(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሚያ ተማሪዎች አመጽ በተቀጣጠለበት ሰሞን መንግስት አስሮ ለረዥም ጊዜ ክስ ሳይመሰርትበት የቆየው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ አበበ ገላው ያደረገውን አድንቀህ ሕዝብን ለማነሳሳት ተጠቅመህበታል እና ከኢሳት ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ጋር በፌስቡክ እና በስልክ አውርተሃል በሚል የሽብርተኝነት ክስ ቀረበበት::
እንደ ክሱ ዝርዝር ከሆነ
“ተከሳሽ (ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው) በሚጠቀምበት ማህበራዊ ድህረገአጽ በተለይም ፌስቡክ አድራሻው ተጠቅሞ በውጭ ሃገር የሚገኝ የሽብር ቡድኑ አመራር እና አባል ከሆነው አበበ ገላው በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት በጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ተከሶ በመዝገብ ቁጥር 112546 የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠው ጋር ግንኙነት በመፍጠር በቀን 01/9/2006 ዓ.ም በአቶ መለስ ላይ ያደረገው ተቃውሞ መስቀል አደባባይ ላይ ከሚደረግ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ የተሳተፈበት የተቃውሞ ሰልፍ የማይተናነስ ነበር:: አሁንም እንዲሁ ኦባማ ላይ ደግሞታል:: የአቤ ጩኸት ዝም ብሎ ያለመገዛት አንድ ድምጽ ብትሆን ለውጥ እንደምታመጣ በጽኑ የማመን ለውጥ አይመጣም ብሎ በተስፋ መቁረጥ ከመቀመጥ የራስን አስተዋጽኦ ማድረግ የተግባር ሰው መሆን ነው በማለት ከሽብር ቡድኑ አባል ጋር የአመጽ ጥሪ በማስተላለፉ”
የሽብር ክስ ተመስርቶበታል
No comments:
Post a Comment