Friday, 23 May 2014

የአዳማው የአንድነት ሰልፍ ለሰኔ አንድ ተላለፈ

ኑና አብረን ድምጻችንን እናሰማ!!
የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የመሀል ቀጠና ፅ/ቤት ለግንቦት 10 ጠይቆትየነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ የተለያዩ ሰበቦችና ምክንያቶች ሲድበሰበስ ከርሞ ለሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም መተላለፉን የመሀል ቀጠና ጽ/ቤቱ በጠራው የአስቸኳይ ስብሰባ መወሰኑንናይህንኑ ውሳኔውንም በቀን መወሰኛ ደብዳቤው ላይ ገልጾ ለአዳማ መስተዳድር ከንቲባ አቶ አብረሐም ማስረከቡን በመረጃ አያይዞ ገልጧል፡፡በመሆኑም ሰኔ አንድ የአንድነት ደጋፊዎችና አባላት እንዲሁም የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆናችሁ ነጋዴዎች፣ተማሪዎችና ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በሰልፋችን ላይ በመገኘት በገዢው ፓርቲ ላይ የተባበረ የተቃውሞ ድምጻችንን በሰላማዊ የትግል ስልት መንፈስ እንድናሰማ ጋብዘናችኋል፡፡ ሰኔ አንድ አይቀርም!
መነሻችን 4፡00ሰዓት ፣አዳማ ራስ ሆቴል (የቀድሞው መነን ሆቴል) ሆኖ፣ በፍራንኮ ሆቴል አርገን ወደ ምንጃር ጎዳና እንወጣና፤ ከሳር ተራ በአዲሱ ግንብ ገበያ ወደ መብራት ሐይል አቅንተን፤ ቁልቁል በአንደኛ መንገድ (ግርማሜ ነዋይ ጎዳና) ከደራርቱ አደባባይ ፊት ለፊት ካለው የፖስታ ቤት ሜዳ ላይ ማሳረጊያ እናደርጋለን፡፡ በጳጉሜ ሶስት የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት የሁለተኛ ዙር ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የሚሊየኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል ላይ ተመስርተን በሀገሪቱ ስላለው ኢፍሀዊ የመሬት ስሪት እንጮሀለን! በመልካም አስተዳደር ዕጦት ስለሚደረጉ የሙስና ወንጀሎች የተቃውሞ ድምጽ እናሰማለን!-ኑ ኑና አብረን ድምጻችንን እናሰማ!!10305607_726441860747899_1605322284415562929_n

የአረና አመራሮች በአዳራሽ ውስጥ ታግተዋል – ፍኖተ ነጻነት

አረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በዛሬው ዕለት በሀውዜን ከተማ ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንዳለ ከመቀሌ የመጡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደርሰው እኛ ሰላማዊ ሰልፍ ስለምናደርግ ስብሰባ የሚባል ነገር የለም በማለት ወደ አዳራሹ የሚመጣውን ሰው ድንጋይ በመወርወር ስብሰባው እንዳይካሄድ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ስብሰባውን እንዲታደም ሲቀሰቅሱ የነበሩ አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና ሁለት አባላት ታርጋ በሌላቸው ሞተር ሳይክሎች በመግጨት አደጋ አድርሰውባቸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አዳራሹ ውስጥ ተዘግቶብን ዙሪያውን ተከበናል ፖሊስ መቆጣጠር ስላልቻለ ተጨማሪ ኃይል ጠይቋል ሲሉ የአረና አመራር ለፍኖተ ነፃነት ገልጸዋል፡፡ ከአሁን ቀደም በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የትውልድ ስፍራ ወላይታ ከተማ በተደራጁ ሰዎች ዝርፊያና ታርጋ በሌላቸው ሞተር ሳይክሎች አደጋ ለማድረስ መሞከራቸውን ፍኖተ ነፃነት መዘገቧ የሚታወስ ነው፡፡

ትኩረት በህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ ላይ ይሁን – ግንቦት 7

ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ መንታ መንገድ ላይ ትገኛለች። በአንድ በኩል ህወሓት እና አገልጋይ ድርጅቶቹ በተለይም ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ የተነሳባቸው ሕዝባዊ ተቃዉሞ ለመሸፈን የሕዝብ ለሕዝብ ጠብ ለመጫር የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ነው። በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ዘርን መሠረት ያደረጉ ስድቦች፣ ዘለፋዎችና ጥቃቶች እንዲኖሩ በካድሬዎቻቸውና በቅጥረኞች አማካይነት እየጣሩ ነው። በዚህ እኩይ ተግባር ውስጥ ባለማወቅ በስሜት ብቻ የሚነዱ የወያኔ ደጋፊ ያልሆኑ ወገኖችም እየተሳተፉበት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በዘውግም ይሁን በአገር ደረጃ የተደራጁ የፓለቲካ ድርጅቶች መሪዎች የጋራ ጠላቶቻችን ወያኔና ግብረአበሮቹ ስለመሆናቸው የጠራ አቋም እየያዙ ነው። ወያኔና ግብረአበሮቹን ለማስወገድ በጋራ መታገል የሚያስፈልግ መሆኑ እና ከወያኔ አገዛዝ በኋላ በእኩልነት ላይ የተመሠረተ አገር የመገንባት የጋራ ኃላፊነት ያለብን መሆኑ ሰፊ ግንዛቤ እያገኘ መጥቷል።
ይህ መንታ መንገድ በሁሉም ቦታ በባሰ ኦሮሚያ ውስጥ ጎልቶ እየታየ ነው። በኦሮሚያ አካባቢዎች የሚደርሰው ጥቃትና መፈናቀል ያስቆጫቸው ወጣቶች የሚያደርጉት ፍትሃዊ ተቃውሞ ቀጥሏል። በአምቦ፣ በነቀምት፣ በጊምቢ፣ በሀረር፣ እና ሌሎችም አካባቢዎች በተለይም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሥርዓቱን በመቃወማቸው ከፍተኛ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ታስረዋል። በእነዚህ ቦታዎች ሁሉ የእንተባበር ጥሪዎች ጎልተው እየተሰሙ ነው። በኦሮሚያ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሌሎች አካባቢዎች ተማሪዎች ከጎናቸው እንዲቆሙ የኦሮሞ ተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥሪዎችን አቅርበዋል። የሌሎች አካባቢዎች ተማሪዎችም ከኦሮሞ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ጎን ቆመዋል። ይህ ተስፋ የሚሰጥ እና መበረታታት ያለበት ነገር ነው። ሆኖም ግን ከዚሁ ጎን ለጎን ህወሓትና ኦህዴድ የሕዝቡን ጥያቄ ወደ ዘር ግጭት ለማዞር እየሠሩ ነው። በተማሪዎች መፈክሮች ውስጥ ዘርን ለይተው የሚያንቋንሽሹ መልዕክቶች ሰርገው እንዲገቡ እየተደረገ ነው። ኦሮሞ ባልሆኑ በተለይም በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው። የወያኔ ጆሮ ጠቢዎችና ካድሬዎች በስሜት የተገፋፉ ወጣቶችን ወደ ዘር ግጭት እየመሯቸው ነው።ይህ እጅግ አሳሳቢና በአስቸኳይ መቆም የሚኖርበት ነገር ነው።
ከመንታ መንገዶቹ ለአገርና ለወገን እንዲሁም ለወደፊቱ ትውልድ ደህንነት የሚበጀውን የመረዳዳት፣ የመደጋገፍ እና የመተባበርን መንገድ መርጠን እርምጃችንን ካላፋጠንን አሁን የደረስንበት ደረጃ እጅግ አስጊ ነው። ማሰብ፣ ማስተዋል እና ጠላትን መለየት በሚያፈልግበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነው የምንገኘው። ድሃ አማራ ለድሃ ኦሮሞ ወገኑ ብቻ ሳይሆን የትግል አጋሩ ነው። ኦህዴድ ውስጥ ያሉ የወያኔ አገልጋዮች ደግሞ ኦሮሞች ስለሆኑ የድሃ ኦሮሞ ወዳጆች አይደሉም። እነሱ የወያኔ ተቀጥላዎች ናቸው። የትውልድ መንደራቸውን ሳይቀር አዘርፈው የሚዘርፉ ስግብግቦች ናቸው።
የኦሮሞ ሕዝብ ትግል በወያኔ እና ተቀጥላዎቹ ድርጅቶች እንጂ በአማራና በኦሮሞ ወይም በኦሮሞና በትግሬ ሕዝብ መካከል አይደለም። የአማራ ሕዝብ ትግል በወያኔ እና ተቀጥላዎቹ ድርጅቶች እንጂ ከማንኛውም አካባቢ ሕዝብ ጋር አይደለም። ወደ እርስ በርስ ቅራኔ ሊዘፍቁን የሚፍጨረጨሩትን ህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድን ከሕዝብ መነጠል መቻል አለብን። እዚህ እኩይ ኃይሎች ሥልጣን ላይ እስካሉ ድረስ ፍትህና ሰላም ማግኘት አንችልም። እዚህ እኩይ ኃይሎች እርስ በርሳችን ሊያጫርሱን እየሠሩ መሆኑን አውቀን ኃይላችንን በማስተባበር እንመክታቸው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በማናቸውም የኢትዮጵያ ግዛት የሚደርስን የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በፍጹም ቁርጠኝነት በጋራ እንታገል፤ በስሜት ከተሞሉና ለእርስ በርስ ግጭቶች ከሚዳርጉ ነገሮች እንቆጠብ፤ አርቆ አስተዋይነትና ታጋሽነት በተላበሰ መንገድ የጋራ ጠላቶቻችን በሆኑትን በህወሓት እና አጫፋሪዎቹ ኦህዴድ፣ ብአዴን እና ደህዴድ ላይ በጋራ እንነሳ ሲል ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Rise up People of Ethiopia

May 23, 2014
by GRAHAM PEEBLES
There are tentative signs that the people of Ethiopia are beginning to organise themselves and stand up against the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) government, a brutal dictatorship, albeit one dressed in democratic western garb.
After 23 years of suppression at the hands of the EPRDF, simmering discontent and anger appears to finally be spilling over onto the streets. Robbed of hope, the people have had enough, enough of the wide-ranging human rights abuses. The denial of constitutional rights, the arbitrary imprisonments and torture, regime violence, the displacement of people from ancestral land, the partisan distribution of aid, and the rising cost of living.

The right to peaceful protest

Like many democratic principles, the right to protest is enshrined in Ethiopia’s constitution. Written in 1991 by the EPRDF, the legally binding document of liberal correctness is routinely ignored by the regime, whose response to public protests has been consistently violent.
Last year Addis Ababa witnessed the first mass demonstrations since 2005, when “security forces killed dozens of protesters [some estimate that up to 200 people were murdered by government forces] and arbitrarily detained thousands of people across the country.” [Human Rights Watch (HRW)] Unsurprisingly since then the streets have been quiet. Until 2013 that is, when in June thousands found the courage to march through the capital demanding the release of political prisoners, “respect for the constitution” and “Justice! Justice! Justice!” [Reuters] And again in November, when enraged demonstrators gathered outside the Saudi Arabian Embassy in Addis Ababa and cities across the world to protest the appalling abuse meted out to Ethiopian migrants in the Gulf State. Many hoped this united response was the beginning of a coordinated movement of collective action, a long overdue movement for change.There are tentative signs that the people of Ethiopia rise up
Ethiopia is young, 65% of the population are under 25, the median age is a mere 17, and like protest movements elsewhere — Egypt, Brazil, Turkey e.g., it is the young who are leading the way. They see clearly the injustices, the violations of fundamental freedoms and the duplicity of a government that presents a democratic face to its international allies and benefactors whilst brutalising its own people.
Since 25th April, students have demonstrated throughout the Oromia Regional State, protesting against the government’s sinister sounding ‘Integrated Development Master Plan’. The Oromo people constitute Ethiopia’s largest ethnic group — around 27 million people — almost a third of the population. They have been marginalised and discriminated against since the 19th century when Empress Taytu Betul (wife of Menelikk II) chose the site of Addis Ababa for the capital. As the city grew Oromos were evicted from their land and forced onto the margins — socially, economically and politically: “time and again, Oromo farmers were removed from their land under the guise of development without adequate compensation.”[Geeska Africa]. Like tyrants everywhere, the paranoid EPRDF is hostile to all forms of dissent no matter the source; however they react with greater levels of brutality to dissenting voices in Oromia than perhaps anywhere else in the country, and “scores of Oromos are regularly arrested based on their actual or suspected opposition to the government.” [Amnesty International (AI)]
The proposed ‘master plan’ would substantially expand the boundaries of Addis Ababa into areas of Oromia surrounding the capital. “Protestors claim they merely wanted to raise questions about the plan — but were answered with violence and intimidation.” [BBC] They rightly feel smallholder farmers and other groups living on government land (all land in Ethiopia is government owned) would once again be threatened, leading to large scale evictions to make way for land leasing or land sales, as has happened elsewhere in the country. In addition many Oromos see the proposed expansion as a broader threat to their regional and cultural identity and say the scheme is “in violation of the Constitutionally-guaranteed protection of the ‘special interests’ of the Oromia state.” [AI] Constitutional guarantees that mean nothing to the members of the ruling party, or a politically controlled judiciary.

Killing, beating, intimidating

University campuses have formed the beating heart of the protest movement that has now spread throughout the region. On Tuesday 29th April around 25,000 people, “including residents of Ambo town in central Oromia, participated in a city wide demonstration, in the largest show of opposition to the government’s plans to date.” [Revolution News] Somewhat predictably, security forces, consisting of the federal police and military Special Forces known as the ‘Agazi’, have “responded by shooting at and beating peaceful protesters in Ambo, Nekemte, Jimma, and other towns with unconfirmed reports from witnesses of dozens of casualties.” [Human Rights Watch (HRW)] A witness told Amnesty International that on the third day of protest in Guder town, near Ambo, the security forces were waiting for the protesters and opened fire when they arrived. “She said five people were killed in front of her. A source in Robe town, the location of Madawalabu University, reported that 11 bodies had been seen in a hospital in the town. Another witness said they had seen five bodies in Ambo [80 miles west of Addis Ababa] hospital.”
Whilst the government says that “at least nine students have died” during the protests, “a witness told the BBC that 47 were killed by the security forces” — a misleading term for government thugs, who are killing, beating and intimidating innocent civilians: Amnesty reports that children as young as 11 years of age were among the dead. In addition to killing peaceful protesters, large numbers have been beaten up during and after protests, resulting in scores of injuries, and hundreds or “several thousands”, according to the main Oromia opposition party, the Oromo Federalist Congress (AFC), have been arbitrarily arrested and are being detained incommunicado. Given the regime’s history those imprisoned face a very real risk of torture.
In many cases the arrests took place after the protesters had dispersed. “Security forces have conducted house to house searches in many locations in the region, [looking] for students and others who may have been involved. New arrests continue to be reported,” [AI] and squads of government thugs are reportedly beating local residents in a crude attempt at intimidation. Amnesty reports the case of a father whose son was shot dead during a protest, being ‘severely beaten’ by security forces, who told the bereaved parent “he should have taught his son some discipline.”
The Oromia community has often been the target of government aggression, and recent events are reminiscent of January 2004, when several Oromia students at Addis Ababa University were shot and killed when protesting for the right to stage an Oromo cultural event on campus. Many more were wounded and 494 [Oromo Support Group (OSG)] were arrested and detained without charge or trial. HRW reported how “police ordered both male and female students to run and crawl barefoot, bare-kneed, and bare-armed over sharp gravel for three-and-half hours; they were also forced to carry each other over the gravel.” The Police, HRW goes on to say, “have repeatedly employed similar methods of torture and yet are rarely held accountable for their excesses.”
The recent level of extreme violence displayed by the State is not unusual and takes place throughout Ethiopia; what is new is the response of the people. Anger at the security forces criminality has fuelled further demonstrations in Oromo as friends and family of those murdered have added their voices to the growing protest movement. This righteous stand against government brutality and injustice is heartening for the country and should be supported with condemnation and pressure from international donors and the UN more broadly. Those arrested during protests must be immediately released and investigations into killings by security personnel instigated as a matter of utmost urgency.

Tools of control

The government’s heavy-handed reaction to the Oromo protests is but the latest example of the regime’s ruthless response to criticism of its policies. Political opposition parties, when tolerated at all have been totally marginalised, dissenting independent voices are quickly silenced and a general atmosphere of fear is all pervading. Despite freedom of expression being a constitutional right virtually all media outlets are either government owned or controlled; “blogs and Internet pages critical of the Ethiopian government are regularly blocked and independent radio stations, particularly those broadcasting in Amharic and Afan Oromo, are routinely jammed.” [HRW] The EPRDF has created “one of the most repressive media environments in the world.” Reinforcing this condition, “the government on April 25th and 26th arbitrarily arrested nine bloggers and journalists in Addis Ababa. They remain in detention without charge.” [Ibid] International human rights groups (whose activities have been severely restricted by the stifling Charities and Societies Proclamation of 2009) as well as foreign journalists are not welcome, and reporters “who have attempted to reach the current demonstrations have been turned away or detained,” [Ibid] making it difficult to confirm exact numbers of those killed by government security personnel.
The UN Human Rights Council recently reviewed Ethiopia’s human rights record under the Universal Periodic Review (UPR). Since the first review in 2009 the human rights condition has greatly deteriorated. The EPRDF rules the country through fear and intimidation, they have introduced ambiguous, universally condemned legislation to control and intimidate: the Charities and Societies Proclamation (CSO law) and the Anti-Terrorism Proclamation specifically. Laws of repression that together have made independent media and civil society completely ineffective. Freedom of assembly – another constitutional right – is not allowed, (or as can be seen with the Oromo protests) is dealt with in the harshest manner possible; the Internet and telecommunications are controlled and monitored by the government and phone records/recordings are easily obtained by security personnel. Arbitrary arrests and false Imprisonment of anyone criticizing the government is routine as is the use of torture on those incarcerated. In the Ogaden region the regime is committing gross human rights abuses constituting crimes against humanity and in Gambella and the Lower Omo Valley large numbers of indigenous people have been forcibly moved into government camps (Villagization Programme), as land is sold for pennies to international companies. In short, human rights are completely ignored by the Government in Ethiopia. As the people begin to come together and protest, international pressure should be applied on the regime to observe the rule of law and uphold the people’s fundamental human rights.
We are living in extraordinary times, times of opportunity and change, times of great hope. With elections due next year now is the time for the various ethnic groups and factions inside and outside Ethiopia to unite, and speaking with one voice demand their rights, to freedom and justice and to live with hope in their hearts.
Graham Peebles is director of the Create Trust. He can be reached at: graham@thecreatetrust.org
Source: Counter Punch

Thursday, 22 May 2014

ይሻል መጣ ብዬ ምርኩዝ አስጨበጨ መንገድ ያሳየሁት፣ ለካ ሌላም አይደል ‘ደርጉ’ን ኖሯል እና ‘ኢህአዲግ’ ነው ያልኩት

ይሻል መጣ ብዬ ምርኩዝ አስጨበጨ መንገድ ያሳየሁት፣
ለካ ሌላም አይደል ‘ደርጉን’ ኖሯል እና ‘ኢህአዲግ’ ነው ያልኩት።
የደርግ እና የኢህአዲግ መመሳሰል ታወሰኝ እና  የኢትዮጵያ ገበሬ ምን ብሎ ያስብ ይሆን? እያልኩ ሳስብ የመጣልኝ ግጥም ነው።
በ 1967 ዓም የንጉሱን ስርዓት ከስልጣን ሲወርዱ በትረ መንግስቱን የተረከበው ደርግ የኢትዮጵያ ሰራዊት አካል በመሆኑ እና በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና አንድነት ላይ የማይደራደር ቢሆንም በአገዛዙ አምባገነንነት ኢህአዲግ ደርግን ተስተካክሎታል ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ ረቀቅ ባሉ ተንኮሎች ”ደርግ የዋህ አልነበር እንዴ!” የሚሉ ድምፆች እንዲበራከቱ እያደረገ ነው። በደምሳሳው ስንመለከተው አይመስልም።ወደ ዝርዝር ነገሮች ስንገባ ግን ኢህአዲግ በትክክል የደርግ አምባገነናዊ አገዛዝ ግልባጭነቱ ፍንትው ብሎ ይታየናል።
እስኪ እነኝህን ነጥቦች እንመልከት -
ደርግ ስልጣን ለሕዝብ እመልሳለሁ ብሎ ምሎ ተገዝቶ መልሶ መለዮውን እያወለቀ ስልጣኑን ያዘ።”ሕዝባዊ መንግስት አሁኑኑ” ያሉትን ገደለ። ኢህአዲግም ስልጣንን ለሕዝብ እሰጣለሁ ብሎ ምርጫ አደረገ ተሸነፈ።”ድምፃችን ተሰረቀ” ብለው አደባባይ የወጡትን አያሌዎችን በአደባባይ ገደለ።
ደርግ ልማቱ እየተፋጠነ ነው። ”እየተዋጋን እናመርታለን” ይል ነበር። ኢህአዲግም ”እድገታችን ሁለት አሃዝ ነው” ፀረ ሰላም ኃይሎችን በአንድ በኩል እየተዋጋን ምርታማነትን እንጨምራለን” ይላል።
ደርግ ሕዝቡን በዘር ሳይለይ አኢወማ (አብዮታዊት ኢትዮጵያ ወጣቶች ማኅበር)፣ አኢሴማ (አብዮታዊት ኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበር) እና ኢገማ (ኢትዮጵያ ገበሬዎች ማኅበር) እያለ ያደራጅ ነበር።
ኢህአዲግ/ወያኔ ረቀቅ አደረገው። በቋንቋ እየሰነጠቀ አማራ፣ኦሮሞ፣ትግሬ፣ሱማሌ እያለ አደራጀው። የኢህአዲግ የከፋ የሚያደርገው  ማህበራትን ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅቶችን ነው በጎሳ የሚያደራጀው።
ደርግ በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ ጤፍ አምራች ገበሬዎች ምርታቸውን በአህያ ጭነው አዲስ አበባ ወፍጮ ቤቶች ድረስ አምጥተው እንዲሸጡ ይፈቅድ ነበር (ጅንአድ ከገበሬው መግዛቱን ሳንዘነጋ)። ኢህአዲግ ገበሬዎቹ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ማገድ ብቻ አይደለም ከመሬታቸው ካለ በቂ ካሳ (ይሰመርበት ካለ በቂ ካሳ) ልቀቁ አለ።
ደርግ የብሔር በሄረሰቦች ኢንስቲትዩት መስርቶ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦችን ባህል፣ወግ፣ ቋንቋ በምሁራን እንዲጠኑ ያደርግ ነበር። ኢህአዲግ ብሔር ብሔረሰቦች በዓመት አንዴ ሞቅ ያለ ዘፈን እየከፈተ በቲቪ እንዲደንሱ በማድረግ እና አብዝቶ ስለነሱ በማውራት ደርግን አስንቆታል።
ደርግ የድሀውን ሕዝብ የኑሮ ችግር ለመደገፍ በእየቀበሌው ከክብሪት ጀምሮ እሰክ ኩንታል ጤፍ እና የተማሪዎች ደብተር ሳይቀር በቅናሽ ዋጋ እንዲዳረስ ያደርግ ነበር። ኢህአዲግ በዘመኑ የኑሮ ውድነቱ ጣርያ ደርሶም እራሱ ”ኑሮ ተወደደ” ብሎ መናገር የሚያሳስር መሆኑን በተግባር አሳየ።(ባለፈው ሰሞን ኑሮ ከበደን ያሉ ሴቶች የደረሰባቸውን ማሰብ በቂ ነው)
ደርግ አንድ ሰው ከቦታ ወደ ቦታ ሲሄድ ስሙ እና ፎቶው ያለበት መታወቅያ እንዲይዝ ያስገድድ ነበር። ኢህአዲግ ግን ስምና ፎቶ ብቻ ሳይሆን ‘ብሔር’ የሚል ጨምሮ ሕዝቡን ለያየው።
ደርግ አዋጅ ሲያወጣ አዋጁን ለምሳሌ የሰዓት እላፊ፣የመሰብሰብ ነፃነት ወዘተ ሲያግድ በራድዮ እና በቲቪ እንዲነገር ለጋዜጠኞች ይሰጥ ነበር።ኢህአዲግ እራሳቸው አቶ መለስ ”ከዛሬ ጀምሮ ከቤት ውጭ የሚደረግ ስብሰባ ተቃውሞ በሕግ ተከለክሏል” ብለው ሲናገሩ አሰማን።(ግንቦት 7/1997 ዓም አቶ መለስ በምርጫ ሲሸነፉ ያወጁትን አዋጅ አስታውሱ)።
ደርግ የኢትዮጵያ ዳር ድንበርን ሳያስደፍር ሲጠብቅ ኖረ።ኢህአዲግ ከባህር በር እስከ ኢትዮ-ሱዳን ድንበር ድረስ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ ሰጠ።Eprdf
ደርግ ሕዝብ ሁሉ ማንበብ እና መፃፍ መቻል አለበት ብሎ የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ ጀመረ። ኢህአዲግ ሕዝብ ሁሉ እስከ ቤተሰብ ወርዶ አንድ ለ አምስት መጠርነፍ (እንደ እርሱ አጠራር መደራጀት) አለበት ብሎ አንዱ ሌላውን እንዲሰልል አደረገ።
ደርግ ባለስልጣናቱ ከስልጣን እስኪወርዱ ድረስ ብዙዎቹ ባለስልጣናት እና የጦር መሪዎች በመንግስት ቤት ውስጥ እንዲኖሩ አደረገ። ኢህአዲግ ባለስልጣናቱ ሁለት እና ሶስት ቪላ እና መኪና እንደ ግምሩክ ባለሥልጣኑ ያሉት ደግሞ አልጋቸው ስር  ’የፎረክስ’ ቢሮ እስኪመስል ድረስ በሺህ የሚቆጠሩ የውጭ ምንዛሪዎች የሚይዙ ሆኑ።
ደርግ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁትን በሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ሥራ ይቀጥር ነበር። ኢህአዲግ ዩንቨርስቲ የጨረሱ ተማሪዎችን ሲመርቅ ገና ከዩንቨርስቲ እያሉ የስነ ልቦና ዘመቻ ይከፍትባቸዋል።ከምረቃ በኃላ ኮብል ስቶን እንደሚሰሩ ያረዳቸዋል። (አቶ ጁነዲን የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ሆነው ለአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተመራቂዎች የተናገሩትን እናስታውስ)።
ደርግ መብራት፣ውሃ እና ስልክ ከመቋረጡ በፊት በራድዮ እና በቲቪ ለምን፣መቼ እና ለምን ያህል ሰዓት እንደሚቋረጥ ይገልፅና ደንበኞቹን ከባድ ይቅርታ ይጠይቅ ነበር። ኢህአዲግ መብራት እና ውሃ ለሰዓታት አይደለም ለቀናት  ሲቆም ይቅርታ ሲያልፍም አይነካው። ለምሳሌ አዲስ አበባ አንድ ሚልዮን ህዝቧ ውሃ አለመኖሩ ብዙ አስጊ የሚባል አለመሆኑን የገለፁት የኢህአዲግ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው።”ውሃ የማያገኘው ሕዝብ 25% ብቻ ነው” ነበር ያሉት አቶ ኃይለማርያም ለጋዜጠኞች ሲመልሱ።
ደርግ ሕዝብ በግዳጅ ሰልፍ እንዲወጣ ያደርግ ነበር። ኢህአዲግ ሕዝብ ከኖረበት ቦታ ተባሮ እንዲወጣ በባለስልጣናቱ ሲደረግ እንዳለየ ለመምሰል እንደ አቶ መለስ ስለምፈናቀሉት ወገኖች ሲጠየቁ ደግሞ ነዋሬውን ”ድሮም ሞፈር ሰበር ነው” ሲሉ ተናገሩ። (እዚህ ላይ ከጉርዳ ፈርዳ፣ ሐረር ጋምቤላ እና ሌሎች ቦታዎች የተፈናቀሉትን አስቡ።)
እንዲህ እንዲህ እያልን ደርግ ተመልሶ በከፋ አገዛዙ መመለሱን እና በአንዳንዶቹማ ይብሱን ደርግ የተሻለባቸው ሁኔታዎች እንደነበሩ ብዙ ማስረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል።
ይሻል መጣ ብዬ ምርኩዝ አስጨበጨ መንገድ ያሳየሁት፣
ለካ ሌላም አይደል ደርጉን ኖሯል እና  ’ኢህአዲግ’ ነው ያልኩት።

Ethiopia: Bloggers of the World, Unite!

May 21, 2014
by ERecycler
Zone 9 Bloggers in Ethiopia Jail
Today is the 25th day in jail for Zone 9 Bloggers in Ethiopia. They have not been charged; in fact, the government could not come up with reasonable cause for detaining the 6 bloggers and 3 journalists. It has now come to our attention that two have been tortured. All they did was blog about conditions in their own country. Corruption has gone out of control; in a decade beginning in 2001 $16.5 billions have been illicitly transferred to foreign banks [according to Washington, DC-based Global Financial Integrity]. There are chronic water, power and food shortages. The state security literally eavesdrops on telephone conversations and controls Internet connectivity making Ethiopia the least served in Africa. The ruling party took office through the barrel of the gun and divided the country arbitrarily along ethnic lines [and later orchestrated a sham elections that it won]. This is 22 years ago. It has made it clear that it will not hand over or share power through the ballot box. It refused to abide by results of the 2005 elections when it was dealt a humiliating defeat. A year later, it abolished all opposition on the pretext of terrorism which the US and UK governments wholly endorsed and financed. All grassroots organizations that the ruling party did not like were de-registered. Ethiopia now leads the world in the number of journalists jailed or exiled and in human rights abuses.
If you are a blogger you can be part of a global effort to give voice to those denied and to help free those in jail for demanding their constitutional and unalienable rights. Please send a note to Obama and Cameron Administrations, to European Parliament, etc or simply to friends. We can change conditions both locally and globally if we come together. We refuse to bend to those who seek to divide our humanity in order to remain in power! Freedom! Freedom! Freedom!

Free or charge the bloggers: IFJ

The International Federation of Journalists (IFJ) on Tuesday severely criticised authorities in Ethiopia following the decision by a court to grant police nearly one more month to conduct investigations against the journalists and bloggers detained in the country last month.Three journalists and six bloggers were arrested on 25 and 26 April by police using an arrest warrant from a public prosecutor in Addis Ababa, the country’s capital city. The police on May 19 said that while the investigations continue the three journalists and six bloggers will remain in prison. “This is a clear human right violation,” said Gabriel Baglo, IFJ Africa Director. “These journalists and bloggers have not been charged yet and must be released immediately. The court is clearly hesitating because there are no strong charges against our colleagues”.
The IFJ criticism comes a few weeks after it wrote an open letter to U.S. Secretary of State, John Kerry, during his visit to the country to ask him to raise his concerns about the ordeal of the imprisoned journalists when he met with Ethiopian Prime Minister, Hailemariam Desalegn. According to media reports, Kerry subsequently raised the arrests during meetings with the Prime Minister and Foreign Minister, Tedros Adhanom, on May 1.
Following the meeting the IFJ welcomed Kerry’s action, but the Ethiopian court has now taken the decision to extend their detention.
The journalists who have been arrested are Tesfalem Weldeyest, who writes independent commentary on political issues for Ethiopia’s Addis Standard magazine and Addis Fortune newspaper, Asmamaw Hailegiorgis, senior editor at an influential Amharic weekly magazine Addis Guday, and Edom Kassaye, who previously worked at state daily Addis Zemen Newspaper and is an active member of the Ethiopian Environmental Journalists Association (EEJA).
The bloggers are reportedly members of the Zone 9 group, which is known to be very critical of government policy. They have a strong following on social media. They are: Atnaf Berahane, Befeqadu Hailu, Mahlet Fantahun, Natnael Feleke, Abel Wabela and Zelalem Kiberet. They are accused of using social media to create instability in the country and collaborating with international human rights organisations.
According to independent news reports, Ethiopian police said on Saturday, May 17, that the detainees were to be charged with the country’s anti-terrorism proclamation, No 652, published on 28 August 2009, which violates international standards on freedom of expression.
The IFJ believes that this proclamation directly threatens freedom of expression and human rights in the country which is Africa’s second worst jailer of journalists and media professionals.
Independent sources have reported that at least three of the detainees have complained of severe torture and long interrogations, while they have only seen the their lawyers twice since their arrests. “Holding detainees without charge for a prolonged period is a new trend that is becoming routine and systematic,” said Baglo. “It is another severe blow to human rights in Ethiopia and the international community must stand up and fight against it.”

መድረክ የጠራው ሰልፍ ተከለከለ – ፍኖተ ነጻነት

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ህዳር 29 ቀን 2006 ዓ.ም ለማድረግ ያሳወቀው ሰልፍ ተከለከለ፡፡ መድረክ
ሰልፉን ለመጥራት በሀገራችን መሰረታዊና ወቅታዊ የሆኑ ችግሮችን እንዲሁም በሳውዲና በአለም ዙሪያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ
ያለው ሰቆቃ መሰረቱ የስደት መንስኤው ላይ በመሆኑ፣ መንግስትን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡
ሰልፉን ለማድረግ የታቀደው ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ አምስተኛ በር ፊት ለፊት ከሚገኘው የመድረክ ቢሮ በመነሳት በአምስት
ኪሎና ስድስት ኪሎ አድርጎ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ድረስ ለመጓዝ ነበር፡፡ ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ
ፅ/ቤት “ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እውቅና የጠየቃችሁበት ስፍራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ አሰራር ስነ-
ስርዓት አንቀፅ አምስት ሀ እና መ የሰላማዊ ሰልፍ የማይካሄድባቸው ቦታዎች ተብለው የተጠቀሱ በመሆናቸው የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍ
እውቅና መስጠት የማንችል መሆናችንን እንገልፃለን” ሲል መልስ ሰጥቷል፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያት እንዲሰጡ የጠየቅናቸው የመድረክ ስራ አስፈፃሚና የአንድነት ፓርቲ ዋና ፀሀፊ አቶ አስራት ጣሴ “መልሱ
የመድብለ ፓርቲ ቅልበሳ ከመሆን አይዘልም” ይላሉ፡፡ አስተዳደሩ እውቅና ለመንፈግ የተጠቀመበት ደንብ ማንም የማያውቀው መሆኑን
የተናገሩት አቶ አስራት በማያውቁት ህግ እንደማይዳኙ ገልፀውልናል፡፡
በ1983 ዓ.ም የወጣው የሰላማዊ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 3/1983) የተከለከሉ ብሎ የሚጠቅሳቸው ቦታዎች
እንደሌሉና ከኤምባሲዎች፣ ት/ቤቶች፣ ሆስፒታሎች፣ የሀይማኖት አምልኮ ስፍራዎች፣ በገበያ ቀን (ከገበያ ስፍራ) መቶ ሜትር መራቅ
እንዳለበት ማዘዙን አቶ አስራት ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ከጦር ካምፕና የደህንነት ተቋማት 500 ሜትር መራቅ እንዳለበት አዋጁ
ማስገደዱን ያስረዱት አቶ አስራት ከዚህ ቀደም አንድነት መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም በጠራው ሰልፍ ይህንን አዋጅ በመሻር በጦር
ካምፕና በደህንነት መስሪያቤቶች በተከበበው ጀንሜዳ እንድንወጣ ነግረውናል ብለዋል፡፡
በተሰጠው መልስ ላይ አቋም ለመያዝ የመድረክ አመራር እንደሚሰበሰብ ከአቶ አስራት ጣሴ ለማወቅ ችለናል፡፡
መድረክ ህዳር 5 ቀን 2006 ዓ.ም መድረክ ለጠራው ሰልፍ አስተዳደሩ ከተደራራበ የስብሰባ ጫና የተነሳ የፖሊስ ሀይል ስለሌለኝ
ጥበቃ ላደደርግለት አልችልም በሚል እውቅና መንፈጉ ይታወቃል፡፡gk2

Wednesday, 21 May 2014

የአንድነት ፓርቲ በደጀን፤በደብረማርቆስና በባህር ዳር ከተማ የምክር ቤቶች ምስረታ አካሄደ – በያሬድ አማረ

በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር አባል ፤የውህደት ጉዳዮች ፀሀፊና የፋይናንስ ክፍል ሀላፊ በሆኑት በአቶ ፀጋዬ አላምረው የተመራው ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሀሙስ ማለትም ከግንቦት 7ቀን 2006ዓ. ም ጀምሮ በሰሜን ቀጠና የሚገኙ የፓርቲውን አደረጃጀት መዋቅሮች በመገምገም ላይ ሲሆን በተለይ በመኢአድና በአንድነት ፓርቲዎች የውህደት ጉዳይ በደጀን በደብረማርቆስና በባህር ዳር ከተማ ከሚገኙ የመኢአድ አባላት በቀረበ ጥያቄ መነሻነት በውህደቱ ጉዳይ ሰፊ ማብራሪያ መሰጠቱንና ከተናጥል ውይይቱ በኋላ የሁለቱ ፓርቲዎች አባላትን በጋራ በመሰብሰብ ስለወደፊት የሰላማዊ ትግል አቅጣጫ ስልት ዙሪያ መመሪያ የተሰጠ ከመሆኑም በላይ በደጀን፤በደብረማርቆስና በባህር ዳር ከተማ በእያንዳንዱ ከተማ 15 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያሉት የምክር ቤት ምስረታ መካሄዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተያያዘ ሁኔታም በቻግኒ ፤ዳንግላ እና አዴት ከሚገኙ ከመኢአድና አንድነት ፓርቲ አባላት ጋር ተመሳሳይ ሰፊ ውይይት የተደረገ መሆኑንና በአዲስ መልክ የስራ አስፈፃሚ አባላት መዋቀሩን እንዲሁም በአዴት ላይ ጽ/ቤት መከፈቱን በቦታው የሚገኘው ልኡካን ቡድን አስታውቋል፡፡ ቡድኑ በቀጣይ ቀናትም የፓርቲውን አደረጃጀት መዋቅር እየገመገመ ተመሳሳይ የማጠናከር ስራውን በሌሎች ቦታዎችም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡UDJ-SEAL

“ጅብ ቲበላህ በልተኸው ተቀደስ” (ከጸጋዬ ገብረ መድኅን አርአያ)

May 21, 2014
ከጸጋዬ ገብረ መድኅን አርአያ
ወያኔዎች አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላ የነበሩትን ዕለታት ክንውኖች በሥርዓት የመመዝገብ ልምድ ያለው ሰው የሚያሰፍራቸው ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ይኖሩታል። ከመጀመሪያው ዕለት አንስቶ። የእኔን የመጀመሪያ ዕለት አጭር ማስታወሻ ልንገራችሁ። በማለዳ ተነስቼ ጋቢዬን አጣፍቼ ከበሬ ላይ ቆሜ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው አህዮች ወደ መሐል ከተማው (አዲስ አበባ) ሲጓዙ አያለሁ። ያንኑ ያህል ባራባሶ ጫማ የተጫሙ፣ የአካል ዝለት የሚታይባቸውና ከእህል ጋር ከተለያዩ አያል ቀን የሆናቸው የሚመስሉ “ሰብአዊ ፍጥረቶች” አብረዋቸው ይሮጣሉ። ሲያሳዝኑ! ቆይ ቆይ…ከፓስተር ኢንስቲቱት በር ላይ አንድ ጥይት ተተኰሰ። ሌላ ጥይት- ሌላ ጥይት! ሰዎቹ ካለፉ በኋላ ወጣ ብለን ያየነው ሟች በሰፈሩ እንደ ሕሊና ሕመምተኛ የሚታወቅ ነበር።
እንግዶቹ አልመው የሚተኩሱ፣ አስበው የሚገድሉ አልመሰሉኝ አሉ። የሚያስቡበትና የሚያልሙበት ሕሊና የሌላቸው ፍጥረታት አድርጌ ላያቸው አልደፈርሁም። ባይሆን ሁሉም ጠላታችሁ ነውና አንዲት ጥይት ጮኸች ወይም አንድ ሰው ትንሽ ድምፅ አሰማ “በለው” በሚል መዘውር የተዘወሩ “መዘውራን” በመሆን በሳሩም በቅጠሉም ኤኬ47ቱን ማንጣጣት ያዙ። ያን ጊዜ በአእምሮዬ ጥግ በምትገኘው የማስታወሻ ሰሌዳዬ ላይ “ይኽ ቀን ገሐነም ባዶውን ያደረበት ዕለት ነው” ብዬ መዘገብሁ። እነዚህ ሰዎች እንደ መሪዎቻቸው በጥላቻ የተጠመቁ ከሆኑ መመለሻው ይቸግረናል። ከቶ ከየት ተነሥተን የት እንደርስ ይሆን? የማልረሳው ማስታወሻዬ ነው።Ethiopian columnist Tsegaye Gebremedhin Araya
የጥንቱ ጋዜጠኛ ግዮን ሐጐስ ጄኔራል መንግስቱ ንዋይ ተከሰው ፍርድ ቤት በቀረቡ ጊዜ ሪፖርተር ሆኖ ተመድቦ ነበር። ያን ጊዜ እኔ የአሥራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ነበርሁ። መሬቱ ይቅለለውና ግዮን ሐጐስ ስለ ጄኔራል መንግስቱ ሲያወራኝ “በንግግራቸው መሐል ኰራ ብለውና ችሎቱን እየቃኙ ዓይናቸውን- አራት ማዕዘን እየወረወሩ- “ የተናቀ ከተማ በአህያ ይወረራል” ይሉ ነበር። ( በነገራችሽን ላይ ጄኔራል መንግስቱ አንድ ዓይናቸው ጠፍቶ ነበር። በወንድማቸው በአቶ ገርማሜ ንዋይ በተተኰሰባቸው ጥይት)
የአህያን ሠራዊት ወግ – በቁሙና በእርቃኑ -እንደገና የሰማሁት ከባድመ ጦርነት በኋላ – ከባድመ ጦርነት ጋር ሲዘገብ ነው። የጦርነቱን ዳፋ- ድልና ሽንፈት – ውጤትና ሰብአዊና ማቴሪያላዊ ኪሳራ ያካተተ አንድ ጥናት እንደሚለው በራስ ስዩም የፈረስ ስም በምትጠራዋ “በይርጋ ጉብታ” ትራያንግል- በባድመ በተደረገው ጦርነት በፊተኛው ረድፍ ተሰልፈው የቀዳሚ- ሰማዕትነትን ሙያ የተወጡ 36ሺህ ኢትዮጵያውያን አህዮች ናቸው። ግፍ የተፈፀመባቸው እንስሳት ይባሉ?..ከጥናቱ እንደ ተረዳሁት ከአርባ ሺህ በላይ የሚሆኑ የሰሜን- ምዕራብ ኢትዮጵያ ገበሬዎች የኢሳይያስ ሠራዊት እንደ ድንች በዚያ አካባቢ የቀበራቸውን ፈንጂዎች እንዲያመክኑ ተደረገ። በአጭሩ አህያውም “ሰውም”- በወያኔ ትርጉም አማራ ሰው ከተባለ- በፈንጂ ማሳ ላይ እየተንደባለሉ አለቁ። አንድ ቀን ነፃነት ከተመለሰ ለዚያ ሁሉ ሕዝብ ውሎ ይደረግ ይሆናል። ለአህዮቻችንም ጭምር!
ይህን የጦር ሜዳ መረጃ በቅርቡ ያገኘሁት አይደለም። ዜናው ከዓለም ኅብረተሰብ ተደብቆ የቆየበትን ሁኔታ ሳስብ ግን በውስጤ ያለውን ክርስትና ጌታ ፍትሕ ወደ መጠየቁ አዘነብላለሁ። በዚህ ዓይነት ይህን ሁሉ ሕዝብ ያስጨረሱትን እኩያን ወገኖች ተፋረዳቸው ማለት ኅጢአት ነውን? ብሎ ግማሽ እኔ ይጠይቃል። ግማሽ እኔ ደግሞ ክርስቲያን ፍርድ አይጠይቅም። ምሕረት እንጂ። ጌታም ገዳዮቹን “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ይለኛል። አሁን ከሕሊናዬ ጋር ወደ መታረቁና ትክክለኛውንም መንገድ ወደ መከተሉ ነኝ። ከሰባት ጊዜ ሰባት በላይ ይቅር ብለናቸዋል። ስለዚህ ወሎዬ ዘመዴ እንደሚለው “ጅብ ቲበላህ በልተኸው ተቀደስ” ይስማማኛል። እናንተንም ይስማማችሁ። እስኪጨርሱን እንቆይ? ጋንዲንና ማርቲን ሉተር ኪንግን እንርሳቸው። ሙሴ ይሻለናል።
እንዲህ ዓይነቱን ዜና ታላቅ ወንድማችን (ቢግ ብራዘር) አልስማም? አላወቀም? በቢሊዮን በሚቆጠር የሳር ክምር ውስጥ የወደቀች መርፌ ዋሽንግተን ተቀምጦ ዴዴሳ በረሃ ለሚያይና ለሚለይ የሲአይኤ ሰላይ ሠላሳ ስድስት ሺህ አህያና አርባ ሺህ የሰሜን ምዕራብ ነዋሪ ህዝብ በፈንጂ ማሳ ውስጥ ተንከባልሎ ሲያልቅ አያውቅም “አላወቀም” ብለን የምንገኝ ተላላዎች ነን..? ሐቁ ወደዚህ ሳይሆን ወደዚያ ነው። ይልቁንም የሾሙአቸው አምባገነኖች በመድረኩ ላይ እስካሉ ድረስ ምንኛ እንደሚቆረቆሩላቸው፣ ምንኛ ምሥጢር ጠባቂያቸው ሆነው እንደሚቆዩ..ነው የሚገባን። አቶ ተስፋዬ ገብረ አብ ከኢትዮጵያ በኩል ያለውን ሰብአዊ ኪሣራ በአንዱ መጽሐፉ ይገልጥልናል። 98ሺህ ይለናል። በመቆርቆር ይሁን ወይም የኤርትራን አሸናፊነት ለመግለጥ አይታወቅም። ሃይማኖቱን አልጠይቅም። ከሕሊና ጋር አልተፈጠረም ደግሞ አልልም። አለዚያ በማን ላይ ትከስሰዋለህ? ከአነስተኛ የሚሊተሪ ሳይንስ ንባቤና ከኤርትራ ግንባር ሰልፌ እንደምረዳው ግን አንድ ሠራዊት ሁነኛ የማጥቂያ ግንባር ይዞና ቀጣናውን በፈንጅ አጥሮ ከተቀመጠ ለማጥቃት የሚመጣው ኅይል ሌላ ስልት መከተል አለበት። ጥበቃው የሳሳ ስፍራ መምረጥ አለበት። እርድ አዘጋጅቶ የተቀመጠውን ኅይል ከዚያ ምሽግ ማስወጣት ዋናው ታክቲክ ነው። በአድዋ ማርያም ሸዊቶ ላይ አጤ ምኒልክ ይህን ነበር ያደረጉት። ለወያኔና ለመለስ ዜናዊ ያንን ያህል “አማራና ኦሮሞ” ማስጨረስ ምንም ዓይነት ሰብአዊ ኪሳራ ሆኖ አልታየም። ኖሮ አይጠቀምበትም በሞቱም አይጐዳም!
በፈንጂ አማካይነት ብቻ ሳይሆን እንዲሁ የወያኔ ሰፈርም ሆነ የኤርትራው ግንባር ዘመናዊ መሳሪያ ማገዶ ሆነው ያለቁት ስንት የሚሆኑ ይመስላችኋል? እንደ ወጡ የቀሩትን ወገኖቻችንን የእልቂት ሁኔታ (ወሬ) የሚያቃምሰን ለምንና እንዴት ጠፋ?..ከጦርነቱ – ከእሳቱና ከእልቂቱ አምልጦ መርዶውን የሚያሰማንማ አልነበረም። እነዚህ በየዕለቱ በእጃቸው ላይ ትኩስ ደም ያለባቸውና ራሳቸውም “ትኩስ ደም ትኩስ ደም” የሚሸቱት አምባገነኖች እኛ ከምናስበው በላይ የሰለጠኑባቸው ተንኮሎች ሞልተዋል። ዊንስተን ቸርችል ከጆሴፍ ስታሊን ጋር የሰነበቱባቸውን ቀናት የምታውቁ ይመስለኛል። በጦርነቱ ወቅት ጄኔራ ሊዝሞ ስታሊን፣ ፕሬዚዳንት ሩዝቬልትና ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ዊንስተን ቸርችል ለተወሰኑ ቀናት በካይሮ በቆዩበት ጊዜ የተፈጠረ ነው። ቸርችልና ስታሊን በጨዋታ ተጠምደው ሳለ ንጥረ ነገሩን (ቮድካና ብራንዲ) ክፉኛ አጥቅተው ኖሮ የሚናገሩት ሁሉ የማይያያዝ – የእብድ ወግ ይሆናል። እንዲያውም ራሳቸውን መቆጣጠር ስላልቻሉ ከአስሩ የስታሊን አንጋቾች አምስቱ ቸርችልን፣ አምስቱ ደግሞ ስታሊንን ክንፍ ክንፋቸውን ይዘው ወደየ ክፍላቸው ወስደው ያስተኙቸዋል። በማግሥቱ ማለዳ ስካሩ ብዙም አልተለያቸውም። ቸርችል ደግሞ በታሪክ ጸሐፊዎቻቸው እንደሚነገረን ገላቸውን ሲታጠቡ እንኳ ሲጋርና ብራንዲ አይለያቸውም። ስለዚህ ከሶቪየቱ መሪ ጋር ሲገናኙ ‘እንደ መጠጥ ያለ አዋራጅ ነገር የለም! ትናንት ተዋረድን። ቢያንስ የርስዎ አጃቢዎች አይተውናል። ተዋርደናል!” ሲሉ ስታሊን “ኒየት! ኒየት! ማንም አያወራብንም። ትላንት የነበሩት ሰዎች እኮ የሉም” አሉ ይባላል። የሰው ነፍስ እጅግ ርካሽ በሆንበት ኢትዮጵያ ሥርዓቱ አንድ ሰሞን ሰማየ- ሰማያት ያጓናቸው ሰዎች በሌላ ወቅት አይኖሩም። ይልቁንም አንዱ ፍልስፍናቸው “ለወሬ ነጋሪነት ማንንም አለማትረፍ” የሚል ነው። እንዲያውም ለታላላቅ የስለላ ድርጅቶች (ኬጂቢ በተለይ) ይነገርላቸው እንደነበረው “ወያኔ እስከመቃብርህ ይከተልሃል” የሚል የውስጥ አዋቂዎች ግምት አለ። አደገኛ ከሆንክ የሞራልን ሕግጋት ሁሉ እየጣሱ ይከተሉሃል። ያጠፉሃል። እስከ ገሐነመ እሳት ይሸኙሃል።
የአዲስ አበባ ቃጠሎ ተብሎ ከሚጠቀሰው የግንቦት መድኅኔ ዓለም ማግስት የነበረውን እናንተ ከረሳችሁት እኔ አስታውሳችኋለሁ። በዚያን ዕለት በቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ግቢ ተገናኝተን አሳብ ለአሳብ የተለዋወጥነው የቀድሞ አምባሰደርና የሃይማኖት ትምህርት እውቀቱ ላቅ ያለ ወዳጄ ምናልባት እንደኔው ያወራው ይሆናል። ልዩ ትርኢትና ልዩ መገለጥ ተብሎ የተወራለት- ማርያም ልጅዋን ታቅፋ (ምስለ ፍቁር ወልዳ) በሰማዩ ላይ እየታየች ነው መባሉ ሲሆን ያንን አየን የሚሉትን ልዩ ቅዱሳን እንበላቸውና ሁለተኛው ከነትርጓሜው አብሮን አለ። በአእምሮዬ ቀርቶአል። ነገሩ እንዲህ ነው። በዚያን ዕለት የታየው ቀስተ ዳመና በቀጥታ ከሰማይ ላይ ወርዶ ምድሪቱ ላይ ተተክሎአል። አጠገቤ ያለ ሰው ሁሉ “እግዜሩ ሊታረቀን ነው። የደግ ቀን ምጽአት ምልክት ነው። እግዜአብሔር ዳግመኛ ምድርን በጥፋት ውኅ አላጠፋትም ብሎ ለኖህ ቃል ኪዳን ሲገባለት እንዲህ ያለ ቀስተ ዳመና በምልክትነት ሰጥቶታል..” ሲሉ እሰማለሁ። ይሁንና ያ የቀድሞ አምባሳደር ወዳጄ ጐተት አደረገኝና “በእኛ ቤተክርስቲያን እምነትና በተለይም በአበው ሊቃውንት ትርጉም መሠረት ይህ ቀስተ ደመና በጥሬው አይተረጐምም። የእልቂት፣ የስደት፣ የደም መፋሰስ ምልክት ነው። ስለዚህ ከሚመጣው አደጋ ሁሉ እንዲሰውረን መጸለይ አለብን፡፤ ቃሌን እንዳትረሳ” አለኝ። ስሙን ብገልጸው ደስ ባለኝ ነበር። የወቅቱ መኳንንት ያንገላቱታል ብዬ ፈራሁለት እንጂ።
እንደ ሕልም፣ ትንቢትና ከላይ የጠቀስሁትን የተፈጥሮ ንባብ (ከነትርጓሜው) በተመለከተ አንዳንድ ሳይኪያትሪስቶችን መጠቃቀስ ይቻላል። ፍሮይድን፣ ፓቭሎቭን..በማንበብ ከትርጓሜው ላይ ለመድረስ -አለዚያም ከንቱ እምነትነቱን ለመግለጥ አይመችም። እነሱም አላጠኑትምና። ለምሳሌ እጅግ ጣፋጭ የሆነችውን የሐዲስ አለማየሁን “ትዝታ” ያነበባችሁ ትዝ የሚላችሁ ቁም ነገር አለ። አቶ ሐዲስ እንደሚገልጡት ከጠላት በፊት በደብረ ማርቆስ ከተማ አስኳላ ሲያስተምሩ አንድ ጥቁር እንግዳ ከቤታቸው ከች ይላል። እንዲያው በችኮላና በቁሙ “ሐዲስ! ኢትዮጵያን ጠላት ይወርራታል። አንተም ትዘምታለህ!” ብሎአቸው ይሄዳል። ከጥቂት ቀናት በኋላ ይኸው ወዳጃቸው ከአባ አሥራት ገዳም ሲመለስ ወደ ሐዲስ ዓለማየሁ ቤት ይሄድና “ላጫውትህ አልችልም። እቸኩላለሁ። ሐዲስ! ኢትዮጵያ ትወረራለች። አንተም ወደ ጦር ሜዳ ትሄዳለህ። ትዘምታለህ!” ይላቸዋል። ከጥቂት ወራት በኋላ የጠላት ከምሥራቅና ከሰሜን መንቀሳቀስና ኢትዮጵያን መውረር ወሬ አየሩን ሞላው። የጐጃሙ ገዥ ራስ እምሩ የጐጃምንና የጐንደርን ጦር እየመሩ ወደ ሽሬ ግንባር ይዘምታሉ። ሐዲስ ዓለማየሁ የጦር ሜዳ የፕሮፓጋንዳ ሃላፊና ለጥቆም የብርቱ ምሥጢር ተላላኪ ሆነው ሲሠሩ ቆዩ። ሰውና ከብት በመርዝ ጋዝ ጢስ ያለቀበትን- የከብትና የሰው ደም ተቀላቅሎ ወንዙን (ተከዜን) ያስነፈጠበትን ሁኔታ ጥሩ ገላጭ የሆነችውን የሐዲስ ዓለማየሁን “ትዝታ” ያነብቡአል። (ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ በዚሁ መጽሐፍ ቀስቃሽነት የፈጠራትን “እስከዳር” መጽሐፍን ልመርቅላችሁ። ወዳጅ ብቻ ሳይሆን ወንድሜ የሆነው ሻለቃ ዳዊት በቅርብ ጊዜ የተጻፉ ታሪካዊ ልብ ወለዶች አንጋፋ ልትባል የምትችል መጽሐፍ በመድረሱ ባርኔጣዬን አነሳለታለሁ)
“አምልኮ ወይም ምልኪ ነው” ልትሉኝ ትችላላችሁ። የፈቀዳችሁትን በሉኝ። ያ አምባሳደር (አ.ወ.አ) ግንቦት 28 1983 የነገረኝ የቀስተ ደመና ትርጉም እንደ ወንጌል ቃል አብሮኝ አለ። ወያኔ በምንም ጊዜና ቦታ፣ ሁኔታና እቅድ ረገድ የሚፈጽመውንና ያቀደውን ከመግለጥ ሸብረክ ያለበት ጊዜ የለም። ደበሎ ሰቅሎ ፍላጐቱንና ግቡን ይለፍፋል። ከዚያ ዓላማው ደግሞ ፈቀቅ ያለበት ወይም በመጠኑም ቢሆን አቋሙን ያለዘበበት አጋጣሚ አልነበረም። ከዚህ ውስጥ- ማለትም ከዚህ ጽንፈኛና ሕመምተኛ መንግሥት አውራ ግብ (ማስተር ፕላን) ውስጥ ዋነኛው አንዱን የተወሰነ ሕዝብና ሃይማኖት ማጥፋት ነው። ሕዝብን ለማስተዳደር (በመሰረቱ ለመግዛት) የመጣ አካል አንዱን የቋንቋ ክፍልና (ብሔረሰብ ለማለት የትርጉም ስሕተት አያለሁ) ሃይማኖቱን (ኦርቶዶክስ ተዋህዶ) ለመደምሰስ እቅድ እንዳለው ሲናገር – በግልጽ በአደባባይ ሕዝቡና ምሑሩ፣ ወጣቱና አእሩጉ፣ ቤተ ሃይማኖቱና ዓለምም በነቂስ አንዲት ትንፋሽ ተቃውሞ አላሰሙም። እንደኔም እንዲህ በሰላም ወጥተው ለመግባትና ሕሊና የሚያዝዘውን አውጥተው ለመናገር የሚችሉ ሁሉ ስለ “አማራው” እልቂት ማውሳት ከወቅቱ የፖለቲካ ፋሽን አንጻር ኋላ ቀር ስለሚያሰኝ ዝምታን መርጠዋል። ሁላችንም- ኦሮሞውም፣ አማራው ራሱም፣ ከምባታውም፣ ሌላ ሌላውም ኢትዮጵያዊ -እኛም የምንጫጭር ሰዎች ስለማንም- በተለይም ስለ አማራው ሕይወትና ንብረት፣ መብትና የግለሰብ ነፃነቱ መጻፍን- ልድገመውና ከፖለቲካው ፋሽን ወደ ኋላ መቅረት አደረግነው። ይኸ ደግሞ አዲስ “ግንዛቤና” አዲስም የፖለቲካ ፈሊጥ አይደለም።
መለስንና አቋሙን የሚያውቁ ሰዎች በምስክርነት እንደሚያረጋግጡት የሰውዬው ቀዳሚ እምነት “አማራ ከገጸ – ኢትዮጵያና ከገጸ- ምድርም መጥፋት አለበት። አንዳንድ ጊዜ አስተዳደጋችሁና ባሕላችሁ በፈጠሩባችሁ ስሜትና ዝንባሌ ምክንያት ወንጀሉን የሚሰሩት ሰዎች የማያፍሩበትን ኅጢያት እናንተ በመጻፋችሁና በመቃወማችሁ ጭብጥ ታህል ትሆናላችሁ። እዚህ አካባቢ እንደታዘብሁት አንድ ጠንካራ ዜጋ “ አንድ ኢትዮጵያዊ ህዝብ ለምን የጥፋት ዒላማ ይሆናል? ” በማለቱ አንዳንዱ ሰው “የትግሬ ጠላት” አድርጐ ይስለዋል። መለስ ዜናዊ፣ ታምራት ላይኔ…አማራንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ስለማጥፋት ሲናገሩ ምን ተሰማን? ምንስ አልን? ለመሆኑ ትግራዩን ሕዝብ በጠቅላላውም ባይሆን አድዋውያንን ስለ ማጥፋት ቢነሳ ዝምታ የዜግነት ግዴታ ነው እንላለን? ከፖለቲካው ፋሽን ውጭ ነውና በዚያው እንቀጥል ይባላል? የዛሬው የፖለቲካ ፋሽን አማራን ለኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ መክሰስ፣ በኅላፊነት ማጋለጥና መዝለፍ ነው። ያ ቢበቃ ደግ ነበር። አንዳንዶች በእምነት፣ አንዳንዶች ለጣቢታ (ኩርማን እንጀራ) አንዳንዶች ደግሞ “እንደ ንጉሡ አጐንብሱ” በሚለው ፍልስፍና መሠረት የሚያሰሙት አዝማች ነው። ለመሆኑ ሕዝብ እያለቀና የበለጠም እንደ ተደገሰ ይሰማችኋልን?
ፕሮፌሰር አሥራት የመላው አማራ ድርጅትን ሲመሰርቱ ከምሁራን መካከል ወዳጆቻቸው የሆኑ ጥቂት ሰዎች በግል እንዳነጋገሩአቸው አውቃለሁ። እኔም በግሌ ከእሳቸው ጋር ባለኝ ራፖርና በተጨማሪም ምክትላቸው ከነበሩት ከአቶ ኅይሉ ሻውል ጋር ፖለቲካ ወደ ጐሳ በሚወርድበት ጊዜ ስለሚከተለው ጣጣና በተለይ የእነሱ ወያኔ በፈጠረው ጉድጓድ ውስጥ መግባት አርአያነቱ የሚያስከትለውን ችግር ሁሉ ዘርዝሬ ሞግቻቸው ነበር። ሙግቴ የበለጠውን ከፕሮፌሰር አሥራት ጋር ሲሆን በእሳቸው በኩል ያለው ጥረት በአርሲ፣ በሐረርጌ..ወዘተ እያለቁ የሚጮህላቸው ያጡትን አማሮች መብት ለመጠበቅ መሆኑንና የፖለቲካ ስልጣን የመፈለግ አዝማሚያ እንዳላሳዩና ወደፊትም እንዳማያሳዩ ገለጡልኝ። ለሁለቱም አንጋፋ ዜጐች በተለያየ ሥፍራና ጊዜ በኢትዮጵያ ስም የሚቋቋም የፖለቲካ አካል (ግንባር፣ ድርጅት ወይም ፓርቲ) ለሁሉም ኢትዮጵያዊ መብትና ነፃነት ስለሚቆም መአሕድ ወደ ፓርቲ የሚያደርገውን ሽግግር ቢያቆሙት እንደሚሻል ለመምከር ሞከርሁ። ምከሬ ደካማ ሆኖ የመአሕድ ፓርቲ ተመሰረተ። ከኢትዮጵያዊ ሁሉ ልብ ሊጠፉ የማይችሉት ታላቅ ዜጋም የዘመናቸው የአገር ሰማዕት ሆኑ። ወያኔ እስከመቃብር ተከተላቸው። በፖለቲካው አምባ እንደ አባዩ የሩሲያ መነኩሴ እንደ ራስ ፑቲን ይቆጠሩ የነበሩት አባ ጳውሎስ ደግሞ ለአሥራት በተቆፈረው መቃብር ዘልለው ለመግባት ፈልገው ነበር ይባላል። አይ ደበበ እሸቱ! በሞታችን ቴያትር እየተሰራብን ነው። ይኸ የአንድ ሰው ሞት አልነበረም። የሺዎች እልቂት እንጂ!
በእኔና እንደኔ ከቀዩ ፍልስፍና መልስ ወደ መንደር መውረድን ዝቅጠት አድርገን ለተመለከትነው ወገኖች በመለስ ዜናዊ በተዘጋጁልን የጐሳ ጉድጓዶች ውስጥ እየሮጡ መወሸቅ አገሪቱን በመበጣጠስ ረገድ ተባባሪ መሆን ይመስለኛል። ይሁንና በዚያው ጊዜ ውስጥየታዘብሁት አንድ አስገራሚ ነገር የማላስባቸው ሰዎችን ከማላስባቸው ሰፈሮች ማግኘቴ ነበር። ለተወሰኑ ሳምንታት ሳይታሰር የቆየና በነበረው ሥፍራ እኔንና ሌሎችን የኢንፎርሜሽን ድርጅቶች ኅላፊዎች እየሰበሰበ ከማለዳ እስከ መንፈቀ ሌሊት እጅ እጅ የሚል ገለጣ ሲሰጠን የኖረን የደርግ አባል ከአንድ የጐረቤት ልቅሶ ላይ አገኘሁ።
“ነፍጠኛ….ነፍጠኞች…ብሔር- ብሔረሰብ..ሕዝቦች ” ሲል ሰማሁትና “ጓድ ማለቴን ትቼ ኦቦ ልበልህ…እንደ አመጣጥህና ፍጥነትህ ወደፊት አንዳች አደጋ ካልደረሰብህ የኢህአዴግ አመራር አባል የማትሆንበት ምክንያት አይታየኝም። ቋንቋቸውን ብቻ ሳይሆን ጽንሰ-አሳቡንም …ዓላማቸውንም ዓላማህ በማድረጉ ረገድ ፈጥነህ ራስህን አስተካክለሃል። በእኔ በኩል ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ በጐሳ በመሸንሸኑ ረገድ የለሁበትም። እነሱ ይዘውት የመጡትን ይህን በሽታ ደግሞ ሁላችንም መድን ተከትበን የምንከታተለው መስሎኝ ነበር” አልሁት። የደርግ አባሉ ሌሎቹ አንጋፋ የደርግ አባላት ከተያዙ በኋላም ለሳምንታት በከተማው ውስጥ ሲነዳ ዓይን ስቦ እንደነበረ ትዝ ይለኛል። በአጭሩ ግን ጥቂት የማይባሉ ከእኛው “የአብዮቱ ሰፈር” ጭቃው ሳይነካቸው፣ ርእዮተ ዓለሙም ሳይጠልፋቸው በአንዳች ኀይል ወደ ወያኔ ሰፈር- የድል አምባ – የተሻገሩ በርከት ያሉ ነበሩ። አሁንም የሉም ትላላችሁ? ሌሎችም አሉ እንጂ! የኢሰፓ አባል ለመሆን ብዙ መከራ አድርገው በሞራላቸው፣ በሥራ አፈጻጸማቸው፣ በየቢሮውና ፋብሪካው በነበራቸው ነውር ተንቀው የቀሩም ግመልና ዝሆን የሚያስገባ አዳራሽ አግኝተው ሲሣይ ማፈስና የጠሉትን መርገጥ ሆነላቸው። የልዩ ዐቃቤ ሕግ ሹም የነበረውን ግርማ ዋቅጅራን ለአብነት ይጠቅሱአል። እነዚህ ሁሉ ዜጐችን ተበቅለው፣ አዋርደውና ገድለው ቢበቃቸው አንድ ነገር ነበር። አገርን በማፍረስና በመናዱ ረገድ ርኅራኄ የተለያቸው ሆኑ! እስመ ዓለም ምሕረቱ!
የአፍሪካ መሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ሲሰባሰቡ በአብዛኛዎቹ በጋዜጠኝነት ተገኝቻለሁ። ገና በነፃነት ጎዳና ብዙ ያልተጓዙት “የአፍሪካ አባቶች” ተብለው የሚጠቀሱት መሪዎች መላልሰው ሲናገሩ እንሰማቸው የነበረው ጐሳ በፖለቲካ፣ ፖለቲካም በጐሳ ውስጥ ሲገባ ሰፊ ራእይ ያየንላት አኀጉራችን መመለሻ ወደሌለው እንጦሮጦስ ትወርዳለች እያሉ ነበር። ያ ልክፍት በእኛ ዘንድ እንደ ልዩ ነገር ሳይቆጠር አልቀረም። እንዲያውም የረጅም ዘመን የነፃነት ኑሮአችን ሰፋ ካለ “ኢትዮጵያዊነት”ና አገራዊ አመለካከት እርከን ላይ አድርሶናል ብለን እንወያይ ነበር። በኩራት!
ወያኔ ከከፍተኛ ማማና ኅብረተሰባዊ የእድገት ደረጃ ላይ ደርሰናል፣ ሕዝባችን የአንድነት መሰረቱ ጽኑ ነው በምንልበት ሰዓት ነው የተናቀና እጅግ ኋላቀር የፖለቲካ ሥርዓት አምጥቶ የዚያ ባዕድ አምልኮ “ጊኒ ፒግ” ያደረገን። በእኔ በኩል ይህን ሒደት የኢትዮጵያ ውርደት፣ የፖለቲካም መዝቀጥ አድርጌ አየዋለሁ። የመለስ ዜናዊ አድናቂዎችንም የምፋለማቸው በዚህ ዓቢይ ነጥብ ነው። በዚያ ላይ ነው እልቂቱ፣ አገር ሸንሽኖ መሸጡ፣ ታላቂቱን ኢትዮጵያ በአረቡ፣ በሕንዱ፣ በፓኪስታኑ..በቻይናው እግር ሥር ማውረዱ የመጣው። እኔ የመጣሁበት ፖለቲካ (ኢሠፓ ነው አትበሉኝና) ሁሉን ሠርቶ አደሮች ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ዜጋ የሚያስተሳስረው – በአንድነትና በአንድ ዓላማ የሚያስተባብረው፣ የኢትዮጵያ ልጅነትን የሚያራምደው አንድ ለሁሉም ሁሉም ለአንድ የሚያቆመው የዜግነት መሠረት ነው። እኔ ከአድማስ ባሻገር የማየው ፖለቲካ በኢትዮጵያ ፍትሕ የነገሠበት፣ ሰው በሰው የማይበዘበዝበት ሥርዓት ነው። ሰውን የሚያከብር፣ የዜጋውን ሰብአዊነትና ሉአላዊነት – ባለስልጣንነት የሚያውቅ ሥርዓተ መንግሥት ነው። የኮሚኒስት ሥርዓት ማለት አይደለም። ከዚያ በላይ የሚያበራ፣ ከዚያ በላይ እምነት የሚጣልበት ሥርዓት ነው። የፖለቲካ ሥርዓት ወይም ሥነ መንግሥት “ኢዝም” ብቻ አይደለም። ከኢዝም በላይ አስባለሁ። አስቡ! ከ1960 ጀምሮ እንዲህ እንዲህ እያለ እየተጠረቃቀመ የሚመጣውን አደጋ በማጤን ኢትዮጵያዊነትና ብሔራዊ ስሜት ከምንም በላይ የሚያበራ ኮከብ ይሆን ዘንድ በግንባር ቀደምትነት ሞክረን ነበር። ውስጥ ለውስጥ ይህን ሲታገሉ የነበሩ ኅይሎች ናቸው ይፋ ወጥተው – ይፋ ግፍ የሚፈጽሙት። አልተኙልንም። አንተኛላቸው። እየገደሉን ናቸው። ጠላትህን መግደል ነው ያልጀመርኸው።
ልምዱንና የፖለቲካ ዓላማውን ከተማሪ እንቅስቃሴ ጋር ከሚያዛምደው ትውልድ መሐል አይደለሁም። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሕግ እውቅናና የማይገሰስ ሕዝባዊ ሥልጣኑ ከታወቀ የምርጫ መብቱና ክብሩ ከተረጋገጠ እንዲበቃኝ ወስኛለሁ። ስለዚህ ከአጠቃላዩ ነጠላውን በመውሰድ እገሌ መታወቅ ያለበት በጐሳው መሆን አለበት ከሚለው ሰፈር ሥፍራ እንዲኖረኝ ፈልጌ አላውቅም። አንዳንድ ሰዎች ይኸ “ናኢቭ አሳብ ነው” ይሉ ይሆናል። የዋህነት አይደለም። የኦሮሞ ነፃነት፣ የአማራ ነፃነት፣ የጉራጌ ነፃነት፣ የትግሬ ነፃነት በሚለው ሰፈር የለሁበትም። በቶሎሳ፣ በጫኔ፣ በጠንክር፣ በሐጐስ…ነፃነት ግን አምናለሁ። እዚህ ላይ እንረፍ።
አሁን ደርሶ የመጣው ልክፍት ለአንዱ ተሰጠ የሚባለው ነፃነት ሌላውን ከገጸ- ምድር የሚያጠፋው ሲሆን ወጣ ብለህ (አፈፍ ብለህ) ከትግሉ ግንባር ውስጥ የሚያሰልፍህ ነው። የፖለቲካው ፋሺን የሚጋብዘው የተወሰኑት የቋንቋ ክፍሎች ተነስተው ከተላለቁ በኋላ የተወሰኑት ደግሞ የመላዋ ኢትዮጵያ ገዢዎች ይሆኑ ዘንድ ነው። ወጣ እናድርገውና አማራና ኦሮሞ ሲጫረሱ፣ ይልቁንም የገዥነት ሚና ነበረው የሚሉት አማራ እስኪያልቅ ድረስ ከተመታ አብዛኛው የአገዛዝ ችግር ይቀረፋል። ሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር ብዙ ሰዎች በአእምሮ ቅልጥፍናና በምሁራዊ ዝንባሌው ሲያደንቁት እሰማለሁ። እንዲህ ያለ የተበላሸ እንቁላል በአእምሮው ውስጥ ይዞ የኖረ ሰው “ቀልጣፋ፣ ምሁር..አሳቢ..ፈጣን…” የሚሉ ቃላትን በእሱ ላይ የሚነሰንሱ ሰዎች ናቸው ሊታዘንላቸው የሚገባ። ትልቁና ዋና ዓላማው የሕዝብ ፍጅት፣ የአገር መበታተንና የሚጠላውን ሁሉ ማጥፋት የሆነውን ሰው እስከ ማወደስ የሚደርስ ሰው በግድ ሳይክያትሪስት ማየት የሚገባው ነው።
ከቀን አንድ ቀን ጀምሮ የነበረው ሁሉ አስደንጋጭ ነው። እንደዚያ ግንቦት 28 ቀን 1983 የታየውን ቀስተ ደመና የእልቂት ደመና አድርጐ እንደ ተረጐመው አምባሳደር በአማራውና በኦሮሞው መካከል የሚፈጠር ፍጅት ያሳሰባቸው አባቶችም ነበሩ። “የፖለቲካውን ፋሽን” ሳልፈራ ሁለት የተከበሩ ዜጐች መኖሪያ ቤት ሄድሁ። አንደኛው ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳ ነበሩ። ሁለተኛው ደግሞ ቢተወደድ ዘውዴ ገብረ ሕይወት ሲሆኑ ከጠላት በፊት ጀምሮ በአስተማሪነት፣ በዲፕሎማሲና በአገር አመራር ሰፊ ልምድና እውቅት ያካበቱ አባት ነበሩ። ሁለቱንም በተለያዩ ጊዜያት ቀጠሮ ይዤ አነጋገርኳቸው። ያን ጊዜ በአርሲ፣ በሐረርጌ፣ ዲማ የሚባል ሰብአዊ ፍጡር አማራ እያባረረ ይገድላል፤ በሐረርጌ በአሰቦት ነፍጠኛ ሁሉ እየተረሸነ ነው የሚባልበት ጊዜ ነበር። ያንን ደግሞ የሚያራግቡ፣ ትልልቁንና በጀግንነቱ የሚታወቀውን ኦሮሞ ጄኔራልና ራስ ሳይቀር በዘላን ቋንቋ የሚዘልፉ ጋዜጦች ወጣ ወጣ ማለት የጀመሩበት ነበር። ይኸ አካሄድ ለቢትወደድም ለኮሎኔል ዓለሙም አልጣማቸውም ነበርና ሊመጣ የሚችለውን አደጋ በማሰብ በሰፊው ተወያየንበት።
ሁለቱንም ጐምቱ ዜጐች ገጽ ለገጽ ማገናኘት አልቻልሁም። ዓላማችን ግን ኮሎኔሉ በኦሮሞ አባትነት፣ ቢተወደድ ደግሞ በአማራ አባትነት አደባባይ ወጥተው “ሕዝቡን ለማጫረስ የተጠነሰሰውን ሴራ በሚያጋልጥ መልክ እንዲያወግዙ ነበር። ሁለቱም የሚወክሉትን ኅብረተሰብ ባሕልና ሥርዓት ስለሚያውቁ ተቃቅፈው ፍቅራቸውን በመግለጥ፣ የሁለቱንም ታሪክና የደም ትስስር በማብራራት እያሳሰበ የመጣውን የፖለቲካ ደመና እንዲያከሽፉት ለመሞከር ነበር። በሦስተኛው ቀን ኰሎኔል ዓለሙ “ሁሉም ነገር ጥሩ ነበር። ትናንትና ከበቀለ ነዲ ጋር ስንነጋገርበት ከእኛ መካከል ወደ እብደት የወሰዳቸው አክራሪዎችን ይጠንቀቁ። እዚሁ አጠገባችን ያለውን..ሰው ይህን ቢያዋዩት ሊገድልዎ ይችላል። አላወቁትም መሰለኝ እንጂ አለኝ” አሉ። በዚህ የተነሣ ፕሮጀክቴ ወደቀ። እኔም አሜሪካ ከሚሉት አገር ገባሁ። ከአንድ የብስጭትና የጭንቅ መንፈስ፣ ከአንድ ማንም ያለመልሰልኝ ጥያቄ ጋር ቀረሁ። እንዲህ ያለውን ጭካኔና ጥላቻ ከቶ ከየት አመጡት? የተወሰኑ ባለስልጣኖች ልትጠላ ትችላለህ። አገር ሙሉ ሕዝብ- ግዑዝዋ አገር..እንዴት የጥላቻ ዒላማና የእልቂት ሰላባ ይሆናሉ? ለመሆኑ እነዚህ ዛሬ በወያኔ ገፋፊነት ከፍልፈል ዋሻ ወጥተው የሚጫጩት ትንንሽ ነፍሳት መጫረስና መፋጨት ለሕዝብ አንዳች መፍትሔ ይሰጣል ብለው እንዴት ሊያስቡ ቻሉ? ወይስ አጀንዳቸውንና የወደፊት ጉዞአቸውን ለምን በግልጽ አይነግሩንም? ሌላውም ኢትዮጵያዊ ከኢትዮጵያ በቀር ሌላ አጀንዳ ስለሌለው ጅቡ- ቲበላው በልቶት ቄደር ለመጠመቅ ዝግጁ ሊሆን ይችላል።
በሰፊው ሲታይ ከኢትዮጵያ ማኅበረሰብ የወያኔን ጡጫና ካራ ያልቀመሰ የለም። ኦሮሞዎች አውቀውታል። ጉራጌው፣ የደቡቡ ኅብረተሰብ፣ አኝዋኩ…ጋምቤላው ተራ በተራ ሰይፍ ተመዞባቸዋል። ችግሩ አንዱ በሚረፈረፍበት ጊዜ ሌላው ሊጮኽለት አለመቻሉ ነው። ከእነዚህ የሕዝብ ክፍሎች መካከል የወጣነው አንዳችም ጩኸት ማሰማት ቀርቶ ጥቂት ጥቂት ተቆርቋሪነት የሚሰማቸውን ጭምር ተቃዋሚዎች መሆናችን ነው። አለዚያ በኢትዮጵያ አብዮት ዘመን የነበርን ሁሉ የወያኔን “ታላቅ ሴራ” እናውቃለን። ሰምተናልም። ከቶውንም እንደማስታወሰው የቀድሞው መሪያችን ጓድ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኅይለማርያም ሦስት ቀን በራቸውን ዘግተው የጻፉትን ዲስኩር እንድንሰማ ተደርጐ ነበር። የዚያን ዕለት ንግግራቸው “ወያኔ በአማራው ላይ ያነጣጠረ፣ እልቂት ማቀዱ..ከቶ ምክንያቱ ምንድነው?” የሚል ነበር። ከዚያ መንግስት የማይሻል የለም በሚል ብቻ የጓድ መንግሥቱን ንግግር አጣጣልነው።
ከሩዋንዳ የ1994 እልቂት በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየትኛውም አገር ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት መከላከያ መዘየዱን ገልጦ እንደነበረ እናስታውሳለን። እንደ እውነቱ ደግሞ በዚሁ ዓለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ አባላት የነበሩ አምባገነን ሥርዓቶች በሕዝቦቻቸው ላይ ወደር የሌለው ጭካኔ ሲያሳዩና እልቂቶችንም ሲፈጥሩ ድርጅቱ የወሰዳቸውን ርምጃዎች አናውቅም። ከ1975- 1979 በካምቦዲያ ከአንድ ሚሊዮን እስከ 2.5 ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ በገዥው (ካይመር ሩዥ) ሲጨፈጨፍ አንዳች ጠያቂ አልነበረበትም። በኋላም አረመኔው ፓልፓት ፍትሕን ፊት ለፊት ሳያይ በእርጅናና በበሽታ ሞቶአል።
በአርሲ፣ በሐረርጌ፣ በወለጋ፣ በጋምቤላ..በጉራፈርዳ..በወያኔና ባሰለፋቸው ጭፍሮቹ በጥይት የተቆሉትን ዜጐች ..ከዚያም በፊትና በኋላ በየሰበቡ በየአደባባዩ የወደቁትን ዜጐች ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን የሚያስበልጡ ሰዎች አሉ። ብዙዎች እልቂቶች ደግሞ አደባባይ እንዳይወጡ፣ በየአገሩ በሚታወቁ የመገናኛ አውታሮች እንዳይነገሩ ተደርገዋል። ይኸም ባሰለፋቸው ልዕለ ኅያል ግፊት መፈጸሙ ምሥጢርነት የለውም። እስከናካቴውም ግዙፋን ማስረጃዎችን ይዘው የዓለምን ፍርድ ቤት ጥሪ የሚጠብቁ እንደ ሒዩማን ራትስዎች፣ አምንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ጄኖሳይድ ዎች ወዘተ ያሉ ድርጅቶች ከነመለስና መንግሥታቸው ደጋፊዎች የሚደርስባቸው የጨለማ ጡጫ የሚቻል አይመስልም። ስለዚህ “አማሮችንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን በጠላትነትና በአላስገዛም ባይነት ገዥም ተባባሪም ተስማምተዋል። ከዚህ ቀደም በዋሽንግተን ዲሲ በሚደረጉ ሰልፎች ላይ ተሳትፌ አውቃለሁ። ለስቴት ዲፓርትማንት ተወካይ መግለጫ የሚሰጥ ሲፈለግ እኔና ወዳጄ አረጋዊ በርሄ በግንባር ቆመን የሰልፉን ዓላማ መግለጥ ጀመርን። ወዲያው የአማራን የጠላትነት አቋም እንደ አንድ ነገር የተጋተው የመሥሪያ ቤቱ ሰውዬ “የአማሮች ሰልፍና የአማሮች አላማ ይገባናል” ይላል። ወደ አረጋዊ በርሄ እያሳየሁ “እሱ ወንድሜ ትግራዊ ከመሆኑም በላይ ቲፒኤልኤፍንም የመሰረተ ነው። የራሱን ድርጅት ፀረ ሕዝብነት በመረዳት ራሱን ያገለለም ነው። እኔ ደግሞ እንዲሁ ተራ ኢትዮጵያዊ ነኝ” አልሁት። “አገር አገር፣ ነፃነትና አንድነት…መብትና..” የሚል ሁሉ በአማራነት ይመደብ ጀምሮአል። ኢትዮጵያዊነትንም ሰብስበው ለአማራው አሸክመውታል። ስለዚህ ከአንዳንድ ፈረንጆች ጋር ስትነጋገሩ ስለኢትዮጵያ አንድነትና ስለ አገሪቱ ክብር ካነሳችሁ “ማን መሆንህን አወቅሁት። አማራ ነህ” ትባላላችሁ። በእኔ በኩል ይህ አነጋገር የኦሮሞውም፣ የከንባታውም፣ የትግሬውም መሆን አለበት። እነዚህ ወገኖቼ በወያኔ ሰንሰለት እግር ከወርች ካልታሰሩ በቀር ይኽ እምነት የሁላችንም ነው። ከፋም ለማም፣ ጊዜ ፈጀ አልፈጀም ኢትዩጵያ የሁሉም እናት ትሆናለች። እስከዚያው የሚከፈለው ሰማዕትነት ግን በዛ። ከበሮ እየተመታ ነው። አላጋንንም። አንዲት ሰረዝ የአጋንኖ አልጨምርበትም። የጦርነትን አቅጣጫ እሱ ባለቤቱ እያዘወረው ነው እንጂ እልቂቱ ከተጀመረ ውሎ አድሮአል። “ተነስ” የሚልህስ ማነው? ተኝተሃል እንዴ ተነሥ የምትባለው?
ገብረመድኅን አርአያ ለብዙ ጊዜያት ብቻውን በምድረ በዳ የሚጮኽ ባህታዊ ሆኖ ቆይቶአል። ጓደኞቹን እንኳ ሳያስተርፍ፣ ለጥላቻቸው ዋጋ ሳይሰጥ ይህንን የኢትዮጵያ አንድና ዋነኛ የሕዝብ ክፍል ለመጨረስ የወያኔን እቅድ ገልጦልን ነበር። ምዕራፍና ቁጥር እየጠቀሰ። ከየትም አቅጣጫ ከማንም ግለሰብ ማስተባበያ አልተሰጠበትም። “በዓለም ላይ በአንዳች ሥፍራ አንድን የሕዝብ ክፍል ለመጨረስ የሚቀነባበር ሴራ ሲያጋጥማችሁ አመልክቱ” የሚለው ከሩዋንዳው እልቂት በኋላ የወጣ መግለጫ ነበር።
በኢትዮጵያ ሁኔታ በሁሉም ሕዝብ ላይ ለሚቀነባበረው ሴራ ፊሽካ ነፊው ወያኔ ነው። የእልቂት አሰልጣኙ ወያኔ ነው። እንደ ሩዋንዳ እልቂት ዝግጅት 1400 ካድሬዎችንና የግድያ ቡድኖችን አሰልጣኝና ቦታ ቦታ አስያዥ ወያኔ ነው። ምናልባት ተኳሾቹ ኦሮምኛ የሚናገሩ ወይም መናገር የሚችሉና በኦሮሞ ስም ኬላውን ለማለፍ የሚችሉ ይሆናሉ። ትርኢቱ የወያኔ፣ ደራሲው ወያኔ፣ መሪው ወያኔ! ዝግጅቱ ብዙ ዘመን ጠይቆአል። ወያኔዎች ለድርሰቱ አልተቸገሩም። ተስፋዬ ገብረአብ የተባለ ወጣት ፕሮፖጋንዲስት ትከሻ ላይ ኅላፊነቱን ሁሉ መጣል ውጤት ያስገኛል ብለው ጣጣቸውን ጨርሰውታል። ተስፋዬ በቃላት መጫወት ይሆንለታል። ቃላትን ከድንጋይ ጋር ያወያያቸዋል። በአንድ ክፍል ውስጥ “ቃላት” ሰብስቦ ያለ ተናጋሪ ያንጫጫል። አዎን ተስፋዬ- ማናቸውም ባለቋንቋዎቹ በማይሆንላቸውና በማይደፍሩበት ሁኔታ ደስታውንና መከፋቱን፣ ዳር ድንበር የሌለውን የወሲብ ረሃቡን የሚናገርለትና የሚናገርበት አማርኛ አለው። ይኸ ጥበብ (ታለንት) ገበያ መውጣት ነበረበት። ወጣ- የቡርቃ ዝምታ ተወለደ። ይኸ የተስፋዬ መንፈስ ዛሬ ኢትዮጵያን እያመሰ ይገኛል። ሐውልት አሠርቶአል። ጦር አማዝዞአል።
ሁላችንም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለመሮጥ ሞክረናል። ተስፋዬ ብቻ ያወቀውና የሚያውቀው ታሪክ ሌላ ነው። ይኸውም በቡርቃ ዝምታ መጽሐፉ ውስጥ አጤ ምኒልክ የጨረሱአቸው የኦሮሞ ጀግኖችና ጡታቸውን የተቆረጡ ሺህ በሺህ ሰዎች ናቸው። ተስፋዬ ይህን መሳይ እንቁላል ጥሎ ወደ ስደት እንደ ሄደ ይነግረናል። ባይነግረንም እናውቃለን። ከዚያ በኋላ ደግሞ እንደገና በቃላት አፍዝ አደንግዝ (ሒፕኖታይዝ ሲያደርገን) የጋዜጠኛው ማስታወሻን፣ የደራሲው ማስታወሻንና በመጨረሻም የስደተኛው ማስታወሻን አዘጋጀልን። “ የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ! ጠላቶችህ በዛሬ ቀንና በዚሁ ሥፍራ በእጅህ ገብተዋልና ዝምታው ምንድነው? አታውቅም እንጂ አማራ አያት ቅድመ አያትህን ጨርሳለች። አንተንም ቢሆን ገድላሃለች- አላወቅህም እንጂ!” ካለ በኋላ ለእኛ ለውጭዎቹ ደግሞ የትኛው የወያኔ ሹም ከየትኛይቱ ኮረዳ…ካልሆነም መለኮን ጋር እንደ ተዳራ፣ ምን እንደ ተጠጣ..ማን ኮንትራባንድ እንደሚነግድ ..ማን ብዙ እንደሚሰክር..ነገረን። ይኸ ቅማል ነበር እንዴ የበላን? የተስፋዬ በማርታ አሻጋሪ ዘፈን እንደ ወንድ አህያ አውሬአዊ የወሲብ አመሉን በሕዝብ እይታ ፊት መፈጸም ም ይፈይድልናል? በቋንቋው ኅይል ያንከራተታቸው ሰዎች አሉ። መሞታቸውን ከእሱ የሰሙ። ታሪካቸውንና ውርደታቸውን ከእሱ ያነበቡ። እስከ ዓለም ምሕረቱ!
ተስፋዬ በስደቱ ዓለም በቆየባቸው ዓመታት ልብ ወለድ መጽሐፉ- የቡርቃ ዝምታ- በአገር ቤትም ሆነ በውጭው (ዳያስፖራ) የፈጠረችውን ቱማታ መለካቱ አልቀረም። “ኦሮሞ ነን” የሚሉ ጉርባዎችን አስከትሎ “ታላቁ የኦሮሞ ሕዝብ ወዳጅ” ተብሎ በሚሞገስበትና በሚሸለምበት ሥፍራ ሁሉ ዲስኩር አድራጊ ሆነ። ጥፋትን አብሮ በማቀድና አብሮም በአንድ ግብ ስር ተሰልፎ ወደ አፈጻጸሙ የመንደርደር ተግባር ሁሉ እስካከናወነ ድረስ በእኔ በኩል ተስፋዬ ምን ጊዜም ከወያኔ ጋር የሚያስተሳስረው እትብቱ አልተቆረጠም። ይልቁንም ልብ ወለድ ድርሰቱ ሐውልት ሊያሠራ መቻሉና የገንዘብና የማቴሪያል ጥቅም ማግበስበስ ላይ መገኘቱ ቀላል ግምት አያሰጠውም። እነሆ በኢትዮጵያ ሕዝብ መሐልም የሚቆም የጥላቻ ግድግዳ፣ የበቀል ግንብና ለትውልዶች የሚተላለፍ መርዝ አበረከተ። መርዝ መርዝ! ነብዩ ኢያሱ በአፍሪካ ቀንድ መጽሔት ላይ ያወጣት አንዲት ግጥም ትዝ አለችኝ። “ወይ ውረድ ወይ ፍረድ!” ነበር የምትለው ( በነገራችን ላይ ተስፋዬ ገብረአብ በግል እኔን ያሞጋገሰኝ ሰው ነው። እንዳልናገር በቅድሚያ የተከፈለ ጉቦ ከሆነ የከመረብኝን ቋንቋ ሁሉ ይውሰድልኝ) በታሪክ ካላደረቅኋችሁ ጥቂት ጊዜና ትዕግስት ስጡኝ። ወጌን አላበቃሁም። አንድ ቃል ልጨምር። ከ “የቡርቃ ዝምታ” በኋላ ነው የስደት ማስታወሻ ቢያንስ በነፃ የተለቀቀው። አነበብሁት። ኢትዮጵያንና አማራ የተባለውን ሕዝብ የሚገልጥበት፣ ተጨቁነዋል የሚላቸውን የተወሰኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን አሥር ቶን በሚሆን ውሸት የሚያንቆለጳጵስበትን ሁሉ አንብቤለታለሁ። መላልሼ ለራሴ ያቀረብሁት ጥያቄ “ለምን ይሆን ተስፋዬ ይህን ሕዝብ ይህን ያህል ለመጥላትና በመቃብሩ ላይም ድንጋይ ለመመለስ የፈለገው? ኢትዮጵያስ በአንድ ሰው ተመስላ የበደለችው ምን ይሆን? ሕዝቡ እንዲጫረስ መንፈሱን ያነሳሳው ምንድነው?”
እንደሚወራው ተስፋዬ በብዙሃኑ ዲያስፖራ የማርያም ጠላት ቢባልም ለራሳቸው አዲስ ስያሜ የሰጡትና አንዲት ቅጠል የኢትዮጵያን ታሪክ አንብበው የማያውቁ ግለሰቦች ደግሞ እጅብ እጅብ እያደረጉት ነው። በሦስተኛው ክፍል ጥቂት አሹዋፊዎች አሉበት። ተስፋዬ የሚነግረን ሁሉ ትክክል ነው። ይህን ሁሉ መከራ እንዴት ቻልነው? ሳናውቀውና ሳይሰማን እንዴት እስካሁንዋ ቀን ደረስን? ይሉታል። ለካንስ ይህን ያህል ተበድለን ነበር? ከተገረፈው ገላችን፣ ከቆሰለው አጥንታችን በላይ የተስፋዬ ቃላት ይናገራሉ። ለካ አልቀን ነበር? የተስፋዬ የእልቂት አዋጅ የሆነው የቡርቃ ዝምታ በሌላውም ምሽግ የምትታወቅ ከሆነች መልሱ “ጅብ ቲበላህ..በልተኸው ተቀደስ” መሆን አለበት። ጋንዲንና ማርቲን ሉተርኪንግን ተዋቸው።

Tuesday, 20 May 2014

Detained Journalists and Bloggers in Ethiopia Must be Charged or Released, says IFJ

May 20, 2014
(reliefweb) – The International Federation of Journalists (IFJ) has today severely criticised authorities in Ethiopia following the decision by a court to grant police nearly one more month to conduct investigations against the journalists and bloggers detained in the country last month.Free Detained Journalists and Bloggers in Ethiopia
Three journalists and six bloggers were arrested on 25 and 26 April by police using an arrest warrant from a public prosecutor in Addis Ababa, the country’s capital city. The police on May 17 said that while the investigations continue the three journalists and six bloggers will remain in prison.
“This is a clear human right violation,” said Gabriel Baglo, IFJ Africa Director. “These journalists and bloggers have not been charged yet and must be released immediately. The court is clearly hesitating because there are no strong charges against our colleagues”.
The IFJ criticism comes a few weeks after it wrote an open letter to U.S. Secretary of State, John Kerry, during his visit to the country to ask him to raise his concerns about the ordeal of the imprisoned journalists when he met with Ethiopian Prime Minister, Hailemariam Desalegn.
According to media reports, Kerry subsequently raised the arrests during meetings with the Prime Minister and Foreign Minister, Tedros Adhanom, on May 1. Following the meeting the IFJ welcomed Kerry’s action, but the Ethiopian court has now taken the decision to extend their detention.
The journalists who have been arrested are Tesfalem Weldeyest, who writes independent commentary on political issues for Ethiopia’s Addis Standard magazine and Addis Fortune newspaper, Asmamaw Hailegiorgis, senior editor at an influential Amharic weekly magazine Addis Guday, and Edom Kassaye, who previously worked at state daily Addis Zemen Newspaper and is an active member of the Ethiopian Environmental Journalists Association (EEJA).
The bloggers are reportedly members of the Zone 9 group, which is known to be very critical of government policy. They have a strong following on social media. They are: Atnaf Berahane, Befeqadu Hailu, Mahlet Fantahun, Natnael Feleke, Abel Wabela and Zelalem Kiberet. They are accused of using social media to create instability in the country and collaborating with international human rights organizations.
According to independent news reports, Ethiopian police said on Saturday, May 17, that the detainees were to be charged with the country’s anti-terrorism proclamation, No 652, published on 28 August 2009, which violates international standards on freedom of expression.
The IFJ believes that this proclamation directly threatens freedom of expression and human rights in the country which is Africa’s second worst jailer of journalists and media professionals.
Independent sources have reported that at least three of the detainees have complained of severe torture and long interrogations, while they have only seen their lawyers twice since their arrests.
“Holding detainees without charge for a prolonged period is a new trend that is becoming routine and systematic,” said Baglo. “It is another severe blow to human rights in Ethiopia and the international community must stand up and fight against it.”

OLF calls Ethiopians to stand with Oromo students

ESAT News
May 20, 2014
The Oromo Liberation Front (OLF), which is led by General Kemal Gelchu, said as the protest of students of the Oromo ethnic group is a protest against the unjust eviction of Oromo farmers, the public needs to stand with them and support them.

OLF in its press release stated that the ruling party in Ethiopia is working to prolong its grip on power by causing inter-ethnic fights and this will hurt the Nation at the end of the day; thus, all political parties should leave their differences aside and struggle together.
It also noted that the demolition of the historic Waldeba Monastery, Northern Ethiopia for sugar development and the sale of lands in Gambella are deplorable. The eviction of Oromo farmers is similarly aimed at selling the lands to investors, which should be opposed by all Ethiopians now.
OLF said Ethiopians without being divided along ethnic, place of origin and religion should rise in unison and continue the protest against the new Addis Abeba Master Plan.
In a related development, Ethiopians in Munich, Germany have held a protest opposing the killing of students in Ambo and other towns of the Oromia region in Ethiopia.
Also, the fact that some Ethiopians were selected to leave from a fund raising meeting recently held for the construction of the Great Ethiopian Renaissance Dam (GERD) in the city had sparked a row. Although the participants that were kicked out by the cadres, had said that they were entitled to attend the meeting as they are Ethiopian citizens; the cadres of the ruling Front did not concur with the demands.
The evicted Ethiopians had voiced their opposition carrying pictures of students that have been recently killed by the government forces in Ethiopia and photographs of detained journalists, politicians and human rights activists.

Silencing the Zone9 by hook or crook

May 20, 2014
by Hindessa Abdul
It has been over three weeks since close to a dozen journalists and bloggers were arrested, most of whom members of the blogging collective known as Zone 9. Their site, hosted in Google’s Blogger platform, was launched two years ago with a catching motto “We blog because we care.” They coined the name after a visit to the Zone 8 of the Kaliti prison, where a fellow journalist, Reeyot Alemu, is serving a five year sentence. Zone 9 is a metaphor to say the rest of the populace is also in jail but in a different cell block. No surprises, their page was blocked within weeks of its launch.An Ethiopian court granted police 10 more days to investigate six bloggers and journalists
Abel Wabela, Asmamaw W/Giorigis, Atnaf Berhane, Befekadu Hailu, Edom Kassaye, Mahlet Fantahun, Natnael Feleke, Tesfalem Weldyes, Zelalem Kebret have been locked up in the notorious Maekelawi in the north of Addis, where the tradition of torture is well alive and kicking.The bloggers were public servants,university professors,information technology professionals, full time journalists so on and so forth.
As it has become absurdly the norm, police had detained then started to investigate the alleged crimes, dashing the hopes of a speedy trial. So far the broad allegations are: working with a foreign organization that claim to be human rights group; conspiring to incite violence via the social media. An advisor to the Prime Minister put it as “criminal activities” without delving into specifics. Police have requested more time to investigate. The courts have no problem granting the wishes of the police at the expense of the detainees.
Some papers that came out in the last couple of days said, weeks after the arrest nobody knows the reason for their detention. However piecing together the words of police and close associates of the ruling party , there are clues to indicate where this thing is going to end up.
The dots
At the beginning of April, security officials detained Patrick Mutahi, a Kenyan national and a staff of Article 19 – a London based rights group working for the defense of freedom of expression — at the Bole International Airport. His earlier visits to the country (said to be five times) have been closely monitored.
Ironically Patrick’s travel to Ethiopia was related to a training on security and safety. Talking of safety, media watchdog groups train journalists in various skills. In recent years, with governments filtering the web, the subject of circumnavigating censorship; concealing the location from where blogs are posted have gained traction. Back in the early days of Internet filtering, the Paris based Reporters without Borders produced a famous manual called Handbook for Bloggers and Cyber-dissidents to help protect journalists in otherwise unfriendly political systems.
While Patrick was deported back to his country after a day in custody, his cell phone was confiscated, leaving behind a trove of information.
Enter HRW
In March of this year Human Rights Watch published a report on the state of surveillance in Ethiopia. The 100 page report entitled: ‘They Know Everything We Do: Telecom and Internet Surveillance in Ethiopia’ explains how security officials willy-nilly eavesdrop on the phone conversation of citizens. Here is a witness telling his encounter in the report:
“After some time I got arrested and detained. They had a list of people I had spoken with. They said to me, “You called person x and you spoke about y.” They showed me the list—there were three pages of contacts—it had the time and date, phone number, my name, and the name of the person I was talking with. “All your activities are monitored with government. We even record your voice so you cannot deny. We even know you sent an email to an OLF [Oromo Liberation Front] member.” I said nothing.”
Hence, the call log in Patrick’s phone will reveal all the individuals he had contacted. No matter what the conversations, it would be construed in a way that justifies the government’s paranoia.
TPLF insiders
A day after the detention of most of the suspects, Mimi Sebhatu, a close confidant of the Meles-Azeb family went on to her radio station and said the suspects had contact with Article 19. Mimi may have an inside knowledge not least because of her association with the inner circle as to her family’s history in the lucrative security business in the country.
In the closed court appearance police told the judges that some of the suspects travelled to Kenya and have received money and training from a human rights group. Police stopped short of mentioning who the rights group was.
TPLF run online media in North America are having a field day attacking Article 19 and the bloggers. They call the group “a neo-liberal extremist organization for hire, created for the sole reason of overthrowing democratically elected governments.” And the bloggers are guilty even before they are formally charged. “It’s a criminal act to make Addis Ababa turn into Ukraine’s Kiev for the sake of money, by working with the likes of ‘Article 19’ Eritrea and Egypt,” opined one.
So there should be no doubt as to what the charges will be associated with. The insiders have told us in no uncertain terms that it is all about Article 19. We, surly, will stay tuned.

ዘር ማጥራትወይስኢህአዴግንማፍረስ? (ተመስገን ደሳለኝ)

ኢህአዴግ ያነበረውን ቋንቋንና ዘውግን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም አደገኛነት በተመለከተ በርካታ ምሁራን፣
ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች… ሳያሰልሱ ለመምከርና ለማስጠንቅቅ መዋተታቸውን አልዘነጋሁም፡፡ እኔም ከ“ፍትህ”
ጋዜጣ እስከ “ፋክት” መጽሔት ድረስ ችክ ያልኩበትም ሆነ ዛሬ በዚህ ተጠየቅ የተመለስኩበት ምክንያት ችግሩ
እያደር እየተባባሰ በመምጣቱና ከምንጊዜውም በላይ አዘናግቶ ወደተፈራው የእርስ በእርስ እልቂት ሊዘፍቀን
እየተንደረደረ በመሆኑ፣ ቅድሚያ ሰጥተን በሕብረ-ድምፅ ‘የሀገር ያለህ!’ ብለን መጮህ እንዳለብን ስለማምን ነው፡፡

አርባ አራት ዓመት ወደኋላ…
በኢትዮጵያ የዘውግ ጥያቄ ለአደባባይ የበቃው በ60ዎቹ መጀመሪያ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ከዘመነኞቹ የተማሪ
እንቅስቃሴ መሪዎች ይህንን ጥያቄ አለቅጥ ለጥጦና አጋንኖ በማቅረብ ግንባር ቀደሙ ዋለልኝ መኮንን ነው፡፡ በ1962
ዓ.ም በአራት ገፅ ቀንብቦ ባዘጋጀው ታሪካዊ ጽሑፉ አማካኝነት “የብሔሮች ጥያቄ” ይፋ ሆኖ ለውይይት ከመቅረቡ
በፊት፣ የተማሪው ዋነኛ የመታገያ አጀንዳ የመሬት ጉዳይ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ (በደብዛዛውም ቢሆን
ይንፀባረቅ የነበረውን መደብ ተኮር መንፈስ ሳንረሳ)፡፡ ዋለልኝ የሀገሪቱን መንግስታዊ አወቃቀርም ሆነ ባሕልን
በአማራና በትግሬ ተፅእኖ ስር ስለመውደቁ በተቸበት በዚያ “ዝነኛ” ጽሑፉ ላይ እንዲህ ይላል፡-
“…ማንንም ሰው የኢትዮጵያውያን ቋንቋ ምንድን ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የኢትዮጵያውያን ሙዚቃ የቱ ነው ብላችሁ
ጠይቁ፤ የኢትዮጵያውያን ባሕል የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ ብሔራዊ ልብሳችሁ የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የአማራ
ወይም የትግሬ ይላችኋል፡፡”
ይህ ሀቲት በወቅቱ በአብዛኛው ተማሪ ዘንድ ቁጣ ከመቀስቀሱም በላይ ዋለልኝን በ‹ፀረ-አማራና ትግሬነት› አስፈርጆ
ለውግዘት ዳርጎት ነበር፡፡ እራሱም ቢሆን በአንድ የዩንቨርስቲው መድረክ ላይ የተሰነዘረበት ከባድ ተቃውሞ
በፈጠረበት ብስጭት ‹‹እኔም አማራ ነኝ፤ ያውም ከአማራ ሳይንት-ቦረና›› ማለቱ ይታወሳል (ቦረና በተለምዶ አማራ
መጥቶበታል የሚባለው አካባቢ መሆኑን ልብ ይሏል)፡፡ ግና፣ ዋናው ጥያቄ የእርሱ አማራ መሆን ያለመሆን
አይደለም፤ እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰበት ምክንያት ከተጨባጩ እውነታ ጋ ምን ያህል ይዛመዳል? የሚል ነው፡፡
ሌላው ነገር ደግሞ ከዚህ ጽሑፍ በፊት ብሔር ተኮር ጎዳዮችን አንስቶ ካለማወቁም በዘለለ፣ ሌሎች ሲያነሱ ፅንፈኛ
ተቃዋሚ ስለነበረ ነው፡፡ ለምሳሌ ተማሪ ኢብሳ ጉተማ (ኋላ ላይ የኦነግ መስራችና አመራር የሆነው) ‹‹ኢትዮጵያዊ
ማነው?›› በሚል ርዕስ ባቀረበው ግጥም እጅግ ተናድዶ ‹‹እንዴት እንዲህ አይነት ግጥም ታቀርባለህ? ዘረኛ ነህ፤
ኢትዮጵያውያንን የመከፋፍል ዓላማ ነው ያለህ?›› በማለት እስከመቃወም መድረሱ የክርክሩ አንዱ ጭብጥ ነው፡፡
ታዲያ ዋለልኝ መኮንን ድንገት እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው ከምን የተነሳ ይሆን? በርግጥ ለዚህ ድንገቴ የአቋም
ለውጥ ሶስት መላ-ምቶች ሲነገሩ ቆይተዋል፡፡ የመጀመሪያው ‹በአፄው ሥርዓት ላይ አሴረዋል› ተብለው
ከተከሰሱትና ‹ኦሮሞ እየተጨቆነ ነው› የሚል እምነት ከነበራቸው ጄነራል ታደሰ ብሩ ጋር በታሰረበት ወቅት፣
በጄነራሉ ስብከት አመለካከቱ ተቀይሮ ሊሆን ይችላል የሚለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ‹‹መገንጠልን መደገፍ
በመጨረሻ የማትገነጠል ሀገር እንድትኖር ያደርጋል›› በማለት ከተከራከረበት ከራሱ አቋም ጋር የሚያያዝ ነው፤
ሶስተኛው ‹የሻዕቢያ (ኤርትራውያን ተማሪዎች) አሊያም የአሜሪካኑ የስለላ ተቋም (ሲ.አይ.ኤ) መጠቀሚያ ሆኖ
ነው› የሚሉት ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ይሁንና ከዋለልኝ ጀርባ ‹ስውር እጅ›ን ለመፈለግ ያስገደደው በጊዜው ብዙሁ ተማሪ
ለሀገሪቱ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ‹የንጉሣዊው አስተዳደር ኋላቀርነት እና ስግብግበነት ነው› ብሎ ከማመኑም ባለፈ፣
ከፌዴራላዊ ይልቅ የቻይና ኮሙኒስታዊ ሥርዓት አድናቂ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የተማሪውን እንቅስቃሴ
1
 በመምራት በዘመኑ ከዋለልኝ የላቀ ተሰሚነት የነበረው ጥላሁን ግዛው ‹‹ጎሰኝነትን›› በአደባባይ አጥብቆ ይቃወም
እንደነበረ፣ በ1968 እ.ኤ.አ የታተመው ‹‹Struggle›› ቅፅ 3፣ ቁጥር 1 መጽሔት ጋር ያደረገውንቃለ-መጠይቅ
መጥቀስ ይቻላል፡-
‹‹በመጀመሪያ ደረጃ በጎሰኝነትና በሶሻሊዝም መካከል ያለውን ልዩነት ማሳየት እፈልጋለሁ፡፡ ጎሠኝነት በተወሰነ
አካባቢ ብቻ የሚቀርና አካባቢ ቀመስ ነው፡፡ ሶሻሊዝም ግን ዓለም ዓቀፋዊ ነው፡፡ …እንደ ዩንቨርስቲ
ተማሪነታችንና እንደ እጩ ምሁርነታችን የሕብረተሰባችንን አቋም ከመደብ አንፃር መተንተን እንጂ በጎሣ መከፋፈል
አይገባም›› ማለቱ ይታወሳልና፡፡
የህወሓት-ውልደት
ዋለልኝ መኮንንን ‹‹የብሔር ጭቆና›› ትንተናን መሰረት ያደረጉ ጥቂት የማይባሉ የፋኖ ድርጅቶች መመስረታቸው
አይካድም፡፡ ከእነዚህም መንግስታዊውን ሥልጣን ለመጨበጥ የበቃው ህወሓት አንዱ ነው፡፡ የአማራና ትግሬ
ጨቋኝነትን የሚያውጀው ጽሑፍ በተሰራጨ በአምስተኛው ዓመት የትግርኛ ተናጋሪውን ብሔራዊ ጭቆና
ለማስረገጥ ጽሑፉን እንደ ሰነድ ማስረጃ ቆጥረው ‹‹ትግራይን ነፃ እናወጣለን!›› ያሉ ፋኖዎች ነፍጥ አንግበው በረሃ
ቢወርዱም፣ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ዓመታት አካባቢ ‹‹እንታገልለታለን›› በሚሉት ዘውግ ተወላጆች ሳይቀር
መናፍቅ ተደርገው መወገዛቸው ይታወሳል፡፡ ደራሲና ገጣሚ አስማማው ኃይሉም ‹‹ኢህአሠ›› በተባለው መጽሐፉ
እንዲህ ይለናል፡-
‹‹በ1969 ዓ.ም አጋማሽ አካባቢ በእምባ ሰገንይቲ ወረዳ ነበለት አካባቢ ሽምዕጭ ተብሎ በሚጠራው መንደር
የህወሓትና የኢሕአሠ አባላት ሕዝብን ለመቀስቀስ ተገኝተው ነበር፡፡ ሁለቱም ቡድኖች የድርጅታቸውን ዓላማ
ካስረዱ በኋላ ያካባቢው አዛውንት ማሳረጊያውን ንግግር አደረጉ፡፡ አዛውንቱ መሔድ የሚሳናቸው ስለነበሩ ሰዎች
ደግፈው ወደ በቅሏቸው እንዲያወጧቸው ከጠየቁ በኋላ የሚከተለውን ንግግር አደረጉ፡፡ ወደ ህወሓት አባላት
እጃቸውን ዘርግተው ‹እናንተ ከሆዳችን የወጣችሁ ልጆቻችን ናችሁ›፤ ወደ ኢሕአሠ አባላትም ፊታቸውን አዙረው
‹እናንተ ደግሞ ከሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት መጥታችሁ ለእኛ ስትሉ ነው የምትታገሉት፡፡ የሆነው ሆኖ እኛ የትግራይ
ሰዎች ሆነን ስንቀር ኢትዮጵያ ከማን ጋር ልትቀር ነው? ስለሆነም እኛ ኢትዮጵያዊ ከሚል ጋር ነው የምንወግነው›
ሲሉ ሃሳባቸውን ሰነዘሩ፡፡›› (ገፅ 235)
ህወሓት በትግራይም ሆነ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል የነበረውን አገዛዛዊ ጭቆና፣ የብሔር አስመስሎ እስከ መገንጠል
ቢንደረደርም፣ የገጠመው ተቃውሞ ፕሮግራሙን ለመከለስ አስገድዶታል፡፡ ዘግይቶ ላገኘው ድጋፍም ቢሆን
ከዘውግ ተኮሩ ተረት-ተረት ይልቅ አምባ-ገነናዊው የደርግ አስተዳደር የወለደው ሽብርና ጭፍጨፋ የተሻለ
ጠቅሞታል፡፡ ለዚህም በዛሬይቷ ትግራይ ከሶስት ያላነሱ ፀረ-ህወሓት ድርጅቶች መኖራቸው ማሳያ ይሆናል ብዬ
አስባለሁ፡፡
በሌላ በኩል ከህወሓት ምስረታ አንድና ሁለት ዓመት አስቀድሞ ወደ አደባባይ የመጡት ኢህአፓና መኢሶን የትግል
አጀንዳቸው የመደብ ቅራኔ ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ ይህ ግን በወቅቱ ከህወሓትም በከረረ መልኩ ‹‹የብሔር ጥያቄ
በመገንጠል ብቻ ነው የሚፈታው›› የሚል እምነት ተከታዩ ኦነግን ህልውና አያስክድም፡፡ እዚህ ጋ የምንመለከተው
ሌላኛው ግራ አጋቢ ጉዳይ የመጀመሪያው የቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን የ‹‹መሬት ላራሹ››ን ሠልፍ
(በ1957 ዓ.ም) አስተባብሮ የሕግ-መወሰኛው ምክር ቤት ድረስ የመራው ባሮ ቱምሳም (በአብዮቱ ሰሞን የኢጭአት
የአመራር አባል ነበር) ሆነ፤ የመኢሶኑ ቁልፍ ሰው እንደሆነ የሚነገርለት ኃይሌ ፊዳን የመሳሰሉ የኦሮምኛ ቋንቋ
ተናጋሪ ልሂቆች፣ ከኦነግ በተቃራኒው ከብሔር ይልቅ የመደብ ጥያቄ አቀንቃኝ የነበሩ መሆኑን ነው፡፡ በነገራችን ላይ
2
 በግሌ ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያዊብያኔ እነዋለልኝ የለጠጡትንና ያጎኑትን ያህል እንኳባይሆንም እንደገና መከለስ
እንደሚያስፈልገው አምናለሁ፡፡
የሆነው ሆኖ ህወሓት መንግስታዊውን ሥልጣን በጨበጠ ማግስት ‹የሰነበተውን የብሔር ቅራኔ በማያዳግም ሁኔታ
የሚፈታ› ሲል ያንቆለጳጰሰውን ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝም ቢተገብርም፤ ከዚሁ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮችን
የመግታት አቅም እንደሌለው ለማረጋገጥ የአንድ እጅ ጣቶች ያህል ዓመታት እንኳን አልፈጀም፡፡ በደቡብ በጉጂ እና
ጌዲዮ፣ በጉጂ እና ቡርጂ፤ በጋምቤላ በአኝዋክ እና ኑዌር፤ በቤንሻንጉል በጉምዝ እና በርታ መካከል የተከሰቱት
የይገባኛል ግጭቶች በማሳያነት ይጠቀሳል፡፡
የፌዴራሊዝሙ ቀዳዳዎች
ዘውግ ተኮር ፌዴራሊዝሙ፣ ገና ከጠዋቱ ለከፋ ዕልቂት ሊዳርግ እንደሚችል በማስታወስ ይሰሙ የነበሩ የተራዘሙ
ጩኸቶችን ችላ ብሎ ዛሬ ላይ ቢደርስም፤ ለፕሮፓጋንዳ በሸነቆራቸው ቀዳዳዎች እየገባ ያለው ከባድ ንፋስ ከራሱ
አልፎ ሀገሪቷንም ከበታኝ አደጋ ፊት አቁሟታል፡፡ ለዚህም አገዛዙ የፈጠራ ትርክቱን ለማስረፅ የሄደበት የኑፋቄ
መንገድ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ በፓርቲው ካድሬዎች በኩል በየዕለቱ የሚዘራው የጥላቻ ፖለቲካ፣ ሐውልት
ማነፅ፣ ከፋፍሎ ማቆም እና መሰል ስልቱ በተጨማሪ ሜጋ በሚያሳትማቸው መጻሕፍት እልቂት ጠሪ ዘውግ ተኮር
ቅስቀሳዎችን እስከማሰራጨት መድረሱን ተመልክተናል፡፡ ለአብነትም የሚከተለውን ግጥም ልጥቀስ፡-

“ነፍጠኞች እቤታቸው በክብር ይጎለታሉ፣
እኛን በኃይል አስገድደው ያሰራሉ፣
ቁጥቋጦ እንደምትመነጥረው መንጥራቸው
ወደመጡበት ወደ ሸዋ አባራቸው፡፡” (“ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” ቅፅ 3፤ ገፅ 145)
ግና ‹‹ሸዋ›› ሱዳን ወይም ግብፅ አይደለምና ዛሬ ከጉራፈርዳ እስከ ደንቢዶሎና ጊምቢ ለተተገበረው የማባረር ዘመቻ
ዋነኛው ተጠያቂ የሥርዓቱ ኤጲስ ቆጶሳት መሆናቸውን ግጥሙ ያስረግጣል፡፡ በግልባጩ እነዚህ ሰዎች በ97ቱ
ምርጫ ዋዜማ፣ ሚያዚያ 30 ቀን መስቀል አደባባይ ቅንጅት በጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ፣ አቶ በድሩ አደም
‹‹ወደመጡበት እንመልሳቸዋለን›› ማለታቸውን፣ ወደ ዘውግ ጥላቻ ከመቀየራቸውም በላይ፣ የቅንጅቱን አመራሮች
ለቅመው ካሰሩ በኋላ የሰውየውን ንግግር ‹‹የዘር ማጥፋት ሙከራ!›› ሲሉ ለመሰረቱባቸው ክስ በማስረጃነት
ማቅረባቸውን አስታውሳለሁ፡፡ በዚያው ሰሞን አቦይ ስብሃት ነጋም የብአዴን ጓዶቻቸውን ‹‹እኛ ወደመቀሌ
ስንባረር፤ እናንተን መንዝ ላይ አራግፈን ነው የምንሄደው!!›› አሉ መባሉም ጉዳዩ በራስ ላይ ሲደርስ ምን ያህል
አሳማሚ እና ለበቀል እንደሚያነሳሳ ሁነኛ ጥቁምታ ቢሰጥም፣ ገዥዎቻችን ትምህርት ሊወስዱበት አለመቻላቸው
ያስቆጫል፡፡ እንዲያውም ከምርጫ 97 በኋላ በዩንቨርስቲዎች ግቢ የሚነሱ ተቃውሞዎች ዘውግ-ተኮር ወደመሆን
ነበር የተሸጋገሩት፡፡ ኢህአዴግም ቢሆን በዩንቨርስቲዎች በተናጠል (በህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴን)
ስር ማደራጀት የጀመረው ከዚሁ ምርጫ በኋላ እንደነበረ አይዘነጋም፤ ለእንዲህ አይነቱ የፓርቲው ተልዕኮ ደግሞ
እንደ ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ አይነት የገዥው-ፓርቲ መንፈስ የሰረፀበት ‹‹ምሁር›› ጠቀሜታን ለመረዳት አሁን አዲስ
አበባ ዩንቨርስቲ ያለበትን ሁኔታ መቃኘቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ በርግጥ ባለፉት ሁለት አስርታት የህወሓት አባልና ደጋፊ
ተማሪዎች የግቢውን መንፈስ አይመረምሩም (አይሰልሉም) ነበር እያልኩ አይደለም፤ በግላጭ የጓደኞቻቸውን
እንቅስቃሴ እየተከታተሉ ሪፖርት ያደርጉ ነበርና፡፡ በአናቱም የዘውግ ተኮር ፖለቲካው መተግበር በጀመረበት ወቅት
ወደ ትምህርት ቤት የተላኩ ልጆች፣ ዛሬ ለዩንቨርስቲ መብቃታቸው፣ አጀንዳው በቅፅበት ሊፈፀም የመቻሉን እውነታ
በኦሮሚያ ሰሞኑን የተመለከትነው ቀውስ በቂ ማሳያ ይሆናል፡፡

3
 የተጭበረበረው አጀንዳ
‹የብሔር ጥያቄ ዋነኛው የቅራኔ ቅርፅ ነው› የሚለው ህወሓት ይህን ጥያቄ መፍታት ሥርዓታዊ ግብእንደሆነ
እስኪሰለቸን ቢደሰኩርም፤ አጀንዳውን ከማጭበርበሪያነት የዘለለ ዋጋ አልሰጠውም፡፡ እናም ታሪክ ቢያንስ በዚህ
በኩል በበጎ እንደማያስታውሰው ለመናገርም ብዙ ማስረገጫዎችን መጥቀስ አይገድም፡፡ አሁንም ኢትዮጵያን
እየናጣት ያለው፤ ጥያቄያችን አልተመለሰም› የሚሉ ብሔርተኛ ቡድኖች መበርከት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በስያሜ
ደረጃ እንኳን (መሬት ላይ ያላቸውን ጉልበት ትተን) ከአስራ አንድ የማያንሱ ተገንጣይ ንቅናቄዎች መኖራቸው
እውነት ነው፡፡ የእነዚህን ከኦጋዴን እስከ ጋምቤላ፤ ከቤንሻንጉል እስከ አፋር ድረስ ያሉ አማፅያን እንቅስቃሴን
የጥቂት ልሂቃን ቅብጠት አድርጎ መውሰድ ርትዕ አይሆንም (ስለምን ቢሉ ደርግም ህወሓትን የሚያስበው እንዲያ
ነበርና)፡፡ እናም ከትልቁ ኦሮሞ ጥያቄ መጠለፍ ጀምሮ፤ እነዚህ ጉዳዮች አስቀድሞ ግንባሩ የብሔር ጥያቄን
ለሥልጣን መወጣጫ ብቻ ለመጠቀም ማስላቱን ይጠቁሙናል፡፡
ሌላኛው ጭብጥ አሁንም ድረስ ማንነት ተኮር ጥያቄዎች አለመቆማቸው ነው፡፡ ከቅማንት እስከ ወለኔ እና ቁጫ
ድረስ ያሉት ‹‹ማንነታችን ታውቆ ዞን ይሰጠን›› ጩኸቶች ማቆሚያቸው የቱ ጋ እንደሆነ ራሱ ኢህአዴግም
የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ በግልባጩ ለእነዚህ ሶስት የማህበረሰብ ክፍሎች ጥያቄ በቅርቡ የሠጠው ምላሽ ጭፍለቃ
መሆኑን ስናስተውል፤ ‹ተነሳሁለት› ከሚለው የብሔር ጭቆናን ማጥፋት አኳያ የሚነግረን ሀቅ ሥርዓቱ የሄደበትን
ቁልቁለት ብቻ ነው፡፡
በሶስተኛነት ከዚሁ ጋር አያይዘን ልናነሳው የምንችለው ርዕሰ ጉዳይ የመገንጠል መብት ነው፡፡ ከዋለልኝ እስከ
ጥላሁን ታከለ እና ቱሞቱ ሌንጮ (ፕ/ር እንድሪያስ እሸቴ) ድረስ የነበሩ የዘመኑ ትውልድ መንፈስ ተርጓሚዎች
መገንጠልን ሕብረ-ሱታፌ (ሶሻሊስታዊ) ሥርዓት ለመገንባት መዳረሻ መንገድ አድርገው ቢያቀርቡትም፤ ጥራዝ
ነጠቆቹ ህወሓቶች ሕገ-መንግስቱ ውስጥ ቀርቅረውታል፡፡ ለዚህም እንደምክንያት ‹‹መገንጠልን ለመከላከል ነው››
ቢሉም፤ ከፌደራሊዝሙ አወቃቀር አኳያ ‹የማይተገበር መብት› ስለመሆኑ ብዙ ተብሏል፡፡ ይህንን ለማስረገጥ
በዋናነት ሁለት ነጥቦች ይነሳሉ፤ ‹እንደ ስታሊኒስቷ ሩሲያ ሁሉ መብቱ በሕገ-መንግስቱ ውስጥ ቢካተትም፣
የማዕከላዊ መንግስቱ ሥልጣን ፍፁማዊ መሆን እንዳይተገበር ያደርገዋል› የሚለው የመጀመሪያው ነጥብ ነው፡፡
ሁለተኛው የመብት አፈፃፀሙ ራሱ በተለያዩ አስገዳጅ ተዋረዳዊ ትግበራዎች መጠላለፉ ነው፡፡ በተለይም ሁለትና
ከዚያ በላይ ዘውጎችን ያቀፉ ክልሎች የመገንጠል ጥያቄ ቢያነሱ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው ለመረዳት የክልሎቹን
አወቃቀር መመልከቱ ብቻ በቂ ይመስለኛል፡፡ ከእነዚህ ሁለት ነጥቦች ስንነሳ የመገንጠል ግብ ያላቸው
እንቅስቃሴዎች በትጥቅ ትግል አገዛዙን ካላስወገዱት በቀር በሕገ-መንግስቱ መሰረት በሰላማዊ መንገድ ሊተገበሩ
አለመቻላቸውን እንገነዘባለን፡፡ ይህ ሁነትም ሥርዓቱ ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ያነበረው ከፋፍሎ
ለመግዛት እንጂ፤ እስክንደነቁር በጩኸት ስለሚነግረን ‹‹ጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች›› መብት ደንታ ኖሮት
እንዳልሆነ ያስረግጥልናል ብዬ አስባለሁ፡፡

ግን እስከመቼ?
በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ከአፄ ኃይለስላሴ ቀጥሎ ረዘም ላለ ዓመታት ሀገሪቱን የመምራት ዕድል ያገኘው
ኢህአዴግ የተሻለች ሀገር የመገንባት በርካታ ዕድሎችን አምክኗል፡፡ ወደሥልጣን በመጣ ማግስት ዘውገኝነትን
የመንግስታዊ መዋቅሩ ብቸኛ ገፅ ሲያደርገው፣ ከብዙ ጫፎች ከተነሳበት ከባባድ ተቃውሞዎች መሀል፡- ቋንቋ ተኮር
ፌዴራሊዝሙ ማሕበረ-ባሕላዊ መሰረቱ በጣም የተሳሳተ መሆኑን እና የዘውግ ማንነትን ብቸኛው የክልሎች ድንበር
አሰማመር መነሻ ማድረግ ለእርስ በእርስ የዜጎች ትንቅንቅ ያጋልጣል የሚሉት ዋነኞቹ ነበሩ፡፡ ሥርዓቱ ይህን ጆሮ
ሰጥቶ ከማዳመጥ ይልቅ ቢያፈገፍግም፣ ያሳለፍናቸው ሃያ ሶስት ዓመታት በሞቶችና በመከራዎች የተፃፉ ኩነቶችን
አሳይተውናል፡፡ ‹‹ባለሥልጣን›› እና ‹‹ሥልጣን የለሽ›› (ባለቤትና መጤ) በሚል ጨዋታ፣ በየክልሎቹ የሚገኙ
4
 የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች ከክልሉየሥራ ቋንቋ ውጪ በመናገራቸው ብቻ፣ አንዳችም ተቋማዊ ውክልና እንዳያገኙ
ማድረጉ፣ ከየአካባቢዎቹ በግፍ ለተፈናቀሉት የማሕበረሰብ ክፍሎች ዋነኛው መነሻሆኗል፡፡ አዲሱን የአዲስ አበባ
የማስፋፊያ ዕቅድ ተከትሎ የተነሳው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞም ሌላ ቅርፅ ወደመያዝ መሻገሩ አንዱ ሰሞነኛ
ማሳያ ነው፡፡ በምዕራብ ወለጋ ለረዥም ጊዜ ኑሯቸውን መስርተው የነበሩት የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች አካባቢውን
ለቀው እንዲወጡ መገደዳቸው የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ፣ የአማራ ክልልን ጨምሮ የየክልሎቹ ዘውጎች ‹‹መጤ››
ያሏቸውን ማባረር ላለመጀመራቸው እርግጠኛ መሆን የምንችልበት ምንም አይነት ዋስትና የለንም፡፡ እናሳ! ይህ
አይነቱ ክልልን ከ‹‹መጤ›› ዘውግ የማንፃት ሂደት ማቆሚያው የቱ ጋ እንደሆነ ማን ሊገምት ይቻለዋል? ዘግናኝ ደም
መፋሰስስ ሳያስከትል ይህንን ክፉ ድርጊት መሻገር የምንችለው እንዴት ነው?
እንግዲህ ይህ ሁሉ የፍርሰት መርዶ እየተሰማ ያለው፣ የሥርዓቱ ሰዎችና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ለዚህ ከፍታ
የበቁበትን ሃያ ሶስተኛ የድል ዓመት በፌሽታ ለማክበር ደፋ ቀና በሚሉበት ዋዜማ ላይ ቆመን ቢሆንም ‹‹ጊዜው
ከቶም ቢዘገይ አልረፈደም›› እንዲሉ፤ ተገፍቶ ገደል ጠርዝ የተንጠለጠለውን የኢትዮጵያን ህልውና በደለደለ
መሰረት አፅንተን ለቀጣዩ ትውልድ ለማሻገር አንዳች እርምጃ መውሰዱ ብቸኛ አማራጭ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ለዚህ
ዘመን ለጣለው ትውልዳዊ የማንነት ዕዳ ክንውን ቀዳሚው ተግባር ኢህአዴግን ‹‹በቃህ!›› ብሎ ማስቆም እንደሆነም
መቀበል የሚያስቸግር አይመስለኝም፡፡ ግና፣ ይህ ሳይሆን በወታደራዊ ጡንቻ ካሳለፍናቸው ዓመታት ጥቂቱን እንኳ
እንዲሰነብት ከፈቀድንለት፣ የደም ባሕር ሲያጥለቀልቀን ቆመን ለመመልከት ተስማምተናል ማለት ነው

በዝዋይ ማረሚያ ቤት በፖለቲካ እስረኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን ህገወጥ ድርጊት አጥብቀን እናወግዛለን!!! -ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሠጠ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የትንሳዔን በዓል ምክንያት በማድረግ በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች እንዲሁም የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በያሉበት እስር ቤቶች ፕሮግራም አውጥቶ በቡድን በቡድን በመሆን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶችን ለማድረስ ችሎ ነበር፡፡ ከእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታችን በተጨማሪ ከፍተኛ አመራሩ አላማ ያሉበትን የአያያዝ ሁኔታ ለመረዳት ጭምር ነው፡፡
በዚህም መሰረት በተለይ በዝዋይ በፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚፈፀምባቸው ለመረዳት ተችሏል፡፡ በዝዋይ ማረሚያ ቤት በሚገኙ የፖለቲካ እስረኞችን እና ጋዜጠኞችን ዝዋይ የተመደበው የልዑካን ቡድን ጎብኝቶ ከመጣበት እለት ጀምሮ ደግሞ በእስረኞቹ ላይ ከፍተኛ የሆነ የአካል እንዲሁም የስነ ልቦና ችግሮች እየደረሱባቸው ይገኛል፡፡ ለዚህም የእስረኞች ቤተሰቦች ለጥየቃ በሚሄዱበት ጊዜ መጎብኘት እንደማይቻልና ይዘውት የሄዱትን ምግብ ይዘውት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡
እስረኞቹ የሚፈፀምባቸውን በደል ለማሳወቅ 3 ቀን የሚቆይ የርሃብ አድማ በማድረጋቸው የዝዋይ ማረሚያ ቤት ኃላፊ ከአራት ወራት በፊት ማንኛውም ቤተሰብ እስረኞችን ለመጠየቅ ወደዚህ ቦታ ድርሽ እንዳይል የሚል ማስጠንቀቂያ በመስጠታቸው የእስረኞች ቤተሰቦች ምን አድርገዋቸው እንደሆነ አላወቅንም በማለት በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ እስረኞቹ ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው ተጠብቆ ከቤተሰቦቻቸውና ከዘመዶቻቸው እንዲሁም ከጠበቆቻቸው ጋር የሚገናኙበት መንገድ በአስቸኳይ እንዲመቻች እንዲሁም በእስረኞች ላይ የተፈፀመው ሕገወጥ ድርጊት በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ ለሕዝብ ይፋ እንዲሆን እንጠይቃለን፡፡
በተለይም ጉዳዩ የሚመለከታችሁ ሀገር ዓቀፍና ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ደርጅቶች፤ ዲፕሎማቶች፤ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ኃላፊዎች፤ ጋዜጠኞችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ በእስረኞች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ህገ-ወጥ ድርጊት ለማስቆምና የፖለቲካ እስረኞችን ለመታደግ እንዲሁም የህግና የሞራል ግዴታን ለመወጣት እንድንረባረብ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ በውጭ ሀገር የምትኖሩ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ይህንን አስከፊ ድርጊት በማውገዝ ድምፃችሁን እንድታሰሙ እንጠይቃለን፡፡
ድል የሕዝብ ነው!!!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)
ግንቦት 11 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባUDJ-SEAL

Monday, 19 May 2014

ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ላለፉት ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን የአራተኛ ዙር ታጋዮችን አስመረቀ

May 18, 2014
የኢትዮጵያዊያንን ስቃይና መከራ ሊያቅብና እንባቸውን ሊየብስ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛው ሕወሃት የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደት ወደ ክብር ለመለወጥና የናቋትና ያዋረዷት በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ ዓላማየ ብሎ ምሎ ዱሩ ቤቴ ካለ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በቃሉ መሰረት አራተኛውን ዙር የታጋዮች የምረቃ በአል ሚያዚያ 26 2006 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ማክበሩን አስታወቀ። ይህ የአራተኛው ዙር ስልጠና በሰልጣኞች ቁጥርም ሆነ በስልጠናው ጥንካሬ ካለፉት ሶስት ዙሮች በእጅጉ የተለየ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ያለውን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጅ በመጠቀም መረጃን መቀበልና ማስተላለፍን የጨመረም እንደነበር ተያይዞ ተጠቅሷል።Ginbot 7 Popular Force - GPF formed
በሀገር ውስጥ ፋሽስት ወያኔ እያደረሰው ባለው መረን የወጣ ግፍ የተበሳጩና ሁሉም ልክ እንዳለው ለማሳየት ቆርጠው የተሰለፉት እነዚህ ምሩቅ ታጋዮች ከወታደራዊው ስልጠና በተጨማሪ የፖለቲካ፣ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ሌሎችንም ተያያዥ ክህሎቶችን በበቂ ሁኔታ እንደቀሰሙም ተጠቁሟል። ስልጠናው ታጋዮቹ ወደፊት ከሚያጋጥማቸው ጠንካራ ፈተናና ከሚሰለፉበት ጥብቅ ግዳጅ አንጻር በቀላሉ ተስፋ እንዳይቆርጡ ለማድረግ በአካልም ሆነ በመንፈስ ዝግጁ እንደሚያደርጋቸው የተገለጸ ሲሆን የተጀመረው ሕዝባዊ ትግል በግለሰብ ደረጃ ሳይሆን በጋራና በተቀነባበረ ሃይል ለድል እንደሚበቃና ይህን የጋራ ሃይል በጠነካራ እጆች ላይ ላመስቀመጥም የተሰጠው ስልጠና ከበቂ በላይ ነበር ተብሏል።
ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በሀገር ውስጥ እንደማእበል እየገነፈለ ያለውን የአታግሉን የሕዝብ ጣያቄ በተደራጀና በተቀነባበረ መንገድ በተገቢው መልኩ ለማስተናገድ እንዲችል እንደ ድርጅት ከመቼው በላይ ራሱን እያደራጀና እያጠነከረ እንደሚገኝና ምቹ አታጋይ ተቋም ሆኖ ለመውጣት ሌት ተቀን እየደከመ መሆኑም ተያይዞ ተጠቅሷል። በታጋዮች ስልጠና ወቅት የተገኙ አንዳንድ የክብር እንግዶች እንደጠቆሙትም ”ባሁኑ ሰአት በሀገር ውስጥ ያለው ሁኔታ ከመቼውም በላይ የተመቻቸ ነው” ካሉ በሗላ ”ሕወሃት የሚተማመንበት ወታደሩ እንኳ ቁጥሩ ካልሆነ በቀር ልቡም ሆነ መንፈሱ ከሕዝብ ጋር ነው፤ በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች እየሆነ ያለው ወያኔ በእርጅና ዘምኑ ማብቂያ ላይ መሆኑን ነው የሚያመለክተው። ስለሆነም በመረጃ መንቀሳቀስና በትብብር መስራት ባጭሩ ለድል ያበቃል። ለዚህ ደግሞ የዛሬ ምሩቅ ታጋዮች ያገኙት ስልጠና ለታሰበው ስኬት የሚያበቃቸው ነው” በማለት ትዝብታቸውን አጠቃለዋል።
በምረቃው ማብቂያ ላይ ራሱን ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ብሎ ከሰየመበት ጊዜ ጀምሮ ለፋሽስት ወያኔ ከፍተኛ ስጋት እንደሆነ በማስረገጥ የጠቆሙት የሕዝባዊ ሃይሉ ሃላፊዎች፤ ከዚህ በፊት ፋሽስት ወያኔ በከፍተኛ ወጭና ጥንቃቄ ሕዝባዊ ሃይሉን ለማፈራረስና ለማትፋት በከፍተኛ ሁኔታ የሰራ ቢሆንም በሕዝባዊ ሃይሉ መረጃና ደህንነት ክፍል መክሸፉን አስታውሰው፤ ዓላማችንን ከዳር ለማድረስና የሕዝባችንን አርነት ለመመለስ ሀገራችንንም ከወያኔ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት በምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አስተላለፈዋል። ይህን ታሪካዊ ጥሪ ለመመለስና የሀገርና የትውልድ ጠላት የሆነውን ወያኔ ሕወሃትን ለማስወገድ አብረን እንቁም ሕዝባዊ ሃይላችንንም ተቀላቀሉ ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ምንጭ፣ ግንቦት 7

ፖሊስ በሶስቱ የዞን 9 ጦማርያን ላይ ሊያቀርብ ያሰበው የአሸባሪነት ክስ ውድቅ ሆነ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ሃሳባቸውን በድረ ገጽ ላይ የሚገልጹ ዘጠኝ ወጣት ጦማርያን ተይዘው በ እስር ላይ መሆናቸው ይታወሳል። ዘጠኙ ጦማርያን ወይም የድረ ገጽ ጸሃፊዎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበት ድረ ገጽ ዞን ዘጠኝ በመባል ይታወቃል። እራሳቸውንም ዞን 9 ብለው ነው የሚጠሩት። እናም ከዘጠኙ መካከል ስድስቱ በትላንቱ እለት አራዳ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር። ፖሊስ “ምርመራዬን አልጨረስኩም፤ ተጨማሪ ቀን ይሰጠኝ” በማለቱ ትላንት የተሰየሙት ዳኛ በጠዋቱም ሆነ በከሰአቱ ችሎት፤ የፖሊስን ጥያቄ ተቀብለው ተጨማሪ ቀን ሰጥተው ወጣቶቹም በእስር ቤት እንዲቆዩ ማዘዛቸው የሚታወቅ ነው። የትላንቱ ዳኛ ዛሬ አልነበሩም። የዛሬው ችሎት ዳኛ ሴት ናቸው። እነሱ ጋር ነበር 3ቱ ጦማርያን ዛሬ የቀረቡት።
በፎቶው ላይ አቤል፣ ማህሌት እና በፍቃዱ ይታያሉ። ከመታሰራቸው በፊት በሰላሙ ግዜ የተነሱት ፎቶግራፍ ነው። (የፎቶ ምንጭ፡ ዞን ዘጠኝ ብሎገር)
በፎቶው ላይ አቤል፣ ማህሌት እና በፍቃዱ ይታያሉ። ከመታሰራቸው በፊት በሰላሙ ግዜ የተነሱት ፎቶግራፍ ነው። (የፎቶ ምንጭ፡ ዞን ዘጠኝ ብሎገር)
ዛሬ እሁድ የቀረቡት ማህሌትፋንታሁን፣በፍቃዱሃይሉእና አቤል ዋበላ ናቸው። በዚሁ የአራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ችሎት ሲቀርቡ፤ ዳኛው ከትላንቱ የተለየ ነገር እንደማያረጉ ና ፖሊስ የጠየቀውን ያስፈጽማሉ ተብሎ ነበር የተጠበቀው። ሆኖም የተጠበቀው ነገር አልሆነም። ዳኛዋ የፖሊስን ጥያቄ አልተቀበሉም፤ ብስራት ወልደሚካኤል ከአዲስ አበባ የላከውን የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ እናስነብባቹህ። እንዲህ ይላል…
ፖሊስ ሊመሰረት ያሰበው የሽብርተኝነት  ክስ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደረገ
ዛሬ እሁድ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. አራዳበሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃፍርድ ቤት 1ኛወንጀል ችሎት በፍቃዱ  ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ እና ማህሌት ፋንታሁን ከረፋዱ 4፡20 ቀርበውነበር፡፡ ይዟቸው የመጣውና እስካሁንምመደበኛ ክስያልመሰረተው የማዕከላዊ ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም፣ ጉዳዩከሽብርጋርስለሚያያዝተጨማሪየ 28 ቀናትየጊዜቀጠሮይሰጠኝሲልቢጠይቅምፍርድቤቱጥያቄውንውድቅአድርጎታል፡፡
ፍርድ ቤቱም”ከዚህ በፊትለ24 ቀናት አስራችሁ ያቀረባችሁት ከሽብርጋር የተያያዘ ባለመሆኑ እና ሌላ አዲስ  ሂደት ስለሌለ ከዚህ በፊት ያላቀረባችሁትን ከሽብር ጋር የተያያዘ  የሚለውን ጭብጥ አልቀበልም፣ ተጨማሪየ28 ቀናት የምርመራ ጊዜ የተጠየቀውምተገቢአይደለም” ካለ በኋላ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመስጠት ለእሁድ ግንቦት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ተለዋጭቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ያቀረበውን ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የሚውን  ውድቅ አድርጎታል፡፡
ትናንትግንቦት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. የነበረው የ 6ቱ ጋዜጠኞች እና ብሎገሮች ፖሊስ ጉዳዩን ከሽብር ጋር  አያይዞ ተጨማሪ የ28 ቀናት የጠየቀው ተፈቅዶለት ለሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ተለዋጭ ቀነቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ትናንት የነበረው የ6 ቱን ጉዳይ የተመለከተው ዳኛ ወንድ ሲሆን የዛሬውን ጉዳይ የተመለከተችው ዳኛ ሴት መሆኗ ተጠቁሟል፡፡
በቀጣይ የምናገኛቸውን ተጨማሪ ዘገባዎች ይዘን እንቀርባለን። ተከታተሉን።