Thursday 28 November 2013

‹‹ሰው ለሰው›› የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትእዛዝ ስክሪፕቱን እንዲቀይር ተገደደ፡፡

በኢትዩጵያ የቴሌቪዥን ድራማ ታሪክ በረዥምነቱ ቀዳሚውን ቦታ በመያዝ የሚታውቀው ሰው ለ ሰው ተከታታይ ድራማ 109 ክፍሎች ያህል ከተላለፈ በኃላ፣ ሰዎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች የድራማው ተዋንያን የሆነውን በትወና ስሙ አስናቀ የተባለውን  ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር  በማመሳስል ገጸባህሪውና ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለስልጣናትን በገንዘብ ይገዛሉ ፤ ፍትህን ይረግጣሉ ፤ በሰው ህይዎት ይነግዳሉ፡ ፤ ሰው ያስገድላሉ፤ ህዝብን ያስለቅሳሉ ፤ በወንጀል ይነግዳሉ፤ ሰው በላ እና ነፍሰ ገዳይ አምባገነን ናቸው ሲሉ እንደሚተቹዋቸው ይታወቃል፡፡
ጉዳዩ ያሳሰባቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን ድራማው የመንግሰትን ስራ እያንቋሸሸ ፤ ከመንግስት ፍላጎት ውጭ እየሄደ በመሆኑ እንዲቀየር የኢቲቪን አስተዳዳሪዎች ማዘዛቸውን የወስጥ ምንጮች ገልጸዋል።
ውስጥ አዋቂዎች ድራማው የወ/ሮ አዜብ መስፍንን ታሪክ የተከተለ እና አብዛኛውን የመንግስት ባለስልጣናት የመክበሪያ ዘዴ የጠቆመ በመሆኑ መንግሰት እንደ ነገሪ ሰሪ ተመልከቶታል ብለዋል፡፡
ጉዳዩ ዙሪያ የኢቲቪን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

በጅጅጋ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ለማድመቅ የተቀረጸው የመለስ ዜናዊ ሃውልት ፈረሰ

-የሶማሌ ክልል 8ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ታከብራለች መባሉን ተከትሎ የክልሉን ዋና መቀመጫ ጅጅጋን  አርቲስቶች እና የመንግስት ባለስልጣናት በየጊዜው እየጎበኙዋት ነው።
ለበዓሉ ዝግጅት የተመደበለትን 31 ሚልዩን ብር ከዝግጅቱ በፊት ቀድሞ ያጠናቀቀው የሶማሌ ክልል መንግስትን ለበአሉ ማክበሪያ እና ማድመቂያ በማለት ተጨማሪ 14 ሚሊዮን ብር ጠይቋል።
ለበዓሉ ማስተናገጃ የሚሆን ስቴዲየም በመገንባት ላይ የተጠመደው ክልሉ ፤ በገጠመው የበጀት እጥረት የተነሳ በጅምር ባለ ስታዲየም በዓሉን ያከናውናል፡፡ የፌድሬሺን ምክር ቤት ባካሄደው ግምገማ ከ10 ሚልየን ብር በላይ ገንዘብ ያለ አግባብ የባከነ መሆኑን አረጋግጦዋል፡፡ በተመደበው በጀት ዘወትር ከስራ ስዓት ውጭ የከስዓት ጊዜን በመጠቀም የክልሉ ባለስልጣናት ገንዘቡን ጫት ቅመውበታል ሲል ምክር ቤቱ ትችት አቅርቧል።
የፌዴሬሺን ምክር ቤት በበኩሉ የተለያዩ ባለስልጣናትና አርቲስቶች የሶማሌ ክልልን ለማስጎብኝት በሁዱበት ወቅት ለመጓጓዝያ እና ለመስተንግዶ  200 ሚልየን ብር  ወጭ አውጥቻለሁ ብሏል፡፡
በዓሉን ለማድመቅ እና የመንግስት ባለስልጣናትን ለማስደሰት በማሰብ በ 243 ሺ ብር ወጭ በጅጅጋ ከተማ ለመለስ ዜናዊ ተብሎ የተቀረፀው ሃውልት እንዲፈርስ ተደርጓል፡፡ በፊደራል አመራሮች ቁጣን የቀሰቀሰው ይህ ምስል ፈጽሞ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ምስል ጋር የማይመሳሰል እና ፈጽሞ  በመልክ እና በቁመና የማይገናኝ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ አስተያየት ሰጪዎች ሀውልቱ ከመለስ ይልቅ ግርማ ወልደ ጊዩርጊስን ይመስላል ሲሉ ተሳልቀዋል፡፡ የክልሉ ባለስልጣናት ሃውልቱ የተሸፋፈነበትን ሸራ እንደገለጡ ከፌደራል መንግስቱ ባለስልጣናት በደረሰባቸው ከፍተኛ ትችት ወዲያው በሸራ ሸፍነው አፍርሰውታል። ቀራፂው  በቁጥጥር ስር ውሎ ካለፉት ሶስት ሳምንታት ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛል፡፡
ለህዳር 29ኙ በአል ከተዘጋጁ ባነሮች መካከል ባቡር ፤ አባይ ግድብ ፤ ቤቶች እና ህገ መንግስት ይገኝበታል። ይህ ባነር ለህዝብ ተደብቆ ከቆየ በኃላ በህዳር 28 ይመረቃል፡፡

ተስፋ የቆረጡ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰሙ

-በርካታ ተስፋ የቆረጡ ኢትዮጵያውያን መዲናህ ከተባለው መጠለያቸው  ግንብ እየዘለሉ  ወደ ታይባን ዩኒቨርስቲ ካምፓስ እንደገቡ የአገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል።
ብርጋዴር ፋህድ ቢን አሚር አል ጋናም እንደገለጹት 15 ኢትዮጵያውያን ወደ ዩኒቨርስቲው ግቢ የገቡ ሲሆን የጸጥታ ሀይሎች ኢትዮጵያውያኑን በመያዝ ወደ ማጎሪያ ካምፓቸው ልከዋቸዋል።
ኢትዮጵያውያኑ በሰዎች፣  በመኪኖች ወይም ህንጻዎች ላይ ጉዳት እንዳላደረሱ የሳውዲ ዩኒቨርስቲ ቃል አቀባይ ገልጸዋል፡
ኢትዮጵያውያኑ ወደ አገራቸው ለመመለስ ቪዛ የማግኘቱ ሂደት ስለዘገየባቸው ተቃውሞ ለማድረግ መገደዳቸው ታውቋል።
ታይባህ ዩኒቨርስቲ መዘጋቱም ታውቋል።
በኢትዮጵያውያን ላይ ስለደረሰው ጉዳት ለማወቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። በሳውድ አረቢያ ውስጥ አሁንም በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ በመጠባባቅ ላይ ይገኛሉ።

የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በታችኛው ኦሞ የተፈጠረውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደሚመረምር አስታወቀ

-በአህጉሪቱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ አካል ነው የተባለው ኮሚሽን፣ ኢትዮጵያ ለስኳር ልማት በሚል በታችኛው ኦሞ አካባቢ የሚገኙ ዜጎችን በማፈናቀል እየፈጸመችው ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በፍጥነት እንድታቆም ጠይቆ፣ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንደሚያደርግም ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት በአካባቢው በሚኖሩ ብሄረሰቦች ላይ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ግርፋት እና እስራት መፍጠሩን የመለከተው ኮሚሽኑ፣ ለኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ በማድረግ የሚታወቁት ምእራባውያን ጉዳዩን አይተው እንዳላዩት ማለፉን አጋልጧል።
ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ዳይሬክተር ስቴቨን ኮሪ  ኢትዮጵያና ተመሳሳይ ችግር የሚፈጥረው ቦትስዋና ዜጎቻቸውን ማፈናቀላቸውን ካላቆሙ የአለም ህዝብ ህገወጥ አገሮች ብሎ ይፈርጃቸዋል ብለዋል።

Tuesday 26 November 2013

በሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በመቃወም የሚደረጉ ሰልፎች ቀጥለዋል

-በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአፍሪካ ፓርላማ  ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በተቃውሞው ላይ የተገኘችው የኢሳት የደቡብ አፍሪካ ተባባሪ ዘጋቢ ዝናሽ ሀብታሙ እንደገለጸችው በሰልፉ ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ኢትዮጵያውያን ታሰትፈዋል።
ተቃውሞውን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ምክትል ሊ/መንበር አቶ ንብረት ጌታሁንም ህዝቡ በተቃውሞው ላይ ተገኝቶ ስሜቱን በከፍተኛ ሁኔታ ገልጿል ብለዋል በተመሳሳይ ዜናም የአፋር ሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ድርጅት፣ የሉቅማን ሙስሊም ማህበር እና የኢትዮጵያ ታስክ ፎርስ በአውሮፓ በቤልጂየም  ብራሰልስ በሳውድ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት  ተቃውሞ አሰምተዋል። በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በዚህ ተቃውሞ በሳውዲ አረቢያ ለደረሰው ሰቆቃ መንግስት ተጠያቂ ነው፣ መንግስት በሳውድ አረቢያ ስደተኞች ስም መነገዱን ያቁም፣ መንግስትን እንፋረዳለን፣ በህዝብ ያልተመረጠ መንግስት ለዜጎች አይቆምም፣ የሳውዲ መንግስት አፈርንብህ የሚሉና  ሌሎችም መፈክሮች ተሰምተዋል።
የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያስተባበሩ የነበሩት ለኢሳት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በጃፓንም ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀሙ

የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ የሚያምኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር  እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ  በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ    10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የመንግስት 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመቷል ብሎአል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው ክፈለ ጦር ላይ በተመሳሳይ ሥፍራ  ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል።
በሕዳር 13/2006 ዓ.ም የኢሕአግና የጋህነን ሰራዊት በወሰዱት ድንገተኛ ወታደራዊ ጥቃት 66 ወታደሮችን ገድለው 113 በማቁሰል እንዲሁም ቁጥራቸው የበዛ የጦር መሳሪያዎችን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርከዋል።
በውጊያው ከሞት ተርፎ ለከባድ ቁስልና የአካል ጉዳት የተዳረገው የ24ኛ ክፈለ ጦር አባላትን ከሁመራ አንስቶ እስከ ትግራይ የሕክምና ማዕከሎች ማጋጋዝ ዋነኛ ተግባሩ ሆኗል ብሎአል ግንባሩ ለኢሳት በላከው መግለጫ።
አርበኞች ግንባር እና የጋምቤላ ህዝብ ንቅናቄ አገኘው ባሉት ድል ዙሪያ የመንግስትን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ።

በሳውድ አረቢያ ምድር በኢትዮጵያ ሴቶች ላይ የሚፈጸመው ግድያ እና አስገድዶ መድፈር እንደቀጠለ ነው

-በሪያድ የሚታየው ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን።
እሁድ  2  ኢትዮጵያን ሴቶች መክረይመንታ ሸባቢያ በሚባል ቦታ ላይ በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መገደላቸውን በአይኔ ተመልክቻለሁ ያሉ የሪያድ ነዋሪ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ሌላ ኢትዮጵያዊት ደግሞ በአካባቢው ከተሰማሩት ወታደሮች ጋር ስትነጋገር በብረት ተመትታ መሞቷን እና አንዲት ኢትዮጵያዊትም እንዲሁ የቀኝ እጇ ተቆርጦ በአካባቢያቸው እንደምትገኝ እኝሁ የአይን ምስክር ይገልጻሉ ከዚህ የከፋና የብዙ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ለአደጋ ያጋለጠ ክስተት መኖሩንም ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያን ይገልጻሉ። ወደ 50 የሚጠጉ መኪኖች ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉ ሰዎችን አሳፍረው አሚራ ኑራና መለዝ የሚባል ቦታ ላይ ላለፉት 17 ቀናት ቆመዋል። ሰዎቹ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸዳዱት መኪኖቹ በቆሙበት አካባቢ በመሆኑ አካባቢው በሽታ መበከሉን የአይን እማኞች ይናገራሉ። ህጻናት በተቅማጥ በሽታ እየተጠቁ መሆናቸውንም የአይን እማኞች ይናገራሉ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሪያድ አካባቢ በተፈጠረው ስሜት ህጋዊ ወረቀት ያላቸው ኢትዮጵያውያንም ስራ እንዳይዙ እየተደረገ በመሆኑ መቸገራቸውን ህጋዊ ወረቀት የያዙ ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።
ምንም እንኳ የኢትዮጵያ መንግስት ለማረጋገጥ በማይቻልበት መንገድ ከ20 ሺ በላይ ሰዎችን ማምጣቱን ቢናገርም በሪያድ መንፉሀ ካምፕ ውስጥ ያሉት ኢትዮጵያውያን ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነው።

Monday 25 November 2013

ህወኃት ወያኔ በሳዉዲ ዜጎቻችን ብቸኛ ተጠያቂ ነዉ

November 24, 2013
Author Roba Pawlos
ሮባ ጳዉሎስ
ኢትዮጵያ የህዝቦችዋ መኖርያና ሀገሪቷ ለህዝቦችዋ መሆንያለባትን እንዳትሆን ላለፉት ፪፪ አመታት ሲወጠን እና ሲደረግ የነበረ የኢሰብአዊና አረመኔያዊ የህወኃት ወያኔ የገማ የዘር ፓለቲካ ዉጤት መልስ ነዉ በሳዉዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ የተፈፀመዉ መታረድና መደፈር።
እኩልነት መቻቻል ሰላም ፍትህና ነፃነት ዜጎችን በመከልከል በሀይማኖት በዘርና በጎሣ በመከፋፈል እየነጠለ በመምታት እንዲሁም ለይቶና ረግጦ መግዛት የማይችልባቸዉን ቦታዎች በኢንቨስትመንት ስም ለዉጪ ወራሪዎች በመስጠት ዜጎችን በዘመናዊ ባርነት ስር በመጣል ከገዛ መሬታቸዉ በማፈናቀልና በማሳፈን ሀገሪቷ ላይ ያለዉን የስራ እድል ለዉጭ ወራሪዎች እና ለገዳዮቻችን የሳውዲ ዜጎች ጭምር በመስጠት ወጣቱን ገሎ አስሮ አሰድዶ አዋርዶናል።በዚህ ስቃይ ዉስጥ ሀገሪቷ ላይ መኖር እና የመስራት ተስፋ ያጡ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የገማ እና የበሰበሰ የህወኃት ፓለቲካ ሽሽት ጭምር ያላቸዉን ብቸኛ አማራጭ በመጠቀም በህጋዊም ሆነ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ዜጎቻችን ያለጠያቂ በአለም ላይ ተበትነዋል።ከዚህም ዉስጥ በብዛት ሴት እህቶቻችን የሚኖሩባት እና ህወኃት ወያኔ እራሱ በዘመናዊ ባርነት ተስማምቶ በፓስፓርት ጭምር ወደ ሳዉዲ አረቢያ የላካቸዉ ዜጎቻችን ተጠቃሽ ናቸዉ። ኢትዮጵያዉያን እህትና ወንድሞቻችን በአረብ ምድር ላይ እስራኤል የመን እና ግብፅን ጨምሮ አስከፊ ችግር እና የህይወት መስዋእትነት ሲከፍሉ የህወኃት ወያኔ መንግስት የሚፈልገዉና የዜጎቻችን በአረብ ሀገር መታረድ የሸተተ የፓለቲካዉ እድሜ ማስቀጠያ ዉጥን ሴራ ስለሆነ ዝም ሲል የኖረና የሳዉዲ አረቢያን ዘግናኝ ድርጊት የደገፈዉ፣ያስጀመረዉም ህወኃት ወያኔ ነዉ ።
በሌላም በኩል ዜጎቹ በሕገ-ወጥ ደላሎች አማካይነት በሁሉም የጎረቤት አገሮች በኩል ወደ ተለያዩ ሀገራት በመሰደድ መጉላላትና አደጋ ሲደርስባቸው የወያኔ/ህውሃት የሕገ-ወጥ ደላሎች ቁጥር መጨመሩን በልማታዊ ጋዜጠኞቹ በሚዲያው ከሚነግረን በቀር ጉዳዬ ብሎ ችግሩን ከምንጩ ለመቅረፍ የሚወስደው እርምጃ ባለመኖሩ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን መወጣት ያቃተው መሆኑ በግልፅ አሳይቶናል፡፡
በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ በየሀገሩ የሚደርሰው ሰቆቃ አዲስ ባይሆንም በቅርብ ግዜ ወዲህ በማዕከላዊ ታንዛኒያ በጫካ ውስጥ ተጥለው የተገኙ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ እጅግ በጣም አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው፡፡ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከሀገራቸው ከወጡ በኋላ በማላዊ አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሉ በኮንቴይነር ተጭነው በታንዛኒያ በኩል ሲጓዙ አየር አጥተው በመታፈናቸው 43ቱ ሕይወታቸው ሲያልፍ በርካቶቹ ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡ ይህ ድርጊት የወያኔ/ህውሃት መንግሥት በካድሬያዊ የአፈና አገዛዙ ከቀዬአቸው እያፈናቀለ በሰው ሀገር ለስቃይ የሚዳርጋቸው ዜጎች ስፍር ቁጥር የሌለው መሆኑን ማሳያ ነዉ።
ግንዛቤ ማጣትም ሆነ ገንዘብ ማጣት ሁለቱም ደህነት ነው፡፡ ስደት በየትም አልነው በየትም አሽሞነሞነው ስደት ድህነት ነው፡፡ ድህነት ደግሞ የብልሹ ፖለቲካ ስርዓት ውጤት ነው፡፡ ሰላም አጥቶ መብቱ ተረግጦ የሚሰደደው ኪሱ የዳለበውም ቢሆን የሰላም ደሀ ሆኖ ነው፡፡ ሌላ ታፔላ መለጠፉም ሆነ ማሽሞንሞኑ ስደትን አያጠቁረውም አያቀላውም፡፡ ጥናት አጥንተናል ባዮችም ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ እንዲሉ ነውና ይልቅ የመፍትሄ ሀሳብ አቅርቡ…ህገ-ወጥ ደላሎች ያላቸውን ተዋረድ እና ሰንሰለት መናገሩ ብቻ ምን ፋይዳ አለው፡፡ እዚህ የመን፣ሳውዲ ያለ ኤምባሲ ስንት የሚያዙትን ህገ-ወጥ ደላሎች ሲፈቱ ዝም ከማለት ውጭ ምን አደረገ? አሁን በቅርቡ ያየነው እንኳን ስልሳ ኢትዮጵያዊያንን አፍኖ የተያዘ ሰው ሲፈታ ዝም አይደል ያሉት ፡፡ አሁንስ ቢሆን በየመን ህገ-ወጥ አጓጓዦች ከኤምባሲው ምን ደረሰባቸው ገብተው ይወጣሉ፡፡ እጅና ጓንት ናቸው፡፡ የመንግስት ስራ ሁሉ የይምሰል ነው፡፡
በመጨረሻም ወያኔ የሳዉዲዉ የዜጎቻችን በደል የራሱ ስራ ስለ ነበረ ከችግሩ ተርፈዉ በተመለሱና ልጆቻቸዉ የታረዱ ባቸዉን እናትና አባቶች ጭምር ለተቃዉሞ በወጡበት በገዛ ሀገራቸዉ እንደ እባብ የቀጠቀጠዉ ያሳዝናል ያቃጥላል ያንገበግባል ነገር ግን የዜጎቻችን እንባና ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም።
ሞት ለሀይለማርያም ደሳለኝ ሞት ለቴዉድሮስ አድሀኖም ሞት ለህወኃት ወያኔዎች።

ተዋርደን አንቀርም!!! ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)

ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡
ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡

ዕንባሽ ተናገረ! አሥራዯው (ከፈረንሳይ)

ዘሇላ ዘሇላ ደብ ደብ በሚሇው፤
ጉንጭሽን ሸርሽሮ ቁልቁል በሚፈሰው፤
ሳግ እንቅ እድርጎ በሚተናነቅሽ፤
በ’ንባሽ እያጠቀስኩ ስንኝ ቋጠርኩልሽ፤
ቃል ኪዲን ነውና አንብቢው አዯራሽ::

ዕንባሽ ተናገረ !
ሆሄያት ቆጠረ፤
ውስጥሽን ፈልፍሎ እየመረመረ፤
ቃላትን አምጦ ስንኞች ቋጠረ፤
ምሥጢሩን አወራ - መዯበቁ ቀረ ::

አይምሮሽን ነድሎ - ልብሽን ሰርስሮ፤
ቆፍሮ ዐይኖችሽን - ጉንጭሽን ሸርሽሮ፤
አንጀትሽን ሞሽልቆ - ጨጓራሽን ልጦ፤
ቁልቁል በሚወርዯው ዯረትሽን አቋርጦ፤
ሳግ እንቅ እድርጎ በሚተናነቅሽ፤
በሚፈልቀው ኩሬ - እያጠቀስኩ በንባሽ፤
ጥቂት ቃል ጻፍኩልሽ፤
አንብቢው አዯራሽ ::

ዕንባሽ ተናገረ !
ፊዯላት ቆጠረ፤
ውስጥሽን ፈልፍሎ እየመረመረ
ቃላትን አምጦ ስንኞች ቋጠረ፤
ምሥጢሩን አወራ - ጮሆ ተናገረ ::



  2
ሃዘንሽ ፈንክቷት ብዕሬ ቆሰሇች፤
ከግራ ወዯቀኝ እየተወራጨች፤
ድምጿን ከፍ አድርጋ - እሪ ብላ ጮኸች፤
ባንቺ ዕንባ ተጠምቃ - ማተቧን ቋጠረች፤
ፊትሽን ሇማበስ - ሮጠች ተሯሯጠች፤
ሃቅሽን አውጥታ - ጻፈች ቸከቸከች::

ያይኖችሽን ኩሬ ነድሎ በሚፈልቀው፤
ጅረት እንዯ ዓባይ አቀብ በሚፈሰው፤
በሚገነፍሇው እያጠቀስኩ በ’ንባሽ፤
ይችን ጥቂት ስንኝ ላንቺ ቋጠርኩልሽ፤
በ’ንባ የጨቀየ የራሰ ነው ብሇሽ፤
እንዲትጠየፊ አንብቢው አዯራሽ ::

ዕንባሽ ተናገረ !
ፊዯላት ቆጠረ፤
ውስጥሽን ፈልፍሎ እየመረመረ
ቃላትን አምጦ ስንኞች ቋጠረ፤
ምሥጢሩን አወራ - ትንቢት ተናገረ ::

እናም :
ጻፍኩልሽ ! ጻፍኩልሽ ! እህቴ ልንገርሽ፤
እያጠቀስኩ በ’ንባሽ፤
ተመኝቼ ሳቅሽን ዲግም እንዲታሇቅሽ፤
እህቴ!


በሳውዱ አረቢያና፤ በመላ አረብ አገራት፤ ሇሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼ፤ ማስታወሻ ትሆን ዘንድ
የተቋጨች ::

ጥቅምት 21/2006 ዓ.ም (October 31/2013)

Sunday 24 November 2013

የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች በአዛዦቻቸው ላይ ውጥረት ፈጥረውል::

መኮንኖቹ በትምህርት በስራ እና በማእረግ እድገት በቤተሰብ እንክብካቤ በደሞዝ ጭማሪ እና በሕገመንግስታዊ የህዝብ መብቶች ዙሪያ ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ወታደራዊ ጥቅማ ጥቅሞች ለአንድ ብሄር አባላት ብቻ ተመድበው እየተሰራባቸው ነው ከተማ ውስጥ ታጥቀው የመሸጉ እና ህዝብን እያጠቁ የሚገኙት የአንድ ብሄር አባላት ናቸው እንዱሁም ከሃገራዊ ጥቅም ይልቅ የፓርቲ ጥቅም እየተስተዋለ ነው:ወታደሩ የጦር ሳይንስን እና ዲሲፕሊን በጎደለው መልኩ እየተስተዳደረ ነው በሰራዊቱ እና በሃገሪቱ ሁሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ሽፋን እና ማዘናጊያ በማድረግ የሙስና እና የዘረፋ መስፋፋት መልስ ሊያገኝ ይገባዋል ጄኔራል መኮንኖች አላቸው የተባለው ንብረት ይጣራ በሃገሪቱ የፖለቲካዊ እና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ሊመለሱ ይገባል የሚሉ እና ተመሳሳይነት ያላቸውን ጥያቄዎች ማንሳታቸው ታውቋል::የመከላከያ አባላቱ በኑሮ ውድነት እና በተቃዋሚዎች ህገመንግስታዊ መብቶች ላይ ያነሱት ጥያቄ አዛዦቹን ያስደነገጠ ከመሆኑም በላይ በአንድ ብሄር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እስከመቼ የሚለውም ጥያቄ መመለስ አለበት በሚል የእግር እሳት እየሆነባቸው ነው::
ይህ ከዚህ ቀደም የተጀመረው እና አሁንም በሰሜን እዝ እና በምስራቅ እዝ የተከሰተው የሰራዊቱ ህገመንግስታዊ ጥያቄ እና የጥቅማ ጥቅም አቤቱታ በመላው ሃገሪቱ ተስፋፍቶ በሁሉም የሰራዊት እዞች ውስጥ ጥያቄው መነሳቱን ምንጮቹ አመልክተዋል::በተለያዩ ጊዜያት እየተንከባለለ የመጣው ይህ የሰራዊቱ አቤቱታ እጅግ አደገኛ አዝማሚያ እያሳየ ሲሆን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እንዲወገድ እና ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥያቄዎች ገፍተው መምጣታቸው ሲታወቅ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በየቀኑ ካለማቋረጥ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ከየእዙ የሚመጣላቸው ሪፖርት መፍታት የሚቻልበትን ጉዳይ እየተወያየ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጮቹ ገልጸው ነበር::
ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ ጡረታ ወቶ በምትኩ የብኣዴን ሜ/ጄ አበባው ይተካሉ ሲባል ወያኔ በድንገት የመለስ የቅርብ ሰው የነበሩትን እና በአንድ ወቅት የአማር ክልል አቶ አያሌው ጎበዜን ላንቻ አከባቢ በመኖሪያ ቤታቸው ለ3 ወር አግተው ሲያሰቃዩ የነበሩት ሌ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀልን በማእረግ ሾሞ ሳሞራ የኑስን ለመተካት የሚያደርገውን ሩጫ የብኣዴን አባላት መቃወማቸውን ተከትሎ ጄኔራል አባባውን ጨምሮ የብኣዴን መኮንኖችን ያገለለ የሕወሃት አባላት የሆኑ ጄኔራሎች ብቻ የተሳተፉበት በትግሪኛ የተመራ ስብሰባ መደረጉን ውስጥ አዋቂ ምንጮቹ ተናግረዋል::በስብሰባው ላይ ቀሪ ከፍተኛ ባለማእረግ መኮንኖች እና የመምሪያ ሃላፊዎች ለምን አልተሳተፉም የሚል ጥያቄ ከአንድ ስማቸው ካልተጠቀሰ ብርጋዴር ጄኔራል መነሳቱን ምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮቹ ጠቁመዋል::
ይህ ስብሰባ ዋና አትኩሮቱ የነበረው በብሄር አደና ላይ ሲሆን እንደ ምንጮቹ መረጃ በአማራ እና በኦሮሞ መኮንኖች እየተመራ ያለውን የለውጥ ጥያቄ በማክሸፉ ዙሪያ እንደነበር እና አሁንም በስፋት የሕወሓትን የፓርቲ አቋም የሚቀበሉ እና የጥቅም ተጋሪ የሆኑ ሰዎችን ለመሾም የታቀደ ሲሆን እንዲሁም ከፖለስ ሰራዊት በከፍተኛ የማእረግ ሹመት ወደ ጦር ሰራዊቱ ለማምጣት የታሰበ ሲሆን በወታደራዊ ደህንነት ዙሪያ ሌላ ተጨማሪ ሰልጣኞችን ከፖሊስ ወስዶ በማሰልጠን ወደ ሰራዊት ማዘዋወር የሚሉ ውይይቶች ተካሂደውበታል:: አሁንም ስብሰባው የቀጠለ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን እንለቃለን::

ሰበር ዜና፡- በአሜሪካ፣ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት፣ በዛሬው እለት ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ቢኒያም አሰፋ እና ባለቤቱ፣ የ3 ወር ህፃን ልጃቸውም በጥይት መሞታቸው ተዘገበ፤

 በአሜሪካ፣ ሜሪላንድ ክፍለ ግዛት፣ በዛሬው እለት ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ቢኒያም አሰፋ እና ባለቤቱ፣ የ3 ወር ህፃን ልጃቸውም በጥይት መሞታቸው ተዘገበ፤ ባልና ሚስቱ ራሳቸውን ያጥፉ ወይም ይገዳደሉ አልታወቀም። ይሄ ሁሉ ሲካሄድ የ5 አመት ልጃቸው ወደ ጎረቤት አምልጣ ተርፋለች። ሙሉ ዜናው እነሆ!

NEW MARKET, Md. (WUSA9) — The Frederick County Sheriff’s Office have identified the three people, including an infant, who died after a shooting Wednesday night.
Officials say they are 40-year-old Benyam Asefa, 42-year-old Barbara Giomarelli, and 3-month-old Samuel Asefa. Authorities say that Giomarelli is an Italian citizen and Asefa is an American citizen. Both were scientists and had been working on medical research. According to the LinkedIn profiles, Barbara was a PhDresearcher at University of Maryland and had spent time at the Institute of Marine and Environmental Technology. Benyam, aslo known as Ben was a clinical immunologist who was a contractor supporting research at the National Institute of Allergy and Infectious Diseases and a graduate of McGill University.
The incident happened before 8:50 p.m. in the 6800 block of Woods Court in New Market, Md., officials say.
A five-year-old girl ran to a neighbor’s house and told the neighbors, who called police, according to officials. The girl and neighbor told deputies that the family members may be injured and in need of assistance.
When deputies entered the home they found a 40-year-old male, a 42-year-old woman and a boy less than 1 year old dead inside the home, say officials. Officials tell us that their injuries were consistent with gunshot wounds and that a handgun was found at the scene but that the wounds will have to be confirmed by autopsies.
Officials say the girl was checked by EMS and was not harmed. The girl is now in child protective custody. She hid in the home when the incident occurred.
Police say they are investigating the incident as a murder-suicide confined to one family in one home.
Authorities say the family recently moved from Howard County and bought the house in New Market.
The three family members will be transported to the Medical Examiner’s Office in Baltimore for autopsies.

ኦቶ ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ

የሳዑዲ ልዑል አንጋቾቻቸውን አወደሱ

Obang Metho Solidarity Movement for New Ethiopia
በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡
ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው ዝርዝር ጉዳይ ግን ከሁኔታው ምስጢራዊነት አኳያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
“አልዘገዩም” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም “አኢጋን ችግር በተከሰተ ቁጥር የሚቋቋምና የሚፈርስ የዕቁብ ይዘት ያለው ድርጅት አይደለም፡፡ ወይም እሣት ሲነሳ ድምጽ እያሰማ እንደሚከንፍ የእሣት አደጋ መኪና የሚመሰል ድርጅት አይደለም” በማለት የጋራ ንቅናቄውን የተጠና አካሄድ በመጠቆም የመለሱት አቶ ኦባንግ ይህ ችግር እንደሚከሰት አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
ችግሩ አስቀድሞ እንደሚከሰት ቢታወቅም ምላሽ የሚሰጥ ብቃት ያለው አካል ባለመኖሩ አንገት የሚያስደፋና ኃፍረት የሚላብስ፤ “አገር አለኝ ወይ?” የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቅ ኃፍረት ሊደርስብን ችሏል፡፡ “ይሁን እንጂ” አሉ ኦባንግ “ይህ መራር ዜና ከተሰማበት ሰዓት ጀምሮ የጋራ ንቅናቄው የበኩሉን” ሲያደርግ መቆየቱን አመልክተዋል፡፡
“ከተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ አግባብ ካላቸው መንግሥታዊ አካላትና በተለያየ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረናል” በማለት አቶ ኦባንግ ተናግረዋል፡፡ ለዓብነት ያህልም የሳዑዲ ም/ጠ/ሚ/ር እና የመከላከያ ሚ/ር፣ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚ/ር፣ የፍትሕ ሚ/ር እና ሌሎች ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን የመንግሥት መ/ቤቶችን ጨምሮ በአውሮጳና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙትን የሳዑዲ ኤምባሲዎችን እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነርን፣ የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ACHPR)፣ ወዘተ ማነጋገራቸውንና በየደረጃውም ምላሽ ማግኘታቸውን አመልክተዋል፡፡
በመላው የመካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዕረፍት የሚሰጥ እንዳልሆነ የጠቆሙት “ጥቁሩ ሰው” ሳዑዲ ካላትና ከምትከተለው “የበርህን ዝጋ ፖሊሲ” አንጻር በአካል በቦታው ላይ ከመገኘት ይልቅ አቅም ካላቸው ዓለምአቀፋዊ አካላት ጋር በአፋጣኝና በቅርበት መሥራቱ ድርጅታቸው የወሰደው አማራጭ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የሎጂስቲክሱ ጉዳይ መስመር ሲይዝም የጋራ ንቅናቄው ከዚህ በፊት በየአገራቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ሲያስፈጽምበት የነበረውንና በውጤታማነቱ የሚታወቀውን አማራጭ እንደሚተገብር ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ኢህአዴግ አገርን እንደሚያስተዳድር ድርጅት በዜጎቹ ላይ እየደረሰ ያለውን አስነዋሪ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ አለመመከቱ ተቃውሞ አስነስቷል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ወገኖቻችንን ድንበር በማሻገርና ኤጀንሲ ከፍተው ወደ አረብ አገራት ሲልኩ የነበሩት ሁሉ ሕግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ የተለያዩ ተግባራት” እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ሼክ መሐመድ አላሙዲ የሠራተኛ ኃይል ወደ ሳዑዲ እንዲላክ ከኢህአዴግ ጋር በይፋ ስምምነት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ ከሚፈልጉበት ክልል መሬት ለመውሰድ፣ ከሚፈልጉበት ባንክ ኮሪደር ገንዘብ ለመበደር ገደብ የሌላቸውና በሞቀበት ሁሉ ባለመጥፋት በጀት መድበው በሚያስተዳድሯቸው ሚዲያዎች እንዲሁም አንደበታቸውን በሙስና ላሰሯቸው ባለሥልጣናት “ኢትዮጵያዊ ነኝ” እያሉ በተገኙበት ቦታ ሁሉ ለሚዲያ ፍጆታ የሚደሰኩሩትና ግጥም የሚያስደረድሩት ሼክ መሐመድ አላሙዲ፣ “ወገኔ” የሚሉት ሕዝብ በአባታቸው አገር ወሮበሎች ሲያልቅና ሲጨፈጨፍ ዝም ማለታቸው ኢንቨስትመንቶቻቸውን ጥያቄ ውስጥ ከትቷል፡፡
አንዳንዶች እንደሚሉት ይህ አሰቃቂ ድርጊት መስመር ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት የሳዑዲ አረቢያ ዜጎችን ከርስ እንዲሞላ በኢትዮጵያ የተቋቋመው ሳዑዲ ስታር ኩባንያ በገንዘብ እጥረት ሊዘጋ እንደሚችል መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ ሳዑዲ ስታር በኪሣራ ወደ መዘጋት መድረሱ የኩባንያው “ባለቤት የሆኑትን ሼክ ሙሐመድ አል አሙዲንና የሳዑዲ ዓረቢያን ስም የሚያጎድፍ ከመሆኑም ባሻገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እስኪታክት የተወራለት ይህ ፕሮጀክት መና መቅረቱ ሁለቱን አካላት በሕዝቡ ዘንድ ለከፍተኛ ትችትና ወቀሳ እንደሚያጋልጣቸውም” ጠቁሞ ነበር፡፡
በአሁኑ ጊዜ “ሕገወጥ ናችሁ” በሚል ሰብዓዊነት የጎደው እርምጃ እየተወሰደባቸው ያለው የበርካታ አገራት ዜጎች በተለይም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመውን ሰቅጣጭ ተግባር ሕገወጦችን የማባረር “ዘመቻ” በማለት ያቃለሉት የሳዑዲው አገር ውስጥ ሚ/ር ልዑል ሞሐመድ ቢን ናይፍ ወንጀለኛ ሬንጀር ለባሾችን፣ ፖሊሶችንና ወሮበሎቹን ሸባቦች አደፋፍረዋል፡፡ “ዘመቻው ይቀጥላል … በተወሰነ ጊዜ የተገደበ አይደለም” በማለት “እስክንጨርስ እንጨርሳችኋለን” የሚመስል የማፊያ መሪ መሰል መልዕክት ለአንጋቾቻቸው አስተላልፈዋል፡፡
አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን በሕጋዊነት የሚኖሩትም ጭምር በሳዑዲ ያለው ሁኔታ አሳሳቢነት ወደፊት ችግር ውስጥ ሊከትታቸው እንደሚችል በመገመት ወደ አገራቸው መመለስ ይፈልጋሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ሰቆቃ የተጋለጡት ኢትዮጵያውያን “ቤት አለን ቤታችን መልሱ” እያሉ የሰቆቃና የድረሱልን ጥሪ በሚያስተላልፉበት ወቅት ሰብዓዊነት የጎደላቸው የኢህአዴግ መሪዎች ይህ ነው የሚባል አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አለመቻላቸው “በእርግጥ ኢትዮጵያውያን አገር አላቸው?” ብሎ የሚያስጠይቅ እንደሆነ በርካታዎች የሚጋሩት ነው፡፡
አቶ ኦባንግ በበኩላቸውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአንድ ሳምንት ሥራውን አቋርጦ እንኳን ቢሆን ስደተኞቹን ባፋጣኝ የማመላለስ ተግባር መፈጸም ይገባው ነበር በማለት ቁጭታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዜጎች በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ህይወታቸው እየተቀጠፈ “3ሺህ ዛሬ ገቡ … ድምሩ 10ሺህ ሆኗል …” የሚል የሞላ ጎደለ ቁማር ዓይነት ጨዋታ በትዊተር መጫወት የቴድሮስ አድሃኖምን ዘመነኛነት ሳይሆን ለሰውልጅ ህይወት ያላቸውን ደንታቢስነት የሚያሳይ መሆኑን ሁኔታው ያስቆጣቸው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አቶ ኦባንግም “ቤቴ መልሱኝ” ብሎ ለሚለምን አንድ ዜጋ የተከፈለው ተከፍሎ ትራንፖርት በማቅረብ ክቡር ህይወትን በአስቸኳይ ለመታደግ አለመቻል ለትውልድ የሚተላለፍ የታሪክ ጠባሳ መሆኑን በአጽዕኖት ተናግረዋል፡፡

ጎንደር ዩኒቨርስቲ አንድ ተማሪ ተገደለ

በጎንደር ዩኒቨርስቲ የ3ኛ አመት ማርኬቲንግ ተማሪ የነበረው አንተነህ አስፋው መገደሉን የደረሰን ዘገባ አመልክቷል። ትላንት ምሽት ወደ ዩኒቨርስቲው ከሴት ጓደኛው ጋር ወደዩኒቨርስቲ እየሄደ የነበረው ወጣት፤ ከግቢው ውጭ የዩኒቨርስቲው ጠባቂ ያስቆመዋል። ተማሪውም “ከዩኒቨርስቲ ውጪ ልታስቆመኝ አትችልም” የሚል ክርክር ይገጥማል። በዚህ መሃል ሴት ጓደኛው ተመትታ ራሷን ስታ ትወድቃለች። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተነሳ ግርግር ጥበቃው ተኩስ ይከፍትና ተማሪዎች ይበታተናሉ። በንጋታው ጠዋት ግን ያልተጠበቀ ነገር ገጠማቸው።
ምሽቱን ተማሪዎችን ለመበተን ይሁን ወይም ሆን ተብሎ በተተኮሰው ጥይት አንድ ተማሪ ቆስሎ ኖሮ፤ ጠዋት ወደ ዩኒቨርስቲ ሲመለሱ፤ አንድ ተማሪ ሞቶ ተገኝቷል። ሁኔታው በጣም አሳዛኝ ነው። በጎንደር ዩኒቨርስቲና በከተማው አካባቢ ይህ ጉዳይ ህዝቡን እያነጋገረ ይገኛል። ይበልጥ ነገሩን ያካረረው ደግሞ፤ የጥበቃውን ተግባር ለመሸፈን ሲባል ፖሊስ “እርስ በርስ በጩቤ ተወጋግተው ነው የተገደለው” ማለቱ ነው። ተማሪዎቹ ግን “የለም። ገዳዩ ምሽት ላይ የተኮሰው የጥበቃ ሰራተኛ ነው” በማለት ላይ ናቸው። እንግዲህ የአስከሬን ምርመራ የሚደረግ ቢሆን፤ የአሟሟቱን ምክንያት ለማወቅ ይቻላል። እስከዚያው ግን ነገሩ እንዳወዛገበ ይቆያል – ማለት ነው።
የሟችን ፎቶ እና ተጨማሪ መረጃዎች ካገኘን ቆየት ብለን እናቀርባለን።