ትላንት ጥር 24 ቀን 2008 ዓ.ም፣ እነ ሃብታሙ አያሌው፣ በሁለት ፍርድ ቤቶች ፣ በጠቅላይ ፍርድ ቤት እነ ከዚያ በላይ በሆነው በሰበር ችሎት ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።
የአንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ፣ አቃቢ “ሽብርተኞች ናቸው” በሚል ላቀረበው ክስ በቂ መረጃ አላቀረበም በሚል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲለቀቁ ቢወሰንም፣ ማረሚያ ቤቱ የፍርድ ቤትን ትእዛዝ በመናቅ እስረኞች ሳይፈታ መቆየቱ ይታወሳል። ቀናቶች ካለፉ በኋላ፣ አቃቢ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ በማለቱ፣ የአንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት የወሰነዉን ዉሳኔ ታግዶ፣ እነ ሃብታሙ በወህኒ እንዲቆዩ ተደርጓል።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ የታችኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ማገዱን በመቃወም፣ ለሰበር ፍርድ ቤት በቀረበው ክስ መሰረት፣ ለሶስት ወራት ጉዳዩ ከታየ በኋላ፣ ሰበር ፍርድ ቤቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ መሰረታዉ የሕግ ጥሰት እንዳለበት ያረጋገጠ ሲሆን፣ ጉዳዩን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እንዲመለከተው ወደዚያ አስተላልፎታል።
በሌላ በኩል በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፣ ከአሥራ አምስት ቀናት በፊት፣ አቃቢ ሕግ እነ ሃብታሙ አያሌዉን ለመክሰስ ያቀረበዉን የኦዲዮ መረጃዎች ይዞ እንዲያቀርብ ተጠይቆ፣ አቃቢ ሕግም 15 ቀናት ይሰጠኝ ባለው መሰረት፣ ለዛሬ ጥር 24 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆን፣ አቃቤ የተጠየቀዉን ማስረጃ ሳያቀርብ ቀርቷል።
ፍርድ ቤቱ ለሚቀጥለው ሳምንት መረጃው እንዲቀርብ ያዘዘ ሲሆን፣ በዚያን ጊዜ መረጃው ካልቀረበ፣ ዉሳኔ እንደሚወስኑ በመግልጽ ተለዋጭ ቀጠሮ ለየካቲት አንድ ቀን ተሰጥቷል።
በሁለቱም ፍርድ ቤቶች የነበረዉን ሁኔታ የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ መለስካቸው አመሐ እንደሚከትለው አቅርቦታል፡
No comments:
Post a Comment