ጥር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መኢአድ መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን፤ ሲል አንድነት ፦” ኢህአዴግን በምንም መልኩ አንፋታውም እያለ ነው።
ባሳለፍነው ሳምንት መግቢያ የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ <<አንድነትና-መኢአድ በውስጠ ድንባቸው መሰረት ያልፈቷቸው ችግሮች አሉ፤ችግሮቻቸውን ካልፈቱ በምርጫው ላይሳተፉ ይችላሉ>> ማለታቸው ነው የውዝግቡ መነሻ።
በወቅቱ በውስጠ-ደንቡ መሰረት ምንም ያልፈታው ችግር እንደሌለ የገለጸው አንድነት ፓርቲ፤ ምርጫ ቦርድ በምርጫው እንዳይሳተፍ ካገደው ውሳኔው ፖለቲካዊ ስለሚሆን ፤ፓርቲውም ተመጣጣኝ የሆነ ፖለቲካዊ ውሳኔ ለመወሰን እንደሚገደድ ማስጠንቀቁ ይታወቃል።
ፓርቲዎቹ ይህን ቢሉም ምርጫ ቦርድ በምክትል ሰብሳቢው በኩል ካንጸባረቀው አቛም ለውጥ ሊያደርግ ባለመቻሉ በ የ እለቱ ውጥረቱ እየተካረረ መጥቷል። ስለጉዳዩ ኢሳት ያነጋገራቸው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ተስፋሁን ኣለምነህ ምርጫ ቦርድ ከ2005 ጀምሮ በመ ኢ አድ የውስጥ ጉዳይ እየገባ ሴራ ሲጎነጉንና ሲበጠብጣቸው መቆየቱን በመጥቀስ እና የዛሬ ሁለት ኣመት ጠቅላላ ጉባ ዔ ከማካሄዽ ጀምሮ አማሉ የተባሏቸውን ነገሮች ሁሉ ቢያሟሉም ቦርዱ ምክንያት እየፈጠረ ሊቀበላቸው እንዳልቻለ በማውሳት፤<< ችግር አለ ከተባለ ላለው ችግር ሁሉ ተጤያቂው ራሱ ቦርዱ ነው።>>ብለዋል።
የችግሩ ምክንያት ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ያልሆነና የገዥው ፓርቲ አንድ ቅርንጫፍ የሆነ ተቋም በመሆኑ ነው ሲሉም የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ይናገራሉ ህልውናችን በምንከፍለው መስዋ እትነት ላይ እንጂ በምርጫ ቦርድ ይሁንታ ላይ የተንጠለጠለ አይደለም”ያሉት አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ<<ምርጫ ቦርድ ፈቀደም አልፈቀደም መኢአድ ለዚች ሀገር ዲሞክራሲያዊ ስር ኣት ግንባታ አስፈላጊ ነው ያለውን ነገር ከማድረግ ወደ ሁዋላ እንደማይል አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ<<ኢህአዴግ-አንድነትን ከምርጫ ውጪ ለማድረግ ደፋ ቀና እያለ ነው፤ ይሁን እንጂ ዘንድሮ ኢህአዴግን በምንም መልኩ አንፋታውም!>>ሲሉ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ገልጸዋል።
ሀላፊው አቶ አስራት እንደጠቆሙት፤ አንድነት በገዥው ፓርቲ በተሸረበበት ሴራ ዙሪያ ለመነጋገርና ምን ማድረግ እንዳለበት ለመምከር ለፊታችን እሁድ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርቷል።
ፓርቲያቸውን ከምርጫ ጨዋታ ውጪ ለማድረግ በገዥው ፓርቲ በኩል የተያዘው አቋም ያስቆጣቸው የሚመስሉት አቶ አስራት<< ኢህአዴግ የእግዴ ልጁ በሆነው ምርጫ ቦርድ በኩል ከአንድነትና ከመኢአድ ጋር የመረረ ትግል ውስጥ ገብቷል ።>>ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
<< አንድነት እጅግ በጣም አስደማሚና አስገራሚ የሆነ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄዶ ሁሉም ማሳፈሩ የሚታወቅ ነው>>ያሉት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ፤ <<ይህን አይቶ ማመን ያልቻለው ኢህአዴግ ግን እስኪ ድገሙት ልየው እያለ ነው!>>ብለዋል።
ዥው ፓርቲ ከዚህም በተጨማሪ አንድነትን ከምርጫ ውጪ ለማድረግ ጭፍሮቹን ይዞ ደፋ ቀና እያለ ቢሆንም አንድነቶች እጅ መስጠት የለም እያሉ እንደሆነ አቶ አስራት ገልጸዋል።
<<አንድነትን ከዘንድሮ ምርጫ ውጭ ለማድረግ የተሸረበውን ሴራ ለማምከን፤ በታሪክም አንድነት ያለምንም ምክንያት ከምርጫው እንደታገደ ለማሳየት አሁንም በድጋሚ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ለእሁድ ጥር ሶስት መጠራቱን የጠቀሱት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው፤ <<ከዚያ በኋላ አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ዓይኑን በጨው አጥቦ አንድነትን ይዘጋው እንደሆን እናየዋለን። ዘንድሮ ኢህአዴግን በምንም መልኩ አንፋታውም!!>>ብለዋል።
የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ <<አንድነትና-መ ኢአድ በውስጠ ድንባቸው መሰረት ያልፈቷቸው ችግሮች አሉ፤ችግሮቻቸውን ካልፈቱ በምርጫው ላይሳተፉ ይችላሉ>> ማለታቸው ይታወሳል።
በውስጠ-ደንቡ መሰረት ምንም ያልፈታው ችግር እንደሌለ የገለጸው አንድነት ፓርቲ በበኩሉ፤ ምርጫ ቦርድ በምርጫው እንዳይሳተፍ ካገደው ውሳኔው ፖለቲካዊ ስለሚሆን ፤ፓርቲውም ተመጣጣኝ የሆነ ፖለቲካዊ ውሳኔ ለመወሰን እንደሚገደድ ማስጠንቀቁ ይታወቃል።
በተያያዘ ዜና ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባ ረግጦ በመውጣቱ ይቅርታ ይጠይቅ ማለቱን ፓርቲው እንደማይቀበለው አስታወቀ። የፓርቲው የየድርጅት ጉዳይ ሀላፊ አቶ ብርሀኑ ተክለያሬድ፦” ጓዶች እኛ ሰማያዊዎች ነን፤ ማስፈራራት እኛ ላይ አይሰራም፡፡ ማንም ሊያንበረክከን ቢሞክር አንንበረከክም፡፡ ከተንበረከክንም ለፍቅር ብቻ ነው፤ አልያም የትእቢተኛውን ጉልበት ጎትተን ለመጣል!!!!!” በማለት ነው ለቦርዱ ይቅርታ ጠይቁኝ መግለጫ ምላሽ የሰጡት።
ምርጫ ቦርድ ወደ ፈንጂ ወረዳ እየተጠጋ እንደሆነ የገለጹት አቶ ብርሀኑ፤<<መስመሩን ያለፍክ ቀን ቀፎው የተነካበት ንብ- ንብ መሳይ ዝንቦችን ለመውረር እየተንደረደረ ይመጣል፡፡>>ብለዋል። የዘንድሮው ብሔራዊ ምርጫ ሊካሄድ ጥቂት ወራት በቀሩበት በአሁኑ ወቅት በገዥው ፓርቲና በተቃዋሚዎች መካከል ውዝግቡ እያየለ፣ውጥረቱ እየተካረረ መጥቷል። መንግስት ከዛሬ ነገ ከፓርቲዎቹ ጋር የገባውን ውዝግብ ያጠብ ይሆናል ተብሎ በሚጠበቅበት በ አሁኑ ወቅት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በሰጠው መግለጫ፦”በሠላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ ለሚፈልግ ኃይል ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር በመኖሩ ብጥብጥ የሚያስነሳ ምንም አይነት ሰበብ የለም ፡፡”የሚል መግለጫ ሰጥቷል።
ይህም መንግስት በፓርቲዎቹ ላይ ከያዘው አቋም እንደማይመለስ የሚያመላክት በመሆኑ-ውጥረቱ እያደር ወደ ከፋ ደረጃ ላይ መድረሱ አይቀርም የሚል ስጋት አሳድሯል።
No comments:
Post a Comment