Thursday, 18 February 2016

በምስራቅ ሐረርጌ ፌደራል ፖሊስ ሁለት አርሶ አደሮችን ገደለ – በጉራዋ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ተቃጠለ

Share1  511  0 
 Share0(ዘ-ሐበሻ) ትናንት የ60 ዓመት አዛውንት በተገደሉበእት የምስራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ወረዳ ዛሬ ደግሞ 2 ገበሬዎች በፌደራል ፖሊሶች መገደላቸው ተዘገበ::
የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች እንዳሉት ማሃዲ ሳኒ እና ሳፊ ኢብሮ የተባሉት አርሶ አደሮች በፌደራል ፖሊሶች የተገደሉት ዛሬ በከተማዋ በተደረገ ህዝባዊ ተቃውሞ ነው::
በምስራቅ ሐረርጌ በተከሰተ ሕዝባዊ ተቃውሞ በርካታ ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን አብዛኞች በህክምና ላይ እንደሚገኙ ታውቋል:: በዚሁ በጉራዋ ወረዳ ፌደራል ፖሊስ ትናንት እና ዛሬ የፈጸመውን ግድያ የተቃወሞ የአካባቢው ነዋሪዎች የፖሊስ ጽህፈት ቤትን ማቃጠላቸው ተሰምቷል:: ሰለፈኞቹ ፖሊስ ጣቢያውን ካቃጠሉ በኋላ እስረኞችን ለማስመለጥ መሞከራቸው ሲገለጽ እስረኞች ያምልጡ አያምልጡ ዘ-ሐበሻ ለማጣራት ያደረገችው ጥረት አልተሳካም::
በሌላ ዜና በም ዕራብ አርሲ የተነሳው የሕዝብ ተቃውሞ በኢዶ ከተማ ቀጥሎ ሕዝቡ ከፌደራል ፖሊስ ጋር ተፋጦ ይገኛል:: በተለይ የም ዕራብ አርሲ ግጭትን ወደ ዘር ግጭት ለማስፋት አንዳንድ ወገኖች ተቃውሞውን በመጠቀም እያደረጉት ያለውን ጥረት ይህን ትግል የሚመሩ ሰዎች ሊያስቡበት ይገባል የሚሉ የአካባቢው ነዋሪዎች አሉ::

የህወሓትን‬ አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ሄሊኮፕተር ይዘው ከሀገር የወጡት እነ ሳሙኤል ግደይ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ) ሳሙኤል ግደይ፣ ፀጋ ዘአብ ግደይ እና ቢልልኝ መኮንን የህወሓትን አገዛዝ በመቃወም ኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር በማብረር ከምስራቅ አየር ምድብ ድሬዳዋ በውሎ የጠፉት በ2007 ዓ.ም ሲሆን የህወሓት አገዛዝ የጦር ፍርድ ቤት የካቲት 4 2008 ዓ.ም በሌሉበት በሞትና እድሜ ልክ እስራት ቀጥቷቸዋል፡፡
የሄሊኮፕተሯ ዋና አብራሪ ሳሙኤል ግደይ በሞት ሲቀጣ ፀጋ ዘአብ ግደይ እና ቢልልኝ መኮንን የእድሜ ልክ እስራት ተበይኖባቸዋል፡፡
ከእነ ሳሙኤል ግደይ በፊትም በ1993 ዓ.ም ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ ኤል-39 ተዋጊ ጀት እያበረረ ከመቀሌ ተነስቶ ኤርትራ መግባቱ፤ መቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬ እና መቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ ኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር እያበረሩ ጅቡቲ ማረፋቸው የሚታወስ ነው፡፡ መቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬና አብዮት ማንጉዳይ በጅቡቲ መንግስት ለህወሓት ተላልፈው ተሰጥተው የእድሜ ልክ እስራት እና የ15 አመት እስር ተፈርዶባቸው መቶ አለቃ አብዮት የእስር ጊዜውን ጨርሶ በመፈታቱ በአሁኑ ጊዜ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅሎ ኤርትራ በረሃ እንደሚገኝ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡
የኤም.አይ-35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር አዛዥ እና የበረራ አሰተማሪ የነበረው ሻለቃ አክሊሉ መዘነም ከአመታት በፊት ስርዓቱን በመቃወም ወደ ኤርትራ መጥቶ አርበኞች ግንቦት 7ን በመቀላቀል ትግል ላይ ይገኛል፡

ብሔራዊ ጭቆና የትግላችን መዘዉር ሆኖ ይቀጥላል! | የሳዲቅ አህመድ የቪዲዮ ዘገባ

ህወሃት መራሹ መንግስት ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማሳሳትና ለማከፋፈል፤ጥቅሙን አስከባሪ በሆነ ጋዜጣ ላይ ያወጣዉን የሐሰት መረጃ አስመልክቶ ድምፃችን ይሰማ ያወጣዉ መግለጫ በድምጽና በቪድዮ ቢቢኤን እስቱዲዮ ዉስጥ ተቀናብሯል። መረጃዉን በማየት፣በማዳመጥና ለሌሎችም በመላክ ሐላፊነቶን ይወጡ።


ሰልፈኞች በቡልቡላ ከተማ የአላሙዲ ንብረት የሆነው የነዳጅ ታንከር አቃጠሉ


tankTrank 1
(ዘ-ሐበሻ) ንብረትነቱ የአላሙዲን የሆነው ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ንብረት የሆነው የነዳጅ ታንከር በኦሮሚያ ክልል በቡልቡላ ከተማ ተቃጠለ::
እንደምንጮች ገለጻ በኦሮሚያ የወርቅ ማዕድኖችን እና የተለያዩ የሕዝብ ንብረቶችን ወደራሱ አስገብቷል ተብሎ ተቃውሞ የቀረበበት የአላሙዲን ንብረት በሆነው ሜድሮክ ኢትዮጱያና በሕወሓት አስተዳደር ሥር ያሉትን ንብረቶች ሁሉ ሕዝቡ እንዳይጠቀምና ከአካባቢውም ጠራርጎ እንዲያስወጣቸው በቀረበው ጥሪ መሠረት በተለያዩ ቦታዎች እርምጃ ሲወሰዱ ቆይተዋል::
በትናንትናው ዕለትም እንዲሁ ንብረትነቱ የትራንስ ኢትዮጵያ የሆነ ቦቴ የተቃጠለ ሲሆን በዚያው ምሽት በቡልቡላ ከተማ ሰልፈኞች የአላሙዲን የነዳጅ ታንከር መቃጠሉን የተሰራጩት ዜናዎች አስታወቀዋል::
በኦሮሚያ የሚገኙ የሕወሓት የንግድ ተቋማትና እንዲሁም የሼህ መሀመድ አላሙዲ ንብረት የሆኑ ድርጅቶች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ከስር ዓቱ የደህንነት ተቋማት ት ዕዛዝ እንደደረሳቸው የሚያስታውቁት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በተለይም በአሁኑ ወቅት መንግስት ለአላሙዲ ድርጅቶች በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስታውቀዋል::
Share1  1776  3 
 Share1

 English በአማርኛ ይፃፉ