Friday, 23 May 2014

የአዳማው የአንድነት ሰልፍ ለሰኔ አንድ ተላለፈ

ኑና አብረን ድምጻችንን እናሰማ!!
የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የመሀል ቀጠና ፅ/ቤት ለግንቦት 10 ጠይቆትየነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ የተለያዩ ሰበቦችና ምክንያቶች ሲድበሰበስ ከርሞ ለሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም መተላለፉን የመሀል ቀጠና ጽ/ቤቱ በጠራው የአስቸኳይ ስብሰባ መወሰኑንናይህንኑ ውሳኔውንም በቀን መወሰኛ ደብዳቤው ላይ ገልጾ ለአዳማ መስተዳድር ከንቲባ አቶ አብረሐም ማስረከቡን በመረጃ አያይዞ ገልጧል፡፡በመሆኑም ሰኔ አንድ የአንድነት ደጋፊዎችና አባላት እንዲሁም የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የሆናችሁ ነጋዴዎች፣ተማሪዎችና ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል በሰልፋችን ላይ በመገኘት በገዢው ፓርቲ ላይ የተባበረ የተቃውሞ ድምጻችንን በሰላማዊ የትግል ስልት መንፈስ እንድናሰማ ጋብዘናችኋል፡፡ ሰኔ አንድ አይቀርም!
መነሻችን 4፡00ሰዓት ፣አዳማ ራስ ሆቴል (የቀድሞው መነን ሆቴል) ሆኖ፣ በፍራንኮ ሆቴል አርገን ወደ ምንጃር ጎዳና እንወጣና፤ ከሳር ተራ በአዲሱ ግንብ ገበያ ወደ መብራት ሐይል አቅንተን፤ ቁልቁል በአንደኛ መንገድ (ግርማሜ ነዋይ ጎዳና) ከደራርቱ አደባባይ ፊት ለፊት ካለው የፖስታ ቤት ሜዳ ላይ ማሳረጊያ እናደርጋለን፡፡ በጳጉሜ ሶስት የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት የሁለተኛ ዙር ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የሚሊየኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል ላይ ተመስርተን በሀገሪቱ ስላለው ኢፍሀዊ የመሬት ስሪት እንጮሀለን! በመልካም አስተዳደር ዕጦት ስለሚደረጉ የሙስና ወንጀሎች የተቃውሞ ድምጽ እናሰማለን!-ኑ ኑና አብረን ድምጻችንን እናሰማ!!10305607_726441860747899_1605322284415562929_n

No comments:

Post a Comment