Saturday, 29 November 2014

በዛሬ ቅዳሜ የሚሊዮኖች ድምፅ የህሊና እስረኞች መርሀ ግብር የዞን 9 ዘጠኝ ጦማሪያንን ታስበው ይውላሉ


  • 1
     
    Share
10486455_735445756540361_3353896174709564280_n
በዛሬ ቅዳሜ የሚሊዮኖች ድምፅ የህሊና እስረኞች መርሀ ግብር የዞን 9 ዘጠኝ ጦማሪያንን ታስበው ይውላሉ፤ እንደሚታወቀው በቃሊቲ ያሉት እስር ቤቶች በተለያዩ ዞኖች ተከፋፈሉ ሲሆን፤ ከዞን አንድ እስከ ዞን ስምንት ይደርሳሉ፤ እኛ በታሰረችው ሀገር በሰፊው እስር ቤት የምንገኝ ደግሞ የዞን ዘጠኝ ታሳሪዎች ነው የምንባለው፤ ስለዚህ ሁላችንም ያለነው ዞን ዘጠኝ ውስጥ ነው፤ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ይህ እውነት ስለገለጡ ነው የታሰሩት።
የሚሊዮኖች ድምፅ የህሊና እስረኞች መርሀ ግብር ከተጀመረ ጀምሮ ብዙ አስደናቂ ነገሮች እየተስተዋሉ ነው ያሉት፤ በትናንትናው ዕለት የአንድነት አባላት ብቻ ተለይተው እነእስክንድር ነጋንና እነ አንዷለም አራጌን በቃሊቲ እንዳይጠይቁ ተከልክሏል፤ መከልከል ብቻ አይደለም ታግተው ውሏል፤ አብዛኞቹ ከሰዓት ላይ ሲለቀቁ፤ አራቱ ደግሞ ማታ ላይ ተለቋል፤ ትግስት ካሳዬ ምትባል የአንድነት የወረዳ አመራር አባል ደግሞ ስትፈታ እዚያው አሳድሯታል።
10408681_735445646540372_7964344976056987440_nታላቁ የህሊና እስረኛ እስክንድር ነጋም ‹‹በርቱ! እንቅስቃሴያችሁ ህጋዊና ሰላማዊ ይሁን እንጂ ትግላችሁን ቀጥሉ!›› የሚል መልዕክት አስተላልፏል። በተጨማሪም አሳሪዎቹ የማናገር ነፃነቱን እዚያው እስር ቤትም ውስጥ ሊገድቡት በመኮሩበት ሰዓት፤
‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል!›› በማለት አሁንም ለመብቱ ያለው ቁርጥ አቋም አሳይቷል። እስክንድር ቃሊቲ ውስጥ ሆኖ እንዲህ ካለ፤ እኛ በሰፊው እስር ቤት ያለነው ታሳሪዎች ምን እንጠብቃለን! እምቢ ለመብቴ እምቢ ለነፃነቴ እምቢ ለሀገሬ ማለት አለብኝ!
ሁላችንም የዞን ዘጠኝ ታሳሪዎች ነን!
Millions of voices for freedom – UDJ

No comments:

Post a Comment