Thursday, 4 February 2016

የወልቃይት የአማራ ብሔር የማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ታስረው ተፈቱ

ጥር 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የታገዱት የወልቃይት የአማራ ብሔር የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና የአካባቢ ሽማግሌዎች ሰኞ ጥር 23 ቀን 2008 ወደ መዲናችን መግባት ችለው ነበር፡፡ የትግራይ ክልል ኮሚቴዎቹና ኅበረተሰቡ በወጡበት ይቅርታ ጠይቀው በቶሎ ካልተመለሱ እርምጃ እንደሚወስድ በትግርኛ ቴሌቪዥን ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ መስጠቱም ይታወሳል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ ቁጥራቸው 22 የሚሆኑ ተወካዮች ለፌደሬሽን ምክር ቤትና ለፌደራል ጉዳዮች ቢሮ አቤቱታቸውን ለማሰማት ከቀኑ 7፡00 ላይ ሃያ ሁለት አካባቢ ከጓደኞቻቸው ተለይተው ሒደው ነበር፡፡ እነዚሁ የኮሚቴ አባላት እስከ ምሽት 2፡00 ከታፈኑ በኋላ ይህን ዜና ለሕዝብ ያሰራጨው የወልቃይት ጠገዴ ሰሜን አርማጭሆ ድምጽ ታስረው መፈታታቸውን ዘግቧል::
ታስረው የነበሩት የወልቃይት የአማራ ብሔር የማንነት አስተባባሪ ኮሚቴዎች:-
1. ኮ/ል ደመቀ
2. አቶ አታላይ ዛፌ
3. አቶ ተሰማ ረታ
4. አቶ ይለፍ በየነ
5. አቶ አደራጀው ዋኘው
6. አቶ አባይ ግርማይ
7. አቶ ሸፈቀ አደም

No comments:

Post a Comment