Thursday 12 June 2014

Political Power and the Art of Political Compromise By Tecola W. Hagos

“The world rests on three Pillars: On Torah (wisdom), on avodah (service, worship), and g’meelut chasadim–acts of loving kindness.”

General Perspective
In the past, especially during the reign of Emperor Haile Selassie I, to a great depth, the State of Ethiopia seemed to have a more integrated society than the current seriously fractured State of “nations and nationalities.” It is a challenge to all of us to think of a unifying history of Ethiopia in as far as what is presented in most history books I read is a segmented view of Ethiopia’s dominant ethnic oriented history rather than a coherent or holistic history of its complex society. To me the most important thing is the fact that we have a long history no matter how it is presented in written form. However, even if we acknowledged such narratives, we must guard against fallacies of composition in accepting limited instances to represent the whole of the human condition in all parts of Ethiopia.
I have studied many ethnic communities throughout the past history of the United States. None have I found that hate and disparage the governments of their respective original home countries as much as many of the Ethiopian Diasporas do, which led me to conclude that Ethiopians in general love the abstract notion of an Ethiopia, but hate and disrespect the concrete Ethiopians right next to us. I see it in the fact that Ethiopians would tolerate extreme forms of abuse in the hands of foreigners, but will not live with mild discomfort generated by the presence or activities in the hands of fellow Ethiopians. This is indeed a curious situation that ought to be studied carefully by sociologists and psychoanalysts in order to understand our national problems with the way our society deals with poverty and totalitarian tendencies in our rulers.
Prof Messay Kebede’s recent article is simply an information piece whereby he is echoing assertions and views made by third parties. It is neither an advocacy for violence or for any form of confrontational strategy against the Ethiopian Government. One must ask now and then fundamental questions such as questions dealing with the purpose of human life. Surly, it is not for the purpose of making politics. The fact is that human beings are involved in politics in order to realize a fulfilling life. The art of compromise is a great art of political gamesmanship, but seems to be acutely missing both in the establishment and the periphery of Ethiopia’s political scene. Two points that one must focus on is the future political life of our future leaders, such as Birtukan Mideksa: is there some political room for her for a come-back or even better to join the current Ethiopian leadership? And the other question: Quo Vadis (where to) PM Hailemariam Desalegn?
Hunger for Political Power: ጉልቻ፣ ቢለዋወጥ፤ ወጥ፣ አያጣፍጥም።
I do not accept the idea that human beings are helpless in the face of what may be considered as inevitable or predetermined ends. I believe we can always change what might seem to be a horrible inevitable end. At any rate, the future is shielded from us, all we can do is take educated guess what the future might hold for us and do the best we could to live a virtuous life. Ultimately we each live an individualized life and not a life to be lived by a committee. Prof Mesfin Woldemariam has shared with us in a succinct article a frightening prediction of our future. Although at times I failed to see Prof Mesfin’s rational in some of his statements, such as his vehement opposition to Seye Abraha at Medrek as opposed to his recent endorsement of Aregawi Berhe, which act seems to me to be in the realm of metaphysics, beyond my understanding, I truly believe Prof Mesfin’s intention is honorable and patriotic. In his own words the following is what he wrote about our apocalyptic fate:
ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ጥላቻ ወደንዴት፣ ንዴት ወደቁጣ ተለውጦ ሲገነፍል ምጽዓት ደረሰ ማለት ነው፤ ሁሉም ሰው ራቁቱን ይሆናል፤ አንደአውሬ ከጥፍሩና ከጥርሱ በቀር ሌላ መሣሪያ አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ በክፋት ወደ አውሬነት ይለወጣል፤ ጠመንጃና ቦምብ አያገለግሉም፤ ሕንጻው ምሽግ አይሆንም፤ መኪናው፣ ባቡሩ፣ ታንኩ ከቆመበት አይነቃነቅም፤ የትም አያደርስም፤ ጭፍራ ሁሉ በየራሱ ፍዳ ታንቆ እንኳን ለሌላ ሊተርፍ ለራሱም የማይበቃ ይሆናል፤ ለነገሩ
ጌታና ሎሌም የለም፤ ሁሉም በአውሬ እኩልነት የተፋጠጠ ነው፤ ርኅራኄ ተሟጦ፣ መግል ያዘለ ልብ ፈርጦ፣ ውይይትና ክርክር አብቅቶ፣ ጥርሱን ያገጠጠና ጥፍሩን የሳለ መንጋ በደም የሚራጭበት ሁኔታ ነው።
I do not want to believe that Prof Mesfin is making a self-fulfilling prophecy for the sake of saying “I told you so” when what he prophesied becomes our nightmarish reality. I believe he is sincere in sharing his profound concern about the future of Ethiopia in that article, with the hope that his gloomy prediction can be averted. In other words, he is urging the people in power to fix the problem that had been pointed out by numerous people both organized in opposition party structures and as expressed by concerned individuals. However, spelling out gloom and doom in itself is not going to help us much. To some extent, Prof Mesfin is exaggerating the degree of calamity he is predicting. The Ethiopian public is not as reckless and as brutal as portrayed by him in its future actions. Moreover, I think his concern is misplaced, and in painting to us a frightening future for Ethiopia is not going to help Ethiopia overcome the serious problems facing us. The Red Terror, for example, would never have happened as an expression of discontent by the Ethiopian public, if it were not for the full agitation and push of the Derg and its civilian hatchet-men.
In the main up to now, our elitist solution to our profound problems is our incessant cry for change of Leadership. Of course, such expressions of discontent are punctuated by demonstrations against specific inequities championing the causes of heroic Ethiopian journalists and politicians. The way I look at our age old problems is that our leaders should be the least of our concern. We seem to forget that we are functioning in a closed system, and changing personalities in leadership positions would not make that much of a difference in the reality of our existence burdened with centuries of accumulated technology deficiency, ignorance of modern means of production, illiterate society, and poverty of all kinds. If we change every single individual now in leadership position in Ethiopia and replace each with the outspoken leaders of the many Diaspora political organizations, we will only succeed making matters worse. ጉልቻ፣ ቢለዋወጥ፤ ወጥ፣ አያጣፍጥም። It is precisely in anticipation of such ineffective new leadership after any revolution that I suggested to use alternative method of change in Ethiopia.
One possible method to effect changes at the grassroots level is to use the Ethiopian Courts by filing complaints on behalf of to get redress from Governmental inequities rather than wait on the sideline while the destructive resentment/hate pressure is building up in society. This is a long term process, but it has the added virtue in teaching us to use the legal system no matter how flawed it may be. The complaints against violations of the rights of citizens and unequal treatment of Ethiopians from different ethnic background can be lodged against individual government officials and/or the government corporate entities. That too is not sufficient, but one ought to try as many solutions and we must be creative to prevent any social explosion. One should read and digest Prof Mesfin’s admonishment very seriously even if it turns out to be a bogyman story told to frighten children.
The Art of Political Compromise
Ambassador Zewde Retta, in his monumental book on Ethiopia and Eritrea [The Eritrean Affair (1941-1963) During the Reign of Emperor Haile Sellassie I, (in Amharic)], narrates an incident that took place while Emperor Haile Selassie was living in exile in England. Young Aklilu Habtewold was working as an aid to the then Ethiopian Ambassador to France during the Italian war on Ethiopia. Aklilu having learned that the Ethiopian Ambassador had scheduled a press conference to announce his defection to the Italian side, was reporting to the Emperor that grave diplomatic debacle. Emperor Haile Selassie, rather than throwing a tantrum and cursing his Ambassador whom he lifted up from dirty to national prominence and great wealth, in great statesman discipline instructed Young Aklilu to go back to the Ambassador and ask him on behalf of the Emperor what would be done for him to persuade him to abandon his planned defection. Here is a lesson in great statesmanship: negotiation and compromise even at the gate to Hell.
The legacy of the Ethiopian Student movement of the 1960s and 1970s is rigidity and fanatical adherence to abstract ideas. The Ethiopian student body of the time of Emperor Haile Selassie had suffered tremendous distortions of self-perception settling ultimately in the 1970s on the image of Che Guevara, Marx and Lenin, with Stalin in tow, and all those aliens were immortalized in the popular students’ song of all ages, Fano Tesemara. I often wonder why we as Ethiopian students at HSIU did not sing of Ethiopian great patriots, such as Belay Zeleke, Abune Petros, Geresu Duki et cetera. Of course, much later I learned that the Ethiopian Students Movement was not a constructive endeavor, but manipulated by third parties using students to destroy their own Ethiopian nationalism. We still are living that tragedy in the way we tear down each other for flimsy ideas totally oblivious of the more important question of the survival of Ethiopia. We students were just pawns unknowingly being used for the sordid interest to benefit Eritrea’s ambition for independence. Generally speaking, the generation of Ethiopian students that traversed the gauntlet of the modern Ethiopian education system were the isolated segment of the Ethiopian society, thus easily manipulated and used against our own self-interest.
What is missing right now in all the dissention voices against the current Ethiopian Government and/or its predecessor is detailed plan/strategy to fix the alleged problems. Such plan need not be a comprehensive governmental plan. Modest changes in the lives of individuals, modest system changes, investment in morality in society, enhancement of individual hygienic life, clean environment, controlling overpopulation et cetera could have complex adoptive and transformative effect in the long run. What must we do now to force the hand that is guiding Ethiopia in the present course of governance to change? But what type of Change? For sure no one is going to hand over power just like that. In fact, the fear of persecution in case the current leaders lose power is another incentive for them to hang on to power by all means. Here is where the art of compromise, creation of escape doors, evolutionary process et cetera would ease transition and change. It is not enough to shout slogans, hurl insults, and write threatening essays across the Atlantic Ocean and a Continent, nor prophecy of doom and gloom would deliver wealth and democracy to people. What is needed is direct engagement by participating in the economic and social life of the nation in the first place, and move into political activity once planting deep roots in the Ethiopian society.
In the movie Braveheart, the former Crusader, and later leper, father of James the Bruce, advised his overzealous son that what distinguished the “nobles” from the “common” Scotts is the ability of the “nobles” to compromise in order to preserve and expand their landholdings and status in court. I am not saying that there is no place for unflinching principled stance that would make historic difference in the life of a community even a nation. Earlier I asked a generic question about the future of new political leaders including Birtukan Mideksa. There is some purpose in my question. I intend to measure the degree of willingness of Ethiopians to compromise and seek politically expedient solutions rather than stay disfranchised narrow minded fanatics whereby the art of modern politics eludes them to the detriment of the Ethiopian society and their own individual lives.
I am taking up the case of Birtukan Mideksa, who graduated from Harvard, Kennedy School of Government a couple of weeks ago, who is already a subject of political tugging by opposition political organizations. Two influential Diaspora figures, Abebe Gellaw and Girma Kassa, have written a couple of articles that are touching and personal, and in a plea for Birtukan to go back to the fold. I think this might be a moment of truth for Birtukan to come up with a wise and equally significant decision in here own self-interest. The Ethiopian Government Leaders also have an opportunity to evolve as sophisticated politicians in their treatment of Birtukan and other opposition leaders. I think the art of compromise is very much needed here under such sensitive situation. I would suggest that the Ethiopian Government appoint Birtukan for high Ethiopian Government position, such as appointment as Ambassador to the United Nations and at the same time free Eskinder Nega, Reyot Alemu, Andualem Arage and all the detained journalists and political prisoners.
Prime Minister Hailemariam Desalegn seems to fade into the contentious background of Ethiopia’s ever intriguing political power struggle. I believe that he must find his tipping-point soon and start a political and economic momentum of his own making rather than tag-on along an already obsolete political and economic structure of the last ten fifteen years. A good leader must have inner fire and a hunger to bring about profound positive change in the lives of his fellow Ethiopians. There are several untapped, untested, and virgin areas for development projects. There are serious administrative, judicial, economic, and political problems that need immediate and effective solutions. There are also serious errors carried over from previous governmental activities and errors due to poor leadership that need corrections without delay, one being the Ethiopian coastal territory on the Red Sea. Far more fully developed paper. [See Tecola W. Hagos, DISILLUSIONMENT OF INTERNATIONAL LAW AND NATIONAL SURVIVAL (2011);
http://irobmablo.org/tecola_hagos.pdf
I watch ETV and read all sorts of news and articles from Ethiopia and from the Diaspora on a daily basis. I am disappointed in the lack of enthusiasm and headlong engagement by the leadership of the Ethiopian Government. They seem to be in infuriatingly relaxed reclining mood, except for few, such as the Minister Alemayehu Tegenu and Engineer Simegnew Bekele who seem fully engaged pouring out their bodies and souls into their respective national undertakings dealing with the GERD. If one has to choose current Ethiopian heroes, there you have them. These are two Ethiopians I trust the fate of our right over our natural resources.
Conclusion: Get a Life, Diaspora Politicians
Warren G. Buffett, the greatest securities and equity investor in the world, said, “We are just the opposite of those who hurry to sell and book profits when companies perform well, but who tenaciously hang on to businesses that disappoint.” Buffett’s statement by analogy would criticize the mind set of Ethiopian “opposition” politicians. In simple form, what Buffett is stating is that one maintains a winning position and get rid of losing stocks. In other words it is not wise to liquidate a winning group in favor of dysfunctional losers or stocks with no record of success.
The tragic fact is that the vociferous often vicious Diaspora opposition members (the ones blogging and chatting) do not represent the majority of Ethiopian immigrants. Those Diaspora members that are belligerent and insulting of anyone with point of views different than their narrow and chauvinistic views are living in serious mental freeze having based their dissident narration on mistaken or delusional presumptions of historical events The reality on the ground was totally contradictory of such narratives of the political and economic condition prior to the rule of the EPRDF. They often forget that all of the resistance/liberation movements, some of whom in power now, were instituted to challenge autocratic and authoritarian regimes.
The lack of rational, cool, and sophisticated analysis of the present state of affair in Ethiopia has led several individuals in the Diaspora to adopt an unproductive even belligerent position in dealing with the current Ethiopian Government. In my last article, in illustrating the unappetizing and delusional hunger of some Ethiopians in the Diaspora communities around North America and Europe for dominance, I narrated the parable of carrying a crown in ones pocket in case the opportunity of kingship is offered (Prof Yacob Hailemariam), which sums up my views about the unrealistic political ambitions of some Ethiopians elites in the Diaspora. Recent articles by Ethiopian elites are becoming exceedingly anachronistic and irrelevant to our social and economic condition, especially when they are disparaging and discounting real projects and activists that Ethiopian men and women are working hard constructing, such as real roads facilitating the movement of commerce and people, real dams generating power, real buildings people use, and rail systems moving millions of tons of goods. In few cases we see our learned politicians turning into a Twenty First Century Jeremiah, the prophet of doom and gloom, telling us that the destruction of our society is just around the corner.
I navigate numerous Websites, including several Ethiopian ones, over a course of a day for years now. What is truly tragic to me is that most Ethiopian Websites are humorless, dry, and sour. In Ethiopian Websites, politics dominates everything. Even our great athletic heroes are pushed aside to make room to endless tirade of articles and comment on a single theme with hundreds of variations: answering to the question who should be in power. I keep wondering whether Ethiopians in the Diaspora might not have normal lives. I do not read involvements in communal healthy relations, except for the Ethiopian Churches. How about social involvement, academic achievements et cetera?
ONWARD ETHIOPIA IN PROSPERITY AND LIBERTY.
Tecola W. Hagos
June 11, 2014

በዞን 1 የሚገኙት ጀግኖቻችን በዛሬው እለት ተበታትነው እንዲደለደሉ ተደረገ! በህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ላይ በማረሚያ ቤት እየተደረገ ያለው ወከባ በአስቸኳይ ይቁም ! (ድምፃችን ይስማ)

June 12, 2014
በሐሰት የሽብር ክስ ህገ መንግስታዊ መብቶችን በጣሰ ሁኔታ መሪዎቻችንን እያጉላላ የሚገኘው መንግስት በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚያደርገውን ወከባ ቀጥሎበታል፡፡ ገና ወደማረሚያ ቤት ከተዛወሩበት ጊዜ አንስቶ ጠያቂዎችን በማጉላላት፣ የጥየቃ ሰአትን ከሌሎች በተለየ መልኩ በመገደብ፣ እንዲሁም በጠያቂዎች ቁጥር ላይ ገደብ በማድረግ በተለያዩ ወቅቶች መብታቸውን ሲነግፍ የቆየው መንግስት ዛሬ ደግሞ በታሪካዊው የካንጋሮ ፍርድ ቤት የችሎት ሂደት ምስክሮቻቸውን እያቀረቡና ትክክለኛው የህዝበ ሙስሊሙ ትግል ገጽታ በችሎት እየተመሰከረ ባለበት በዚህ ወቅት በፍርድ ቤት እየደረሰበት ያለውን ሽንፈት ለመቋቋም ወኪሎቻችን ላይ የተለያዩ ወከባዎችን እየፈጸመ ይገኛል፡፡ እስካሁን ድረስ በእስር ቤቱ ታሪክ በምንም መልኩ የማያስጠይቅን፣ ይልቁንም በማረሚያ ቤቱ ደንብ ጥበቃ የተደነገገለትን ገንዘብ የመያዝ መብት እንደወንጀል በመቁጠር በኮሚቴው ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና በሸኽ መከተ ሙሄ ላይ፣ እንዲሁም በሌሎች ታሳሪዎች ላይ ሲያደርስ የነበረውና በቅርቡ የተረጋጋው ወከባ መሪዎቻችንን የማጥቂያ ሰበብ ፍለጋ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ ግልጽ ነበር፡፡Ethiopian Musilms
አሁንም ይህንኑ ህገወጥ ድርጊቱን የቀጠለበት የእስር ቤቱ አስተዳደር በዞን አንድ በሚገኙ ጀግኖቻችን፣ (ማለትም በሸኽ መከተ ሙሄ፣ በኡስታዝ አቡበከር፣ በኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፣ በኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ፣ በጋዜጠኛ አቡበከር ዓለሙ፣ በወንድም አብዱረዛቅ አክመል እና በወጣት ሙባረክ አደም) ላይ በዞን አንድ በሚገኙት 8 ክፍሎች እንዲበታተኑና እንዲለያዩ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡ ጓዞቻቸውንም ወደየተመደቡበት ክፍሎች እንዲቀይሩ እንደተነገራቸው ታውቋል፡፡ ባለበት የጤና ችግር ምክንያት ልዩ ትኩረትና ረዳት ጓደኛ የሚያስፈልገውን ወንድም አብዱረዛቅን ድጋፍ ለማግኘት አስቸጋሪ እንደሚሆንበት እያወቁ ብቻውን መድበውታል፡፡ ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋንም እንዲሁ ጊዜያዊ ማቆያ ተብሎ በሚታወቀውና በእስረኞች ቶሎ ቶሎ ተለዋዋጭነት ምክንያት ማህበራዊ ትስስር መመስረት አስቸጋሪ በሆነበት ክፍል ሆን ተብሎ እንዲመደብ ተደርጓል፡፡
የማረሚያ ቤቱ ደንብ በአንድ የክስ መዝገብ ችሎት የሚከታተሉ ታራሚዎች በችሎታቸው ዙሪያ በየጊዜው መነጋገርና መወያየት እንዲችሉ በአንድ ዞን የመታሰር መብት የሚሰጥ ቢሆንም አስተዳደሩ ግን ይህንን የሚያደርገው ሆን ብሎ የችሎታቸውን ፍሰት ለማስጓጎል እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ሆኗል፡፡ ሆነ ተብሎ እነሱን ብቻ የለየ ጥቃትና የመብት ጥሰት የሚፈጸምባቸውም በእስር ቤት ውስጥ ባለቻቸው ውስን ነጻነት የገነቧትን ማህበራዊ ትስስር ለማፍረስና የመጪውን ረመዳን ጾምም ተረጋግተው መጾም እንዳይችሉ ጫና ለማሳደር መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ አወዛጋቢው የፍርድ ሂደት ቀጥሎ የሰው ምስክርነት እየተደመጠ ባለበት ሁኔታ የመጨረሻ ውሳኔ የማስለወጥ ሃይል ባይኖረውም እየተደመጠ ያለው ምስክርነት እጅግ እንዳደናገጣቸውና በዚህም ይህንን እርምጃ ለመውሰድ እንደተገደዱም የሚያሳብቅ ሆኗል፡፡ መንግስት በሃሰት የሽብር ክስ ማንገላታቱ ሳያንሰው በእስር ቤት ውስጥ እንኳን ታራሚዎች ላይ የሚያደርሰው በደል በእርግጥም የአገሪቱ የፍትህ ስርአት የቁልቁለት ጉዞውን እያፋጠነ ለመሆኑ ከበቂ በላይ ምስክር ነው፡፡
የእስር ቤቱ አስተዳደር ውስጥ ያሉት አንዳንድ ሀላፊዎች በግፍ እስር ላይ ለሚገኙት የህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ያላቸውን ጥላቻ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲያሳዩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ካሁን ቀደም የደሴ ወጣት ታሳሪዎች ወደጨለማ ክፍል እንዲገቡ መወሰኑን ተከትሎ ሌሎች እስረኞች ተቃውሟቸውን ለማሰማት በተሰበሰቡበት ወቅት በቅጽል ስሙ ሻእቢያ ተብሎ የሚጠራው የማረሚያ ቤቱ የጸጥታ ሀላፊ ‹‹እኒህን አሸባሪዎች ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ መረሸን ነበር!›› ብሎ ቁጭቱን ሲገልጽ በግላጭ የተሰማ ሲሆን በተለያዩ አጋጣሚዎችም ጥቃት ከመፈጸም ወደኋላ እንደማይሉ መታዘብ ተችሏል፡፡ በማረሚያ ቤቱ ግቢ ውስጥ ካሁን ቀደምም በሌሎች በርካታ ታሳሪዎች ላይ አሰቃቂ የጅምላ ድብደባ ሲፈጸም የነበረ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ ይህን መሰል የህገ መንግስቱን የእስረኛ አያያዝ ደንብ በግላጭ የሚጥሱ ወከባዎችና በደሎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ይጠይቃል! ህዝበ ሙስሊሙ ላይ ያወጁትን ጦርነት ሲያስፈጽሙ የቆዩት ደህንነቶችና የመዋቅራቸው አካላት ከህግ በላይ የሆነ አካሄዳቸውን በአስቸኳይ እንዲያቆሙም ያሳስባል! በህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ላይ የሚፈጸም ማንኛውም ወንጀል በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የሚፈጸም ወንጀል ነው፡፡ እነርሱ ላይ የሚደርስ በደል ፈርሞ ወደመንግስት በላካቸው ሰፊው ህዝበ ሙስሊም ላይ የሚደርስ በደል ነው፡፡ በመሆኑም በወኪሎቻችን ላይ አንዳች ነገር ቢደርስ ሃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ የሚወስደው መንግስት መሆኑን እያስታወቅን ሰላማዊው ህዝበ ሙስሊምም ይህን መሰሉን ድንበር ያለፈ ጥቃት እስከመጨረሻው የሚፋረደው መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን!
በህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ላይ በማረሚያ ቤት ውስጥ እየተደረገ ያለው ወከባ በአስቸኳይ ይቁም!
የእስር ቤቱ አስተዳደር ከህግ በላይ መሆኑን በአስቸኳይ ያቁም!
የህዝብ ወኪሎችን ማጉላላት ይብቃ!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን ማን ይፈራቸዋል? (ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም)

June 11, 2014
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የእስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችን…የዴሞክራሲያዊ መብት የመጠቀም የትግል እንቅስቃሴ ሲመለከት እንደሚዳቋ እየበረገገ የሚስፈነጠረው ማን ነው?Ethiopian government scared of bloggers and journalists
የኢትዮጵያ የነጻው ፕሬስ እና ጦማርያን ቁንጮ የሆነው እስክንድር ነጋ ሀሳቡን በነጻ በመግለጹ ብቻ በአምባገነኑ የወሮበላ ቡድን ስብስብ የይስሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት የ18 ዓመታት እስር ተበይኖበት በገዥው አካል የማጎሪያ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ሟቹ መለስ ዜናዊ ልዩ ትዕዛዝ እስክንድር ነጋ በቁጥጥር ስር እንዲውል እና የ18 ዓመቱ የሸፍጥ እስራት እንዲበየንበት ተደርጓል፡፡ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ማናቸውም ጋዜጠኞች የበለጠ እስክንድር ነጋን ይፈራዉና ይጠላው ነበር፡፡ ዝሆን አይጦችን “ይፈራል” ከሚለው ኢ-ስነ አመክንዮ አንጻር በተመሳሳለ መልኩ መለስም እስክንድር ነጋን እንደጦር ይፈራው ነበር፡፡
በቅርቡ እስክንድር ከማጎሪያው እስር ቤት ለ8 ዓመት ልጁ ለናፍቆት እንዲህ የሚል ግልጽ ደብዳቤ ጽፏል፣ “እንዲያው ሁኔታውን ሳየው እያለሁ የሌለሁ የዘፈቀደ አባት ሆኛለሁ፣ ምክንያቱም በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፈረንሳዮች ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍቅር እያሉ ደጋግመው ይጠሯቸው የነበሩትን ሶስት ቀላል ቃላትን በመውሰድ እኔም በሀገሬ ነጻነት፣ እኩልነት እና ፍቅር እንዲሰፍን በማሰብ እነዚህን ቃላት በማስተጋባቴ ነው በሸፍጠኞች ለእስር የተዳረግሁት“ ብሏል፡፡ እስክንድር ለነጻነት፣ ለእኩልነት እና ለአብሮነት ፍቅር ጦማሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ለእኔ የጀግናዬ ተምሳሌት የሚሆነው!
የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ቀንዲል ጀግናዋ የ34 ዓመቷ ወጣት ርዕዮት ዓለሙ በተመሳሳይ መልኩ በአቶ መለስ ዜናዊ የ14 ዓመታት እስር በይኖባታል፡፡ ይህች ጀግና ወጣት በዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ “እውነት ተናጋሪዋ ኢትዮጵያዊት እስረኛ” በመባል ትታወቃለች፡፡ ርዕዮት ለእስር የተዳረገችው የግድብ ፕሮጀክት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን በተመለከተ በገዥው የፖለቲካ ፓርቲ ላይ ጠንካራ ትችት በማቅረቧ እና በቅርቡ በህይወት የተለዩት የሊቢያ አምባገነን መሪ ሙአማር ጋዳፊ እና መለስ ዜናዊ ከአንድ ባህር የሚቀዳ ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው መሆናቸውን በይፋ በመግለጿ ነው፡፡ ርዕዮት በእስር ቤት ተዘግቶባት እና አፏን ተሸብባ ለመቀመጥ ባለመፍቀድ በድፍረት አንገቷን ቀና አድርጋ ስልጣኖቻቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በህገወጥነት ለሚጠቀሙት ህገወጦች እና ትዕቢተኞች እውነት እውነቱን እንዲህ በማለት እቅጬን ተናግራለች፣ ”የተሻለች ኢትዮጵያን ለማየት እኔ በግሌ የሚጠበቅብኝን ሁሉ ማበርከት አለብኝ የሚል እምነት አለኝ፣ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ኢፍትሀዊነቶች እና ጭቆናዎች ተንሰራፍተው ስለሚገኙ እነዚህን እኩይ ተግባራት በምጽፋቸው ትችቶቸ ማጋለጥ እና ከንቱ መሆናቸውን መቃወም አለብኝ… ለዚህ በጎ ዓላማ በድፍረት ትግል በማካሂድበት ወቅት ሊያስከፍለኝ የሚችለውን ዋጋ ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ“ በማለት ከእስር ቤት አፈትልከው በሚወጡ የእጅ ጽሁፎቿ ገልጻለች ጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ፡፡ በማይበገረው እና በማይንበረከከው ትክክለኛ የጽናት አቋሟ ምክንያት ገዥው አካል ሰብአዊነት የሚባለውን ክቡር ነገር በመደፍጠጥ የህክምና አገልግሎት እንዳታገኝ ቅጣት ጥሎባታል፡፡ መቀመጫውን ሎንዶን ያደረገ የህግ መከላከል የተነሳሽነት ሜዲያ/Media Legal Defense Initiative የተባለ ተቋም በአልጃዚራ ባቀረበው ዘገባ መሰረት ርዕዮት “በሰውነት አካሏ ላይ የተከሰተ እብጠት የተገኘ ቢሆንም ተገቢ የሆነ ህክምና እየተሰጣት እንዳልሆነ ግልጽ አድርጓል፡፡ ምንም ዓይነት የሰመመን መስጫ ማደንዘዣ ሳይሰጣት በጡቷ ላይ የቀዶ ህክምና ስራ በማከናወን የቀዶ ህክምና መስፊያ ክሩ ከጡቷ ሳይወጣ ከዓመት በላይ ከመቆየቱም በላይ ከደህረ ቀዶ ህክምናው በኋላም ቢሆን ተገቢ የሆነ ህክምና የተሰጣት አይደለም“ ብሏል፡፡ ለእኔ ርዕዮት የጀግና ተምሳሌታዬ ናት!
የማይበገረው ጋዜጠኛ እና አርታኢ ውብሸት ታዬ የመናገር አንደበቱን ተሸብቦ በመለስ ዜናዊ ዝዋይ በሚባል አስፈሪ እና ጭራቃዊ የማጎሪያ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ በእርሱ ላይም የ14 ዓመታት እስራት ተበይኖበታል፡፡ ውብሸት የገዥውን አካል ሙስና እና ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀምን አስመልክቶ በጋዜጣ ላይ የሚያቀርባቸውን ትችቶች እና አስተያየቶች በፍጹም አያቋርጥም፡፡ ውብሸት ለሚጠዘጥዝ የኩላሊት ህመም ተጋልጦ የሚገኝ ቢሆንም እርሱም ህክምና እንዳያገኝ ተደርጎ በመሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ በማጎሪያው እስር ቤት ለሚገኙት የህሊና እስረኞች የህክምና አገልግሎት መንፈግ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እለት በእለት የሚፈጽማቸው በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ የቅጣት ወንጀሎች ናቸው፡፡ ፍትህ እየተባለ የሚጠራው የውብሸት የአምስት ዓመት ልጅ እንዲህ በማለት ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛል፣ “ሳድግ እና ለአቅመ አዳም ስደርስ እኔም እንደ አባቴ ሁሉ ወደ እስር ቤት እጋዛለሁን?“ ሕፃኑ ፍትህ በአሁኑ ጊዜ አጥር የሌለው እስር ቤት ውስጥ እየኖረ መሆኑን ሊገነዘብ አይችልም፡፡
ከጥቂት ሳምንታት በፊት “የኢትዮጵያ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች” (የፖለቲካ እስረኞችን ከያዘው ከመሀል ከተማ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኘው የ “መለስ ዜናዊ ታዋቂው የቃሊቲ እስር ቤት” ህንጻዎች ቀጥሎ የተሰየመ) እና ሌሎች ጋዜጠኞች በስም አጥናፍ ብርሀኔ፣ ዘላለም ክብረት፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋቤላ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ተስፋለም ወልደየስ እና ኤዶም ካሳዬ የክሱ ጭብጥ ባልታወቀበት ሁኔታ ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር ውለው ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ፖሊስ በእነዚህ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ላይ ምን ዓይነት ክስ መመስረት እንዳለበት ገና በመለግ ላይ ይገኛል፡፡
(የገዥው ፖሊስ የሚጠረጥረውን ዜጋ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር አውሎ እና እስር ቤት በማጎር እያሰቃዬ ተሰራ ለተባለው ጥፋት ማስረጃ እና መረጃ በመፈለግ በዜጎቿ ላይ ሰብአዊ መብትን በመደፍጠጥ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ብቸኛዋ አገር ናት!!! የይስሙላዎች የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶች በዘፈቀደ ከህግ አግባብ ውጭ በቁጥጥር ስር ለዋሉት ዜጎች ዋስትና በመንፈግ ፖሊስ እና አቃቤህግ የሚባሉ የገዥው አካል የማጥቂያ መሳሪያ ሎሌዎች የሚፈበረኩ የፈጠራ ውንጀላዎችን አቀነባብረው እስኪያቀርቡ ድረስ የተንዛዙ እና አሰልቺ የሆኑ ማያልቅ ቀጠሮዎችን በመስጠት እና የይስሙላውን ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደት ከሚገባው በላይ በማዘግየት በንጹሀን ዜጎች ላይ የቁማር ጨዋታ በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ነው አነዚህን ፍርድ ቤቶችን “የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤቶች እያልኩ የምጠራቸው፡፡” እውነተኛው የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ወንጀል ሀሳብን በነጻ በመግለጽ የሚያምኑበትን ነገር በነጻ ማራመዳቸው እና እነርሱ የተሻለች ኢትዮጵያ በማለት ስለሚጠሯት ኢትዮጵያ ህልም ማለማቸው ነው፡፡ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንን ጉዳይ የሚመለከተው በቅርቡ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የዳኝነት ችሎት ለህዝቡ እና ጉዳዩን በቅርበት ለሚከታተሉት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ዝግ ነበር፡፡
እስክንድር ነጋን፣ ርዕዮት ዓለሙን፣ ውብሸት ታዬን፣ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንን… የሚፈሯቸው ለምንድን ነው?
ናፖሊዮን ቦና ፓርት የተባሉት የፈረንሳይ አምባገነን መሪ በዚያች አገር የነጻው ፕሬስ ላይ ጦርነት ባወጁበት ወቅት “ከአንድ ባታሊዮን ጦር ይልቅ አራት ተቃዋሚ ጋዜጦች የበለጠ ይፈራሉ“ የሚለውን እውነታ የበለጠ ግልጽ አድርጎታል፡፡ ላለፉት 23 ዓመታት በኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ እንደ መዥገር በስልጣን ላይ ተጣብቆ ለሚገኘው ገዥ አካል ኤኬ – 47 ከታጠቀ አንድ ባታሊዮን ጦር ይልቅ ብዕር እና የኮምፒውተር ኪይ ቦርድ የያዙ ጥቂት ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን የበለጠ ያስፈሩታል፣ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ እንዲወሸቅ ያደርጉታል፣ ያርዱታል፣ ያስደነብሩታል፣ የሚይዝ የሚጨብጠውን ያሳጡታል፣ የቀን ቅዠት ይፈጥሩበታል፣ በላብ እንዲጠመቅም ያደርጉታል፡፡ በታሪክ መነጽር ሲታይ እና ሲገመገም ሁሉም አምባገነኖች እና ጨቋኞች የነጻውን ፕሬስ የእውቀት እና የክህሎት ኃይል አጥብቀው ይፈሩታል፡፡ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ተንፈራጥጠው የሚገኙት አምባገነኖች ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው ከታቀው እና በልዩ ልዩ የጦር ክፍሎች ተዋቅሮ በጠላት ላይ ቅጽበታዊ ድልን የመቀዳጀት አቅም ካለው እና የጠላትን ኃይል በማያንሰራራ መልኩ ከሚያደባይ የጦር ኃይል ይልቅ የነጻውን ፕሬስ የዕውቀት እና የክህሎት ኃይል አጥብቀው ይፈራሉ፡፡
ጠቅላላ የብዙሀን መገናኛዎችን እና ነጻውን ፕሬስ መቆጣጠር የገዥዎች እኩይ ምግባር ነው፡፡ የመረጃ ፍሰቶችን በመቆጣጠር በኃይል የሚገዙትን ህዝብ ልብ እና አእምሮ የተቆጣጠሩ እንደሚመስላቸው እምነት አላቸው፡፡ የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎችን በመቆጣጠር እንደ በቀቀን እየደጋገሙ ከሚቀፈቅፉት ነጭ ውሸታቸው እውነትን የሚፈበርኩ ይመስላቸዋል፡፡ ነጻውን ፕሬስ አፈር ድሜ በማብላት ሁሉንም ህዝብ ሁልጊዜ ማሞኘት የሚችሉ ይመስላቸዋል፡፡ ሆኖም ግን “እውነት ለዘላለም ተቀብራ እንደማትቀር እና ግፈኞችም በጉልበት ነጥቀው በያዙት የስልጣን ዙፋን ወንበር ላይ ለዘላለም ተጣብቀው እንደማይቆዩበት ድንጋይ በሆነው ልባቸው ያውቁታል፡፡“ ሁልጊዜም ስልጣናቸውን የሚያጡ እየመሰላቸው እለት በእለት የውሸት ድሪቷቸውን እየደረቱ ኑሮ አድርገው ይዘውታል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተጣብቆ የሚገኘው አረመኔ አምባገነን ገዥ ከብዙ ዓመታት በፊት ናፖሊዮን ተጋፍጦት የነበረውን ዓይነት ሁኔታ ተጋፍጦ ይገኛል፡፡ “ጋዜጠኛ የህዝቡን እሮሮ የሚያሰማ፣ ስህተትን አራሚ፣ ምክርን የሚለግስ፣ የሉዓላዊነት ወኪል እና የአገሮች መምህር ነው፡፡“ ጋዜጠኛ “አገርን የሚያስተምር” ነው፣ መረጃን ለህዝብ የሚሰጥ ነው፣ ህዝቡን በእውቀት የማነጽ እና የማስተማር ኃላፊነት አለው፡፡ እንግዲህ እነዚህ እውነታዎች ነበሩ ናፖሊዮን ነጻውን ፕሬስ እንዲፈሩት ያስገደዳቸው፡፡ የነጻው ፕሬስ ኃይል የናፖሊዮንን አምባገነናዊ አገዛዝ ትርጉም ባለው መልኩ እንደሚያጋልጠው እና በህዝቡ ዘንድ ተጠያቂ እንደሚያደርገው ናፖሊዮን ይገነዘቡ ነበር፡፡ ናፖሊዮን የፈረንሳይን ህዝብ ለማስፈራራት በማሰብ መጠነ ሰፊ የሆነውን የስለላ መረባቸውን በመዘርጋት ሲያካሂዱት የነበረውን ስለላ ሲያጋልጡ የነበሩትን ጋዜጠኞች ለማስፈራራት፣ በእስር ቤት ለማጎር፣ በስራዎቻቸው ላይ ቁጥጥር ለማድረግ እና አንደበታቸውን ለመሸበብ ጊዜ አላባከኑም፡፡ ነጻው ፕሬስ የናፖሊዮን ወታደራዊ እቅድ መክሸፉን አጋልጧል፡፡ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ባልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ማንንም ሳይለይ በጅምላ በዋና ዋና መንገዶች ላይ የተካሄዱትን ጭፍጨፋዎች እና የእርሳቸው የፖለቲካ ተቀናቃኝ በሆኑት ቡድኖች እና ግለሰቦች ላይ የተካሄደውን እስራት፣ ማሰቃየት እና ግድያ አውግዟል፡፡ በኢትዮጵያ እንደ መዥገር በስልጣን ወንበር ላይ ተጣብቀው የሚገኙት አምባገነኖች በናፖሊዮን ቅዠት በመውደቅ በተመሳሳይ መልኩ ወጣት ጦማሪያንን እና የነጻው ፕሬስ አባላትን ያስራሉ፣ ያሰቃያሉ፡፡ እውነታውን በመፍራት እንቅልፋቸውን አጥተው በነጭ ላብ ተዘፍቀው ያድራሉ!
የኢትዮጵያ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ልዩ የኢትዮጵያ ጀግናዎች እና ጀግኒቶች ናቸው፡፡ የእውነት ተናጋሪ ተዋጊዎች ናቸው፡፡ አረመኔ አምባገነኖችን በብዕሮቻቸው እና በኮምፒውተር ኪቦርዶቻቸው ይዋጋሉ፡፡ የእነዚህ ወጣቶች ጥይቶች እውነት፣ ቃላት፣ ሀሳቦች፣ እውነታዎች እና እምነቶች ብቻ ናቸው፡፡ የተንሰራፉትን ውሸቶች በእውነት ጎራዴ ይከትፏቸዋል፡፡ መጥፎ እና መሰሪ ሀሳቦችን በጥሩ ሀሳቦች ያሳድዷቸዋል፣ እናም ያረጁ እና ያፈጁ፣ እንዲሁም የጃጁ፣ እና የበከቱ አሮጌ አስተሳሰቦችን በአዲስ እና ተራማጅ በሆኑ አስተሳሰቦች ለመተካት የማስተማር ጥረታቸውን ቀጥለዋል፡፡ የህዝቦችን ተስፋቢስነት በመዋጋት በተስፋ ቃላት ያለመልማሉ፡፡ ፍርሀት በጀግንነት እና በደፋርነት ድል እንደሚመታ ለህዝቡ ያስተምራሉ፡፡ ድንቁርናን እና ኃይለኛ ደንቆሮዎችን በእውቀት እና በምክንያታዊነት ይዋጋሉ፡፡ በእብሪት እና ትእቢት ለተወጠሩት የገዥው አካል አባላት በሰለጠነ መልኩ ለማስተማር እና ለማግባባት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ትዕግስትየለሽነትን በታጋሽነት፣ ጭቆናን ከመሸከም በጽናት ታግሎ በማስወገድ እና በጥርጣሬ ከመሸነፍ በሙሉ እምነት አሳድሮ ድል በመምታት ለመቀየር ይፈልጋሉ፡፡ የህዝቡን ልብ እና አእምሮ ለመያዝ በሚደረገው የትግል አውድ እንደ ወሮበላው የገዥ አካል ስብስብ በተራ የውሸት ፕሮፓጋንዳ እና በኃይል በጉልበት ጨፍልቆ ለመያዝ ሳይሆን እውነታውን እና እውነቱን ብቻ ለወገኖቻቸው በማሳየት በብዕሮቻቸው እና በኮምፒውተር ኪቦርዶቻቸው ይታገላሉ፡፡
ክህደት፣ ውሸት እና ፍርሀት በተንሰራፋባት ምድር ላይ መኖር፣
በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እውነት ውሸት በሆነባት፣ እውነት በእየለቱ በምትደመሰስባት እና ሸፍጠኛ አታላዮች በፍርሀት ተዘፍቀው የሚኖሩባት የእራሳቸውን ምድር ፈጥረዋል፡፡ ገዥው አካል እንዲህ የሚለውን የካርቴሲያንን መርህ አዛብቷል፣ “በኛ አስተሳሰብ ብቻ ነገሮች ሁሉ ህልውና ይኖራቸዋል ወይም ደግሞ ህልውና አልባ ይሆናሉ“፡፡ መለስ ዜናዊ የክህደት አለቃ ነበር፡፡ ሁልጊዜ በሱ የማጎሪያ አስር ቤቶች ውስጥ ምንም ዓይነት የፖለቲካ እስረኛ የለም በማለት ሽምጥጥ በማድረግ ይክድ ነበር፣ እንዲህ በማለት፣ “በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የፖለቲካ እስረኛ የለም፡፡ በእስር ቤት ያሉት አመጸኞች እና አሸባሪዎች ናቸው፡፡ እናም በእስር ቤቶቻችን የፖለቲከ እስረኞች አሉ ብሎ ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው ምክንያቱም የፖለቲካ እስረኞች አይደሉምና፡፡ በሱ የንጉስነት ወቅት ምንም ዓይነት ረሀብ እና ቸነፈር እንዳልነበረ ሙልጭ አድርገው በመካድ እንዲህ ብሎ ነበር፣ በጣም ጥቂት የሆኑ በጣት የሚቆጠሩ በምግብ እጥረት ጉዳት የደረሰባቸው በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ የወረዳ ኪስ ቦታዎች እና በሶማሊ ክልል አካባቢ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ብቻ ነው የነበሩት በማለት ዓይኔን ላፈር ብለዋል፡፡ በአገሪቱ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ያፈጠጠ እና ያገጠጠ እውነታ ሙልጭ አድርገው በመካድ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የሰብአዊ መብት ጥሰት የለም“ ብለዋል፡፡ ይህንን ለማስረገጥ በማሰብ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ኦጋዴን አካባቢ መንደሮችን አቃጥለዋል እየተባለ ውንጀላ ቀርቦብናል፡፡ ሆኖም ግን በእርግጠኝነት ልነግራችሁ እፈልጋለሁ፤ ኑስ አንድ መንደር እንኳ አልተቃጠለም፡፡ እናም እኔ እስከማውቀው ድረስ አንዲት ጎጆ አልተቃጠለችም፡፡ እኛ እየተከሰስን ያለነው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ቀድሞ ከነበሩባቸው መንደሮች በማንቀሳቀስ ወደ መጠለያ ካምፖች በማስገባታችን ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ቅንጣት መረጃ ሊቀርብ አይችልም“ ብሎ ነበር፡፡ የአሜሪካ የሳይንስ እድገት ማህበር/American Association for the Advancement of Science በኦጋዴን መንደሮች ላይ የተካሄደውን የጅምላ የመንደሮች ማቃጠል ወንጀል በሳቴላይት ምስሎች የተረጋገጠው እውነታ ለመለስ ምድር ምናባዊ ህይወት ምንም አይደለም፡፡ አደናጋሪ የፕሬስ ህግ አዋጅ በማውጣት በደርዘን የሚቆጠሩ ምርጥ የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ለእስር እና ግዞት ሲዳረጉ የሌባ አይነ ደረቅ እንዲሉ በሀሰት በነተበው አንደበታቸው መልሰው “ከዓለም የተሻለ ምርጥ የፕሬስ ህግ” በማለት ያደናግራሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 የተካሄደውን አገር አቀፋዊ “ምርጫ” ተከትሎ አቶ መለስ ፓርቲያቸው ምርጫውን በ99.6 በመቶ ያሸነፈ መሆኑን በኩራት ተናግረው ነበር፣ ምክንያቱም ህዝቡ ፓርቲያቸውን የሚወደው ስለሆነ ነው በማለት አፋቸውን ሞልተው ተናግረው ነበር፡፡ አቶ መለስ የኦርዌላን/Orwellian የእንስሳት ትረካ ዓይነት እውነታን የሚያራምዱ ሰው ነበሩ፡፡ ውሸታቸውን ለመንዛት ሲፈልጉ “የፖለቲካ ቋንቋን በመጠቀም የለየለትን ነጭ ውሸት እውነት እንዲመስል አድርገው በማቅረብ፣ ግድያ መፈጸም ወንጀል እና የስነምግባር ዝቅጠት መሆኑ ቀርቶ የሚያስከብር እንደሆነ አድርገው በማቅረብ ነጩን ውሸት የእውነት ቅርጽን እንዲላበስ አድርገው በማስመሰል የማቅረብ የባዶ ብልጣብለጥነት አካሄድ መንገድን ይጠቀሙ ነበር፡፡”
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተቀምጠው አገሪቱን እያተራመሱ በመግዛት ላይ ስለሚገኙት ስብስቦች አንድ የማይካድ ሀቅ አለ፡፡ ሁሉም በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተወሽቀው ነው እየኖሩ ያሉት፡፡ ያገጠጠውን እና ያፈጠጠውን እውነታ አየፈሩ ነው በመኖር ላይ ያሉት፡፡ የነጻው ፕሬስ ኃይል እውነታውን የሚያጋልጥ ስለሆነ የነጻውን ፕሬስ ኃይል በመፍራት ነው እየኖሩ ያሉት፡፡ በአንድ ወቅት የእነርሱ የአመለካከት ፍልስፍና አለቃ ቁንጮ የነበሩት ቪላድሚር ሌኒን “የመናገር ነጻነት እና የፕሬስ ነጻነት ለምንድን ነው የሚፈቀደው? ለምንድን ነው መንግስት ትክክል ነው ብሎ ያመነበትን ነገር ሲሰራ ትችት እንዲቀርብበት የሚፈቅደው? ተቃዋሚዎችን የጠላት መሳሪያ እንዲሆኑ መንግስት መፍቀድ የለበትም፣ ሀሳቦች ከጠብመንጃ የበለጠ የገዳይነት ባህሪ አላቸው፡፡ ለምንድን ነው ማንም ሰው የማተሚያ ቤት እንዲገዛ እና የሚቀርቡ ሀሳቦችን አትሞ በማሰራጨት በስልጣን ላያ ያለውን መንግስት በተቀነባበረ ስሌት ለመተቸት እና ለማሳፈር እንዲችል የሚፈቀደው?“ እንዳሉት ማለት ነው፡፡
እውነታውን በሚገባ ያውቁታል ምክንያቱም እውነታው ህዝቡን ነጻ እንዲሆን ያግዘዋል፡፡ ነጻነትን ይፈራሉ ምክንያቱም አዲስ ሀሳቦችን ይፈራሉ፡፡ አዲስ ሀሳቦችን ይፈራሉ ምክንያቱም ለውጥን ይፈራሉ፡፡ ነጻ የሆነ ህዝብ የእውነትን ጥሩር ታጥቆ የሀሳብ ነጻነትን ተጎናጽፎ በእራሱ ፈቃድ የእራሱን የመንግስት ዓይነት ለመመስረት ሙሉ ነጻነት አለው፡፡
በኢትዮጵያ ላይ ስላለው ገዥ አካል ያለው እውነታ ምንድን ነው? እውነታው በሰው ልጆች ላይ ግፍን የፈጸሙ ወንጀለኞች ናቸው፡፡ ምንም ዓይነት ህጋዊነት የላቸውም፡፡ በጠብመንጃ ኃይል በጉልበት በስልጣን ወንበር ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው የሚገኙ አምባገነኖች ናቸው፣ ምርጫዎችን በመስረቅ እና በመዝረፍ ተመርጠናል እያሉ በማታለል ተክነዋል፣ በጥልቅ የሙስና ማእበል ውስጥ ተዘፍቀው የአገሪቱን ሀብት በማውደም ላይ ይገኛሉ፣ ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በህገወጥ መንገድ በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፣ የህግ የበላይነትን በመደፍጠጥ በጫካው ህግ የሚገዙ ህገወጦች ሆነዋል፣ እውነታው ሲታይ በአጠቃላይ በሸፍጥ የታወሩ የጫካውን አስተዳደር ወደ መንግስታዊ አስተዳደርነት አዙረው ህዝብን በማተራመስ ላይ የሚገኙ የስግብግብ ወሮበላ ቡድን ስብሰቦች ናቸው፡፡ እውነታው በአጠቃላይ ሲታይ የአፍሪካን የጨካኝ ዘራፊነት ስርዓት በሀገራችን ላይ የሚተገብሩ ወሮበላ ዘራፊዎች ናቸው፡፡
እነዚህ ወሮበላ ዘራፊዎች ነጻ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያንን ይፈራሉ ምክንያቱም እነዚህ ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪዎች አምባገነኖቹ የሚሰሯቸውን ወንጀሎች እና ሙስናዎች፣ የመከኑ እና የወደቁ ፖሊሲዎቻቸውን፣ የአቅም ድሁርነታቸውን እና ድንቁርናቸውን በማጋለጥ እውነታውን ያወጡባቸዋል፡፡ እነዚህ ጭራቃዊ ፍጡሮች በጫማቸው ስር እረግጠው የያዟቸው የግፍ ሰለባዎች ነጻ ቅዱስነት እና የያዙት ጸበል ስለሚያቃዣቸው ነጻ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪያንን አጥብቀው ይፈራሉ፡፡ በያዙት ሁሉ ኃይል በመጠቀም እውነቱ ወጥቶ ለህዝብ እንዳይደርስ እና እንዳይታወቅባቸው ማንኛውንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም፡ የሳቴላይት ስርጭቶችን ሳይቀር አፍነዋል፣ የኢንተርኔት ግንኙነቶችን አቋርጠዋል፣ ጋዜጦችን በመዝጋት ጋዜጠኞችን በእየእስር ቤቶች አጉረዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የአረብሳት ለዓለም አቀፉ የግንኙነት ህብረት/International Communication Union እና ለአረብ ሊግ/Arab League ኢትዮጵያ ስርጭቱን ያፈነች መሆኗን እና “ወንጀለኛውን ለመቅጣት አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ” እና በዚህ ህገወጥ ድርጊት ምክንያት ለደረሰው ጉዳት ወይም በዚህ ህገወጥ የአፈና ተግባር ምክንያት ወደፊት ለሚደርስ ማንኛውም አደጋ ተገቢውን ካሳ እንድትከፍል እንዲደረግ ተማጽዕኖውን አቅርቧል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ገዥው አካል በገበያ ላይ የቀሩትን እና በገዥው አካል ላይ ጠንካራ ጥችት የሚያቀርቡትን ጥቂት ጋዜጦች በየመንገዶች እያዞሩ የሚሸጡትን ጋዜጣ አዟሪዎችን እያሳደደ፣ እያስፈራራ እና በቁጥጥር ስር እያዋለ ይገኛል፡፡
እውነታው በኢትዮጵያ ሀሳብን በነጻ ከመግለጽ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እየተካሄደ ላለው ጭቆና እና አፈና የቻይናዎች ስውር እጆች ያሉበት መሆኑ ነው፡፡ ቻይናዎች ለገዥው አካል የማፈኛ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ማቅረብ ብቻ አይደለም የሚያከናውኑት፡፡ ሆኖም ግን ለተንቀሳቃሽ ስልኮች እና ለኢንተርኔት አገልግሎት የመሰረተ ልማት ስራዎችም ግንባር ቀደም ተዋንያን ናቸው፡፡ የመረጃ ፍሰት ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ እና ወደ ኢትዮጵያም እንዳይገባ ለመገደብ እና ለማቋረጥ የአንድ መስኮት ፈጣን የአግልግሎት መስጫ ኪቶችን ይዘዋል፡፡ ከዛሬ ሁለት ዓመታት ገደማ በፊት የቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሄላሪ ክሊንተን ዛምቢያን በመጎብኘት ላይ ሳሉ የቻይናውያን በአፍሪካ አህጉር ላይ ያላቸውን ሚና በማስመልከት እንዲህ ብለው ነበር፣ “በቅኝ ግዛት ዘመን ጊዜ መምጣት እና ለመሪዎቹ ገንዘብ በመስጠት የተፈጥሮ ሀብቶችን ከአፍሪካ መውሰድ ቀላል ነበር፣ በምትለቅቅበት ጊዜ እዚህ ላለው ህዝብ ምንም ነገር ትተህ አትወጣም፣ በአሁኑ ጊዜ አዲስ ቅኝ ተገዥነት በአፍሪካ ማየት አንፈልግም“ ብለው ነበር፡፡ እውነታው ግን ቻይናውያን በኢትዮጵያ መቆየታቸው እና የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት መያዛቸው ብቻ ሳይሆን ለገዥው አካል የቴክኒክ እገዛ በመስጠት፣ የኦዲዮ እና ቪዲዮ መሳሪያዎችን በማቅረብ የመረጃ ምርመራ በማድረግ እና በኤሌክትሮኒክ መገናኛ ብዙሀን ላይ አፈናዎችን በማካሄድ ነጻ አሰተሳሰብን በመጨቆን በዋናነት ተጠያቂዎች ናቸው፡፡
ነጻነትን ይፈራሉ፡፡ ነጻነት ምንድን ነው? የሁሉም የሰው ልጆች ነጻነቶች ባህሪያት ከፍርህት የሚገኙ ነጻነቶች ናቸው፡፡ በተግባራዊ ሁኔታ ሲታይ አንድ ሰው ያሰበውን ለመናገር መፍራት ወይም ደግሞ አንድ ሰው ደስ ያለውን መጻፍ መፍራት ወይም በአንድ ሀሳብ ማለትም ሀይማኖት ወይም ፍልስፍና ላይ ማመን እና አለማመንን መፍራት ወይም ደግሞ አንድ ሰው ከመረጠው ሰው ጋር አብሮ መምጣት መፍራት ማለት አይደለም፡፡ ዋናው እና የመጨረሻው የሰው ልጅ ሁሉ ሊያደርገው የሚገባው ህዝቡ እራሱ ስልጣን የሰጣቸው በስልጣን ወንበር ላይ ያሉት ሰዎች ናቸው በህብረተሰቡ የኑሮ ሂደት ላይ መፍራት እና ህዝቡን ማክበር ያለባቸው፡፡
ሀሳብን ይፈራሉ፡፡ “ሀሳቦች ከጠብመንጃ የበለጠ ገዳዮች ናቸው“ በማለት ሌኒን አስጠንቅቀዋል፡፡ ሀሳቦች ሳይንስን፣ ፖለቲካን እና ማናቸውንም የሰው ልጅ የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች ሁሉ የመለወጥ ኃይል አላቸው፡፡ ከምንም በላይ ዓለም ጠፍጣፋ አይደለችም፡፡ ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ያሉ ገዥዎች የአዲስ ጠፍጣፋ መሬት ባለቤቶች ናቸው፡፡ እንደ ጥንቱ ንጉሶች፣ ዛሮች፣ እና ማሃራጃሆዎች ሆነው ከህዝቡ ፈቃድ ውጭ ( በተሰረቀ ስምምነት) መሰረት መግዛት ይፈልጋሉ፡፡ ጥቂት ሞራላዊ ጠቀሜታ ያላቸው ሀሳቦች ሲኖሯቸው ነገሮችን በቀላሉ ለመገንዘብ እና አዳዲስ ሀሳቦችንም ለማድነቅ እና ተቀብሎ ወደ ተግባር ለማዋል የምሁርነት አቅሙ የሌላቸው የመንፈስ የአስተሳሰብ ድሁሮች ናቸው፡፡ ሆኖም ግን የጎሳ ክፍፍልን ለማራመድ፣ ስግብግብነት እና ጥላቻን ለማምጣት፣ የጥላቻ ከባቢን የመፍጠር፣ ግጭትን የመጫር፣ ሙስናን ለማስፋፋት እና ለማጠናከር፣ ህብረትን በመናድና የጥላቻ መንፈስን በመዝራት እንዲሁም በሰዎች መካከል ጥርጣሬ እና አለመተማመን እንዲነግስ በማድረግ ጭንቅላቶቻቸው ዋና የዲያብሎሳዊነት ቤተሙከራዎች ናቸው፡፡ ህዝብን ሊያስተባብሩ እና ሊያፋቅሩ የሚችሉ ሀሳቦችን ለማመንጨት፣ በጎሳዎች መካከል ፍቅርን የማስፈን፣ ብሄራዊ አንድነትን የማምጣት፣ የጋራ መግባባትን የመፍጠር፣ የጓዳዊነት መንፈስ የማጠናከር እና እምነትን የማራመድ አቅመቢሶች ናቸው፡፡
አዳዲስ ሀሳቦችን የሚፈሩ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተቆናጥጠው የሚገኙ አምባገነኖች የአዲስ ሀሳብ አመንጭ እና ባለራዕይ መስለው ለመታየት ይሞክራሉ፡፡ ህዝቡ እና ዓለም ወደፊት ጥሩ ነገር የሚያስቡ መልካም ነገር አላሚዎችና ፈጣሪዎች እንደሆኑ አድርጎ እንዲመለከታቸው እና እምነት እንዲኖረው ይፈልጋሉ፡፡ ሆኖም ግን በህልም የቅዠት ፍርሀት ተዘፍቆ ያለ ማንም ሰው መልካም አላሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ባለራዕይ መሪዎች ለሚያደርጓቸው ማለትም ታማኝነት፣ ኃላፊነትነትን የመሸከም ብቃት፣ ሌሎችን አነቃቅቶ እና አሳምኖ በስራ የማሳተፍ ችሎታ፣ ያለፉትን ስህተቶች በግዴለሽነት እንዳሉ ከመድገም ይልቅ ከስህተት እና ከውድቀት መማርን፣ ስህተት በሚሰሩበት ጊዜ ይቅርታ አድርጉልኝ ብሎ መጠየቅን፣ ግልጽነት፣ ትክክለኛውን ነገር ለመስራት ፍትሀዊነት እና በፍቅር ላይ የተመሰረተ ሆኖ ከመገኘት ተግባራት ጋር ሁሉ አይተዋወቁም፡፡ መጥፎ እና ዕኩይ ተግባራትን ለማድረግ ፍቅር ያላቸው መሰሪ መሪዎች ናቸው፡፡ ኪሶቻቸውን የሚወጥሩትን የተዘረፉ በርካታ ገንዘቦችን ዓይኖቻቸው በቀላሉ ማየት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን አሁን እየፈጸሟቸው ያሏቸው በርካታ ወንጀሎች በዘለቂነት ለወደፊት ሊያስከትሉት የሚችሏቸውን እንደምታዎች ለማየት የታወሩ ናቸው፡፡ ጠንካራን ሀሳብ ጊዜው እየመጣ ያለውን ሀሳብ የሚያቆመው ምድራዊ ኃይል የለም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነት የሚያደርገውን ተጋድሎ የሚያቆመው ኃይል የለም፡፡ አንዴ ከተጀመረ በመንገዱ ላይ ያለውን ጋሬጣ ሁሉ እየጠራረገ ወደፊት ይገሰግሳል፡፡
ለውጥን ይፈራሉ፡፡ ለውጥ ምንድን ነው? ለውጥ በሁሉም ነገር የሚከሰተውን የዕድገት እና የመበስበስ ዓለም አቀፋዊ ዘላለማዊ የለውጥ ህግ የሚገዛ ሂደት ነው፡፡ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው ገዥ አካል ለውጥን አጥብቆ ይፈራል ምክንያቱም በህበረተሰቡ ላይ ያላቸውን የኢኮኖሚ እና የፖሎቲካ የበላይነት ቦታ ስለሚያሳጣቸው ነው፡፡ ለውጥን ሊያመጡ የሚችሉ ነገሮችን በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ለማምጣት የሚንቀሳቀሱትን ማናቸውንም ሙከራ ሁሉ ይደመስሳሉ፡፡ ከዚህ አንጻር “በሰላማዊ መንገድ የለውጥ አብዮት እንዳይመጣ የሚከለክሉ ሁሉ የአመጽ ለውጥ በኃይል እንዲመጣ ይገደዳሉ“ የሚለውን ሀቅ ለመገንዘብ የተሳናቸው ይመስላል፡፡
በፖለቲካ ህጋዊነት ማጣት እና በመንግስት አቅም ማጣት ምክንያት ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በፖለቲካ መበስበስ የመጨረሻ ጠርዝ ላይ ያለችበት ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡ የጨነገፈ መንግስት ሆናለች፡፡ ባለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት የጎሳ ክፍፍል ፖሊሲ (የጎሳ ፌዴራሊዝም) “ልማታዊ መንግስት” ባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዘገብን በማለት የሚራገበው እርባናየለሽ ፕሮፓጋንዳ ቢኖርም እንኳ ኢትዮጵያን በሁለት አማራጮች ላይ ጥሏታል፡፡ የእነርሱ ነጭ ውሸት ብቻ ነው በባሁለት እና በባለሶስት አሀዝ እድገት ያስመዘገበው፡፡
ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ቆማለች፡፡ እንደተባበረች ሀገር አንድ ሆና ወደፊት ተገሰግሳለች ወይም ደግሞ ወደተለያዩ ትናንሽ የተበጣጠሱ ክልሎች ትገነጣጠላለች፡፡ የአፓርታይድ ዓይነት ባንቱስታንስ በኢትዮጵያ ክልል እየተባለ በዘር እና በቋንቋ የተቀየደ የአገዛዝ ስርዓት ነው፡፡ ኢትዮጵያ የተበጣጠሱ ግዛቶች ስብስብ የምትሆን ከሆነ የመጀመሪያው ቸግር ቀማሽ የሚሆኑት አሁን በስልጣን ላይ ተጣብቆ የሚገኘው ገዥው አካል፣ የእነርሱ ጋሻጃግሬዎች እና ደጋፊዎች ናቸው፡፡ በፖቲካ ስልጣን ማጣት ብቻ የሚቆም ሳይሆን ቢያንስ እስከ አሁን ድረስ በአገር ውስጥ የሚደረግ ለውጥ ዘግይቶ እንደደረሰ ባቡር ይቆጠራል፡፡ በምስራቅ አውሮፓ በመካከለኛው ምስራቅ ሲነፍስ የነበረው የለውጥ ነፋስ ያለምንም ጥርጥር በኢትዮጵያም መንፈሱ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ሊነሳ የሚችለው ብቸኛ ጥያቄ ግን እነዚህ ነፋሶች ተስማሚ እና በሰላም የሚያልፉ ወይስ ደግሞ ሁሉንም ነገር እየገነደሱ እና እየቦደሱ የሚጥሉ ኃይለኛ የሁሪኬን/hurricane-force ሞገዶች ይሆናሉ የሚለው ነው፡፡
እውነት ነጻ ያወጣሀል ነጻ አስከሆንክ ድረስ ሆኖም ግን ነጻ ያልሆኑት ይሰቃያሉ፣
“እውነት ነፃ ታወጣሀለች” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ነጻነት እና ፍርሀት ለእየራሳቸው ተነጥለው የሚኖሩ ናቸው፡፡ የነጻው ፕሬስ እና ጦማሪያን ብቸኛው ተግባራቸው እንዳዩት እውነታውን ወዲያውኑ መናገር ነው፡፡ ስለ እውነታው ያላቸውን ሀሳብ የለምንም ፍርሀት የመግለጽ ነጻነት አላቸው፡፡ ሆኖም ግን ህዝቡ እውነታውን ቀድሞም ቢሆን ያውቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ በባለሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግባለች የሚለው ነጭ ውሸት ቢሆንም ህዝቦች እውነታውን ያውቁታል፡፡ የሚበላ በቂ ምግብ እንደሌለ ያውቃሉ፣ እናም ሚሊዮኖች በየቀኑ እየተራቡ እንዳሉ ያውቃሉ፡፡ እንዲሁም በቂ የውኃ አገልግሎት ወይም የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሌለ ያውቃሉ፡፡ አናሳ የህክምና አገልግሎት ነው እየተሰጠ ያለው፣ ወጣቶች ጥራት ያለው ትምህርት አያገኙም እናም ስራ አጦች ናቸው፡፡ ገዥው አካል በሙስና ማጥ ውስጥ የተዘፈቀ እና የበከተ ነው፣ እንዲሁም በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ይፈጽማል፡፡ ህዝቦች በግልጽ የአየር ድባብ ውስጥ እስረኛ ሆነው እንደሚኖሩ ያውቃሉ፡፡
የነጻ ጋዜጠኞች እና የጦማሪዎች ወንጀል የሚያውቁትን ነገር ለማያውቁት ወገኖቻቸው መግለጻቸው ብቻ ነው፡፡ የእነርሱ ወንጀል የማዕድን ሙስና እና ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀምን፣ እንዲሁም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች እየቆፈሩ በማውጣት ማስረጃ በማቅረባቸው ነው፡፡ ለዚህም በስልጣን ላያ ያለው ገዥ አካል እየፈራቸው ያለው፡፡ ገዥው አካል እውነታው ሳይታወቅ ተቀብሮ እንዲቀር እና እንዲረሳ ይፈልጋል፡፡ ገዥው አካል እውነታው እንዳይታወቅ በመደበቅ፣ እውነት ተናጋሪዎችንም ጸጥ በማስደረግ እና በየእስር ቤቶች በማጎር ለዘላለም ጸጥ በማድረግ ትንፍሽ እንዳይሉ በማድረግ እውነትን የመግደል እምነት አለው፡፡ ጆርጅ ኦርዌል እንደጠቆሙት፣ ”የማጨበርበር እና የሀሰት ሸፍጥ በተንሰራፋበት ጊዜ እውነትን መናገር አብዮተኛነት ድርጊት ነው“ ብለው ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ጦማሪያን የኢትዮጵያ የማይበገሩ አብዮተኞች ናቸው፡፡
ፍርሀትን በብዙሀን መገናኛ እንደ መሳሪያ መጠቀም፣
በስልጣን ላይ ያለው ገዥ አካል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ዋና ድክመትን እንደ ትልቅ መጠቀሚያ መሳሪያ አድርጎ ይጠቀምበታል፡፡ ህዝብን ግራ ለማጋባት፣ እርስ በእርስ ለመከፋፈል፣ ለማታለል፣ ጥላሸት ለመቀባት እና ሀሳብን ከዋናው ጉዳይ አቅጣጫውን ለማስቀየስ ፍርሀትን በዋና መሳሪያነት ይጠቀምበታል፡፡ ማቋረጫ የሌለው የፍርሀት ዘመቻ በህብረተሰቡ ላይ ለመንዛት ሲፈልግ፣ ጥላሸት ለመቀባት እና ለማጠልሸት ሲፈልግ በህዝብ የግብር መዋጮ የሚተዳደረውን መገናኛ ብዙሀን ለእኩይ ምግባር ሌት ቀን ይጠቀማል፡፡ ገዥውን አካል የሚቃወሙትን ቡድኖች እና ግለሰቦች ጸጥ ለማድረግ ሲፈልግ እርባናየለሽ በውሸት ላይ ተመስርተው የተቀነባበሩ ዘጋቢ ፊልሞችን በመፈብረክ “አሸባሪ” የሚል ታፔላ በመለጠፍ በአሰልችው የመገናኛ ብዙሀን እንደበቀቀን ይደጋግማቸዋል፡፡ የውሸት ሸፍጥ በታጨቀበት እና ለመስማት እና ለማየትም አስቀያሚ በሆነው “አኬልዳማ” ብሎ በሰየመው ለምንም የማይውል እርባናየለሽ ዘጋቢ ፊልም ኢትዮጵያ በዲያስፖራው ተቃዋሚ ኃይል እና በአገር ውስጥ ባሉ የእነርሱ የግብር ተመሳሳዮች አማካይነት እንዲሁም ሌሎች አሸባሪ ቡድኖች ትብብር እና ርብርብ አደገኛ የሽብር አደጋ ተደቅኖባት እንደሚገኝ አደንቋሪ ጩኸታቸውን አሰምተዋል፡፡ “አኬልዳማ” በዓለም ላይ የተደረጉትን በጣም አስፈሪ እና አስቀያሚ ምስሎችን ሁሉ ለቃቅሞ በቪዲዮ በማሳየት በቅርቡ በህይወት የተለዩት አቶ መለስ ዜናዊ ተቃዋሚዎቻቸውን ጥላሸት በመቀባትና በሶማሌ የሚንቀሳቀሰው የአልቃይዳ እና አልሻባብ ቅጥረኞች ናቸው ብለው በአሸባሪነት በመፈረጅ የጥቃት ብቀላቸውን በንጹሁነ ዜጎች ላይ በሰፊው ተግብረውታል፡፡
በሌላ “ጅሃዳዊ ሀራካት” በተባለ እርባናየለሽ ዘጋቢ ፊልም በክርስቲያን እና በሙስሊሙ ህብረተሰብ መካከል ፍርሀት እና ጥላቻን ለማስፋፋት በማሰብ ጸረ እስልምና እሳትን የመጫር ሙከራ አድርገው በህዝቡ አርቆ አስተዋይነት እና የንቃት ደረጃ ምክንያት እኩይ ምግባራቸው ሳይሳካ መክኖ ቀርቷል፡፡ ለዘመናት አብሮ እና ተከባብሮ እየኖረ ያለውን የክርስቲያን እና የሙሰሊም ማህበረሰቡን በማጋጨት የእስልምና አሸባሪዎች በድብቅ ጅሀዳዊ መንግስት ለመመስረት ዕቅድ አውጥተው ተንቀሳቅሰዋል በማለት በሁለቱ ታላላቅ ኃይማኖቶች እምነት ተከታዮች መካከል የማያባራ እልቂት እና የደም ጎርፍን ለማዝነብ የታቀደ ዲያብሎሳዊ የድርጊት ዕቅድ ነድፈው ነበር፡፡ አሁንም ህዝቡ የነቃባቸው እና ከእነርሱ እኩይ አስተሳሰብ ውጭ የመጠቀ ሀሳብ ስላለው እና ስላወቀባቸው ዕቅዳቸው አሁንም መክኖ ቀርቷል፡፡
ፍርሀት እና ጥላቻን በህዝቡ ውስጥ ለማስፋፋት እና ምናባዊ የሆነ የዘር እና የጎሳ እልቂት እንዲሁም የኃይማኖት ጽንፈኝነት እልቂት እንደሚከሰት በመስበክ ይህንንም እልቂት ለማስወገድ ብቸኛ ቅዱሶች እነርሱ እንደሆኑ አድርገው በማቅረብ እና በማደናገር ጸረ ኢትዮጵያ እና ዘረኛ አስተሳሰብ የተጠናወታቸው ጎጠኞች መሆናቸውን በአደባባይ አስመስክረዋል፡፡ አሁንም ተስፋ ባለመቁረጥ አንዱን ጎሳ በሌላው ላይ በማስነሳት ለማጋጨት ሌት ቀን በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ “የጎሳ ፌዴራሊዝም/ethnic federalism” በሚል እኩይ ስልት የዘር ማጽዳት ዘመቻቸውን ቀጥለውበታል፡፡ የጎሳ ጥላቻን ለመቀስቀስ ታሪካዊ ብሶቶችን እየፈበረኩ እና ጥቃቅን ነገሮችን እያጋነኑ በህዝቡ ዘንድ አለመተማመን እና ግጭቶች እንዲነሱ አበርትተው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ህዝቡ ግን ስለነቃባቸው በባዶነታቸው ቀልበቢስ በመሆን እንደ አበደ ውሻ ከወዲያ ወዲህ በመቅበዝበዝ ላይ ይገኛሉ፡፡ የእራሳቸውን ፍርሀት እንደ መሳሪያ በመጠቀም ህዝቡን ለማደናገር ይሞክራሉ፡፡
በኢትዮጵያ ትንታግ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ላይ የተከፈተው ጦርነት በእራሷ በእውነት ላይ የተከፈተ ጦርነት ነው፣
በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ገዥ አካል በነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና በጦማሪያን ላይ ያወጀው ጦርነት በእውነት በእራሷ ላይ ያወጀው ጦርነት ነው፡፡ ገዥው አካል ላለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት በተደረጉት ጦርነነቶች እና ግጭቶች ሁሉ በድል አድራጊነት ተወጥቷል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ ጎራዴ እና ኤኬ 47 አውቶማቲክ ጠብመንጃዎችን በታጠቁ አምባገነኖች እና ብዕሮች እና የኮምፒውተር ኪቦርዶችን በሚጠቀሙ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን መካከል የሚደረገው ወሳኙ ፍልሚያ ተቃርቧል፡፡ ያ ጦርነት እና ፍልሚያ በኢትዮጵያውያን/ት ልብ እና አእምሮ ውስጥ ሰርጾ ሁሉንም ዜጎች ለወሳኙ ፍልሚያ እና ለድል ጉዞ ጥርጊያ መንገዱን የሚያመቻች ይሆናል፡፡ የዚያ ጦርነት እና ፍልሚያ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን በእርግጠኝነት የምናገረው ነገር ቢኖር ፍልሚያው የሀገሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚወስን ይሆናል፡፡ በእርግጥ ያ ጦርነት በእውነት አራማጅ ወገኖች አሸናፊነት እንደተደመደመ እምነት አለኝ፡፡ ኤድዋርድ ቡልዌር ሊቶን የተባሉት ገጣሚ በትክክል እንዳስቀመጡት ጎራዴ በታጠቁት እና ብዕርን በጨበጡት ተዋጊዎች መካከል በሚደረግ የጦርነት ፍልሚያ በመጨረሻ ሁልጊዜ የወሳኙ ድል ባለቤት የሚሆኑት ብዕርን የጨበጡት ናቸው፡፡ እውነትን ጨብጠዋልና!
እውነት፣ ይህ!
ከሰዎች አገዛዝ ስር ሌላ ታላቅ ነገር አለ፣
ብዕር ከጎራዴ የበለጠ ኃይል አለው፡፡ አስተውል/ይ
ቀስት ተሸካሚዎች ይፈነድቃሉ፣ ግን ምንም የሚመጣ ነገር የለም!-
ልዩ ታምር ከጌታቸው እጀ ይቀበላሉ፣
እናም ቄሳሮችን በድን ለማድረግ ያምጻሉ
ታላቋ መሬት ትንፋሽ ያጥራታል!- ጎራዴውን ከዚህ ወዲያ ውሰዱ-
መንግስታት ከእርሱ ውጭ ሊጠበቁ ይችላሉና!
ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ያለውን ገዥ አካል ማዳን ወይስ ደግሞ የኢትዮጵያን ነጻ ፕሬስ እና ጦማሪያንን ማዳን የሚል ወሳኝ ጥያቄ ቢቀርብልኝ ቶማስ ጃፈርሰን እንደመረጡት ሁሉ እኔም የኋለኛውን ማዳን የሚለው እንዲጠበቅልኝ እመርጣለሁ፡፡ ቶማስ ጃፈርሰን እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው የሚከተለውን መልስ ሰጥተው ነበር፣ ”የእኛ መንግስት መሰረቱ የህዝብ ሀሳብ እንደመሆኑ መጠን የመጀመሪያው ዓላማ መሆን ያለበት ያንን መብት ማስከበር ነው፡፡ እናም ጋዜጦች የሌሉበት መንግስት ከሚኖር ወይም ደግሞ መንግስት በሌለበት ጋዜጦች ብቻ ከሚኖሩ የትኛው የተሻለ ነው የሚል ምርጫ ቢቀርብልኝ የኋለኛውን ለመምረጥ ለሰከንድ እንኳ ጥርጣሬ አይኖረኝም፡፡ ሆኖም ግን ይህን ስል ማንኛውም ሰው እነዚህን ጋዜጦች መቀበል እና ማንበብ መቻል አለበት፡፡“
በተመሳሳይ መልኩ ለእኔም ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን የሌሉበት ገዥ አካል ከሚኖር ወይም ደግሞ ገዥ አካል በሌለበት ነጻ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ብቻ ከሚኖሩ የትኛው የተሻለ ነው የሚል ምርጫ ቢቀርብልኝ የኋለኛውን ለመምረጥ ለሰከንድ እንኳ ጥርጣሬ አይኖረኝም፡፡ ከሁሉም በላይ ለዓላማ በጽናት የቆምኩ፣ ለምሰራው ትክክለኛ ስራ ሁሉ ኩራት የሚሰማኝ፣ ላመንኩበት ዓላማ ከልብ እና በወኔ የቆምኩ፣ ዓላማየን ለማስፈጸም በከባድ እርምጃ ወደፊት የምገሰግስ፣ ላልሰራሁት ወንጀል ይቅርታን የማልጠይቅ፣ በምሰራው ስራ ሁሉ የማላፍር፣ ቆራጥ እና የማያወላውል ባህሪን የተላበስኩ የኢትዮጵያ ጦማሪ ነኝ!!!
ኃይል ለነጻ ጋዜጠኞች እና የኢትዮጵያ ጦማሪያን!
ውድቀት እና ሞት ህዘብን በጠብመንጃ ኃይል አስገድደው ለመግዛት ለተነሱ የዕኩይ ምግባር አራማጆች!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሰኔ 3 ቀን 2006 ዓ.ም

Wednesday 11 June 2014

Association for International Broadcasting denounces Ethiopia’s intentional signal jam

Tue, 10 Jun 2014 10:25
Deutsche Welle, BBC, France 24 and Voice of America are amongst numerous members of the Association for International Broadcasting (AIB) who are angered by Ethiopian authorities’ intentional jam of satellite programs, and claim the action is a violation of international agreements. 

This also prevents audiences from being able to freely access the media and violates the internationally recognized freedom of speech and freedom of the press rights as per Article 19 of the United Nation’s Declaration of Human Rights. AIB is responding by lodging protests with the Ethiopian Foreign Ministry and its Missions in London, Berlin, Paris, Riyadh and Washington DC.

Simon Spanswick, Chief Executive of the AIB stated, “AIB and its members call for the immediate and complete cessation of this unwarranted interference by Ethiopia in the region’s telecommunications and broadcasting services. Significant, harmful interference has been directed at satellites in the Arabsat and Eutelsat fleets, and consequently to the broadcasts of a wide range of TV and radio channels.

“This deliberate interference is illegal and contravenes international law. It deprives viewers and listeners across the region of access to news, information and entertainment. The interference also adversely impacts the important operational role that Arabsat and Eutelsat have in distributing content. It also harms their businesses. Extensive technical research has confirmed that the jamming originates within the territory of Ethiopia. AIB reminds the authorities in Ethiopia that causing interference is in direct contravention to the agreements that the Ethiopian government is party to at the International Telecommunication Union. “

Liliane Landor, acting Director of the BBC World Service Group, added, “The BBC calls upon the Ethiopian authorities to end this interference. They are disrupting international news broadcasts for no apparent reason. This is a deliberate act of vandalism that tarnishes their reputation.”


Eutelsat reports increase in jamming from Ethiopia

French satellite provider Eutelsat has said its satellite fleet has experienced a drastic rise in interference originating from Ethiopia, according to a report.
NexTV reports the company’s disruptions in its satellite service from the region have increased from 5 per cent in 2010 to 15 per cent last year.
HumanIPO reported last week the British Broadcasting Corporation (BBC) and numerous other international broadcasters had claimed television and radio broadcasts on the Arabsat satellites had been intentionally jammed by the Ethiopian authorities.
“The BBC calls upon the Ethiopian authorities to end this interference. They are disrupting international news broadcasts for no apparent reason. This is a deliberate act of vandalism that tarnishes their reputation,” said Liliane Landor, acting director of the BBC World Service Group.
According to Eutelsat, its provision of signal to Saudi Arabia has also been disrupted by the jamming programme. It said the antennae are located in the northeast of the country and serve to disrupt programming on its satellites at 7 degrees West and 21 degrees East.
The company said it would be reporting the disruptions to the French National Frequencies Agency (ANF), the International Telecommunication Union (ITU) and the Ethiopian government.
Additionally, the Ethiopian government has been accused of implementing surveillance programmes targeting those in the country and its refugees being housed by foreign states.
According to Human Rights Watch (HRW) the country hasbeen using foreign technology to boost its widespread telecoms surveillance of opposition activists and journalists in Ethiopia and abroad.
Privacy Internationallodged a criminal complaint with the United Kingdom’s (UK) National Cyber Crime Unit (NCCU) of the National Crime Agency for the allegedly unlawful interception of personal communications of an Ethiopian political refugee living in the UK.
The privacy groups said that the UK-based company Gamma International played a role in the development of commercial surveillance software Finspy, which has been used by the Ethiopian government to target dissenters.

ኦባንግ “ከምርጫው” በፊት ለተቃዋሚዎች “ምርጫ” አቀረቡ

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በአገር ውስጥ ለሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና አግባብ አላቸው ለሚሏቸው አካላት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተቀምጠው እንዲመክሩ ማሳሰቢያ ሰጡ፡፡ ኢህአዴግ በውስጥ ችግሩ፣ በውጭ ተጽዕኖ ወይም በፖለቲካው የተፈጥሮ ባህርይ የሚከስምበት ደረጃ መድረሱን ያሳሰበው በ”ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ስምና ፊርማ የተበተነው የአኢጋን ደብዳቤ፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ልዩነታቸውን አጥብበው እንዲሠሩ ጠይቋል፡፡ ይህንን ለኢትዮጵያና ለሕዝባቸው ሲሉ መሥራት የማይችሉ ከሆነ ከኢህአዴግ በላይ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል፡፡
የፖለቲካ ዕርቅ በመጀመሪያ በተቃዋሚዎች ደጅ ሊተገበር እንደሚገባው ያሳሰበው አኢጋን፤ ይህንኑ ዕርቅ መሠረት በማድረግ ወደ ኅብረት እንዲመጡ በደብዳቤው ገልጾዋል፡፡ ወደ ኅብረት ሲመጡ የፖለቲካ ሥልጣን የመጨበጥ ዓላማቸውን ወደ ጎን መተው እንዳለባቸውና ኢትዮጵያን በማዳን ተግባር ላይ እንዲያተኩሩ በጥብቅ አሳስቧል፡፡
መግለጫው ሲቀጥልም “የጋራ ንቅናቄያችን ከበርካታ ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ካለው ግንኙነት አኳያ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ መረጃ ይሰበስባል፡፡ በቅርቡ አንድ ታዋቂ የምዕራቡ ዓለም የፖሊሲ አውጪ ሲናገሩ ኢትዮጵያውያን የምዕራቡ ዓለም ነጻ ያወጣናል ብለው በጭራሽ ማመን የለባቸውም፡፡ ከውጭ የሚላከውን ዕርዳታና ድጋፍ ብናቆም እንኳን ይህ የሚሆን አይደለም፡፡ የለውጥ አራማጅና መሪ መሆን ያለባቸው ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ናቸው እንጂ ለጋሽ መንግሥታት አይደሉም፡፡ ኢትዮጵያውያን ይህንን ሊረዱ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ከህወሃት/ኢህአዴግ የተሻለ አማራጭ በሚፈጥሩበት ጊዜ እኛ የግድ እንድንደግፋቸው ያደርጉናል በማለት ለጋራ ንቅናቄያችን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል” በማለት በመረጃ ላይ የተደገፈ ጭብጥ አቅርቧል፡፡
ሰሞኑን የዚህ ዓመት የSEED ተሸላሚ የሆኑት ይህ የአቶ ኦባንግ የምርጫ አማራጭ ግልጽ ደብዳቤ መጪውን ሁኔታ በሚከተለው ሁኔታ ገልጾታል፤ “አገራችን በበርካታ ድሎች ያንጸባረቀ ታሪክ ያላት ነች፡፡ ከሁሉ በበላይ የሚጠቀሰው የዓድዋ ድል በድጋሚ የሚፈጸምበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው፡፡ የዓድዋን የጦር ድል በፖለቲካው መድረክ እንድገመው፡፡ መጪውን ምርጫ ፖለቲካዊ የዓድዋ ድል የምንጎናጸፍበት እናድርገው፡፡ ነጻነታችን እንደ ዕርዳታ እህል ከምዕራባውያን የሚለገሰን አይደለም፡፡ ስለዚህ እኛው ራሳችን እንደ አድዋ ድል አንድ ሕዝብ ሆነን በመውጣት የራሳችን የምናደርገበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ቅንነት ካለ የጦር ሜዳውን አድዋ በፖለቲካው ሜዳ ላይ መድገም ይቻላል፡፡ አንድ ሊያደርጉንና ሊያስተባብሩን የሚችሉምኒልኮችንለመጠቀም ፈቃደኛና ቅን እንሁን፡፡
በአኢጋን አድራሻና በዋና ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ ስምና ፊርማ የተሰራጨው ይህ የማሳሰቢያ ግልጽ ደብዳቤ አኢጋን በተለይ በዕርቅ ዙሪያ የሚጠየቀውን ማንኛውንም ጥያቄ ድጋፍ እንደሚሰጥ ያረጋገጠ ነው፡፡ የደብዳቤው ሙሉ ቃል ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

“ነጻነትነታችን እንደ ዕርዳታ እህል ከምዕራባውያን የሚለገሰን አይደለም!”
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የፖለቲካ መሪዎች ያስተላለፈው ግልጽ መልዕክት
የተወደዳችሁ በኢትዮጵያ የምትገኙ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤
በቅድሚያ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የአክብሮት ሰላምታ በማቅረብ በትግሉ መስክ የምትከፍሉትን መስዋዕትነት የሚያደንቅ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በተለይ በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ ምህዳሩ እጅግ ጠብቦ የለም የሚባልበት ደረጃ በደረሰበት ወቅት በምታገኙት ስንጥቅ ሁሉ እየተጠቀማችሁ ለህዝባችሁ የብርሃን ጭላንጭል ስለምትፈነጥቁ አኢጋን ሥራችሁን ያደንቃል፤ ያከብራል፡፡ እኛ በሥራችሁ ስኬት የምንመኘው ለቆማችሁለት የፖለቲካ ዓላማ ብቻ ሳይሆን ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት አቅቷቸው መፈናፈኛ ላጡትም የመወሰን ኃይል እንደምትሰጧቸው በማመን ነው፡፡
አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ የበርካታዎች ጥያቄ “ህወሃት/ኢህአዴግን በምን ዓይነት የተሻለ አስተዳደር እንዴት መለወጥ ይቻላል የሚለው ነው?” ይህ ጥያቄ “እኛ ኢትዮጵያውያን የዘርና የጎሣ ትንንሽ አጥሮቻንን አፍርሰን ሁሉን አቀፍ ትግል ለማድረግ ተዘጋጅተናል ወይ?” ብለን ራሳችንን መልሰን አንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ እንዲሁም ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ በመስጠት ሁሉም ነጻ ሳይወጣ ራሳችንን ነጻ ለማውጣት እንችላለን ወይ? ብለንም እንድንጠይቅ የሚያስገድደን ነው፡፡
ህወሃት/ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ አልፎ ለቀጣናው እንዲሁም ለመላው አፍሪካ “የሚተርፍ” እኩይ የዘርና የጎሣ ፖለቲካ በማስፋፋት አገራችንን እንደዚህ ባለ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በጣለበት በአሁኑ ወቅት የብዙዎች ጭንቀት አገራችን ወደ ምን ዓይነት አዘቀት ውስጥ እየገባች ይሆን የሚለው ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ነገር ግን ይህንን ፍርሃት ወደ ተስፋ የሚቀይር አማራጭ እስካሁን ተግባራዊ መሆን ባለመቻሉ አማራጭ የጠፋ ይመስል ህወሃት/ኢህአዴግም “እኔ ከሌለሁ …” እያለ ያስፈራራል፤ ተቃዋሚዎችም በእርስበርስ ሽኩቻ የህዝብ አመኔታ በማጣት ወደ አለመታመን ከመሄዳቸው የተነሳ መልሶ ተዓማኒነትን ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ገና ብዙ የሚቀር አለ፡፡ ይህም ሆኖ ግን ለኢትዮጵያ ሕጋዊ አማራጭ በመሆን ለሕዝባችን መፍትሔ የምታመጡበት ወሳኝ ጊዜ አሁን መሆኑን የጋራ ንቅናቄያችን ያምናል፡፡
እንደምታውቁት የዛሬ ዓመት ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ ነው፡፡ ምርጫውንና አመራረጡን ከሥሩ ጀምሮ የተቆጣጠረው ህወሃት/ኢህአዴግ ሆኖ ሳለ በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ይካሄዳል ብለን አናምንም፡፡ ሆኖም ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩል የሚፈለገው ተግባር ከተከናወነ በአገራችን እውነተኛ ለውጥ ይመጣል ብለን እናምናለን፡፡ ዓመኔታ የሚጣልበት አማራጭ ከተገኘ ዓለምአቀፉ ኅብረተሰብ ህወሃት/ኢህአዴግን አንቅሮ ለመትፋት ከምንጊዜውም ይልቅ ዝግጁ ነው፡፡ ይህንንም የምንለው ከምንም ተነስተን ሳይሆን ድርጅታችን በአውሮጳ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በሌሎች የዓለም ክፍሎች ባለው የግንኙነት መስመር ከሚያገኘው ተጨባጭና ተዓማኒ መረጃ በመነሳት ነው፡፡ በምዕራቡ ዓለም ዘንድ ህወሃት/ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያራምደው የዘር ፖለቲካ፣ የሚከተለው እጅግ ጭቋኝ ፖሊሲ፣ በየጊዜው በሚያወጣቸው አረመኔያዊ ህግጋት፣ ወዘተ ኢትዮጵያን ለከፍተኛ አደጋ የጣለና ለአህጉሩ መጥፎ ምሳሌ እየሆነ በመምጣቱ በኢትዮጵያ የሥርዓት ለውጥ የመከሰቱ ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ አሳማኝ የሆነበት ጊዜ ላይ ይገኛሉ፡፡ አሁንም ጥያቄው “ህወሃት/ኢህአዴግን ማን ይተካዋል?” የሚለው ነው፡፡ ይህንን የመመለሱ ኃላፊነት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ የወደቀ ቢሆንም በተለይ አገር ውስጥ ያላችሁት የፖለቲካ ፓርቲዎች በቅድሚያ ልትመልሱት የሚገባ ጥያቄ ነው፡፡ አመኔታ የሚጣልበት አማራጭ ሆናችሁ የመቅረባችሁ ሁኔታ ስለምርጫው ነጻና ፍትሃዊነት ከመጠየቅ ባልተናነሰ መልኩ ተጠይቆ መልስ ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡
አገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለእናንተ ማስረዳት የሚያስፈልግ አይመስለንም፡፡ በየቀኑ የሚፈጸመውን በደልና ግፍ መከታተል ብቻ ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆነ በበቂ ሁኔታ የሚያመላክት ነው፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ እንደ ተቀጣጣይ (ክላስተር) ቦምብ በየቦታው የበተነው የጎሣ ፖለቲካ ፈንጂ ከፋፍሎ በመግዛት ለራሱ የሥልጣን ማቆያ ቢጠቀምበትም በአሁኑ ጊዜ አገራችንን ከላይና ከታች እያነደዳት ይገኛል፡፡ ከዚህ አኳያ በአገራችን ላይ ሊፈነዳ የሚችለው ነገር ሁሉንም የሚያሳስብ እንደሆነ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ ራሱ በፈጠረው ችግርና በበተነው መርዝ ራሱን በራሱ ሊያጠፋው እንደሚችል ከድርጅቱ ውስጥ የሚታዩት የሥልጣን ሽኩቻዎች ሁሉም “ሳይቀድሙኝ ልቅደም” በሚል አስተሳሰብ እንደተወጠረ የሚያመለክት ነው፡፡ አገራችን ነጻነቷን ከመጎናጸፏ በፊት ይህንን ዓይነቱ የህወሃት/ኢህአዴግ እርስበርስ መበላላት የሚያሳስባቸው ኢትዮጵያውያን እጅግ በርካቶች ናቸው፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ እናንተ ባላችሁ ኃላፊነት ይህንን በውል የምታጤኑት እንደሆነ የጋራ ንቅናቄያችን ያምናል፡፡
ህወሃት/ኢህአዴግ ከውስጥ በሚነሳበት ግፊትና የመበላላት ስጋት፤ ከውጪ በሚመጣበት ተጽዕኖ ወይም በሁለቱ ጥምረት ከሥልጣን መወገዱ የማይቀር ነው፡፡ ይህንን የሚቀበል ካልሆነም ሥርነቀል ተሃድሶ ማድረጉ እየጎመዘዘው የሚጠጣው ሐቅ ነው፡፡ በየትኛውም መልኩ የሚከሰተው ለውጥ አገራችንን መልሶ መልኩን ለቀየረ በዘር ላይ ለተመሠረተ አገዛዝ አሳልፎ የሚሰጣት መሆን የለበትም፡፡ ይልቁንም የሚመጣው ለውጥ ሕዝባችንን እውነተኛ ነጻነት የሚያጎናጽፍ፣ ፍትሕ የሚሰጥና ወደ ዕርቅ የሚመራ መሆን ይገባዋል፡፡ አገራችን በዚህ ጎዳና ላይ እንድትጓዝ የማድረጉ ኃላፊነት የእናንተ እንደሆነ የጋራ ንቅናቄያችን ያሳስባል፡፡
ይህ ደግሞ ሥልጣን ከመጨበጥ ባለፈ ምኞት ላይ የተመሠረተና እያንዳንዱ ነጠላ ፓርቲ ከሌሎች ጋር በኅብረት በመሥራት ተግባራዊ ሊያደርግ የሚገባው መሠረታዊ ዓላማ ነው፡፡ አገራችን ካለችበት ታላቅ ችግር አኳያ የፓርቲዎች መተባበርና ከተቻለም መዋሃድ ወደ መፍትሔ በሚወስደው መንገድ ላይ የመጀመሪያው ስኬት ነው፡፡ ይህ ግን በቀላሉ አይገኝም፤ ሆደ ሰፊ መሆንን፣ ከራስ ይልቅ ለአገርና ለሕዝብ እንዲሁም ለመጪው ትውልድ ማሰብን፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ ከፍተኛ የመንፈስ ልዕልናን የሚጠይቅ ነው፡፡ ሥልጣንን፣ የራስን ክብር፣ የበላይነትን፣ “እኔ ከሌላው የተሻልኩ ነኝ” ማለትን፣ ወዘተ እያውጠነጠኑ ለአገር አስባለሁ ማለት በእጅጉ አስቸጋሪ ነው፡፡ “ከጠላት” የላቀ የመንፈስ ልዕልና ከሁሉም ይጠበቃል፡፡
በመጪው ምርጫ ከምንጊዜውም በበለጠ በመጽናት ለለውጥና ለነጻነታችን የምንታገልበት ሊሆን ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የናፈቀውን ነጻነት ሊጎናጸፍ የሚችልበት አማራጭ ሊፈጠር እንደሚችል አኢጋን ያምናል፡፡ ይህ ሊከሰት የሚችለው በአገር ውስጥ ያላችሁት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥቃቅን ልዩነታችሁን አስወግዳችሁ አጀንዳችሁን ሕዝባዊ በማድረግ በኅብረት ለመሥራት ስትወስኑ ነው፡፡ የጋራ ንቅናቄያችን ባደረገው ጥናት አብዛኞቻችሁ ያላችሁ ልዩነት መሠረታዊ እንዳልሆነ ለመረዳት ችሏል፡፡ ይህም የሚያሳየው እርስበርስ ከሚያለያያችሁ ነገሮች ይልቅ ሊያስማሟችሁ የሚችሉት በርካታዎች እንደሆኑ ነው፡፡ በተለይ በአመራር ላይ ያላችሁ በተለያየ ጊዜ ከሌሎች ጋር የተከሰቱ ልዩነቶችና ግጭቶች እንዲሰፉ ምክንያት ከመሆን ይልቅ ለአገርና ሕዝብ በማሰብ ኢትዮጵያን የመታደግ ኃላፊነት ወድቆባችኋል፡፡ አገር ከሌለ ምንም ሊኖር አይችልም፤ እንደ ትልቅ የያዛችሁት ልዩነትና ችግርም ከንቱ ይሆናል፤ አብሮ ይከስማል፡፡
በተደጋጋሚ የሚሰማው ነጠላ ዜማ “በኢትዮጵያዊ ውስጥ ተስፋ የሚጣልበት ተቃዋሚ ፓርቲ የለም” የሚል ነው፡፡ በእርግጥ ለዚህ ጥያቄ ዋንኛ ተጠያቂው ኢህአዴግ ነው፡፡ ምክንያቱም በአስመሳይ ዲሞክራሲና ተግባራዊ ባልሆነ ሕገመንግሥት ሕዝባችንን ከመጠርነፍ አልፎ የፖለቲካ ፓርቲዎችንም በተመሳሳይ ሁኔታ ሸብቧቸዋል፡፡ ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለው ፕሮግራም በኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ እንዳይኖር ያደረገ ለመሆኑ ማንም የሚክደው አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በኢህአዴግ ብቻ እያመካኙ መኖር ተቀባይነት የሌለው አካሄድ ነው፡፡ እያንዳንዱ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ፓርቲ ዓላማው የኢህአዴግን መሰሪነትና አፋኝነት ለመስበክ ሳይሆን ሕዝብን ለነጻነት ማብቃት ነው፡፡ እታገለዋለሁ ከሚለው አካል መላቅ ካልቻለ ለትግል ብቁ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡
ሽንፈት ላይ እያተኮሩና የጠላትን ኃይለኛነት እየሰበኩ ድል አይገኝም፡፡ ልዩነትን እያራመዱ ኅብረትና አንድነት ተግባራዊ መሆን አይችልም፡፡ ለአገራዊ ዕርቅ እንሰራለን እያሉ በፓርቲ መካከል ከዚያም በታች በግለሰብ ደረጃ መተራረቅ ካልተቻለ ብሔራዊ ዕርቅ ከቀን ቅዠት አያልፍም፡፡ እያንዳንዳችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ፣ መኢአድ፣ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ ኦህኮ፣ አረና፣ እና ሌሎች እጅግ በርካታ ፓርቲዎች የተቋቋማችሁትና ዓላማ ያደረጋችሁት ኢህአዴግን እየተቃወማችሁ ለመኖር እንዳልሆነ የፓርቲ ፕሮግራማችሁ ይመሰክራል፡፡ ወይም ዓላማችሁ የራሳችሁን የፓርቲ ምርጫ የማድረግና ፕሬዚዳንት (ሊቀመንበር)፣ ምክትል፣ ሥራ አስፈጻሚ፣ … በመምረጥ አዙሪት ውስጥ ራሳችሁን ላለማሽከርከር እንደሆነ ከማንም በላይ ራሳችሁ ታውቁታላችሁ፡፡ ከዚህ አንጻር በጥንቃቄና በብዙ ጥናት የተቀመጠው የፓርቲያችሁ ፕሮግራምና ዓላማ ለአገራችን አንዳች ለውጥ ሳያመጣ እንደዚሁ እንዳማረበት ቢቀመጥ ለሕዝብ የሚያመጣው ትርፍ ምንድርነው? እናንተንስ ለመቃወም ብቻ የምትሰሩ አያደርጋችሁምን? ለኢህአዴግና ወዳጆቹስ ጣት የሚጠቁሙበትን ዕድል እየሰጣችሁ እስከመቼ ትኖራላችሁ? ስለዚህ የእስካሁኑ በነጠላ የመጓዙ ጉዳይ ካልሰራ በኅብረት የመሥራቱ ጉዳይ የግድ ይሆናል፡፡ ይህ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ አኢጋን ያምናል፡፡
የጋራ ንቅናቄያችን ከበርካታ ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ካለው ግንኙነት አኳያ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ መረጃ ይሰበስባል፡፡ በቅርቡ አንድ ታዋቂ የምዕራቡ ዓለም የፖሊሲ አውጪ ሲናገሩ “ኢትዮጵያውያን የምዕራቡ ዓለም ነጻ ያወጣናል ብለው በጭራሽ ማመን የለባቸውም፡፡ ከውጭ የሚላከውን ዕርዳታና ድጋፍ ብናቆም እንኳን ይህ የሚሆን አይደለም፡፡ የለውጥ አራማጅና መሪ መሆን ያለባቸው ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ናቸው እንጂ ለጋሽ መንግሥታት አይደሉም፡፡ ኢትዮጵያውያን ይህንን ሊረዱ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ከህወሃት/ኢህአዴግ የተሻለ አማራጭ በሚፈጥሩበት ጊዜ እኛ የግድ እንድንደግፋቸው ያደርጉናል” በማለት ለጋራ ንቅናቄያችን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ይህ ንግግር በአገር ውስጥ ለምትገኙት ብቻ ሳይሆን በዳያስፖራ ለምንገኘውም ልንገነዘብ የሚገባው ሐቅ ነው፡፡ ነጻነት ከምዕራቡ ዓለም ብቻ ሳይሆን በዳያስፖራ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያንም ሊመጣ አይችልም፡፡ የነጻነታችንን ጥያቄ ተግባራዊ የሚሆነው እናንተ በአገር ውስጥ የምትገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኅብረት በመሥራት ሕዝባችንን ለለውጥ ስታስተባብሩት ብቻ ነው፡፡ እኛ ይህንን ከራሳችን ትከሻ ላይ ለማውረድና እናንተን በኃላፊነት ለመጠየቅ የምንጭነው ሳይሆን አገር ውስጥና ውጭ መሆናችን በታሪክም ይሁን በሌላ ምክንያት የተከሰተ በመሆኑ በቅንነትና በሐቅ የምንናገረው እውነታ ነው፡፡ እኛም ከአገር ውጭ ነን በማለት እጃችንን አጣጥፈን የምንቀመጥ ሳይሆን በአገር ውስጥ የሚካሄደውን ትግል የመደገፍ፣ የማገዝ፣ የምዕራባውያንን አመለካከት የማስቀየር፣ በአገር ውስጥ የሚካሄደውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የማሳወቅ፣ … ኃላፊነት እንዳለብን በመገንዘብ ነው፡፡ አኢጋን ይህንን ዓይነቱን ተግባር ሲያካሂድ የቆየ አሁንም ከአገር ውስጥ የሚመጣውን ጥያቄ ለመመለስና በሚችለው ሁሉ ለማገዝ ሙሉ ዝግጁ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡
ከዚህ በፊት በተካሄዱት ምርጫዎች እንደታየውና በፓርቲያችሁ ፕሮግራም ላይ እንደሰፈረው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ በምርጫ ተወዳድራችሁ ሥልጣን የመያዝ ዓላማ እንዳላችሁ ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም ግን ማናችሁም ብትሆኑ በነጠላ ፓርቲነት ተወዳድራችሁ ሥልጣን በመያዝ ለውጥ እንደማታመጡ በግልጽ ልንነግራችሁ እንወዳለን፡፡ በምርጫ አሸነፋችሁ ቢባል እንኳን ሥልጣን የሌለው ቢሮ ከመያዝና የህወሃት/ኢህአዴግ አሻንጉሊት ከመሆን እንደማታመልጡ እሙን ነው፡፡ ይልቁንም ይህ ዓይነቱ አካሄድ ህወሃት/ኢህአዴግ በተለይም ለምዕራቡ ዓለም ለሚደሰኩረው የይስሙላ ዴሞክራሲ ማረጋገጫ ሆኖ በማቅረብ የኢህአዴግ ዕድሜ መቀጠያ መድሃኒት ነው የምትሆኑለት፡፡ ስለዚህ ከመጪው ምርጫ አኳያ ትግሉ የተናጠል ሳይሆን ፓርቲዎች በኅብረት በመሆን ኢህአዴግን በእርግጠኝነት ሊተኩ የሚችሉበት አማራጭ ሊሆን ይገባዋል፡፡
በበርካታ አገሮች እንደሚታየው እናንተም በኅብረት በመሆን ኃይላችሁን አስተባብራችሁ ለሕዝባችሁ ስትሉ እርስ በርስ መጠላለፍ፣ መነቋቆር፣ መካሰስ፣ ወዘተ አሁኑኑ ማቆም ይገባችኋል፡፡ በእስራኤል፣ ብሪታኒያ፣ ጀርመን፣ … በተለያዩ ጊዜያት እንደታየው ፓርቲዎች ጥምር መንግሥት በመመሥረት ሕዝባቸውን ታድገዋል፣ አገልግለዋል፡፡ በኢትዮጵያስ ይህ ሊሆን የማይቻልበት ምክንያት ምንድርነው? መልሱን መመለስ የሚገባችሁ እያንዳንዳችሁ የፓርቲ አመራሮች ናችሁ፡፡
ይህ ሳይሆን የሚቀር ከሆነ በቅርቡ የፖለቲካ ታሪካችን እንደታየው በዚህም ዘመን በተመሳሳይ መልኩ ይደገማል፡፡ በዘመነ አጼ ኃይለሥላሴ የተነሳው የህዝብ ብሶት ዳር ሳይደርስ ደርግ ለራሱ አስቀረው፡፡ በደርግ ዘመን መከራውንና ስቃዩን ያየው ሕዝብ ህወሃት/ኢህአዴግ “የሕዝብ ብሶት” የወለደኝ ነው ብሎ ሲመጣ የመከራው ዘመን ማብቂያው የደረሰ መስሎት ተስፋ አደረገ፡፡ “ብሶት” ወለደኝ ያለው ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ታይቶ በማይታወቅ የዘር “ድንበር” ከፋፍሎ የሕዝባችንን ብሶት ለ23ዓመታት በየቀኑ እያበዛው ይገኛል፡፡ አሁንም ጥንቃቄ ወስዳችሁ ሁላችሁም ለሕዝባችን የሚሆን መፍትሔ የማታመጡ ከሆነ የሕዝባችን ብሶት እንዲቀጥል የምታደርጉ ብቻ ሳይሆን በመጪው ትውልድም ከመጠየቅ አታመልጡም፡፡
በቅንጅት ጊዜ ሕዝብ እጅግ ተስፋ አድርጎ ውጤት ሲጠብቅ ቅንጅቶች “መቀናጀት” አቅቷቸው ጫፍ ላይ ደርሶ የነበረው የሕዝባችን ድል ገደል ገባ፤ በራሱ ተቀናጅቶ የነበረው ሕዝብ የህወሃት/ኢህአዴግ የበቀል እርምጃ ሰለባ ሆነ፡፡ የጋራ ንቅናቄያችን ከበርካታ ወገኖች ጋር ባለው ግንኙነት አሁንም ተመሳሳይ ችግር ይፈጠራል እያሉ ስጋታቸውን የሚገልጹልን ቁጥራቸው በርካታ ነው፡፡ በአገራችን ላይ በርካታ ችግሮች የተጋፈጥን ቢሆንም ከፈጣሪ በኩል ግን ሁልጊዜ መፍትሔና የተበላሸውን የማስተካከል ዕድል አለ፡፡ ይህም ዕድል አሁን እንደሆነ አኢጋን ያምናል፡፡ ከዚህ አንጻር ጥቂት ሃሳቦችን ለማካፈል እንወዳለን፤
  1. በምንም መልኩ በኢትዮጵያ አማራጭ ፓርቲ የለም የሚለውን ተስፋ አስቆራጭ ንግግር አትቀበሉ፡፡
  2. ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብራችሁ ልትሰሩ የሚያስችላችሁን ነጥቦች ዘርዝሮ በማውጣት በሚያስማማችሁ ጉዳዮች ላይ የጋራ አስተሳሰብ ልትወስዱ የምትችሉበትን መንገድ አመቻቹ፡፡
  3. በዕቅዳችሁና ከሌሎች ጋር በጥምረት በመሆን ምንም እንኳን አስቸጋሪ ቢሆን በዋንኛነት በአገራችን የፖለቲካ ምህዳር የሚሰፋበትንና ዕርቅ የሚመጣበትን መንገድ ከመቀየስ ተስፋ አትቁረጡ፡፡
  4. የፓርቲ ፕሮግራምና ማኒፌስቶ ከሰማይ የወረደ፣ የማይገሰስ፣ የማይሻርና የማይለወጥ የፈጣሪ ቃል አይደለም፡፡ ስለዚህ ወደ ውኅደት በሚደረገው ጉዞ መሻሻል፣ መለወጥ፣ መስተካከል፣ የሚገባው የፕሮግራም አንቀጽ የፓርቲያችሁን ኅልውና አደጋ ላይ እስካልጣለ ድረስ ተፈጻሚ ለማድረግ ሆደሰፊ ሁኑ፡፡
  5. ከመሪዎች ጀምሮ በፓርቲያችሁ ውስጥ ውህደትን፣ ጥምረትን፣ … ተግባራዊ ለማድረግና በጋራ ለመሥራት ዕንቅፋት የሚሆኑ ግለሰቦችን በግልጽ መውቀስና እንዲታረሙ ወዲያውኑ ማድረግ ወሳኝነት ያለው ተግባር ነው፡፡ “እገሌን እንዴት እወቅሰዋለሁ” ወይም “አቶ እገሌ የፓርቲያችን የጀርባ አጥንት ነው እንዴት ተሳስተሃል እላልሁ” በሚሉ የይሉኝታ አስተሳሰቦች ለአንድ ሰው ሲባል አገርና ሕዝብ መከራና ስቃይ እንዲቀጥል መደረግ የለበትም፡፡ አገር ለመምራት ፓርቲ መሥርታችሁ ሕዝብን በይሉኝታ መንግሥት ማስተዳደር ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ለይሉኝታ በራችሁን ዝግ ይሁን፡፡
  6. ሁልጊዜ ለመምራት ሳይሆን ለመመራት ተዘጋጁ፡፡ የሰላማዊ ትግል መሪ መመሪያ ይኸው ነው፡፡ ለመመራት የተዘጋጀ መሪ ለመሆን ምንም አይቸግረውም፡፡ ከሥልጣንህም ተነሳ ሲባል ፓርቲውን አይገነጥልም ወይም “እኔ ከሞትኩ …” በሚል ጭፍን አስተሳሰብ በሕዝብ ላይ የውድመት ተግባር አይፈጽምም፡፡ ይህ ምንም የምንደባበቅበት ነገር አይደለም በተግባር ሲፈጸም የኖረ ነው፤ መስተካከልና መሻሻል የሚያስፈልገው ነው፡፡ ከመገልገል ይልቅ ለማገልገል ትሁት ሁኑ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው ትክክለኛ አስተዳደር ነው እንጂ ህወሃት/ኢህአዴግን በሌላ መተካት አይደለም፡፡ ሕዝባችን ይህ ያንሰዋል እንጂ አይበዛበትም፡፡ ስለሆነም “ኢህአዴግ ይነሳ እንጂ” የሚለው ጠባብና ሰንካላ ሃሳብ የእውነተኛ ለውጥ መርህ ስላልሆነ በጭራሽ ለሕዝባችን አትመኙለት፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንግዲህ ወዲህ የሚያስፈልገው “ከጎሣና ዘረኝነት ይልቅ ሰብዓዊነት” የሚያብብባትና “አንዱ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ነጻ የወጣባትን”፤ ፍትህ፣ ሰላምና ዕርቅ የሰፈነባትን አዲሲቷን ኢትዮጵያን ነው፡፡ ከዚህ ያነሰ ለውጥ በለውጥ ደረጃ ሊታሰብም ሆነ ሊታቀድ አይገባውም፡፡
እናንተ አገር ውስጥ ሆናችሁ በየጊዜው በምታደርጉት የመስዋዕትነት ተግባር የጋራ ንቅናቄያችን ከጎናችሁ ይቆማል፡፡ ሥራችሁንም በታላቅ አክብሮት ይከታተላል፡፡ የመስዋዕትነታችሁ ውጤት ፍሬ እንዲያፈራ የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ በውጭ ከበርካታ ወገኖች ጋር ባለን ግንኙነት ለምትፈልጉን ሥራ በምንችለው ሁሉ ለመተባበር ፈቃደኛ መሆናችን እንገልጻለን፡፡ በተለይ በዕርቅ መንገድ ላይ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የሚጠየቀውን ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኝነቱን ይገልጻል፡፡ ይህ ጉዳይ በዚህ ደብዳቤ ላይ ለፕሮቶኮል ብለን የምንናገረው እንዳልሆነ እንድትረዱልን እንፈልጋለን፡፡
አገራችን በበርካታ ድሎች ያንጸባረቀ ታሪክ ያላት ነች፡፡ ከሁሉ በበላይ የሚጠቀሰው የዓድዋ ድል በድጋሚ የሚፈጸምበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው፡፡ የዓድዋን የጦር ድል በፖለቲካው መድረክ እንድገመው፡፡ መጪውን ምርጫ ፖለቲካዊ የዓድዋ ድል የምንጎናጸፍበት እናድርገው፡፡ ነጻነታችን እንደ ዕርዳታ እህል ከምዕራባውያን የሚለገሰን አይደለም፡፡ ስለዚህ እኛው ራሳችን እንደ አድዋ ድል አንድ ሕዝብ ሆነን በመውጣት የራሳችን የምናደርገበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ቅንነት ካለ የጦር ሜዳውን አድዋ በፖለቲካው ሜዳ ላይ መድገም ይቻላል፡፡ አንድ ሊያደርጉንና ሊያስተባብሩን የሚችሉ “ምኒልኮችን” ለመጠቀም ፈቃደኛና ቅን እንሁን፡፡
እርስበርሳችን እንደ ወንድምና እህት ለመተያየትና ለመግባባት ፈጣሪ ቅን ልብ ይስጠን፡፡ እናንተንም ለፍትሕ፣ ለነጻነት፣ ለሰብዓዊነት፣ ለፍቅርና ዕርቅ ስትታገሉ ማስተዋልንና ጥበብን ይስጣችሁ፡፡
ከአክብሮት ጋር ለአገራችን ፈውስ እንዲመጣ የትግል አጋራችሁ፤
ኦባንግ ሜቶ
ዋና ዳይሬክተር፤
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) Ethiopian People's Congress for United Struggle (Shengo)

የአንድነትና መኢአድ ስምምነት፣ ሊበረታታ የሚገባው መልካም ተግባር!
ሰኔ 2፣ 2006 (June 9, 2014)
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሸንጎ)፣ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ)ና አንድነት ለዴሚክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በትላንትናው ዕለት ለውህደት  የሚያበቃ የመጀመሪያ ስምምነት በመፈራረማቸው የተሰማውን ታላቅ ደስታና አድናቆት ይገልጣል።  
ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባት፣ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባትና የሰብዓዊ መብቶች ሳይሸራረፉ እውን የሚሆንባት፣ በዜጎች እኩልነት ላይ የጸና መሰረት ያላት ዴሞክራሲያዊት ሀገር በጋራ ለመገንባት እንድንችል የስርዓት ለውጥን የሚሹ የተቃዋሚ ድርጅቶች  ሁሉ ጥቃቅን ልዩነቶችን ትተው በመተባበርና አንድ ላይ በመምጣት ህዝባዊ ኃይሉ በአንድነት በመቆም አምባገነናዊነትን በጽናት እንዲታገል ማብቃት ይጠበቅባቸዋል። 
ከዚህም አንጻር፣ ውስብስብ ችግሮችን አልፈውና የብቸኛነት ድንበርን ሰብረው በአንድነትና በጋራ ዓላማ መሰለፍን መምረጥ ትልቅ አስተዋይነትና ለወደፊት ጉዞም አስተማማኝ መሰረትን የሚጥል  በመሆኑ በሁለቱ ድርጅቶች በኩል የደረሱበት ቅድመ ውህደት ስምምነት ትልቅ ተስፋ ሰጭና  በሁሉም የአንድነትና የዴሞርራሲ ኃይላት ሊበረታታ የሚገባ ነው።  ሌሎቹም በተናጠል እየታገሉ የሚገኙ በኢትዮጵያዊነታቸውና በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ ኃይሎች ይህን የመኢአድንና የአንድነትን ፈለግ እንደምሳሌ ወስደው የመተባበርንና የአንድ የመሆንን ጎዳና እንዲመርጡና   አስፈላጊውን እርምጃም ሳይዘገዩ እንዲወስዱ  በአንክሮ ለማሳሰብ እንወዳለን። 
እንደዚህ ያሉ ሂደቶች እንዳይሳኩ በጸረ አንድነት ሃይሎች መሰናክሎች መዘርጋታቸው አይቀሬ ነው። ህወሓት/ኢሕአዴግ   ለሚሸርበው ተንኮልና ለሚያደርሰው ጉዳት ፣ ሳይበገሩ  ያሰቡትን ዓላማ ከግብ ማድረስ ግን  የጀግንነት ሙያ ነው።
የአንድነትና የመኢአድ አባላትና መሪዎች ለገጠማቸው ችግርና የገዥው ቡድን ተጽዕኖ ሳይንበረከኩ ወዳቀዱት የውህደት መጀመሪያ ደረጃ ላይ መድረሳቸው ሊያኮራቸው የሚገባና የሚመሰገኑበት ሲሆን ወደ ዘላቂ ግብ ለመድረስም በሚያደርጉት ጉዞ የበለጠ  መሰናክልና ዕይን ያወጣ አፍራሽ ፈተና ሊገጥማቸው እንደሚችል አውቀው እስካሁን እንዳደረጉት ሁሉ  በድፍረትና በብልሀት የጀመሩትን ጉዞ በስኬት እንደሚያጠናቅቁ ታላቅ ተስፋችን ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) ቀደም ሲልም ሆነ አሁንና ወደፊት በተናጠል የቆመው የአንድነትና የዴሞክራሲ ጎራ ተባብሮ በአንድ የጋራ አመራር ስር ተሰልፎ ትግሉን አቀናጅቶ እንዲቀጥል ማድረግ ከተመሰረተባቸውና እውን ለማድረግ  ከፍተኛ ጥረት ከሚያደርግባቸው ዋና ዋና ራዕዮቹ ውስጥ አንዱ ነው። ስለሆነም፣ በመኢአድና በአንድነት መካከል የተጀመረው የውህደት ሂደት ያስደሰተው ሲሆን ከፍጻሜ ደርሶ ለማየት ከፍተኛ ጉጉት አለው። ጅምሩ የተሳካ እንዲሆን ምኞቱን እየገለጸ ለቀጣዩ የትግል ጉዞ አብሮ ለመቆም ያለውን ፍላጎትና አጋርነቱን ከወዲሁ ሊገልጽ ይወዳል።
አንድነታችን  ለድላችን  ዋስትናችን ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ(ሸንጎ)  

“ነጻነትነታችን እንዯ ዕርዲታ እህሌ ከምዕራባውያን የሚሇገሰን አይዯሇም!” ሇአዱሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ሇሚገኙ የፖሇቲካ መሪዎች ያስተሊሇፈው ግሌጽ መሌዕክት

የተወዯዲችሁ በኢትዮጵያ የምትገኙ የፖሇቲካ ፓርቲ መሪዎች፤
በቅዴሚያ ሇአዱሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የአክብሮት ሰሊምታ በማቅረብ በትግለ መስክ የምትከፍለትን መስዋዕትነት የሚያዯንቅ መሆኑን ይገሌጻሌ፡፡ በተሇይ በአሁኑ ጊዜ የፖሇቲካ ምህዲሩ እጅግ ጠብቦ የሇም የሚባሌበት ዯረጃ በዯረሰበት ወቅት በምታገኙት ስንጥቅ ሁለ እየተጠቀማችሁ ሇህዝባችሁ የብርሃን ጭሊንጭሌ ስሇምትፈነጥቁ አኢጋን ሥራችሁን ያዯንቃሌ፤ ያከብራሌ፡፡ እኛ በሥራችሁ ስኬት የምንመኘው ሇቆማችሁሇት የፖሇቲካ ዓሊማ ብቻ ሳይሆን ከህወሃት/ኢህአዳግ አገዛዝ ራሳቸውን ነጻ ሇማውጣት አቅቷቸው መፈናፈኛ ሊጡትም የመወሰን ኃይሌ እንዯምትሰጧቸው በማመን ነው፡፡
አገራችን ካሇችበት ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ የበርካታዎች ጥያቄ “ህወሃት/ኢህአዳግን በምን ዓይነት የተሻሇ አስተዲዯር እንዳት መሇወጥ ይቻሊሌ የሚሇው ነው?” ይህ ጥያቄ “እኛ ኢትዮጵያውያን የዘርና የጎሣ ትንንሽ አጥሮቻንን አፍርሰን ሁለን አቀፍ ትግሌ ሇማዴረግ ተዘጋጅተናሌ ወይ?” ብሇን ራሳችንን መሌሰን አንዴንጠይቅ የሚያዯርገን ነው፡፡ እንዱሁም ከጎሣ ይሌቅ ሇሰብዓዊነት ቅዴሚያ በመስጠት ሁለም ነጻ ሳይወጣ ራሳችንን ነጻ ሇማውጣት እንችሊሇን ወይ? ብሇንም እንዴንጠይቅ የሚያስገዴዯን ነው፡፡ 
ህወሃት/ኢህአዳግ ከኢትዮጵያ አሌፎ ሇቀጣናው እንዱሁም ሇመሊው አፍሪካ “የሚተርፍ” እኩይ የዘርና የጎሣ ፖሇቲካ በማስፋፋት አገራችንን እንዯዚህ ባሇ አሳሳቢ ዯረጃ ሊይ በጣሇበት በአሁኑ ወቅት የብዙዎች ጭንቀት አገራችን ወዯ ምን ዓይነት አዘቀት ውስጥ እየገባች ይሆን የሚሇው ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋሌ፡፡ ነገር ግን ይህንን ፍርሃት ወዯ ተስፋ የሚቀይር አማራጭ እስካሁን ተግባራዊ መሆን ባሇመቻለ አማራጭ የጠፋ ይመስሌ ህወሃት/ኢህአዳግም “እኔ ከላሇሁ …” እያሇ ያስፈራራሌ፤ ተቃዋሚዎችም በእርስበርስ ሽኩቻ የህዝብ አመኔታ በማጣት ወዯ አሇመታመን ከመሄዲቸው የተነሳ መሌሶ ተዓማኒነትን ሇማግኘት ጥረት እያዯረጉ ቢሆንም ገና ብዙ የሚቀር አሇ፡፡ ይህም ሆኖ ግን ሇኢትዮጵያ ሕጋዊ አማራጭ በመሆን ሇሕዝባችን መፍትሔ የምታመጡበት ወሳኝ ጊዜ አሁን መሆኑን የጋራ ንቅናቄያችን ያምናሌ፡፡ 
እንዯምታውቁት የዛሬ ዓመት ምርጫ የሚካሄዴበት ጊዜ ነው፡፡ ምርጫውንና አመራረጡን ከሥሩ ጀምሮ የተቆጣጠረው ህወሃት/ኢህአዳግ ሆኖ ሳሇ በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ይካሄዲሌ ብሇን አናምንም፡፡ ሆኖም ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩሌ የሚፈሇገው ተግባር ከተከናወነ በአገራችን እውነተኛ ሇውጥ ይመጣሌ ብሇን እናምናሇን፡፡ ዓመኔታ የሚጣሌበት አማራጭ ከተገኘ ዓሇምአቀፉ ኅብረተሰብ ህወሃት/ኢህአዳግን አንቅሮ ሇመትፋት ከምንጊዜውም ይሌቅ ዝግጁ ነው፡፡ ይህንንም የምንሇው ከምንም ተነስተን ሳይሆን ዴርጅታችን በአውሮጳ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በላልች የዓሇም ክፍልች ባሇው የግንኙነት መስመር ከሚያገኘው ተጨባጭና ተዓማኒ መረጃ በመነሳት ነው፡፡ በምዕራቡ ዓሇም ዘንዴ ህወሃት/ኢህአዳግ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያራምዯው የዘር ፖሇቲካ፣ የሚከተሇው እጅግ ጭቋኝ ፖሉሲ፣ በየጊዜው በሚያወጣቸው አረመኔያዊ ህግጋት፣ ወዘተ ኢትዮጵያን ሇከፍተኛ አዯጋ የጣሇና ሇአህጉሩ መጥፎ ምሳላ እየሆነ በመምጣቱ በኢትዮጵያ የሥርዓት ሇውጥ የመከሰቱ ጉዲይ ከምንጊዜውም በሊይ አሳማኝ የሆነበት ጊዜ ሊይ ይገኛለ፡፡ አሁንም ጥያቄው “ህወሃት/ኢህአዳግን ማን ይተካዋሌ?” የሚሇው ነው፡፡ ይህንን የመመሇሱ ኃሊፊነት በሁለም ኢትዮጵያውያን ሊይ የወዯቀ ቢሆንም በተሇይ አገር ውስጥ ያሊችሁት የፖሇቲካ ፓርቲዎች በቅዴሚያ
ሌትመሌሱት የሚገባ ጥያቄ ነው፡፡ አመኔታ የሚጣሌበት አማራጭ ሆናችሁ የመቅረባችሁ ሁኔታ ስሇምርጫው ነጻና ፍትሃዊነት ከመጠየቅ ባሌተናነሰ መሌኩ ተጠይቆ መሌስ ሉሰጠው የሚገባ ነው፡፡
አገራችን ያሇችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ሇእናንተ ማስረዲት የሚያስፈሌግ አይመስሇንም፡፡ በየቀኑ የሚፈጸመውን በዯሌና ግፍ መከታተሌ ብቻ ኢትዮጵያ ወዳት እየሄዯች እንዯሆነ በበቂ ሁኔታ የሚያመሊክት ነው፡፡ ህወሃት/ኢህአዳግ እንዯ ተቀጣጣይ (ክሊስተር) ቦምብ በየቦታው የበተነው የጎሣ ፖሇቲካ ፈንጂ ከፋፍል በመግዛት ሇራሱ የሥሌጣን ማቆያ ቢጠቀምበትም በአሁኑ ጊዜ አገራችንን ከሊይና ከታች እያነዯዲት ይገኛሌ፡፡ ከዚህ አኳያ በአገራችን ሊይ ሉፈነዲ የሚችሇው ነገር ሁለንም የሚያሳስብ እንዯሆነ በእርግጠኝነት መናገር ይቻሊሌ፡፡ ህወሃት/ኢህአዳግ ራሱ በፈጠረው ችግርና በበተነው መርዝ ራሱን በራሱ ሉያጠፋው እንዯሚችሌ ከዴርጅቱ ውስጥ የሚታዩት የሥሌጣን ሽኩቻዎች ሁለም “ሳይቀዴሙኝ ሌቅዯም” በሚሌ አስተሳሰብ እንዯተወጠረ የሚያመሇክት ነው፡፡ አገራችን ነጻነቷን ከመጎናጸፏ በፊት ይህንን ዓይነቱ የህወሃት/ኢህአዳግ እርስበርስ መበሊሊት የሚያሳስባቸው ኢትዮጵያውያን እጅግ በርካቶች ናቸው፡፡ ከሁለ በሊይ ዯግሞ እናንተ ባሊችሁ ኃሊፊነት ይህንን በውሌ የምታጤኑት እንዯሆነ የጋራ ንቅናቄያችን ያምናሌ፡፡ 
ህወሃት/ኢህአዳግ ከውስጥ በሚነሳበት ግፊትና የመበሊሊት ስጋት፤ ከውጪ በሚመጣበት ተጽዕኖ ወይም በሁሇቱ ጥምረት ከሥሌጣን መወገደ የማይቀር ነው፡፡ ይህንን የሚቀበሌ ካሌሆነም ሥርነቀሌ ተሃዴሶ ማዴረጉ እየጎመዘዘው የሚጠጣው ሏቅ ነው፡፡ በየትኛውም መሌኩ የሚከሰተው ሇውጥ አገራችንን መሌሶ መሌኩን ሇቀየረ በዘር ሊይ ሇተመሠረተ አገዛዝ አሳሌፎ የሚሰጣት መሆን የሇበትም፡፡ ይሌቁንም የሚመጣው ሇውጥ ሕዝባችንን እውነተኛ ነጻነት የሚያጎናጽፍ፣ ፍትሕ የሚሰጥና ወዯ ዕርቅ የሚመራ መሆን ይገባዋሌ፡፡ አገራችን በዚህ ጎዲና ሊይ እንዴትጓዝ የማዴረጉ ኃሊፊነት የእናንተ እንዯሆነ የጋራ ንቅናቄያችን ያሳስባሌ፡፡ 
ይህ ዯግሞ ሥሌጣን ከመጨበጥ ባሇፈ ምኞት ሊይ የተመሠረተና እያንዲንደ ነጠሊ ፓርቲ ከላልች ጋር በኅብረት በመሥራት ተግባራዊ ሉያዯርግ የሚገባው መሠረታዊ ዓሊማ ነው፡፡ አገራችን ካሇችበት ታሊቅ ችግር አኳያ የፓርቲዎች መተባበርና ከተቻሇም መዋሃዴ ወዯ መፍትሔ በሚወስዯው መንገዴ ሊይ የመጀመሪያው ስኬት ነው፡፡ ይህ ግን በቀሊለ አይገኝም፤ ሆዯ ሰፊ መሆንን፣ ከራስ ይሌቅ ሇአገርና ሇሕዝብ እንዱሁም ሇመጪው ትውሌዴ ማሰብን፣ ከሁለ በሊይ ዯግሞ ከፍተኛ የመንፈስ ሌዕሌናን የሚጠይቅ ነው፡፡ ሥሌጣንን፣ የራስን ክብር፣ የበሊይነትን፣ “እኔ ከላሊው የተሻሌኩ ነኝ” ማሇትን፣ ወዘተ እያውጠነጠኑ ሇአገር አስባሇሁ ማሇት በእጅጉ አስቸጋሪ ነው፡፡ “ከጠሊት” የሊቀ የመንፈስ ሌዕሌና ከሁለም ይጠበቃሌ፡፡ 
በመጪው ምርጫ ከምንጊዜውም በበሇጠ በመጽናት ሇሇውጥና ሇነጻነታችን የምንታገሌበት ሉሆን ይገባሌ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የናፈቀውን ነጻነት ሉጎናጸፍ የሚችሌበት አማራጭ ሉፈጠር እንዯሚችሌ አኢጋን ያምናሌ፡፡ ይህ ሉከሰት የሚችሇው በአገር ውስጥ ያሊችሁት የፖሇቲካ ፓርቲዎች ጥቃቅን ሌዩነታችሁን አስወግዲችሁ አጀንዲችሁን ሕዝባዊ በማዴረግ በኅብረት ሇመሥራት ስትወስኑ ነው፡፡ የጋራ ንቅናቄያችን ባዯረገው ጥናት አብዛኞቻችሁ ያሊችሁ ሌዩነት መሠረታዊ እንዲሌሆነ ሇመረዲት ችሎሌ፡፡ ይህም የሚያሳየው እርስበርስ ከሚያሇያያችሁ ነገሮች ይሌቅ ሉያስማሟችሁ የሚችለት በርካታዎች እንዯሆኑ ነው፡፡ በተሇይ በአመራር ሊይ ያሊችሁ በተሇያየ ጊዜ ከላልች ጋር የተከሰቱ ሌዩነቶችና ግጭቶች እንዱሰፉ ምክንያት ከመሆን ይሌቅ ሇአገርና ሕዝብ በማሰብ ኢትዮጵያን የመታዯግ ኃሊፊነት ወዴቆባችኋሌ፡፡ አገር ከላሇ ምንም ሉኖር አይችሌም፤ እንዯ ትሌቅ የያዛችሁት ሌዩነትና ችግርም ከንቱ ይሆናሌ፤ አብሮ ይከስማሌ፡፡
በተዯጋጋሚ የሚሰማው ነጠሊ ዜማ “በኢትዮጵያዊ ውስጥ ተስፋ የሚጣሌበት ተቃዋሚ ፓርቲ የሇም” የሚሌ ነው፡፡ በእርግጥ ሇዚህ ጥያቄ ዋንኛ ተጠያቂው ኢህአዳግ ነው፡፡ ምክንያቱም በአስመሳይ ዱሞክራሲና ተግባራዊ ባሌሆነ ሕገመንግሥት ሕዝባችንን ከመጠርነፍ አሌፎ የፖሇቲካ ፓርቲዎችንም በተመሳሳይ ሁኔታ ሸብቧቸዋሌ፡፡ ህወሃት/ኢህአዳግ የሚከተሇው ፕሮግራም በኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ የፖሇቲካ ፓርቲ
እንዲይኖር ያዯረገ ሇመሆኑ ማንም የሚክዯው አይዯሇም፡፡ ሆኖም ግን በኢህአዳግ ብቻ እያመካኙ መኖር ተቀባይነት የላሇው አካሄዴ ነው፡፡ እያንዲንደ የተቀናቃኝ ፖሇቲካ ፓርቲ ዓሊማው የኢህአዳግን መሰሪነትና አፋኝነት ሇመስበክ ሳይሆን ሕዝብን ሇነጻነት ማብቃት ነው፡፡ እታገሇዋሇሁ ከሚሇው አካሌ መሊቅ ካሌቻሇ ሇትግሌ ብቁ ነው ሇማሇት ያስቸግራሌ፡፡ 
ሽንፈት ሊይ እያተኮሩና የጠሊትን ኃይሇኛነት እየሰበኩ ዴሌ አይገኝም፡፡ ሌዩነትን እያራመደ ኅብረትና አንዴነት ተግባራዊ መሆን አይችሌም፡፡ ሇአገራዊ ዕርቅ እንሰራሇን እያለ በፓርቲ መካከሌ ከዚያም በታች በግሇሰብ ዯረጃ መተራረቅ ካሌተቻሇ ብሔራዊ ዕርቅ ከቀን ቅዠት አያሌፍም፡፡ እያንዲንዲችሁ የፖሇቲካ ፓርቲዎች መዴረክ፣ መኢአዴ፣ አንዴነት፣ ሰማያዊ፣ ኦህኮ፣ አረና፣ እና ላልች እጅግ በርካታ ፓርቲዎች የተቋቋማችሁትና ዓሊማ ያዯረጋችሁት ኢህአዳግን እየተቃወማችሁ ሇመኖር እንዲሌሆነ የፓርቲ ፕሮግራማችሁ ይመሰክራሌ፡፡ ወይም ዓሊማችሁ የራሳችሁን የፓርቲ ምርጫ የማዴረግና ፕሬዚዲንት (ሉቀመንበር)፣ ምክትሌ፣ ሥራ አስፈጻሚ፣ … በመምረጥ አዙሪት ውስጥ ራሳችሁን ሊሇማሽከርከር እንዯሆነ ከማንም በሊይ ራሳችሁ ታውቁታሊችሁ፡፡ ከዚህ አንጻር በጥንቃቄና በብዙ ጥናት የተቀመጠው የፓርቲያችሁ ፕሮግራምና ዓሊማ ሇአገራችን አንዲች ሇውጥ ሳያመጣ እንዯዚሁ እንዲማረበት ቢቀመጥ ሇሕዝብ የሚያመጣው ትርፍ ምንዴርነው? እናንተንስ ሇመቃወም ብቻ የምትሰሩ አያዯርጋችሁምን? ሇኢህአዳግና ወዲጆቹስ ጣት የሚጠቁሙበትን ዕዴሌ እየሰጣችሁ እስከመቼ ትኖራሊችሁ? ስሇዚህ የእስካሁኑ በነጠሊ የመጓዙ ጉዲይ ካሌሰራ በኅብረት የመሥራቱ ጉዲይ የግዴ ይሆናሌ፡፡ ይህ ወሳኝ ጉዲይ እንዯሆነ አኢጋን ያምናሌ፡፡
የጋራ ንቅናቄያችን ከበርካታ ዓሇምአቀፋዊ ዴርጅቶችና ታዋቂ ግሇሰቦች ጋር ካሇው ግንኙነት አኳያ በኢትዮጵያ ጉዲይ ሊይ መረጃ ይሰበስባሌ፡፡ በቅርቡ አንዴ ታዋቂ የምዕራቡ ዓሇም የፖሉሲ አውጪ ሲናገሩ “ኢትዮጵያውያን የምዕራቡ ዓሇም ነጻ ያወጣናሌ ብሇው በጭራሽ ማመን የሇባቸውም፡፡ ከውጭ የሚሊከውን ዕርዲታና ዴጋፍ ብናቆም እንኳን ይህ የሚሆን አይዯሇም፡፡ የሇውጥ አራማጅና መሪ መሆን ያሇባቸው ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ናቸው እንጂ ሇጋሽ መንግሥታት አይዯለም፡፡ ኢትዮጵያውያን ይህንን ሉረደ ይገባሌ፡፡ ኢትዮጵያውያን ራሳቸው ከህወሃት/ኢህአዳግ የተሻሇ አማራጭ በሚፈጥሩበት ጊዜ እኛ የግዴ እንዴንዯግፋቸው ያዯርጉናሌ” በማሇት ሇጋራ ንቅናቄያችን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋሌ፡፡  
ይህ ንግግር በአገር ውስጥ ሇምትገኙት ብቻ ሳይሆን በዲያስፖራ ሇምንገኘውም ሌንገነዘብ የሚገባው ሏቅ ነው፡፡ ነጻነት ከምዕራቡ ዓሇም ብቻ ሳይሆን በዲያስፖራ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያንም ሉመጣ አይችሌም፡፡ የነጻነታችንን ጥያቄ ተግባራዊ የሚሆነው እናንተ በአገር ውስጥ የምትገኙ የፖሇቲካ ፓርቲዎች በኅብረት በመሥራት ሕዝባችንን ሇሇውጥ ስታስተባብሩት ብቻ ነው፡፡ እኛ ይህንን ከራሳችን ትከሻ ሊይ ሇማውረዴና እናንተን በኃሊፊነት ሇመጠየቅ የምንጭነው ሳይሆን አገር ውስጥና ውጭ መሆናችን በታሪክም ይሁን በላሊ ምክንያት የተከሰተ በመሆኑ በቅንነትና በሏቅ የምንናገረው እውነታ ነው፡፡ እኛም ከአገር ውጭ ነን በማሇት እጃችንን አጣጥፈን የምንቀመጥ ሳይሆን በአገር ውስጥ የሚካሄዯውን ትግሌ የመዯገፍ፣ የማገዝ፣ የምዕራባውያንን አመሇካከት የማስቀየር፣ በአገር ውስጥ የሚካሄዯውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የማሳወቅ፣ … ኃሊፊነት እንዲሇብን በመገንዘብ ነው፡፡ አኢጋን ይህንን ዓይነቱን ተግባር ሲያካሂዴ የቆየ አሁንም ከአገር ውስጥ የሚመጣውን ጥያቄ ሇመመሇስና በሚችሇው ሁለ ሇማገዝ ሙለ ዝግጁ መሆኑን ሇመግሇጽ ይወዲሌ፡፡
ከዚህ በፊት በተካሄደት ምርጫዎች እንዯታየውና በፓርቲያችሁ ፕሮግራም ሊይ እንዯሰፈረው እንዯ ፖሇቲካ ፓርቲ በምርጫ ተወዲዴራችሁ ሥሌጣን የመያዝ ዓሊማ እንዲሊችሁ ግሌጽ ነው፡፡ ሆኖም ግን ማናችሁም ብትሆኑ በነጠሊ ፓርቲነት ተወዲዴራችሁ ሥሌጣን በመያዝ ሇውጥ እንዯማታመጡ በግሌጽ ሌንነግራችሁ እንወዲሇን፡፡ በምርጫ አሸነፋችሁ ቢባሌ እንኳን ሥሌጣን የላሇው ቢሮ ከመያዝና የህወሃት/ኢህአዳግ አሻንጉሉት ከመሆን እንዯማታመሌጡ እሙን ነው፡፡ ይሌቁንም ይህ ዓይነቱ አካሄዴ ህወሃት/ኢህአዳግ
በተሇይም ሇምዕራቡ ዓሇም ሇሚዯሰኩረው የይስሙሊ ዳሞክራሲ ማረጋገጫ ሆኖ በማቅረብ የኢህአዳግ ዕዴሜ መቀጠያ መዴሃኒት ነው የምትሆኑሇት፡፡ ስሇዚህ ከመጪው ምርጫ አኳያ ትግለ የተናጠሌ ሳይሆን ፓርቲዎች በኅብረት በመሆን ኢህአዳግን በእርግጠኝነት ሉተኩ የሚችለበት አማራጭ ሉሆን ይገባዋሌ፡፡
በበርካታ አገሮች እንዯሚታየው እናንተም በኅብረት በመሆን ኃይሊችሁን አስተባብራችሁ ሇሕዝባችሁ ስትለ እርስ በርስ መጠሊሇፍ፣ መነቋቆር፣ መካሰስ፣ ወዘተ አሁኑኑ ማቆም ይገባችኋሌ፡፡ በእስራኤሌ፣ ብሪታኒያ፣ ጀርመን፣ … በተሇያዩ ጊዜያት እንዯታየው ፓርቲዎች ጥምር መንግሥት በመመሥረት ሕዝባቸውን ታዴገዋሌ፣ አገሌግሇዋሌ፡፡ በኢትዮጵያስ ይህ ሉሆን የማይቻሌበት ምክንያት ምንዴርነው? መሌሱን መመሇስ የሚገባችሁ እያንዲንዲችሁ የፓርቲ አመራሮች ናችሁ፡፡ 
ይህ ሳይሆን የሚቀር ከሆነ በቅርቡ የፖሇቲካ ታሪካችን እንዯታየው በዚህም ዘመን በተመሳሳይ መሌኩ ይዯገማሌ፡፡ በዘመነ አጼ ኃይሇሥሊሴ የተነሳው የህዝብ ብሶት ዲር ሳይዯርስ ዯርግ ሇራሱ አስቀረው፡፡ በዯርግ ዘመን መከራውንና ስቃዩን ያየው ሕዝብ ህወሃት/ኢህአዳግ “የሕዝብ ብሶት” የወሇዯኝ ነው ብል ሲመጣ የመከራው ዘመን ማብቂያው የዯረሰ መስልት ተስፋ አዯረገ፡፡ “ብሶት” ወሇዯኝ ያሇው ኢህአዳግ ኢትዮጵያን ታይቶ በማይታወቅ የዘር “ዴንበር” ከፋፍል የሕዝባችንን ብሶት ሇ23ዓመታት በየቀኑ እያበዛው ይገኛሌ፡፡ አሁንም ጥንቃቄ ወስዲችሁ ሁሊችሁም ሇሕዝባችን የሚሆን መፍትሔ የማታመጡ ከሆነ የሕዝባችን ብሶት እንዱቀጥሌ የምታዯርጉ ብቻ ሳይሆን በመጪው ትውሌዴም ከመጠየቅ አታመሌጡም፡፡
በቅንጅት ጊዜ ሕዝብ እጅግ ተስፋ አዴርጎ ውጤት ሲጠብቅ ቅንጅቶች “መቀናጀት” አቅቷቸው ጫፍ ሊይ ዯርሶ የነበረው የሕዝባችን ዴሌ ገዯሌ ገባ፤ በራሱ ተቀናጅቶ የነበረው ሕዝብ የህወሃት/ኢህአዳግ የበቀሌ እርምጃ ሰሇባ ሆነ፡፡ የጋራ ንቅናቄያችን ከበርካታ ወገኖች ጋር ባሇው ግንኙነት አሁንም ተመሳሳይ ችግር ይፈጠራሌ እያለ ስጋታቸውን የሚገሌጹሌን ቁጥራቸው በርካታ ነው፡፡ በአገራችን ሊይ በርካታ ችግሮች የተጋፈጥን ቢሆንም ከፈጣሪ በኩሌ ግን ሁሌጊዜ መፍትሔና የተበሊሸውን የማስተካከሌ ዕዴሌ አሇ፡፡ ይህም ዕዴሌ አሁን እንዯሆነ አኢጋን ያምናሌ፡፡ ከዚህ አንጻር ጥቂት ሃሳቦችን ሇማካፈሌ እንወዲሇን፤
1. በምንም መሌኩ በኢትዮጵያ አማራጭ ፓርቲ የሇም የሚሇውን ተስፋ አስቆራጭ ንግግር አትቀበለ፡፡ 2. ከላልች ፓርቲዎች ጋር አብራችሁ ሌትሰሩ የሚያስችሊችሁን ነጥቦች ዘርዝሮ በማውጣት በሚያስማማችሁ ጉዲዮች ሊይ የጋራ አስተሳሰብ ሌትወስደ የምትችለበትን መንገዴ አመቻቹ፡፡ 3. በዕቅዲችሁና ከላልች ጋር በጥምረት በመሆን ምንም እንኳን አስቸጋሪ ቢሆን በዋንኛነት በአገራችን የፖሇቲካ ምህዲር የሚሰፋበትንና ዕርቅ የሚመጣበትን መንገዴ ከመቀየስ ተስፋ አትቁረጡ፡፡ 4. የፓርቲ ፕሮግራምና ማኒፌስቶ ከሰማይ የወረዯ፣ የማይገሰስ፣ የማይሻርና የማይሇወጥ የፈጣሪ ቃሌ አይዯሇም፡፡ ስሇዚህ ወዯ ውኅዯት በሚዯረገው ጉዞ መሻሻሌ፣ መሇወጥ፣ መስተካከሌ፣ የሚገባው የፕሮግራም አንቀጽ የፓርቲያችሁን ኅሌውና አዯጋ ሊይ እስካሌጣሇ ዴረስ ተፈጻሚ ሇማዴረግ ሆዯሰፊ ሁኑ፡፡ 5. ከመሪዎች ጀምሮ በፓርቲያችሁ ውስጥ ውህዯትን፣ ጥምረትን፣ … ተግባራዊ ሇማዴረግና በጋራ ሇመሥራት ዕንቅፋት የሚሆኑ ግሇሰቦችን በግሌጽ መውቀስና እንዱታረሙ ወዱያውኑ ማዴረግ ወሳኝነት ያሇው ተግባር ነው፡፡ “እገላን እንዳት እወቅሰዋሇሁ” ወይም “አቶ እገላ የፓርቲያችን የጀርባ አጥንት ነው እንዳት ተሳስተሃሌ እሊሌሁ” በሚለ የይለኝታ አስተሳሰቦች ሇአንዴ ሰው ሲባሌ አገርና ሕዝብ መከራና ስቃይ እንዱቀጥሌ መዯረግ የሇበትም፡፡ አገር ሇመምራት ፓርቲ መሥርታችሁ ሕዝብን በይለኝታ መንግሥት ማስተዲዯር ፈጽሞ አይቻሌም፡፡ ሇይለኝታ በራችሁን ዝግ ይሁን፡፡   
6. ሁሌጊዜ ሇመምራት ሳይሆን ሇመመራት ተዘጋጁ፡፡ የሰሊማዊ ትግሌ መሪ መመሪያ ይኸው ነው፡፡ ሇመመራት የተዘጋጀ መሪ ሇመሆን ምንም አይቸግረውም፡፡ ከሥሌጣንህም ተነሳ ሲባሌ ፓርቲውን አይገነጥሌም ወይም “እኔ ከሞትኩ …” በሚሌ ጭፍን አስተሳሰብ በሕዝብ ሊይ የውዴመት ተግባር አይፈጽምም፡፡ ይህ ምንም የምንዯባበቅበት ነገር አይዯሇም በተግባር ሲፈጸም የኖረ ነው፤ መስተካከሌና መሻሻሌ የሚያስፈሌገው ነው፡፡ ከመገሌገሌ ይሌቅ ሇማገሌገሌ ትሁት ሁኑ፡፡ 
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈሌገው ትክክሇኛ አስተዲዯር ነው እንጂ ህወሃት/ኢህአዳግን በላሊ መተካት አይዯሇም፡፡ ሕዝባችን ይህ ያንሰዋሌ እንጂ አይበዛበትም፡፡ ስሇሆነም “ኢህአዳግ ይነሳ እንጂ” የሚሇው ጠባብና ሰንካሊ ሃሳብ የእውነተኛ ሇውጥ መርህ ስሊሌሆነ በጭራሽ ሇሕዝባችን አትመኙሇት፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንግዱህ ወዱህ የሚያስፈሌገው “ከጎሣና ዘረኝነት ይሌቅ ሰብዓዊነት” የሚያብብባትና “አንደ ብቻ ሳይሆን ሁለም ነጻ የወጣባትን”፤ ፍትህ፣ ሰሊምና ዕርቅ የሰፈነባትን አዱሲቷን ኢትዮጵያን ነው፡፡ ከዚህ ያነሰ ሇውጥ በሇውጥ ዯረጃ ሉታሰብም ሆነ ሉታቀዴ አይገባውም፡፡
እናንተ አገር ውስጥ ሆናችሁ በየጊዜው በምታዯርጉት የመስዋዕትነት ተግባር የጋራ ንቅናቄያችን ከጎናችሁ ይቆማሌ፡፡ ሥራችሁንም በታሊቅ አክብሮት ይከታተሊሌ፡፡ የመስዋዕትነታችሁ ውጤት ፍሬ እንዱያፈራ የሚቻሇውን ሁለ ያዯርጋሌ፡፡ በውጭ ከበርካታ ወገኖች ጋር ባሇን ግንኙነት ሇምትፈሌጉን ሥራ በምንችሇው ሁለ ሇመተባበር ፈቃዯኛ መሆናችን እንገሌጻሇን፡፡ በተሇይ በዕርቅ መንገዴ ሊይ ሇአዱሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የሚጠየቀውን ሁለ ሇማዴረግ ፈቃዯኝነቱን ይገሌጻሌ፡፡ ይህ ጉዲይ በዚህ ዯብዲቤ ሊይ ሇፕሮቶኮሌ ብሇን የምንናገረው እንዲሌሆነ እንዴትረደሌን እንፈሌጋሇን፡፡
አገራችን በበርካታ ዴልች ያንጸባረቀ ታሪክ ያሊት ነች፡፡ ከሁለ በበሊይ የሚጠቀሰው የዓዴዋ ዴሌ በዴጋሚ የሚፈጸምበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው፡፡ የዓዴዋን የጦር ዴሌ በፖሇቲካው መዴረክ እንዴገመው፡፡ መጪውን ምርጫ ፖሇቲካዊ የዓዴዋ ዴሌ የምንጎናጸፍበት እናዴርገው፡፡ ነጻነታችን እንዯ ዕርዲታ እህሌ ከምዕራባውያን የሚሇገሰን አይዯሇም፡፡ ስሇዚህ እኛው ራሳችን እንዯ አዴዋ ዴሌ አንዴ ሕዝብ ሆነን በመውጣት የራሳችን የምናዯርገበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ ቅንነት ካሇ የጦር ሜዲውን አዴዋ በፖሇቲካው ሜዲ ሊይ መዴገም ይቻሊሌ፡፡ አንዴ ሉያዯርጉንና ሉያስተባብሩን የሚችለ “ምኒሌኮችን” ሇመጠቀም ፈቃዯኛና ቅን እንሁን፡፡ 
እርስበርሳችን እንዯ ወንዴምና እህት ሇመተያየትና ሇመግባባት ፈጣሪ ቅን ሌብ ይስጠን፡፡ እናንተንም ሇፍትሕ፣ ሇነጻነት፣ ሇሰብዓዊነት፣ ሇፍቅርና ዕርቅ ስትታገለ ማስተዋሌንና ጥበብን ይስጣችሁ፡፡ 
ከአክብሮት ጋር ሇአገራችን ፈውስ እንዱመጣ የትግሌ አጋራችሁ፤   
ኦባንግ ሜቶ ዋና ዲይሬክተር፤ ሇአዱሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)