Monday 18 November 2013

ዋ! አንቺ ሳውዲ ምድር!!

ዋ! ዋ! ዋ! አንቺ ሳውዲ ፤ የምድር ገሃነም ፤
በግፍ የቀዳሽ፤ ከንቱ ያስደፋሽ የአበሻን ደም፤
ሰውነት ያስተለተልሽ፤አጥንት የሰበርሽ፤በቁም የቀበርሽ፤
አንቺ ምድር ከቶ ስንቱን ገመና ሸሽጓል፤ቀብሯል፤ከርስሽ።

በደም የጨቀየው አሸዋሽ፤ በእንባ ያጎረፈው ጎዳናሽ፤
በንጹሃን ኤሉሄ፤ በለቅሶ የደነቆረው አድባርሽ፤
በሃጢያትሽ ስንክሳር የመከራ ደመና በላይሽ፤
እንደ ጆሚራ የሚራኮተው ነፍሰ በላ አሕዛብሽ፤
እንዴትስ ግፍሽን ተሸከሙት ሰማይና ምድርሽ፤
አንቺ ‘ቅድስት’ ወይስ ‘ሰዶም-ና-ገሞራ’ አፈጣጠርሽ።

አንቺ ፈጠገት ምድረ-በዳ፤ ከከርስሽ ነዳጅ ቢቀዳ፤
በረከትሽ እንዳይሆን ክፉ መርገምት የትውልድ ፍዳ፤
ካ‘በሉ ንጉሥ፤ ልጆችሽ ክደው የነብይሽን የቃል ዕዳ፤
አለቅጥ ሰክረው በንዋይ የሚዘርፉ ሕይዎት ምንዳ፤
ምስኪን አገልጋዮችን እያረዱ፤ በጐዳናሽ እንደ ፍሪዳ፤
ልጅ፤ሚስት፤እህት፤እናት ተቧድነው እሚደፍሩ በመደዳ፤
በክርስትና፤ እስልምና የተወገዙ እርኩስ ምግበረ ወራዳ፤
ውለታ፤ ወረታ ቢሶች ያልተማሩ የእምነት ፋይዳ፤
ሺህ ጨፍጭፈው የሚያግዙ፤ ጥገኛ አገልጋይ እንግዳ።
ዋ! ዋ! ዋ! አንቺ ምድር አለብሽ ብዙ፤ፍዳ፤ብዙ በቀል፤
ከአሸዋሽ የሰረገው ጥቁር ደም ከድፍድፍሽ ሲቀላቀል፤
በነዳጅ የሰከረው ዘላን ልጅሽ፤ንጉሥሽ ሳይዳኝ ሳይሸመግል፤
እንደ እንሰሳ ሰው ማጋዙን፤ መግደሉንም ቢቀጥል፤
በጫረው እሳተ- ገሞራ ለዘላለም ተለብልቦ እንዲቃጠል፤
በዶፍ ትጥለቅለቅ፤ በማዕበል፤ በመብረቅ ተንጫራ ትቀቀል፤
የኢትዮጵያ አምላክ ይፈርዳል፤ ሃያል ገድሉን ያሳያል።




No comments:

Post a Comment