ እየታደኑ እየታሰሩ መሆኑን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ሀሙስ ሚያዝያ 22/2007 ዓ.ም ብሌን መስፍንና ተዋቸው ዳምጤ ከመስሪያ ቤት ተይዘው የታሰሩ ሲሆን ሚያዝያ 24/2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ‹‹ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተደረገውን አመጽ መርታችኋል፡፡›› በሚል ፖሊስ ክስ እንዳቀረበባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ ዛሬ ሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም ማቲያስ መኩሪያ ቤቱ ውስጥ እያለ በፖሊስ ተይዞ ታስሯል፡፡ ማቲያስ፣ ብሌንና ተዋቸው ወረዳ 10 (ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ) ታስረው ይገኛሉ፡፡ ይህንን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የሚደረገው እስርም ‹‹መንግስት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ የጀመረውን የሀሰት ክስ እውነት ለማስመሰል የታቀደ ነው፡፡ ፖሊስ ምርመራ ሳይጨርስ በሀሰት 20 አባላትንና 6 አመራሮችን አስረናል ብለው ነበር፡፡ እነሱ የፈለጉት ይህን ሚዲያ ላይ ወጥተው በሀሰት የፈፀሙትን ውንጀላ ማሰመሰል ነው፡፡›› ሲል አቶ ዮናታን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
በሌላ ዜና በየ ክፍለ ሀገሩ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ደህንነትና ፖሊስ የሚፈፅመው ድብደባ አሁንም መቀጠሉ ተገልጾአል፡፡ በዛሬው ቀን የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪና የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችው የሀሳብ ጌታቸው ‹‹ለሰማያዊ ፓርቲ ወረቀት በትነሻል›› በሚል ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀሙባት ተገልጾአል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ የአፍሪካ ህብረት 5ኛውን ሀገራዊ ምርጫ እንዳይታዘብ እንደሚፈልግ ለህብረቱ ታዛቢ ቡድን ገለጸ፡፡ የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ዛሬ ሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም በምርጫ የሚወዳደሩ ፓርቲዎችን በተናጠል በምርጫው ዙሪያ ያነጋገረ ሲሆን፣ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ቡድኑን ያነጋገሩት አቶ ወረታው ዋሴ እና አቶ እምዕላሉ ፍስሃ ህብረቱ ምርጫውን እንዳይታዘብ እንደሚፈልጉ አስረድተዋል፡፡
የህብረቱ ታዛቢ ቡድን ከአሁን ቀደም በተካሄዱት ሀገራዊ ምርጫዎች መታዘቡን ያወሱት የሰማያዊ ተወካዮች፣ ህብረቱ በሪፖርቱ ለአምባገነኖች እውቅና ከመስጠት ያለፈ አንዳች እውነታውን የሚያሳይ ትዝብቱን አላስቀመጠም ሲሉ ለታዛቢ ቡድኑ መግለጻቸውን ተናግረዋል፡፡
‹‹ህብረቱ የአምባገነኖች ስብስብ ነው›› ያሉት የፓርቲው ተወካዮች፣ የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ በኢትዮጵያ ምርጫ ላይ ተስፋ በማጣት በታዛቢነት እንደማይሳተፉ ማሳወቃቸውን በመግለጽ፣ የአፍሪካ ህብረት ግን ለአምባገነኖች እውቅና ለመስጠት መምጣቱ በሰማያዊ ፓርቲ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል፡፡
‹‹ቀደምት ፓን አፍሪካኒስቶች አፍሪካን ከቅኝ ግዛት ነጻ ለማውጣት ታግለዋል፤ የአሁኖቹ እውነተኛ ፓን አፍሪካኒስቶች ደግሞ አፍሪካን ከአምባገነኖች ነጻ በማውጣት ወደ ዴሞክራሲ ማሸጋገር ይጠበቅባቸዋል›› በማለት ለህብረቱ ታዛቢዎች የገለጹት የፓርቲው ተወካዮች፣ በዚህ ረገድ ህብረቱ ተገቢውን ስራ እያከናወነ ነው ለማለት እንደማይቻል አስረድተዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ መንግስት ጋባዥነት 5ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለመታዘብ በቅርቡ አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል፡፡ ህብረቱ በዛሬው ዕለት ያነጋገራቸው ፓርቲዎች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ በውል አልታወቀም፡፡

የተቀዳደደዉ የዜጐች ነጻነት በኢትዮዽያ (በመሃመድ አሊ)

May 5, 2015
በመሃመድ አሊ
በግንቦት 1983 በኢትዮዽያ አቆአጣጠር ሕ.ወ.ሀ.ት መራሹ ጦር የመንግስት ወንበር ከተቆጣጠረ በኋላ ግዜዉ የሚያሥገድደዉንና በምዕራባያዉያንም ተፅእኖ ጭምር አዲሥ ሊባል የሚችል ሕገመንግስት ማርቀቁ ይታወሳል፡፡
በ1985 የፀደቀዉ የኢትዮዽያ ሕገመንግስት ቀድሞ ከነበሩት የደርግና የዘዉዳዊ መንግስት በብዙ መልኩ እንደሚሻል በሃገር ዉስጥም በዉጭ መንግስትም ችሮታ ተለግሶት ነበር፡፡ ሆኖም የበግ ለምድ የለበሰዉ ተኩላ ባሕሪዉ የመንግስት ስልጣንን ላለመልቀቅ ራሱ ያፀደቀዉን ሕገመንግስት በየግዜው እየሸረሸለዉ ይገናል፡፡ ከቶም እየናደዉ ካሉት ሕጎች መካከል የዜጐች የመናገር፣ የመፃፍና የመደራጀት መብት ዛሬ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ተሸርሽፘል፡፡
በ1997 በዜጎች የመደራጅት መብት ተጠቅመዉ ሕብረብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ መብትን በተግባር ለማዋል ተቀናጀተዉ የነበሩ ፓርቲዎች በሐገሪቱ ሕዝብ ንቃተ ሕሊና ማዳበራቸዉ ስልጣን ላይ የተቀመጠዉን የወያኔ መንግስት አስደምብሮት አዉሬያዊ ባሐሪዉ እንዲገነፍል አድርጐታል፡፡በወቅቱ ተከስቶ የነበረዉ አዲስ የዴሞከራሲ ጅምር ሕብረተሰቡ መቅመሱ በሰዉ ልጅ ላይ ድርድር አለመኖሩን አሳይቶ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ነገሮች ሁሉ መገልበጣቸዉ በይፋ መታየት ጀመፘል፡፡
ዛሬ ኢትዮዽያዊ በሐገሩ የዜግነት መብት በነፃነት የመናገር ፣የመፃፍም ሆነ መደራጀቱ በጥርጣሬ እንዲታይና ወህኒ ማደርያዉ እንዲሆን እያስደረገዉ ይገኛል፡፡ ሐገራችን የዜጐች መብት የተጨፈለቀበት በመሆኑ ሰዉ እርስ በርሱ መተማመን እያቃተዉ በጥርጣሬና በመፈራራት እየኖረ ገዢዉ ፓርቲ አንባገነንነቱን ከመቼዉም ግዜ በላይ በማናር አንዱን ከሌላናዉ ጋር በማጋጨት ዜጐች ተግባብተዉ እንዳይኖሩ እያደረገ ይገኛል፡፡በኢትዮዽያ እስር ቤቶች ከጋዜጣና መፅሔት ስራ ጋር የተገናኙ አዘጋጆች፣ ሪፖርተሮች፣ የጋዜጣና መፅሔት ባለቤቶች ስለ ነፃነት በመፃፋቸዉ ብቻ የመከራ ግፋትን እንዲቀምሱ ተደርጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በ1997 በብዛት ይታዩ የነበሩ ጋዜጣና መፅሔቶች ዛሬ ለዐይን አይታዩም፡፡በከተማዋ በመንግስት የሚደጐሙ ጥቂት የፓርቲ ልሳን የሆኑ ነፃ መሰል ጋዜጦች እንጂ አንድም ነፃ ፕሬስ አይገኝም፡፡ እስከ ቅርብ አመት ስለ ነፃነትና ስለ ዜጐች መብት ሲዘምሩ የነበሩ ጋዜጦች ወይ ከሐገር ተሰደዋል አልያም እጅና እገሮቻቸዉ ተጠፍሮ ወህኒ ገብተዋል፡፡እስር ላይ ከሚገኙ ዜጎች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት የዜጐች መብት ላይ ጥያቄ የሚያቀርቡ የነቁና የተማሩ ኢትዮዽያዊያን ናቸዉ፡፡ በመንግሰት ወንበር ላይ ከተቀመጡት ባለሥልጣናት በላይ በኢትዮዽያ እስር ቤቶች ሐገሪታን መምራት የሚችሉ የነቁ ሙሑራን ወህኒ ታጉረዋል፡፡
በኢትዮዽያ በአሁኑ ግዜ በየትኛዉም የዜጎች መብት ላይ በነፃነት ሚናገሩ ዜጎችን ማግኘት አይቻልም፡፡ ከአምስት በላይ ሰዎች አንድ ቦታ ላይ ተሰብስበዉ መነጋገር ካለባቸዉ ለመንግስት ማሳወቅ እንዳለባቸዉ ይፋ ባልሆነ መንገድ እየተገለፀ ይገኛል፡፡ በቅርቡ አንድ ጋደኛዬ በትምህርት ጉዳዮች ላይ ባዘጋጅዉ አጫጭር ዉይይቶች በተደጋጋሚ ከደህንነቶች ማስፍራሪያና ዛቻ ገጥመዉታል፡፡በሐገራችን ዉስጥ መብት ላይ የሚፅፉ ሰዎች ስልካቸዉ ሊጠለፍ፣የግል ምስጢር ሳጥኖቻቸዉ ሊሰበሩ፣ የፌስቡክና የዌብ ሳይት አድራሻቸዉ መንግስት ባቃቃመዉ INSA በተባለ ድርጅት ሊሰበር ይችላል፡፡ በ24 አመታት የአገዛዝ ዘመን ወያኔ የባለስልጣናትን ኪስ ከማደለብና ንቅዘትን በሰፊዉ ከመዘርጋት ውጭ የሚታዩ ተጨባጭ ለዉጥ ሰዎች ላይ አይታይም፡፡ ሐገሪቱ እያስመዘገበች ነዉ ሚባለዉ እድገት በዜጎች ሕይወት ላይ ለዉጥ አላመጣም፡፡ መብትን የጣሰ እድገት ከቶም ሊኖር አይችልም፡፡
በአጭሩ ኢትዮዽያ ዉስጥ የዜጎች መብት ከላይ የተጠቀሰዉን ይመስላል ፡፡ለአብነት ያክል የታዩትን ነገሮችን ማስተዋል ለቻለ ሰዉ ዜጎች እንዴት ያለ በግፍ ስርዐት ዉስጥ ህይወታቸዉን እየገፉ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህንን ለዉጥ ለማምጣት ሁሉም ሊረባረብና አለምአቀፍ ጫና እንዲኖር ሀያላን መንግስቶች፣ ለዜጎች መብት ዴሞክራሲ መከበር የሚጮሁ ሁላን ኢትዮዽያ ዉስጥ የዜጎችን መብት ለሚደፈጥጥዉ የወያኔ አፋኝ ሥርዐት የብድርና የመሳሰሉትን ድጋፍ እንዲያቆሙና ሥርዐቱ እንዲወገድ ሁላችንም ልንረባረብ ይግባል እያልኩ ፅሁፌን በዚሁ አበቃለዉ፡፡