-በሪያድ የሚታየው ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ነው ይላሉ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን።
እሁድ 2 ኢትዮጵያን ሴቶች መክረይመንታ ሸባቢያ በሚባል ቦታ ላይ በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መገደላቸውን በአይኔ ተመልክቻለሁ ያሉ የሪያድ ነዋሪ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ሌላ ኢትዮጵያዊት ደግሞ በአካባቢው ከተሰማሩት ወታደሮች ጋር ስትነጋገር በብረት ተመትታ መሞቷን እና አንዲት ኢትዮጵያዊትም እንዲሁ የቀኝ እጇ ተቆርጦ በአካባቢያቸው እንደምትገኝ እኝሁ የአይን ምስክር ይገልጻሉ ከዚህ የከፋና የብዙ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ለአደጋ ያጋለጠ ክስተት መኖሩንም ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያን ይገልጻሉ። ወደ 50 የሚጠጉ መኪኖች ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉ ሰዎችን አሳፍረው አሚራ ኑራና መለዝ የሚባል ቦታ ላይ ላለፉት 17 ቀናት ቆመዋል። ሰዎቹ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸዳዱት መኪኖቹ በቆሙበት አካባቢ በመሆኑ አካባቢው በሽታ መበከሉን የአይን እማኞች ይናገራሉ። ህጻናት በተቅማጥ በሽታ እየተጠቁ መሆናቸውንም የአይን እማኞች ይናገራሉ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሪያድ አካባቢ በተፈጠረው ስሜት ህጋዊ ወረቀት ያላቸው ኢትዮጵያውያንም ስራ እንዳይዙ እየተደረገ በመሆኑ መቸገራቸውን ህጋዊ ወረቀት የያዙ ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።
ምንም እንኳ የኢትዮጵያ መንግስት ለማረጋገጥ በማይቻልበት መንገድ ከ20 ሺ በላይ ሰዎችን ማምጣቱን ቢናገርም በሪያድ መንፉሀ ካምፕ ውስጥ ያሉት ኢትዮጵያውያን ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነው።
No comments:
Post a Comment