Monday 25 November 2013

ዕንባሽ ተናገረ! አሥራዯው (ከፈረንሳይ)

ዘሇላ ዘሇላ ደብ ደብ በሚሇው፤
ጉንጭሽን ሸርሽሮ ቁልቁል በሚፈሰው፤
ሳግ እንቅ እድርጎ በሚተናነቅሽ፤
በ’ንባሽ እያጠቀስኩ ስንኝ ቋጠርኩልሽ፤
ቃል ኪዲን ነውና አንብቢው አዯራሽ::

ዕንባሽ ተናገረ !
ሆሄያት ቆጠረ፤
ውስጥሽን ፈልፍሎ እየመረመረ፤
ቃላትን አምጦ ስንኞች ቋጠረ፤
ምሥጢሩን አወራ - መዯበቁ ቀረ ::

አይምሮሽን ነድሎ - ልብሽን ሰርስሮ፤
ቆፍሮ ዐይኖችሽን - ጉንጭሽን ሸርሽሮ፤
አንጀትሽን ሞሽልቆ - ጨጓራሽን ልጦ፤
ቁልቁል በሚወርዯው ዯረትሽን አቋርጦ፤
ሳግ እንቅ እድርጎ በሚተናነቅሽ፤
በሚፈልቀው ኩሬ - እያጠቀስኩ በንባሽ፤
ጥቂት ቃል ጻፍኩልሽ፤
አንብቢው አዯራሽ ::

ዕንባሽ ተናገረ !
ፊዯላት ቆጠረ፤
ውስጥሽን ፈልፍሎ እየመረመረ
ቃላትን አምጦ ስንኞች ቋጠረ፤
ምሥጢሩን አወራ - ጮሆ ተናገረ ::



  2
ሃዘንሽ ፈንክቷት ብዕሬ ቆሰሇች፤
ከግራ ወዯቀኝ እየተወራጨች፤
ድምጿን ከፍ አድርጋ - እሪ ብላ ጮኸች፤
ባንቺ ዕንባ ተጠምቃ - ማተቧን ቋጠረች፤
ፊትሽን ሇማበስ - ሮጠች ተሯሯጠች፤
ሃቅሽን አውጥታ - ጻፈች ቸከቸከች::

ያይኖችሽን ኩሬ ነድሎ በሚፈልቀው፤
ጅረት እንዯ ዓባይ አቀብ በሚፈሰው፤
በሚገነፍሇው እያጠቀስኩ በ’ንባሽ፤
ይችን ጥቂት ስንኝ ላንቺ ቋጠርኩልሽ፤
በ’ንባ የጨቀየ የራሰ ነው ብሇሽ፤
እንዲትጠየፊ አንብቢው አዯራሽ ::

ዕንባሽ ተናገረ !
ፊዯላት ቆጠረ፤
ውስጥሽን ፈልፍሎ እየመረመረ
ቃላትን አምጦ ስንኞች ቋጠረ፤
ምሥጢሩን አወራ - ትንቢት ተናገረ ::

እናም :
ጻፍኩልሽ ! ጻፍኩልሽ ! እህቴ ልንገርሽ፤
እያጠቀስኩ በ’ንባሽ፤
ተመኝቼ ሳቅሽን ዲግም እንዲታሇቅሽ፤
እህቴ!


በሳውዱ አረቢያና፤ በመላ አረብ አገራት፤ ሇሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊ ወገኖቼ፤ ማስታወሻ ትሆን ዘንድ
የተቋጨች ::

ጥቅምት 21/2006 ዓ.ም (October 31/2013)

No comments:

Post a Comment