በአምቦ ከተማና በሌሎች የኦሮምያ ክልል ውስጥ የዩኒቭርሲቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ያቀረቡት ሕገ-መንግሥታዊ ጥያቄ ያገኘው ምላሽ በጨካኙ የአግዓዚ ጦር አልሞ ተኳሾች በጥይት መደብደብን ስለሆነ፣ ይህንን አሰቃቂ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ ያውም ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰብአዊ መብት መከበር ግምባር ቀደም መመሪያ ሆኖ በዓለማችን ላይ በገነነበት ጊዜ በመፈፀሙ፣ ወንጀለኞች ከተጠያቂነት ሊያመልጡ አይችሉም። ይህንን የተገነዘበው የባእዳንን ዓላማዎች ለማስፈፀም በጫንቃችን ላይ የተኮፈሰው የወያኔ መንግሥት አገልጋዮቹ ለፈፀሙት ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ ወንጀሉን በመሸፋፈን የሕዝብ ትኩረት ወደ እርሱ ሙገሳ እንዲዞር እነሆ 23ኛውን የወረራ በዓሉን ሲያከብር በመፍጨርጨር ላይ ይገኛል። ነገር ግን ግንቦት 20 የኢትዮጵያ ውርደት ጥቁር ቀን ተብሎ መዘከሩ አይቀርም።
ወያኔና ከርሱ በፊት የነበሩት ሁለት መንግሥታት
ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ጀምሮ ጥቂት ምሳሌዎቸን ጠቅሼ በማወዳደር የወያኔን ውሸት ላንባብያን ላቅርብ፦
1.የ1997 ምርጫ አለደም መፋሰስ የሥልጣን ሽግግር የተደረገበት ታሪካዊ ወቅት ነው ሲል ነውረኛው የወያኔው አምባገነን መሪ መለስ ዚናዊ ሲመፃደቅ በኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ታይቷል። ያ አልበቃ ብሎት፣ ወያኔ በ99.6% አሸንፌያለሁ ብሎ የቀጠፈበት የ2002ቱ ደግሞ በጥራቱ እንከን ያልተገኘበት ምርጫ ነበር እያለ መለስ ዚናዊ ሲያፌዝብን አዳምጠናል። በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች፦ የሕዝብ ደምና ሕይዎት ተሰውቷል፣ የመራጮች ድምፅ ተሰርቋል፣ ድላቸው ተቀምቷል፣ አሸናፊዎች ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ተወርውረዋል፣ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ በተለይ ወጣቶች የምርጫውን መጭበርበር በአደባባይ ስለተቃወሙ በግፍ ታስረዋል። ይህንን አረመኔያዊ የወያኔ ፋሺስታዊ ተግባር፣ ታሪክ ምንጊዜም አይረሳውም።
2.የብሔር ብሔረሰቦች ጉዳይ ሲነሳ አፄ ኃይለ ሥላሴ በድል አድራጊነት ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ ሕዝባቸው በቆየው እምነቱ፣ ባሕሉና ልማዱ መሠረት መብቱ እንዲጠበቅለት ወዲያው አውጀዋል። በዘመነ መንግሥታቸው የባህል ሚዩዚየም እንዲከፈት አድርገዋል። አፄው ባመቻቹላው አዋጅ መሠረት፦ ሀ) በአዲሰ አበባ ጊፍቲ (እመቤት) ጂፋሬ የተባሉት ባለውቃቢ የጥንቆላ አገልግሎት ይሰጡ ነበር፤ አልተባበርህም ያሉትን አርበኛ አባታቸውን ፋሺስት ኢጣልያ ቁልቆል ዘቅዝቆ በመግደሉ ይህ እንደ ውለታ ተቆጥሮ፣ ወ/ሮ ጂፋሬ “የኢትዮጵያ ሀገር ፍቅር ማህበር” ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል፤ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ፣ ልዑል አልጋወራሽ አስፋወሰን በቀብር ሥነሥርዓታቸው ላይ መገኘታቸውን አውቀለሁ፤ ለ) አምቦ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ደንፋ እየተባሉ የሚጠሩ በንጉሠ ነገሥቱ የሚታወቁ ባለውቃቢ እንደነበሩ አውቃለሁ፤ አፄው አዘውትረው አምቦን ይጎበኙ ስለነበር፣ ደንፋ ፈረሰኞች እስከ ጊንጪ(36 ኪሎሜትር ከአምቦ) ድረስ ልከው እንደሚያሳጅቧቸው ይታወቃል፤ ሐ) ሕዝብ ታዋቂ የማምለኪያ ቦታዎች፣ የየረሩ ንጉሥ ተብሎ የሚጠራው ባለውቃቢ የሚኖርበት በአዲሰ አበባ አካባቢ፣ ሆራ አርስዴ በቢሾፍቱ፣ የአርሲ እመቤት መኖሪያ በአርሲ፣ ሶፍ ዑመር በባሌ እንደነበሩ ይታወቃል።
3.የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና ዛሬ መሬቱ የሚነጠቀው የኦሮም ተወላጅ አያት/ቅድመ አያት የአካባቢወ ሕዝብ ማንም ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ሳያዘው ለጥምቀት በዓል ወደ ጃንሜዳ እየጎረፈ እጅግ የሚማርኩ የየባህሉን ዘፈኖች፣ ጭፈራዎችና ውዝዋዜዎች መመልከት ለኢተዮጵያን ኩራትና ፈንጠዝያ፣ እስከ ዛሬም ለቱሪስቶች መስህብ ሆኖ በመገኘቱ የወያኔ መሪዎች ዶላር ያፍሱበታል። በሕግ የተደነገገ የአለባበስ ኮድ ስላለነበረ ሁሉም በየባህሉ ልብስ አጊጦ ጃንሜዳን አጥለቅልቆ ያውባት ነበር። በወያኔ አበረታችነት ሳይሆን እስካሁንም እንደዚያው ነው።
4.በደርግ ዘመነ መንግሥት የብሔር ብሔረሰቦች ኢንስቲቱት ተቋቁሞ ነበር። “የዘር የሃይማኖት ልዩነት አንሻም፣ ይላሉ ልጆችሽ ኢትዮጵያችን ትቅደም”፣ ተብሎም ተዘምሯል። የባህል ዘፈኖችና ቲያተሮች በየክፍላተ ሀገር አብበው ነበር።
5.የወያኔ ዘመነ መንግሥት እስር ቤቱ በኦረሚፋ ተናጋሪዎች ታጭቋል ተብሎ ተነግሮለታል… የብሔር ብሔረሰቦች ወያኔ ለፖለቲካ ፍጆታ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የማሞኛ በዓል ከመሆን አልፎ፣ የ83ቱንም ብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋዎችንና ልማዶች አቆይቶ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ የሚዘልቅ አይደለም።
6.ረሀብን በማስወገድ ረገድ ሶስቱም መንግሥታት ሀላፊነታቸውን ሙሉ በሙሉ አልተወጡትም። የአፄው አገዛዝ የወሎውን ረሀብ ለመሸሸግ መሞከሩ ሊወገዝ ይገባዋል። የደርግ መንግሥት ረሀብ በሀገሪቱ ውስጥ እያለ ሥልጣን ላየ የወጣበትን 10 ዓመት ለማክበር የአልኮል መጠጦችን ከውጪ ሀገር በዶላር ማስገዛቱ ያስወግዘዋል። ወያኔ የሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አሰመስግቤያለሁ እያለ ሲፎልልባት በቆየበት ሀገር 6.5 ሚሊዎን ረሀብተኞች ኸተባበሩት መንግሥታት የምግብ እረዳታ ይጠብቃሉ መባሉ የአገዛዙን ጭካኔ ያመለክታል።
7.የወያኔ መንግሥት መሪዎች ለሱዳን መሬት ቆርሰው ለመስጠት እየተሯሯጡ ነው። የቀድሞ መንግሥታት እንኳን ሊያደርጉት የማያስቡት ወራዳ ድርጊት በታሪክ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል
8.ወያኔ ኢትዮጵያን አስገንጥሎ ወደብ-አልባ ያደረጋት ሞራላዊም ሆነ ሕጋዊ ብቃት የሌለው ቅጥረኛ መንግሥት።
9.መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶችን ረገጣ በተመለከተ የወያኔ መንግሥት ሬኮርድ አሳፋሪና ዘግናኝ መሆኑን ዓለም ያወቀው ሐቅ ነው። እነዚህን መብቶች ለማስከበር የወያኔን አገዛዝ በተባበረ ተቃውሞ ማንበርከክ ግድ ይላል።
10. በአፄው ዘመነ መንግሥት በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመሥራት ጥናቱ ተጠናቆ ነበር፤ ሆኖም በገንዘብ እጦት ምክንያት ግድቡ አልተሰራም። የግብፅ ኤክስፐርቶችም በአባይ ወንዝ ላይ እስከ 40 ግደቦች ለመሥራት እነደሚቻል በጠናት አረጋግጠው፣ ችግሩ የገንዘብ ጉዳይ መሆኑን አስምረውበታል። የህዳሴው ግድብ የሌሎችን የልማት ፕሮጄክቶች በጀት የሚሻማ የመዝረፊያ ፕሮጀክት ከመሆኑም በላይ፣ በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል የሦስትኦሽ ወገን ውይይት ተደርጎ ስምምነት ካልተደረሰ በስተቀር፣ ውጤቱ ንትርክና አልፎም ወጣቱን ትውልድ በማያባራ ጦርነት ውስጥ መዝፈቅ ይሆናል። የአባይ ውሀ የገዘፈው ከአማራውና ከኦሮሚያ ክልሎች በሚያፈሱለት ገባር ወንዞች አማካይነት ነው። ታዲያ ሁለቱ ክልሎች ከህዳሴው ግድብ የሚያገኙት ድረሻቸው ምን ያህል ነው? የብሔር ብሔረሰቦችን ከፋፋይ ፖሊሲ በውስጥ እያዳከመን እያለ ሁኔታውን በሚያባብስ ተግባር ላይ ማተኮር የሚያስከትለው አደጋ ከባድ ስለሚሆን በቀና መንፈስ መወያየት ለሁሉም ይበጃል።
አለመታመን፣ ለወያኔ ሰቀቀን
ዋሽቶ ማስዋሸት የወያኔ ቁንጮዎች የፖለቲካ መሳሪያ ሆኖ ቆይቷል። ሆኖም ዛሬ፣ ውሸት አገዛዙን የሕዘብ ተዓማኒነት አሳጥቶት ውድ ዋጋ እያስከፈለው ይገኛል። ጉዳቱ ለምንወዳት ሀገራችንም ጭምር ነው። ምክንያቱም የውጭ ጠላት መጥቶባት ክተት ቢታወጅ፣ የተለመደ ውሸቱ ነው በማለት ወያኔን የሚያምን ኢትዮጵያዊ ስለማይገኝ በቆየው ባህላችን መሠረት ሆ! ብሎ የሚነሳና አጥቂውን ለመፋለም ፈቃደኛ ተዋጊ እንደማይገኝ አምናለሁ።
በደርግ ዘመነ መንግሥት ማብቂያም ውሸት ስለበዛ፣ የአካባቢ ወጣቶች እንደተለመደው በአርበኝነት ወኔ ተነሳስተው የክተት ጥሪ ለመቀበል ፈቃደኞች ሁነው ስላልተገኙ፣ በቀበሌዎችና በገበሬ ማህበራት አስገዳጅነት እየታፈሱ ለለብ ለብ ሥልጠና ወደ ወታደራዊ ተቋማት ከተላኩ በሗላ በውጊያ ልምድ ያዳበረውንና በአረቦች ፔትሮ-ዶላር ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታቀውን የወያኔ ሠራዊት እንዲገጥሙ የተገደዱትንና የረገፉተን ወጣቶች ማሰታወስ ግድ ይላል። አስከፊው ሁኔታ እዚያ ደረጃ ላይ እሰኪደርስ ድረስ ደርግ ወያኔን እንደ ተራ ሺፍታ እያቃለለ ፕሮፓጋንዳውን ይነዛ ነበር። የሥልጣን ባለቤት የሆነውን ሕዝብ መዋሸት፣ የሚያስከትለው መዘዝ ብዙ ነው።
ከእንግሊዞች ፖለቲካ ምን ይማሯል?
በደርግ ዘመነ መንግሥት ማብቂያም ውሸት ስለበዛ፣ የአካባቢ ወጣቶች እንደተለመደው በአርበኝነት ወኔ ተነሳስተው የክተት ጥሪ ለመቀበል ፈቃደኞች ሁነው ስላልተገኙ፣ በቀበሌዎችና በገበሬ ማህበራት አስገዳጅነት እየታፈሱ ለለብ ለብ ሥልጠና ወደ ወታደራዊ ተቋማት ከተላኩ በሗላ በውጊያ ልምድ ያዳበረውንና በአረቦች ፔትሮ-ዶላር ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታቀውን የወያኔ ሠራዊት እንዲገጥሙ የተገደዱትንና የረገፉተን ወጣቶች ማሰታወስ ግድ ይላል። አስከፊው ሁኔታ እዚያ ደረጃ ላይ እሰኪደርስ ድረስ ደርግ ወያኔን እንደ ተራ ሺፍታ እያቃለለ ፕሮፓጋንዳውን ይነዛ ነበር። የሥልጣን ባለቤት የሆነውን ሕዝብ መዋሸት፣ የሚያስከትለው መዘዝ ብዙ ነው።
ከእንግሊዞች ፖለቲካ ምን ይማሯል?
ፀሐይ በእንግሊዝ ግዛት ከቶም አትጠልቅም (The sun never sets on the British Empire”) ተብሎ ሲጠቀስ ከልጅነቴ ጀምሮ እሰማ ነበር። የጥቅሱም ትርጉም፣ እንግሊዝ (ብሪቲሽ) የቅኝ ግዛቶቿን ጨምሮ በዓለማችን ላይ የነበራት ግዛት እጅግ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ፣ ጀምበር አንዱ ጋ ስትጠልቅ ሊላው ጋ ትወጣለች ማለት ነው። ዛሬ ደሞ፣ ጀምበር በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገሮች ላይ አትጠልቅም ለማለት እደፍራለሁ። አዎ! በያዝነው 21ኛው ክፍለ ዘመን ብዙ ቋንቋዎች እየከሰሙ በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንደሚተኩ አዝማሚያው በሂደት እየታየ ነው። አንዳንድ ጥናቶች ይህንኑ አዘማሚያ እያሳዩ ነው። የቋንቋዎች ብዛት እያነሰ በሄደ ቁጥር፣ የሰው ልጆች የርስ በርስ መግባባት እየጨመረ እንደሚሄድ የሚያጠራጥር አይመስለኝም።
እንግሊዞች ፖለቲካቸው የሚሳካላቸው በእራሳቸው ላይ መሳቅ ስለሚችሉ ነው ተብሎ ሲነገርም ሰምቻለሁ። በአሁኑ ጊዜ በአውሮፓ ህብረት ውሰጥ እንቆይ በሚሉት በሌበር ፓርቲ እና ሊብራል ፓርቲ ባንድ ወገን፣ እና የለም ከህብረቱ እንውጣ በሚለው የወግ አጥባቂው ፓርቲ መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ እንደሚሄድ የተገነዘቡት ሌሎች አውሮፓውያን፣ እንግሊዝ የሌለችበት ፖለቲካ አይጠፍጥም እያሉ ሲተቹ ይሰማሉ፡፤
በኢትዮጵያ ሀገራችንም ቢሆን አማራና ኦሮሞ የማይሳተፉበት የጋራ ፖለቲካ ከሌለ፣ ኢትዮጵያ እንደ ውሁድ ሀገር አትኖርም፤ የአፍሪካ ሕብረትም ሕልውና አጠራጣሪ ይሆናል። ታዲያ የጥቁሮቹ የኩሽ፣ የካምና የሴም ልጆች እጣ ፋንታ ምን ሊሆን ነው? አዎ! የዛሬን ስናነሳ ትናንትን ሳንረሳ አስታውሰን በሞኝነታቸን ላይ ስቀን ስህተታችንን አርመን ወደፊት መጓዝ ብልህነት ነው።
በሀገራችን በኢትዮጵያም ቢሆን የቋንቋዎች ብዛት እያነሰ መሄዱ አይቀሬ መሆኑን ካሁኑ አምኖ መቀበል ብልህነትና አርቆ አስተዋይነት ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም። በዚህ አስተሳሰብ በመጓዝ፣ ወያኔ ከጫነብን ደም አፋሳሽ የጎሳ ፖለቲካም ለመገላገል ፍቱን መድሐኒት አአአእናገኛለን።
በኢትዮጵያ ሀገራችንም ቢሆን አማራና ኦሮሞ የማይሳተፉበት የጋራ ፖለቲካ ከሌለ፣ ኢትዮጵያ እንደ ውሁድ ሀገር አትኖርም፤ የአፍሪካ ሕብረትም ሕልውና አጠራጣሪ ይሆናል። ታዲያ የጥቁሮቹ የኩሽ፣ የካምና የሴም ልጆች እጣ ፋንታ ምን ሊሆን ነው? አዎ! የዛሬን ስናነሳ ትናንትን ሳንረሳ አስታውሰን በሞኝነታቸን ላይ ስቀን ስህተታችንን አርመን ወደፊት መጓዝ ብልህነት ነው።
በሀገራችን በኢትዮጵያም ቢሆን የቋንቋዎች ብዛት እያነሰ መሄዱ አይቀሬ መሆኑን ካሁኑ አምኖ መቀበል ብልህነትና አርቆ አስተዋይነት ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም። በዚህ አስተሳሰብ በመጓዝ፣ ወያኔ ከጫነብን ደም አፋሳሽ የጎሳ ፖለቲካም ለመገላገል ፍቱን መድሐኒት አአአእናገኛለን።
የግል ሚዲያ/ነፃ ፕሬስ መታፈንና መዘዙ
በእድሜዬ ዘመን ያጋጠሙኝን ሶስት መንግሥታት ላንሳ። እነዚህም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ የመንግሥቱ ኃይለማርያም (ደርግ) እና እንደወራሪው ፋሺስት ጣልያን ኢትዮጵያውያንን በጥይት የሚቆላው ወያኔ ናቸው። ሦስቱም የነፃ ፕሬስና መሠረታዊ የሕዝብ መብቶች በተለያየ ደረጃም ቢሆን አንቀው በመያዛቸው ይታወቀሉ። በዚህ ምክንያት ሁለቱ ከሥልጣናቸው ተዋርደው ሊወድቁ በቅተዋል፤ ወያኔም ተመሳሳይ ዕጣ ይጠብቀዋል። ተንሽ ላብራራ፦
1. ጃንሆይ ያፈኑትን የፕሬስ ነጻነት ደርግም ወርሶ በሥራ ላይ ስላዋለው፣ በመንግሥት ሙሉ ቁጥጥር ሥር በሚገኙ ሚዲያዎች ለሚነዛባቸው የሃሰት ፕሮፓጋንዳና የስም ማጥፋት ዘመቻ ዓፄውም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው በነፃ ፕሬስ አማካይነት አጸፋዊ መልስ ለመስጠትና እራሳቸውን ለመከላከል አልቻሉም። ለምሳሌ ገና ወጣት ሳሉ በደጃዝማችነት ማዕረግ የአስበ ተፈሪ አውራጃ ገዢ ሆነው የከተማውን መሬት ሸንሽነው አላንዳች አድልዎ በርስትነት ማከፋፈላቸው፣ በ1946 ዓ.ም በፕሬዚዳንት አይዘንሐወር ጋባዥነት ከአሜሪካ ጉብኝት በሗላ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ፣ ሕዝቡ ታጥቆ በመነሳት በርሻ ልማት እንዲሰማራ ለማረስ ለሚፈልግ አትዮጵያዊ በነብስ ወከፍ አንዳንድ ጋሻ የገጠር መሬት እንዲሰጥ አውጀው እንደ ነበርና በዚህ አዋጅ የሰፈሬ ሲቪሎች ተጠቃሚ እነደበሩ አውቃለሁ፣ከኔ ጭምር በርካታ የአየር ሀይል መኮንኖች በሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ነጭ ሳር ተብሎ በሚጠራው ቦታ የተሰጠንን አንዳንድ መሬት ለማልማት በዝግጅት ላይ ነበርን። ጃንሆይ ሌሎች አያሌ አኩሪ ሥራዎችን ማከናወናቸው ሐቅ ነው፡፡ ነፃ ፕሬስ ቢፈቀድና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተፈጥረው ቢሆን ኖሮ እነዚህን አኩሪ ክንውኖችን በመጥቀስ ደጋፊዎቻቸው ሊከራከሩላቸው በቻሉ ነበር፡፡ ግና፣ የአምባገነን ትዕቢታቸው ስላልፈቀደላቸው ነፃ ፕሬስ መፍቀድ አልተዋጠላቸውም። ሰለዚህ ተዋርድው ከዙፋናቸው ወረዱ፤ የሌሎችም ዲክታተሮችም ዕጣ ፋንታ ከዚህ የተለየ እንደማይሆን ታሪከ አስተምሮናልና።
ብዙዎቻችን አጥብቀን የታገልንለት የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ንጉሠ ነገሥቱ በሕይዎታቸው እያሉ አቆጥቁጦ እያደገ ከእርሳቸው ሕልፈት በሗላ የእንግሊዞችን ሞዴል የመሰለ ሞናርኪ ሊፈጠር በቻለ ነበር። እኔም የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት እንዲፈጠር ሁኔታ እንዲመቻችና ነፃ ፕሬስ እንዲፈቀድ ያቀረብኩት ተማጽኖ በኢትዮጵያን ሄራልድ ላይ በ1966 ዓ.ም ታትሞ ነበር። ግን ሰሚ አላገኘም፤ ለዚያውም በዚያን ጊዜ ማን ተደማምጦ።
2. የደርጉ ሊቀ መንበር ሻለቃ መንግስቱ ኃይለማርያም ነሐሴ 12 ቀን 1966 ዓ.ም በቁጥር አ/ኮ/072/66 ለሁሉም ወታደራዊ ክፍሎችና በየጠ/ግዛቱ ለተቋቋሙት ንዑስ ኮሚቴዎች በያሉበት ከጻፈው ደብዳቤ ጋር አያይዞ ሀያ (20) ነጥቦችን የያዘ አንድ ገጽ የሥራ ዝርዝር መመሪያ ልኮ ነበር።
የአየር ኃይል ንዑስ ደርግ ከመመሪያው ውስጥ የተወሰኑትን መርጦ በተለይ በተራ ቁጥር 15 የተገለጸውን ቅድሚያ በመስጠት ነሐሴ 17 ቀን 1966 ዓ.ም. ቁጥር ፦ አሀ/ንደ/ // /66 በጻፈው ደብዳቤ የሚከተለውን መልስ ሰጥቷል፦
የአየር ኃይል ንዑስ ደርግ ከመመሪያው ውስጥ የተወሰኑትን መርጦ በተለይ በተራ ቁጥር 15 የተገለጸውን ቅድሚያ በመስጠት ነሐሴ 17 ቀን 1966 ዓ.ም. ቁጥር ፦ አሀ/ንደ/ // /66 በጻፈው ደብዳቤ የሚከተለውን መልስ ሰጥቷል፦
“ጉዳዩ፦ በአየር ኃይል ንዑስ ደርግ የቀረበ ሀሳብ
ለጦር ሀይሎች፣ ለፖሊስ ሠራዊትና ለብሔራዊ ጦር አጠቃላይ ደርግ
የአየር ሀይል ንዑስ ደርግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እንዲፈጸሙለት በአየር ሀይል ሠራዊት ስም ይጠይቃል፦
ለጦር ሀይሎች፣ ለፖሊስ ሠራዊትና ለብሔራዊ ጦር አጠቃላይ ደርግ
የአየር ሀይል ንዑስ ደርግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እንዲፈጸሙለት በአየር ሀይል ሠራዊት ስም ይጠይቃል፦
የተጀመረው ንቅናቄ “ብሔራዊ” እንዲሆን የሰላማዊ ሕዝብ ተካፋይ መሆን አለበት። ስለዚህ ለምሳሌ፦
ሀ. ከኢትዮጵያ ሠራተኞች አንድነት ማህበር፣
ለ. ከአሠሪዎች ማህበር፣
ሐ. ከዩኒቨርስቲ መምህራን፣
መ. ከዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣
ሠ. ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር፣
ረ. ከብሔራዊ ሸንጎ /ፓርላማ/
ሰ. በቻርተር ከሚተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች፣
ሸ. ደርጉ ከሚያምንባቸው ልዩ ልዩ ሌሎች ክፍሎች መወከል አለባቸው።”
ለ. ከአሠሪዎች ማህበር፣
ሐ. ከዩኒቨርስቲ መምህራን፣
መ. ከዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣
ሠ. ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር፣
ረ. ከብሔራዊ ሸንጎ /ፓርላማ/
ሰ. በቻርተር ከሚተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች፣
ሸ. ደርጉ ከሚያምንባቸው ልዩ ልዩ ሌሎች ክፍሎች መወከል አለባቸው።”
ቀን የደረስንበትን ውሳኔ ልዕልቲቱ ማታ ታሽረዋለች እያሉ ጠቅላይ ምኒስትሩ ያማርራሉ ተብሎ ስለተወራ፣ የታሠሩት ባለሥልጣኖች የቴሌቪዠን ሰዓት ተሰጥቷቸው አመራር ለመስጠት የተቸገሩበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንዲገልፁ ይደረግ ዘንድ በሻለቃ አዲስ ተድላ በኩል በጽሑፍ የቀረበው ሀሳብ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከባድ ስህተት ሊፈፀም ችሏል። ምክር አልሰማም ባይነቱ የደርግን መንግሥት አንኮታኮተው!
3. ነፃ ፕሬስ፦ በሰው ልጆች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሕይዎት ውስጥ ወሳኝ ሚና አለው። ነፃ ፕሬስ የዜጎች እኩልነት መለኪያ ነው፤ የግለሰብ ነፃነት ዋስትና ነው፤ የሥልጣኔ ምልክት ነው፤ የሕዘብን ብሶት መግለጫ ነው፤ የመልካም አስተዳደር መንገድ ጠቋሚ ነው። እነዚህን ለመረዳት ያልፈለገው የወያኔ አገዛዝ ገና ሥልጣን እንደያዘ ማበብ ጀምረው የነበሩትን ድንቅ ጽሑፎች አከሰመ፤ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት አውታሮች በሙሉ በአገዛዙ ጥብቅ ቁጥጥር ስር ዋሉ። ስለዚህ ከሕዝብ ተለይቷልና የሕወሐትም ሞት አይቀሬ ነው!
ወያኔና ሙስና
የወያኔ ቁንጮ መሪዎችና ቡችሎቻችው ከማይወጡበት የሙስና ባህር ውስጥ ገብተው በመስጠም ላይ ናቸው።
ኢኮኖሚያቸው በአሁኑ ጊዜ እየመጠቀ በመሄድ ላይ የሚገኘው የቻይና ኮሙኖስት ፓርቲ መሪዎች፣ በሀገራቸው ስር የሰደደ ሙስና የቱን ያህል እንዳሳሰባቸው ለመግለፅ እነዲህ ብለው ነበር፦
“ይህንን ጉዳይ ቆጣጠር ካቃተን፣ ፓርቲውን ለሞት ከሚዳርግ አልፎም ከሚገድል፣ ሀገሪቱንም ለውድቀት የሚያበቃ ሁኔታ ሊመጣ ይችላል (“If we fail to handle this issue well, it could prove fatal to the Party, and even cause the collapse of the Party and the fall of the state”. ) ብለው የፓርቲው ዋና ጸሐፊ የተነገሩትን እንደ አውሮፓ ኖቬምበር 15 ቀን 2012 “Reform in China vs crisis within EPRDF” በሚል ርዕስ ከተብኩትን ጽሑፍ በድረ-ገጾች ላይ አስለጥፌ አስነብቤያለሁ።
“ይህንን ጉዳይ ቆጣጠር ካቃተን፣ ፓርቲውን ለሞት ከሚዳርግ አልፎም ከሚገድል፣ ሀገሪቱንም ለውድቀት የሚያበቃ ሁኔታ ሊመጣ ይችላል (“If we fail to handle this issue well, it could prove fatal to the Party, and even cause the collapse of the Party and the fall of the state”. ) ብለው የፓርቲው ዋና ጸሐፊ የተነገሩትን እንደ አውሮፓ ኖቬምበር 15 ቀን 2012 “Reform in China vs crisis within EPRDF” በሚል ርዕስ ከተብኩትን ጽሑፍ በድረ-ገጾች ላይ አስለጥፌ አስነብቤያለሁ።
ቅጥረኛው የወያኔ ነውረኛ አገዛዝ ላለፉት 23 ኣመታት የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅሞች ሲያዳሽቅ፣ ንብረቷን ሲመዘብርና ንዋይና የቡና ምርት የመሳሰሉትን ሀብት ሠርቆ ወደ ውጪ ሀገር በስውር በማሸጋገር ከብሮና ብቸኛው ባለመሬት ሆኖ፣ የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ የበላይነትን አስፍኖ፣ የዴሞክራሲ ግብዓቶቸን በሙሉ ተቆጣጥሮ እነሆ ዛሬ በማንአለብኝነት ሙስና አለቅጥ ባልጎ እንዳሻው እየገደለ፣ እያሰረ፣ ዜጎችን ከመኖሪያቸው እያፈናቀለ፣ ይገኛል። የወያኔ ቁንጮ መሪዎችና ቡችሎቻችው ከማይወጡበት የሙስና ባህር ውስጥ ገብተው በመስጠም ላይ ናቸው።
ይህ መውደቂያው አይቀሬ፣ ከአንድ አናሳ ጎሳ ከተውጣጡ በዘረፋ የከበሩ ጄኔራሎች የሚደገፈው መንግሥት እስከ አሁን ካደረሰው ዘግናኝ በደል በላይ ሌላ ሳጨምር በአፋጣኝ በቃህ ሊባል ይገባል!!!
ስለ የሙስና ንግሥት ሕዝቡ ምን ይላል?
ወልቃይት ብናስጠይቅ አሉን እዚያ የለች
ቀዳማዊ እመቤት ታዲያ ወዴት ሄደች
የሙስና ንግሥት ዘርፋን የከበረች
ፈልጓት ባካችሁ የት እንደ ደረሰች
እንድንፋረዳት ፍርድ ቤት አቅርበን
መች እንዲህ እንቀራለን ተገድለን ተገርፈን
ባባታችን ሀገር ተዘርፈን ተዋርደን
የመብት ጥያቄ ስናነሳ ታስረን
መለስ የዘራውን የጎጠኞች ፍሬ
አድጎ ሳይስቸግር እንቅጨው በጥሬ
ማምከን በተግባር ነው አይደለም በወሬ
ይህ ነው የኔ ምኞት ለኢትዮጵያ ሀገሬ
ንግሥቲቱን አየን ጥቀር ለብሳ ከስማ
በጣይቱ ከተማ ተደብቃ ከርማ
ወንጀሏ ይዘርዘር አንዱ ይንገር ላልሰማ
ወህኒ ቤት እንስደድ አዜብ ጎላንማ
ቀዳማዊ እመቤት ታዲያ ወዴት ሄደች
የሙስና ንግሥት ዘርፋን የከበረች
ፈልጓት ባካችሁ የት እንደ ደረሰች
እንድንፋረዳት ፍርድ ቤት አቅርበን
መች እንዲህ እንቀራለን ተገድለን ተገርፈን
ባባታችን ሀገር ተዘርፈን ተዋርደን
የመብት ጥያቄ ስናነሳ ታስረን
መለስ የዘራውን የጎጠኞች ፍሬ
አድጎ ሳይስቸግር እንቅጨው በጥሬ
ማምከን በተግባር ነው አይደለም በወሬ
ይህ ነው የኔ ምኞት ለኢትዮጵያ ሀገሬ
ንግሥቲቱን አየን ጥቀር ለብሳ ከስማ
በጣይቱ ከተማ ተደብቃ ከርማ
ወንጀሏ ይዘርዘር አንዱ ይንገር ላልሰማ
ወህኒ ቤት እንስደድ አዜብ ጎላንማ
ኑሮን ያልጠገቡ የኦሮሞ ልጆች ወጣት ተማሪዎች
ሕይዎታቸው ጠፍቶ፤ ደማቸው ተረጭቶ ባጋዚ ተኳሾች
አርፋ አትቀመጥም ሕዝብን ካለጋጨች፤ ካላተራመሰች
ታዲያ እንዴት ይኖራል አዜብ ተጠፍራ ቶሎ ካልታሰረች
ሕይዎታቸው ጠፍቶ፤ ደማቸው ተረጭቶ ባጋዚ ተኳሾች
አርፋ አትቀመጥም ሕዝብን ካለጋጨች፤ ካላተራመሰች
ታዲያ እንዴት ይኖራል አዜብ ተጠፍራ ቶሎ ካልታሰረች
ጸሎቴና አድናቆቴ
በ24/5/2014 መድረክ አዲስ አበባ ላይ ባካሄደው ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የታየው የተቃዋሚ ሀይሎች አስደናቂ ትብብር የበለጠ አይሎ፣ ጎልብቶ፣ አድጎና ፈርጥሞ ወያኔን በሰላማዊ መንገድ ለማንበርከክና በእናት ሀገራችን ውስጥ ጎጠኝነት ፈጽሞ እንዲከስም የዘወትር ጸሎቴ ነው።
ኦቦ ቡልቻ ደመቅሳ ላሳዩት ሞራል ገንቢ ተሳትፎ አድናቆቴን ከልብ እገልጻለሁ፤ ለመድረክ አመራሮችና አባላት ልባዊ መሥጋናዬን አቀርባለሁ።
የታሰሩት የፖለቲካና የህሊና እስረኞች አለምንም ቅድመ-ሁኔታ በአስቸኳይ ይፈቱ!
በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ወንጀል የፈፀሙ ሁሉ ለፍርድ የቅረቡ፤ ለሞቱት ተማሪዎች ቢተሰቦች መንግሥት ካሳ ይክፈል!
በ24/5/2014 መድረክ አዲስ አበባ ላይ ባካሄደው ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የታየው የተቃዋሚ ሀይሎች አስደናቂ ትብብር የበለጠ አይሎ፣ ጎልብቶ፣ አድጎና ፈርጥሞ ወያኔን በሰላማዊ መንገድ ለማንበርከክና በእናት ሀገራችን ውስጥ ጎጠኝነት ፈጽሞ እንዲከስም የዘወትር ጸሎቴ ነው።
ኦቦ ቡልቻ ደመቅሳ ላሳዩት ሞራል ገንቢ ተሳትፎ አድናቆቴን ከልብ እገልጻለሁ፤ ለመድረክ አመራሮችና አባላት ልባዊ መሥጋናዬን አቀርባለሁ።
የታሰሩት የፖለቲካና የህሊና እስረኞች አለምንም ቅድመ-ሁኔታ በአስቸኳይ ይፈቱ!
በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ወንጀል የፈፀሙ ሁሉ ለፍርድ የቅረቡ፤ ለሞቱት ተማሪዎች ቢተሰቦች መንግሥት ካሳ ይክፈል!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
rababya@gmail.com
rababya@gmail.com
No comments:
Post a Comment