Tuesday 13 January 2015

በአንድነት አባላት እንዴት inspired እነደሆንኩ! – ሶሊያና ሽመለስ (የዞን 9 ቦልገር)

ትላንትና ያየሁት የአንድነት ፓርቲ አባላት ፎቶ ጭንቅላቴ ውስጥ ተቀርጾ ዋለ፡፡ ፎቶው ላይ ምርጫ ቦርድ የጠራው አስገዳጅ ጉባኤ ላይ ለመገኘት መጥተው ፓርቲው ቢሮ ውስጥ መሬት የተኙ አባላት ፎቶ ነበር፡፡
አንዱን እዛ መሬት ላይ የተኛ አባል አሰብኩት፡፡
“Most probably” ብዙም የኢንተርኔት ተጠቃሚ አይደለም፡፡ ( ኦፍ ላየን ያለው ነገር ደሞ ኦን ላየን ካለው ይበልጥ ተስፋ ያስቆርጣል) አገር ቤትም ሁሉም ሰው ጸጥ ባለበት ዘመን፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ለመሆን በመድፈሩ፣ በማህበራዊ ኑሮው በሰፈሩ ብዙ እየከፈለ ነው ፡፡ በጉዞ ደክሞት መሬት ላይ ነው የተኛው። እናም በዚያ ትግል ውስጥ ፓርቲውን ለማዳን ተስፋ አድርጓል፡፡ በማግስቱ ስብሰባውን ሲካፈል የምርጫ ቦርድ ተወካይ ተለጣፌው የ20 ሰው ስብስብ የጠራውን ስብሰባ ለመካፈል በመሄዱ እንደማይመጣ ይሰማል፡፡ ይሄ በራሱ ተስፋ አስቆርጦ ብርር የሚያደርግ ንዴት ይፈጥራል፡፡ ነገር ግን አማራጭ የለም ይሞክራል፡፡ እሁድ ጠዋት አንደማንኛውም ሰው ለልጆቹ ጋር ያለነጻነት፣ ግን በሰላም ማሳለፍ ይችል ነበር፡፡ የሚብሰው ሰሞ የሚከፍለው መስዋእትነት ምናልባት ውጤት የለሽ ሊመስልም ይችላል፡፡ ፓርቲውን ሊያግዱበት ካልሆነም የቀረውን 4 ወር የህጋዊነት ጨዋታ ሲያጫውቱ ከርመው ባለቀ ሰአት ካሻቸው በሉ ተሳተፉ ብለው ሂደቱንም ውጤቱንም ሊቀሙት( ድሮ ውጤት ብቻ ነበር የሚቀሙት) እና ለራሳቸው ጥቅም ሊያውሉት ወይም ደሞ ጭራሽ ሊያባርሩት ይችላሉ፡፡ ግን ማቆም ምርጫ አይደለም፡፡
በአንድነት አባላት እንዴት inspired እነደሆንኩ!
ዝም ብሎ የሚገርመኝ ነገር እንደው እንደኛ በሽብር የተከሰሰ የተሰደደ ሰው ሳይቀር አነዚህ ሰዎች ትንሽ ቦታ ሊከፍቱ ይችላሉ ብሎ ተስፋ አድርጎ ይጠብቃል፡፡ እነሱ ጭራሽ ብቻቸውን ለመሮጥ ( ለማሸነፍ አላልኩም- እሱ ታወቀ ነው) ነው ያቀዱት ፡፡ ህግና ስርአቱ ቀርቶ ይሉኝታና ነውር አንኳን አያውቁም ፡፡
ውጤቱ ቀርቶ ሂደቱ የሚሰጠውን ትርፍራፌ እድል ለመጠቀም አንኳን የማይቻልባት አገር ሆናለች ኢትዮጲያ አሁን፡፡ የዛሬው አይነት ቀን ደሞ ትካዜን ይጨምራል ፡፡ እናም ለዚህ ትካዜ ምክንያት ከሆነኝ ኢህአዴግ በላይ ( አምባገንን አይን አውጣ ምኑ ይተከዝለታል? ) ምርጫ ቦርድ ነን ብለው የተቀመጡ ግለሰቦች ላይ ነበር፡። ማታ እንዴት ይተኛሉ ? እንዴት የሰፈር ሰው እና ጎረቤት ፌት ቀና ብለው ይሄዳሉ ? አንዴት ዴሞክራሲን የሚያህል ስም እና ስራ እየናዱ ፈገግ ይላሉ እያልኩ ሳስብ ነበር፡፡ አንደግለሰብ እንዴት ቢያስቡ ነው ያን ያህል የማይቆቁራቸው ? ( ስሜት እነዳለው ሰው ሳስባቸው ዋልኩ)

10888719_760787797339490_5698232838446960729_n
አንድነት ቢሮ ውስጥ መሬት ላይ ተኝተው የሚታዩት ጉባኤውን ለመስተፍ ከየክፍለሃገሩ የመጡ የአንድነት አባላት
10600483_760787794006157_8891944273890351365_n
አንድነት ቢሮ ውስጥ መሬት ላይ ተኝተው የሚታዩት ጉባኤውን ለመስተፍ ከየክፍለሃገሩ የመጡ የአንድነት አባላት

No comments:

Post a Comment