በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ ከማንነት ጋር በተያያዘ የተነሳው ተቃውሞ መፍቴ አጥቶ እንደቀጠለ ባለበት ወቅት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን የአነጋግረናቸው የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል።
በዛሬው እለት በርካታ የአገር ሽማግሌዎች የጸጥታ ሀይሎች እያደረሱባቸውን ያለውን ስቃይ ለማስታወቅ በጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጽህፈት ቤትና በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቢገኙም የሚያነጋግራቸው አጥተው ተመልሰዋል። አገር ሽማግሌዎቹ ጉዳያቸውን ለጠ/ሚንስተሩ ለማምልከት በተደጋጋሚ ወደ አዲስ አበባ ቢጓዙም እስካሁን የሚቀበላቸው አላገኙም።
እንዲሁም ዛሬ ጠዋት ቀደም ብሎ ፍርድ ቤት በዋስ የለቀቃቸው ከ40 በላይ የከተማዋ ታዋቂ ሰዎች ተመልሰው በአርባ ምንጭ እስር ቤት እንዲታሰሩ ተደርጓል። የሽማግሌዎቹ መታሰር በወረዳዋ ሌላ ውጥረት መፍጠሩም ታውቋል።
ጠበቆች፣ መምህራንና በርካታ ፖሊሶች ከህዝቡ ጥያቄ ጎን እጃቸው አለበት በሚል ታስረዋል።በአካባቢው የተሰማራው የፌደራል ፖሊስ ህዝቡን በዘር በመለያየት ግጭት ለመፍጠር እየሞከሩ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ፖሊሶቹ በወጣቶች ላይ ከፍተኛ ድበደባ እና የተለያዩ ስቃዮችን እየፈጸሙ መሆኑም ነዋሪዎች ገልጸዋል
በጉዳዩ ዙሪያ ወረዳውን ባለስልጣናት ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም
No comments:
Post a Comment