Monday, 22 February 2016

ነፃ መውጣት እንፈልጋለን አንፈልግም? – ዳዊት ዳባ

ዛሬ እየሰፋ እየገዘፈና ጉልበት እያገኘ የመጣው ህዝባዊ እንቢታ ከአረቡ አገሩ ህዝባዊ አልገዛም ባይነት የጀመረ ይመስለኛል። ያኔ ከዚህ ስርአት በዚህም መንገድ መገላገልም ይቻላል ለካ? የሚለው እሰቦት በአይምሮው ያልዞረ ኢትዬጵያዊ  ነበር ለማለት አይቻልም። የስርአቱም ደጋፊዎችም ቢሆኑ በግልባጩ እንቅልፍ ያጡበት ጉዳይ ነበር። አልገዛም ባይነቱ በኛ አገር ይሄ- ያ ይጎድለዋል። ይህ አደጋ አለው። በዚህ አንመሳሰልም ይሉ የነበሩትም ቢሆን ግምት ውስጥ አስገብተው አስበውበት ስለነበር ነው። ሀላፊነት ወስደው ይሰሩበት የጀመሩ ስብቦች እርግፍ አድርገው ቢተውትም። ድርጅቶች የስትራተጂ ለውጥ ቢያደርጉና ትኩረታቸው ወደሌላ ቢያዘነብልም  ሂደቱ የሚገታ አልሆነም።  የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ትግል በኛ አገር ተጨባጭ ሁናቴ ህዝባዊ እንቢተኝነት ማድረግ እንደሚቻል ያስረገጠ ሆነ። አሁን ያለበትን ደረጃ የበዛነው እጃችንን አጣምረን እያየነው ቢሆንም ነፃ የሚያወጣን ትግል ነው። አገዛዙ እንደስርአት መቀጠል የማይችልበት ደረጃ ደርሷል።ጊዜው  እንደ አንድ አገር ህዘብ ከዚህ ዘረኛ፤ አድሏዊ ፤ ጨፍጫፊና የደናቁርት ስርአት መገላገል እንፈልጋለን አንፈልገም? የሚለውን ጥያቄ የሚያስነሳ ሆኗል።

መንገድ አለመዝጋት  ከዘጋችሁ መልሶ ህዘቡ በደቦ ወጥቶ ካልሆነ በወታደር ሀይል ሊከፍተው የማይችል አድርጋችሁ ዝጉ።  ሁሉም ያስፋልት መንገድ ላይ ከክምር ላይ ክምር ብቻ እስከጭራሹ ሊነዳበትና ሊፀዳ የማይቻል ማድረግ ያስፈልጋል።  በየተወሰነ እርቀት ተቆፍሮ ጉርጓድ ማበጀቱም ጥሩ ነው። ማፍረሻው ከተገኘ ድልድዬችንም አፍርሱ። ትግሬ ወያኔዎች በቀጣይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ለማድረግ የሚያስችላቸውን ፖለቲካ እየሰሩ ነው። አንዳንድ  ለለውጥ ቆመናል የሚሉም የድርሻቸውን እገዛ እያደረጉም ነው። ጫጩት ፊት ፈንግል እንደማይወራ ጠፍቶ ግን አይደለም። ለማንኛውም  ዝም ብለህ ተጨፍጨፍ የሚል ህግ የለም። ትግልም አይደለም። እራስህን በሁሉም መንገድ ተከላከል። የሚከፋቸውና ፖለቲካ ሊሰሩበት የሚሞክሩ እንደሚኖሩ  ይታወቃል። ስህተት ጥበቃ ለጉድ አቆብቅበዋል። ያ ችግራቸው ነው። ተገዳላይ ሆይ ትክክልና አግባብነት ያሌለውን የግድ መደረግ ካለበት ትለያለህ። “የሚካሄደው ትግል ነው”።   የሚቻልህን አይደለም ከሚቻልህም በላይ ጥንቃቄዎችን በያዝከው መንገድ ማድረጉን ቀጥል አለቀ።
መንገዱ ይዘጋ ያኔ ሊገድል ባገሬው የተበተነው  ዳቦ በታንክ ይቀርብለት እንደው እናያለን። ለማንኛውም ከመዓከሉ  ተቆርጠው የሚቀሩ ወታደሮች የህዝብን ትግል መቀላቀል መፈለጋቸው ስለማይቀር  ጥሪም ማድረግ ግንኙነት መፍጠርና፤ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ያስፈልጋል።  ትግሉን የተመለከተውን በዚህ ልዝጋው የኦሮሞን ህዘብ ከመፍራትም ሆነ ከመጥላት ብቻ በየትኛውም ሰበብ  ይሁን ይህን ትግል ከዳር ሆነን ባንመለከተው ኖሮ በዚህ ሳምንት ውስጥ ይህን ስርአት ተገላግለን ነበር። ይሄኔ ነፃ ህዝቦች ነበርን።
ጥያቄ 1.  አሁን ኦሮሚያ ውስጥ እየሆነ ያለው ምንድን ነው?።
ሀ. ግርግር  ለ. ግጭት  ሐ. ስሜታዊነት  መ. መልሱ ከነዚህ ውስጥ አንዱም አይደለም።
ሁላችንም ቢገባን ይህ ህዝብ ለኢትዬጵያዊነት የከፈለው መሰዋትነት   ለሮሞነቱ ከከፈለው መሰዋትነት እጅጉኑ የበዛ ነው።  ድሮም ቢሆን እንዳአገርና ህዝብ  የማይታለፍ የሚመስል ችግር ውስጥ በተገባና  ባጋጠመ ጊዜ ሁሉ ሊመዘን የማይችል መሰዋትነትን ከፍሎ አሻግሯል። ኢትዬጵያዊነትን አስቀጥሏል።የዛሬውም ከዛ የተለየ አይደለም። ኢትዬጵያ ትኖራለች። ሊያውም ዲሞርራሲያዊት፤ የዜጎች መብት የሚከበርባት፤ እኩልነት የሰፈነባትና የበለፀገች ሆና።  ለዚህ ባህሉ፤ አናኗሩ፤ በሰከነ ሁኔታ መነጋገርና ማሰብ የሚችል መሆኑና አናሳ አለመሆኑ ተጨምሮበት  ዛሬ ላይ ሆኖ በልበ ሙሉነት ይህን ለመናገር ያስደፍራል።
እንግዳ የሆነብንና አልመቸን ያለው ይህ ህዘብ ሁሉ ነገር ክሽፈት እየሆነ ስለተቸገረ መዘወርያው ላይ የሚገባውን ቦታ ማግኘት ወሳኝ መፍትሄ አድርጎ መውሰድ ነው። የሚገባውን ድርሻ ይዥ ወሳኝ በሆነ ሁኔታ በአገራዊ ጉዳይ ላይ አስተዋፆ ካላደረኩ ከዚህ የቁልቁለት መንገድ መውጣት አይቻልም ሲል አጥብቆ ማመኑ  ነው።  እዛች አገር ላይ የተንጋደደው ሚዛኑ ይስተካከል ብሎ በመጮህ ብቻ ሊስተካከል እንደማይችል ማወቁ ነው። ይህ ፍላጎቱና ድምዳሜው ትግሉን በኦሮሞነትም በኢትዬጵያዊነትም እንዲያካሂድ ግድ ማለቱ የፈጠረው ብዥታ ነው። በእርግጥ ይህ ህዝብ ከኢትዬጵያዊነት ጋር ያለውን ቁርኝት ሙሉ በሙሉ አውጥቶ በማየት ረገድ አንዳንድ የኦሮሞ ምሁራኖች ጋርም ስህተቱም ብዥታውም አለ። ለዚህ ገፊ የሆነው ምክንያት ይህን ህዝብ ጠልቆ ካለማወቅና ስር ከሰደደ ጥላቻ የሚዥጎደጎደው የዳቦ ስም ብዛትና ስድብ ነው። ዘረኛ፤ ጠባብ፤ ጎጠኛ፤ ሰውነት ደረጃ ያልደረሰ አውሬ…… ማቆሚያ የለውም። ያም ሆነ ይህ ግን በመጨረሻ ዲሞክራሲያዊት የሆነች ኢትዬጵያ  ነው የምትኖረን። በነፃነት መምከርና ውሳኔ ላይ ሲመጣ የተንዘላዘለውን ሀሳብ እንደሚገርዘው ጥርጥር የለኝም።
የዶ/ር ብርሀኑን ንግግር ደጋግሜ አዳምጬዋለው። የኦሮሞን ህዝብ ትግል በሚመለከት የተናገረው  ጠቅለል አድርጌ የተረዳሁት እየሞቱ ነው እዘኑላቸው። ግን ? በሚል አይነት ነው። “አይታችሗቸዋል” እያለ ሲያወራ ጭቃ እያቦኩ እቃቃ ስለሚጫወቱ የኬንያ ህፃናት የሚያወራም መስሎ ተሰምቶኛል። “ስለማንነትና ዲሞክራሲ ግንባታ” የተናገረው አዳራሽ ሙሉ ጭብጨባ ስለተቸረው፤ ካዛም በሗላ ብዙ ዶ/ሮች ድንቅ ትክክል የሆነ ንግግር ስላሉት ትክክል ነው ብለን እንውሰደው። ለኔ ግን ገና አልገባኝም። እንዲገባኝ ማንነት ማለት ምንድን ነው። ብዙ ማንነት ነው ያለው ስለየትኛው ማንነት ነው?። ማንነት ተፈጥሯዊ ነው ፈልገን የምንይዘው ነው?። ማንነት ላይ ያልተመሰረተ ፖለቲካ ማካሄድ ይቻላል ወይ?። ዲሞክራሲ በሰፈነባቸው አገሮች ማንነት የለም ወይ?። ማንነት ለዲሞክራሲ ግንባታ እንቅፋት የሚሆነው እንዴት ነው?። ንግግሩ ላይ ለዚህ ድምዳሜው አስረጅ አድርጎ ያቀረባቸውን አስረጆች ተያያዥነት አላቸው የላቸውም?። ብዙ ብዙ ጥያቄ አጭሮብኛል። በመጨረሻ የምደርስበት ድምዳሜ ዶ/ር ብርሀኑ ያለው ሊሆንም ላይሆንም ይችላል።
ለሁኑ አሁን ባለው ያገራችን ተጨባጭ እውነታ ትክክለኛ መስሎ የሚታየኝ ግልፅ አድርጌ ላስቀምጥ። የማንነት በዋናነት የኦሮሞ ህዝብ የማንነት ፖለቲካ ኢትዬጵያን በቀጥታ ዲሞክራሲያዊት የሚያደርግ ነው። እንደውም ከዚህ ውጪ ኢትዬጵያ ዲሞክራሲያዊ ልትሆን የምትችልበት እድል ዚሮ ነው። እንዴት? የሚለውን ከፈለጉ ዶ/ር ብርሀኑን ጨምሮ ሌሎችም እንደኔ ጥያቄዎችን አውጥተው ተመራምረው ስህተተኛ ያድርጉኝ። እንደውም ይህን የተረዱ ምሁራን ኦሮሞ ፖለቲካው ላይ ተፅኖ አድራጊ ከሚሆን ከሚል ነው ለኢትዬጵያ በእርግጥ ዲሞክራሲ ያስፈልጋታል ወይ? በማለት  ፈራ ተባ እያሉ ጥያቄውን ማንሳት የጀመሩት። እይታዬን ከበድ ላድረገውና በድጋሚ በመሬት ላይ ካለው ተጨባጭ እውነታ በቀጣይ ለስልጣን እራሳቸውን ከሚያዘጋጁት ውስጥ ከኦሮሞ ብሄርተኞች ውጪ ያሉት በሙሉ ዲሞክራሲያዊ ሊሆኑ አይደለም እስከዛሬ ከነበሩን አንባገነኖች የከፉ ጨፍጫፊ አንባገነን ሳይሆኑ ስልጣን ላይ አንድ አመት መዝለቅ አይችሉም።
እንግዲህ ዲሞክራሲ ሰላማዊ የበለፀገች ኢትዮጵያ እንድትኖር ካለው ወሳኝነት አኳያ በእርግጥ ማነው ለዚህች አገር አንድነት አደጋ ሊሆን የሚችለው የሚለውን ጥያቄ ሁሉ ያስነሳብኛል። እኔም አገር እንዲኖረኝ  እፈልጋለዋ።
ኦቦ ጀዋር አትቸኩል። ብዙ እየሰራህና ትክክለኛነት እያለህ ስህተት ታበዛለህ።  የምን ጠላትነት ነው የምታወራው። ጠላትነት የለም። የማንስማማበት ጉዳይ አለ ምን አለ። እውነቱን ልንግረህ ያንን ትውልድ መሰልከኝ። ለነገሩ አንተም አፍሮ ታበጥራለህ መሰለኝ።
አቶ ግርም ካሳ የምን መጨራረስ ነው የምታወራው። ደሮም ሰላማዊም ታጋይም እንዳልሆንክ ጠርጥሬያለው። ሰላማዊ መጨራረስ ነው በለን ደግሞ። መጋኛ መንዘላዘያህን ይጨርሰው ሌላ ምን እላለው። እሱም እኔም ስለማናነበው ቢሞትም ዝም ብለህ ለመልስ ዜናዊ ግልፅ ደብዳቤ ፃፍ። ላስታውስህ አምሳ አንደኛ ግልፅ ደብዳቤ ላይ ነበር ያቆምከው።
ብሄራዊ ጭቆና ያብቃ።
ዳዊት ዳባ

ከ 1983 እስከ 2007 ዓ.ም በዐማራው ነገድ ላይ የደረሰ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል ጥናት ውጤት ማጠቃለያ ዘገባ! (ሞረሽ ወገኔ)

ኢትዮጵያ አገራችን እያከተመ ባለው ምዕተ-ዓመት ሁለት የተለያዩ የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ለውጦችን አስተናግዳለች። የመጀመሪያው በ 1966 የፈነዳው አብዮትና ሶሻሊስታዊ እንቅስቃሴ ሲሆን፣ ሁለተኛው በክስተቱም ሆነ በውጤቱ እጅግ የተለየው ደግሞ ከ1983 ጀምሮ የተንሰራፋው የዘመነ መሳፍንት ተምሳሌት ወያኔ መራሹ ፓለቲካ ነው። ይህ በጎጥና በመንደረተኛነት ላይ የተመሠረተ አምባገነናዊ አገዛዝ እነሆ! ከ 25 አመታት ቆይታም በኋላ ኢትዮጵያን እያመሳት መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ኅልውናዋን፣ ሉዓላዊነቷንና አንድነቷን አናግቷል። እያናጋም ነው።
በያዝነው  ዓለም አቃፋዊነት ዘመን (ዘመነ ግሎባላዜሽን)፣ ዓለም እየጠበበችና አንድ መንደር እየሆነች መጥታለች። የአገራት ጂኦግራፊያዊና የኢኮኖሚ ክልል ሳይገድባቸው ባለሀብቶች ባሻቸው አሕጉር፣ አገርና ማናቸውም ሥፍራ መዋዕለ-ነዋያቸውን በማፍሰስ እራሳቸውን ጠቅመው ተቀባዩን አገርና ኅብረተሰብ እንዲጠቅሙ የሚበረታቱበት ውቅት ነው። ባለሙያዎች ዜግነትና ድንበር ሳያግዳቸው በሚፈለጉበት አገር ሁሉ ሙያቸውን እንዲያጋሩ በሩ በተከፈተበት ዘመን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የጎሳ ፓለቲካ ባሰመረው ክልል የተነሳ፣ የጋራ ደም የተከፈለባት ኢትዮጵያ የጋራ አገር ልትሆን አልቻለችም። ኢትዮጵያ ውስጥ፣ አገሪቱ የሁሉም ነገዶቿና ጎሣዎቿ አገር ሆና ሳለ፣ «የእኛና» «የእናንተ» እየተባለ በተከለለ የጎሳ አጥር፣ ሕዝቡ ተዘዋውሮ መሥራት እንዳይችል  ገደብ ተጥሎበት ይገኛል። ነገዶችና ጎሣዎቻችን ጌጦቻችን መሆናቸው ቀርቶ፣ ለመከፋፈላችንና ለአንድነታችን መፍረክረክ ምክንያት እንዲሆኑ፣ በዘረኞች ቀመር ዞሪያ እየተሽከረከሩ ይገኛሉ። የውጭ ጻህፍት ሳይቀሩ «የነገዶች ሙዚየም» ብለው ያሞካሿት ኢትዮጵያ፣ በከፋፍለህ ግዛው የፓለቲካ ጦስ የእርስ በርስ ጦርነት መሻኮቻ መድረክ ሆናለች።
በቀዝቃዛው ጦርነት ማክተሚያ ወቅት፣ ኮሙኒዝምን ለመበቀል በዛቱት ምዕራባውያን ትከሻ፣ ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር በለስ የቀናቸው የትግሬ-ወያኔዎች፣ ኢትዮጵያን ለመበታተን ሌት ተቀን እየሠሩ ለመሆናቸው ገሃድ ከሆነ ውሎ አድሯል። የኢትዮጵያን መሠረታዊና ጥንታዊ ዕሴቶች፣ የሕዝቧን ኅብረትና አብሮነት ለመናድ ሳይታክቱ ጠንክረው እየሠሩ ነው። ገና ከጽንሳቸው ጀምሮ፣ የጥፋት ዒላማቸው ያደረጉት ደግሞ የዐማራውን ማኅበረሰብ ነው። ዐማራውን ያለ ስሙ ስም ሰጥተው ፣ያለጥፋቱ ጥላሸት ቀብተው ፣ ብሔራዊ  መለያ ደማቅ ቀለሙን አደብዝዘው ፣ አኩሪ ታሪካዊ ሚናውን አኮስሰው፣ ኮንነውና አጥላልተው  ባምሳላቸው ለቀረጿቸው ጎጠኞች የጥቃት ዒላማ አድርገውታል። እነዚህ በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ያለፈቃዱ የተፈናጠጡ የወያኔ ዘረኛና ጠባብ ናዚዎች በውስጣቸው በተፈጠረ የበታችነትና የቅናት ስሜት የተነሳ፣ በሰነቁት ጥላቻ ይህንን ታላቅ፣ ታታሪና ለኢትዮጵያ የክፉ ቀን ዘብ የቆመንና ኢትዮጵያን እንዳገር ለማፅናት የታገለ ሕዝብ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመውበታል። እየፈጸሙበትም ነው።
ጥቃቅን ችግሮችን በማጋነንና ልዩነት በመፍጠር አብሮ በኖረ ሕዝብ መካከል በቀላሉ የማይጠፋ እሳት ለኩሰዋል። ለጠባብ ዓላማቸው ስኬት ሲሉ፣ የጎሣ ፓለቲካን ከሚገባው በላይ አራግበውና አጡዘው፣ ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ መንስዔ የዐማራው ነገድ እንደሆነ ጧት ማታ በመልፈፍ፣ ልበወለድ ታሪኮችን በመፈብረክና ዕኩይ ፕሮፖጋንዳ በመንዛት መጠነ ሰፊ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ዘመቻ ከፍተውበታል።
ዐማራው በ18ኛው ክፍለ-ዘመን መባቻ ላይ፣ ኢትዮጵያን ሊቀራመቱ ከመጡ ቅኝ ገዢዎች መንጋጋ ሕይወቱን ገብሮ እንዳላዳናት፣ በ 21ኛ ክፍለ-ዘመን በዚችው አገር እንደባዕድና እንደወራሪ ተጨፈጨፈባት ። በተሰዋላት ኢትዮጵያ ውስጥ በግፍ ሕይዎቱን በግፈኞች ተነጠቀ። የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጸመበት። ዘርን መርጦና ለይቶ የወል ወንጀል ሲፈጸም፣ ይህ በዐማራው ላይ የደረሰው በአገራችን ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው መሆኑ ነው።
አብዛኛው ዐማራ፣ በኑሮው ከማንኛውም የኢትዮጵያ ነገዶች ባነሰና በከፋ የድህነት አርንቋ ውስጥ መኖሩ በግልጽ እየታየ ፤ ገዛ፣ በዘበዘ ፣አደህየን ወዘተ በማለትና የሌለበትን ኃጢያት በመደርደር፣  ለዕኩይ ዓላማቸው የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ተጠቅመውበታል። ዐማራ የጎጠኝነትና የጠባብነት ስሜት ከቶ ኖሮት አያውቅም። ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ተጋብቶና ተስማምቶ የሚኖር ብቻ ሳይሆን፣ በሄደበት ቦታ ሁሉ፣ በታታሪነቱና ባለው የዳበረ ማኅበራዊ መስተጋብሩ ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ የሚኖር ማኅበረሰብ መሆኑ ማንም የሚያውቀው ነው። የጎጠኞች ፀረ-ዐማራ ርካሽ ቅስቀሳና መሠረተ ቢስ ክሳቸው፣ ተከላካይ ባለማግኘቱና ለዓመታትም በመደጋገሙ፣ ሌሎች ጠባቦችን ለመቀፍቀፍና ለማነሳሳት በቅቷል። በመሆኑም ዐማራው በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ዜግነቱን፣ ጥቅሙን፣ መብቱንና ክብሩን ብቻ ሳይሆን፣ ሰብአዊነቱንና ሕይዎቱንም ጭምር ተነጥቆ፣ቀሪው የሰቀቀን ሕይዎት በመግፋት ላይ ይገኛል።
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፣ የዐማራው ድምፅ ለመሆንና የገጠመውን መጠነ ሠፊ ችግር ለዓለም ማኅበረሰብ ለማመላከትና ለማሳወቅ  ከተመሠረተ እነሆ ሦስት ዓመት ሊያስቆጥር ነው። በዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ የዐማራው ድምጽ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ ዐማራው ምን እንደተፈጸመበት፣ ምን ሊፈጸምበት እንደታቀደና ያንዣበበትን  ከፍተኛ የኅልውና አደጋ የቱን ያህል የከፋ እንደሆነ፣ እንዲገነዘብና እንዲያውቅ  የበኩሉን ጥረት አድርጓል። አንቅቷል። ሞረሽ ሊያከናውናቸው ካቀዳቸው ግቦዎቹ ውስጥ አንዱ፣ ዐማራው ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተከታተለ ማጋለጥና አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ ነው። በዚም መሠረት ሞረሽ አንዱና ቀዳሚው ተግባሩ ያደረገው፣ ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረበት ከዚያ ክፉ ቀን ጀምሮ፣ እስከ ዛሬ በዐማራው ነገድ ላይ የተከፈተውን መጠነ ሠፊ የማፈናቀልና የዘርማጥፋት ወንጀል ለማወቅና አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እንዲቻል በመረጃ ላይ የተመሠረተ ጥናት ማካሄድ ነው። ይህንንም እንደሚያደርግ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ማስተዋወቁ የሚታወስ ነው። ስለሆነም በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በተለይም በዐማራው ላይ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች የተፈጸሙባቸው አካባቢዎችን  ያካተተ በተጨበጠ፣ ግልጽና አስተማማኝ መረጃዎች ላይ የተመሠረተውን ይህንን ጥናት አስጠንቶ ለራሱ የዐማራ ነገድ ተወላጆች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ለታሪክ ተመራማሪዎች የኅሊና ፍርድ አቅርቧል።
ጥናቱ የዐማራውን መጠነ ሠፊና በዝምታ ዕልቂት ለዓለም ይፋ ለማድረግ ተዘጋጅቷል። ጆሮ ያለው እንዲሰማ፣ ዓይን ያለው አጥርቶ እንዲያይ፣ ዐማራው በዚህ በጎጠኞች ዘመን የተደገሰለትን በአሉባልታ ሳይሆን፣ በተጨበጥና በሚዳሰስ መረጃ ቀርቦለታል። የዚህ ጥናት ውጤት ተነቦና ከንፈር ተመጦ እንደ አንድ የትራጄዲ ልበወለድ ለተወሰኑ ጊዜ ቆዝመው የሚተው አይደለም። ይልቁንም ማናቸውም ኢትዮጵያዊ በተለይም ዐማራው ኅብረተሰብ ከዚህ የከፋ ምንም እንደማይጠብቀው አውቆና ከራሱ በስተቀር ማንም ተገን እንደለሌው ተረድቶ፣ ለራሱ መቆም እንዳለበት እንዲገነዝብ የሚያግዝ  ሁነኛ ዋቢ ታሪካዊ መረጃ ነው። ይህንን ግድያ ያቀነባበሩ፣ ያበረታቱና ቀጥታ ወንጀሉን የፈጸሙት ጎጠኞችና ጠባቦች የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ የሚጠየቁበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም። የሞረሽ ወገኔ ፍላጎትም፣ የዚህ ጥናት የመጨረሻ ግብም ወንጀለኞችን ለሕግ ማቅረብ ነው።

የጥናቱ ዐብይ ዓላማ፦ ለአለፉት 25 ዓመታት በዐማራው ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል የተጨበጠ መረጃ በማሰባሰብ፣ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ በሚኖሩ ወንጀለኞች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ሲሆን፣ የወንጀሉን ደረጃና መጠን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም፣ ሰለባ ለሆነው ለዐማራው ኅብረተሰብ፣ ወንድምና እህቶቹ መርጠው ባልተወለዱበት ዘራቸው ተነቅሰውና ተፈርጀው የገጠማቸውን ሰቆቃ፣ እልቂትና ሰብአዊ ውርደት በትክክል እንዲያውቅ ማድረግ ነው። የጥናቱ ዓላማ በዝርዝር፦
■        ከ 1983 ዓ.ም ጀምሮ ያለቁና የተፈናቀሉ ዐማሮችን መጠን ለማወቅ፣ እንዲሁም የወያኔ የጎሳ ፓለቲካ በዐማራው ሕዝብ ላይ ያደረሰውን ጥፋት በግልጽ ለማሳየት፣
■        የተፈናቃዮችንና የሟቾችን ማንነት ዝርዝር መረጃ ለማጠናቀር፣
■        በዐማራው ላይ የደረሰውን የጭፍጨፋ መጠን ለማሳየት፣
■        በዐማራው ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጽዳት ወንጀል ቀጣይነት ያለውና፣ ሆን ተብሎ በዕቅድ እየተፈጸመ መሆኑን ለማሳየት፣
■        ዐማራውና ሌሎች የኢትዮጵያ ነገድ አባላት በወገናቸው ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍና እልቂት እንዲገነዘቡ ለማድረግ፣
■        ወንጀለኞቹንና ድርጊታቸውን ለማጋለጥና ለሕግ ለማቅረብ፣


የጥናቱ ሥልት፦ ጥናቱ በማኅበራዊ ሳይንስ ጥራታዊ (Qualitiative) አጠናን ሥልት መሠረት የተካሄደ ነው። የጥናቱ ግብዓቶች በጥንቃቄ በተዘጋጁ የተመጠኑ ጥያቄዎች ላይ ተመሥርቶ በተዘጋጁ ቃለመጠይቆች በተሰጡ መልሶች፣ የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑ ሰዎች፣ በቃል፣ በጽሑፍ፣ በቦታና በድርጊት የተሰበሰቡ መረጃዎች ናቸው ። ቃለመጠይቆቹ የተካሄዱት በገጽና ድርጊቱ በተፈጸሙባቸው አካባቢዎች ሆኖ፣ የወንጀሉ ሰለባዎች ከሆኑትና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ነው። ጥናቱ በተጨማሪም የሰነድ፣ የፎተግራፍና የቦታ ማስረጃዎችን አካቷል። በቃለመጠይቁ የተሳተፉት ሰዎች ምስልና ድምጽም ተቀርጿል። ለዚህ ጥናት 216 ዐማሮች የእማኝ ቃላቸውን በመስጠት በጥናቱ ውስጥ ተሳታፊ ሆነዋል(የየአካባቢው የጥናቱ ተሳታፊዎች ቁጥር ዝርዝር ዝቅ ብሎ በሚገኘው ግራፍ ላይ ተመልክቷል።)
የጥናቱን ተሳታፊዎች ለመምረጥ ስኖው ቦል (Snow Ball) የናሙና አመራረጥ ዘዴ ተግባራዊ ሆኗል። በሁሉም ቦታዎች የተካሄዱት መጠይቆችና ውይይቶች በድብቅ የተከናወኑ ናቸው።





ጥናቱ የተካሄደባቸው አካባቢዎችም፦ ሐረር፣ አርሲ፣ ቤንች ማጂ፣ ጅማ፣ ወለጋ፣ ከማሽ፣ መተከል፣
አፋር(ዐባይ ነጌስ ጎጥ) እንዲሁም ባሕርዳርና ጎንደር ከተሞች ናቸው።

በኦሮምያ ክልል የተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄና የሃገራችን መጻሒ ሁኔታ! | ከኃይለገብርኤ አያሌው

 | 

በኦሮምያ ክልል የተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄና የሃገራችን መጻሒ ሁኔታ! | ከኃይለገብርኤ አያሌው

Share1  662  0 
 Share3
ሃገራችን በረጅም ዘመን ታሪኳ አያሌ ግጭትና ጦርነቶችን እስተናግዳለች ። በተደጋጋሚ ሕልውናዋን ሊያጠፉት የተቃረቡትን የውጭና የውስጥ አደጋዎች ተቋቁማ ዛሬ የደረስንበት ዘመን ላይ ደርሳለች። በነዚህ ዘመናት ውስጥ የገጠሟትን ችግሮች ፤ ዘር ሃይማኖት የቋንቋ ልዩነት ሳይገድባቸው ቆራጥና አስተዋይ ልጆቿ በሕብረት በከፈሉት ወደር የለሽ ተጋድሎ ሕልውናዋን እስጠብቃ ኖራለች። ሃገራችን ከዓለም ቀድምት ከሆኑት የስልጣኔና ፈር ቀዳጅ ጥቂት ሃገራት ተርታ የሚቆጠር አኩሪ ታሪክ ያላት ፡ በምድር የከበረች በሰማይም የተመሰገነች ፤ የቅዱሳን መሸሸጊያ የነጻነት ተምሳሌት ሆና ታፍራና ተከብራ   መኖሯ እርግጥ ነው።
Oromia
ኢትዮጵያ ዙሪያዋን በከበቧት እረፍት የለሽ የቅርብና የሩቅ ጂዖ ፖለቲካዊ ስትራቴጂካዊና ታሪካዊ ጠላቶቿ ሴራ በተራዘመ የግጭት አዙሪት ውስጥ ወድቃ እንድትኖር የቀበሩት ግዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ በተደጋጋሚ ጉዳት ሲያደርስብን ቆይቷል። እነዚሁ ከራሳችን ሊወርዱ የማይሹት ባላንጣዎቻችን የተንኮል ሴራ ፍላጎታቸውን  ሊያስፈጽሙ የሚችሉ ሃገር በቀል  እንደ ሕውሃት ያለ ቅጥረኛ ባንዳዎች ያልተቋረጠ ድጋፍ ሲሰጡ ቆይተዋል። በዚህም  ትላንት በቀጥታ ያልቻሉትን በገዛ ወንድሞቻችን ጀርባ ተረማምደው የሃገራችንን ሕልውና በማፍረስ ሃገሪቱን በእጅ አዙር ለመቆጣጠር ብዙ ግዜ ሞክረው ያልተሳካላቸው ፖሊሲ ይህው በ 21 ክ/ዘ ተሳክቶላቸው በባህል በሃይማኖት በጋብቻና  በዕለት ተዕለት ሕይወት ተቆራኝቶ ተስማምቶ ለዘመናት የኖረውን ሕዝባችንን በዘውግ  ፖለቲካ ተከፋፍሎ፤  ያለፈ ታሪክ ማጥ ውስጥ ጥለውን እርስ በዕርስ እንድንጠፋፋ ሲያመቻቹን ከርመዋል። ሕወሃትና ሸሪኮቹ  ሃገራችንን እየቀሙን በስደት የባዕዳን አሽከር በሃገራችንም ሁለትኛ ዜጋ ሆነን ተነጣጥለን እንድንቆም ማድረግ በመቻላቸው ብሶትና መከራችን የጋራ መሆኑ ቀርቶ ክልልን የማይሻገር በጎጥ የታጠረ የተናጥል እንዲሆን ተድርጎ ቆይቷል።
በተለይም አውሮፓውያን አፍሪካን እንደ ቅርጫ ስጋ ተከፋፍለው ባካሄዱት ሕገወጥ የጭካኔ ወረራ ድፍን አፍሪካን ተቀራምተው ፍላጎታቸውን ለማሳካት ሲበቁ ፤ እንቢኝ አሻፋረኝ ብለው ለቅጥሯ ዘብ ሆነው ወራሪዎችን አይቀጡ ቅጣት እየቀጡ የሃገራችንን ሕልውና ለማስጠበቅ አባቶቻችን ቢችሉም ፥ ይህ ሽንፈት ያልተዋጠላቸው  ምዕራባዊ ተስፋፊ ሃይሎች ከገዛ ልጆቿ ማህል በመለመሏቸው ባንዳና ሹንባሾች ፤ በብሔሮች መካከል ጸንቶ የኖረውን ውህዳዊ የአብሮነት ኑሮ ለመበረዝ ጨቋኝና ተጨቋኝ ፤ ቅኝ ገዥና ተገዢ የሆነ ሃገር በቀልና ብሔርን መሰረት ያደረገ አስተዳደር  እንዳለና እንደነበር  አድርገው የረጩት ፕሮፓጋንዳና ያቀዱት የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ ዘመን ተሻግሮም ቢሆን ሊሰምርላቸው ችሏል።
በዚህ ባለንበት የ21ኟው ክፍለ ዘመን ዓለም በቴክኖሎጂ መንጥቆ የመገናኛ ዘዴዎችን ባቀለለበት የህዝቦች የባህል ፤ የኢኮኖሚና የጸጥታ ጉዳዮችን  በቀላሉ ከአንዱ ወደ ሌላው ክፍለ ዓለም በሰከንድ መረጃ በሚያደርስበት ግሎባላይዜሽን በሚዘመርበት የሃሳብ የበላይነት ገኖ በወጣበት በዚህ ባለንበት ዘመን ራሱን የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ብሎ የሚጠራው ፤ ከቅኝ  ገዥዎች  መቃብር ላይ የበቀለ የጥፋትና የዘረፋ ቡድን ዘመን የሻረውን ሗላ ቀርና  በታኝ የከፋፍለህ ግዛው ፍልስፍና በሃገራችን ላይ አንብሮ  በተንኮልና በአሻጥር ሲያተራምሰን  ቆይቷል።
ይህ ከዘመኑ አስተሳሰብ የተጣላ የዕውቀት ጠር ጨካኝና አረመኔ አገዛዝ ባለፉት 25 አመታት ሃይማኖትን በሃይማኖት ፤ ብሄርን ፤ ከብሄር የሚያጋጭ ክፉ ፖለቲካ ሲያራምድ ቆይቷል። እንደዚህ ፋሽስታዊ ቡድን ቅስቀሳና ፍላጎት ምንም ሕዝባችን ወደ አጠቃላይ ግጭት ባያመራም ፤ ነገር ግን ጸንቶ የኖረውን የሕዝባችንን አብሮነት በማወክ ለጋራ ሃገራዊ አላማዎች  የጋራ ሕብረት እንዳይኖረው ማድረግ የሚያስችል መሰሪ ዕቅዱ ለረጅም ግዜ ተግባራዊ ሆኖ ቆይቷል። ዛሬም ቀጥሏል ።  ለነገም ይህን እኩይ ሴራ ነቅቶ  ማክሸፍ የማይቻል ወገን ካለ መከራውም ይረዝማል ፥ ልዩነቱም ይሰፋል ፤ ባርነቱም ፤ ይቀጥላል!!
ለዘመናት በአንድነት የኖረው ሕዝባችንን አንድነቱን አላልቶ በቅራኔ አፋጦ ባለፈ የታሪክ ጠባሳ ላይ ስንታገል ሕወሓት ግን አፓርታይዳዊ ዘረኛና ዘራፊ አገዛዙን በላያችን ጭኖ ያሻውን ሲያደርግና ሲፈጽምብን ቆይቷል።  የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት  ይህው የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ እስከግዜውም ቢሆንም ተሳክቶለት ፤ አማራው ሲጠቃ ፤ ኦሮሞው ቆሞ እንዲያይ ፤ ኦሮሞው ሲጎዳ አማራው በጸጥታ ሲያልፈው ፤ እንዲሁም ክርስቲያኑ ችግር ሲገጥመው ሙስሊሙ ዝም ሲል ፤ ሙስሊሙን ጉዳት ሲገጥመው የክርስቲያኑ ጸጥታ እስከ ተወሰነ ግዜ ገዥዎችን ሲጠቅም ቆይቷል። በነዚህ ዘመናት የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት እያፈራረቀ በተለያየ አጀንዳና ግንባር የሚፈልገውን እየደፈጠጠ አገዛዙን በሕዝብና በሃገር ላይ አጽንቶ ልክ እያስገባን ይገኛል።• ።
የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት የረጨው የጥላቻና የመለያየት መርዝ ነቅቶ በግዜ በማርከስ ሕዝብን ማቀራረብ የነበረባቸው የአማራውና የኦሮሞ  ምሁራን መካከል ተካሮ የቆየው ልዩነት ለዘረኛው አገዛዝ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠሩም በላይ ሁለት ግንባር በአንዴ ከማጥቃት ተቆጥቦ ስልታዊና ታክቲካዊ ሽግሽግ በማድረግ የግዜና የሁኔታዎችን አመቺነት እያሰላ ፤ በተከታታይ እንደታየው የተነሳበትን ሕዝባዊ ተቃውሞና የአመጽ እንቅስቃሴ ለማዳፈን አንዱን በሌላው ላይ እየቀሰቀሰ ከጎኑ ለማሰለፍ ሲችልና ሲያደርግ ቆይቷል ፤ አሁንም ያንኑ ስልቱን በመቀመር በከፋና ምንአልባትም ሃገሪቷን ሊበታትን የሚችል የዘር ግጭት ለመቅስቀስ እየተንቅሳቅስ ለመሆኑ ከሚወጡት መረጃዎች መረዳት ይቻላል።
በተለይም ባልፉት አራት አስዕርተ አመታት ውስጥ በአንዳንድ የኦሮሞ ምሁራን ተላላነት በጥቂት ሆድ አድሮችና በእንዳንድ ጽንፈኞች ቅንብር እና በትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት አዝማችነት በተሳሳተ ፕሮፓጋንዳና በተንሸዋረረ የማንነት ውዥንብር  የኦሮሞን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት ማዕከል ለመነጠል ያልተቋረጠ ሴራ ሲራመድ ቆይቷል። የዚህም ሴራ ዋና አላማ  እንዱ  የኦሮሞ ማሕበረሰብ ዙሪያውን ካሉት ሌሎች ብሄሮችና ከእንድነት ሃይሎች ጋር ያልተቋረጥ ቅራኔ ውስጥ  ከቶ ፋታ በመንሳት በተፈጥሮ ሃብት የበለጸገውን የኦሮምያ ምድር በምስለኔዎቹ ተረማምዶ ለዘመናት ትቆጣጥሮ ያለ ከልካይ ሲመዘብር ለመኖር ካለው ሕልም የተንሳ ነው።
በዚህም የሴራ ቅመራ ባለፉት አመታት እንደሆነውና እንደታየው ፥ በተለይ የአማራ ተወላጆችን ከኦሮሞ ማህበረሰብ ፍላጎትና ፈቃድ ውጪ የጥላቻ ቅስቀሳ በማድረግ በካድሬዎቹ አዝማችነት ተወልደው ካደጉበት ፤ ለፍተው ያፈሩትን ሃብትና ንብረት እየቀሙ ከክልሉ በገፍ እንዲባረሩ ሁን ተብሎ  በትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት በተቀነባበረ ሴራ በብዙ ሺህ በሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የጅምላ ግድያና ፥ የዘር ማጥፋት ወንጀል በኦሮሞ ነገድ ስም ሲፈጸም   ቆይቷል። ዛሬም ይህው ሴራ  ቀጥሏል ፥ ነገም በጋራ ካልቆምን ካሁን ቀደሙም የከፋ የእርስ በዕርስ መተላለቅ ሊከሰት እንደሚችል ለመረዳት ነብይ መሆን አይጠይቅ።
ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነው ፤ ኢትዮጵያም የኦሮሞ ናት! ይህን ሊፍቅና ሊያስቀር የሚችል ምንም ውሃ የሚቋጥር ምክንያት የለም። የኦሮሞ ልጆች ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነትና ለወሰኗ ክብርና ለሉዓላዊነቷ ወደር የሌለው መስውዕትነት ሲከፍሉ ኖረዋል። ይህንን የክብርና የኩራት ታሪክ ንደው የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን ከሃገራዊውና ከአህጉራዊው ተምሳሌታዊ ሕዝብነት አርቀው የባርነትንና የተገዥነትን የሃሰት ማቅ ሊያለብሱት በጠባብ ብሔረተኝነትና በጨለምተኛ የስሜት ፖለቲካቸው እሳት ውስጥ ትውልዱን ሊጥሉት የሚራወጡ ጽንፈኞች የሚያራምዱት ኦሮሚያ ለኦሮሞ የሚል ከፋፋይና አፍራሽ እንቅስቃሴ ለማንም የማይጠቅም ዘመኑን ያልዋጀ መፈክር ነው።
እርግጥ ነው ፥ መላው ሕዝባችን በየግዜው በተፈራረቁት መንግስታት ሲበዘበዝና ሲጨቆን የመኖሩን ሃቅ ሊዘነጋ የማይችልና ጠባሳውም ያልጠፋ ነው። ነገርግን ትላንትም ሆነ ዛሬ ጥቂት መሳፍንት ባላባትና ኤሊቶች ፥ ከአንዱ ወይ ከሌላው ብሄር በቁጥር ልቀውና የስልጣን ወንበር ይዘው ቆይተው ሊሆን ይችላል። አንድ ብሄረሰብ አጠቃላይ ተጠቃሚና የበላይ ሌላው ጎሳና ነገድ ተገዥ የሆነበት የመንግስት መዋቅር ፥  አልነበረም  ፥ የለምም ።
ምናልባት ዛሬ የትግሬዎች የበላይነት አለ የሚል  ክርክር ሊነሳ ይችላል። እርግጥ ነው በሃገራችን ታሪክ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ በማይታወቅ ደረጃ የሃገሪቱን የስልጣን ፥ የኢኮኖሚ ፥ ወታደራዊና ፥ ማህበራዊ ሴክተሮች ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ በትግራይ ተወላጆች ተይዞ ለመገኘቱ አይን የሚያየው ሃቅ ነው።  ይህም ሆኖ ግን በስመ ትግሬነት ሁሉንም የብሄሩን ተወላጆች ከስልጣኑም ከዘረፋውም እንጥፍጣፊው ያልደረሳቸውን ጨምሮ በአንድ  ቅርጫት ከቶ የመፈረጁ አተያይ ተገቢም አስፈላጊም አይሆንም። ዛሬ ሕዝባችንን አለያይቶ የዘረፋ አገዛዙን ያነበረው የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ፥ ለዚህ አሁን ለደረሰበት ልዕልና ያበቃውን የትግራይ አርሶ አደር ክዶ ብዙ ሺዎች የከፈሉትን የሕይወትና የአካል መስዋዕተነት  ረስቶ  ቁንጮ መሪዎቹና አጫፋሪዎቻቸው በሃብት ላይ ሃብት ሲያካብቱ ፥ የራሳችውን መደብ ለይተው በቅንጡ ቪላ ሲምነሸነሹ ያስተዋልው የትግራይ ሕዝብ አፓርታይድ መንደር ሲል ብሶቱን መግለጹ ይታወሳል።
ዛሬ ለደረስንበ ሃገራዊ ውድቀት አያሌ ምክንያቶች መጥቀስ ይቻላል ነገር ግን እንደ አንድ የዚህ የጥበብና የግሎባልይዜሽን አለም ውስጥ እንዳለ እንድ ሕብረተሰብ ዛሬም በዛው እንዲያውም በባሰ ደረጃ ተዳክመን ለመገኘታችን ተጠያቂው ማን ነው። ሃገራችንን በብረት ክንዱ ደቁሶ የከፋፍልህ ግዛው ያረጀና ያፈጀ ሃገር በታኝና ትውልድ እውዳሚ የጥላቻና የጎሳ አስተሳስብ እየገዛ ያለው የህውሃት ቡድን በዋናነት ሊጠቀስ የሚችል ቢሆንም ፤ ይህ እኩይ ሴራ  በአንድም ሆን በሌላ ምክንያት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ተቀብለን ፤ ዘውገኛ   አመለካከትን ያራባንው ፤  በጠባብና ግትር አመለካክት ተካርን ለዘመናት ተዋልዶና ትጋብቶ በፍቅርና በአብሮነት የኖረውን ሕዝባችንን ጠላቶቻችን  ዘር መሰረት ያደረገ ግንብ ሲያጥሩልን ድንጋይ ያቀብልነው ፤ አጥፊነቱን እያወቅን በዝምታ ያለፍንው ፤ ጊዚያዊ ጥቅምና ጎጠኘነት አይሎብን ጸጥታን የመረጥንው ፤ ሁላችንም የተጠያቂንቱን ድርሻ ማንሳት ይኖርብናል ።
ታሪክ ሠሪው ሠፊው ሕዝብ ነው አዋቂዎች እንዲሉ ፤ የትላንት ገናናነታችን የዛሬው ውድቀታችን ተመስጋኙም ሆነ ተወቃሹ በዘምኑ ያለ ትውልድ  ነው። ቀደምት አባቶቻችን ዘርና ሃይማኖት ቋንቋና ነገድ ሳይሉ ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ቢያንስ በዓለም አደባባይ አንገታችንን ቀና አድርገን እንድንሄድ ታላቅ የስነልቦና ውርስ ትተውልን አልፈዋል።
ዛሬም ያለነው ትውልዶች ከቀደሙት አባቶቻችን መልካሙንና በጎውን ባህልና ፥ እሴት ጠብቀን አሮጌውን ጥለን እንደ ግዜያችን ዘመን የዋጀው ህይወት እንዲኖረን ፤ ለመብትና ነጻነታችን ዋጋ ሰጥተን ራሳችንን አስከብረን ሌሎችንም አክብረን ለመኖር የሚያስችል አስተዳደራዊ ስርዕት በሃገራችን እንዲኖር ፤ አሮጌ አስተሳሰቦችንና የጭቆና መዋቅሮችን እጅ ለእጅ ተያየዘን አፍርሰን የሕዝቦችን መብት የሚያከብር መንግስታዊ ስርዓት ልንመሰርት የሚያስችለንን ትግል በጋራ ልናደርግ ይገባል ።
በአሁኑ ወቅት ሃግራችንን የገጠማት የህልውና አደጋ ከምን ግዜውም የከፋ ሆኖ ይታያል ። የሕወሃት መራሹ ዘረኛና አፓርታይዳዊ አገዛዝ ባለፉት ሁለት አስዕርተ ዓመታት ሲከተለው በቆየው የጥቂት ወገኖችን ፍላጎት ማዕከል ያደረገ የአገዛዝ መዋቅርና የኢኮኖሚ ፖሊሲ የፈጠረው የጭቆናና የችጋር ወጀብ ሃገራችንንና ሕዝባችንን ውድቀት አፋፍ አድርሶዓታል። ይህ ሃገራዊ አደጋ እንዳይከሰት አስቀድመው ድምጻቸውን ያሰሙ የፖለቲካ መሪዎች  የኢኮኖሚ ባለሙያዎችና አክቲቪስቶች የተለያየ ስንካላ ምክንያትና የፈጠራ ወንጀል እየከሰሰ ከሃገራዊ ጉዳይ እንዲገለሉ ሲያደርግ ቆይቷል።
ሕወሃት ላለፉት 25 አመታት ቁልፍ የስልጣን ቦታዎችን ያለተቀናቃኝ ይዞ በመቆየቱ በሕዝባችን ላይ የፈለገውን ሲያደርግ ሊገድበው የሚችል ሳይኖር ቆይቷል። የዚህ የግፍና የጭካኔ ሰለባ የሆነው መላው ህዝባችንን በየግዜው ከማሃሉ ብሶቱን ብሶቴ ብለው በአደባባይ የታገሉትን ፖለቲከኞችን ጋዜጠኞችና የመብት ተከራካሪዎች ሲገልና ሲያስር የቀሩትንም ያለፍላጎታቸው ሃገር ለቀው እንዲሰደዱ አድርጓል።
ሕዝባችን ሕወሃት ባነበረበት አስከፊ የድህነት ሕይወት የሚካሄድበትን ጭቆና በጋራ መከላከያ እንዳይቻል በእለታዊ ኑሮው እንዲጠመድ ሁን ተብሎ ከመደረጉም በላይ አንዳንዴም ገንፍሎ ሲወጣ የተወሰደበት ምህረት የለሽ ጭፍጨፋ አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር አስገድዶት ቆይቷል።  የአገዛዙን ግፈኛ እርምጃ በትግዕስት ችሎና በፍርሃት ተሽብቦ መቀመጡ ይበልጥ ልባቸው እንዲደነድን የሆኑት የህወሃት መሪዎች የከተማውን ሕዝብ በግፍና በገፍ አፈናቅለው ራሳቸው ለፈጠሯቸው የጠፍ ጨረቃ ከበርቴዎች አከፋፍለዋል። በከተማ የጀመሩትን  የመሬት ዝርፊያና ቅርምት  አልበቃ ብሎዐቸው የገጠሩን አርሶ አደር ያለ ተመጣጣኝ ካሳ ከመሬቱ እያፈናቀሉ ለድህነትና ለጎዳና አዳሪነት አድርገውታል።
በኦሮሚያ ከአመት በፊት ይህንን ግፍና በደል ያስተዋሉ የምስኪን ገበሬዎች ዋይታና እንባ ያስቆጫቸው ተማሪዎች በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመቃወም አደባባይ በወጡ ተማሪዎች ላይ እብሪተኛው የሕወሃት አገዛዝ የለመደውን ጭፍጨፋ በማካሄድ ተቃውሞውን ለማርገብ የቻለ መስሎት ቆይቷል
ብሶት ጭቆናና ፥ የመብት ረገጣ እስካለ ድረስ ትግል መኖሩ እይቀርም ። በኦሮምያ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን መሰረት በማድረግ ዳግም ሌሎች በደሎች ገፊ ምክንያት ታክሎበት የፈነዳው አመጽ ከመጀመሪያው በይዘትም በመጠንም ሆነ  በአይነት የተለየ ከመሆንም በላይ ሕወሃትን በጣም የተገዳደረ ፥ ተምሳሌትነቱ ለመላው የሃገራችን ሕዝቦች የሆነ ፥ የጸረ አፈና ትግልን መረብ በጣጥሶ ፤ ሕዝባዊ እንቢተኝነትን ያሳየ ፥ ጠንካራ የለውጥ ሃይል የታየበት ፥ የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት  መግደል እስከ ቻለ ድረስ ለመሞት የቆረጠ የማይፈራ ትውልድ በየአደባባዩ ለፍትህ የተሰዋበት ፥ ወጣት ህጻን አዋቂው በጋራ በሰው በላው የወያኔ አጋዓዚ ወታደሮች  አፈሙዛቸው ስር በድፍረት በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞዎች ሲያሰማ በየማህበራዊ ሚድያዎች ተመልክተናል ።
በኦሮምያ በተለያዩ ቦታዎች ላለፉት ተከታታ ወራት ሲካሄድ የቆየውና አሁንም እንደቀጠለ ያለው ሕዝባዊ ትግል ከዚህ ሁሉ መስዋዕትነት በሗላ እንዳይቀለበስ የፖለቲካ ሃይሎች ና ሲቪክ ተቋማት በመሰብሰብ ፥ ከዘውገኝነት ከፍ ያለ ሃገራዊነት የተላበስ ፤ በፋሽስታዊው የሕወሃት አገዛዝ የተማረረውን መላውን ሕዝባችንን ያሳተፈ የተቀናጀና ፥ በስልት የታጀበ ሕዝባዊ ትግሉ እንዲፋፋምና ለውጤት እንዲበቃ አመራር ለመስጠት በሚያስችላቸው ደረጃ ልዩነታቸውን ወደ ጎን በማድረግ በዚህ ቀውጢ ወቅት ለሕዝብ ያላቸውን አጋርነትን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።
ይህ በኦሮምያ ክልል ያሉ ትንታግ ወጣቶች የተጀመረው መሬት አንቀጥቅጥ የሰላማዊ ትግል ሕዝባዊ ንቅናቄ የሃገራችንን መጻሒ እድል ሊወስን የሚችል እንቅስቃሴ በመሆኑ ፤ ወደ ሌሎችም ክልሎች ተዳርሶ በእንድ የጋራ አጀንዳና መፈክር ስር ታጅቦ ለስር ነቀል ለውጥ ትግሉን ለማብቃት ሁሉም ወገን በየአካባቢው መንቀሳቀስ ይኖርበታል። ህዝባችን የወያኔ አገዛዝ ሰልችቶታል ፥ ከጥቂት የዘረፋው ተቋዳሾች ውጪ ይህንን መንግስት እንዲለወጥ የማይፈልግ ወገን የለም ።ይህንን የሚሊዮኖች የጋራ ብሶት አንቀሳቅሶ ወደ ሕዝባዊ እንቢተኝነት ለመለወጥ የሁሉም ወገን የጋራ ጥረትን ይጠይቃል። ይህም ሲባል ለጥቂት የፖለቲካ ሃይሎች ብቻ የሚተው ሳይሆን ሁሉም ያገባኛል የሚል ዜጋ በያለብት በሚችለውና ባለው እቅም ተሳትፎ የማድርግን ሃላፊንትን በመወጣት የተጀመርው ሕዝባዊ እንቢተኝነት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ የሁኑንም ወገን ጥረት ይጠይቃ ።
እግዚያብሔር ኢትዮጵያን ይባርክል ! !

የኢህአዴግ የተበሉበት 7 ሙዶች

የኢህአዴግ የተበሉበት 7 ሙዶች

Share1  2486  0 
 Share1

eprdf
ከአቡ ባይሳ
1. በኢትዮጵያ፣ ህዝብ ጥቅሙን የሚጎዳ ነገር አልቀበልም በማለት ተቃውሞ ካነሳ ትምክተኛ ሲባል፤ ኢህአዴግ የህዝብ ጥቅም የሚጎዳ ነገር በግድ ካልተቀበላችሁ ብሎ ሙጭጭ ካለ ግን የዓላማ ፅናት ነው::
2. በኢትዮጵያ፣ ህዝብ በኢህአዴግ ላይ ቁጣ ሲያስነሳ ሽፍታ ሲባል፤ ኢህአዴግ ቁጣውን ለማብረድ ንፁሃንን ሲገድል ግን የማያዳግም እርምጃ ነው።
3. በኢትዮጵያ፣ ጋዜጠኛ ሆኖ ኢህአዴግን ከተቸ ወይም ከተቃወመ አሸባሪ ሲባል፤ ጋዜጠኛ ሆኖ ኢህአዴግን ከደገፈ ግን ልማታዊ ጋዜጠኛ ነው::
4. በኢትዮጵያ፣ ኦሮሞ ሆኖ ኢህአዴግን ከተቃወመ ኦነግ፣ አማራ ሆኖ ኢህአዴግን ከተቃወመ ደግሞ ግንቦት ሰባት ሲባል፤ ኢህአዴግ ህዝቡን ሲቃወም ግን መንግስት ነው::
5. በኢትዮጵያ፣ ህዝብ የኢህአዴግን ወታደር ሲገድል ሽፍታ ጋኔን ሲባል፤ የኢህአዴግ ወታደሮች ህዝቡን ሲገድሉ ግን ፀጥታ ለማስፈን ነው::
6. በኢትዮጵያ፣ ጥፋተኞች ተብለው ነገርግን ያለምንም ጥፋት ከኢህአዴግ ጋር ፍርድ ቤት የቆሙ በሙሉ ሲፈረድባቸው፤ ኢህአዴግ ግን ጥፋተኛም ሆኖ ይፈረድለታል
በኢትዮጵያ፣ ህዝብ “ዴሞክራሲ መሰረታዊ ነገር ነው” ሲል፤ ኢህአዴግ ግን ” ዴሞክራሲ ቅንጦት ነው::
7. በኢትዮጵያ፣ ህዝብ ሲሳሳት ኢህዴግ ለምን ተሳሳተ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል ፤ ኢህአዴግ ሲሳሳት ግን ” ከኢህአዴግ ስተት ከብረት ዝገት አይጠፋም……… ” በማለት የተበላበት ሙድ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለመያዝ ይሞክራል………………።

ሰልፈኞች በኮፋሌ የሕወሓት (ኤፈርት) ንብረት የሆነውን የጭነት መኪና በእሳት አጋዩት

ሰልፈኞች በኮፋሌ የሕወሓት (ኤፈርት) ንብረት የሆነውን የጭነት መኪና በእሳት አጋዩት

Share5  2795  5 
 Share6

kofale
(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ ክልል ባለው ተቃውሞ ወደዚያው ክልል እንዳይሄዱ ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው የሕወሓት ኤፈርት እና የአላሙዲ መኪኖች ናቸው:: ይህን ተላልፈው በሚገኙት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ቀድሞ በተሰጠው ማስጠንቀቂያ መሠረት ሰልፈኞች ንብረትነቱ የኤፈርት የሆነውን የጭነት መኪና በ እሳት አነደዱት::
በአጋዚ ሰራዊት ጥይት እየተተኮሰበት በኮፈሌ ተቃውሞውን የቀጠለው ሕዝብ የጭነት መኪናውን ያነደደው ለስ ዓቱ ያለውን ተቃውሞ ለማሳየት ነው ተብሏል::
ሰልፈኞቹ መኪናውን ሲያቃጥ;ኡት በረዳቱና በሹፌሩ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አለማድረሳቸው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል::
በኦሮሚያ ክልል ለሾፌሮች ማስጠንቀቂያ መሰጠቱና የአላሙዲን እና የኤፈርትን መኪኖች የማይነዱ አሽከርካሪዎች ሰልፈኞችን ሲያገኙ ነጭ ጨርቅ ካውለበለቡ ማንም እንደማይነካቸው መግለጹ ይታወሳል::

ነዳጅ በዓለም አቀፍ ገበያ ቢቀንስም በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ዋጋ ሊጨምር ነው

  • ከሰሞኑ የህዝብ ትራንስፖርት ዋጋ ቅናሽ ተደርጎ ነበር
(ዋዜማ ራዲዮ)-የነዳጅ ዘይት ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቢያሽቆለቁልም… ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ሽያጩ በቀድሞው ዋጋ ቀጥሎ ሠንብቷል። በትላልቅ ከተማዎች ለወራት የነዳጅ እጥረት ችግር ለመታየቱ የተለያዩ ምክንያቶች ይቀርባሉ። ከሰሞኑ ደግሞ የነዳጅ ዋጋ ላይ ቅናሽ መደረጉ ታውቋል። የቤንዚን ዋጋ በሊትር 82 ሳንቲም ቅናሽ መደረጉን “ከአህጉሪቱ ትልቁ ቅናሽ” መሆኑ በመንግስት ተጠቅሷል። ያለፉትን ጊዜያት የዓለም ነዳጅ ዋጋ አወራረድና የኢትዮጵያ መንግስት ተመን የተከታተሉ ወገኖች ደግሞ የነዳጅ ዋጋ በሊትር የሚሸጥበት 17 ብር ላይ ቢያንስ የ7 ብር ቅናሽ ማሳየት እንደነበረበት ያስረዳሉ። የነዳጅ ዋጋ ሲቀንስ የትራንስፖርት ታሪፍ መቀነሱ የተለመደ ሆኖ ቢዘልቅም… አሁን ግን በአዲስ አበባ የታክሲ ታሪፍ መጨመር የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁን መረጃዎች ያመላክታሉ።
[ዳንኤል ድርሻ ያዘጋጀውን መሰሉ ንጉስ ታቀርበዋለች፡አድምጡት]
በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ መውጣት መውረድ ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖው ቀላል አይደለም፡፡ የነዳጅ ገበያ መዋዠቅ ፤ በግብርና ምርት፣ በማዳበሪያ፣ በትራንስፖርት እና በሌሎችም ዘርፎች ላይ የዋጋ ለውጥ እንዲከተል አቢይ ሚና ይጫወታል ፡፡ ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል ዓለም አቀፍ ደረጃ ዋጋው ያለማቋረጥ እያሽቆለቆለ ሲሄድ ፤ በነበረበት የዘለቀው የኢትዮጵያ ነዳጅና የትራንስፖርት ዋጋ ከሰሞኑ ተከልሷል፡፡ አምና በዚህ ወቅት አንድ በርሜል ድፍድፍ ዘይት በአማካኝ ይሸጥ ከነበረበት ከ 60 ዶላር በግማሽ ወርዶ በአሁኑ ወቅት ወደ 30 ዶላር አካባቢ ወርዶ እየተሸጠ ነው ፡፡ ይሕ ከተገለጸ ከቀናት በኋላ ግን በአዲስ አበባ በቅርቡ እንደገና የታክሲ ትራንስፖርት ዋጋ ይጨምራል መባሉ ግን ግርታ ፈጥሯል፡፡
በ2006 በጀት ዓመት 10 የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች በመላ ኢትዮጵያ በሚገኙ 660 ማደያዎቻቸው 2.6 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ አከፋፍለዋል፡፡ በ2007 ደግሞ የሃገሪቱ ብቸኛ ነዳጅ አስመጪ ኢንተርፕራይዝ 2.8 ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ወደ ሃገር አስገብቷል፡፡ ከአጠቃላይ ፍጆታ 75 ከመቶ የሚሆነው ቤንዚን የሚገባው ከሱዳን ሲሆን፣ እንደ ኪሮዚንና የአውሮፕላን ነዳጅ የመሳሰሉ ምርቶች ግዢ ደግሞ ከኩዌት፣ ሳዑዲ አረቢያና ሌሎች የባሕረ ሠላጤው ሃገራት ይከናወናል፡፡ የነዳጅ ፍላጎት በ12 ከመቶ እየጨመረ መሄድ ከአቅርቦቱ ጋር አለመመጣጠኑ በየጊዜው ለሚስተዋለው የነዳጅ እጥረት በምክንትነት ይጠቀሳል፡፡
የነዳጅ ዘይት ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአንድ ዓመት ተኩል በማያቋርጥ ሂደት እያሽቆለቁል ሄዶ፣ አሁን ከ30 ዶላር አካባቢ ይሸጣል፡፡ ወደ ፊት 20 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል የሚተነብዩም አሉ ፡፡ ዋጋው ከ18 ወራት በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በሁለት ሦስተኛ መቀነሱን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ዋጋው በዓለም ደረጃ እንዲህ ሲቀንስ በዚያው መጠን በሀገር ውስጥ እንዲቀንስ አለመደረጉ በሕዝብና በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ማስከተሉን ኢኮኖሚስቶች በተለያዩ ጊዜያት ተናግረዋል ፡፡ በሌላ በኩል ግን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ ቤት ሃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ እንደሚሉት መንግስት በነዳጅ ችርቻሮ ዋጋ ላይ ያደረገው የዋጋ ማስተካከያ መረጋጋት እንደፈጠረ፣ በኢትዮጵያ ያለው የነዳጅ መሸጫ ዋጋም በአፍሪካ ዝቅተኛ የሚባል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የንግድ ሚኒስቴር ከየካቲት 2008 መግቢያ ጀምሮ የ1 ሊትር ቤንዚን መሸጫ ከ17 ብር ከ43 ሳንቲም ወደ 16 ብር ከ61 ሳንቲም መውረዱን አሳውቋል፡፡ በግልጽ እንደሚስተዋለው የተደረገው ቅናሽ የ82 ሳንቲም ቢሆንም፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ባሰራጨው መግለጫ ግን የገለጸው በቤንዚን ላይ የ1 ብር ከ35 ሳንቲም ቅናሽ መደረጉን ነው ፡፡ በተመኑ መሰረት ነጭ ናፍጣ (በሊትር) 14 ብር ከ16፣ ኪሮሲን 12 ብር ከ43፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 12 ብር ከ42፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 11 ብር ከ77 ሳንቲም ይሸጣሉ፡፡
የትራንስፖርት ባለሥልጣንም የትራንስፖርት ታሪፍ መቀሱን ገልጿል፤ 1 ብር ከ 40 ሳንቲም የነበረው አጭር ርቀት የከተማ ሚኒባስ ታሪፍ ወደ 1 ብር ከ35 ሳንቲም ሲቀንስ፣ 4 ብር ከ80 ይከፈልበት ለነበረው ርቀት የ20 ሳንቲም ቅናሽ ተደርጎበታል፤ 1 ብር ከ 95 ሳንቲም የነበረው የሚዲ ባስ ዋጋ ወደ 1 ብር ከ 85 ሳንቲም ወርዷል፤ 4 ብር ከ80 ሳንቲም የነበረው አራት ብር ከ60 ሳንቲም ሆኗል። አንበሳ አውቶቡስ እስከ ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ርቀት 1 ብር ከ50 የነበረው የ10 ሳንቲም ቅናሽ ሲደረግበት፣ 8 ብር ከ75 ሳንቲም ይከፈልበት የነበረው ርቀት ላይ ሃምሳ ሳንቲም ተቀንሷል፡፡
የሃገር ውስጥ የነዳጅና የትራንስፖርት ታሪፍ ቅነሳ መረጃው ከተነገረ ከጥቂት ቀናት በኋላ የአዲስ አበባ ከተማ የታክሲ ታሪፍ የሚጨምረው ከነዳጅ ዋጋ ጋር በተያያዘ አይደለም ተብሏል፤ የታክሲ ባለንብረቶች ማሕበራት አቅርበውታል ለተባለው የጭማሪ ጥያቄ የመኪና መለዋወጫዎች እና የጎማ ዋጋ መወደድ የመሳሰሉ ጉዳዮች ተጠቅሰዋል፡፡
በ2002 ዓ.ም የተመሰረተው የአዲስ አበባ ታክሲ ባለንብረቶች ማህበር በአምስት ዞኖች የተዋቀሩ 13 ማህበራት አሉት። ማሕበራቱ የገዢው ፓርቲ ፖለቲካ ማስፈጸሚያ ከመሆን ባለፈ፣ የከተማይቱን ትራንስፖርት ችግር መቅረፍ አለመቻሉም ይነገራል፡፡ በከተማዋ ከ 11 ሺህ ባላይ -ከ12 ወንበር በላይ ያላቸው አውቶቡሶች እና ከ 23 ሺህ የሚበልጡ -ከ11 ወንበር በታች ያላቸው ታክሲዎች ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ 12 ሺህ ባለንብረቶችን በአባልነት ይዘው የነበሩት ማሕበራት በአሁኑ ወቅት ከስድስት ሺህ የማይበልጡ ሰዎችን ብቻ ነው በአባልነት የያዙት፡፡ አብዛኛዎቹ ማሕበራት በስድስት ዓመት ቆይታቸው አንድ ጊዜ እንኳ ኦዲት ሳይደረጉ ሕልውናቸው አለማክተሙ በመንግስት በክፉ ላለመታየታቸው እንደ አብነት ይቀርባል፡፡ እነዚህ ማሕበራት የ“ጎማና መለዋወጫ ዋጋ ተወደደብን” ጥያቄ፣ ለታሪፍ ጭማሪ ጥናት ተቀባይነት ማግኘቱ “ያልተለመደ” መሆኑም ተወስቷል፡፡
የታሪፍ ክለሳውን ያጠናው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ነው ፡፡ ጉዳዩን ለውሳኔ ወደ ፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን እንደላከውም ታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት ዘርፍ አስተዳደር እና ቁጥጥር ሥራን በበላይነት የሚመራው ይኸው የፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ነው፡፡ ከባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የተገኘ ሠነድ፣ የታክሲ ታሪፍ ክለሳ በሶስት ነጥቦች ላይ ብቻ መመስረቱን ያረጋግጣል፡፡ የነዳጅ ዋጋ፣ የተሽከርካሪው ሰው የመጫን ልክ እና ከመነሻ እስከ መድረሻ ያለ ርቀት፡፡ ለ“ሠንደቅ” ጋዜጣ ማብራሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ “እስከዛሬ የታክሲ ዋጋ የነዳጅ ታሪፍን መሰረት ባደረገ መንገድ ብቻ እንደነበር” በመጠቆም በሠነዱ የተጠቀሰውን አሰራር ትክክለኛነት አረጋግጠዋል፡፡ አቶ ያብባል አክለውም የዋጋ ጭማሪው አይቀሬ መሆኑን፣ በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በሚወሰንበት ወቅት፣ ጭማሪው በተጠቃሚው ህዝብ ላይ አለበለዚያም ደግሞ መንግስት ላይ ሊያርፍ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ አስተያየት ሠጪዎች ደግሞ መንግስት ወጪውን የመሸከም ፍላጎት ቢኖረው መረጃው አደባባይ እንዲወጣ ባላደረገ ነበር ይላሉ፡፡ የዓለም ነዳጅ እየቀነሰ ሲሄድ የሚገባውን ታሪፍ ቅነሳ ያላደረገው መንግስት፣ አሁን ሊጨምረው ያቀደው የታሪፍ ጭማሪ አሳማኝ ምክንያት የማይቀርብበት መሆኑም ተነግሯል፡፡
በ marketwatch.com መረጃ መሰረት በሕዳር 2006 ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል ከ80 እስከ 90 ዶላር ይሸጥ ነበር ፡፡ በጥር 2007 ግን ወደ 52 ዶላር ወርዷል፡፡ ከጥር 2007 አንስቶ እስካለፈው ወር ድረስ የቀጠለው የሃገር ውስጥ ነዳጅ መሸጫ ታሪፍ ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ተመሳሳይ እንደነበር ተጠቅሷል፤ ከአምስት ዓመት በፊት የዓለም ነዳጅ ዋጋ በበርሜል 100 ዶላር ነበር፤ ያኔ አንድ ሊትር ቤንዚን በ17 ብር ከ88 ሣንቲም ይሸጥ ነበር፡፡ እስካለፈው ወር ድረስ የዓለም ገበያ ዋጋ ከ30 እስከ 35 ዶላር ሆኖም፣ በአገር ውስጥ ቤንዚን በሊትር 17 ብር 43 ሣንቲም ሲሸጥ ቆይቷል፡፡
ዋጋው ባሽቆለቆለበት ወቅት መንግስት ቢያንስ የነዳጅ ዋጋን በሊትር እስከ 9 ብር ማውረድ እንደነበረበት ያስረዱ ዓለም አቀፍ ተቋማት መንግስት በእነዚህ ጊዜያት ከነዳጅ ሽያጭ ከፍተኛ ትርፍ እንደሰበሰበ አጋልጠዋል፡፡ በዓለም አቀፉ የነዳጅ ዋጋ መውረድ መጠን ከታየ፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የነዳጅ ችርቻሮ ዋጋ በሊትር በ5 እና በ6 ብር መሸጥ እንደነበረበት የሚያብራሩ አካላት እንደገና የታሪፍ ጭማሪ ከማድረግ ይልቅ “ትክክለኛ የነዳጅ ቅናሽ ማድረግ አለያም ለታክሲዎች ብቻ የልዩ ቅናሽ የነዳጅ ኩፖን ማዘጋጀት መሰል አማራጮች መታየት አለባቸው” የሚል ሃሳብ ይሰነዝራሉ፡