Tuesday 13 January 2015

አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከሥልጣናቸው ተነሱ

 

  • 1584
     
    Share





Berehanu Adelo
(ዘ-ሐበሻ) ከጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በአንድ ላይ የደህዴን ፖሊት ቢሮ አባል የነበሩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክኒያት ድንገት ከስልጣናቸው መነሳታቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጹ::
የኢትዮጵያ አዕምሮአዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው ይሰሩ የነበረ ሲሆን ከዚያም ቀደም ብሎ የደቡብ ክልል ምክትል የፍትህ ቢሮ ሃላፊ ሆነው ሰርተዋል:: በሌላም በኩል በርከት ያሉ የስርዓቱ ተላላኪዎች ሃገርን በመልካም ሁኔታ የሚመራ ትምህርት ሳይሆን ተንኮል ይማሩበታል በሚባልበት የሲቭል ሰርቭስ ኮሌጅ አስተማሪ ሆነው ያገለግሉ ነበር::
የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ብርሃኑ አዴሎ በሃይለማርያም ደሳለኝ የተፈረመ ደብዳቤ በደረሳቸውና ከስልጣናቸው በተነሱበት ዕለት በርሳቸው ምትክ አቶ ግርማ በጅጋ ተሹመዋል::

No comments:

Post a Comment