የሕወሃቱ ምርጫ ቦርድ፣ አንድነት ፓርቲ እንደገና ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ማዘዙን የሚጠቁሙ ፍንጮች ደርሰዉኛል። የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ባላበት፣ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ፣ ምርጫ ቦርድ በወቅቱ እንዲሻሻል የጠየቀው ደንብ ተሻሽሎ የኮረም ቁጥር ማስገባቱ ማለት ነው) ፣ ብሄራዊ ምክር ቤቱ መርጦት የነበረዉን አዲስ አመራር እንደገና አጽድቆ ተለያይቶ ነበር። ሆኖም ምርጫ ቦርድ ፣ አይ ምርጫ እንደገና በሚስጠር መካሄድ አለበት በሚል አንድነት ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ ካልጠራ የምርጫ ምልክት እንደማይሰጥ አሳውቋል። ኢንጂነር ግዛቸው በፍቃዳቸው ሲለቁ፣ በደንቡ መሰረት ብሄራዊ ምክር ቤቱ ሶስት ተወዳዳሪዎችን አሳልፎ ምርጫ አደረገ። አዲስ አመራር መጣ።
ምርጫ ቦርድ ለአዲሱ አመራር እውቅና ሰጥቶ ነገር ግን ደንብ ማሻሻል አለባችሁ በሚል ደብዳቤ ላከ (የጠቅላላ ጉባኤ ኮረም ቁጥር አስገቡ የሚል) ። ደንብ ለማሻሻል ጠቅላላ ጉባኤ መጠራት ስለላበት ጠቅላላ ጉባኤ ተጠራ። የደንብ መሻሽል ተደረገ። አዲሱን አመራርን ጠቅላላ ጉባኤው እንደገና ኣጸደቀ።
ሆኖም ምርጫ ቦርድ አሁንም እንደገና ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ አዘዘ። ከዚህ በፊት የገለጸዉን ቀልብሶ፣ አመራሩ በጠቅላላ ጉባኤ እንደገና በሚስጠር ድምጽ አሰጣጥ እንዲመረጥ የሚል።
ጠቅላላ ጉባኤ እንደገና ለመጥራት ትልቅ ወጭ አለው። ሆኖም ሰላማዊ ትግል ማለት አንዱን መሰናክል እያለፉ ወደፊት መሄድ በመሆኑ አንድነት እርግጠኛ ነኝ ምርጫ ቦርድ እንደገና የደቀነበት መሰናክል በቀላሉ አልፎ እንደሚሻገር። እንኳን ለሁለትኛ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሩ ማለት፣ የአንድነት አመራሮችና አባላት ለመታሰር፣ ለመሞት የተዘጋጁ ናቸዉና።
ጠቅላላ ጉባኤ እንደገና ለመጥራት ትልቅ ወጭ አለው። ሆኖም ሰላማዊ ትግል ማለት አንዱን መሰናክል እያለፉ ወደፊት መሄድ በመሆኑ አንድነት እርግጠኛ ነኝ ምርጫ ቦርድ እንደገና የደቀነበት መሰናክል በቀላሉ አልፎ እንደሚሻገር። እንኳን ለሁለትኛ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሩ ማለት፣ የአንድነት አመራሮችና አባላት ለመታሰር፣ ለመሞት የተዘጋጁ ናቸዉና።
ምርጫ ቦርድ ለይቶ አንድነት ላይ እንደዚህ መዝመቱ አሳዛኝ ቢሆንም እንደ አንድነት ደጋፊ የኮራሁበትም ነገር ነው። አንድነት ጥሩ ሥራ እየሰራ እንዳለ፣ በአገዛዞችም ላይ ፍርሃትን እና ድንጋጤን መፍጠሩን እንዳወቅ አድርጎኛል። ወደ ስድሳ ምናንም የሚሆኑ ኮልቶሌ ድርጅቶችን አንዲት ነገር ያላለ ምርጫ ቦርድ፣ ይሄን ያህል በአንድነት ፓርቲ ላይ ጡንቻውን ማንሳቱ፣ በርግጥ የኢትዮጵያ ህዝብን የሚመራ፣ ሊያታግል የሚችል ጠንካራ ድርጅት መኖሩን አመላካች ነው። በርግጥም የፊታችን 2007 ምርጫ አገዛዙን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ህዝቡን አስተባበሮ ድምጹን እንዲያስከብር የማድረግ አቅም እንዳለም ተረድቻለሁ። ለዚህም ነው ህውሀአት ርጫ ቦርድ ተጠቅሞ ደባ እየፈጸመ ያለው። ሆኖም ይሄን የአገዛዙን ደባ ህዝቡ ያጠዋል ወይም ታጋዮች በዚህ ይወናበዳሉ ብዬ አላስብም።
አንድነት ወደ ምርጫ እገባለው ብሎ ሰፊ ንቅናቄ የማድረጉም አንዱ ሌላ ድልም፣ ይሄው የምርጫ ቦርድን የገጠጡ ጥርሶች እንዲታዩ ማድረጉ ነው። ይህ ምርጫ ቦርድ መመሪያ ከሕወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ የሚቀበሉ መሆናቸዉን በግልጽ ለማየት ችለናል።
No comments:
Post a Comment