Saturday 6 December 2014

ሰበር ዜና) ቴዲ አፍሮ ከሃገር እንዳይወጣ ታገደ


  • 5928
     
    Share
ዘ-ሐበሻ) በአውሮፓና የተለያዩ የሩቅ ምስራቅ አገራት የሙዚቃ ኮንሰርቶቹን ለማቅረብ ወደ ውጭ ሃገር ሊወጣ የነበረው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከሐገር እንዳይወጣ መታገዱን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው የታማኝ ምንጮች መረጃ አመለከተ። ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርቱን በፊንላንድ ሄልሲንኪ በነገው እለት ይጀምራል ተብሎ የነበረ ሲሆን የሙዚቃ ባንዶቹ አባላትና ማናጀሩ እዛው ፊላንድ ቢገቡም ቴዲ በደህንነቶች ከሃገር እንዳይወጣ በመታገዱ የተነሳ የነገው የፊንላንድ ኮንሰርት መሰረዙን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
ከጥቂት ወራት በፊትም ቴዲ አፍሮ ወደ አሜሪካ ሊመጣ ሲል እንዲሁ በደህነንቶች ተይዞ በኤርፖርት ሲጉላላ እንደቆየና በኋላም ወደ ውጭ እንዲወጣ እንደለቀቁት ያስታወሱት የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች፤ በአሁኑ ጭራሹኑ እንዳይወጣ ፓስፖርቱን ውስደውበታል ብለዋል። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የቴዲ አፍሮ ፓስፖርት ያልተመለሰለት ሲሆን ወደፊት እንዲወጣ ይፍቀዱለት አይፈቀዱለት የታወቀ ነገር የለም ብለዋል።
የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ቴዲ ለምን ከሃገር እንዳይወጣ እንደታገደ የተገለጸለት ነገር የለም:።
በሄልሰንኪ ፊላንድ የቴዲን መምጣት በጉጉት የሚጠባበቁ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በርካታ ሲሆኑ አዘጋጆቹም ቴዲ ይመጣል በሚል በርካታ ትኬቶችን ሸጠው ነበር። ሆኖም ግን ኮንሰርቱ በመሰረዙ የተነሳ ትኬቱን የገዙ ሰዎች ገንዘባቸው እንደሚመለስላቸው አዘጋጆቹ በቪድዮ ለዘ-ሐበሻ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል። ቪድዮውን ይመልከቱት።
በዚህ ዙሪያ የቴዲ አፍሮ ማናጀር የሆነውን አቶ ዘካሪያስ ጌታቸውን ዘ-ሐበሻ ለማነጋገር እየሞከረች ሲሆን ማናጀሩን እንደገኘነው ሃሳቡን ለአንባቢዎቻችን እናካፍላለን።
teddy afro

በአዳር ሰልፉ ኢህአዴግ “ተሸብሯል”

በስውርና በግልጽ አፈናው ተጧጡፏል
police 11
* የከምባታ ጠንባሮ ዞን ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉ ተገለጸ
* የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ በፖሊስ ተከብቦ አደረ
የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በፖሊስ ተከብቦ ማደሩንና አባላት ከውጭ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ለአዳር ሰልፉ ቅስቀሳ ዝግጅት ቢሮ ያደሩ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አመራሮችና አባላቱ እራት በልተው ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ሲመለሱ ቢሮው በፖሊስ ተከብቦ እንዳገኙትና ወደ ውስጥ እንዳይገቡ እንደተከለከሉ በቦታው የነበሩት የፓርቲው አመራሮችና አባላት ገልጸዋል፡፡
police 14አመራሮችና አባላቱ ፖሊስ ከ200 ሜትር ርቀት ውጭ ወደ ፖለቲካ ፓርቲ ጽ/ቤት መጠጋት እንደማይችል ቢከራከሩም ፖሊሶቹ “መመሪያ ተሰጥቶናል፤ አንሄድም!” ማለታቸው ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ከፖሊስ ጋር ሲከራከሩ የአካባቢው ህዝብ በመውጣቱ ፖሊሶቹ ፓርቲው ጽ/ቤት እንደራቁ ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ከውጭ ወደ ቢሮ ከሚመጡበት ወቅት የፓርቲው ቢሮ አካባቢ ምንነቱ ያልታወቀ ወረቀት ተበትኖ እንዳገኙና እነሱ ሲደርሱ ፖሊሶቹ እንዳነሱት የፓርቲው የምክር ቤት አባል ወጣት እየሩስ ተስፋው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡
*********************
በነገረ ኢትዮጵያ የፌስቡክ ገጽ ላይ የታተመው መረጃ እንደሚያመለክተው ፖሊስና ደህንነቶች ወደ ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የሚገቡና የሚወጡ አባላትንና አመራሮችን እያዋከቡ ይገኛሉ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንና አባላትን “እንፈልጋችኋለን!” በሚል እየያዙ ሲሆን በተለይ ደህንነቶቹ መታወቂያ አሳዩ ሲባሉ ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡
ሰማያዊ ቢሮ ጽ/ቤት የሚገኙ ደህንነቶች የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን እያፈኑ እየወሰዱ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ የሆነውን ፍቅረ ማሪያም አስማማውን አፍነው ወስደውታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የገዥው ፓርቲ ደህንነቶች ተጨማሪ ሰዎችን አፍነዋል፡፡ የነገረ ኢትዮጵያ ምክትል ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ እና የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ምክትል ኃላፊ እንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት ፀኃፊ ወጣት ሳሙኤል አበበ በደህንነቶች ታፍነው መወሰዳቸውን ነገረ ኢትዮጵያ በዚሁ የፌስቡክ ገጹ ዘግቧል፡፡volunteers of 9 parties
ከጥቂት ሰዓታት በፊት የተሰራጨው መረጃ እንደሚያመለክተው የአዳር ሰልፉን የጠሩት የ9ኙ ፓርቲዎች ቢሮ በፌደራል ፖሊስ ተከብቧል፡፡ እንዲሁም የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አባል የሆነው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቸርቺል የሚገኘው ጽ/ቤት በፌደራል ፖሊስ ተከቧል፡፡ ከሰማያዊ ጽ/ቤት መውጣትም ሆነ መግባት የማይቻል ሲሆን በርካታ አመራርና አባላት ታፍነው ታስረዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የትብብሩ አመራሮች ስልክ እንዳይሰራ እየተደረገ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲና የትብብሩ ሊቀመንበር የኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ስልክ እንዳይሰራ ተደርጓል፡፡
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በተሰራጨ መረጃ መሠረት የሰማያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚ ፀኃፊ የሆነው ወጣት አወቀ ተዘራ ወደ ቤቱ በሚገባበት ወቅት በስርዓቱ የደህንነት ኃይሎች ተይዞ ታስሯል፡፡ ፍቅረማሪያም አስማማው፣ አወቀ ተዘራና ተስፋሁን አለምነህን ጨምሮ በደህንነቶች የታፈኑት ወጣቶች የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
በተያያዘ ዜና የከምባታ ጠንባሮ ዞን ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉ ተገለጸ፡፡ በገዥው ፓርቲ አድሏዊ አሰራር ምክንያት ልማትና መልካም አስተዳደር ባለመኖሩ የከንባታ ጠንባሮ ነዋሪዎች ዛሬ ህዳር 26/2007 ዓ.ም ዱራሜ ከተማ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን የከምባታ ህዝብ ኮንግረንስ ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዲሎ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ህዝብ ያለ ማንም ቀስቃሽና አስተባባሪ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣቱን የገለጹት አቶ ኤርጫፎ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት አከብራለሁ በሚል ለፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ ከማድረጉ ውጭ በተግባር ግን በህዝብ ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸመ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የከንባታና ጠንባሮ ህዝብ ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ተቃዋሚዎችን በተለይም የከምባታ ህዝብ ኮንግረንስን ትደግፋላችሁ በሚል በደል እንደሚደርስበት የገለጹት አቶ ኤርጫፎ “ህዝቡ በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት በደል እየደረሰበት ነው፡፡ ምርጫ ሲደርስ መንገድ፣ ዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ይሰራልሃል ይባላል፡፡ ምርጫው ሲያልፍ ለማታለያነት ይሰራሉ የተባሉ ነገሮች ተግባራዊ አይሆኑም፡፡ እስካሁን ከ1993 ዓ.ም አንስቶ ይሰራል የተባለ መንገድ አልተሰራም፡፡ በምርጫ ወቅት አርሶ አደሮችን እያፈናቀሉ ኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ እንሰራለን ይላሉ፡፡ ከምርጫ በኋላ ግን ይህ መሬት የሚሰጠው ለሹመኞች ነው፡፡ ሁለቱም ጠቅላይ ሚኒስትሮች የምርጫ ሰሞን በየቦታው የመሰረት ድንጋይ ተክለዋል፡፡ ከምርጫ በኋላ ግን ለሹመኞች ይሰጣል፡፡ ዛሬ ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣውም ከዚህ አንጻር ነው” ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
የከንባታ ጠንባሮ ህዝብ ባለፉት ምርጫዎች ተቃዋሚዎችን በመምረጥ ከገዥው ፓርቲ ጋር ያለውን ልዩነት በግልጽ እንዳሳየ የገለጹት አቶ ኤርጫፎ “ወጣቶች ልማትና የትምህርት እድል ስለማያገኙ ወደ ደቡብ አፍሪካና አረብ አገራት እየተሰደዱ መንገድ ላይ እየሞቱ ነው፡፡ በቀን 11 አስከሬን የመጣበት ጊዜ አለ፡፡ በስርዓቱ አድሏዊ አሰራር ምክንያት ከንባታ ጠንባሮ ወጣቱ ከቀየው እየተፈናቀለ የሚሰደድበት ትልቁ ዞን ነው ማለት ይቻላል” በማለት አስረድተዋል፡፡
በዛሬው እለት አርሶ አደሩ፣ ተማሪውና ነጋዴው የዞኑ ጽፈት ቤት ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ከማድረጉም ባሻገር በቀጣይነት በየወረዳዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚየደርግ ገልጾአል ሲሉ ሊቀመንበሩ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ (ለመረጃ ጥንቅሩና ለፎቶዎቹ፡ ነገረ ኢትዮጵያ)

Semayawi Party office in Ethiopia’s capital surrounded by police and kidnapped more members - See more at: http://www.zehabesha.com/semayawi-party-office-in-ethiopias-capital-surrounded-by-police-and-kidnapped-more-members/#sthash.R6FYmXYU.dpuf

Filed under: News,News Feature | 
semayawi
addis ababa semayawi party
addis ababa semayawi
Federal Police surrounded Semayawi Party’s office in Addis Ababa, Ethiopia, ahead of the 24 hour protest demonstration that was called by a coalition of 9 opposition groups for this coming weekend. The protest is planned to be held at Meskel Square.
10 semayawi members are kidnapped by the Ethiopian Junta/Gov`t Security forces.
- See more at: http://www.zehabesha.com/semayawi-party-office-in-ethiopias-capital-surrounded-by-police-and-kidnapped-more-members/#sthash.uBELQvkR.dpuf

Friday 5 December 2014

ግልጽ ደብዳቤ ለወይዘሮ ገነት ዘውዴ – ከፈቃደ ሸዋቀና


geneteየዱሮ ወዳጄ ሰላምታዬ ይድረስሽ። እንደምታውቂው ከተያየን ከሁለት አስርት አመታት በላይ ሆኗል። እኔም ካገሬ ከወጣሁ 21 ዓመት አለፈኝ።
በጤናና በምቾት እንደምትኖሪ እሰማለሁ። እግዚአብሄርም መንግስትም ጥሩውን ነገር ሁሉ አብዝቶ እንዲሰጥሽ ምኞቴ ነው። አዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ በጓደኝነት ከምቀርባቸውና ከማከብራቸው ስዎች ውስጥ አንቺ አንዷ እንደነበርሽ ራስሽም ብዙ ሰዎችም ያውቃሉ። ከጊዜ ብዛትና
በስልጣንም ርቀት ምክንያት ጓደኝነቴን ብትረሽውም አልፈርድብሽም። እኔ ግን ከሀገሬ ባለስልጣኖች አንዷ በመሆንሽ አልፎ አልፎም ቢሆን
ስላንቺ የሚባለውን ከፉም ደግም እሰማለሁ። ብዙ ጊዜ ሰዎች ስላንቺ ክፉ ሲናግሩ ስሰማ የጓደኝነት ነገር እየሆነብኝ ደስ አይለኝም። ተሳክቶልኝ
እንደሆን ባላውቅም ስላንቺ የማውቃቸውን በጎ ነገሮች በማንሳትም ልሟገት የሞከርኩበት ጊዜ ጥቂት አይደለም። ብዙ ሰዎች ያኔ 41 መምህራን
ከዩኒቨርሲቲ ስንባረር አንቺን እንዳባራሪ እያዩሽ ለምን እንደማልጠላሽ ይገርማቸዋል። እስከዚህ ደቂቃ ድረስ ዉሳኔው ሲቀርብልሽ
አትፈርሚም ብዬ ባልከራከርም አንቺ በኔ መባረር ላይ ትወስኛለሽ ብዬ አስቤ አላውቅም። አስተያየት እንድትሰጭ ብትጠየቂም በኔ ላይ ክፉ
የምትናገሪም አይመስለኝም። መንግስታችን ላንቺ አይነት ሰዎች ትልቅ ወንበር እንጂ ትልቅ የውሳኔ ሰጭነት ስልጣን አብሮ እንደማይሰጥ እንደ
ብዙ ሰው አውቃለሁ። ድሮ ጀምሮ ካንቺ ጋር ውቃቢያችሁ የማይዋደደው ወዳጄ ዶክተር መረራ ጉዲና “ያቺ በተገናኛችሁ ቁጥር ስትሳሳሙ
የማያችሁ ጓደኛህ መጨረሻ ላይ እኔን ትታ አንተን ነከሰችህ” እያለ ያሾፍብኛል። በቅርቡ የጻፈው መጽሀፍ ላይም ይህንኑ እንደቁም ነገር ጽፎታል።
“ገነት እኔን አላባረረችኝም፣ እሷ እንዳላባረረችኝ ማስረጃዬ ያንተ አለመባረር ነው” እያልኩ መልሼ አሾፍበታለሁ። በዚያ የደርግ የመከራ ዘመን
ብዙ ክፉ ነገር ያየሽ ሰው መሆንሽን እንዳወኩ በውስጤ ላንቺ ትልቅ የተቆርቋሪነት ስሜት ነበረኝ። እንደነገርኩሽ እኔ እድለኛም ሆኜ ከዚያ መአት
ነፍሴ የተረፈች ሰው ብሆንም የምወዳቸው ደርግ የገደላቸው ጓደኞቼ ሀዘን የነበረብኝ ስው ስለነበርኩ ያን መከራ አቋርጠው ለተረፉ ሰዎች ሁሉ
ስስ ልብ ነበረኝ። እንደጥንካሬ ተምሳሊትም (inspiration) እንድቆጥርሽና እንደ እህትም እንድቀርብሽ ያደረገኝ ያ ይመስለኛል።
ዛሬ ካለወትሮዬ ይህን ደብዳቤ የምጽፍልሽ ወድጄ አይደለም። እግዚአብሔር ይይልሽና የረሳሁትን ነገር ቀስቅሰሽ ሕሊና የሚነዝር ነገር
ስለሰጠሽኝ ነው። በቅርቡ የሆኑ ወዳጆቼ ጉድህን ስማ ብለው ሸገር ኤፍ ኤም የሚባል ሬዲዮ ላይ የሰጠሽውን ቃለ ምልልስ የያዘ ክሊፕ
ላኩልኝ። ረጅም ጊዜ ያልሰማሁትን ድምጽሽን ሳዳምጥ ቆይቼ ጋዜጠኛዋ ስለረሳሁት ስለ 41ችን ከአዲስ አበባ ዩኒበቨርሲቲ መባረር ጉዳይ
አነሳችብሽ። እግዜር ይይላትና የተረሳ ነገር ብትተወውስ። እውነቱን ለመናገር አሁን እድሜሽም ብዙ ማይል ስለሄደ ለማሰላሰልም ጊዜ
ስላገኘሽ የጸጸት አስተያየት የምትሰጭ መስሎኝ ነበር። በቃለ ምልልስሽ ላይ ስለተናገርሽው ሌላ ብዙ ዕውነት ያልሆነ ነገር እንኳን ብዙም
አልተገረምኩም። እኛ ሀገር ውሸት ከስልጣን ፓኬጅ ጋር አብሮ የሚመጣ መሆኑን ስለማውቅ እሱ ብዙ አልደነቀኝም። ዕብሪት የተሞላበት
ስድብና ዘለፋሽ ግን አሳዘነኝ። የተባረርነውን መምህራን ያንቺኑ ቃል ልጠቀምና ለማስተማር ፊት (fit) ስላላደረጉ (በአማርኛው ብቃት
ስለጎደላቸው ለማለት ፈልገሽ መሰለኝ) ነው የተባረሩት ፥ የኮንትራት ሰራተኞች ስለሆኑ ኮንትራታቸው fit ስላላደረጉ ተቋረጠ፥
ቴኑር(tenure)ስለሌላቸው ነው፥ የተባረሩት 41 ብቻ እኮ ናቸው ያውም ካንድ ዩኒቨርሲቲ ፥ በዚህ የደረሰ ጉዳት የለም ፥ አሁን እኮ
የማስተርሱ ብዛት ፣ የፒኤችዲው ብዛት ሕዝብ ይፈርደዋል፣ ተረረም ተረረም. . . .” የሚል ከቅብጥርጥርነቱ ይበልጥ ስድብነቱ የበዛ ነገር
ውስጥ ለምን እንደገባሽ በጣም ነው የገረመኝ። አለቃሽ ሟቹ አቶ መለስ እንኳን ነፍሱን ይማረውና ከብዙ ጊዜ በኋላም ቢሆን በዚህ ጥያቄ
ላይ የሰራው ስራ ስህተት መሆኑን መቀበሉን ሰምቼ ይቅርታ አድርጌለት ነው የሞተው። እናም ይህን የምጽፈው በፖለቲካ ልዩነት ተገፍቼ
አይደለም። ነገርሽ ስለጓጎጠኝ ብቻ ነው። እዚህ ለስድብሽ የምሰጥሽን አስተያየት ላለቆችሽ አቅርበሽ የመንግስት ተቃዋሚ persecute አደረገኝ
ብለሽ ለሰማዕትነት እንድትጠቀሚበት አይደለም። “ዮዲት ጉዲት” ተብሎ የወጣልሽን ስም በሿሚዎችሽ ዘንድ እንደሜዳልያ አንግባና
እንደሰማዕትነት ተቆጥሮላት እንደ ጥገት ላም አለበችው እያሉ ብዙ ሰዎች ሲያሙሽ ሰምቻለሁ። የምናገረው ስለሀገር ፖለቲካ ሳይሆን ስለ
ለከት የለሹ ስድብሽ ነው። ታስታውሽ እንደሆነ የተሾምሽ ሰሞን በርቺ እዚህ ትርምስ ወስጥ ጥሩ ድምጽ ልትሆኚ ትችያለሽ ብዬ አበረታትቼሽ
ነበር። እኔ እንዴውም ያንን ማዕከላዊ የሚባለውን የቶርቸር ማዕከል አስፈርሰሽ ትምህርት ቤት ታስደርጊዋለሽ ብዬ አስቤም ነበር። ዛሬ
ተሻሽሎ አገልግሎቱን መቀጠሉን እሰማለሁ። አንቺ ያየሽውን መከራ ሌላ ትውልድ እንዳያይ ክሩሴደር ሳትሆኚ ቀርተሽ የራስሽንም
መስዋዕትነት ትርጉም ታሳጭዋለሽ ብዬ አላሰብኩም ነበር።
በዚህ ከመንደር ጥጋበኛ አፍ ብቻ ሊወጣ በሚችል ስድብሽ መገረሜን የነገርኳቸው ብዙ ሰዎች አድምጦ ከቁም ነገር የሚወስዳት ብዙ ሰው
የለም ስላሉኝ ስቄ ልተወው አስቤ ነበር። ትንሽ ቆይቼ ግን ሁለት ነገሮች ከነከኑኝ። ይህን ደብዳቤ ለመጻፍም ምክንያቶቼ እነዚህ ሁለት ነገሮች
ናቸው። አንደኛ ከተባረርናውና ይህን ዘለፋ ከምታወርጂብን 41ዳችን መሀል ሁለቱ በህይወት ስለሌሉ መልስ ሊሰጡሽ እንደማይችሉ ሳስብ
ልቤ ብጅጉ ተነካ። እንደምታውቂው ፕሮፌሰር አስራትና ዶክተር መኮንን ቢሻው ዛሬ በህይወት የሉም። ሁለተኛው ምክንያቴ ደግሞ ልጆቼና
የልጅ ልጆቼ ናቸው። እዚህ በስደት ሀገር የዘራኋቸውና ወደፊት የምዘራቸው ልጆቼ የልጅ ልጆቼና የነሱ ልጆች በብርቱ ሰራተኛነቱ የሚኮሩበት
አባት እንጂ አንቺ እንዳልሽው ለመምህርነት fit ማድረግ ባለመቻሉ የተባረረና የተሰደደ ሰው አድርገው እንዳያዩኝ ፈራሁ። ደግሞስ ከኦባማ
በኋላ ማን ያውቃል። እንዱ ወይም አንዷ የልጅ ልጄ ፕሬዚዳንትነት ወይም ሴናተርነት መወዳደር ይችሉና አባታችሁ አገሩ በመምህርነት ሥራ
“fit” ማድረግ አቅቶት የተባረረ ሰው ነበረ ብለው አንቺን ጠቅሰው እንዳያሳፍሯቸው ሬከርዴን ማስተካከል አለብኝ ብዬ አሰብኩ። የትምህርት
ሀላፊ (Educator in Chief) ከነበረች ሰው አንደበት የወጣ ስለሆነ እውነትነት ይኖረው ይሆን ወይ ብለው ቢያስቡና ቢሸማቀቁስ? የልጅ
ልጆቼ ጠንካራና ታታሪ አያታቸው ስደት ሀገር ስራ-አጥ የሚል ፓስፖርት ይዞ መጥቶ ከምንም ተነስቶ የቆመ ፣ ከኛ አልፎ ለብዙ የተረፈ፣
ኢትዮጵያን እኛን ልጆቹንና ስራውን የሚወድ ታታሪ ነበር እያሉ እንዲኮሩ እፈልጋለሁ። ይህን ደብዳቤ የምጽፈው ለነሱም ውለታ ለመስራት
ብዬ ነው። እኔና እንቺ በዚህ አስተሳሰብ ብዙ ልዩነት ሳይኖረን አይቀርም። አንቺ ልጆችሽና የልጅ ልጆችሽ “የጉዲት ልጆች” ወይም “የዚያችድሀ
ህዝብ ልጆች ላይ እንደ አይጥ ሙከራ ያካሄደች ሴትዮ ልጆች” እየተባሉ ጣት እየተቀሰረባቸው መኖራቸው ምንም ላይመስለሽ ይችል
ይሆናል። እኔ ድግሞ ለራሴ ክብር ያለኝ ሰው ነኝ። እኔ ከሞትኩ በኋላ ሰርዶ አይብቀል ያለች አህያ ብቻ ነች እያሉ ያሳደጉ ቤተሰቦች ነበሩኝ።
እኔ በግሌ ከዚያ ዩኒቨርሲቲ መባረሬ በጅጉ ጠቀመኝ እንጂ አልጎዳኝም። የተሰደድኩ ሰሞን ኑሮ ትንሽ ቢያንገዳግደኝም አሁን የምወደውን ስራ
እየሰራሁ እኖራለሁ። ያባረሩኝን ሰዎች እንደባለውለታ ነው የምቆጥራቸው። እንቃቸዋለሁ እንጂ አልጠላቸውም። በዓለም ላይ ትልቁ የጤና
ምረምር ተቋም ውስጥ ነው የምሰራው። አንድ ኮሌጅ ውስጥም መምህር ነበርኩ። ከኛ በጅጉ በሚበልጠው የስደት ሀገሬ ውስጥ እንዳንቺ “fit”
አታደርግም ብሎኝ የሚያውቅ የለም። ለነገሩ እዚህ አገር ሰው fit አታደርግም አይባልም። ቃሉን ለጫማ ፥ ለልብስና ለመለዋወጫ ዕቃ እንጂ
ለሰው አይጠቀሙበትም። የመደዴ አነጋገር ነው። የምኖርበት ሀገር ከባለስልጣን እስከተራ ያገሬ ሰዎች በሎተሪ የሚመጡበት አሜሪካ ነው።
መንግስታችሁ ሀብታም አደረኳቸው እያለ የሚኮራባቸው ብዙ ሰዎችም ሚስታቸው ስታረግዝ አሜሪካዊ ልጅ እንዲኖራቸው እዚህ እያመጡ
ነው የሚያስወልዱት። ሀገሬ ሀብት ያላቸው ሰዎች እንኳን ለልጆቻቸው የማይመኟት ሀገር መሆኗ አንጀቴን ይበላኛል እንጂ ለኔስ አልከፋኝም።
። ሟቹ መለስንም ሌሎቹንም እባራሪዎቼን እዚህ እግኝቻቸው አውቃለሁ። ሀገራችን ጦርነት ገባች ቢባል ሁሉንም ነገር ረስቼ ሰው
እስኪገርመው ድረስ ዋሺንግተን ዋና ድጋፍ አስተባባሪ ነበርኩ። አባቶቻችን ከመንግስት ተቀያይመውም ጠላት ሲመጣ የራሳቸውን ስንቅ
ይዘው ጦርሜዳ የሚሄዱበትን ወግ አድርሻለሁ። በጥላቻ አላየኋቸውም። እንቺንም ባገኝሽ ከድሮው ባልተናነሰ ክብርና ፍቅር አስተናግድሽ
እንደሆን እንጂ የጥላቻ ስሜት አታገኝብኝም። ጥላቻ የበለጠ የሚጎዳው ጠዪውን መሆኑን አውቃለሁ።
ያሁኖቹ ሹዋሚዎችሽ ስልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊትና እንደወጡ ሰሞንም እኔና እንቺ ስለነሱ ብዙ አውርተን እናውቃለን። ካንቺ በበለጠ
ለነሱ ገራገር አመለካከት የነበረኝ እኔ እንደነበርኩ የምትረሺ አይመስለኝም። ብዙዎቹን በተማሪነታችን ጊዜ እንደማውቃቸውና
ዲሞክራሲያውያን ሊሆኑ እንደሚችሉ ስነግረሽ እንደነበር ታስታውሻለሽ። ሰለነሱ ቀና ነገር በተናገርኩ ቁጥር ሰውነትሽ እንዴት ይለዋወጥ
እንደነበርም አስታውሳለሁ። አንድ ጊዜ እንዴውም ስለህወሀቶች እንደዚህ ማውራት ከቀጠልን ልጠላህ እችላለሁና እናቁም ብለሽ
ማቆማችንንም የምታስታውሽ ይመስለኛል። እሁን ሰዎችን ትምክህተኛ እያልሽ ታሸማቅቂያለሽ ብለው ሰዎች ነግረውኝ የግርምት ሳቅ ስቄ
ነበር። ይህን በዝርዝር ማውራት ከወዳጆችሽ ማቀያየም ይሆንብኛል እንጂ ስለህወሀቶች በተለይ ስለትግሬዎች ባጠቃላይ ከነበሩሽ
እመለካከቶች ውስጥ ብዙ ነገሮች ጠቅሼ አስታውስሽ ነበር። ብዙዎቹን ቃል በቃል አስታውሳቸዋለሁ። ወደ ተራ ሰባቂነት መውረድ
ስለማልፈልግ በዚሁ ይቅር። አንድ ጉብዝናሽን ግን አደንቃለሁ። ቢያንስ እኔን በዚህ በጣም ትበልጭኛለሽ። ስለወያኔዎች እንቺ በአወንታውም
በአሉታውም በኩል ሁለት ጊዜ ልክ ሆንሽ። እኔ ሰዎች ሲመስሉኝ ላንቺ ጭራቅ ነበሩ ፥ ለኔ ክፋታቸው ሲገለጥልኝ ደግሞ ላንቺ መላዕክት
ሆኑ። እንቺ ሁለት እኔ ዜሮ ወጣን ማለት ነው። በቡጢ ቋንቋ በዝረራ ነው ያሸነፍሽኝ። ይቺ ድንቅ ችሎታ ነች። ከሁሉ በላይ ደግሞ ከዚህ
ሁሉ ጂምናስቲክ በኋላ ከህሊናሽ ጋር አብሮ የመኖር ችሎታሽ ሊደነቅልሽ ይገባል።
እስኪ ስለዋናው ስለተነሳሁበት ስላወረድሽብን ስድብ ጉዳይ እንነጋገር። ለመሆኑ እንዴት አይነት የኮሌጅ ኮንትራክት ነው እባክሽ ሴሚስተር
መሀል በመጋቢት ወር መምህር fit አላደረገም ተብሎ ሲቋረጥ ያየሽው? አንቺ እንደምትዪው ተራ የኮንትራት ማቋረጥ ጉዳይ ከሆነ ታዲያ
በዩኒቨርሲቲው ግቢ ዙሪያ እንዳንደርስ ለምን በወታደር ከለከላችሁን? ጎዳና ላይ እየተከተሉ ማስፈራራትንና ማዋከብንስ ምን አመጣው።
ዩኒቨርሲቲ መምህር ቀጣሪም ኮንትራት ሰራዥም የሙያ ዲፓርትሜንቱ እንደነበረ ረስተሽው ነው ወይስ ሸገር ሬዲዮ የሚሰማው ሰው በሙሉ
ደንቆሮ መሰሎሽ ነው? ለመሆኑ ኮንትራት የሚቋረጠው ቁራጭ ወረቀት አባዝቶ አንድ ቀን ጠዋት ተነስቶ ለሰራተኛው ያውልህ ብሎ አፍንጫ
ላይ በመወርወር ነው? ትልቁ መመለስ ያለብሽ ጥያቄ ደግሞ ይህ ነው። እንዴው ለመሆኑ ማነው የት ቁጭ ብሎ የማስተማርና የምርምር
ችሎታችንን የመዘነውና አንቺ እንዳልሽው fit አለማድረጋችንን ያረጋገጠው? ርግጠኛ ነኝ ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ የለሽም። ነገሩ አፍ
እንዳመጣ ለመናገር የሚገፋፋ የጥጋብ አነጋገር ነው ያልኩሽም ለዚህ ነው። መልስሽ ሁሉ የሚያደምጡሽን ሰዎች በመናቅ ላይ የተመሰረተ
ነው።
አንዳንድ ጊዜ አፍ ሞልቶ ሌሎችን መሳደብ ቀርቶ ለመተቸት እንኳን ራስን ትንሽ ማየት ይጠይቃል። አንቺ ለሹመት በመብራት ተፈልገሽ የተገኘሽ
ከባድ ሚዛን ምሁር እንዳይደለሽ ራስሽም ብዙ ሰዎችም እናውቃለን። በየት በኩል ሄደሽ ለሹመት እንደበቃሽ ብዙ ሰዎች ያውቃሉ። ይህ ብቻ
ትሁት (humble) ሊያደርግሽ ይገባ ነበር። ስልጣንና ዕውቀትን የሚያደባልቀው ያገራችን ዛር አንቺ ላይ የሚፈልቅ አልመሰለኝም ነበር። ያ
የደርጉን ሀምሳ አለቆች ባንድ ሰሞን የማርክሲስት ሶሻል ሳይንስ ሊቅ ያደረገው ዛር። ያ አቶ በረከት ስምኦንን ስልጣን የያዘ ሰሞን ስድስት ኪሎ
መኮንን አዳራሽ ውስጥ የዩኒቨርሲቲውን ፕሮፌሰሮች ሰብስቦ ታሪክ እንዲያስተምር ያዘዘውና ሲያንቀዠቅዥ አምጥቶ ያላተመው ዛር።
ሳትሳደቡ ታማኝነታችሁን ላለቆቻችሁ ማረጋገጥ አትችሉም? ያ አስገራሚ ያማራ ህዝብ መሪ ነኝ የሚል ጓድሽ እንዲመራቸው መረጡኝ
የሚላቸውን ከገዛ ሀገራቸው በግፍ የተፈናቀሉ ዜጎች ለሀጫሞች ብሎ ሲሳደብ ሰምቼ ገርሞኝ ነበር። ውሏችሁ አንድ ላይ ቢሆንም አንቺ ከሱ
ብዙ የምትሻይ መስሎኝ ነበር።
ሌላው የገረመኝ ደግሞ 41 ፕሮፌሰሮች ማባረርን ተራ የቁጥር ነገር አድርገሽው የተባረሩት 41 ብቻ በመሆናቸው የሚጎዳ ነገር እንዳልተከተለ
አድርገሽ የተናገርሽውና ለዚያም ከዚያ በኋላ የተገኘውን የባለ ማስተርስና ፒኤችዲ ብዛት እንደማስረጃ ያቀረብሽው ገለባ ነገር ነው። 41 ብቻ
ስትይ ልክ አንድ ገበሬ ዶሮዎቹን የሚቆጥረው ነገር አስመሰልሺው። ገበሬውም ቢሆን ዶሮዎቹን አንድ ሁለት ሶስት ብሎ ይቁጠራቸው እንጂ
ገበያ ላይ ሲወጡ ላባ ብቻ የሆኑትንና ዳጎስ ያሉትን የሚሸጣቸው በተለያየ ዋጋ መሆኑን ያውቃል። ወይዘሮ Educator in Chief ምሁራን
የሚቆጠሩት ከአካዳሚክ ልምድና ችሎታቸው ክብደት ጋር መሆኑን ስተሽዋል። ከዚህ ቁጥር ጋር ከኛ መባረር በኋላ በብሽቀት በራሳቸው
የለቀቁትን ፥ ሞራላቸው ተነክቶ ተነሳሽነታቸው የተጎዳውን ከቁጥርም አላስገባሽውም። በዚህ ላይ የኛን ሁኔታ ያዩ ብዙ ውጭ ሀገር ትምህርት
ላይ የነበሩ ጓደኞቻችን በወጡበት መቅረታቸውንም ደብቀሻል። የኔ እህት በቁጥር መዋሸት ጥንቃቄ ይጠይቃል። አገር የሚያውቀው ነገር ላይ
መዋሸት ደግሞ የመሀይም ፈጠጤነት እንጂ እንዳንቺ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ዘመን ካሳለፈ ሰው አይጠበቅም። ያንቺና የአለቆችሽ የቁጥርናስታቲስቲክስ
አጠቃቀም አንድ ያንቺ ብጤ ዝነኛ የሂሳብ ሊቅ ያስታውሰኛል። ሂሳብ አዋቂው ጥቂት ቁመታቸው ረጅም ከሆነ ብዙ አጫጭር
ሰዎች ጋር ሲጓዝ የሞላ ወንዝ ያጋጥማቸዋል። ወንዙን በግር ተራምዶ ለመሻገርም ይፈራሉ። የሂሳብ “ሊቁ” አንድ መላ መጣለትና የወንዙን
ጥልቀትና የተሻጋሪውን ቁመት በሙሉ ለካ። የሰዎቹን ቁመት አማካይ (Average) አሰላና ከወንዙ ጥልቀት እንደሚበልጥ ካረጋገጠ በኋላ
ለተሻጋሪዎቹ በአማካይ(on the average) ሁሉም ሰው መሻገር ይችላል ብሎ አወጀ። ሰዎቹም በሊቅነቱ አምነው ማቋረት ጀመሩ። ምን
ያደርጋል። ቁመታቸው ከአማካይ በታች የሆኑትን በሙሉ ውሀው በላቸው። አየሽ እህቴ ቁጥር ትርጉም የሚኖረው በደረቁ ሳይሆን በይዘቱ
ሲተረጎም ብቻ ነው። ይህንን ላንቺ መንገር እንዴት ያሳፍራል መሰለሽ። አለማቀፍ ረጅዎቻችሁ ርዳታ ለመጨመር የሰራችሁትን ስራ ውጤት
አሀዝ እንደሚጠይቋችሁ በዚያም ተመስርተው እርዳታ እንደሚሰጧችሁ እናውቃለን። ትምህርት ከተጀመረ በኋላ ተንጠባጥበው የሚቀሩትን
ሺዎች ሰርዛችሁ መስከረም ላይ በዘመቻ የመዘገባችኋቸውን ተማሪዎች ቁጥር ያህል አስተማርን እያላችሁ ርዳታም እንደምታገኙ አገር
ያውቀዋል። ለፈረንጅ መዋሸታችሁ ብዙ ገንዘብም ያስገኛል። ፈረንጆቹ ውሸቱን ቢያውቁትም ግድ የላቸውም። ይህን ውሸት ለኛው
ለባለቤቶቹ እውነት ነው ብሎ መንገር ግን ዐይን አውጣነትም ሰው ንቀትም ብልግናም ነው።
የቁጥር ነገር ከሆነ አሁን እስቲ የተባረረውን የማቲማቲክሱን ፕሮፌሰር አየነው እጅጉንና ራስሽን ለምሳሌ ያህል አወዳድሪ። እውነቱን
ከተነጋገርን ለዚያ ዩኒቨርሲቲ ተብሎ ብትቆጠሩ እሱ መቶ አንቺ አንድ የምትሆኑ ነው የሚመስለኝ። ይህንኑም ላንቺ ቸር ሆኜ ነው። እኔን
አንድ ቀን አንድ አለማቀፍ ጉባዔ ላይ እንዳጋጠመኝ ምሁራን ስራውን ለምርምር እንደተገለገሉበት እያደነቁ ሲጠቅሱ ብትሰሚ ዝሆን አጠገብ
የቆመች እይጥ ሆነሽ ነበር ራስሽን የምታገኝው። የዚህን ለምሳሌ ያህል የጠቀስኩልሽን ምሁር ፕሮፋይል ይህን ማስፈንጠሪያ ጠቅተሽ
(http://www.linkedin.com/in/ayenewejigou) ምን እንደሚመስል እስቲ ተመልከች። ትንፋሽ ያሳጥራል አይደል? እሱ ወዲያው ሰው አገር
ዩኒቨርሲቲ ሄዶ ያንድ ፋኩልቲ ዲን መሆን ችግር አልነበረበትም። የኛ ሀገር ደፋር ግን አፍሽን ሞልተሽ Fit አያደርግም ትይዋለሽ። የፕሮፌሰር
አስራት ወልደየስን የህክምና እውቀትና መምህርነት ሰንት ድንጋይ ቀጥለሽ ተንጠራርተሽ ብቁነታቸውን ለመጠየቅ እንደሞከርሽ ገርሞኛል።
ካንቺ ዘለፋና እሳቸው አወጡልሽ ከሚባለው የሙገሳ ስም የትኛው ለዕውነት የሚቀርብ ይመስልሻል? ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል
የሚለውን አባባል በጥሬው የተረጎምሽው መሰለ። አሁን ባለስልጣን ሲያረጅ የሚሰጠውን የዲፕሎማትነት ሹመት መሾምሽን ሰምቻለሁ።
ይህን ዓይነት የቋንቋ አጠቃቀም ይዘሽ ምን አይነት ዲፕሎማትሲ እንደምትሰሪ ማሰብ ከባድ ነው።
41 ፕሮፌሰሮችን ማባረርና ባንቺ ስልጣን ዘመን የተገኘውን የዲግሪ ብዛት የቁጥር ነገር ብቻ ስታደርጊው የሰራሽው ሌላ ስህተት ምን ያህል
ግዙፍ እንደሆነ በቀላል ምሳሌ ላስረዳሽ። ለምሳሌ አንቺ ታስተምሪ የነበረውን ዓይነት የማስተማር ሙያ ካንድ ቢሮ ውስጥ እንድ ሴክሬታሪ
ጠርቶ እንድትሸፍነው ማድረግ ይቻላል። ያው እንዳስተማርሻት ታስተምራለች ማለት ነው። ሌላ ልጨምርልሽ። አምና አራተኛ ዓመት
የጨረሰ ኮሌጅ ተማሪ ዘንድሮ የአራተኛ ዓመት ተማሪዎችን ገብቶ የተማረውን ደግሞ በተማረበት ዘዴ “ማስተማር” ይችላል። ሁለት
ፕሮፌሰሮች በይ ባንቺ አቆጣጠር። ለነገሩ አሁን ዩኒቨርሲቲ እያላችሁ በምትከፍቱዋቸው ቦታዎች ትምህርት የሚሰጠው በዚህ መንገድ
መሆኑን ሰምቻለሁ። በዚህ መልክ የተማሩት ተማሪዎች ደግሞ አንቺ እንደዶሮዎችሽ የምትቆጥሪውን ዲግሪ ይይዙና ዞረው አስተማሪ
ይሆናሉ። አየሽው የቁልቁለቱን መንገድ? ዛሬ የኢትዮጵያን ትምህርት ጥራት ገፍታችሁ የለቀቃችሁት በዚህ የቁልቁለት ላይ ነው። እንዲህ
አይነት ትምህርት አስተምሮ እግዚአብሄርንና ታሪክን ወይም ያለምአቀፍ ስታንዳርድ ችግር ካልፈሩ ዲግሪ መስጠት የሚከለክል የለም።
በየስርቻው ዩኒቨርሲቲና የፒኤችዲ ፕሮግራም መክፈትም የሚከለክል ነገር አይኖርም ማለት ነው። ነገሩ እንዲህ ከሆነ ደግሞ በያመቱ ዲግሪ
እንደቆሎ እየዘገኑ ለመስጠት የሚያግድ የለም። ይህ ግን ከፍተኛ ትምህርት አይባልም ወይዘሮ Educator in Chief። የከፍተኛ ትምህርት
ትርጉም ባጭሩ የዕውቀትን ዳር ድንበር መግፋት (pushing the envelope) ነው ሲባል ስምተሽ እንኳን አታውቂም? የከፍተኛ ትምህርት
ማለት የከረመ ነባር ዕውቀት እንዳለ መገልበጥና ማንከባለል ማለት አይደለም። የከፍተኛ ትምህርት ዓላማ የታወቀው ነገር ላይ አዲስ ነገር
መጨመር ፣ ያልተገለጠ ነገር እንደሽንኩርት ወደ ውስጥ እየላጡ መግለጥ ፣ ቅቡል (ኮንቬንሽናል) ዕውቀትን መሞገትና መጠየቅ ፣ ኢኖቬት
ማድረግና መፍጠር ፣ ህዝብ በዘመናት ያካበታቸውን ጠቃሚ ሀገር በቀል (indigenous) ዕውቀቶች እየፈለፈሉ እያጠኑ ጥቅም ላይ ማዋል ፣
ይህን ሁሉ ደምሮ የሰውን ልጅ ኑሮ ማቅለል ማለት ነው ባጭሩ። የኔ እህት ሰው እኮ ትምህርት ቤት ሳይገባም የሚማራቸው ነገሮች አሉ ዲግሪ
አያሰጡም እንጂ። የባለፒኤችዲ መብዛትም የዕውቀት መስፋፋት መለኪያ የማይሆነው ለዚህ ነው። የኮንቴነር ኮሌጅ ከፍተው ዲግሪ
ስለሚያንበሸብሿችሁ ሰዎች ጉዳይ እኮ አንድ ጥሏችሁ የመጣ ሚኒስትር ሰሞኑን ነገረን። የዲግሪ ቁጥር ከምትነግሪን በነበረን ዕውቀት ላይ
ስንት አዲስ ነገር እንደጨመርን ፣ ምን ያህል ሳይንሳዊ ኢኖቬሽን እንደተገኘ፣ ወይም ባለዲግሪዎቹ በፈጠራ ስራቸው የሰሩትን አዲስ ስራ
ብትነግሪን ነበር ነገረሽ ትርጉም የሚኖረው። ድንጋይ ፈላጭነት ስለሚቀጠሩት የኮሌጅ ምሩቃንና ለትምህርታቸው ስለባከነው የህዝብ ገንዘብ
ምን ታስቢያለሽ ብላ ጋዜጠኛዋ ሳትጠይቅሽ ቀረች። ለሱ የምትሰጭው መልስ ናፍቆኝ ነበር።
ርግጥ ነው ሁሉንም የተባረርነውን መምህራን መተካት ይቻላል። ቀላል ያልሆነ ጊዜና ንብረት ግን ይወስዳል። ለኢትዮጵያ ደግሞ ጊዜ ከጎኗ
አይደለም። የሰው ሀይል መገንባት የተቃጠለ ቤት መልሶ እንደመገንባት ቀላል አይደለም። ለዚህ ነው እህቴ በተባረርነው ሰዎች የተፈጠረውን
ጥፋት እንደ ሀገር ኪሳራ ወስዶ ከመሄድ ውጭ በምላስ መድፈን የማይቻለው። ለፖለቲካ ስንል ሀገሪቱን ያስከፈልናት ሂሳብ ነው ብሎ
መቀጠል ማን ገደለ? ታዛቢ ቢኖር እንጂ ጠያቂ እንደሆን የለ። የተባረርነውን ብዙ መምህራን ቦታ እንዴት ባጭር ጊዜ መሸፈን እንደማይቻል
ልንገርሽ። ራሴን ምሳሌ ልስጥሽ። እኔ ለምሳሌ ካንቺ ባገልግሎት ዘመንም በዕድሜም የማንስ ገና ብዙ ልሰራ ተስፋ የማደርግና ብዙ ያልሰራሁ
ጁኒየርና መምህር ነበርኩ። ከብዙዎቹ ከተባረሩት በጣም ያነሰ ደረጃ ላይ ነበርኩ። በምማርበት መስክ ግን በዓይነቱና በዘመኑ አዲስ የሆነ
የዕውቀት ዘርፍ ተማሪ ነበርኩ። ያን ጊዜ ገና እየተጀመረ የነበረውን GIS(Geo-information Systems) ቴክኖሎጂ ከህክምና ሳይንስ ጋር
አገናኝቶ በመጠቀም ሀገራችን ላይ የሰፈኑና በየጊዜው የሚከሰቱ በሽታዎችን ከባቢያዊ ባህርይ ከተጠቂ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ባህሪ
ጋር ቁርኝታቸውን በማግኘት ለመቆጣጠር የሚበጅ ሳይንስ ነበር። ዩኒቨርሲቲው ውስጥ የነበረው ሜዲካል ጂዖግራፈር እኔ ብቻ ነበርኩ። ያ
ድሀ ህዝብ ፈረንጅ ፕሮፌሰር በዶላር ቀጥሮ ነው ያስተማረኝ። እስከአሁን እዚያ ብኖር ኖሮ ብዙ ተማሪዎች አስተምርና ፣ ምርምርም እንሰራና፣
ምናልባትም ተላላፊ በሽታ ሰርጭትን አስቀድሞ የማየትና መመከቻ ዘዴና ሞዴል በማበጀት ህይወት አድን ዕውቀትና ዘዴ ከሌሎች
ባለሙያዎች ጋር ሆነን እንገነባ ነበር። ይህ ቀዠት ሊመስልሽ ይችላል። ለኔ ህልሜ ነበር። ይህ ለኛ አይነት ደሀ አገር የሚሆን ፕሮግራም
በነበርኩበት ዲፓርትመንት እስከዛሬም አለመጀመሩን አውቃለሁ። እኔ ስባረር እንደቀረ ቀረ። ዛሬ ለትምህርቴ ስሙኒ ያልከፈለው የስደት
ሀገሬ ይህን ሙያዬን በደንብ ይጠቀምበታል። ጊዜ የለም እንጂ ሌላም ብዙ ምሳሌ እሰጥሽ ነበር። እኔ ትንሹ ይችን ታክል ካጎደልኩ ግዙፎቹ
ምሁራን ምን ያህል እንደሚያጎድሉ ብቻ አስቢው።
ደብዳቤዬን ከመዝጋቴ በፊት ትምህርትን አስመልክቶ ስለተናገርሻቸው ሌሎች አሳፋሪ ነገሮች ትንሽ ልንገርሽ። በቃለ ምልልስሽ ላይ
ከሰቀጠጡኝ ነገሮች አንዱ እስከ አራተኛ ክፍል ድረስ ተምረው ማንበብና መጻፍ ሳይችሉ ስለቀሩት ተማሪዎች ተጠይቀሽ የሰጠሽው መልስ
ነበር። እነዚያን እንደጊኒ ፒግ የተጫወታችሁባቸውን የድህ ህዝብ ልጆች ለዚያ ሁኔታ የበቁበትን ምክንያት ካለምንም ይሉኝታ እንዳለ
በመምህራኑ ላይ ደፈደፍሽው። ቆየት ብለሽ ደግሞ ወደፊት ቴሌቪዥን ተክቶን ስራችንን እናጣለን ብለው የፈሩ መምህራን ናቸው ችግሩን
የፈጠሩት ስትይ መምህራኑን ምንም የማያውቁ ቂሎች አስመስለሽ ሰደብሻቸው። አነጋገርሽ የጥጋበኛ ይመስላል ያልኩሽ ይህን ሁሉ ታዝቤ
ነው። እንዲመክሩበት ያልጋበዛችኋቸውን የፖሊሲ ችግር ተቋቁመው እንደዚያ እንደሻማ እየቀለጡ በድህነት እየተቆራመዱ የሚያስተምሩ
መምህራን ካለቃቸው ከስድብ የተሻለ ይገባቸው ነበር። ያንቺንና ያለቆችሽን ጥፋትና ተጠያቂነት ግን “ቻሌንጅ ነበረብን” በምትባል የጮሌዎች
የንግሊዝኛ ቃል በኩል አድርገሽ ለመደበቅ ሞከርሽ።
ሌላም ሳልነግርሽ ማለፍ የማልፈልገው አለ። ስለነዚያ ከሻሸሜኔ አካባቢ ቢሮሽ ድረስ ላቤቱታ መጥተው የተቃዋሚዎች ፕሮፓጋንዳ ገዝተው
ቋንቋችን ወንዝ አያሻግርምና ልጆቻችን ባማርኛ ቋንቋ ይማሩልን አሉ ብለሽ ስለተዛበትሽባቸው ሽማግሌዎች አንድ ነገር ሳልነግርሽ ብቀር
ውለታ አጎድልብሻለሁ። ሽማግሌዎቹ ብዙ እንደበለጡሽ የገባሽ አልመስለኝም። ባንቺ ቤት ቋንቋችን ወንዝ አያሻግርም ያሉት ያው
የትምክህተኞችን ወሬ ሰምተው ራሳቸውን በመናቃቸው ነው። ቋንቋ ወንዝ አያሻግርም ሲሉ ልጆቻችን አማርኛ ካልቻሉ ባካባቢያችን
ስለሚቀሩ በትልቅ ሀገር ውስጥ ተዘዋውረው መስራት አይችሉም ሊሉሽ ፈልገው እንጂ እናንተ ባትከልሉትም የጎሳቸው መኖሪያ የት ድረስ
እንደሆነ አጥተውት እንዳይመስልሽ። አማርኛም ባህር ስለማያሻግር ነው እንግሊዝኛ የምንማረው አይደል? አማርኛም ቢሆን በብዙ ያገራችን
አካባቢዎች የማያሻግራቸው ወንዞች አሉ። ይህ እውነት እንጂ ምኑ ነው ስድብነቱና ንቀትነቱ ወይም አለማወቅነቱ? እንደ ቋንቋ ወላይትኛ
ካማርኛም ከንግሊዝኛም አያንሰም። የሰዎች የኑሮ መሻሻል ዕድል(opportunity) ሰፋት ግን መናገር ከሚችሉት ቋንቋ ጂዖግራፊያዊ ስፋትና
በተለይ የሰራ ዕድል ባለባቸው ከተሞች ውስጥ ብዙሃኑ ከሚናገሩት ቋንቋ ችሎታ ጋር የተያያዘ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ አማርኛ በቅጡ
አለመቻል ያንድን ሰው የኑሮ ህልምና የማደግ ጣራ ይገድባል። ሽማግሌዎቹ ይህ ገብቷቸዋል። አንቺና አለቆችሽ ቋንቋውን ከአማራ ረጋሚ
ፖለቲካችሁ ጋር ስለምታገናኙት ነው የተምታታባችሁ። እነዚያ ሽማግሌዎች ደግሞ ብዙ ልጆች ባካባቢያቸው ባማርኛ ተምረው ከፍ ያለ ዕድል
ሲያገኙ አይተዋል። ቋንቋ እንደ አካፋና ዶማ መሳሪያ መሆኑ ገብቷቸዋል። ባለስልጣናቱ ለልጆቻችሁ የማትመኙትን ለነሱ
እንደተመኛችሁላቸው አውቀዋል። ለመሆኑ አሁን አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በወላይትኛ ብቻ እየተናገረና ባስተርጓሚ ጠቅላይ ሚኒስትር
ይሆን ነበር ብለሽ ታምኛለሽ? አቶ መለስም ጥሩ አማርኛ ተናጋሪ ባይሆን ኖሮ እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትር የህወሀትም መሪ ለመሆን የሚቸገር
ይመስለኛል። ሰው በራሱ ቋንቋ ቢማር ጥሩ ነው። ትምህርት ያቀላል። በሁለተኛ ቋንቋ ተምሮ ሰው አዋቂ መሆን የማይችልና ጥቅም የማያገኝ
አስመስለሽ ያወራሽው ግን ተራ ድንቁርና ነው። ያማርኛን ቋንቋ ራሱን ካዳበሩት ሰዎች ውስጥ ብዙዎች አማራ ያልሆኑ አማርኛን በሁለተኛ
ቋንቋነት የተማሩ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የምታውቂም አይመስልም። አማርኛ አለመቻል ባለንበት ባሁኑ ዘመንና ለመጭውም ብዙ
ዓመታት ይጎዳል። የአዳጊውን ትውልድ ዕድል (opportunity) ይቀንሳል። ይህን የሚጠራጠር መሬት ላይ ያለውን ዕውነት ማየት የማይችል
ወይም ኢትዮጵያን የባቢሎን ግንበኞች አገር በማድረግ የማይግባባ ህዝብ ፈጥሬ ትርፍ አገኛለሁ ብሎ ያሰበ ብቻ ነው። እንዴውም ኦሮምኛን
አማርኛ ላይ ብትጨምሩት ሀገርነታችንንና ህዝቡን ብዙ ትጠቅሙት ነበር። አማርኛ ከማንም ቋንቋ በልጦ ሳይሆን ታሪክ በሰጠው አጋጣሚ
ምክንያት ባብዛኛው ኢትዮጵያ የክተማ (urbanization)ና የሀገሪቱ ዘመናዊ ኢኮኖሚና ኢንዱስትሪያላይዜሽን ቋንቋ ነው። ወደፊትም ለረጅም
ጊዜ ሆኖ መቀጠሉ አይቀርም። ታዲያ ሽማግሌዎቹ ምን አጠፉ? ሽማግሌዎቹ ይህን ፊት ለፊት አይተዋል። የምታገለግይው ፖለቲካ ላንቺ ወደ
ማጅራትሽ አዙሮ ሰውሮብሻል። ይህ ብጅጉ ሊያሳፍርሽ ይገባል።
ፖሊሲያችሁ አንድ ትውልድ ስለመጉዳቱ ለተጠየቅሽው ጥያቄም ያሁኑን ኢኮኖሚ እድገት ታዲያ እንዴት ተገኘ? ለመሆኑ ከሀያ አመት በፊት
ከነበረችበት አገራችን አልተሻለችም?” ብለሽ በጥያቄ መልሰሻል። እኔ የማየው የኤኮኖሚ እድገት በትምህርት አጋዥነት በተፈጠረ ዕውቀትና
ኢኖቬሽን ሳይሆን ከውጭ በሚገኝ ርዳታና በገፍ የተሰደደው ኢትዮጵያዊ በሚልከው ገንዘብ የተገኘ መሆኑን ነው። ለገበያ የምታቀርቡት
እንደሆን ያው እንደዱሮው ቡናና ቆዳ ነው አይደል? ከትምህርት በተገኘ አዲስ ግኝት ይህ ተገኘ ሲባል ሰምቼ አላውቅም። እስከ አርባ በመቶ
የሚደርስ የገጠር ልማት በጀት በርዳታ እንደሚሸፈንና ከሰሀራ በታች ዋና በርዳታ የምትኖር ሀገር እያስተዳደራችሁ መሆኑ ሚስጥር
አይደለም። ብድሩም 20 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ይባላል። ይህን መጠን በርቀት እንኳን የሚቀርብ ገንዘብ ቢያገኙ በዘመናቸው በነበረው
የተማረ ሰው ሀይል ብቻ አሁን ተሰራ የምትሉትን ነገር መስራት ለደርግም ለኃይለስላሴም አያቅታቸውም። እዚያ አገር ውስጥ በትምህርት
አዲስ ዘዴ አፍልቃችሁ የፈጠራችሁትን የሀገር ሀብት አንድ ሁለት ብለሽ መቁጠር አትችዪም። ለምሳሌ ገበሬው ከሚያመርተው እህል ከ 30
እስከ 40 በመቶ ያህል በቴክኖሎጂ ችግር ምክንያት ውድማና ርሻው ማሳ ላይ እንደሚባክን ዛሬም ባለሞያዎች ይነግሩናል። ቢከፍቱ ተልባ
የትምህርት ፖሊሲያችሁ እህል ተለምኖ በሚኖርበት ሀገር ይችን እንኳን የሚያስወግድ የገጠር ቴክኖሎጂ ዕውቀት ማፍራት አልቻለም። ባቡር
መንገድ ሰራን ፣ ህንጻ ገነባን የምትሉት ፕሮፓጋንዳ ዱሮ አጼ ኃይለስላሴን “ውሀ ፎቅ ላይ ያወጣ ንጉስ” ከሚለው ከንቱ ውዳሴና ፕሮፓጋንዳ
ብዙም አይለይም። የደብዳቤዬ ትኩረት የትምህርት ስታርቴጃችሁን መተቸት አይደለም እንጂ ብዙ ልነግረሽ የምችለው ነበረኝ። ይህን ደብዳቤ
እየጻፍኩ አንድ የህክምና ፕሮፌሰር አአዩ ሜዲካል ፋኩልቲ ውስጥ ሲያስተምር የተመለከተውን አስደንጋጭ አስተያየት አነበብሁ። በቁጥር
ልታደልቢው የምትሞክሪው የትምህርት ፖሊሲ ምን ያህል ሀገር አደጋ ላይ የጣለ መሆኑን እንደ አንድ ዜጋ እንድትመለከችው እዚህለጥፌልሻለሁ
(http://www.ethiomedia.com/11notes/2816)። ቢያንስ በሰው ህይወት ላይ ብዙ ቀጥተኛ እጅ ያላቸውን የሀኪሞች
ትምህርት የቁጥር ነገር ባታደርጉት ምን ትሆናላችሁ? ይህ ፕሮፌሰር ሀኪም ድፍረቱን አግኝቶ ይህን ባደባባይ መረጃውን አቅርቦ ስለተቸ ክብር
ይገባዋል። ብዙ ጊዜ ለኔ ብጤ ተችዎቻችሁ (critics) እንደምትሰጡት መልስ ከሆነ ወንጀለኛ ብትሉት አይገርመኝም።
የሰዎች መሻሻል የሚገኘው ዝቅተኞቹ ወደ ላይ እንዲያድጉ በማገዝ ሳይሆን የተሻሉትን ዝቅ በማድረግ ነው የሚለውን የመለስ ዜናዊ Reverse
Affirmative Action የፖሊሲ መመሪያ ባታደርጉትና ቢያንስ ከነችግሩ በዓለም ተወዳዳሪ ሆኖ የቆየውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለበት
ብታቆዩትና በላዩ ብትጨምሩ ለሌሎቹ የሚተርፍና ብዙ ቀዳዳ የሚሞላ (Flagship) ተቋም መሆን ይችል ነበር። ዛሬ ይህን ተሳድቦም ፣
ተቆጥቶም ፣ አስፈራርቶም ሰዎች እንዳይጠይቁ ማድረግ ይቻላል። ሁላችንም በማንኖርበት የወደፊቱ ዘመን ግን ታሪክ ይህን ጥይቄ ጮሆ
እንዳይጠይቅና ፍርድ እንዳያገኝ ማድረግ አይቻልም።
እህቴ ተናግረሽ ብዙ አናገርሽኝ። ኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ከባድ ዝናብ መምጣቱን እንደሚያበስር ደመና የሚያስገመግም የህዝብ ብሶት ድምጽ
ከሩቁ ይሰማኛል። እሱ ከሚያስነሳው ማዕበል ይሰውርሽ።
(Fekadeshewakena@yahoo.com)
December 3, 2014

Human Rights in Polarized Ethiopia: the need for collaboration By Aklog Birara (DR)

Part one of three
Remark
This series is intended for the benefit of those who did not attend the forum.
Why are human rights essential?
If we respect ourselves as people and want the world community to respect us and support our causes, we must face up to the demanding responsibility of owning and leading the struggle for human dignity, rights, the rule of law and representative governance ourselves. No one will do it for us. In terms of justice, rights, fair distribution of incomes and access to opportunities, sustainable and equitable development and the like the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) controlled and led government of Ethiopia has failed. This is one part of the story. The other is what the rest of us are doing to redress the situation. Blaming others, including the repressive regime is easy. Offering a compelling alternative is hard

Thursday 4 December 2014

ተመስገን ደሳለኝን ተቀበልኩት (ሕገ-መንግስት ሆይ የት ነው ያለኸው?) – ከክንፈሚካኤል ደበበ በረደድ (አበበ ቀስቶ) ከዝዋይ ወህኒ ቤት

ከክንፈሚካኤል ደበበ በረደድ (አበበ ቀስቶ) ከዝዋይ ወህኒ ቤት

Temesgen-Desalegn41ቀኑ ቅዳሜ በመሆኑ ቤተሰቦቻችን እኛን ለመጠየቅ /ፈርዶባቸው የለ/ ወደ ዝዋይ ወህኒ
ቤት የሚመጡበት ሰዓት ደርሶ፣ ተጠርተን እንደወጣን፣ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ የጠየቅናቸው
ነገር ቢኖር፣ ምን አዲስ ነገር አለ የሚለውን የተለምዶ ጥያቄያችንን ነበር፡፡
በዕለቱም የመጣልን የምስራች ልበለው ዜና አሊያም መርዶ ጋዜጠኛ ተመስገን ሦስት
(3) ዓመት ተፈረደበት የሚል ነበር፡፡ በዜናው አልተደነቅንም፤ አልተገረምንም፤ ምክንያቱም
በሥልጣን ላይ ያለው የህወሓት /ኢህአዴግ/ አምባገነን መንግስት፣ ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዚህ ሌላ ሊሸልመው
የሚችለው መልካም ሽልማት /ሜዳሊያ/ የለውምና፡፡ በነገራችን ላይ ዜናው ለኔ ፍጹም አልገረመኝም፤ እገረም የነበረው
አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ተመስገንን በነጻ ቢለቀው ነበር፡፡
የሆነው ሆኖ፣ ከቤተሰብ ጥየቃ ተመልሰን ገና ምሳ በልተን አረፍ እንዳልን ግን፣ የሰማነውን ዜና እውነታ በአካል
የሚያረጋግጥልን አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ፍራሹን ተሸክሞ እኛ አለንበት ጭለማ ቤት /የቅጣት ቤት/ ድረስ
መጣ፡፡ ዓይኔን ማመን እስቲያቅተኝ ድረስ ተጠራጠርኩ፤ ግን ሆነ፡፡ ተመስገን መጣ፡፡ እናም ውለን ሳናድር ተመስገን
ደሳለኝን ተቀበልኩት! እነሆ ተመስገን ዝዋይ ከመጣ ዛሬ 15 ቀን ሆነው! … ሕገ-መንግስት ሆይ የት ነው ያለሽው!?
ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዳሉ፤ እግረ መንገዴን እስቲ አንድ ገጠመኜን ደሞ ላጫውታችሁ፡፡ ህወሓት
/ኢህአዴግ/ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ በሁኔታው ያልተደሰትን ጓደኛማቾች ተሰባሰበን፣ ከኛ ቀድመው ከብላቴ
ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ወደ ኬንያ የተሰደዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችንና ሌሎች ወገኖቻችን ተቀላቅለን ለመታገል
በመወሰናችን ተሰባስበን፡፡ ወደ ኬንያ የስደት ጉዞ ጀመርን፡፡ ይህ የሆነው ግንቦት 23 ቀን 1983 ዓ.ም ከሃያ ሦስት ዓመት
በፊት ነው፡፡
ታዲያ በዚህ ጉዟችን በአጋጣሚ አገረማርያም ከተማ የማረፍ ዕድል ገጥሞን ነበር፡፡ እዚያም አቶ አብርሃም ያየህና
ጓድ ጌታቸው ሮበሌ (የአኢወማ ሊቀመንበር የነበሩ) ወደ ኬንያ ለመሸሽ በዚህ ሲያልፉ ተይዘው ያቤሎ ከተማ ፖሊስ
ጣቢያ ታስረዋልና እባካችሁ ያቤሎ ከተማ ጐራ ብላችሁ አስፈትታችሁ ይዛችኋቸው ሂዱ የሚል የወገን ጥቆማ ደረሰን፡፡
እኛም ይህን ጥቆማ ተቀብለን በሰማነው ዜናም ተደናግጠን ጉዟችንን ወደ ሞያሌ በማድረግ፣ ከምሽቱ 3፡30
ሰዓት ላይ ያቤሎ ከተማ ደርስን፡፡ በወቅቱ ህዝቡ በነበረው /በተከሰተው/ ሁኔታ እጅግ ተቆጥቶ ከተማዋን ከዘራፊና
ከዝርፊያ ለመጠበቅ በሚል ተደራጅቶ በየተራ ከተማውን ይጠብቅ ስለነበር መኪናችንን አስቁመው ከመሸ ከተማ መግባት
እንደማንችል በትህትና አስረድተውን፣ ከከተማው ወጣ ብለን በማደር፣ ማለዳ መግባት እንደምንችል ነግረውን፣
ተስማምተን ከከተማው ወጣ ብለን አደርንና ጠዋት ማለዳ ላይ ወደ ያቤሎ ከተማ ገባን፡፡
ወዲያውም ወደ ያቤሎ ፖሊስ ጣቢያ ሄድን፤ የታሰሩትን አቶ አብርሃም ያየህና ጓድ ጌታቸው ሮበሌን እንዲፈቱና
እኛ ጋር ወደ ኬንያ እንዲሄዱ እንፈልጋለን ስንል በወቅቱ ለነበሩ የፖሊስ አባላት ጥያቄ አቀረብን፡፡ ፖሊሶቹም ፍጹም
ትህትና በተሞላበት ሁኔታ ተቀብለውን ካነጋገሩን በኋላ፣ ሁለቱ ሰዎችና ሌሎች አባሪዎቻቸው ትናንትና ተፈተው ወደ
ሞያሌ ሔደዋል አሉን፡፡ እኛም ለፈጸሙት መልካም ተግባር አመሰግነን፣ ጉዟችንን ወደ ሞያሌ ቀጠልን፡፡
ልብ አድርጉ! … ያኔ በዚያ በ20ዎቹ የመጀመሪያ እድሜ ላይ የነበርን ወጣቶች የታሰሩ ወገኖቻችን ካልተፈቱ
በሚል ነበረ ስንቆጣ የነበረውም፣ የጮህነውም፤ ዛሬ በጉልምስና እድሜያችን ግን በግፍ በወህኒ ቤት ተወርውረን ምንም
ማድረግ ባንችል፣ ልክ እንደኛ የግፍ ሰለባ የሆነውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ተቀበልነው፡፡ ከነዚያ አገራቸውን
ተመስገን ደሳለኝከውድቀት ለማዳን ሲሉ ብላቴ ከዘመቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል ሁለቱ አሁን ከኔ ጋር ባንድ ቤት ሆነው በእስር
እየማቀቁ ነው፡፡
ልብ በሉ! … ተመስገን ደሳለኝን የተቀበልነው ቤተመንግስት አይደለም፤ ሸራተን ወይም ሒልተን ባለአምስት
ኮከብ ሆቴል አይደለም፡፡ ካምቦሎጆ አይደለም፡፡ ከ23 ዓመታት በኋላ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳናሳይ፣ ያችን እንኳ በዚያች
ዕድሜያችን ያሳየናትን የፍቱልን ጥያቄ ማቅረብና እምቧ-ከረዩ ማለት አቅቶን፤ የነጻነት፣ የፍትህ፣ የዲሞክራሲና የእኩልነት
ጥያቄያችን ባለመመለሱም የተነሳ፣ እድለ ቢስ ሆነን ነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን የተቀበልነው፤ በዝዋይ ወህኒ ቤት
በሚገኝ 9ኛ ቤት በሚባል ጭለማ ቤት /የቅጣት ቤት/ ውስጥ ሆነን ነው፡፡ እረ ጐበዝ አንድ በሉ!… ይህ ነገር ማቆሚያው
የትና መቼ ነው?…
ተመስገን ደሳለኝ በአካል ወደኛ የመጣው ቅዳሜ በ22/02/2007 ዓ.ም ይሁን እንጂ፣ በተደጋጋሚ “ያልተገሩ
ብዕሮችና!” ሌሎች የኢቲቪ ዶክመንመተሪ ፊልሞች፣ እንዲሁም በኢቲቪ የሚዲያ ዳሰሳ ፕሮግራሞች አማካኝነት
ሳይወሰንበት በፊት በሀሳብ ከኛ ጋር ተቀላቅሎ ነበር፡፡
እኛም ከነዚህ ዘገባዎች በመነሳት፣ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ዕጣ-ፈንታ የተለመደው የግፍ እስራት ሊሆን
እንደሚችል ከህወሓት /ኢህአዴግ/ ባህሪ የተነሳ፣ መገመት ብቻ ሳይሆን፣ ሙሉ ለሙሉ አምነን ነበር፡፡ የሆነውም ደግሞ
ይህ ነው፡፡ ምክንያቱም በአፍሪካ ውስጥ፣ በተለይም በእኛይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነት፣
እንዲሁም ለሰው ልጆች የመናገርና የመጻፍ ነጻነት የሚታገል ታጋይ ሁሉ፣ ዕጣ- ፈንታው እስራት፣ ግርፋት፣ ስደት እና ሞት
ብቻ ነው፡፡ ተሜም የመረጠው ለነጻነት፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነትና ለዲሞክራሲ እየታገለ የሚመጣውን መከራ መቀበልና
የሚከፈለውንም ዋጋ መክፈል ብቻ ነው፡፡ “የፈራ ይመለስ!” አይደል ያለው፡፡ ቃሉንም በተግባር አደረገው፡፡ ብራቮ ተሜ!!!
ተመስገን ፍራሹን ተሸክሞ እኛ ወዳለንበት ጭለማ ቤት /ቅጣት ቤት/ ሲመጣ፣ መጀመሪያ የያሁት እኔ ነበርኩ!…
በቀጥታ ተንደርድሬ ተመስገንን ተቀበልኩት፡፡ ሌላ ምንም ምርጫ የለኝም፡፡ እሱም ቢሆን እኔንና ጓደኞቼን ሲያይ፣ ለቤቷ
እንግድነት አልተሰማውም፡፡ ከዚያማ ምን ልበላችሁ፣ የተራብነውን መረጃ አንድ ባንድ አብራራልን፤ ዘረገፈልን ማለት
ይቀላል፡፡
ለኔ እንደ ምግብ ዝርዝር (ሜኑ) የተሰናዳ – ዝርዝር መረጃ ሳገኝ፣ በ3 ዓመቱ የእስራት ዘመኔ የመጀመሪያዬ
በመሆኑ ተደስቻለሁ፡፡ እንደውም የተሰማኝ እርካታ ቃላት ሊገልጸው ከሚችለው በላይ ነው፡፡ በ21ኛው ክ/ዘመን መረጃ
የተራብነውና የተቸገርነው የኢህአዴግ መንግስት ባለንበት እስር ቤት ከኢቲቪ ውጭ ማየትና ማድመጥ ስለከለከልንና
ስላፈነን ነው፡፡
ሰው መቼም ወደ እስር ቤት ይምጣ ባይባልም እንኳ፣ በተለይም ለወዳጅ ይህን ባይመኙለትም፣ እንደ ተመስገን
ያለ አንጀት አርስ የመረጃ ሰው ለአንድ- አንድ ቀን ቢመጣልን የእስራት ጊዜያችንን ያጣፍጥልን ነበር፡፡ ግን! … ለምን? …
ለምን?… ለምን ይምጣ!?
ለትኩስ መረጃ ካለኝ ጉጉት አንጻር ይህንን ብልም እንኳ፣ የተመስገን ደሳለኝ መታሰር ለእኔ ፍጹም- ፍጹም
ተገቢም አስፈላጊም አይደለም፡፡ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በውሳኔያቸው በፍጹም ተሳስተዋል፡፡ ኢህአዴጎች ሆይ!…
ተመስገንን እንዲታሰር በመወሰናችሁ በዲሞክራሲ ላይ እጅግ ተሳልቃችኋል!… ድሮም የሌላችሁን የመንግስትነት ግርማ
ሞገስ በድጋሚ አጥታችሁታል፡፡ የራሳችሁ ሕገ-መንግስት በአንቀጽ 29 ላይ የሚደነግገውን ድንጋጌ በመጣስ ለሕገ-
መንግስታችሁ ክብር አሳጥታችሁታል … ኢህአዴግ ሆይ ሕገ-መንግስትህ ወዴት ነው ያለው፤ ፈልገህ ካገኘኸው ላክልኝ! …
እናም ወገኖቼ! በተመስገን ደሳለኝ ላይ የተጣለውን የግፍ ውሳኔ አጥብቄ እቃወማለሁ! … ደግሜ- ደጋግሜ አወግዛለሁ!››
ከ5 ዓመት በፊት በወጣ አንድ “አዲስ ራዕይ!” በሚባል የኢህአዴግ መጽሔት ስለመተካካት በሚያወራው ጽሑፉ
ላይ “በአሁኑ ሰዓት ያለው መተካካት፣ የሰው መተካካት እንጂ፣ የፓርቲ መተካካት አይደለም፤ በአሁኑ ሰዓት የፓርቲ
መተካካት አይኖርም፡፡ እንደ ኢህአዴግ አስተሳሰብ የፓርቲ መተካካት ሊኖር የሚችለው ከ3 እና ከ4 ምርጫዎች በኋላ
ነው፡፡ እስከዚያ ድረስ ኢህአዴግ በሥልጣን ላይ ያለማቋረጥ መቀጠል አለበት›› ይላል፡፡ ካልተሳሳትኩ ይህንን ያነበብኩት
ከ2002 ምርጫ በፊት ይመስለኛል፡፡ ታዲያ ይህንን የኢህአዴግ አቋምና ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ ሲባል፣ ለሂደቱ እንቅፋት ይሆናሉ ተብለው
የተጠረጠሩና የተገመቱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማርያን (ብሎገሮች) ሁሉ በሰበብ-በአስባቡ
ተሰብስበው ወደ ወህኒ ቤት ይወረወራሉ፡፡ አገር ጥለው እንዲሰደዱ ይገፋሉ፡፡ ምክንያቱም ኢህአዴግ ላቀደውና ላስበው
ረዥም የሥልጣን ዘመን እድሜ እንቅፋት ናቸውና፡፡ እናም ተመስገን ደሳለኝ የዚህ የኢህአዴግ እቅድ ቀንደኛ ተቃዋሚ
ተደርጎ ስለሚወስድና ቢገፉት… ቢገፉት ከሀገር አልሰደድ ስላለ፣ በግፍ ወህኒ ቤት እንዲገባና እንዲማቅቅ ተፈረደበት፡፡
አለቀ በቃ! እውነታውና ሃቁ ይህ ነው፡፡
ከላይ በገለጽኩት ጉደኛ የኢህአዴግ መጽሔት ላይ “አንድ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ የጡረታ
መውጫ እድሜ 65 ዓመት ነው” ይላል፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች 65 ዓመት እስቲሞላቸው ድረስ መጓዝ የፈለጉትና ለመጓዝ
የወሰኑት የዲሞክራሲን መርሆዎች በመጣስና በመጨፍለቅ ነው፡፡ ዕድሜያቸው 65 እስቲሞላ ድረስም፣ እንደ ጋዜጠኛ
ተመስገን ደሳለኝ አይነት ቆራጥና የማይንበረከክ ጋዜጠኛ እጣ ፈንታው የግፍ እስራት ነው፡፡ ምክንያቱም
አልተንበረከክምና፡፡ የቆመበትን የጋዜጠኝነት መርህ ለኢህአዴግ በሚመች መልኩ አልሸጥምና፡፡ እንደውም ከዚህ
ከኢህአዴግ ፍላጎት በተቃራኒው “ጉዞዬን እስከቀራኒዮ ያደረገው!” በሚል ተፋልሟቸዋልና “እምቢ አልንበረከክም!” ብላ
ዘማሪ አዜብ ኃይሉ እንደዘመረችውም ተመስገንም እምቢ አልንበረከክም እያለ የመከራን ጽዋ በመጎንጨት፣ መጓዝን
መርጧል፡፡ ብራቮ ተሜ…በርታ!…በርታ!
እኔ ግን በዚህ በ21ኛው ክ/ዘመን እጅግ አድርጌ ለአገሬና ላልታደለው ህዝቧ አዘንኩ! … አፈርኩ! … ምክንያቱም
በዚህ ሥልጣኔ ባበበበት ዓለም፣ የቀደሙትን ትተን በዚህ በ2 ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ20 በላይ የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች
አገር ለቀው ተሰደዋል፡፡ ሦስት ጋዜጠኞች እና ስድስት ጦማርያን (ብሎገሮች) ተከሰው ፍ/ቤት እየተመላለሱ ነው፡፡
ቀደም ሲል፣ የግፍ ፍርድ የተጣለባቸው እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርዕዮት ዓለሙን
የመሳሰሉት ጋዜጠኞችን በወህኒ ቤት መማቀቅ ከጀመሩ 3 ዓመት አልፏቸዋል፡፡ ይህ ሁሉ አነሰ ብሎ አምባገነኑ የኢህአዴግ
መንግስት የተዘጋና የተቋረጠ ክስ ከመንደርደሪያ ላይ አንስቶ ቆሻሻውን በማራገፍና እንደ አዲስ በመቀስቀስ ተመስገን
ደሳለኝን 3 ዓመት ፈረደበት፡፡ … እኔ ግን! … እኔ ግን ይህንን የግፍ ውሳኔ አጥብቄ እቃወማለሁ! አወግዛለሁም!
ከተሰደዱት ጋዜጠኞች መካከል፣ ቀድሞ የኢትኦጵ ጋዜጣ ባልደረባ ሆኖ የማውቀው ሚሊዮን ሹርቤ፣ በነጻነት
እየተናገረና እየጻፈ ባገሩ መኖር አቅቶት፣ በስደት አገር መሞቱም እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ ይህም ልብ ይነካል፡፡ እናንተ የነጻው
ፕሬስ አባላት ሆይ፣ የመከራ ዘመናችሁ መቼ ያበቃል! … ስለእናንተ ልቤ በእጅጉ ያዝናል፤ … በሀዘንም ብዛት ይደማል፡፡
ነገር ግን ሁሌም በእናንተ እኮራለሁ፡፡ … በመልካም ተግባራችሁ ለአገራችሁና ለህዝባችሁ ስትሉ ስለምትከፍሉትና
ስለከፈላችሁት መራር መስዋዕትነት ልባዊ አድናቆትና ክብር አለኝ!
ኢህአዴግ ተመስገንን ለምን ፈራው?… በተመስገን የሚመራው አሳታሚ ድርጅት በተለያዩ የህትመት ውጤቶቹ
ከፍተኛ የህትመት ኮፒዎችን በማሳተም፣ በአገራችን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲያብብ ከፍተኛ አስተዋጽ
በማድረጉ የተለያዩ የፖለቲካና የእምነት ልዩነት ያላቸውን ጹሑፎች በነጻነት በማስተናገድ ከኢህአዴግ ፍላጎት ውጭ
በመንቀሳቀሱ፣ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ከሚታተሙ የፕሬስ ውጤቶች የተሻለ ተነባቢና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ አመኔታ
በማትረፉ ጭምር ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
ይህ ኢህአዴግን ያላመመው ምን ይመመው?… በዚህ ያልተቆጣ በምን ይቆጣ?… በነገራችን ላይ የኢህአዴግን
ከፍተኛ አመራሮች ከመጽሐፉ ቅዱስ ቃል በእጅጉ የሚገባቸው “እኔ ቀናተኛ አምላክ ነኝ” የሚለው ቃል ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ
ቀኑ- ቀኑና ቀናተኛ መንግስት ሆኑ፤ ቀናተኛ መንግስት ደግሞ በግፍ ከማሰር፣ ከመግረፍ፣ ከመግደልና ዜጎች አገራቸውን
ጥለው እንዲሰደዱ ከማድረግ ውጭ ስራ የላቸውምና ኢህአዴጎችም ተመስገንን በማሰር ይህንን የአምባገነንነት
መገለጫቸው በተግባር አሳዩን፡፡
እኔ ባለኝ መረጃ፣ ኢህአዴግ ፍትህ ጋዜጣን በህትመት ሂደት ላይ ሳለች ሲያግታት፣ ተመስገንና ጓደኞቹ፣ አዲስ
ታይምስ መጽሔትን ይዘው ብቅ አሉ፤ አዲስ ታይምስ መጽሔት ከሕትመት ፈቃድ ውጪ ስትደረግ ደግሞ ልዕልና ጋዜጣን
ይዘው ብቅ አሉ፤ ኢህአዴግ ይህንንም በተለመደው ስራና ጥበቡ አቋረጣቸው፡፡ ይሄኔም አይታክቴዎቹ- ተመስገንና ጓደኞቹ
ፋክት መጽሄትን እያሳተሙ በሰፊው ህዝብ ዘንድ ተነባቢነታቸው ቀጠለ፡፡ይህን ከድፍረት የቆጠረው የኢህአዴግ መንግስት በተመስገን ደሳለኝ ላይ እየከፈተ ካቋረጣቸው 126 ክሶች
ውስጥ፣ የሶስቱን ክሶች ቆሻሻውን አራግፎ ክስ ሊመሰርት አነሳሳው፡፡ ከዚያም አደርገው፡፡ በለመደው የግፍ ፍርዱም
ተመስገንን 3 ዓመት ፈርደበት፡፡ በእኔ ዕምነት ተመስገን የተቀጣውና የግፍ እስራት ተፈርዶበት ወህኒ ቤት የተወረወረው
ሮጦ ባለመድከሙ፣ ብዕሩ አልነጥፍ በማለቱ፣ በአልሸነፍ ባይነቱ እና በእልኽኝነቱ የተነሳ ነው፡፡ ሌላ ምንም ጥፋት
የለበትም፤ ሊኖርበትም አይችልም፡፡ እኔ በዚህ መልኩ ገብቶኛል! … ወገኖቼ!… እናንተስ?
እናም ቀናተኛው የኢህአዴግ መንግስት በተመስገን ተስፋ አለመቁረጥና ቢገፋ … ቢገፋ ከአገር አልወጣ በማለቱ
በእጁ ካቴና (ሰንሰለት) ከቶ አስረው በቃ! … ተመስገን የታሰረበት እውነታ ይሄ ነው! … የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር
የሆንክ/ሽ/ ሁሉ፣ ሕገ-መንግስት የት ነው ያለው? … ካገኛችሁት እባካችሁ ዝዋይ ወህኒ ቤት በሚገኘው 9ኛ ቤት /ጭለማ
ቤት/ ቅጣት ቤት ድረስ ላኩልኝ፡፡
በመጨረሻ ተመስገን እኛ በተከሰስንበት ክስ ላይ ያለኝን ተቃውሞ አስመልክቶ “ማቆሚያና ገደብ ያጣው
የምስኪኗ የእናቴ እንባ!” በሚል ርዕስ የፃፍኳትን የመቃወሚያ ሀሳብ ሚያዝያ 5 ቀን 2004 ዓ.ም በፍትሕ ጋዜጣ አትሞ
አውጥቷል፡፡ በዚህም ለተገፉና ለተበደሉ ድምጽ ሆኖ ሲያገለግል እንደነበር እመሰክርለታለሁ፡፡
ይህችን ጽሑፍ በማተሙ የተነሳ በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ሚያዚያ 19
ቀን 2004 ዓ.ም አብረን ቀርበን፣ ችሎቱ ሚያዚያ 22 ቀን 2004 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተመስገንን 4 ወር እስራት ወይም
ሁለት ሺህ (2000) ብር በግፍ ሲቀጣው፣ እኔም ወግ ደርሶኝ እንደ አቅሚቲ 8 ወር እስራት ተፈርዶብኝ እንደነበር
አስታውሳለሁ፡፡ በአሁኑ የግፍ ቅጣት ጥፋተኛ ነው ብዬ እንደማላምን ሁሉ፣ ያኔም በተፈረደበት የግፍ ቅጣት አላምንም፡፡
አላመንኩበትም፡፡ ይህ የሚያሳየው ነገር ቢኖር፣ የሥርዓቱ መሪዎች አፋኝነትና ግፈኝነት አለመቆሙን ብቻ ነው፡፡ ኢህአዴግ
የግፍ ተግባር መፈጸሙን በሥልጣን ላይ እስካለ እንደማያቆም ጭምር ነው፡፡
ለማንኛውም የተመስገንን ጥንካሬ ልታውቁ የምትችሉት እንደ እኔና እንደ ጓደኞቹ ለአስርም፣ ለአስራ አንድ ቀንም
አብራችሁ ስትኖሩ ነውና፣ እኔም አሁን በእስር ቤት ውስጥ ባለው ጥንካሬ ተደንቄያለሁ፤ ተገርሜያለሁ፡፡ በርታ! ተሜ …
በርታ! ተሜም የነጻነት ቀናችን መምጣቱን በተግባር እስኪረጋገጥ ድረስ ትግሉን እንደማያቆም ዕምነቴ ጽኑ ነው፡፡ ትግሉ
ይቀጥላል!!!
አሉዋ ኮንትኑዋ!
ከዝዋይ ወህኒ ቤት የተላከ
ክንፈሚካኤል ደበበ በረደድ
(አበበ ቀስቶ)

Tuesday 2 December 2014

ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ

በተለያዩ ዘመናት በአገራችን ወደ ሥልጣን የመጡት ገዥዎች፤ ሕብረተሰባችን ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲያመቻቸው የዘር ግንድ እየቆጠሩ አንዱን ከሌላው የተሻለ አስመስሎ በመሳል፤ አንደኛውን በሌላኛው ወግን ላይ በስነልቦና ቂም እያናከሱ፤ የግፍ ግዛት ዘመናቸውን አሳልፈው አሁን ከአለንበር ዘመን ደርሰናል። በአሁኑ ጊዜ በሥልጣን ላይ የተፈናጠጠው መንግሥት ደግሞ ገና ከጅምሩ ወደ ሥልጣን ሲመጣ በረቀቀ ተንኮል የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘር ሐረግ ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲያመቸው አንቀጽ 39ኝን በሕገመንግሥት አጽድቆ ለረዥም ዘመን በጋራ ሕብረተስባዊ ገመድ ተሳስረው የኖሩትን ኢትዮጵያዊያን በጎሳ በመከፋፈል በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ያሉ ብሔረሰቦች ተፈጥሮአዊ የሆነውን እና ሊከባበሩበት የሚገባውን ማንነታቸውን ጦርና ጋሻ አድርገው እንዲዋጉበት በማድረግ ነው የሥልጣን እድሜውን እያራዘመ ያለው።
(ጎንደር ፋሲል ግምብ - ፎቶ ፋይል)
(ጎንደር ፋሲል ግምብ – ፎቶ ፋይል)

ታዲያ ይህ መንግሥት ለአገራችን ሰላም ያመጣል በሚል ከፋፍሎ ለመግዛት እራሱ በቀመረው የጎሳ ክልል ቀቢጸ ተሥፋ “በብሔሮች” ራሥን በራሥ የማሥተዳደር ሥም፤ አብሮ የኖረውን እያራራቀ፤ ተፈቃቅዶ ይኖር የነበረውን እንደጠላት እያሥተያዬ፤ አካባቢያዊ ሰላምን እያደፈረሰ፤ እርሥ በርሥ እያጋደለ ያለው ትልቁ ችግር በአገራችን ላይ የተደነገገው ህገመንግሥታዊ አደጋ፤ ከሃያ ሦስት ዓመት በኋላ ህግ አውጭውን አካል እና መንግሥታዊ መዋቅሩን በማሥጨነቅ እርስ በራሱ ሲያተራምስ እያየን ነው። በመሆኑም፤ ባለፈው ሚያዝያ ወር ባወጣነው እና በድህረ-ገጽ ለማሳነበብ እንደሞከርነው ሁሉ፤ አሁንም በድጋሚ የምናሥገነዝበው፤ መንግሥታት መጥተው፤ መንግሥታት ሲያልፉ፤ የማያልፈውን የቅማንት እና የአማራ ህብረተሰቦች የጋራ ታሪክ ዘመኑ ባመጣው የጎሳ ፖለቲካ ጉንፋን መሰል አሥተሳሰብ እና ድርጊት የኋላ ታሪካቸውን ማጥቆር እና የወደፊቱንም ማህበራዊ ግንኙነታቸውን ማጨለም አይገባም እንላለን።
ሰለዚህ ይህን አገር አፍራሽ፤ ሰላም አደፍራሽ የሆነውን አንቀጽ 39ኝን እንደ መብት ማስከበሪያ በመጠቀም የቅማንት የማንነት እና ራሥን በራሥ የማሥተዳደር ጥያቄ ያነሱ የቅማንት ተወላጅ ወገኖቻችን ያልተገነዝቡት ነገር፤ ተዋልዶና ተጋብቶ፤ አንድ ሐይማኖት አምልኮ ለረዥም ዘመን ከኖረው ወገናቸው ጋር አብሮ የማያኗኑር መሆኑ ነው። ቅማንት እና አማራ ጊዜ እና ቦታ አንድ ላይ ያሥቀመጣቸው ብቻ ሳይሆኑ፤ እጅግ ብዙ የጋራ ችግር እና ደሥታን ጽዋ አብረው የተጎነጩ፤ ረዥም የታርክን ጎዳና አብረው የተጓዙ፤ እምነትና ቋንቋ ባንድ ገመድ ያስተሳሰራቸው ሕዝቦች መሆናቸውን ነው። ይህ ሲባል ግን፤ መለሥተኛ ችግሮች ተከስተው አያውቁም ማለት አይደለም። በሁለቱ ህብረተሰቦች መሃከል የነበረው ችግር ግን፤ በሁለት ወንድማሞች መካከል ከሚከሰት ችግር የተለዬ አልነበረም። ስለሆነም ነው በየጊዜው የሚፈጠሩ መለሥተኛ ችግሮቻቸውን በጋር እየፈቱ እና መቻቻልን መሰረት አድርገው የአንድነታቸውን ታሪክ ጠብቀው ከዚህ የደረሱት። ወደፊት ማደግና መቀጠልም ያለበት በዚሁ መንገድ ነው። ይህ ደግሞ በማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ያለ እና የሚኖር ነው።
ይህን ሥንል ግን፤ የቅማንት ብሔረሰብ ወገኖቻችን ይህን ጥያቄ ያለ ብሶት አነሱት በማለት በጭፍን ለመኮነን አይደለም። ሆኖም፤ በኛ እይታ፤ አሁንም በድጋሚ ማሥገንዘብ የምንፈልገውው፤ ችግሩ የመልካም አሥተዳደር በደል እንጂ፤ ለቅማንቱ ችግር ምንጭ አማራው አይደለም። ለአማራውም ችግር ምንጭ፤ ቅማንቱ አይደለም። ይህ የአሥተዳደር በደል ቅማንቱ ራሱን ሥለከለለ ይፈታል ብሎ ማሰብ፤ እጅግ ሥህተት ነው። በመላ አገሪቱ የተንሰራፋው የአሥተዳደር በደል፤ በመላ አገሪቱ ሳይፈታ፤ ለአንድ ጎሳ ብቻ ነጻ እና ዲሞክራሲያዊ መብት እንደ መና ከሰማይ ሊወርድ አይችልም። እሁን እዬተሄደበት ባለው መንገድ ሊመጣ የሚችል ለውጥ ቢኖር፤ በአካባቢው ባልተወለዱ ባልሥልጣኖች ከመበዝበዝ ይልቅ፤ ከራሳችን በተወለዱ መሪዎች መበዝበዝን ነው። ምክንያቱም በዬትኛውም የአገራችን የጎሳ ክልልን እንደ ነጻነት ቆጥረው በተግባር ለማዋል የሞከሩት አካባቢዎች ያተረፉት ሃቅ ይህ ሲሆን አይተናል እና።
ስለሆነም፤ በሰሜን አሜሪካ የምንኖር ጉዳዩ ያገባናል የምንል የቅማንት ብሔረሰብ ተወላጆች፤ በአገር ቤት የተወሰኑ የቅማንት ተወላጆች፤ ያነሱት የማንነት እና የራሥን በራሥ ማሥተዳደር ጥያቄ አለመመለሥ ምክንያት በተወሰኑ ግለሰቦች መካከል እርሥ በርሥ መተነኳኮስ መጀመሩን ሰምተን እጅግ በጣም አዝነናል፤ ቀጣዩም አሳስቦናል። የዚህን ጥያቄ አደገኛነት ባለፈውም ጠቁመናል፤ እሥከ የት ሊዘልቅ እንደሚችልም አመላክተናል። አሁንም በድጋሚ ያለፈውንም ሆነ የወደፊቱን የጋራ ባህላችን እና የጋራ አካባቢያዊ የኑሮ ዘይቤ አበላሽቶ እና መጥፎ አሻራ ጥሎ የሚያልፍ መሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል።
አሥተሳሰቡ እና ድርጊቱ፤ ሁሉንም የሕብረተሰብ አባሎች የማይወክል እንደሆነ ብናውቅም፤ የሁኔታው መከሰት ግን፤ በራሱ አሥደንጋጭ እና አሳዛኝ፤ እንዲሁም አሳፋሪም ጭምር ነው። ይህ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግሥት ባመጣው የጎሳ ወጥመድ ውስጥ የገቡ ወገኖች የሚያራምዱት አስተሳሰብ አስከፊ ውጤት ሊሆን የሚችለው፤ መንግሥታት መጥተው፤ መንግሥታት ሲያልፉ፤ የማያልፈውን የሁለቱ ህብረተሰቦች የኋላ ታሪካቸውን ማጥቆር እና የወደፊቱንም ማህበራዊ ግንኙነታቸውን ማበላሸት ብቻ ነው።
እንዲህ አይነቱ ለማንም ወገን የማይጠቅም ልብ የሚኢያሻክር ድርጊት በአስቸኳይ መቆም አለበት። ይህን በማለታችን እንደ ድፍረት ሊያሥቆጥርብን አይገባም። እኛም ለተወለድበት አካባቢ፤ ለተፈጠርነበት ህብረተሰብ የሚበጀውን የቅርብ እና የሩቅ ራዕይ የማመላከት ግዴታ አለብን እና። ይሁንና፤ በሁለቱ ሕዝቦች ውሥጥ የሚገኙ ሽማግሌዎች፤ አዋቂዎች፤ እና ምሁራን ሁኔታውን አግባብ ባለው እና በሰከን መንገድ ይፈቱታል ብለን እናምናለን። ከሁሉም በላይ የአካባቢውን ሰላም እና መረጋጋት ታሳቢ አድርገው በሁለቱ ህብረተሰቦች መሃከል ሰላማዊ ንግግር ተጀምሯል የሚል ሰምተናል። ይህ ጅምር ከወዲሁ የሚበረታታ ሲሆን፤ የጋራ ወገኖቻችንን የቆዬ ፍቅር የሚያረጋግጥ ክሥተትም ጭምር በመሆኑ፤ ጠንክሮ እንዲቀጥል በአክብሮት እናሳሥባለን። እኛም የአብሮነት ሂደቱ እና በአካባቢው ሰላማዊ ኑሮ እንዲቀጥል የምንችለውን ሁሉ ለመተባበር ዝግጁ ነን።
በተጨማሪም፤ ማንኛውም ግለሰብ፤ ቡድን፤ ድርጅትም ሆነ የመንግሥት አካል በሥሜት ተገፋፍቶ እና ባለማወቅ ወይም ሁኔታውን ለተለዬ የግል አላማ አሥቦ የሚንቀሳቀስ ቢኖር፤ “አንተ ሰላም እንድትውል ጎረቤትህ ሰላም ይሁን” እንዲሉ፤ የሚፈጠረው የሰላም መደፈረስ ሁሉንም የሚጎዳ በመሁኑ ከመጥፎ ተግባር እንዲቆጠብ ለማሳሰብ እንወዳለን። ህዝቡም፤ የላይ የታች ሳይባባል በአንድ ሆኖ ለጥፋት የሚንቀሳቀሱትን ትክክል አደላችሁም ማለት የሚገባ መሆኑን ጊዜው እያመላከተ ነው። አገር በሰነፎች እንደማይገነባ ሁሉ፤ ሰላምም በነገረኞች አይረጋም እና።
በዚህ አጋጣሚ ሁለቱም ህዝቦች መገንዘብ ያለባቸው አጠቃላይ ሁኔታውን እና የሰሞኑንም ቤተሰባዊ አለመግባባት የፈጠረው የመንግሥት ፖሊሲ እና አሰራር መሁንን ነው። “ውኃው ሂያጅ ደንጊያው ቀሪ” እንደ ሚባለው ሕዝብ ይኖራል መንግሥት ግን ያልፋልና። የሚያልፍ መንግሥት ዘላለማዊ የሚኖር የታሪክ ጠባሳ ጥሎ እንዳያልፍ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው። እያንዣበበ ያለው ችግር ከፍ ሲል የኢትዮጵያ ዝቅ ሲል ደግሞ የጎንዳር ሕዝብ ችግር ነውና አብረን ተባብረን ወደ ሰላም እና የዘር ክልል ያልበከለው ሁለንተናዊ የአንድነት ወንድማማቻዊ ጎዳና እንምራው።
በመጨረሻም፤ “እርቅ፤ ደም ያደርቅ” እንዲሉ፤ የተጣላውን እያሥታረቀ ለዘመናት ራሱን ጠብቆ የኖረ ህዝብ፤ ዛሬም የገጠሙትን ችግሮች በለመደው ባህላዊ የሽምግልና ጥበብ እየፈታ ወደፊት እንዲቀጥል ጥርጥር የለንም። ለሁሉም ወግኖቻችን እና ሕዝባችን፤ ሰላሙን እና ደህንነቱን የምንመኘው ከልብ ከሚመነጭ ፍቅር እና አክብሮት ጋራ ነው።
ጉዳዩ ይመለከተናል ከምንል የቅማንት ብሔረሰብ ተወላጆች፤ ሰሜን አሜሪካ።