Wednesday, 4 May 2016

ከሆላንድ ወደ ኢትዮጵያ የገባውን ዲያስፖራ ስምንት ቦታ በሳንጃ ወግተው የገደሉት አልተያዙም!

Ethiopian Diaspora from Holland, Leykun Eshetu
(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከሚኖርበት  ሆላንድ  ወደ  ትውልድ  ሃገሩ  ኢትዮጵያ  የገባው  ወጣት ለይኩን  እሸቱ  በፋሲካ  በዓል ዋዜማ  ስምንት ቦታ በስለት  ወግተው  የገገደሉት  ወንጀለኞች  እስካሁን  አልተያዙም። የአካባቢው ነዋሪዎች  እንደሚሉት ከሆነ  ገዳዮቹ  ባለጊዜዎች ስለሆኑ ሟች ደመ ከልብ ሆኖ ቀርቷል።
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የአካባው ነዋሪ ሲናገሩ፣  “ፍጹም፣ ቴዲ እና ባርያው በመባል የሚታወቁ እነዚህ ተጠርጣሪ ነብሰ ገዳዮች በአካባቢው ነዋሪን በእጅጉ ሲያስጨንቁ የኖሩ ናቸው። ይህ ግድያ የመጀመርያቸው አይደለም። ከወር በፊትም የንጹህ ዜጋ አይን አፍስሰዋል። ፖሊስ ግን አይይዛቸውም። ”  ብለዋል።
ይህ ሁሉ ሲሆን ፍትህ የሚያስከብር የመንግስት አካል እና  ህግ አስከባሪ ጉድዩን ችላ ብሎታል::  ከአንዳንዶች እንደሚሰማው ከሆነ ፖሊስ ለወንጀለኞቹ ሽፋን እየሰጣቸው ነው።  ከሟች የቀብር-ስነ ስርዓት በኋላ ህዝቡ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ  በሚገኘው ፖሊስ ድረስ በመሄድ ተጠርጣሪዎቹ በአስቸኳይ  እንዲያዙ ቢጠይቅም፤  ፖሊስ ለህዝቡ በጎ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በህዝቡ ላይ ተኩስ መክክፈት ለቀስጠኛው  እንዲበተን አድርጓል።  ቪድዮውን ይመልከቱ።
የሟች ጓደኛ ዳንኤል ንጉሴም በግድያው  በተጠረጠሩት  አምስት  ግለሰቦች  በሳንጃ ተወግቶ ጥቁር አንበሳ  ሆስፒታል  ከፍተኛ ቀዶ ጥገና  ተደርጎለታል።
ለዚህ አሰቃቂ ግድያ እና አደጋ መነሻ የሆነ ምክንያት እንደሌለ ነው ሰዎች የሚናገሩት። ከህግ በላይ የሆኑ ባለግዜዎች እና  ጉልበተኞች እንዲሁ በማናለብኝነት የፈጸሙት ወንጀል ነው። ሃገሪቱ  ሰው ከቤቱ በስላም ወጥቶ ለመግባት ምንም ዋስትና የሌለበት ሃገር ሆናለች።
ይህ አሰቃቂ ግድያ  በሆላንድ የሚኖሩ የለይኩን ወዳጆችን በእጅጉ አስደንግጧል። ከቶውንም “ዲያስፖራ” ፣” ኢንቨስተር” ወዘተ እየተባለ የሚለፈለፈው ሁሉ ለዲያስፖራው ዋስትና ከማይሰጥ መንግስት መሆኑም አሁን ግልጽ የሆነ ይመስላል።

No comments:

Post a Comment