እንደምታውቁት እሁድ እለት መርህ ይከበር ከሚሉት የወያኔ አፍራሽ ቡድን እኔንም ጠርቶኝ ባለማወቄ በቦታው ተገኝቼ ነበር፤ እኔም በቦታው የተገኘሁት ሲጠሩኝ የሆነ የእርቅ ኮሚቴ አቋቁመናልና የቡድኑ የኮሚቴ አባል እንድትሆን ነው ብለውኝ ነበር። መቼም እርቅን የሚጠላ የለምና ደስብሎኝ ነበ፤ ነገሩ ግን የእርቅ ኮሚቴ ሳይሆን አንድነት ፓርቲን ለማፍረስ እንደሆነ ነው የገባኝ፤ ሰዎቹ እኛ የምንፍልገው ፓርቲው ፈርሶ ሌላ ፓርቲ ለማቁዋቁዋም ነው፤ ለዚህም አስፈላጊውን ውጭ የሚመድብልን ሰው አለ እሱም እንጂነር ዘለቀ ነው አለ በይፋ ይሄን ያለው ወዲ የማነ ነው በመቀጠል አንድነት አሁን ባለው አመራር አንድነትን በተመለከተ ምንም አይነት ስራ እንዳይስራ የሚል ፊርማ ማስፍረም ጀመሩ፤ ሁሉም ፈረመ፤ እኔንም ፈርም ሲሉኝ እኔ አልፈርምም የማልፈርመውም አንደኛ ፓርቲ የማፍረስ ተልእኮ የለኝም ፓርቲውንም እየመራ ያለው ህጋዊ ቡድን ነው፤ የመረጠውም ጠቅላላ ጉባኤ ነው፤ እናንተ የምትሉት አልገባኝ፤ ብዬ በዚሁ አቆምኩኝ የሚገርመው አንጃው ትእዛዝ የሚሰጠው ቀጥታ ከምርጫ ቦርድ ነው፤ እንደውም የማነ በመሀል ስልክ ሲደወልለት ከምርጫ ቦርድ ሰዎች ነው ብሎናል። እንግዲህ እነዚህ ሰዎች ከምርጫ ቦርድ ትእዛዝ እየተቀበሉ ነው ፓርቲውን ለማፍርስ የሚሯሯጡት፤ ይህ ቡድን ከመንግስት ጋርም በቅርበት እንደሚስራ አንድ አንድ አባላትም ነግረውናል። በሚገርም ሁኔታ እኛን መንግስት ይፍልገናል ለምን ከመንግስት ጋር አንሰራም? ሲል ዳንኤል ሙላት ብዙ ሰዎችን ጠይቆአል፤ ይህ ቡድን ነው እንግዲህ መርህ ይከበር! የሚለን ጎበዝ ይህ ፓርቲ እኮ ብዙ ህይወት የተከፈለለት ፓርቲ ነው፤ ብዙ ጀግኖች መሰዋትነትን እየከፈሉለት ያለ ፓርቲ ነ፤ እንዴትስ በመንደር ወሮበሎች ይፈርሳል? እኔ የሚገርመኝ ከወረዳ 6 ተመርጠው ለስላሳ ጠጥተው አንድነትን ለማፍረስ የመጡት አባል ያልሆኑት የሰፍር ወጥምሾች ነው፤ ያለ ጫት የማያውቁትን ሰዎች ይዞ መምጣት እራሱ ስብስቡ እራሱ የቦዘኔ ስብስብ መሆኑን በዚው ያስታውቃል።
የኢትዮጽያ ህዝብ አንድነትን ይጠብቃል!! የኢትዮጽይል ህዝብ ከአንድነት ትልቅ ተሰፋም አለው፤ ይህን የህዝብ ፓርቲ ነው እንግዲ የስፍር ዱርዬ ከወያኔ ጋር ከምርጫ ቦርድ ጋር ተባብረው ከጫወታ ውጭ ለማድርግ ተግተው እየሰሩ ያሉት አንዳንዱ ለምን አልተቀጠርኩም ነው አንጃ ያደረገው፤ አንዱ ደሞ ባጠፋው ጥፋት ለምን በዲሲፕሊን ኮሚቴ ተገመገምኩኝ ብሎ ነው ፓርቲውን ካላፈረስኩኝ የሚለው እንግዲህ እኔም ላጠፋሁት ጥፋት መላውን የአንድነት አባልና ደጋፊን እንዲሁም የኢትዮጽያን ህዝብ ከልቤ ይቅርታ እጠይቃለሁ!!
No comments:
Post a Comment