Thursday 4 February 2016

የወልቃይት ባህልና ማንነት — መልስ ለአቶ ሃይሉ የሺወንድም (ከጎሹ ገብሩ)

ከጎሹ ገብሩ  
የወልቃይት ባህልና የማንነት ጥያቄ በሚል ባለ ስምንት ገፅ መጣጥፍ ጥር 6 2016 በኢትዮሚድያ ድህረ ገጽ የወጣው ጽህፍ ደግሜ ደጋግሜ አንብቤዋለሁ። ወንድሜ ኃይሉና እኔ ተወልደን ያደግነው ... በምትባል ከትግራይ አብራክ የተፈጠረች አረመኔ የፋሽሽቶች ጥርቅም ከአያት ቅድመ አያቶቻችን ይዘነው የኖርነውን ባድማችን ቀምታ ወገኖቻችን በመግደልና በማባረር ዘር አልባ ባስቀረችዉ በወልቃይት ጠገዴ አካባቢ ስንሆን ሁለታችንም የሚያስተሳስረን የዝምድና ሰንሰልት አለን ። ለተወሰነ አመትም በቅርበት አብረን በጎንደር ከተማ ስንኖር በመከባበርና በመደጋገፍ ጥሩ ጊዜ አሳልፈናል አቶ ኃይሉ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ተሞክሮን ለማዳበር (ሰርቪስ ትሬኒንግ) በአስተማሪነት ተመድበው እኔም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኜ ነው። በዛን ወቅት ወንድም ኃይሉ በእዉቀት የበሰሉና በተማሪዎች ንቅናቄም ዋና ተዋናኝ እንደነበሩ ብዙ ምልክቶች አይ ነበር። እኔም በወቅቱ ፖለቲካዊ አስተሳሰቤ ብስለት ያልነበረው፤በአገር ወዳድነትና በስሜት የምጋልብ ነበርኩ። አኔና አቶ ኃይሉ የሺወንድም ከ 1969 ዓ.ም ጀምሮ ለብዙ ዓመታት ተለያይትን ከቆየን በኋላ በ2006 ዓ.ም  ኖርወይ እያሉ በተሌፎን ኮንፈረንስ ተገናኝተን በወቅታዊው የአካባቢያችን ችግር ለተወሰን ግዜ ጠለቅ ያለ ዉይይት ስናደርግ ወልቃይትን አስመልክቶ የነበራቸው አመለካከት ተሐህት ቦታችን ለቃ መውጣት አለበት ደንበራችን ተከዜ ነው የሚል አቋም ነበር ሲያስተጋቡት የነበረው። አሁን ያጋጠማቸው እንቅፋት ትክክለኛ መንስኤው ባላውቅም ምክንያት ይሆናል ብዬ የገመትኩት በስልጣን እየባለጉ ባሉት ስጋ ዘመዶቻቸው ተፅእኖ ብየ እንዳልል ወንድም ኃይሉ በትምህርት የበሰሉት በወያኔ ከበሮ ተታለው የትውልድ ሃረጋቸው፤ ባድማቸውና ወገኖቻቸውን ያስጨፈጨፉ ከሃዲዎች ሲሉ የሚወዱት ሞላውን የወልቃይት ሕዝብ ለታሪክ ጠባሳነት አሳልፈው ይሰጣሉ ብዬ አልገምትም ሌላ የተደበቀ አጀንዳ ካልነበራቸው በቀር።
ወደ ተነሳሁበት አርዕስት ወደ አቶ ኃይሉ መጣጥፍ ልመለስና በፅሁፉቸው ላይ ያስነበቡን አሉታዊ አባባሎች ሃቁን በማያንፀባርቁ ክሶች ላይ አስተያየቴን ስሰነዝር በፅኃፊው ግለሰብ ላይ ምንም ዓይነት የጥላቻ ቁርሾ እንደለለኝ ቅድምያ ግልፅ ማድረግ እሻለሁ። በ.ተ.ሐ.ህ.ት አረር ጥይት የተቆላው የወልቃይት ህዝብ ለሁለታችንም እኩል የሚደርሰን ቢሆንም በሁለታችን መካከል የሃሳብ አለመግባባት ልዩነት ሊኖሩን ይችላል። አቶ ሐይሉ የመሰላቸው መጻፍ መብታቸው ሲሆን እኔም በፅሁፉ የተሰማኝን መተቸት መብቴ ነዉ። ወንድም ሐይሉም ተተቸሁ ብለው ከንፈርዎ እንደማይነክሱ እርግጠኛ ነኝ።
1ኛ/ በወልቃይት ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል በሚሉ አካላት የወልቃይትን ባህል ለማጥፋት በትግራይ ነፃ አውጭ የተቀናጀና የተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ደርሶብናል ከትግራይ ጋር በባህል፤በስነልቦናና በመሳሰሉት መስፈርቶች አንገናኝም በማለት የወልቃይት አማራ ማንነትን አንግበው የተነሱ ይሉናል።
በመሠረቱ ይህን ጥያቄ ከሚያነሱት መካከል አንዱ እኔ ነኝ ነገር ግን የእርስዎ አቋም ግልጽ ያልሆነልኝ ነገር ቢኖር ወገነዎ በሆነው በወልቃይት ህዝብ ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያና ጭፍጨፋ እንደሚጋሩ ለስለስ ባለ አረፍተነገር ጠቁመዋል። ተ.ሐ.ህ.ትን ግን በዘር ማጥፋት ወንጀል አልከሰሷትም እንዲያውም ተ.ሐ.ህ.ት ምክንያት ይሆነኛል ብላ ለምታቀርበው የማካለል ቆርጠህ ቀጥል ምክንያቶች ድጋፍ በመስጠት ከበሮዋ እስኪቀደድ ድረስ እንድትደልቅ አድርገዋታል። የወልቃይት ህዝብ ትግርኛ በመናገሩ የተነሳ ነው የተካለለው የሚል ቃል እርስዎን በመሰለ የታሪክ ምሁር አንደበት መነገሩ በጣም የሚያሸማቅቅ፤ ተስፋ የሚያስቆርጥና የሚያሳዝንም ነው። የትውልድ ቦታዎን የመዘበረችና የወገኖችዎ ደም ላፈሰሰች ጠላት ደርጅት አጋር መስለው ለመታየት የመረጡበት ምክንያት ይሆናል ብየ የገመትኩት የነብሰ ገዳይዋ ድርጅት ጡት እያላመጡ ያደጉትን ከሁለት ሦስት ለማይበልጡት ዘመዶችዎ ብለው ከሆነ ከእርስዎ የማይጠበቅ ድርጊት ነው። አቶ ኃይሉ ትላንት አንግበው የተነሱለት ብሩህ አላማ መስመሩ ስቶ ብር ማለቱ ‘ፈጭቸ ፈጭቸ ቋቱን ብዳስሰው እልም ብሎ ቀረ እንደ ዘመኑ ሰው’ እንዳሉት አበው ሆነና እንደ ግመል—ወደ ኋልዮሽ መጓዝዎ በጣም ያሳዝናል። ወንድሜ ሆይ ተ.ሐ.ህ.ት ወደ ወልቃይት ተንደፍድፋ የመጣችበትን ጉዳይ ስር መሰረቱ እያወቁ በሸፍንፍን ለማለፍ መሞከርዎ ወልቃይት የጎረፈው የንፁሃን ደም መች የአውሬዎች ሆነና የኔም የርስዎም ወገኖች ደም እኮ ነው ያለ ምንም ምክንያት እንደ እንሰሳ ባልሰላ ቢላዋ በ.ተ.ሐ.ህ.ት ቅጥረኛ ምልሻዎች ተቆራርጠው ለዘልዓለም ያሸለቡት ምናልባት የእርስዎ ቅርብ ዘመዶች ሌላው ወልቃይቴ የደረሰበት የሞት ፅዋ አልደረሰም ይሆናል በወንድምዎ እና በአክስትዎ ልጅ ተከላካይነት። በአካባቢው ተወልደን ያደግን በተለያዩ የዓለም ዙርያ የምንኖረው ላንቃችን እስኪዘጋ ድረስ የምንጮኸው ለግል ጥቅማችን ብለን ሳይሆን ድምፃቸው ለታፈኑት ወገኖቻችን ድምፅ ለመሆን ነው እንጅ መች እንደ የቀበሮዋ ታሪክ የበሬ—ይወድቅልኝ ይሆናል ብላ ስትከተል እንደ ዋለችው እኛም ለሆዳችን ስንል በወገኖቻችን ደም ለታጠቡት ወያኔዎች ተንበረከክን። ይህን በማድረጋችን ታፍኖ የቆየው የወልቃይቴዎች ግፍና በደል ሁሉም እንዲያውቀው በማድረጋችን በርቱ እንደማለት ፈንታ በጥላቻ የታወሩ የሚል ስያሜ በእርስዎ ቃል ተሰንዝሯል ቢሆንም በጣም ኩራት ይሰማናል የደደቢት ሽፍታ ያልተጠላ ማን ይጠላ ብለው ነው። እንደነ አቶ ገብረመድህን አርአያ የመሳሰሉ አገር ወዳድ የትግራይ ተወላጆች የዘር ሃረግ ሳይገድባቸው ተ.ሐ.ህ.ት በወልቃይት ሕዝብ ላይ የፈፀመችው የዘር ማጥፋትን ድርጊት ለመላው ኢትዮጵያዊና ለዓለም ሕብረተሰብ ሲያጋልጡ እርስዎ ግን የወገንዎን ማንነት ለችርቻሮ ገበያ በማቅረብ ስራ መጠመድዎ በጣም አሳፋሪና የሚያሸማቅቅ ነው። ወንድሜ ሆይ ትግርኛ በመናገራችን ብቻ አይደለም ይህን ሁሉ በደል የፈፀመችብን ከአያት ቅድመ አያት ይዘነው  የቆየነውን ለም መሬት ዘርፋ ወርቃማው ወገኔ እያለች በባዶ ሜዳ ላይ ለምትደልለው የትግራይ ህዝብ ለመጥቀም ብላ ሳይሆን ኢትዮጵያን ለማጥፋት ስትል እቅድ አውጥታ ለተነሳችበት ዕኩይ ተግባሯ ለማሳካት ስትል እንጅ የወልቃይት ህዝብን በወገንነት ዛሬም ሆነ ትላንትና ፈርጃው አታውቅም። ወገኔ ነው ብላ የምታምን ቢሆን ኑሮ በጥይት ባሩድ በነበልባል እሳት እያቃጠለችና እየጨፈጨፈች ከቀየው ባላባረረችው ነበር። ትግርኛ በመናገሩ ከለልኩት ያለችው ሕብረተሰብ እኮ አጥፍተዋለች መሬቱ ብቻ ነው ትግርኛ ተናጋሪ ሁኖ የቀረው። “ጌታውን ፈርቶ አሽከሩን” እንዲሉ ሆነ እንጅ ተጋድሎ ሐርነት ትግራይ በቋንቋ ማካለል ከፈለገች  ከኤርትራ የበለጠ የሚቀርባት ወገን ያለ አይመስለኝም።
2ኛ/ ለምሳሌ ያህል ይሉና አሜሪካውያን እና እንግሊዛውያን የአንድ ቋንቋ ማለትም የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ናቸው ነገር ግን አንድ ብሔር አይደሉም ስለዚህ የተለያዩ ብሔረሰቦች የተለያዩ ቋንቋ መናገር ይኖርባቸዋል ማለት አይደለም ይሉና…..
ተ.ሐ.ህ.ት የወልቃይትን  ሕዝብ ትግርኛ በመናገሩ በገመድ ጎትታ ተከዜን አሻግራ ትግሬ መሆን አለብህ እንዳለችው  እንግሊዝም አሜሪካዉያንን  ቋንቋየን ሰለምትናገሩ የያዛችሁት መሬት በቁጥጥሬ ሥር አዉዬ የፈለኩትን አደርጋለሁ ማለት ትችላለች እንደማለት ነው። የወልቃይት ሕዝብ ከአማራው ወገኑ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ በመከባበር ለዘመናት ያዳበረውን የትዉልድ ዝርያ በማንም ጠመንጃ ነካሽ ሽፍታ ሊቀለበስ እንደማይችል በልበ ሙሉነት ላረጋግጥልዎ እወዳለሁ። የወልቃይትና የትግራይ ሕዝብ ክልል ሳያግደው በጉርብትና አና በኢትዮጵያዊነት ተከባብሮና ተደጋግፎ እንደቆየው አሁንም አብሮ ይኖራል ። ከኢትዮጲስ የግዛት ዘመን ጀምሮ መጠርያው የሆነውን ብሔረሰብ በሃይል ተቀምቶ የደደቢቶች አዲሱን የመሳፍንታዊ ትውልድ አቤት ወዴት እሺ ጌቶች ብለህ ተቀበል ብሎ ወደ ጠፋው የባርነት ሥርዓት ለመመለስ ሽርጉድ ማለቱ ለሁላችንም የሚበጅ አይሆንም አሁኑን መቆም ይኖርበታል። ሸዉራራ ታሪክ ትቶ ማለፍ ለዘልዓለም ያስወቅሳል። ፋሽሽት ኢጣልያ ሃገራችን በወረረችበት ወቅት እንደ አሁኖቹ ባንዳወች በጥቅም ተደልለው ከጠላት ጋር ያበሩት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ በባንዳነት ሲወቀሱ ይኖራሉ። ዛሬ ቢመሽ ነገ ይነጋልና አርቆ ማሰቡ አማራጭ የማይገኝለት ዘዴ ነው። ስለዚህ ግዜው ሳይመሽ ለእውነት እንጂ ለጥቅም መሯሯጥ ዉርደትን ያስከትላል።
3ኛ/ የወልቃይት ህዝብ ከትግራይ ብሔረሰብ ጋር የሚመሳሰለው በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ ነው።
ይህ አባባል አስደንጋጭም አሳዛኝም አሳፋሪም ነው። ጎበዝ አባት እንደለለን ሜዳ ላይ እንደዋለልን መቅረታችን ነው? እንደ ወንድም ኃይሉ አገላለፅ በተዘዋዋሪ የሚል ህብረተስብ ሰምቼ አላውቅም የተዘዋዋሪ ጦርነት(ፕሯክሲ ዋር) አሜሪካ ለቅጥረኛውና ተላላኪው መለሰ ዜናዊ ገንዘብ እየሰጠች በአልሸባብ ላይ እየተደረገ እንደ ቆየውና አሁንም እንድቀጠለው ጦርነት ወልቃይቴን አመሳስሎ በምሳሌ ማቅረብ የተሳሳተ አገላላፅ ነው። ተ.ሐ.ህ.ትም በወልቃይቴወች ተቀባይነት እንደለላት ተረድታ የከበሳ ትግረኛ ስለምትናገሩ ወደኛ አካለልናችሁ ለማለት እንዲያመቻት ይሆን አዲሱ ማንነት የተሽለምነው? ለተወደዳችሁ አገር ወዳድ ወልቃይቴዎች በ አቶ ኃይሉ የሽወንድም የተሰጠን አዲሱ ማንነት እንደ አለፈው የባርያው ስራዓት ለአሁኖቹ የደደቢት ሽፍቶች ወፍጮ ፈጭዎችና አረም አራሚዎች ሆነን ከምንቀር ሁላችን በጋራ በመነሳት ወላጆቻችን ያጎናጸፉን ጀግንነት በማደስ የተጀመረውን ትግል አፋፍመን ከደደቢት ሽፍቶች መንጋጋ ነፃ መዉጣት አለብን። አቶ ኃይሉ በግል በቤተሰቦቻቸው ውስጥ የኤርትራም የትግራይም ዝምድናና ትስስር ሊኖራቸው ይችላል ነገር ግን ወልቃይቴ የሆነው ሁሉ ግን በልበ ሙሉነት የፈለቀበትን ታሪክ የሚያውቅ በማንነቱ ሊሸጥ ሊለወጥ የማይችል ኩሩ ሕዝብ እንጅ ዘሩን ክዶ ለጥቅም የሚንበረከክ አይደለም።
4ኛ/ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ ወልቃይቴወች አማራም ትግሬም እንዳልሆኑ ይናገራሉ ስለዚህ የወልቃይት ጥያቄ ዘላቂ መፍትሄ ከነዚህ ሶስት መስመሮች በአንዱ ላይ የሚመረኮዝ ይሆናል(በትግሬ፤በአማራ ወይም ራስ ገዝ)
ለወልቃይት ህዝብ ፍፁም ዲሞክራሲ  ሰፍኖ ምርጫህ ምንድን ነው ቢሉት መልሱ አንድና አንድ ብቻ ነው። ይሄውም ተንደላቅቄና ተከብሬ የኖርኩበት የአማራነት ዘር ግንድ ቅንጣት ያህል በደል ያልበደለኝ፤ በሃብቴና በርስቴ እንደፈለኩ አዝዤ፤ጠረፌን ራሴ በነደፍኩት ወታደራዊ ስልትና በንብረቴ የገዛሁትን መከላከያ በመጠቀም ደንብሬና ጠረፌን ሳላስደፍር ጠብቄ እንድኖር መብቴንና ማንነቴ አስከብሮ ከተወለድኩበትና ካደኩበት አካባቢ በሰላም እንድኖር መብት ለሰጠኝ ብሔረ አማራነትን ብሎ 99% ድምፅ በመስጠት ማንነቱን ያለ ማወላወል ይፋ እንደሚያደርግ በእርግጠኛነት መናገር እችላለሁ። ቀሪው 1% የቤተሰብ ስብስብ ደግሞ የወይዘሮ አዜብ ስርወ መንግስት አሟሟቂዎችና የተ.ሐ.ህ.ት ጉርሻ ጠባቂዎች ድምፅ ሆኖ የወልቃይት ህዝብ በአቸናፊነት እንደሚወጣ መተንበይ ሳይሆን ሀቀኝነት ያለው አባባል ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያ ሃገራችን በደደቢት ሽፍታዎች እጅ ሥር በወደቀችበት ዘመን 100% አሸነፍን ባሉበት ወቅት ምርጫ የሚባል ማደናገሪያ የሚታሰብ አይሆንም። የወልቃይት ጥያቄ እኮ የመገንጠል ጥያቄ አይደለም የማንነት፤ የግለሰብ መብት፤ የህልውናና የእኩልነት እንጅ የግለሰብ ፈላጭ ቆራጭ ገዥነት ጥም ለማርካት አይደለም። ይህ ኩሩ ህዝብ የሚያምነው ማንኛውም ኢትዮጵዊ ክልልና ዘር ሳያግደው በሙያውና በእውቀቱ ብቁ የሆነ ድርጅት  ወይም ግለሰብ ይምራኝ ነው እያለው ያለው። ይህች ራስ ገዝ የሚሏት ፅንሰ ሃሳብ እንደ አሁን ይፋ አልሆነችም  እንጂ ከ10 ዓመት በፊት በውጭ ያለነውን የወልቃይት ተወላጆች ለማታለል የ.ተ.ሐ.ህ.ት ታማኝ ካድሪዎች የሆኑ ሁለት ትውልደ ወልቃይቴዎች 1ኛ አቶ ፈረደ የሽወንድም( የአቶ ሃይሉ የሽወንድም ታናሽ ወንድም ) 2ኛ አቶ ፀጋይ አስማማው በተ.ሐ.ህ.ት ሳንባ የሚተነፍስና በሃሰት የሚፈርድ በጌቶቻቸው ተልከው እንደመጡ ሕዝቡን በእጅ አዙር ሰብስበው የነሱ ደጋፊ የሆነ አንድ ግለሰብ ስብስባው ከመጀምሩ በፊት እንዲህ ብለህ ጠይቅ ተብሎ መመርያ ተሰጥቶት ባህር አቋርጠው የመጡበትን አጀንዳ በጥያቄ አቅርቦታል። የወልቃይት ህዝብ የራስ ገዝነት መብት አለው ወይ ብሎ መጠየቁ በስብሰባው ላይ የነበሩ አገር ወዳድ የወልቃይት ተወላጆች “እኛም አውቀናል ጉድጓድ ጭረናል”ብለው አፊዘውባቸዋል። ያን ግዜ የተወጠነው ደባ ነው አሁን በተግባር ላይ ለማዋል ያልነበረ ታሪክና ያልተፈጸም በደል በአማራዎች ተፈፅመ እየተባለ ያለው። በአሁኑ ጊዜ የወልቃይት ህዝብ ለ40 ዓመት እንዳልናገር አፌን ሸብባችሁ በፍርሃት ቆፈንና በድህነት አሮንቃ የኖርኩት ይበቃኛል ብሎ በጥቁር መጋረጃ የተሸፈኑትን አይኖቹንና እንደ በሬ የተሸበበው አፉን ለማውለቅ በሚፈረጋገጥበት ወቅት የአዜብ መስፍን ስርወ መንግስት የፋሽሽቱን ባለቤቷ መፈክር በማደስ በደማችን የወረርናት ወልቃይት አማራ መልሶ አይቆጣጠራትም ከፈለጋችሁ በ.ተ.ሐ.ህ.ት መጉዚትነት ራስ ገዝ መጠየቅ ትችላላችሁ በማለት የወልቃይት ህዝብ እንደተቀበረ እንዲኖር ይህ ዓይነት ማነቆ ያዘጋጁለት። “ደሮንሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ ለዚህ አርዕስት የሚስማማ ነው።
5ኛ/ በአማረኛ ተናጋሪዎቹ ገዥዎችና በትግርኛ ተናጋርዎቹ ወልቃይቴዎች መካከል በዙ የቋንቋና የባህል ልዩነቶች ስለነበሩ የባህሎች መደባለቅና አንዱን ሌላውን የመተካት እድል የተመቻቼ አልነበረም።
እኔ በ60ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ያለሁ ነኝ ከህፃንነቴ ጀምሬ የሰማሁትና ያየሁት ወልቃይት ጠገዴ ሲያስተዳድሩ የነበሩት ወልቃይት ተወልደው ያደጉ በተፈጥሮ እዉቀት የበሰሉና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላቸው ገለሰቦች እንጂ ከሌላ አካባቢ የቋንቋና የባህል ልዩነት የነበራቸው አይደሉም የመተካካት ችግርም አልነበረም።ሥለዚህ አቶ ኃይሉ እርስዎም የሚዘነጉት አይመስለኝም ገዥው ወልቃይቴና ተገዥው ወልቃይቴ አማርኛ የሚናገሩና የአማራ ባህል ይዘው ለብዙ ዘመናት የኖሩ ስለሆነ ትግርኛ ተናጋሪዎቹ ወልቃይቴ የሚል ቃል ሕዝቡን ለመከፋፈል ረቂቅ የሆነ የተ.ሐ.ህ.ት ዘዴ ነው፡፡ ለምሳሌ፦ ጀግናውና አርበኛው ቢትወደድ አዳነ መኮነን፤ ደጃዝማች ደስታ ማሩ፤ቀኛ/ ገብሩ ገብረመስቀል፤ ቀኛ/ትርፌ ጣሰው ደጃዝማች መኮነን፤ደጃዝማች በዛብሕ አደመ፤ ግራዝማች ተገኘ ቢተው፤ፊታውራሪ አዲሱ መኮነን፤ ፊታውራሪ የሺወንድም ናደው(የእርስዎ ወላጅ አባት)፤ቀኛ/ ይርጋ ነጋሽ፤ፊታዉራሪ መለሰ ኃይሉ፤ ቀኛ/ ኃለማርያም ደሴ፤ቀኛ/አባይ ወልደማርያም፤ ፍታውራሪ ነጋ፤ ልጅ ተድላ ወልደማርያም፤ልጅ አስማማው ይርጋ፤ልጅ አቡሃይ አብተው፤ አቶ እንደሻ አያለው፤ አቶ ባየው ቸኮል ወዘት. ነበሩ በተለያየ የስራ ዘርፍ ተመድበው አካባቢውን ሲያስተዳድሩ የነበሩት። እንግዲህ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት አካባቢውን ሲያስተዳድሩ የነበሩ ባህላቸውና ቋንቋቸው እንደማንኛውም ምልአተ ወልቃይቴ አማራዊነት ታሪካቸውን አክብረው ይዘው ቆይተው ለተተኪው ትውልድ አስረክበውን ያለፉት። አንድም የትግራይ ተወላጅ ተከዜን ተሻግሮ ወልቃይትን ያስተዳደረበት ግዜ የለም። ደንበራችን ተከዜ እንጅ ተ.ሐ.ህ.ት ጠፍጥፎ በሰራው ካርታ አንከለልም።
ሌላው አሳፋሪ ነገር ተ.ሐ.ህ.ት የወልቃይትን ወጣትና ሽማግሌ በብዛት ግድያ(ማስ መርደር) እንደተፈፅመበት ሳይጠቅሱ ከአምሳ ሁለት ዓመት በፊት በአቶ መኮነን በርሄ የተፈጸመው ግድያ አግዝፈውና አባዝተው በአማራነት የከሰሷቸው ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮነንን ያለ ምክንያት አይደለም በጠገዴ ሕዝብና በወልቃይት ህዝብ ልዩነት ተፈጥሮ ለመብቱ በአንድነት እንዳይነሳ መሰናክል ለመፍጠር ይመስላል ግን እኮ የእርስዎ መላ ምት አይመስለኝም ምን አልባት ከመጋረጃው በኋላ የተውጠነጠነ ሃሳብ እንዳይሆን እጠረጥራለሁ። የወልቃይትን ንብረት ዘማች በማሰማራት ይዘረፉት ነበር ላሉት ክስም የወልቃይት ሕዝብ ብቻውን በልቶ አያውቅም እንኳንስ ለተከበሩ ቢትወደድ አዳነ መኮነን ወር ለማይሞላ እንግድንት ቀርቶ ለ40 ዓመታት ያህል ንብረቱና ልጆቹን ለበላበት የደደቢት ሽፍቶችም ቆሽቱ እያረረ ከየትም ቦታ ቀምሰውት የማያውቁ ምግብ በመመገብ የጠወለገው ፊታቸው ፈካ አንዲል ያደረገ ለጋስ ህዝብ ነው። ቢትወደድ አዳነ ወደ ቃፍትያ የመጡበት ምክንያት ያካባቢዉን ህዝብ ለማራቆት ብልው ሳይሆን በዝያን ግዜ አካባቢውን ያስተዳድሩ የነበሩት ግለስብና የአቶ መኮነን በርሄ ዘመዶች ጭምር የአካባቢያችንን  ሰላም ያወከ ግለሰብ አለና መጥተው መፍትሄ እንዲሰጡን ብለው በጠየቁት ጥያቄ መስረት ነበር ወደ ቦታው የሄዱት። ከቦታው ተገኝተው ቅድምያ ያደረጉት ነገር ቢኖር አቶ መኮነን በርሄ፤ዘመድ አዝማድና የአካባቢው ህዝብ በተገኘበት ጉባኤ ጠርተው ካነጋገሩ በኋላ በጥፋት የተከሰሱትን ግለሰብ ነገሩ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ዋስ እንዲጠሩ ተጠየቁ ከስብሰባው ውስጥ የነበረው ባዕድም ይሁን የቅርብ ዘመድ ለአቶ መኮነን በርሄ እዋሳለሁ የሚል ሰው ሲታጣ  በል ዋስ እስከሚገኝ ድረስ በማረፍያ ቤት እንዲቆዩ ሲባሉ ከኪሳቸው ሽጉጥ አውጥተው በተኮሱት ጥይት ቢትወደድ አዳነ መኮነን ተመትተው ሲወድቁ ከዘበኞቻቸው አንዱ ተኩሶ አቶ መኮነን በርሄን ገደላቸው ከሁሉ የሚገርመው ለተፈፅመባቸው የግድያ ሙከራ ሳያዝኑ የአቶ መኮነን በርሄ መሞት ሲሰሙ ለምን ገደላችሁት ለክፉ ቀን የሚሆን ጀግና ብለው ከልብ አዘኑ እንጂ ደግ ሰራችሁ አላሉም። አቶ መኮነን በርሄም ወደ ስብሰባው ከመግባታቸው በፊት አብረዋቸው ከነበሩት የተወሰኑትን ከውጭ ሆነው ሁኔታው እንዲጠባበቁና ተኩስ ከተጀመረ ሽፋን እንዲሰጧቸው የተበሉት ግለስቦች ተኩስ እንደሰሙ ፈርጥጠው ነበር የሄዱት እንግዲህ እንዲህ አይነቱ የበሰለ አመራር ከአሁኖቹ ነብሰ በላ ህወሃቶች ጋር ለማመሳሰል መጣሩ ፍርዱ ላንባብያን ልተወው። ሌላው የአቶ ኃይሉ አሳፋሪ ክስ ዘማች ሆነው የሄዱት አስገድደው ሴቶችን ይደፍሩ ነበር ላሉት ከአሁን በፊት ተሰምቶና ተነግሮ የማይታወቅ የወልቃይቴዎችን ጀግንነት የሚያጎድፍ የጠላት ወሬ ነው።
6ኛ/ ወልቃይት በትግራይ ክልል ውስጥ መቀጠሉ የተሻለ አማራጭ መሆኑን የሚያሳምኑ ብዙ የመከራከሪያ ነጥቦች አሉ ይሉናል።
የተ.ሐ.ህ.ት ሥም ማጥፋት ዘመቻ በእርስዎ ቃል መድገሙ ምን ዓይነት ትምህርት ይሰጣል ብለው እንዳሰቡ ግራ የሚያጋባ አባባል ነው። አልያም የእርስዎ ስም ተጠቅሞ የፃፈ ይኖር ይሆን የሚል ጥረጣሬ አድሮብኛል? ‘ትግሬ ነህ ሰው’ የሚለው የማጥላላት ቃል ለ50 ዓመታት ያሰለቸ እውነትነት የለለው ቃል በእርስዎ አፍ መደገሙ ማንን ለማስደሰት ይሆን ከቶ? በስልጣን ያለችው ወንበዴዋ ድርጅት በወልቃይት ህዝብ የተነሳው እረሮ የአጀንዳውን ይዘት ለማስቀየር ሆን ብላ የተጠቀመችበት ግዜ ያልፈበት ዘዴ ነው። ይህ ቃል ተናገርች የሚባለው ሁመራ ውስጥ በሴተኛ አዳሪ ስትኖር የነበረች የትግራይ ተወላጅ በአንድ ቀን ውስጥ የአስራ አንድ ሰዎች ሬሳ በቤቷ ደጃፍ አድርጎ ወደ ማርያም ቤትክርስትያን ሲያልፍ በሀዘን እየተከዘች እያለች 12ኛው ሲመጣ ይሄስ ‘ሰው ነው አማራ’(የትግራይ ሰው ነው ወይንስ አማራ)ማለቷ ነው እንጅ አንዱን ዘር አግዝፋ ሌላውን ለማንቋሸሽ የተጠቀመችበት ቃል አልነበረም። ተንኮለኞች ግን ሕዝብ ከሕዝብ ጋር ለማጋጨትና ለማጣላት ወልቃይቴዎች እንዲህ እያሉ ይንቁን ነበር እያሉ የማይረሳ አፍ ወለድ የጥላቻ ቁርሾ አሁንም እንደ ታላቅ ታሪካዊ አባባል ተቆጥሮ በመስኮት ብቅ ማለቱ አንገት የሚያስደፋ ግዜው ያለፈበት አፅያፊ ፌዝ ነው።
አንድ ህብረተሰብ አብሮ የመኖሩን እድል ከፍ የሚያደርገው ትግርኛ በመናገሩ ነው ብዬ አላምንም ምክንያቱም ቋንቋ ለመግባቢያ ከመሆኑ አልፎ ለሌላ ጥቅም የሚውልበት ምክንያት አይታይም “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” ሆነ እንጅ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ አማርኛ መናገር ይችላል ለምን አማራ ነህ አይባልም? ስለዚህ የወልቃይት ህዝብ ትግርኛ በመቅሰሙ የትግራ ዜግነት ሳያምንበት መቀበል አለብህ ብሎ ማስገደድ የነብሰ በላው የእህትዎ ባለቤት የመለሰ ዜናዊ የጥፋት ራዕይ ሲባል የሰፊው ሕዝብ ሥቃይና መከራ ዳግም ለማራዘም ቀዳዳ መሻቱ ለልጅ ልጅ የሚተርፍ የዘቀጠ ታሪክ ነው የሚሆነውና ለአንድ አፍታ ቆም ብለው በማሰብ ለህዝብዎ የሚጠቅም ያልተወላገደ ታሪካዊ ትምህርት ለማስተማር እንዲጥሩ ወንድማዊ ምክሬን ልለግስልዎት አወዳለሁ። ህዝባችን አልተማረም ብለን በማር የተለወሰ የኮሶ መድሃኒት እንደ የጋርዮሽ ዘመን ና እንጋትህ ብንለው ጉዳቱና ጥቅሙ ሳይመረምር አሺ ብሎ መቀበሉ ቀርቷል። እኔም ሆንኩ እርስዎ በጫርነው ማስታወሻ የሚደለል ህዝብ ያለ አይመስለኝም። ከሁለት ሦስት ለማይበልጡ የአካባቢው ተወላጅ ካድሬዎች ጥቅም ለማስከበር ተብሎ ለዘመናት የቆየዉን የህብረተሰብ ትስስር በዉሃና ዘይት መስሎ ግራ ለማጋባት መጣሩ በታሪክ ያስወቅሳል። ወንድምዎ አቶ ፈረደ የሺወንድም እጁ በወልቃይት ንፁህ ሕዝብ ደም የከረፋ መሆኑ እያወቁ ህዝብን ይቅርታ እንደ መጠየቅ ፈንታ ዳግም አገርሽቶበት ከመቀሌ አዲስ አበባ፤ከጎንደር ሁመራ፤ማይ ካድራ፤ቃፍትያና ወልቃይት እየተዘዋወረ እጃችሁ ይቆረጣል፤ አይናችሁም ይጠፋል እያለ የወልቃይትን ወጣቶች ከተወለዱበት ቦታ ገፍትሮ እያስወጣ አንገታቸው ለአረብ ስለት እያመቻቸ መሆኑ ተነቅቶበታልና ከእንደዚህ ዓይነት ተግባር ተቆጥቦ ሕዝቡን ይቅርታ መጠየቁ ብልህነት እንጂ ወርደት አይደለም። አቶ ኃይሉ ወልቃይት ለትግራይ እንጅ ለአማራ ቅርበት የለውም ባሉ ሳምንት ባልሞላው ግዜ የአሜሪካ ራድዮ ድምጽ አቶ አታላይ እና ኮሌኔል ደመቀ እንዲሁም አንዱን የተ.ሐ.ህ.ት ተወካይ የሆነው ግለሰብ ወይዘሮ ትዝታ በላቸው ባቀረበችላቸው ጥያቄ የዓማራ ማንነታችን ያለሕዝብ ፍቃድ በጠበንጅ ኃይል ነው ወደ ትግራይ የተካለልነው እና ወደ አማራው ብሄራችን መመለስ አለብን የሚለው የወልቃይት ሕዝብ ወክሎ ያስቀመጠን ተወካዮቹ ነን በማለት ለቀረበላቸው ጥያቄ ማስረጃን በማስደገፍ በሚያረካ ቃል ሃቁን ፍርጥርጥ አድርገው ሲገልፁ በተሐህት በኩል የቀረበው ወኪል ግን ሊያዝና ሊጨበጥ በማይቻል በውሸት የተቀነባበረ መተባተብ ስሰማ ያዘንኩት ለሆድ አደሩ ግለሰብ እንዲህ በል ተብሎ ተፅፎ ለተሰጠው ሳይሆን ያ ሁሉ እውቀት ይዘው ወገናቸው የሆነውን የወልቃይት ሕዝብ ለውርደት የዳረጉት አቶ ኃይሉ የሽወንድምን ነው። አቶ ኃይሉ ለብዙ ዓመታት ተደብቀው ከቆዩበት ዋሻ በጋህድ እንደ ነጭ በሬ ዛሬ በግልጽ አደባባይ መታየት የፈለጉበት ምክንያት በእኔ ግምት ራስ ገዝ የምትባለው የተሐህት ማደናግርያ ቃል ጠልፋ አታለለቻቸው መሰለኝ ያሳዝናል እርስዎን የመሰለ አዋቂ ግለስብ ከአቶ አቦሃይ ጋር አደባባይ ላይ መዋል ያሳፍራል ሹመት ይባርክ እላለሁ።
7ኛ/ አማራውና ወልቃይቴውን በዉሃና ዘይት፤ ትግሬውና ወልቃይቴውን በዉሃና ወተት ይመሰላል ይሉናል!!
ወንድም ኃይሉ የመሰለዎትን አቋም ለመግለፅ ለምን አቀበትና ቁልቁለት መዝለቅና መውረድ አስፈለገዎት የወልቃይትን ህዝብ እንደፈለጉት በወተትና ውሃ ወይም በዘይትና ውሃ ቢመስሉት የህዝቡ መልስ አንድ አና አንድ ብቻ መሆኑ በተለያዩ አጋጣሚዎች ግልፅ በሆነ ቋንቋ  ኢፋ ሲያደርግ እንዲህ ነበር ያለው ማንነቴን ማንም ሊነግረኝ አይችለም የጠራሁ የነጠርኩ ጎንደሬ አማራ እትዮጵያዊ ነኝ።
8ኛ/ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ስርአት በበጎ ጎኑ የሚታወቀው በኢትዮጵያ ውስጥና ሰላም ባልሰፈነባቸው ቀጠናዎች ሰላምና መረጋጋትን በማምጣቱ ነው። የብሄረሰቦችን መልስ በመገኘቱ፡›
አሁንስ የኢትዮጵያን ህዝብ ጆሮ እንደሚያደነቁረው የመለሰ ዜናዊ ሬድዮ ጣብያ ሆኑብኝ የሰላምን ትርጉም ከእርስዎ የበለጠ የሚያውቅ ይኖራል ብየ አልገምትም እስኪ የኢትዮጵያ ህዝብ ያለ ችግርና መከራ የዋለበት ቀን ይቁጠሩልኝ ሰላምና መረጋጋት ከኖረ ለምን ወጣቱ በዱር ገደሉ፤በባህርና በየብሱ እንደ ቅጠል ይረግፋል፤ለምን የተወለደበትን አገር አስጠላው፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ ዲሞክራሲን ያሰፈንኩ ድርጅት ነኝ ባለች በበነገታው መሳርያ ባልታጠቁ ወጣት ተማሪዎች ላይ ለምን የጥይት ኢላማ ተደረጉ፤ለመሆኑ ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ያሉበትን ቦታ ያውቃሉ? በኢትዮ ኤርትራ አላስፈላጊ ጦርነት የህዝብን ብሶት ለመሸፋፈን ሲባል ከመቶ ሺህ ህዝብ በላይ የተቀጠፈበት ጦርነት፤የአሜሪካን ምፅዋት ለማግኘት ሲባል አማችዎ መለሰ ዜናዊ ያስፈጀው ወጣት ወዘተ. እስቲ ይንገሩኝ የትኛው ብሄረሰብ ነው መብቱ የተከበረለት? ከተከበረለትስ ለምን የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን ለመብታቸው ስለጮሁ አናት አናታቸው በጥይት የተመቱ። ከአሁን በፊት ካልሰሙ እኔው ልንገርዎት ሰላም በአገራችን ሰፍኖ አያውቅም ምናልባት በመለሰ ዜናው ግቢ፤በአግአዚ ቅልብ ወታደሮች፤ፍርፋሪ ለቃሚ ካደሬዎች ሰላም ሰፍኖ ሊሆን ይችላል እንጂ ሌላው ኢትዮጵያዊ ከመቃብር በታች ነው እየኖረው ያለው። በአካባቢያችን ዙርያ ከሚኖሩት ጋር ሰላም ሰፍኗል ያሉት ለምን አይሰፍንም የእኔና የእርስዎ አያትና ወላጆች በደማቸው ያቆዩትን ለም መሬት ለገጸበረከት ለሱዳን ሲሰጥ፤ በአረቦችና ቻይናዎች ተደፍራ የማታውቀውን አገር ካስደፈርክ ለምን በሰላም መኖር አይቻልም። ለወንድሜ አቶ ኃይሉ የማሳስበው በሰለጠነው ህብረተሰብ ለብዙ ግዜ አብረው ኑረዋል በአስተሳሰብ ልዩነት ቢጋጩ ቢፋጩም አገራቸውን የሚጎዳ ነገር ሲመጣ ልዩነታቸው ወደ ጎን በመተው በአንድነት ነው የሚቆሙት እንጅ ጥላቻን መሰረት ያደረገ ቁርሾ አይገቡምና ሁላችንም የአገራችን ጉዳይ ማስቀደም ከሁሉም የበበለጠ ስራ መሆን ይኖርበታል የሰው ልጅ ተሰባሪ እቃ ነው አገርና ታሪክ ግን ህያው ናቸው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ከአሁን በፊት በዘር የመከፋፈል ችግር ገጥሞት አያውቅም ነገር ግን ሊካድ የማይችል የአስተዳደር ብልሹነት ነበረ። በዘር አድሎ ግን አንዱን ጎድቶ ሌላውን የጠቀመበት ግዜ አልነበረም በርግጥ ውስን የሆኑት በስልጣን መዋቅር ላይ የነበሩት ህዝቡን ይበዘብዙት ነበር ግን እንደ አሁኖቹ ባለጌ የደደቢት ሽፍቶችን ያህል በደል በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ አያዉቅም። ይህችን አውሬ የሆነች የሁላችን ጠላት ድርጅት ከምድረ ገፃችን ካላሰውገድን በሰላም የመኖር ተስፋችን የመነመነ ነው የፖለቲካ ልዩነቶች ወደ ጎን ትተን ህልውናችን ለማረጋገጥ በጋራ መነሳት ሲገባን አንዱ በአንዱ ጣት እየተቀሳሰርን የወገናችን ችግርና ስቃይ እያራዘምነው ያለን እኛው እራሳችን እንጂ ማንም ሊወቀስ አይችልም ወያኔን በየመድረኩ ከመርገም ይልቅ ሰብሰብ ብለን በአንድነት ተማምነን ስንቆም ብቻ ነው ጠላትን ማርበድበድ የምንችለው ሥለዚህ ግዜው አሁን ነው።
ዘረኝነት ይጥፋ!
ኢትዮጵያችን ለዘልዓልም ትኑር።
ጥር 22/2008 ዓ.ም

እውን ወልቃይት ትግሬ ነው? (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ
ወቅቱ 1994 ክረምት ነው፡፡  በየአመቱ ት/ት ቤቶች ሲዘጉ መምህራንን አንደም በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ለማጥመቅ ሁለትም ስራ ፈተው ከዋሉ የሚሰሩት ስለማይታወቅ ጠርንፎ ለማቆየት የሚዘጋጀው ስብሰባ ጎጃም ደብረ ማርቆስ በሶስት አዳራሾች እየተካሄደ ነው፡፡ ቤተ መንግሥት አዳራሽ ሲኒማ ቤትና መንገድ ትራንስፖርት አዳራሽ፡፡
በሲኒማ ቤቱ  ስብሰባ በአወያይነት ከተመደቡት አንዱ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል ድረስ በእንድ መምህር  ስለሚካሄደው የትምህር አሰጣጥ የሚያውቀውን ሳይሆን የተነገረውን በተረዳው መጠን ለተስባሳቢው ገለጸ፡፡ ይሄው የትምህርት አሰጣጥ አማራ ክልልን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ ውጤታማ ሆኗል ያለው  አወያይ በትግራይ ክልል ብቻ ተግባራዊ አለመሆኑ ጠቅሶ ምክንያት ተብሎ የተነገረውንም  ሲናገር በዚህ ደረጃ የተመደቡት በአብዛኛው ሴቶች ነበሩ፣ ከእነዚህ አብዛኛዎቹ ደግሞ በተመሳሳይ ውቅት በማርገዛቸው ፕሮግራሙን ማስቀጠል አልተቻለም  አለ ፡፡ በዚህ ግዜ አዳራሹ በሳቅ ተሞላ፡፡ መድረኩ ለውይይት ክፍት መሆኑ ሳይገለጽም  ለአስተያየትና ለጥያቄ በርካታ እጆች በአየር ላይ ታዩ፡፤
እውያዩ ገለጻውን አብቅቶ (የተነገረውን ተናግሮ) ቀጣዩ ሰአት የውይይት መሆኑን ገልጾ ቅድሚያ ለሴቶች በሚል የመጀመሪያውን የመናር እድል ለሴት ሰጠ፡፡ እድሉ የተሰጣት መምህርትም ከአንድ እስከ አራተኛ ክፍል በአንድ መምህር ማስተማር በአማራ ክልል ውጤታማ ሆኗል ተብሎ ከመድረክ የተገለጸው  እኛ በተግባር ከምናውቀው ጋር የሚገናኝ አይደለም በማለት ከአወያዩ ገለጻ በተቃራኒ የሆነ አስተያየት ከሰጠች በኋላ አንድ ጥያቄ አለኝ እሱም ምንድን ነው በትግራይ ክልል በዚህ ደረጃ የተመደቡት  አብዛኛዎቹ ሴት መምህራን በመሆናቸውና ከእነርሱም ብዙዎቹ በተመሳሳይ ወቅት በማርገዛቸው ፕሮግራሙ ተግባራዊ አለመሆኑና ወደ ቀድሞው አሰራር መመለሱ ተገልጻል፡፡ እዚህ አማራ ክልል እኛ ሴቶቹ ማርገዝ አልችል ብለን ነው; ወይንስ ወንዱ ማስረገዝ አቅቶት; ጥያቄየ ያሄ ነው ብላ ስትቀመጥአዳራሹ በጭብጨባ በሳቅ በውካታ ተናጋ፡፡ አወያዩ የሚይዝ የሚጨብጠው ጠፍቶት ተደነጋግሮ እየተርበተበተ ቀልዱን አቁሙና ወደ ቁም ነገር አንግባ ማለት ጀመረ፡፤
መምህርቷ አጋጣሚውን በመጠቀም አጠቃላይ ፖለቲካዊ መልእክት ለማስተላለፍ አስባ ያደረገችው ይሆን ወይንም በመድረክ የተነገረው ስሜቷን ነክቶት ለዚሁ ምላሽ ለመስጠት  ብላ የተናገረችው  የምታውቀው እሷ  ብቻ ብትሆንም የተናገረችው ቃል ግን  ጥልቅ መልእክት ያለው ነበር፡፡  የአማራ ወንዶች ማስረገዝ አቃታቸው ወይ; ከባድ ጥያቄ ነው፡፡
ከአስር ዓመታት በላይ ወደ ኋላ ሄጄ ይህን እንዳስታውስ ያደረገኝ አቶ አቦሆይ የተባሉ የህውሀት ሰው ሰሞኑን ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር  ባደረጉት ቃለ ምልልስ  ያለምንም ማንገራገር  በድፍረት ወልቃይት ትግሬ ነው ሲሉ መስማቴ ነው፡፡ ሰውየው በዚህ አላበቁም ወልቃይት ትግሬነቱን ለማስከበር የትጥቅ ትግል ማካሄዱን  አሁን በትግራይ ክልል ስር በመሆኑ ደስተኛ መሆኑን ኮሚቴ የሚባሉት ሰዎች ህዝቡን የማይወክሉ እንደሆኑ ወዘተ ተናገሩ፡፡ ንግግራቸው ፈር የለቀቀና ከእውነት የራቀ  መሆኑ ሳያንስ ድፍረታቸው ያስገረማት ጋዜጠኛ (ትዘታ)  ጥያቄዋን ጠንከር ስታደርግባቸው አሁን ትንሽ ስራ አለብኝ ሌላ ግዜ ደውለው እንነጋር በማለት  ጥያቄዋን ከዛ በላይ አንዳትገፋ  አደረጓት፡፡
ግለለሰቡ የአንድ ወረዳ ሹም ቢሆኑም የተናገሩት የተነገራቸውንና ርሳቸው በቦታው ተሸመው እያስፈጸሙት ያለውን የድርጅታቸውን እምነት በመሆኑ በአነስተኛ ሥልጣን ለይ ያለ ሰው የተናገረው ተብሎ ተቃሎ የሚታይ አይደለም፡፡
ታሪክን ሽረው እውነትን ክደው ወልቃይት ትግሬ ነው ሲሉ ንግግራቸው ሳይሆን ንቀታቸው ያበግናል፣ ማንአለብኝነታቸው  ስሜትን ይፈታተናል፤  ድፍረታቸው እልህ ያሲዛል፡፡ የአማራ ወንድ ማስረገዝ ኣቃተው እንዴ  የሚለውን ከላይ የጠቀስናትን መምህርት ጥያቄም ያስታውሳል፡፡ ወልቃይት በብልሀትም በጉልበትም  መሬቱን ተነጥቆ፣   ማንነቱ ተለውጦ ያለአባቱ ትግሬ ተብሎ ሀያ አራት አመት በትግራይ ክልል ስር  መገዛቱ ሳያንስ  ወያኔዎች ደፍረው ወልቃይት ከጥንትም ትግሬ ነው ለማለት የበቁት የወልቃይትን አማራነት የሚያረጋገጥ ወንድ ጠፍቶ ነው ; የሚያሰኝም  ነው፡፡ (በቅርብ ግዜ ተጠናክሮ የቀጠለውን የኮሚቴዎች እንቅስቃሴ ሳይጨምር ነው ታዲያ)
ከላይ ከአፋፉ ላይ ካልከሉት ጠላት አይን የለውም ይገባል ከቤት በማለት ድንበር የሚገፋን ሆነ ግዛት የሚያስፋፋን
ገና ሲጀማምር  ማስቆም እንደሚገባ  በቀረርቶ የሚገልጸው አማራ በምን መንገድ ተታሎ ወይንስ በምን ያህል ጫና ተረቶ ት ነው እንዲህ በገዛ መሬቱ እሱ አንደ ጭሰኛ  ቀማኛው  አንደአባቢድራ ለመኖር የበቃው የሚያሰኝም ነው፡፡ መምህሯ አንዳለችው ማስረገዝ አቅቶት ይሆን!
እንደምንሰማው ከሆነ በወሰዱት ለም መሬት ያረኩት ይበልጡኑ የጎመዡት ወያኔዎች ከወሰዱት የሚበልጥ መሬት እንደሚቀራቸውና ያንንም ለመጠቅለል  እንደሚያልሙ ነው፡፡  ይህም አያያዙን አይተው ጭብጦውን ቀሙት አይነት መሆኑ ነው፡፡
የጥምቀትን በዐል በተለይም የጃንሆይ ሜዳ ክብረ በአልን በልዮ አጨፋፈራቸው በማድመቅ የሚታወቁት የቀድሞው ሰሜን ወሎ የአሁኑ ደቡባዊ ትግራይ ዞን ነዋሪዎች (ራያዎች) በሆታቸው የሚሉት ግጥም በአብዛኛው ፖለቲካዊ ነው፡፡ታዲያ ገና የወያኔ መንግስት ባልረጋ ባልተረጋገባት ግዜ አንስቶ እስከ ቀርብ ግዜ ድረስ ራያ እንጨት ስበር ቆቦ ውኃ ቅዳ ፣ላስታ አንጨት ስበር ጎንደር ውኃ ቅዳ እያሉ ወያኔ ወደመሀል አገር የተንደረደረባቸውን አካባቢዎች ይጠቃቅሱና ወዴት ትሸሻለህ ጎትተህ ጎትተህ ባመጣኸው እዳ  በማለት የአካባቢውን ፖለቲካዊ ሁኔታ ይገልጡት ነበር፡፡
ወያኔ ከደርግ አይብስም ብሎ በተለይም በመላኩ ተፋራ አረመኔያዊ ድርጊት ተማሮ ለወያኔ ድጋፉን የሰጠው ጎንደር መሬቱን ተነጠቀ፤  የጫርኩት እሳት እኔኑ ፈጀኝ ብሎ በድርጊቱ ተቆጭቶ ይህን  ለልጆቼ አላስተልፍም በማለት አማረነቴ ይታወቅ ድንበሬ ይከበር ሲል  ወልቃይት ከጥንትም ትግሬ ነው ተባለ፤ አረ እንዴት ሆኖ በማለት ትግሉን ሲያጠናክር  አማራና ቅማንት የሚል የማዳከሚያ ልዩነት ተፈጠረበት ይህም አልበቃ ብሎ የሱዳንን መሬት ወሮ የሚያርስ ሽፍታ ተብሎ ተወግዞ ጥቃት ታወጀበት፡፡ በወያኔ ስለተቀማው መሬት ሲከራከር ምን ታመጣለህ ተብሎ ቀሪው ለም መሬቱም ለሱዳን ሊሰጥበት ነው፡፡ ይህን ሲያደርጉ ሱሪውን ተጠራጥረውት ወንድነቱን ንቀውት ይሆን፡፡ …እነርሱ ምን ያርጉ ከእኛ ሰው ሲታጣ ነው ያለው ያ ድምጻዊ፡፡
ራያዎች በሆታቸው እንዳሉት  አሁን ያለው ትውልድ ይበጃል ብሎ ጎትቶ ያመጣው  በመሆኑ አንድ ውል ሳያሲዝ ከነገሩ መሸሽ ስለሌለበት ስለማይችል፤ ሁለትም የአካባቢው ሁኔታ በዚህ መልኩ ለመጪው ትውልድ መተላለፍ የሌለበት በመሆኑ የወልቃይትን አማራነት  የድንበሩንም ተከዜነት ማረጋገጥ የዚህ ትውልድ ግዴታ ነው፡፡ ወያኔዎች በብልሀትም በጉልበትም ተከዜን ተሻግረው መሬት መውረር ግዛት ማስፋፋታቸውን በተለያየ መንገድ የተቃወሙ የአካባቢው ተወላጆች የደረሱበት እንደማይታወቅ ሰሞኑን እየሰማን ነው፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህም ነገሩን የምር ይዘው በህግ ለማስፈጸም የሚጣጣሩትን የኮሚቴ አባላት ከማወከብ አልፎ አዲስ አበባ እንዳይገቡ  እስከማገት ተደርሷል፡፡ይህ ሁሉ ንቀት ነው ማናለብኝነት፡፡
ቢሆንም ግን ይህና መሰል የወያኔ አድራጎት  ምሬቱን አክፍቶትና ብሶቱን አብሶት ነገሮች እነርሱ ወደሚፈልጉት ለኢትዮጵያውያን ግን ወደማይበጅ  አቅጣጫ እንዳያመሩ ቁስለቱን ሁሉ ችሎ፣ ንቀቱን ታግሶ፣ ጥቃቱን ተቋቁሞ ከእነርሱ በላይ ማሰብን ይጠይቃል፡፡ የገበያ ግርግር ለሌባ ያመቻል አንዲሉ እነርሱ ተጠቃሚ የሚሆኑት ህዝብ ተፋቅሮ ተከባብሮ ሲኖር ሳይሆን ርስ በርሱ ሲጋጭ መተማመን አጥቶ የጎሪጥ ሲተያይ ወዘተ በመሆኑ ነገሮች ወደዛ እንዳያመሩ ብርቱ ጥንቃቄ ያሻል፡፡ከምንም በላይ ትግርኛ ተናጋሪውን ወገን ከሌላው ኢትዮጵያዊ አቆራርጠው የህውሀት ምርኮኛ ለማድረግ የሚዘሩት መርዝ ፍሬ እንዳያፈራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አማራ አንጂ ትግሬ አይደለሁም ድንበሬም ተከዜ ነው ማለት ራሱ የወያኔው ሕገ መንግሥት የሚደግፈው ጥያቄ በመሆኑ ነገሮች ወያኔዎች ወደሚጎትቱት አቅጣጫ ሳይሆን ህዝብ ወደሚፈልገው አቅጣጫ እንዲያመሩና ዘላቂ ሰላም ሊያስገኙ በሚያስችል መልኩ መፍትሄ አንዲያገኙ ቆራጥና የሰከነ ትግል ማካሄድ የግድ ይላል፡፡ አለበለዚያ ዳሩ ካልተከበረ መሀሉ ዳር ይሆናል እንደሚባለው የወልይት ጎንደሬነት ታሪክ ሆኖ ይቀራል፡፡ አለያም ግዜ እየጠበቀ የሚፈነዳ ፈንጅ ይሆናል፡፡
የወልቃይትን አማራነትና የድንበሩንም ተከዜነት ለማረጋገጥ የሚካሄደው ትግል ከወያኔ ጋር ብቻ አይደለም፡፡ ኦህዴድ በአዲስ አበባው ማስተር ፕላን እንደተፈተነው ሁሉ ብአዴንም በዚህ ወሳኝና ወቅታዊ ጉዳይ መፈተን አለበት፡፡ ወልቃይት አማራ ነው ትግሬ ፤  ከጎንደርና ከወሎ ወደ ትግራይ የሄደው መሬት ቋንቋን መሰረት ባደረገው የፌዴራሊዝም አከላለል ነው ወይንስ ከጥንትም የትግራይ መሬት በመሆኑ ነው፡ ለሱዳን የሚሰጠው መሬት የኢትዮጵያ ነው  ወይንስ አቶ ኃይለማሪያም እንዳሉት የጎንደር ሽፍቶች በኃይል የያዙት የሱዳን መሬት ነው፡፡  ከብአዴኖች መልስ የሚሻ ጥያቄ ፡፡

በነሃብታሙ ጉዳይ ሰበር ችሎት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ የሕግ ስህተት አለበት አለ

ትላንት ጥር 24 ቀን 2008 ዓ.ም፣ እነ ሃብታሙ አያሌው፣  በሁለት ፍርድ ቤቶች ፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት እነ ከዚያ በላይ በሆነው በሰበር ችሎት ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።
የአንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ፣ አቃቢ “ሽብርተኞች ናቸው” በሚል ላቀረበው ክስ በቂ መረጃ አላቀረበም በሚል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲለቀቁ ቢወሰንም፣ ማረሚያ ቤቱ የፍርድ ቤትን ትእዛዝ በመናቅ እስረኞች ሳይፈታ መቆየቱ ይታወሳል። ቀናቶች ካለፉ በኋላ፣ አቃቢ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ በማለቱ፣ የአንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት የወሰነዉን ዉሳኔ ታግዶ፣ እነ ሃብታሙ በወህኒ እንዲቆዩ ተደርጓል።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ የታችኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ማገዱን በመቃወም፣  ለሰበር ፍርድ ቤት በቀረበው ክስ መሰረት፣ ለሶስት ወራት ጉዳዩ ከታየ በኋላ፣ ሰበር ፍርድ ቤቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ መሰረታዉ የሕግ ጥሰት እንዳለበት ያረጋገጠ ሲሆን፣ ጉዳዩን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እንዲመለከተው  ወደዚያ አስተላልፎታል።
በሌላ በኩል በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፣ ከአሥራ አምስት ቀናት በፊት፣ አቃቢ ሕግ እነ ሃብታሙ አያሌዉን ለመክሰስ ያቀረበዉን የኦዲዮ መረጃዎች ይዞ እንዲያቀርብ ተጠይቆ፣   አቃቢ ሕግም  15 ቀናት  ይሰጠኝ ባለው መሰረት፣ ለዛሬ ጥር 24 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆን፣  አቃቤ የተጠየቀዉን ማስረጃ ሳያቀርብ ቀርቷል።
ፍርድ ቤቱ  ለሚቀጥለው ሳምንት መረጃው እንዲቀርብ ያዘዘ ሲሆን፣  በዚያን ጊዜ መረጃው ካልቀረበ፣  ዉሳኔ እንደሚወስኑ በመግልጽ ተለዋጭ ቀጠሮ ለየካቲት አንድ ቀን ተሰጥቷል።
በሁለቱም ፍርድ ቤቶች የነበረዉን ሁኔታ የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ መለስካቸው አመሐ እንደሚከትለው አቅርቦታል፡

ማኅበረ ቅዱሳን ለፓትሪያርኩ ደብዳቤ ጻፈ | “የፓትርያርኩ መመሪያ የእውነት ጠብታ የለበትም”

§ ቅዱስ ሲኖዶስ እርምት እና አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥበት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ተማፅኗል
§ ከአስተዳደር በደል እና ከዝርፊያ የተነሣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ሁኔታ እንዳሰጋው ገልጧል
§ አግባብነቱን የጠበቀ ወቅታዊ እርምትና መተማመኛ ያለው አሠራር ተግባራዊ እንዲኾን ጠይቋል
በአዲስ አበባ ዛሬ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው:-
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ኮሌጆች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የማያቋርጥ ትግል እንዲያካሒዱ በደብዳቤ ላስተላለፉት ክሥ እና ወቀሳ አዘል መመሪያ ማኅበሩ የጽሑፍ ምላሽ ሰጠ።
mahibere-kidusan-logo
የማኅበሩ ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ፥ በኮሌጆቹ ውስጥ በስውር የሚካሔደው “የተሐድሶ መናፍቃን” እንቅስቃሴ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በመጥቀስ ያቀረበውን ተከታታይ ዘገባ ተከትሎ ፓትርያርኩ ባለፈው ሳምንት ሰኞ ለቅድስት ሥላሴ፣ ለሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ እና ለቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጆች በአድራሻ በጻፉት ደብዳቤ፥ ማኅበሩ የቅዱስ ሲኖዶስን ሥልጣን በመጋፋት በቤተ ክርስቲያንና በት/ቤቶቿ ላይ የጥፋት ጣቶቹን መቀሰሩን በመግለጽ ለሕግ ተገዥ እስኪሆን ድረስ እንዲታገሉት ኮሌጆቹን አሳስበዋል።
ክሡን በግልባጭ እንኳ እንዲያውቀው አለመደረጉንና የደብዳቤው ዓላማና ተልእኮው ምን እንደሆነ ለመገመት መቸገሩን የገለጸው ማኅበረ ቅዱሳን በበኩሉ፤ ፓትርያርኩ ያስተላለፉት መመሪያ ፍጹም እውነትነት በሌለው መረጃ ላይ የተመረኮዘና ማኅበሩን የማይገልጽ እንደኾነ በመጥቀስ ዝርዝር የጽሑፍ ምላሽ ሰጥቷል። በዘገባው በተነሡት ሐሳቦችና ስለማኅበሩ አሠራር መወያየት አስፈላጊ ሲሆንም መገሠጽ እየተቻለ ሰዎችን በሚያስቆጡ ቃላት መሸንቆጥ የምእመናኑን ትዕግሥት እየተፈታተነ እንዳለ በምላሹ ተገልጧል።
ማኅበሩ፥ ጥር 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በቁጥር ማቅሥአመ/239/02/ለ/08 ለፓትርያርኩ፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአድራሻ በጻፈውና ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱና ለተለያዩ መንግሥታዊ አካላት ደግሞ በግልባጭ ባሳወቀው ደብዳቤ፤ አባታዊ መመሪያና ቡራኬ ለመቀበል፣ በሚነሡበትም ክፉ ጉዳዮች ለመወያየት በአካል በመቅረብ፣ ለስድስት ጊዜያት ደብዳቤ በመጻፍ እንዲሁም ብፁዓን አባቶችን ጨምሮ በተለያዩ አካላት በኩል ፓትርያርኩን ለማነጋገር ቢጠይቅም ጊዜ ሰጥተው ሊያወያዩት እንዳልቻሉ አውስቷል።
abune matias
በአንጻሩ ማኅበሩን በመክሰስ ለሚቀርቡ የተለያዩ አካላት ፓትርያርኩ ጊዜ እየሰጡ እንደሚያነጋግሩ የጠቀሰው ደብዳቤው፣ “ለአንድም ቀን እንኳን በተከሰስንበት ጉዳይ ቀርበን ቃላችንን እንድንሰጥ አለማድረግዎ አስደንቆናል፤” ብሏል። “የተሐድሶ እምነት አራማጆች” በሚያዘጋጇቸውና በሚመሯቸው ድረ ገጾችና ብሎጎች ማኅበሩን ለመክሰስ የሚያወጧቸው ሐሳቦች በፓትርያርኩ መመሪያም ተጠቅሰው መታየታቸው እንዳሳዘነውና እንዳስገረመው ማኅበሩ ገልጾ፣ ከሳሾች ባቀረቡት ቃል ላይ ብቻ ተመሥርቶ ፍርድ መስጠት እውነተኛውን ሕግ በምትተረጉመው ቤተ ክርስቲያናችን ፍጹም እንግዳ ሥርዓት እንደኾነ ተችቷል፤ እውነታውን ለማወቅና ለሚነሡ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የጉዳዩን ባለቤቶች ጠርቶ ፊት ለፊት በማነጋገርና በመመካከር መፍታት እንጂ አንድ ጩኸት በተሰማ ቁጥር ደብዳቤ መጻፉ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንደማይበጅ ማኅበሩ አስገንዝቧል። (የማኅበረ ቅዱሳን ደብዳቤ ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ተያይዟል)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ቁጥር ማቅሥአመ/239/02/08
ቀን 24/05/2008
ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣
ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ
ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ
በያላችሁበት
ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ
ጉዳዩ፡- በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ስለተጻፈና የተሳሳተ መረጃ
የያዘ ደብዳቤን ይመለከታል
ቅዱስ አባታችን ሆይ፡-
በደብዳቤ ቁጥር ል/ጽ/179/338/2008 ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም ከቅዱስነትዎ የተጻፈና ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ለሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና ለቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ በአድራሻ የተጻፈ፤ ማኅበረ ቅዱሳንን አስመልክቶ ፍጹም እውነትነት የሌለው መረጃ ላይ በመመርኮዝ መመሪያ ያስተላለፉ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ በተለያዩ ሚዲያዎች ተሰራጭቶ ተመልክተናል። ይህም ጉዳይ እኛን የቤተ ክርስቲያን አካል የሆንን ልጆችዎን እጅግ አሳዝኖናል። የደብዳቤው ዓላማና ተልእኮም ምን እንደሆነ ለመገመት አስቸግሮናል። ምንም እንኳ በደብዳቤው የሰፈረው ሃሳብ ፍጹም እኛን የማይገልጸን ቢሆንም ስለተከሰስንበት ጉዳይ በግልባጭ እንኳ እኛ እንድናውቀው አልተደረገም። ይሁንና እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ እንዳደረግነው እውነቱን ለማስገንዘብ አሁንም ይህንን ደብዳቤ ለመጻፍ ተገደናል።
ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ስር ሕጋዊ በሆነ ሥርዓት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ ዕውቅናና ፈቃድ ተዋቅሮ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ እነሆ 23 ዓመታትን አሳልፏል። ማኅበሩ የሚመራበትና የሚተዳደርበት ደንብም በመጀመሪያ በማደራጃ መምሪያው በኩል በኋላም በ1992 ዓ.ም በቅዱስ ፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በኩል በዝርዝር የሚያጠኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመሩት ኮሚቴ ታይቶና ተመርምሮ የጸደቀለት እንዲሁም በ1994 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ደረጃ ቀርቦ የታየ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመሩት፣ የተለያዩ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት እና የሕግ ባለሙያዎች የተሳተፉበትና ከ6 ወራት በላይ የፈጀ ጥናት የተደረገበት የማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ እንደገና ታይቶና ተፈትሾ በምልዓተ ጉባኤው የጸደቀና ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ፊርማቸውን ያስቀመጡበት መሆኑን ቅዱስነትዎ ጠንቅቀው ያውቁታል ብለን እናምናለን። ይህንንም ማድረጋቸው ብፁዓን አባቶቻችን ዘመኑን በመዋጀት በዘመናዊ ትምህርት የሚመረቁ ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ አርቀው በማሰባቸው ነው። እውነታው ይኽ ሆኖ ሳለ በደብዳቤዎ ላይ ማኅበሩን «ጥቅሙና ጉዳቱ በሚገባ ሳይጠና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር የሚያስከትለው የሃይማኖትና የሥርዓት ተፋልሶ ሳይፈተሽ በአንድ ወቅት ራሱ አርቅቆና አዘጋጅቶ ባቀረበው ደምብ በቅዱስ ሲኖዶስ የተፈቀደልኝ ሕጋዊ ማኅበር ነኝ ይላል$ በማለት መግለጽዎ ለምን እንደሆነ አልገባንም። ይህ ሀሳብም ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና አሠራር የተቃረነ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በ2004 ዓ.ም የማኅበሩ አገልግሎት እየሰፋ በመሄዱ እና በወቅቱ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊዎች ጋር የነበረውን አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓተ ጉባኤ ደረጃ በአጽንኦት ከተመለከተ በኋላ ለጊዜው የማኅበሩ ተጠሪነት ለብፁዕ ዋና ሥራ አሥኪያጅ እንዲሆንና ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ እና ማኅበሩን ከነበረበት ደረጃ የበለጠ ሊያሠራው የሚችል ደንብ እንዲኖረው በማሰብ ቅዱስ ሲኖዶስ እርስዎም በተገኙበት ጉባኤ ደንቡን የሚያሻሽል (የጉዳዩ ባለቤት የሆኑ የማኅበሩ አባላትም የተካተቱበት) ኮሚቴ መሰየሙ ይታወሳል። ይኸው ማሻሻያ ተሠርቶ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ግን ማኅበሩ በ1994 ዓ.ም ጸድቆ የተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ ሕጋዊ ሆኖ እንደሚቀጥልም አጽንኦት ተሰጥቶበት መታለፉ ግልጽ ነው። ቅዱስነትዎ በመንበሩ ከተሰየሙ በኋላም ይኽው አጥኚ ኮሚቴ ሥራውን አጠናቅቆ ቢያቀርብም ቅዱስነትዎ በተደጋጋሚ አልቀበልም በማለትዎ መዘግየቱን የሚዘነጉት አይመስለንም። እንዲያውም ከዚህ አንፃር በርስዎ በኩል የቀረበ እና በየትኛውም አሠራር ቢሆን እንግዳ የሆነ ውሳኔን ማኅበሩ ይሁን ብሎ ተቀብሎታል። ይኸውም በመንግሥታትም አሠራር ቢሆን አንድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሊሰጥ የሚደራጅን ማኅበር ሊያገለግልበት የፈለገበትን አቅጣጫና የሚመራበትን ውስጠ ደንብ ከተቋሙ ሕግ አንፃር አርቅቆ በማቅረብ በፈቃድ ሰጪው አካል ያስጸድቃል እንጂ ፈቃድ ሰጪው አካል ራሱ ሕገ ደንብ አርቅቄ ካልሰጠኹህ አይልም። ሆኖም ግን ቀደም ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ የሰየመውና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መሪነት ከአንድ ዓመት በላይ የደንብ ማሻሻያውን ጥናት ሲሠራ የቆየው ኮሚቴ ያዘጋጀውን ጥናት አልቀበልም ብለው እንግዳ በሆነ መልኩ አንድም የማኅበረ ቅዱሳን ተወካይ የሌለበት ሌላ አዲስ ኮሚቴ እንዲቋቋም መደረጉን ሲሰማ ማኅበሩ በይሁንታ ነው የተቀበለው። ይህንንም ያደረግንበት ምክንያት በብፁዓን አባቶቻችን ላይ ካለን አመኔታና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታዛዥ ከመሆናችን የተነሣ ነው። ይሁንና ቅዱስነትዎ ይህንን በአዲስ መልክ የተቋቋመውን ኮሚቴ አባላቱ እነማን እንደሆኑ እንኳ ለኛ ባላሳወቁበት ሁኔታ “በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን የደንብ ማርቀቅ ሥራ ሆን ብሎ በማሰናከል ያለ ደንብ እየሠራ ይገኛል” በማለት በደብዳቤዎ ላይ ማስቀመጥዎ እጅግ አስገራሚ ነው።
ይህ ሁሉ ቢሆንም ማኅበረ ቅዱሳን በአባቶች ምክር፣ ጸሎት እና ድጋፍ ምንም ዓይነት የሕግም ሆነ የሥርዓት ተፋልሶ ሳያስከትል ለአባቶች እየታዘዘ አሁንም አገልግሎቱን ግልጽ በሆነ አሠራር እያከናወነ ይገኛል። ከእርስዎ ከቅዱስ አባታችንም ዘንድ ቀርበን አባታዊ ቡራኬና መመሪያ ለመቀበል፣ እንዲሁም አንዳንድ ለቤተ ክርስቲያናችን ቅን የማያስቡ ወገኖች የማኅበሩን ስም በክፉ ባነሱበት ጊዜ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በተደጋጋሚ ከእርስዎ ጋር ለመወያየት በአካልም እየቀረብን በደብዳቤም ከስድስት ጊዜ በላይ (በቁጥር ማቅሥአመ/80/02/ለ/06 ቀን 21/1/06 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ /118/02/ለ/06 ቀን 9/5/06 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ/127/02/ለ/06 ቀን 25/6/06 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ /138/02/ለ/06 ቀን 24/8/06 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ/165/02/ለ/07 ቀን 01/02/07 ዓ.ም፣ በቁጥር ማቅሥአመ /212/02/ለ/07 ቀን 3/13/07 ዓ.ም) ለቅዱስነትዎ በቀጥታ ጽፈን መጠየቃችን ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ ከብፁዓን አባቶች ጀምሮ የተለያዩ አካላትንና ግለሰቦችን ከርስዎ ጋር እንዲያወያዩን በተደጋጋሚ ጠይቀን ነበር። ነገር ግን እርስዎ ጊዜ ሰጥተው ሊያነግግሩን አልቻሉም። በአንጻሩ ማኅበሩን ከቅዱስነትዎ ዘንድ ከስሰው የሚቀርቡ የተለያዩ አካላትን ጊዜ እየሰጡ ማነጋገርዎ ብቻ ሳይሆን አንድ ቀን እንኳን በተከሰስንበት ጉዳይ ቀርበን ቃላችንን እንድንሰጥ እንኳ አለማድረግዎ አስደንቆናል። ክስ የቀረበበትን አካል አቅርበው ሳይጠይቁ ከርሱም ሳይሰሙ ከሳሾች ባቀረቡት ቃል ላይ ብቻ ተመስርቶ ፍርድ መስጠት በማንኛውም አካል ዘንድ በተለይም እውነተኛውን ሕግ በምትተረጉመው ቤተ ክርስቲያናችን ፍጹም እንግዳ የሆነ ሥርዓት ነው።
ቅዱስ አባታችን ሆይ፡-
የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና የሚያስጠብቀው ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 2007 ዓ.ም ባደረገው ጉባኤ ከተወያየባቸው ጉዳዮች መካከል ተሐድሶን በተመለከተ በቃለ ጉባኤው ያሰፈረው እንደሚከተለው ይነበባል “… የተሐድሶ መናፍቃን መገኛ ምንጫቸው ከየት እንደሆነ ጉባኤው በመወያየት ደቀ መዛሙርቱ ከየአኅጉረ ስብከቱ ሲላኩ ጤናማ እንደሆኑ ነገር ግን ተመርቀው ሲመለሱ ግን ከነችግራቸው ሌላ ሰው ሆነውና መስለው ይመለሳሉ። ለዚህ የችግሩ ምንጮች ኮሌጆቹ እንደሆኑ ያመለክታል። ምክንያቱም መንፈሳዊ ኮሌጆች ተልከው መናፍቃን ሆነው ሲመለሱ እያንዳንዱን ኮሌጅ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባዋል። ስለዚህ ሁሉም ኮሌጆች ሊፈተሹና ሊመረመሩ ይገባል …“ ካለ በኋላ ቃለ ጉባኤው የሚከተለው ውሳኔ መተላለፉን ይገልጻል። “… የመምህራን ክህሎት እና የሃይማኖታቸው ጉዳይ፣ የኮሌጆች የትምህርት ካሪኩለም አቀራረጽ፣ የመማሪያ መጻሕፍት ዝግጅት ምን እንደሚመስል ታይተውና ተፈትሸው ሊሠራባቸው ይገባል” የሚል ውሳኔ ማስተላለፉና ይህንንም የሚያጠና አንድ ኮሚቴ ማቋቋሙ ይታወቃል። ይህንን ውሳኔ ለተቋቋመው ኮሚቴ ለማሳወቅ ቅዱስነትዎ ኅዳር 4 እና 11 ቀን 2007 ዓ.ም በጻፏቸው ደብዳቤዎች ላይ “መናፍቃንና የተሐድሶ አራማጆች በቤተ ክርስቲያናችን ኮሌጆች ተምረው ስውር ዓላማቸውን በማካሄድ ሕዝበ ክርስቲያኑን በመከፋፈል ላይ ስለሚገኙ ከኮሌጆቻችን ጀምሮ … በማስረጃ የተደገፈ ጥናት እንድታቀርቡ” በሚል አጽንኦት ሰጥተው መግለጽዎ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪ ባለፉት ሁለት ዓመታት በተደረጉት የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ አኅጉረ ስብከት የቀረቡ ሪፖርቶችና አስተያየቶች ከየመንፈሳዊ ኮሌጆች የተመረቁ አንዳንድ መምህራን የተሐድሶ መንፈስ እያራመዱ እንዳስቸገሯቸውና የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ማወካቸውን በግልጽ ማቅረባቸው፣ እነዚህም ሀሳቦች በጉባኤዎቹ ሲቀርቡ በተሰብሳቢዎቹ ከፍተኛ ድጋፍ ሲሰጣቸው እንደነበር ይታወሳል።
የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ የሆነችው ስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ጋዜጣም ይህንን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና የአኅጉረ ስብከት ሪፖርቶች መነሻ በማድረግ ከመስከረም ወር 2008 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ንቁ በሚለው አምዷ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ መልኩን እየቀያየረ እና በረቀቀ መልኩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕልውና አደጋ ውስጥ እየከተተ የመጣውን የተሐድሶ መናፍቃኑን አጠቃላይ የኅቡዕ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ዘገባ እየሠራች መረጃ መስጠት ቀጥላለች። በተለይም በኅዳር እና በታኅሣሥ አጋማሽ እትሞቿ ተሐድሶዎች ቤተ ክርስቲያናችን በምትመካባቸው መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን ውስጥ በስውር ምን እያደረጉ እንደሆነ እና ለነርሱም መግቢያ ቀዳዳ ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን በማሳያነት በመጥቀስ ዘገባ ማቅረቧ እውነት ነው። ለዚህም ዘገባ የተለያዩ አካላት ያወጧቸውን ሪፖርቶች ጋዜጠኛው ወይም ጸሐፊው በመጠቀም በኮሌጆቹ አካባቢ የተሐድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴ የሚያመላክት የዳሰሳ ጥናት ማድረጉ ተገልጿል። በንጹሕ ስንዴ መካከል እንክርዳድ መገኘቱ ፍጹም እንግዳ ባይሆንም ቁጥሩ እየጨመረ መምጣቱ ግን አሳሳቢ መሆኑ በጽሑፉ ተዳስሷል። በሌላ መልኩ ደግሞ ቤተ ክርስቲያናችን እጅግ የምትኮራባቸው መምህራንና ሊቃውንት ከነዚሁ ኮሌጆች በብዛት መገኘታቸውን እና የየኮሌጆቹ የሥራ ኃላፊዎችም ሆኑ እውነተኞቹ ደቀ መዛሙርት ይህንን የተሐድሶዎችን እንቅስቃሴ ተረድተው ምን ዓይነት ተጋድሎ እያደረጉ መሆኑን፣ ችግሩ ግን ሰፊ ሆኖ ከዐቅማቸው በላይ እንዳይሆን የሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካላት የነቃ ተሳትፎና ርብርብ እንደሚያስፈልግ በጋዜጣዋ በሰፊው ታትቶ ቀርቧል። ማኅበረ ቅዱሳንም ችግሩን በአጠቃላይ አሠራር ደረጃ እንዲፈታ ማድረግ ላይ ማተኮር እንጂ በቤተ ክርስቲያናችን የሚመለከተው አካል ውሳኔ ሳይሰጥባቸው አንዳንድ የችግሩ መገለጫ የሆኑ ግለሰቦችን በስም እየጠቀሱ በጋዜጣ የማውጣት ዓላማ የለውም።
ሆኖም ግን ይኸው መረጃ በይፋ መውጣቱና ጉዳዩም ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ በየደረጃው ባሉ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያናችን አካላት ሁሉ ዘንድ ትኩረት በማግኘቱ የተደናገጡት የተሐድሶ እምነት አራማጆች የሰርጎ ገብ እንቅስቃሴያቸው እንዳይገታባቸው ማዘናጊያ መፍጠር ነበረባቸው። ለዚህም እንዲረዳቸው ማኅበረ ቅዱሳን በስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ጋዜጣው “መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶቹን በጅምላ በሕፀፀ ሃይማኖት ከሰሰ” በማለት የጋዜጣዋን አንድ እትም አንጠልጥለው ከአንድ ወር በኋላ ወሬውን በአዲስ መልክ በየኮሌጆቹ አካባቢ በስፋት ማናፈስ ጀመሩ። ይህንን ወሬ የሰሙ አንዳንድ እውነተኛ ሰዎችም ሳይቀር ሙሉውን ተከታታይ ጽሑፍ ሳያነቡት ቅሬታ ተሰምቷቸው ቀርበው አነጋግረውናል ፤ አንዳንዶቹም የተወሰነውን ጥቅስ በማንሳት ለምን እንዲህ እንደተገለጸ እንድናብራራላቸው በደብዳቤ የጠየቁንም አሉ። ከእነዚህ ጋር ጥሩ ውይይት አድርገን መግባባት ላይ ደርሰናል። ነገር ግን ይህንን የተሐድሶዎቹን ድብቅ ዐላማ ያልተረዱ አካላት አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ጭምር በማሳሳት የዚህ የስውር እንቅስቃሴያቸው ደጋፊ እንዲሆኑ አድርገዋቸዋል። እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ከየኮሌጆቹ ከሚማሩ ደቀ መዛሙርት መካከል በውድም ሆነ በግድ እንዲፈርሙ ተደርገው ለቅዱስነትዎ የቀረበልዎትን የቅሬታ ጥያቄ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነው ውሳኔ መሆኑ ተዘንግቶና የማኅበረ ቅዱሳን አንድ ተወካይ እንኳ ተገኝቶ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሳይደረግ እንዲህ ዓይነት ብያኔ በርስዎ በቅዱስ አባታችን መሰጠቱ በከፍተኛ ሁኔታ አሳዝኖናል። ጥቂት የተሐድሶ እምነት አራማጆችን “በርቱ፣ ተቃውሟችሁንና ማደናገራችሁን ቀጥሉበት” የሚል የሚመስል መልእክት የያዘ ሐሳብ በቅዱስነትዎ ፊት መሰጠቱም እጅግ አስደንቆናል። እንደ እውነቱ ከሆነ በጋዜጣው ላይ የወጣው አጠቃላይ የጽሑፉ ጭብጥ ሲታይ ቅዱስ ሲኖዶስ ከወሰነው ውሳኔ የተለየ ስምዐ ጽድቅ የጻፈችው ምን አለ? በጥሞና ከታየ የቀረበውን መረጃ ወስዶ በቅዱስ ሲኖዶስ እንደገና የተቋቋመው ኮሚቴ እንዲያጠናው ማድረግ የሚገባ እንጂ ሊያስከስስም ሆነ እንዲህ ዓይነት ደብዳቤ ሊያስጽፍ የሚችል ነገር ለመኖሩ በፍጹም አልታየንም።
ቅዱስ አባታችን ሆይ፡-
የማኅበረ ቅዱሳን አደረጃጀት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን የመንፈሳዊ ትምህርት ሥርዓት ለመከታተል፣ አባላቱ በሙያቸውና በበጎ ፈቃዳቸው ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን የትሩፋት አገልግሎት ለማስተባበር ተብሎ በሀገረ ስብከትና በወረዳ ደረጃ ብቻ መዋቅር የተዘረጋለት መሆኑ ይታወቃል። በአጥቢያ ደረጃ ማኅበሩ ምንም ዓይነት ተቋማዊ አደረጃጀት እንደሌለውም የተገለጠ ነው። ይኽ አደረጃጀቱም በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ የተሰጠው መሆኑ ለሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካላት ግልጽ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የማኅበሩ አባላት በፍጹም ታዛዥነት ቀርበው በቤተ ክርስቲያን መዋቅር እየተመራንና ብፁዓን አበው መመሪያ እየሠጡን እንሥራ ብለው ወደ ቤተ ክርስቲያን ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት መቅረባቸው የሚያስመሰግን እንጂ የሚያስወቅስ አልነበረም።
በቤተ ክርስቲያናችን የአገልግሎት ማኅበር ሲቋቋም ማኅበረ ቅዱሳን የመጀመሪያው አይደለም። ቤተ ክርስቲያን እውቅና ሰጥታቸው የተቋቋሙ፣ የራሳቸው ጠቅላላ ጉባኤ ፣ የራሳቸው ውስጠ ደንብ ፣ የራሳቸው አመራር ያላቸው ብዙ ማኅበራት በቤተ ክርስቲያናችን ነበሩ፤ አሁንም አሉ። ሆኖም ግን በእንዲህ ዓይነት መንገድ የተቋቋሙትና የቤተ ክርስቲያን የቅርብ ክትትል ያልተለያቸው ማኅበራት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ሲጠቅሙ እንጂ ጉዳት ሲያደርሱ ታይቶ አይታወቅም። በርግጥ ቤተ ክርስቲያን የማታውቀውና በቤተ ክርስቲያንም ሥርዓት የማይመራ ማኅበር ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ሊሆን እንደማይችል ግልጽ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለእምነታቸው ቀናዕያን የሆኑ አንዳንድ ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ተሰባስበው ሃይማኖታቸውን ለመማር መነሳሳታቸው፣ በተማሩትም ትምህርት መሠረት ስለወንጌል መስፋፋት እገዛ ማድረግና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት መጀመራቸው እንዳሻቸው መሆን ለለመዱት ተሐድሶዎች እና ጥቅመኞች ነገሩ ስላላማራቸው ‹‹ማኅበራት በሌላ ቦታ እንጂ በቤተ ክርስቲያን አመራር ሥር መዋቀራቸው ቀኖና የጣሰ ነው›› የሚል ሀሳብ ይዘው ብቅ አሉ። ይህ አባባል እንደ እውነታ ተወስዶ በእርስዎ ደብዳቤም መጻፉ ቅር የሚያሰኝ ነው። ለቤተ ክርስቲያናቸው ቀናዒ ሆነው የድርሻቸውን ለመወጣት የሚደራጁ ማኅበራት ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሳካት እስከሆነ ድረስ ማኅበረ ቅዱሳን ስለነዚህ ማኅበራት መደራጀት በጎ አመለካከት ቢኖረውም ማኅበረ ቅዱሳን ከራሱ ውጪ ለየትኛውም ማኅበር መቋቋምም ሆነ መክሰም ኃላፊነት የለበትም።
ማኅበረ ቅዱሳን ከቀድሞ ጀምሮ የዓመት ዕቅዱንና በየስድስት ወሩ ደግሞ የአፈጻጸም ሪፖርቱን ተጠሪ ለሆነለት አካል በጽሑፍ ሲያስገባ ቆይቷል። እንዲሁም የፋይናንስ (የገቢና የወጪ) አሠራሩን ዘመናዊ በሆነ መንገድ በመመዝገብ ገለልተኛ በሆኑና በመንግሥት በተፈቀደላቸው የውጭ ኦዲተሮች ጭምር በየዓመቱ እያስመረመረ ሪፖርቱን ለሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያናችን አካላት እያቀረበ መጓዙ ለማንም ግልጽ ነው። በ2007 ዓ.ም የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ለቤተ ክርስቲያን ቁጥጥር የተሻለ እንዲሆን በቤተ ክርስቲያን ሥር የተቋቋሙ ማኅበራት ሁሉ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተፈቅዶ በሚሰጣቸው የገቢና የወጪ ደረሰኝ እንዲጠቀሙ በተወሰነው መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን የዚህ ውሳኔ አፈጻጸም ፋና ወጊ በመሆን ይህንኑ ካርኒ አሳትሞ መጠቀም መጀመሩ ይታወቃል። ይህንኑም በያዝነው ዓመት በቀረበው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዓመታዊ ሪፖርት ላይ የቁጥጥር መምሪያውም ማረጋገጡን በግልጽ መስክሯል። ማኅበሩ የአገልግሎትና የፈቃድ ማኅበር እንደመሆኑ አባላቱ እንደየገቢያቸው መጠን የአባልነት አስተዋጽኦ ይከፍላሉ። የማኅበሩም ዋናውና ቋሚው የገቢ ምንጭ ይኸው በመሆኑ ማንኛውም የማኅበሩ የሥራ ማስኬጃ የሚሸፈነው በአባላቱ መዋጮ ነው። የማኅበሩ አመራር አባላትም አገልግሎታቸው የበጎ ፈቃድ በመሆኑ ጊዜአቸውን መስዋዕት አድርገው ከመስጠታቸው በተጨማሪ ለትራንስፖርትም ሆነ ሌሎች ወጫአቸውን ሁሉ የሚሸፍኑት ከኪሳቸው አውጥተው ነው። እንዲያውም ብዙ ጊዜ ለሥራ ማስኬጃ የሚሆን ገንዘብ ሲያነስ ተጨማሪ መዋጮ እንዲያዋጡ ኃላፊነት ይኖርባቸዋል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ማኅበሩ በተለየ ሁኔታ ገንዘብ እየሰበሰበ ለማይታወቅ አገልግሎት ያውላል ተብሎ መገለጹ ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላ ከመሆኑም በላይ ከአንድ ቅዱስ አባት የማይጠበቅ በመሆኑ በእጅጉ ያሳዝናል።
ማኅበሩ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ በግልጽ በተፈቀደለት መሠረት አባላቱ ሙያቸውንና ዕውቀታቸውን አስተባብረው ገዳማትን በልማት ራሳቸውን እንዲችሉና የአብነት ትምህርት ቤቶች በደጋፊ ማጣት የትምህርት አሰጣጣቸው እንዳይስተጓጎልና እንዳይበተኑ ለማድረግ ፕሮጀክት ቀርፀው ለቤተ ክርስቲያናችን አባላት ለሆኑ በጎ አድራጊዎች በማኅበሩ በኩል ያቀርባሉ። ለፕሮጅክቱ የሚሆን ገንዘብም ሲገኝ ማኅበሩ በሥራ ላይ አውሎ ለሚመለከተው አካል (ለገዳማቱ ወይም ለአብነት ትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች) ያስረክባል። ይህም የሚፈጸመው በቅድሚያ በገዳማቱ በደብዳቤ ሲጠየቅ ወይም በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወይም በሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ሲታዘዝ (ሲጠየቅ) ነው። የእነዚህ ፕሮጀክቶች አፈጻጸማቸውንም ሆነ የፋይናንስ አወጣጣቸውን የሚያሳየውን ሪፖርት በየጊዜው እየተዘጋጀ ገንዘቡን ላዋጡት ምእመናን (ወይም ማኅበራት) እንዲሁም ፕሮጀክቱ ለሚተገበርላቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት የሚቀርብላቸው ሲሆን ይህም በየዓመቱ በውጭ ኦዲተሮች እየተመረመረ ሪፖርቱ ለሚመለከታቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አካላት እየቀረበ ይገኛል። በመሆኑም አገልግሎቱ የየሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ ክትትል አይለየውም። እንግዲህ በዚህ አሠራር መጓዝ የትኛውን የቤተ ክርስቲያን ቀኖና እንደሚጥስ ለእኛ አልገባንም። እንዲሁም “ከቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን አመራር አይቀበልም፣ አባቶችን ይዳፈራል” ተብሎ በእርስዎ ደብዳቤ መገለጹ አግባብነት አለው ብለን አናምንም።
የማኅበሩ አባላት በአብዛኛው ወጣቶች የሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን አማንያን ናቸው። ከነርሱ መካከልም የመንፈሳዊ አገልግሎት ዝንባሌ ያላቸው የአብነት ትምህርቱን ከትምህርታቸው ጎን ለጎን እየተማሩ፣ በየሊቃነ ጳጳሳቱ እየተፈተሹና መሥፈርቱን እያሟሉ ክህነት ይቀበላሉ። ቅዱስ አባታችን እርስዎም በአሜሪካ በነበሩ ጊዜ በዚሁ መንገድ ለአንዳንዶቹ ክህነት መስጠትዎን አይዘነጉትም። ይህ ደግሞ በሁሉም ብፁዓአን አባቶች የታወቀ ጉዳይ ሆኖ ሳለ በደብዳቤዎ ላይ “ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጪ … ለአባላቱ በጅምላ ክህነት እያሰጠ …” ብለው መግለጽዎ በምን ምክንያት እንደሆነ ግልጽ አይደለም። መቼም ክህነት የሚሰጠው በእናንተ በብፁዓን አባቶች እንጂ በሌላ አካል እንዳልሆነ ይታወቃል። ታዲያ በዚህ ጉዳይ ቀኖና ተጥሶስ ከሆነ የጣሰው ማን ነው ለማለት ነው; ምናልባት ካሁን ቀደም ብፁዓን አባቶችን ለማንቋሸሽ ሲባል አንዳንድ ሰዎች በየመድረኩ ሲናገሩት የነበረውን ድጋፍ ለመስጠት ታስቦ ካልሆነ በስተቀር ማኅበረ ቅዱሳን የሚከሰስበት አንዳች ምክንያት የለውም። ደግሞም አሁን ባለው ሁኔታ የዘመናዊውን ትምህርት መስፋፋት ተከትሎ ብዙ ብሩኅ አእምሮ ያላቸው ወጣቶች ከአብነት ትምህርቱና ከቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት ተለይተው እንዳይቀሩ መሥራት የቤተ ክርስቲያናችን ድርሻ ነው። በአሁኑ ሰዓትም በርከት ያሉ የአብነት ትምህርት የተማሩና በትምህርቱም የገፉ ወጣቶች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየገቡ በመሆኑ ገና ብዙ አብነቱን እና የአስኳላውን ትምህርት ያጣመሩ ምሁራን ቤተ ክርስቲያናችን ይኖሯታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ይህም አርቆ ላሰበ ሰው ለቤተ ክርስቲያን አንድ ሰፊ የአገልግሎት አቅጣጫ ነው።
በውጭ ሀገር ስላለው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትም ምናልባት ያለፉት ሦስት ዓመታት አስረስተዎት ካልሆነ በቀር የማኅበሩ አባላት ስለቤተ ክርስቲያን አንድነት በሚያደርጉት ከፍተኛ ተጋድሎ እንደ ገና ዳቦ ከሁሉም አቅጣጫ እሳት እየነደደባቸው የሚታገሉ መሆኑን በየጊዜው ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከውጪ ሀገር በመጡ ቁጥር ይመሰክሩት የነበረ ነው። በቅርቡም በአሜሪካ ሄደው በነበረ ጊዜ የተጋበዙባቸው አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እዚያ ደረጃ እንደደረሱና ማን መሥዋዕትነት እንደከፈለባቸው፣ አሁንም ቢሆን በቅዱስነትዎ ጉዞ ወቅት ማን እንዳስከበርዎ ልቡናዎ ያውቀዋል። ከዚህም በላይ በሀገር ውስጥ ለተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶች በሚዘዋወሩበት ጊዜ በየቦታው በደመቁ ሰልፎች ተሰልፈው እየዘመሩ በማጀብ የሚቀበሉዎ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያውቁና አባቶቻቸውን እንዲያከብሩ ስላስተማራቸው መሆኑ ግልጽ ነው።
ቅዱስ አባታችን ሆይ፡-
በተጨማሪም በደብዳቤዎ ላይ አንዱ ዋና ወንጀል ተደርጎ የተገለጸው «በሌለው ሥልጣን የጾም አዋጅን እስከማወጅ ደርሷል” የሚል ይገኝበታል። በአጭር ቋንቋ ለመግለጽ ማኅበረ ቅዱሳን ያወጀው ጾም የለም። ጾም በቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚታወጅም ጠንቅቆ ያውቃል፤ ያስተምራልም። ለጾም አድሉ ብላ በምታስተምር ቤተ ክርስቲያናችን ተጨማሪ ጾም ታውጃላችሁ ተብሎ የቀረበብን ክስ በቤተ ክርስቲያን ጾም በዝቷልና ካልተቀነሰ እያሉ በከንቱ የሚደክሙትን ተሐድሶዎች ሀሳብ ለምን አትደግፉም የሚል ያስመስለዋል።
በአጠቃላይ ካሁን ቀደም በተለያዩ የተሐድሶ እምነት አራማጆች በሚያዘጋጇቸውና በሚመሯቸው ድረ-ገጾችና ብሎጎች ላይ በተደጋጋሚ ማኅበረ ቅዱሳንን ለመክሰስ ሲያወጧቸው የነበሩትና አንድም የእውነት ጠብታ እንኳ የሌላቸውን ሀሳቦች በርስዎ ደብዳቤ በአጭር በአጭሩ ተጠቅሰው ማየታችን እጅግ አሳዝኖናል፤ አስገርሞናል። እነርሱ ሁል ጊዜም እውነት መናገር ልማዳቸው እንዳልሆነ በሁሉም ዘንድ ስለሚታወቅ ንቀን መልስ ሳንሰጣቸው ቆይተናል። በርስዎ ደረጃ ይህ እንደገና ሲስተጋባ ግን ዝም ማለቱ ተገቢ ስላልሆነ ነው ይህን ምላሽ ለመስጠት የተገደድነው። ይህ ለመንፈሳውያን ኮሌጆቹ በአድራሻ የተጻፈላቸው ደብዳቤም ዓላማው በእውነት ግልጽ አይደለም። ስለዚህ አሁንም ቢሆን እውነታውን ለማወቅና ለሚነሱ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት የጉዳዩን ባለቤቶች ጠርቶ ፊት ለፊት በማነጋገር እና በመካከር መፍታት እንጂ አንድ ጩኸት በተሰማ ቁጥር ደብዳቤ መጻፉ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚበጅ አይመስለንም። በርስዎ ስም የሚጻፉ ደብዳቤዎችም ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉና ክብርዋን የሚያስጠብቁ፣ በሁሉም አካላት ተአማኒነት ኖሯቸው ትኩረት ሰጥተው የሚመለከቷቸው እንዲሆኑ ቢደረግ እጅግ ደስ ይለናል።
ክቡራን ንዑዳን ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ፡-
ማኅበረ ቅዱሳን በናንተ ቡራኬና መመሪያ ሰጪነት በብዙ ገዳማውያን አባቶቻችን ጸሎት እና በምእመናን ከፍተኛ ድጋፍ ቤተ ክርስቲያንን በአገልግሎቱ ለመደገፍ ላለፉት 23 ዓመታት የዐቅሙን ያህል ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። የነበረው አገልግሎት አልጋ በአልጋ ባይሆንም በተለይ በአሁኑ ወቅት ያለው የቤተ ክርስቲያናችን ሁኔታ እያሰጋን መጥቷል። የተሐድሶ መናፍቃኑ በማን አለብኝነት የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርተ ሃይማኖት እና ቀኖና በሚጻረር መልኩ የእምነት መግለጫቸውን በይፋ በመጽሐፍ መልክ አሳትመው እያሰራጩ ባሉበት ወቅት፣ ጥቅመኝነት በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ ክብር ተሰጥቶት በይፋ ዝርፊያ በሚፈጸምበት እና አገልጋዮች ካህናት በየቦታው በሚበደሉበት በዚህ ጊዜ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ርዕሰ መንበር ደረጃ በቅዱስነታቸው እንዲህ ዓይነት ለቤተ ክርስቲያን የማይበጁ ደብዳቤዎች እየተፈረሙ ሲወጡ ማየት እጅግ ከባድ አደጋ እንዳለው ይሰማናል። ምንም እንኳ ማኅበሩን አጥጋቢ ሥራ ሠርቷል ወይም አልሠራም፣ ስሕተቶችንም ይፈጽማል አይፈጽምም ብሎ መከራከር መውቀስና በሀሳቦቹም መወያየት፣ አስፈላጊም ሲሆን መገሠጽ እየተቻለ ከአንድ ቅዱስ አባት ቀርቶ ከየትኛውም የተቋም ሓላፊ በማይጠበቁና የሰዎችን ስሜት በሚያስቆጡ ቃላት መሸንቆጥ በእጅጉ የሚያሳዝን ሆኖ ተሰምቶናል። ለአብነት ያህልም ማኅበሩን ከሳሾቹ እንኳን በማይሉት መንገድ “የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየፈጸመ ይገኛል” የሚለው ሊጠቀስ ይችላል። ይህ አገላለጽ ለማኅበሩ አመራርና አባላት ቀርቶ ደብዳቤውን በየሚዲያዎቹ ያዩት ሁሉ ትዕግሥትን የሚፈትን እንደሆነ እየገለጹልን ይገኛሉ። የጥቅምቱን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተከትሎም ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያናችንን ስብከተ ወንጌል ለዓለም የሚያሰራጭበት የቴሌቪዥን መርሐ ግብር ሲቋረጥ ለሚመለከተው የቤተ ክርስቲያናችን አካል ብናመለክትም በቅዱስነታቸው ደብዳቤ እንዲቆም መደረጉም ሌላው አሳዛኝ ተግባር ነው። ከዚህም በላይ በዘመናችን ባለው ቴክኖሎጂ ምክንያት የትኛውም መረጃ ወይም ጉዳይ በሚዲያ ለሕዝቡ በከፍተኛ ፍጥነት የሚዳረስ መሆኑ አይዘነጋም። ይህንም ተከትሎ ብዙ ዓይነት ስሜቶችና አጸፋዎች ከምእመናን ይደመጣሉ። በመሆኑም በወቅቱ አግባብነቱን የጠበቀ ዕርምትና ለወደፊቱም መተማመኛ ያለው አሠራር ተግባራዊ እስካልሆነ ድረስ የሚከተለው አደጋ ትልቅነት ይታየናል።
ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ በጉዳዩ ላይ በአንክሮ እንዲወያይበት እና እርምት እንዲሠጥበት ለእኛም ከዚሁ አንፃር አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን እንድታደርጉልን ከእግረ መስቀላችሁ ሥር ወድቀን በፍጹም ትሕትና እንጠይቃለን።
የቅዱስነትዎ ቡራኬ ይድረሰን
የብፁዓን አባቶቻችን የጸሎታችሁ ረድኤት አትለየን
ግልባጭ፡-
Ø ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት
Ø ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
Ø ለኢ.ፊ.ዲ.ሪ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጽ/ቤት
Ø ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ጽ/ቤት
Ø ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
Ø ለብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት
Ø ለውስጥ ደኅንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ
Ø ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ
Ø ለትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
Ø ለትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን
Ø ለትግራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ጽ/ቤት
መቐሌ
Ø በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለሚመሩት አህጉረ ስብከት
በያሉበት
Ø ለማኅበረ ቅዱሳን ለሁሉም ማእከላት
በያሉበት
Ø ለኦዲትና ኢንስፔክሽን አገልግሎት
Ø ለዋና ጸሐፊ ቢሮ
ማኅበረ ቅዱሳን
ቀሲስ ዶ/ር ሰሙ ምትኩ
የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ
ፊርማና ማህተም አለው¾

ሕወሓት የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለኦሮሞ ሕዝብ ትግል ድጋፉን እየሰጠ ነው – ሰራዊቱ ድጋፉን ያሳየባቸው ፎቶዎች እየተለቀቁ ነው

ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ ሕወሓት ከላይ የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለኦሮሞ ህዝብ ትግል ድጋፋቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ:: በሠራዊቱ ውስጥ በተለይ የኦሮሞና የአማራ ተወላጅ የሆኑ የጦር ሰራዊቱ አባላት አንድነት በመፍጠር ላይ እንደሚገኙ ከመከላከያ ምንጮች ያገኘናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ::
በቅርቡ ሕብር ራድዮ ላይ ቀርቦ ቃለምልልስ የሰጠው ጀዋር መሐመድ “በሰራዊቱ ውስጥ የማደራጀት ሥራ ሰርተን ጨርሰናል:: በኦህ ዴድ ውስጥም እንዲሁም:: ሠራዊቱ መተኮስ ባለበት ወቅት ወደ ስር ዓቱ መተኮስ የሚችልበትን ሥራ ሰርተናል” ማለቱ የሚታወስ ሲሆን… ዛሬ በሶሻል ሚድያዎች እየተለቀቁ ያሉት ፎቶዎች እንደሚያሳዩትም የተለያዩ የሠራዊቱ አባላት እጃቸውን ወደላይ አድርገው በማጣመር ለኦሮሞዎቹ ትግል ያላቸውን አጋርነት በመግለጽ ላይ ናቸው::
wetader 2
ሕወሓት የሚመራው መንግስት በግድ ሕዝቡ እንዲቀበለው እያስገደደው የሚገኘውን ባንዲራም እየቀደዱ የሚያሳዩ ፎቶዎች ተለቀዋል::
ከመከላከያ ያገኘናቸው መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአሁኑ ወቅት ውስጥ ውስጡን የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች የሆኑ ወታደሮች በ ስር ዓቱ ግፍ በመንገብገብ የተደራጁ ሲሆን የሕወሃት ባለስልናት እርስ በ እርሳቸው እንዲከፋፈሉ ያዘጋጁትን ወጥመዶች እየበጣተሱ እንደሚገኙም ታውቋል::
wetader
በተለይ የኦሮሞና የአማራ ወታደሮች በአንድ ላይ ሕብረት መፍጠራቸው ያሰጋው ሕወሃት ሊያስተባብሩ ይችላሉ የሚላቸውን ወታደሮች በግድ የዓመት ፈቃድ እንዲወጡ እንዲሁም እያሰረም እየገመገመም እንደሚገኝ የዘ-ሀበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

የሀገር አድን ጥሪ ለወጣቱ!(ከአርበኞች ግንቦት7 ወጣቶች መምርያ )

ኞ ፣2 ፌብሩወሪ 2016
12042873_868355303254893_5731700769108826326_nወጣቶች በሃገራችን ላይ የተጫነብን የወያኔ የመርገምት አገዛዝ ያጎሳቆለን፤ በኑሮ የተበደልንና በሰላም ለመኖር ያልታደልን ፍጡሮች ብንሆንም ህዝባችን ነጻነቱን ሲቀማ፣ መብቱ ሲደፈር፣ ክብሩ ሲዋረድ ከዳር ቁመን የምንመለከትበት አንዳች ምክንያት ሊኖረን አይገባም። ወቅቱ ለነፃነታችንና ለመብታችን ባላንጣ የሆነውን አምባገነን የወያኔን ስርዓት ፊት ለፊት ተጋፍጠን፣ በትግላችን ደቁስን ማንነታችንን የምናስመስክርበት ወቅት እንጂ በፍርሃትና በዝምታ ተውጠን ወደኋላ የምንልበት ስዓት አይደለም። ደግሞም እኛ ወጣቶች ለመብት እና ነፃነታችን ተፈጥሮ የለገሰችንን እምቅ ኃይልና ጉልበት ተጠቅመን በቁርጠኝነት ተነስተን ካልታገልን የሥርዓቱን አምባገነናዊ የጭቆና አገዛዝ በፍርሃትና በዝምታ እንደተቀበልን ተደርጎ መወስዱ የማይቀር ነው።
ከምንግዜውም በላይ እኛ ወጣቶችን ዛሬ ሁለት አበይት ጉዳዮች በጉልህ ያሳስቡናል፤ ሊያሳስቡንም ይገባል። እነዚህም ሃገራችን ያለችበት አሳሳቢ ሁኔታና የኛ የተተኪው ትውልድ የወደፊት ተስፋ ምን ሊሆን ይችላል? የሚሉት ናችው። በቀደመው ጊዜ በሃገራችን የተፈራረቁት አምባገነን ገዥዎች ለወጣቱ ተስፋና የተሻለ ነገር ከመስጠት ይልቅ በጠላትነት ፈርጀው በሽብር እየገደሉና ጥቃት እየፈጸሙበት ሲያሳድዱት ኖረዋል። የወጣቱ ሰቆቃ አሁን በወያኔ ዘመን ደግሞ እጅግ በጣም በከፋ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል።
የወያኔ መሪዎች ለኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ማዕከላዊን፡ ቃሊቲን፤ ሽዋሮቢትን፣ ዝዋይን እና የመሳስሉ የሰቆቃ እስር ቤቶችን ሲያሰፉ እንጂ የሥልጠናና የምርምር ተቋም ሲያድሱና ሲገነቡ ለማየት አልታደልንም። የሚገነቡ የትምህርት ተቋማትም ለሥርዓቱ የእድሜ ማራዘሚያ እንጂ የእውቀት ማስጨበጫ ተቋም እንዳልሆኑ ተግባራቸውንና ውጤታቸውን መመልከት ይቻላል። በአደባባይ ያለፍትህ የሚገደለው ወጣት ባንክ ሲዘርፍ ተገኘ፣ ወንጀል ሲሰራ ተያዘ የሚሉ የሀሰት ምክንያቶች እየተለጠፉበት ያለኃጢአቱ የሀሰት ስም በመቀባት ዳግም ይገሉታል።
የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ከሚፈራበት የትምህርት ተቋም ድረስ በመግባት የአማራ ህንጻ፣ የኦሮሞ ህንጻ፣ የትግሬ ህንጻ…ወዘተ እያሉ የትምህርት ሥርዓቱን ከጠባቡ የፓለቲካ ግባቸው ጋር በማያያዝ በነገ ተስፋችን ላይ ዘምተው የልዩነት ግድግዳ ባሳፋሪ መልክ እየገነቡ ቀጥለዋል። አላማው ደግሞ በጎስኝነት በሽታ ተውጠን ከእህቶቻችንና ከወንድሞቻችን ጋር እየተባላንና እየተገዳደልን የምንኖርበት ሲኦል ለመፍጠር መሆኑ አያጠያይቅም። በዚህም ሳቢያ ብሔራዊ ሰሜታችን እየደበዘዘ ሄዷል። ብሔራዊ ሰሜት ከሌለን ደግሞ አገር አለን ማለት ጨርሶ የሚታስብ እንደማይሆን ግልጽ ነው።
በነገራችን ላይ ዛሬም ድረስ ወያኔዎች ለእድገትና ለልማት መዘጋጀታችውን እየደሰኮሩ ህዝብን በማታለል የስልጣን ዘመናቸውን ለማርዘም መውተርተራቸውን አላቆሙም። በየጊዜው ኢትዮጵያ ተመነደገች፤ ልማቱ ተፋጥኗል እያሉ በሃሰት ህዝብን ለማወናበድ ይሞክራሉ።እውነታው ግን በእጅጉ ተቃራኒ መሆኑን የህዝቡን የኑሮ ሁኔታን በመመልከት መረዳት ይቻላል። ዛሬ የፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝ በፈጠረው የተወሳሰበ ችግር በሀገሪቱ የወጣት ሥራ ፈትና ተጧሪ ሞልቶና ተትረፍርፎ በሚታይበት፤ ሥራ የማግኘት እድል በፓለቲካ ታማኝነት ብቻ በሆነባት ሃገርና ወያኔ የፓለቲካ ሥልጣኑንና ወታደራዊ ኃይሉን ተጠቅሞ የሀገሪቷን ሀብት እያጋበስ በሚዘርፍበት ሁኔታ ላይ ቆመን ልማትና እድገት ማለት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ተራ ማጭበርበሪያና ዲስኩር ካልሆኑ በስተቀር ፈጽሞ ትርጉም የሚሰጥ አይደለም።
ለነገሩ ወያኔ ከመጀመሪያው ጀምሮ ያዘጋጀልን ቃሊቲ፤ ማዕከላዊ፤ ሁርሶን፤ ሽዋሮቢትንና የመሳሰሉትን የማሰቃያ ማጎሪያዎች መሆኑን የተረዳን ስለሆነ በዚህ የምንደናገር አይደለም። ለዚህም ነው በአሁኑ ወቅት እኛ ወጣቶች ተሰባስበንና ተደራጅተን ከመታገል ውጪ ሌላ ምርጫ የለንም ብለን በድፍረት የምንናገረው።
አምባገነንነት ስርዓት ካልተገታ የአገር ሰላም ሆነ የህዝብ ህልውና እና አንድነት ዋስትና አያገኝም። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሥልጣን የጨበጡት ወንበዴ ግለሰቦች የኢትዮጵያ ህዝብን ሀብት እየተቀራመቱ ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉ፣ ህዝቡን የሚገሉ፤ የሚረግጡና የሚበድሉ በተለይ ደግሞ ለባእድ ጥቅም የተገዙ ናቸው። እነዚህ ግለስቦች ብሔራዊ ስሜታችውን አሽቀንጥረው የጣሉ፤ የራሳችውን ባህል፤ ወግ፤ ታሪክና ሕዝብ አምርረው የሚጠሉ ከራሳቸውና ሥልጣን ላይ ካስቀመጧቸው መንግሥታት ጥቅም ውጪ ሌላ ምንም የማይታያቸው ናችው።
ታዲያ የሃገራችን ህልውና ከመቼውም በላይ ለከፋ አደጋ ተጋልጦ ባለበት በአሁኑ ወቅት በተለይ የእኛ የወጣቶች ግዴታና ድርሻ ምን መሆን አለበት ብለን ራሳችንን መጠየቅና ብሎም መልስ ለመስጠት መዘጋጀት ሀገራዊ ግዴታንና ኃላፊነትን ለመወጣት የመጀመሪያው እርምጃ መሆን ይኖርበታል።
ጭቆናንና በደልን በመታገል ረገድ ደግሞ የቀደምት የታላላቅ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን አኩሪ ገድል ለዛሬው ትግላችን ትልቅ የትምህርት ማእከል ሆኖ ያገለግለናል። ሀገራችን ከኋላቀር ሥርዓትና ከብልሹ አገዛዝ ተላቅቃ፤ ድህነትን አሸንቀጥራ ጥላ በልማት ጎዳና እንድትራመድ፤ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን እንዲሆን፤ ማህበራዊ ፍትህ እንዲስፍን ባጠቃላይም ተጨባጭና ዘላቂ ለውጥ በሃገራችን እንዲመጣ ጽኑ እምነት ሰንቀው ለሕዝባዊ ትግሉ ሕይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ሲታገሉ የነበሩ ጀግና ወጣቶች እንዳሉ ታሪክ ያስገነዝበናል።
ዛሬም ጭምር ግንባራችውን ሳያጥፉ መስዋእትነትን በመክፈል እያስመስከሩ ያሉ መኖራቸውን ስንመለከት ጀግና የሚያፈራው ጀግናን ነውና እኛም ወጣቶች አንገታችንን ቀና አድርገን ዛሬም እንደ ትናንቱ ለሃገራችንና ለህዝባችን ነፃነት መታገል ብሔራዊ ግዳጃችን ብቻም ሳይሆን ታላቅ ክብርም ጭምር መሆኑን ተገንዝበን ለሞት ሽረቱ ትግል በቁርጠኝነት መነሳት ይኖርብናል። ከፊታችን ለሚጠብቀንና ሃገራችን እያሰማች ላለው የሀገር አድን ጥሪ መልስ ለመስጠት እኛ የኢትዮጵያ ወጣቶች ከሃገር ቤት እስከ ውጪው አለም ድረስ የተቀናጀና የተቀነባበረ ንቅናቄ በመፍጠር ምላሽ ልንሰጥ ይገባል።
በኅብረትና በጽናት ከታገልን ደግሞ የወያኔን የሰቆቃ አገዛዝ አሰወግደን የሕዝባችንን ሮሮ የማናስቆምበት እና ተጨባጭ ለውጥ በሀገራችን ለማምጣት የማያስችለን አንዳች ምድራዊ ሃይል እንደማይኖር በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል። ዛሬ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንዳለ ብልጭ ብልጭ እንደሚል ኮኮብ ብንመስልም በርግጠኝነት ነገ ከፀሐይ ደምቀን ከአሽዋ በርከትን የምንታይበት ጊዜ ይመጣል፤ እየመጣም ነው።
በመጨረሻም የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ወጣቱን ትውልድ መብቱንና የዜግነት ክብሩን ለመጎናጸፍ እንዲችል ብሎም የሀገር እና የወገን ነፃነትን ለማምጣት ወያኔን ታግሎ ማሸነፍና ከስልጣኑ ማውረድ ግድ ነው ብሎ በጽኑ ያምናል። በአገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም ተበታትኖ የሚገኘውን ወጣት በአገሩ ተከብሮ እንዲኖር የተለየና የተቀደሰ አማራጭ አለው። ይኸውም እየተደራጁ መታገል፣ እየታገሉ መደራጀት ነው ብሎ ንቅናቄያችን ያምናል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የነደፈውን ጊዜ የማይሽረውን ሁለገብ የመታገያ ስልትና አላማን ከግብ ለማድረስ ትግልን በጽናት መቀጠል የሚለው መርሁ ሲሆን ተደራጅቶ በጽናት መታገልን በተግባር ለማዋል ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወጣት ንቅናቄውን እንዲቀላቀል ጥሪ ያደርጋል። ተደራጅቶ ሊያጠፋን የተነሳን ጠላት በተደራጀ ሃይል ማንበርከክና ከስር መሰረቱ ማስወገድ ይቻላልና። ስለዚህ የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ በአረመኔው የወያኔ አገዛዝ ላይ የሚካሄደውን ትግል አጠናክሮ በመቀጠል በአገር ውስጥ ወጣቱን በህቡዕ ከማደራጀት ጀምሮ በውጭው ዓለም በየአህጉሩ በተዋቀሩ የንቅናቄው መዋቅሮች አማካኝነት ወጣቱን አደራጅቶ በማንቀሳቀስ አስፈሪ የሆነ የነፃነት ማዕበል ፈጥሯል። አሁንም የንቅናቄውን ዓላማ የሚደግፉና በነፃነት ትግሉ ለመሳተፍ የቆረጡ ወጣቶች እንዲቀላቀሉ የአርበኞች ግንቦት7 ወጣቶች መምርያ በድጋሚ ሃገራዊ ጥሪ ያቀርባል!
ፈሪዎችንና ባንዳዎችን ወደ ጎን በመተው እውነተኛ ታጋዮችን ይዘን ትግላችንን እንቀጥላለን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

ማኅበረ ቅዱሳን ለፓትርያርኩ ምላሽ ሰጠ | መልካም ሞላ

በቅርቡ ማኅበሩን አስመልክቶ በቅዱስ ፓትሪያሪኩ የተጻፈው መመሪያ/ ደብዳቤ አሳዝኖናል የደብዳቤው ዓላማ እና ተልእኮ ምን እንደሆነ መገመት አስቸግሮናል ያለው ማኅበረ ቅዱሳን፤ የተከሰስንበት ጉዳይ መሰረት የሌለው እና እኛን የማይወክለን ነው ሲል ለቀረበበት ክስ በቁጥር ማቅሥአመ/239/02/ለ/08 በቀን 24/05/2008 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ጋዜጠኛ መልካምሰላም ሞላ
ጋዜጠኛ መልካምሰላም ሞላ

‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ጥቅሙና ጉዳቱ በሚገባ ሳይጠና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር የሚያስከትለው የሃይማኖት እና የስርዓት ተፋልሶ ሳይፈሽ ራሱ አርቅቆ ባጸደቀው ደንብ በቅ/ሲኖዶስ የተፈቀደልኝ ህጋዊ ማኅበር ነኝ ይላል …›› ለሚለው የፓትሪያርኩ ክስ፤ ማህበሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ስር ህጋዊ በሆነ ስርዓት በቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ እውቅናና ፈቃድ ተዋቅሮ የሚመራበት ደንብ በመጀመሪያ በማደራጃ መምሪያው በኩል በኋላም በ1992 ዓ/ም በቅዱስ ፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በኮሚቴ ታይቶና ተመርምሮ የጸደቀለት እንዲሁም በ1994 በቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ደረጃ ቀርቦ የታየ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እና ሊቃነ ጳጳሳት የተሳተፉበት ለ 6 ወር የፈጀ ጥናት የተደረገበት የማኅበሩ ደንብ በምልዓተ ጉባኤው የፀደቀና ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት የፈረሙበት መሆኑን ጠቅሰው ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡ በ2004 ዓ/ም ከማኅበሩ አገልግሎት መስፋት ጋር ተያይዞ ከማደረጃ መምሪያው ጋር በነበረ አለመግባባት ለጊዜው ማኅበሩ ተጠሪነቱ ለብጹዕ ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሆን እና ማኅበሩን የበለጠ እንዲሰራ የሚያደርገው ደንብ ማሻሻያ እንዲያደርግ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራውን አጠናቆ ቢጨርስም ፓትርያርኩ በተደጋጋሚ አልቀበልም በማለታቸው መዘግየቱን በደብዳቤ ተገልጧል፡፡
abune matias
ቀደም ሲል በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰየመው ኮሚቴን ጥናት አልቀበለም በማለት ሌላ የማኅበረ ቅዱሳን ተወካይ የሌለበት ኮሚቴ እንግዳ በሆነ መልኩ ቢያቋቁሙም ለቤተ ክርስቲያን ካለን አመኔታ አኳያ ይሁን ብለን ብንቀበልም ‹‹ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ደንብ ማርቀቅ ስራ ሆን ብሎ በማሰናከል ያለ ደንብ እየሰራ ይገኛል›› የሚለው ወቀሳ እንዳስገረመው ማኅበረ ቅዱሳን ገልጧል፡፡ ከስድስት ጊዜ በላይ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ቀርበን ለመወያት ብንሞክርም ፍቃደኛ አልሆኑልንም ሲል ማኅበሩ ቅሬታውን በደብዳቤው አትቷል፡፡
በ2007 ዓ/ም ቅዱስ ሲኖዶስ ተሀድሶን በተመለከተ በቃለ ጉባኤው ‹‹የተሀድሶ የችግር ምንጭ ኮሌጆቹ እንደሆኑ ያመለክታል›› በማለት በኮሌጆች ውስጥ ያለው አሰራር መታየት እና መፈተሸ አለበት የሚል ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ቢሆንም ኮሌጆቹ ላቀረቡት የሀሰት ክስ እኛ ተገኝተን ሳንጠየቅ ውሳኔ ማሳለፍዎ ቅር አሰኝቶናል፤ በበጎ ፍቃድ ቤተ ክርስቲያንን ማገልገላችን የሚያስመሰግን እንጂ የሚያስወቅስ አይደለም ብለዋል፡፡
ማኅበሩ የዓመቱን እቅድና በየስድስት ወሩ የአፈጻጸም ሪፖርት ተጠሪ ለሆነለት አካል ሲያስገባ እንደቆየ እና የገቢ እና የወጭ አሰራሩንም በመንግስት በተፈቀደላቸው የውጭ ኦዲተሮች ጭምር በየዓመቱ እያስመረመረ ሪፖርት ያቀርባል ያለው ደብዳቤው፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተፈቅዶ በሚሰጣቸው ደረሰኝ መጠቀም እንደጀመረ አስረድቷል፡፡ ማኅበሩም በበጎ ፈቃድ የተመሰረተ በመሆኑ የማህበሩ የስራ ማስኬጃ በአባላቱ እንደየገቢያቸው መጠን በሚከፍሉት የአባልነት አስተዋጾ ይሸፈናል፡፡ ተጨማሪም ወጭ ሲኖርም አባላቱ አዋጥተው እንደሚሸፍኑ ቢታወቅም ‹‹ማኅበሩ በማይታወቅ ሁኔታ ገንዘብ እየሰበሰበ ለማይታወቅ አገልግሎት ያውላል›› ተብሎ መገለጹ የውሸት ውንጀላ ከመሆኑም በላይ ከአንድ ቅዱስ አባት የማይጠበቅ ተግባር ነው ሲል በደብዳቤው ተገልጧል፡፡ ማኅበሩ ገዳማት ራሳቸውን እንዲችሉ፣ የአብነት ተማሪዎች ድጋፍ አጥተው እንዳይበተኑ ለማድረግ ፕሮጀክት ቀርጾ ግልጽ እና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ለሚመለከተው ክፍል አቅርቦ ስራ ላይ ያውላል፡፡ ስራውም በየሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳሳት የቅርብ ክትትል እንደማይለየው እየታወቀ ‹‹ከቤተ ክርስቲያን አባቶች የሚሰጠውን አመራር አይቀበልም ፤ አባቶችን ይዳፈራል›› ተብሎ መገለጹ አግባብነት አለው ብሎ እንደማያምን ማኅበሩ አስታውቋል፡፡
አብዛኛው የማኅበሩ አባላት ወጣት በመሆናቸው ተምረው መስፈርቱን እያሟሉ ክህነት እንደሚቀበሉ እና እርስዎም አሜሪካ እያሉ ክህነት መስጠትዎ አይዘነጋም ያለው ደብዳው፤ ክህነቱ የሚሰጠው በብጹዓን አባቶች በመሆኑ ቀኖና ቢጣስ እንኳን ማኅበሩ የሚጠየቅበት ምክንያት የለም ሲሉ ‹‹ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ በጅምላ ክህነት እያሰጠ›› በማለት የተገለጸው አግባብነት እንደሌለው አስረድተዋል፡፡
‹‹ባለፉት ሶስት አመታት እረስተውት ካልሆነ በቀር የማኅበሩ አባላት ለቤ/ን አንድነት በሚያደርጉት ከፍተኛ ተጋድሎ እንደ ገና ዳቦ ከሁሉም አቅጣጫ እሳት እየነደደባቸው የሚታገሱ መሆኑን በየጊዜው ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከውጭ ሀገር በመጡ ቁጥር ይመሰክሩ ነበር፡፡ በቅርቡም አሜሪካ ሄደው በነበረ ጊዜ የተጋበዙባቸው አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እዚያ ደረጃ እንደደረሱና ማን መስዋዕትነት እንደከፈለባቸው ፤አሁንም ቢሆን በቅዱስነትዎ ጉዞ ወቅት ማን እንዳስከበርዎ ልቦናዎ ያውቀዋል፡፡ … በሀገር ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ጉዞ ሲያደርጉ በደማቅ ሰልፍ የሚቀበሎት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያውቁና አባቶቻቸውን እንዲያከብሩ ስላስተማራቸው መሆኑ ግልጽ ነው›› ሲል አቡነ ማትያስ ፓትሪያሪክ ከመሆናቸው በፊት ለማኅበሩ ሲያደርጉት የነበረውን እገዛ እና ቀና አስተሳሰብ በማስታወስ አሁንም ማኅበሩ ወጣቶች ላይ እየሰራ ያለውን እንቅስቃሱ ገልጦ ጽፏል፡፡
‹‹በሌለው ስልጣን የጾም አዋጅ እስከማወጅ ደርሷል ›› ለሚለው ውንጀላም ማኅበረ ቅዱሳን እስከዛሬ ያወጀው ጾም የለም ያለ ሲሆን ክሱ ‹በቤተክርስቲያን ጾም በዝቷል ካልተቀነሰ› የሚሉት ተሀድሶዎችን ሀሳብ ለምን አትደግፉም የሚል ይዘት አለው ብሏል፡፡ በተሃድሶ እምነት አራማጆች በሚያዘጋጇቸው እና በሚመሯቸው ድረ-ገፆች እና ብሎጎች ማህበሩን ጥላሸት ለመቀባት ይነሱ የነበሩ ሃሳቦች በእርስዎ ደብዳቤ ማየታችን አሳዝኖናል አስገርሞናልም፡፡ እነሱን ንቀን መልስ ሳንሰጣቸው የቆየን ቢሆንም በእርስዎ ደረጃ ይህ በመነሳቱ ለመመለስ ተገደናል ሲል የገለጠው የማኅበሩ ደብዳቤ አሁንም ተነጋግረን መፍትሄ ማምጣት የተሻለ አካሄድ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
ማኅበሩ አጥጋቢ ስራ ሰርቷል ወይም አልሰራም፤ ስሕተቶችንም ይፈጽማል አይጽምም ብሎ መከራከር መውቀስ እና በሃሳቦም መወያየት አስፈላጊም ሲሆን መገሰጽ እየተቻለ ከአንድ ቅዱስ አባት የማይጠበቅ የሰዎችን ስሜት በሚያስቆጡ ቃላት መሸንቆጠረ በእጅጉ አሳዝኖናል ብለዋል፡፡
ስለዚህ ጉዳዩን ቅዱስ ሲኖዶስ ተመልክቶ ተወያይቶ እርምትና መፍትሄ እንዲሰጥበት እንጠይቃል በማለት የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ቀሲስ ዶክተር ሰሙ ምትኩ ደብዳቤውን በፊርማቸው አረጋግጠዋል፡፡

የወልቃይት የአማራ ብሔር የማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ታስረው ተፈቱ

ጥር 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የታገዱት የወልቃይት የአማራ ብሔር የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና የአካባቢ ሽማግሌዎች ሰኞ ጥር 23 ቀን 2008 ወደ መዲናችን መግባት ችለው ነበር፡፡ የትግራይ ክልል ኮሚቴዎቹና ኅበረተሰቡ በወጡበት ይቅርታ ጠይቀው በቶሎ ካልተመለሱ እርምጃ እንደሚወስድ በትግርኛ ቴሌቪዥን ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ መስጠቱም ይታወሳል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ ቁጥራቸው 22 የሚሆኑ ተወካዮች ለፌደሬሽን ምክር ቤትና ለፌደራል ጉዳዮች ቢሮ አቤቱታቸውን ለማሰማት ከቀኑ 7፡00 ላይ ሃያ ሁለት አካባቢ ከጓደኞቻቸው ተለይተው ሒደው ነበር፡፡ እነዚሁ የኮሚቴ አባላት እስከ ምሽት 2፡00 ከታፈኑ በኋላ ይህን ዜና ለሕዝብ ያሰራጨው የወልቃይት ጠገዴ ሰሜን አርማጭሆ ድምጽ ታስረው መፈታታቸውን ዘግቧል::
ታስረው የነበሩት የወልቃይት የአማራ ብሔር የማንነት አስተባባሪ ኮሚቴዎች:-
1. ኮ/ል ደመቀ
2. አቶ አታላይ ዛፌ
3. አቶ ተሰማ ረታ
4. አቶ ይለፍ በየነ
5. አቶ አደራጀው ዋኘው
6. አቶ አባይ ግርማይ
7. አቶ ሸፈቀ አደም