Thursday, 24 July 2014

የፖሊስ ሃላፊዎች ጥያቄዎችን አነሱ

ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር በየደረጃው የሚገኙ የፖሊስ ሃላፊዎች ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ በሰንዳፋ እና በኮልፌ ፖሊስ ማሰልጠኛዎች
ከደህንነት ጋር በተያያዘ ስልጠና እየተሰጣቸው ሲሆን፣ የሰልጠና ተሳታፊዎች የሚያነሱዋቸውን  ጥያቄዎችን አሰልጣኞች መመለስ አለመቻላቸውን በስልጠናው ላይ የሚሳተፉ ፖሊሶች ለኢሳት ገልጸዋል።
ፖሊሶቹ ” መንግስትበተለይከሙስሊምሃይማኖትተከታዮችየሚነሳውንዲሞክራሲያዊየሆነጥያቄለምንአይመልስም?  ለምን በፖሊስተቋምላይየስራጫናእንዲበዛ ይደረጋል?ህዝቡበፖሊስላይያለውጥላቻ
ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፣እኛህብረተሰቡን በተገቢውመንገድማገልገልእንፈልጋለንና አስተዳዳራዊ ሁኔታዎች ይለወጡ” የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል። አሰልጣኞቹ የሚቀርቡት ጥያቄዎች ከአቅማቸው በላይ
መሆኑንና የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች የሚመልሱዋቸው እንደሆነ እየገለጹ ነው። በሚሰጠው መልስ ደስተኛ ያልሆኑት ፖሊሶች፣ ትክክለኛውን መልስ የሚሰጠው አካል ይመጣል ብለው ቢጠባበቁም
እስካሁን ድረስ አርኪ መልስ የሚሰጥ ባለስልጣን አላገኙም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከፌደራልጉዳዮችናኢህአዴግጽ/ቤትበተላለፈትዕዛዝመሰረትበአዲስአበባበሁሉምክ/ከተማዎችናበ116 ወረዳዎችየሚኖሩሙስሊምኢትዮጵያውያንንለማደንእንቅስቃሴ
እንዲጀመር ትእዛዝ መሰጠቱ ታውቋል።ትእዛዙየተሰጠውለሁሉምከፌደራልእስከወረዳድረስለሚሰሩየኢሀአዴግአባላትሲሆንየጽ/ቤትሃላፊዎችበየጽ/ቤታቸውየሚገኙአባላትንበመጥራት
ስለወጣው ትእዛዝ ገልጸውላቸዋል፡፡  የቀበሌመታወቂያየሌለውሙስሊምታፍሶእንዲታሰርናወደመጣበትአካባቢእንዲሸኝይደረጋል፡፡
ይህንንልዩተልዕኮየሚመሩትበየክ/ከተማውናበየወረዳውየሚሰሩበጥቅምየተሳሰሩሙስሊሞችናቸው ሲሉ ምንጮች አክለዋል፡፡  ባለፉት 3 ቀናት የተለያዩ የደህንነት አባላት በሚያውቁዋቸው
ሙስሊሞች ዘንድ በመደወል ለማስፈራራት መሞከራቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
ባለፈው አርብ ኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች በረመዳን ጾም ላይ በሚገኙት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰዱት እርምጃ ጥቁር ሽብር ተብሎ መሰየሙ ይታወቃል። ኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች በቀሰቀሱት
ግጭት በርካታ ሙስሊሞች ተደብድበው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን፣ በብዙ መቶወች የሚቆጠሩት ደግሞ ታስረው ከፍተኛ የሆነ ስቃይ ከደረሰባቸው በሁዋላ ብዙዎቹ ተለቀዋል፡፡ በተለይ በሴቶች  ላይ የተወሰደው
እርምጃ አስከፊ እንደነበር የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

No comments:

Post a Comment