Friday 1 August 2014

የአንድነት ፓርቲ ሶስቱ ፕሬዘዳንታዊ እጩዎች የጋራ መግለጫ ሰጡ

ጉዳዩ፥ ከአንድነት ፓርቲ ሶስቱ ፕሬዘዳንታዊ እጩዎች የተሰጠ የጋራ መግለጫ
ውድ ወገኖች፣
የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትሕ ፓርቲ በዴሞክራሲ ሂደትና ባህል አጥብቆ ያምናል። በአጭር እድሜው ፓርቲው አባላቶቹ በነጻነት የአሳብ ፍጭት አድርገው አሳባቸውን እንዲገልጹ በማድረግ ሶስት ፕረዚዳንቶችን ግልጽና ተጠያቂነት በተሞላበት ሁኔታ መርጧል። ፓርቲያችን መሪዎቹን የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ ባህሉን ይጠብቃል። የፓርቲያችን አባላቶችና ደጋፊዎች የዚህ ባህል ደጋፊ ብቻ ሳይሆኑ ሐዋሪያትም እንዲሆኑ አጥብቀን እናሳስባለን።
ፓርቲያችን ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅ ጋር ነሃሴ 4 ቀን 2006 ዓ.ም. በሚደረገው የጋራ ጉባኤ ተዋሕዶ ለፍትኅ፧ ለሕግ የበላይነት እና ለዴሞክራሲ እውን መሆን የጀመርነውን ትግል በተቀናጀ መንገድ ለመምራት ጉዞ ከጀመረ ውሎ አድሯል።
“ነገር ግን በቅርቡ አንድነትን ወክሎ ከመኢአድ እጩ ተወካይ ጋር ተወዳድሮ የውህዱን ፓርቲ የሚመራ ፕረዚዳንት ለመምረጥ በሂደት ላይ ሳለን፣ አንዳንድ እጩዎች ባላቸው ሐሳብ ላይ ያልተመረኮዘ፣ አላሰፍለጊ ቅስቀሳዎች፣ በአንዳንድ ወገኖች ታዘብናል። ይሄን በሂደት ይሻሻላል ብለን እናምናለን። በፕሬዘዳንታዊ እጩዎች መካከል የሚደረገው ፉክክር መንስዔ የአሳብ ልዩነት እንጂ ጥላቻ እንዳልሆነ እና ሁላችንም አንድነቶች መሆናችን ለአንድ አፍታም ቢሆን እንዳንዘነጋ አደራ እንላለን።
ስለዚህ እኛ ስማችን ዝቅ ብሎ የተዘረዘረው የአንድነት ፓርቲ ሶስት ፕረዚዳንታዊ እጩዎች ይሄን ቁልፍ የሽግግር ወቅት በአስተዋይነት እና በብስለት አብራችሁን ከስኬት እንድታደርሱ በአክብሮት እንጠይቃለን።
እ/ር ግዛቸው ሽፈራው
አቶ በላይ ፈቃዱ
አቶ ትዕግስቱ አወሉ
ሐምሌ 25/2006 (Thursday July August 1/2014)10523227_758965607495524_448766099872658266_n

No comments:

Post a Comment