ዛሬ ጀግኖች ልጆቻችን ካንጋሮው ፍ/ቤት የቀረቡበት ቀን ነው የአሁኑ ለየት እሚለው ገና ከ ጊዮርጊስ ጀምሮ የፌደራል እና የፖሊስ መአት ከተማዋን ወሮታል እንዴት ነው ዛሬ እያልን ወደ ፍ/ቤቱ ግቢ ገባን እስከዛሬ ፍተሻ አልነበረም ዛሬ አንድ ሰውን ለሁለት ሶስት ሆነው ነው እሚፈትሹት ከአስቸጋሪው ብርበራ በኋላ ወደውስጥ ዘለቅን ከወትሮው በርካታ ሰው ግቢውን ሞልቶታል ሰው ሰብሰብ ብሎ ጥላ ያለበት በታ ላይ ቆሞ ጀግኖቹን በጉጉት ይጠብቃል የማእከላዊው ምርመራ ክፍል ሃላፊ ኮማንደር ተክላይ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ወደ ግቢ በመግባት የለመዱትን ሽብር መንዛት ጀመሩ ተሰብስበን ከቆምንበት ቦታ እንድንለቅ ተደረግን ፀሃዩ ላይ መሰጣት ግድ አለን ሁሌ እንደሚያደርጉት የማስጠንቀቂያውን ናዳ ያወርደው ጀመር ፎቶ እንዳታነሱ፣ እንዳታጨበጭቡ፣ አንዴ ከገቡ መውጣት የለም ፒሪሪም ፒሪሪም………..
ችሎቱ ተሰየመ የመንግስት ጋዜጠኞች መግባት እንደሚችሉ ተነገረ የETV ይቅርታ ይሄ ስም እኮ አፌ ላይ አልመጣ እያለኝ ተቸገርኩ የEBC ጋዜጠኞች ሊገቡ ተንደረደሩ በእውነት በጋዜጠኞቻችን ኮራሁ የተለያዩ ነፃ ጋዜጠኞች ተገኝተው ነበር( ከሸገር፣ኢትዮ ምህዳር፣ ነገረ ኢትዮጵያ፣ ፍኖተ ነፃነት ፣ የጀርመን ራዲዮ ድምፅ) እኛም ጋዜጠኞች ነን ለነሱ ከተፈቀደ እኛም እንገባለን ፍቃድ አለን ብለው ሲያስደስቱ ዘራፍ አሉ ከብዙ ንትርክ በኋላ ሁሉም አይገቡም ተባለ
8 ሰዓት የገባን እስከ 10 ሰዓት ማንም አልመጣም በባዶው እንዴ ወደ ቀኝ አንዴ ወደ ግራ ሲያንገላቱን ቆዩ::
10 ሰዓት ላይ የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት አቶ ሃብታሙ አያሌው እና ድርጅት ጉዳይ ምክትል ሃላፊው አቶ ዳንኤል ሺበሺ ቀረቡ 11 አካባቢ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ የሺዋስ አሰፋ እና የ አረና ፓሪቲ ምክትል ህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ የቀረቡ ሲሆን እጃቸውን አንስተው ሰላም እንዳይሉን እጃቸው በፌደራል ፖሊሶች ተይዞ ነበር፡፡ ይህ ችሎት ለመጀመርያ ጊዜ ካለ ጠበቃ ብቻቸውን ነው የቀረቡት ችሎቱ 11፡30 አካባቢ ያለቀ ሲሆን እስረኞቹ ከአካባቢው እስኪርቁ ድረስ የፍ/ቤቱ በር ተዘግቶ ምንም እንዳይወጣ ተደርጓል፡፡ የተባሉትን ለመስማት ወደ ችሎቱ ስንጠጋ ክልክል ነው ወደዛ መጠጋት እያሉ ደነፉብን በዚህም ምክንያት ትክክለኛውን የጊዜ ቀጠሮ ማወቅ አልቻልንም ኮማንደር ተክላይ ጥቅምት 20 ሲል ፖሊሶች ደግሞ ጥቅምት 22 ነው ሲሉ ነገሩን ምንኛቸው ይሆኑ ትክክል?
በዛሬው እለት የታዘብኩት ችሎቱን ለመከታተል የተገኙት የፓርቲ አባላት፣ የእስረኞቹ ቤተሰቦች፣ ጋዜጠኞች፣ እንዲሁም ጥቂት ደጋፊዎች እና ብዙ ሰላዮች ናቸው የተገኙት ፌስ ቡክ ላይ አብርሃ ደስታ ይፈታ እከሌ ይፈታ እምትሉ ሁላ ቢያንስ ፍ/ቤት ተገኝቶ ድጋፍን መግለፅ እንዴት ይከብዳችኋል? የፌስቡክ ብቻ ጀግና አንሁን እንጂ ጎበዝ
በነገው እለት በዚሁ ፍ/ቤት የሰማያዊ ፓርቲ የ40 ምንጭ አመራሮች ከቀኑ 8 ሰዓት ስለሚቀርቡ ተገኝተን ድጋፋችንን እንግለፅላቸው!!!!1

No comments:
Post a Comment