Wednesday, 20 November 2013

ወደ ኢትዮጵያ ለነፃነት: ባርነትን ከሚያላምደን የተቃውሞ ትግል እንላቀቅ !ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት፣ሰሞኑን በወገኖችችን ላይ በደረሰው እና እየደረሰ ባለው ጥቃት ጥልቅ ሃዘን እና ቁጭት ተሰምቶናል። የዛሬውም ልዩ ጥሪያያችን ለመከራችን ምንጭና መነሻ የሆነውን ኃይል የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር ከስልጣን ማስወገድ ዋና እና ቀዳሚ የመፍትሄ ተግባራችን ሊሆን እንደሚገባ ለማሳሰብ ነው።
እኛ ኢትዮጵያውያን አገራችንን እና ወገናችን የምንወድ ሩህሩህ እና አዛኝ ሕዝብ ነን። በወገን ላይ መከራና ስቃይ ፣ግፍና ሞት ሲደርስበት በጣም እናዝናለን ፣እናለቅሳለን ፣ሆኖም ግን የዚህ ዓይነቱ ችግር እና ሰቆቃ እንዳይደርስብን ተገቢውን ንቃትና ጥንቃቄ አናደርግም፤ግፍና መከራም በሚከስትበትም ግዜ በአስቸኳይ መከራውን የሚያስቆም ቆራጥ እርምጃ አንወስድም። ይህ አንዱ አሳሳቢና መቀየር ያለበት ነባራዊ ዕውነታ ነው ። ለዚህም ነው ለዘመናዊው ቀስ በቀስ ባርነትንና የበታችነትን ከሚያላምደን የተኮላሸ የተቃውሞ የትግል ስልት እንላቀቅ የምንለው::
እስከዛሬ ሰልፍ ወጥተናል ፣መግለጫ የያዙ ደብዳቤዎች ጽፈናል፣ ይመለከታቸዋል ላልናቸው የዓለም መንግስታት እና ዓለማቀፋዊ ተቋማት አቤት ብለን አመልክተናል ፣በአንጻሩ የኢትዮጵያውያን መከራና ሰቆቃ እንዲሁም ብሔራዊ ውርደት እየጨመረ መጣ እንጂ መፍትሄ አልሆነንም። ወገኖቻችን በገሃድ በየአደባባይ ይደፈራሉ ይቀጠቀጣሉ፣እየታፈኑ ወዳልታወቀ ሥፍራ ይወሰዳሉ፣ ይታረዳሉ ፤ አቤት ባይ የራስ መንግስት የለንም ፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ነን ባይ ድርጅቶች እንዲሁም ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ፣ ሁሉም አንድ ላይ ያደሙ ይመስላል፣ አላየንም አልሰማንምን መርጠዋል፤ ይህ ለእንኛ እንግዳ ና አዲስ ሊሆን የሚገባ ጉዳይ አይደለም ፣በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መነሻ ላይ ጣልያን አገራችንን በወረረች ግዜም ሊግ ኦፍ ኔሽን የተባለው እና የዛሬው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገሮች አብዛኛዎቹ ፈታቸውን አዙረውብን ከጣልያን ፋሽስቶች ጎን ቆመው እንደነበረና ፣አርበኞቻችን ከውስጥ ባንዳዎቹ የዛሬ ገዢዎቻችን ወላጆች እና ወራሪ ፋሽስቶች ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀው በጀግንነት ነጻነታችንን ማስከበራቸው በታሪክ ተመዝግቦ የሚገኝ እውነታ ነው። ይህም ድል የተገኘው በራሱ የሚተማመንና ለራሱ ማንነት ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጥ ሕዝብ ስለነበረ ነው።
ስለዚህ ይህን መከራና ውርደት የሚያስቆም ለውጥ ለማምጣት ሁለት ነባራዊ ሁኔታዎች መቀየር አለባቸው ። አንደኛው እስከዛሬ የተለመደውና የሚመቸንን መፍትሄ ቢስ የተቃውሞ ሂደትን መቀየር ሲሆን ፣ሁለተኛው እየተባባሰ የመጣውን የኢትዮጵያውያንን ስቃይና መከራ በፍጥነት ማስቆም ነው። ይህም ተልዕኮ የሚሳካው ፣የችግራችን ምንጭ የሆነውን ፣ ሕዝብን እና አገርን ለባርነት ገበያ አቅራቢውን ደላላ የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር በኃይል ስናስወግድ ብቻ ነው። ይህን በዋናነት ውጤታማ ለማድረግ የሚቻለውም የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆነው ኢትዮጵያዊ ኃይል ሲነሳ ብቻ ነው። ይህም የሚሳካው ኢትዮጵያውያን ለራሳቻው ነፍስና ሕይወት ዋጋና ክብር ሲሰጡ ነው።
ከታሪካችን እና ከአርበኞቻችን ታሪካዊ ገድል በመማር ውጤት አልባ ተግባር ላይ ተሰማርተን ከመባዘን ወይም ለተወሰነ ግዜያዊ የቁጣ ማብረጃና የፖለቲካ ፍጆታ ከማሙዋላት ውጭ የህብረተሰባችንን መሠረታዊ ችግር በማይፈታ፣ ባርነትን ከሚያላምደን የትግል ስልት መላቀቅ አለብን። በመላው ዓለም የተቃውሞ ድምጻችንን ማሰማታችን ለተበደሉ ወገኖቻችን ድምጽ መሆናችን ተገቢ ተግባር ሆኖ ሳለ የሰቆቃ ህይወታችንን ግን እንደማይለውጠው በጽኑ ልንረዳ ይገባል። ይህ ዕውነታ የሚለወጠው የችግሩን ምንጭ ስናደርቅ ብቻ ነው ። ይህ ዓለም አቀፋዊ ችግራችን የአገር ውስጥ ነባራዊ ሁኔታ ነጸብራቅና ተቀጥላ መሆኑን በመገንዘብ ፣ የችግሩን መሰረት ማስወገድ አስፈላጊና ወሳኝ ነው። አማራጩ ከነፃነት ወዳጅ እና ቆራት የሆኑ ሕዝቦች የትግል ስልት በመማር ዋና የሰቆቃችንን መንስኤ የሆነውን የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባርን በአስቸኳይ አስወግዶ በምትኩ በሕዝብ ፈቃድ ወደ ስልጣን የሚመጣ ኢትዮጵያዊ ስርዓተ መንግስት መገንባት የሚሰችልን ሁለገብ ቆራጥ ትግል ማድረግ ብቻ ነው ።
ለዚህም ክቡር አላማ ባአገራችን ውስጥ በቆራጥነት እንድንታገል ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት ለሁሉም የሕብረተሰቡ ክፍል የትብብር ጥሪ እናቀርባለን። የህልውናችን ወሳኝ ኃይል ፈጣሪያችን እና እኛ ብቻ መሆናችንን ስንገነዘብ ያለመስዋዕትነት የለም ነፃነት ብለን ቆርጠን እንነሳለን።
ተነሽ ! ተነስ ! ለነፃነት
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት
ህርዳ 2006

No comments:

Post a Comment