ኢሳት ዜና :-ከማንነት፣ ከልማትና መልካም አስተዳዳር ጋር በተያያዘ በአርባምንጭ እስር ቤት የታሰሩ የ232 የቁጫ ወረዳ ነዋሪዎች ስም ዝርዝር የወጣው ከራሳቸው ከእስረኞች ነው። ለኢሳት ከተላከው ስም ዝርዝር ለመረዳት እንደተቻለው አብዛኞቹ እስረኞች አርሶ አደሮች ቢሆኑም፣ 5 የሃይማኖት አባቶች፣ 7 መምህራን፣ 6 ነጋዴዎች፣ 25 ተማሪዎች፣ 22 በልዩ ልዩ የመንግስት ስራ ላይ የሚገኙ፣ 5 መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩና አንድ ፖሊስ ይገኙበታል።
ከእስረኞች መካከል 27ቱ እድሜያቸው ከ60 እስከ85 የሚጠጋ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ከ50 በታች ናቸው።፡ በጸታ ደረጃ ደግሞ 7ቱ ሴቶች ናቸው። በትምህርት ደረጃም ፒ ኤች ዲ፣ ማስተርስ እና የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ምሁራን ታስረዋል።
ካልተሰሩት ነገር ግን ከስራ የተሰናበቱ 6 ፖሊሶች በዝርዝር ውስጥ ሲካተቱ፣ ከ20 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከስራ መባረር እስከ ወር ደሞዝ ቅጣት እንደደረሰባቸው ተመልክቷል። 17 ሰዎች ደግሞ የእስር ጊዜያቸውን አጠናቀው በተለያየ ቅጣት ተለቀዋል።
የስም ዝርዝሩ ከሰኔ 28/2005 ዓ.ም እስከ ጥር 13/2006 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የታሰሩና የተከናወኑ ድርጊቶችን የሚዘረዝር ነው።
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ክልል ተወካይ አቶ ዳንኤል ሽበሺ በእስር ላይ የሚገኙት የቁጫ ነዋሪዎች ከ400 በላይ ይደርሳሉ
No comments:
Post a Comment