Monday, 19 May 2014

ፖሊስ በሶስቱ የዞን 9 ጦማርያን ላይ ሊያቀርብ ያሰበው የአሸባሪነት ክስ ውድቅ ሆነ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ሃሳባቸውን በድረ ገጽ ላይ የሚገልጹ ዘጠኝ ወጣት ጦማርያን ተይዘው በ እስር ላይ መሆናቸው ይታወሳል። ዘጠኙ ጦማርያን ወይም የድረ ገጽ ጸሃፊዎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበት ድረ ገጽ ዞን ዘጠኝ በመባል ይታወቃል። እራሳቸውንም ዞን 9 ብለው ነው የሚጠሩት። እናም ከዘጠኙ መካከል ስድስቱ በትላንቱ እለት አራዳ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር። ፖሊስ “ምርመራዬን አልጨረስኩም፤ ተጨማሪ ቀን ይሰጠኝ” በማለቱ ትላንት የተሰየሙት ዳኛ በጠዋቱም ሆነ በከሰአቱ ችሎት፤ የፖሊስን ጥያቄ ተቀብለው ተጨማሪ ቀን ሰጥተው ወጣቶቹም በእስር ቤት እንዲቆዩ ማዘዛቸው የሚታወቅ ነው። የትላንቱ ዳኛ ዛሬ አልነበሩም። የዛሬው ችሎት ዳኛ ሴት ናቸው። እነሱ ጋር ነበር 3ቱ ጦማርያን ዛሬ የቀረቡት።
በፎቶው ላይ አቤል፣ ማህሌት እና በፍቃዱ ይታያሉ። ከመታሰራቸው በፊት በሰላሙ ግዜ የተነሱት ፎቶግራፍ ነው። (የፎቶ ምንጭ፡ ዞን ዘጠኝ ብሎገር)
በፎቶው ላይ አቤል፣ ማህሌት እና በፍቃዱ ይታያሉ። ከመታሰራቸው በፊት በሰላሙ ግዜ የተነሱት ፎቶግራፍ ነው። (የፎቶ ምንጭ፡ ዞን ዘጠኝ ብሎገር)
ዛሬ እሁድ የቀረቡት ማህሌትፋንታሁን፣በፍቃዱሃይሉእና አቤል ዋበላ ናቸው። በዚሁ የአራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ችሎት ሲቀርቡ፤ ዳኛው ከትላንቱ የተለየ ነገር እንደማያረጉ ና ፖሊስ የጠየቀውን ያስፈጽማሉ ተብሎ ነበር የተጠበቀው። ሆኖም የተጠበቀው ነገር አልሆነም። ዳኛዋ የፖሊስን ጥያቄ አልተቀበሉም፤ ብስራት ወልደሚካኤል ከአዲስ አበባ የላከውን የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ እናስነብባቹህ። እንዲህ ይላል…
ፖሊስ ሊመሰረት ያሰበው የሽብርተኝነት  ክስ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደረገ
ዛሬ እሁድ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. አራዳበሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃፍርድ ቤት 1ኛወንጀል ችሎት በፍቃዱ  ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ እና ማህሌት ፋንታሁን ከረፋዱ 4፡20 ቀርበውነበር፡፡ ይዟቸው የመጣውና እስካሁንምመደበኛ ክስያልመሰረተው የማዕከላዊ ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም፣ ጉዳዩከሽብርጋርስለሚያያዝተጨማሪየ 28 ቀናትየጊዜቀጠሮይሰጠኝሲልቢጠይቅምፍርድቤቱጥያቄውንውድቅአድርጎታል፡፡
ፍርድ ቤቱም”ከዚህ በፊትለ24 ቀናት አስራችሁ ያቀረባችሁት ከሽብርጋር የተያያዘ ባለመሆኑ እና ሌላ አዲስ  ሂደት ስለሌለ ከዚህ በፊት ያላቀረባችሁትን ከሽብር ጋር የተያያዘ  የሚለውን ጭብጥ አልቀበልም፣ ተጨማሪየ28 ቀናት የምርመራ ጊዜ የተጠየቀውምተገቢአይደለም” ካለ በኋላ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመስጠት ለእሁድ ግንቦት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ተለዋጭቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ያቀረበውን ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የሚውን  ውድቅ አድርጎታል፡፡
ትናንትግንቦት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. የነበረው የ 6ቱ ጋዜጠኞች እና ብሎገሮች ፖሊስ ጉዳዩን ከሽብር ጋር  አያይዞ ተጨማሪ የ28 ቀናት የጠየቀው ተፈቅዶለት ለሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ተለዋጭ ቀነቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ትናንት የነበረው የ6 ቱን ጉዳይ የተመለከተው ዳኛ ወንድ ሲሆን የዛሬውን ጉዳይ የተመለከተችው ዳኛ ሴት መሆኗ ተጠቁሟል፡፡
በቀጣይ የምናገኛቸውን ተጨማሪ ዘገባዎች ይዘን እንቀርባለን። ተከታተሉን።

No comments:

Post a Comment