ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የምስራቅ ኢትዮጵያ ወኪል እንደዘገበው በምስራቅ ሃረርጌ ኦሮምያ ቆላማ ክፍል በሚገኙ
ግራዋ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ፣ ፈዲስ ፣ ሚዲጋ እና ሚደጋ ቶላ ወረዳዎች የተከሰተው ረሃብ አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር ህዝቡን ለስደት ሊያደርገው ይችላል።
ባለፈው እሁድ 50 የሚሆኑ የወረዳው ህዝብ ተወካዮች ሀረር ከተማ በመግባት አቤቱታቸውን ያሰሙ ሲሆን፣ ተወካዮቹ ህዝቡ አንድ ጊዜ ነቅሎ ከመሰደዱ በፊት
መንግስት እርምጃ ይወስድ ዘንድ ተልከው መምጣታቸውን ገልጸዋል። በአካባቢው ከፍተኛ ረሃብ በመግባቱ ህዝቡ የሚበላውን እንዳጣ መናገራቸውን ተከትሎ የክልሉ
ባለስልጣናት በተወሰኑ መኪኖች በቆሎ እና ዘይት ጭነው ወደ ወረዳዎች ተንቀሳቀስዋል። ችግሩን አጥንተን አስፈላጊው እርዳታ እንዲመጣ እንደሚገኝ ቃል መግባታቸውንና
ህዝቡ ባለበት ሆኖ እርዳታ እንዲጠይቅ ተማጽነዋል።
No comments:
Post a Comment