Thursday, 18 February 2016

በምስራቅ ሐረርጌ ፌደራል ፖሊስ ሁለት አርሶ አደሮችን ገደለ – በጉራዋ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ተቃጠለ

Share1  511  0 
 Share0(ዘ-ሐበሻ) ትናንት የ60 ዓመት አዛውንት በተገደሉበእት የምስራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ወረዳ ዛሬ ደግሞ 2 ገበሬዎች በፌደራል ፖሊሶች መገደላቸው ተዘገበ::
የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች እንዳሉት ማሃዲ ሳኒ እና ሳፊ ኢብሮ የተባሉት አርሶ አደሮች በፌደራል ፖሊሶች የተገደሉት ዛሬ በከተማዋ በተደረገ ህዝባዊ ተቃውሞ ነው::
በምስራቅ ሐረርጌ በተከሰተ ሕዝባዊ ተቃውሞ በርካታ ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን አብዛኞች በህክምና ላይ እንደሚገኙ ታውቋል:: በዚሁ በጉራዋ ወረዳ ፌደራል ፖሊስ ትናንት እና ዛሬ የፈጸመውን ግድያ የተቃወሞ የአካባቢው ነዋሪዎች የፖሊስ ጽህፈት ቤትን ማቃጠላቸው ተሰምቷል:: ሰለፈኞቹ ፖሊስ ጣቢያውን ካቃጠሉ በኋላ እስረኞችን ለማስመለጥ መሞከራቸው ሲገለጽ እስረኞች ያምልጡ አያምልጡ ዘ-ሐበሻ ለማጣራት ያደረገችው ጥረት አልተሳካም::
በሌላ ዜና በም ዕራብ አርሲ የተነሳው የሕዝብ ተቃውሞ በኢዶ ከተማ ቀጥሎ ሕዝቡ ከፌደራል ፖሊስ ጋር ተፋጦ ይገኛል:: በተለይ የም ዕራብ አርሲ ግጭትን ወደ ዘር ግጭት ለማስፋት አንዳንድ ወገኖች ተቃውሞውን በመጠቀም እያደረጉት ያለውን ጥረት ይህን ትግል የሚመሩ ሰዎች ሊያስቡበት ይገባል የሚሉ የአካባቢው ነዋሪዎች አሉ::

No comments:

Post a Comment