Friday, 1 August 2014

ትግሉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ጠንካራ መሪ ማውጣት የወቅቱ አንገንጋቢ ጥያቄ ነው!!! የአንድነት ቦስተን ድጋፍ ድርጅት

የአንድነት ቦስተን ድጋፍ ድርጅት፣ ለአመታት አገር ቤት የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግል የሚደግፍ ድርጅት እንደ መሆኑ፣ በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ የሚደረገዉን የዉህደት እንቅስቃሴ በደስታና በጉጉት እየተከታተለው ነው። የአመራር አባላትን ለመምረጥ የሚደረገዉ አስደሳች ዴሞክራሲያዊ ዉይይትና ቅስቀሳ ፣ አንድነት ምን ያህል የዲሞክራሲ ባህል እያዳበረ እንዳለ አመላካች ከመሆኑም በተጨማሪም ያኮራን ነገር ነው።
የእጩ ፕሬዘዳንት ምርጫ ላይ ድምጽ የሚሰጡትና የሚወስኑት፣ አገር ቤት ያሉ፣ ትልቅ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ጀግኖች ወገኖቻችን ናቸው። እንደዚያም ሆኖ ግን ፣ አንድነት የሕዝብ እንደመሆኑ ፣ የአንድነት ቦስተን የድጋፍ ድርጅት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት፣ ረቡዕ ጁላይ 30፣ 2014 ዓ. ም በተጠራ ስብሰባ፣ ሰፊ እና ጥልቅ ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ ድጋፍ ማህበሩ እንደ አንድነት ደጋፊ፣ ያለውን ሐሳብ በማጋራት፣ የዲሞክራሲያዊ ሂደቱ አካል መሆኑ ጠቃሚ እንደሆነ በመገንዘብ፣ ከዚህ የሚቀጥለውን መግለጫ አውጥቷል።
1ኛ. የአንድነት እና መኢአድ ውህደትን አስመልክቶ የአንድነት ፓርቲ ፤ ፓርቲውን ወክሎ የሚወዳደር እጩ ተወዳዳሪዎችን በመመዝገብ እና ለሕዝብ ይፋ በማድረጉ ፓርቲው ምን ያህል ዲሞክራሲያዊ እና ግልጽ ምርጫ እያደረገ ያለ መሆኑን የሚያሳይ ፤ ሊበረታታ የሚገባው በመሆኑ አሁንም በተለይ በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ ያሉ ደጋፊዎች እና በምርጫው የሚሳተፉ የፓርቲው ተወካዮች የበለጠ ሰለ እጩዎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው መድረክ በማዘጋጀት የበለጠ እንዲተዋወቁ ቢደረግ የተሻለ እንደሚሆን ከመጠቆም አናልፍም።
2ኛ. በአንድነት በኩል እጩ ፕሬዘዳንቶችን አስመልክቶ በፓርቲው ክርክር ተደርጎ፤ እጩ ፕሬዘዳንቶቹ ወደ ጠቅላላ ጉባዔ ሄደው ከሦስቱ አንዱ እንዲመረጥ በዴሞክራሲያዊ መንገድ በድምፅ የተወሰነ ሲሆን ፤ በፓርቲው እጩ ሆነው ለውድድር የቀረቡት እጩ ፕሬዘዳንቶች
1. ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው
2. አቶ በላይ ፍቃዱ
3. አቶ ትዕግስቱ አወሉ መሆናቸውን ፓርቲው ይፋ አድርጓል፤ ይህም ዲሞክራሲያዊ አሰራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሙሉ እምነታችን ነው፤
3ኛ. አንድነት ካቀረባቸው ሦስት ጠንካራ እጩዎች መካከል የጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፊው አንዱን እጩ ፕሬዝዳንት አድርጎ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ይመርጣል፤ በዚሁ መስረት ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው፤ ፓርቲውን ለረጅም ጊዜ በምክትል ፕሬዘዳንት እና ተጠባባቂ ፕሬዘዳንት፤ እንዲሁም አሁን በድጋሚ ፕሬዘዳንት በመሆን ለፓርቲው እዚህ ደረጃ መድረስ ትልቅ አስተዋጻኦ ማድርጋቸው ግልጽ ነው፤ በተጨማሪም ‹‹ወጣቶችን ለአመራርነት ለማብቃት›› ለመስራት እንደሚጥሩ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በርካታ ወጣቶች በፓርቲው ከፍተኛ አመራር ላይ ይገኛሉ፤ ከነዚህም ወጣቶች አንዱ አቶ በላይ ፈቃዱ፣ የአንድነት ምክትል ፕሬዘዳንት፤ የፍኖተ ነጻነት ኤዲቶሪያል ቦርድ ስብሳቢ ሲሆኑ፣ ለአመታት ፓርቲው እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ ድርሻ ይወጡ የነበሩ እጩ ተወዳዳሪ ናቸው። አቶ በላይ ካላቸው የስራ ልምድ እና አገልግሎት፣ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ባሉ የአንድነት ደጋፊዎች ዘንድ፣ በተለይ በወጣቱ አካባቢ፣ ያላቸው ተቀባይነት፣ ትግሉን ወደ ሕዝቡ ለማውርድ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ፣ ትርጉም ወዳለው ደረጃ ከፍ ያደርጉታል የሚል እምነት አለን። በአሁኑ ሰዓት ተበታትነው የሚገኙትን የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማሰባሰብ፣ ወደ ውህደት ወይም በቅርብ ተባብሮ በመስራት ደረጃ ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ፣ በሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችም ዘንድ ከበሬታ ያላቸው መሪ ናቸው። አቶ በላይ በተለያየ ጊዜያት ለውጭው ማህበረስብ የሚያደርጓቸውን ውይይቶች በአንክሮት ስንከታትለው የነበረ ሲሆን ፣ በሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት እንቅስቃሴ፣ ሐሳቡን ከማመንጨት ጀመሮ፣ በግንባር ቀደምትነት እንቅስቃሴዉን እየመሩ ያሉ፣ ብሩህ ራእይ ያላቸው፣ ለፓርቲው ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም መሪነት ተስፋ የሚጣልባቸው ወጣት አመራር ናቸው። በተለይ በአሁኑ ወቅት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን ውስብስብ ችግሮችን በሚገባ የሚረዱ እና መፍትሄ በመፈለግ አገሪቷ ከገባችበት ማጥ፣ በቀላሉ ለማውጣት ይችላሉ ከሚባሉ መሪዎች መካከል አንዱ ናቸው ብለን እናምናለን፡፡

በመሆኑም፣ የቦስተን አንድነት ድጋፍ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተወያይቶ፣ በሙሉ ድምጽ፣ አቶ በላይ ፍቃዱ ቢመረጡ ደስተኛ እንደሚሆን በአክብሮት እየገለጸ ኢንዶርስመንቱን ለአቶ በላይ በፍቃዱ ይሰጣል።
ሙሉ ባለስልጣን እና ወሳኙ አካል የሆነው የዉህዱ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ዲሞክራሲያዊና ግልጽ በሆነ መንገድ ፣ ከአቶ በላይ ዉጭ ሌላ ፕሬዘዳንት ከመረጠ፣ ድርጅታችን፣ የጉባኤውን ዉሳኔ ሙሉ ለሙሉ እንደምንቀበልና ከአዲሱ አመራር ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን ትግሉን እንደምንቀጥል ለማረጋገጥ እንወድለን።
አንድነት ቦስተን ድጋፍ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
ቦስተን
ረቡዕ, ጁላይ 30, 2014 ዓ. ም.10523227_758965607495524_448766099872658266_n

የአንድነት ፓርቲ ሶስቱ ፕሬዘዳንታዊ እጩዎች የጋራ መግለጫ ሰጡ

ጉዳዩ፥ ከአንድነት ፓርቲ ሶስቱ ፕሬዘዳንታዊ እጩዎች የተሰጠ የጋራ መግለጫ
ውድ ወገኖች፣
የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትሕ ፓርቲ በዴሞክራሲ ሂደትና ባህል አጥብቆ ያምናል። በአጭር እድሜው ፓርቲው አባላቶቹ በነጻነት የአሳብ ፍጭት አድርገው አሳባቸውን እንዲገልጹ በማድረግ ሶስት ፕረዚዳንቶችን ግልጽና ተጠያቂነት በተሞላበት ሁኔታ መርጧል። ፓርቲያችን መሪዎቹን የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ ባህሉን ይጠብቃል። የፓርቲያችን አባላቶችና ደጋፊዎች የዚህ ባህል ደጋፊ ብቻ ሳይሆኑ ሐዋሪያትም እንዲሆኑ አጥብቀን እናሳስባለን።
ፓርቲያችን ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅ ጋር ነሃሴ 4 ቀን 2006 ዓ.ም. በሚደረገው የጋራ ጉባኤ ተዋሕዶ ለፍትኅ፧ ለሕግ የበላይነት እና ለዴሞክራሲ እውን መሆን የጀመርነውን ትግል በተቀናጀ መንገድ ለመምራት ጉዞ ከጀመረ ውሎ አድሯል።
“ነገር ግን በቅርቡ አንድነትን ወክሎ ከመኢአድ እጩ ተወካይ ጋር ተወዳድሮ የውህዱን ፓርቲ የሚመራ ፕረዚዳንት ለመምረጥ በሂደት ላይ ሳለን፣ አንዳንድ እጩዎች ባላቸው ሐሳብ ላይ ያልተመረኮዘ፣ አላሰፍለጊ ቅስቀሳዎች፣ በአንዳንድ ወገኖች ታዘብናል። ይሄን በሂደት ይሻሻላል ብለን እናምናለን። በፕሬዘዳንታዊ እጩዎች መካከል የሚደረገው ፉክክር መንስዔ የአሳብ ልዩነት እንጂ ጥላቻ እንዳልሆነ እና ሁላችንም አንድነቶች መሆናችን ለአንድ አፍታም ቢሆን እንዳንዘነጋ አደራ እንላለን።
ስለዚህ እኛ ስማችን ዝቅ ብሎ የተዘረዘረው የአንድነት ፓርቲ ሶስት ፕረዚዳንታዊ እጩዎች ይሄን ቁልፍ የሽግግር ወቅት በአስተዋይነት እና በብስለት አብራችሁን ከስኬት እንድታደርሱ በአክብሮት እንጠይቃለን።
እ/ር ግዛቸው ሽፈራው
አቶ በላይ ፈቃዱ
አቶ ትዕግስቱ አወሉ
ሐምሌ 25/2006 (Thursday July August 1/2014)10523227_758965607495524_448766099872658266_n

የተደራጁ ወንበዴዎች ለመፍጠር እየፈለጉ ያሉትን ብዥታ ለማጥራት -ከዳንኤል ተፈራ

ባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በጣም ወሳኝ የሆነ ስራ ሲሰራ ነበር፡፡ እሱም ውህደት ነው፡፡ የአንድነት/መኢአድ ውህደት ወሳኝና መሰረታዊ ድርድሮችን አልፎ የቅድመ ውህደት ፊርማው ከተቀመጠም ከወር በላይ ሆነው፡፡ከፊርማው በኋላ ውህደት አመቻች ኮሚቴ ተዋቅሮ በአጭር ጊዜ ነገሮችን መልክ ለማስያስ የቻለ ሲሆን ውህደቱም የሁለቱ መስራች የጉባዔ አባላት በተገኙበት ነሐሴ 3 እና 4 ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ታዲያ ከመስራች ጉባዔው አስቀድሞ ሁለቱ ፓርቲዎች በተናጠል ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት የውህዱን ፓርቲ ደንብና ፕሮግራም፤ ለውድድር የሚቀርብ እጩ ፕሬዘዳንት መምረጥ፣ አዲስ ስያሜ በመጠቆም እንዲሁም ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎችን በመስራት ይጠናቀቃል፡፡ በነገራችን ላይ የተናጠሉ ጉባዔ ስራውን የሚጀምረው አዲሱን የጋራ ደንብ በማፅደቅ ይሆናል፡፡ አጠቃላይ ውህደቱን ተቀበለው የሚባለው ደንብና ፕሮግራሙን ሲያፀድቅ ይሆናል፡፡
በአንድነት ፓርቲ በኩል በምክር ቤት ደረጃና በተለያዩ መዋቅሮቹ የሀሳብ ክርክር ማድረግ የተለመደ እንጅ ብርቅ አይደለም፡፡ የሃሳብ ክርክር ሲደረግ ‹‹ተባሉ፣ ምናምን›› እያሉ የሚጮሁት ከክርክሩ ትርፍ ለመሸመት የተሰለፉ ባእድ ሃይሎች እንጅ አንድነቶች አይደሉም፡፡ ነገዳቸው የሃሳብ ክርክር ከማውቀው ጎራ ስለሆነ የአንድነት አባላት የሃሳብ ፍጭት ሲያደርጉ ይደነግጣሉ፡፡ በአንድነት በኩል እጩ ፕሬዘዳንቶችን አስመልክቶም የተለመደው ክርክር ተደርጎ፤ እጩ ፕሬዘዳንቶቹ ወደ ጠቅላላ ጉባዔ ሄደው ከሦስቱ አንዱ እንዲመረጥ በዴሞክራሲያዊ መንገድ በድምፅ ተወሰነ፡፡ የቀረቡት እጩ ፕሬዘዳንቶች ከታወቁ በኋላም ደጋፊዎቻቸው እከሌ ቢመረጥ ይሻላል የሚል ሀሳብ የማቅረብ መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ እኔም እከሌ ቢመረጥ ፖለቲካውን የተሻለ ያንቀሳቅሰዋል የሚል መብት አለኝ፡፡ ይህንን መብት የሰጠኝ ማንም ሳይሆን አንድነት ነው፡፡
ሀቁ ይሄ ቢሆንም የአንድነት ወገን ያልሆኑ ስማቸውን የደበቁ ወሮበላ ተላላኪዎች ሶሻል ሚዲያውን በመጠቀም የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ ለማስፈፀም መንፈራገጣቸው አልቀረም፡፡ ዘመቻ ከተከፈተባቸው መካከል ደግሞ አንዱ እኔ መሆኔ ፈገግ ያሰኘኛል፡፡ ብዥታውን ማጥራት ያስፈለገኝም ለምን ስሜ ተጠቀሰ ብየ ሳይሆን የሀሰት ዘመቻውን አንድምታና ከየት አቅጣጫ እንደተሰነዘረ ለመጠቆም ነው፡፡ ዘመቻው የውሸት ስሞችን በመጠቀምና ማስጃ አልባ የተቀነባበሩ ስድቦችን በማዥጎድጎድ ብዥታ መፍጠር ነው፡፡ በተለይም ስርዓቱ ምንደኛ የሆኑ ተላላኪ ግለሰቦች ‹‹አሉላ እንደገና፣ ሰለሞን ሳልሳዊ፣ የፍቅር ቃልና አፄ ልብነድንግል›› የሚሉ የተልኮ ስሞችን በመጠቀም ውህደቱ ከመደረጉ በፊት ክፍፍል ለመፍጠር ኢህአዴጋዊ ተልዕኮ ተሰጥቷዋቸው እየባዘኑ ይገኛሉ፡፡ አንድነት አበቃለት እያሉ ስማቸውን ደብቀው እንደተራበ ቁራ ያንቋርራሉ፡፡ እነዚህን ከሙታን የሚለያቸው በድን ተንቀሳቃሽ መሆናቸው ነው፡፡ ህሊናቸውን የሸጡ ርካሽ ፍጡራን ናቸው፡፡
ዋናው ቁምነገር ዘመቻው ለምን ተከፈተ የሚለው ነው፡፡ የሚጠበቅም ነበር፡፡ ዘመቻው በተለይም በእኔና ጓዶቼ ላይ የተከፈተው ስለለውጥ፤ የተቃዋሚ ጎራውን የማይናድ መሰረት ስለማስያዝና የተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ስለተናገርን ብቻ ነው፡፡ ስለሰራን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ መስራትን ደግሞ የአንድነት ልጆች ይደግፉታል እንጂ አይቃወሙትም፡፡ የሚቃወመው ሃይል ‹‹ተቃዋሚው ማንሰራራት የለበትም፤ እግር ማውጣት የለበትም›› ብሎ የሚያምነው ኢህአዴግ ብቻ ነው፡፡ የስም ማጥፋት ዘመቻው በቀጣይ አመት የሚካሄደው ምርጫ ላይ የሚኖረንን ተሳትፎና ትግል አጋጣሚውን ተጠቅሞ የመምታት ነው፡፡ እነዚህ ከላይ የተቀስኳቸው የሀሰት ስም ተጠቃሚ ባንዳዎች ሀብታሙ አያሌው ላይ ተመሳሳይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተው ነበር፡፡ ስም በማጥፋት እንደማይበገር ሲያውቁ አሰሩት፡፡
አንድነት ካቀረባቸው ሦስት ጠንካራ እጩዎች መካከል የጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፊው አንዱን ይመርጣል፡፡ ዋናው የሂደቱ ዴሞክራሲያዊ መሆን ነው፡፡ ኢንጅነር ግዛቸውና አቶ ትዕግስቱ ለአንድነት እዚህ መድረስ ያደረጉት ትልቅ አስተዋፅኦና የከፈሉት ዋጋ ሳይዘነጋ ነገር ግን አሁንም የእኔ እምነትና ፍላጎት ሀቅን መካድ ስለማይቻል ለአንድነት ፓርቲ አሁን ያለበት ከፍታ ላይ መድረስ በላይ ፈቃዱ ዋናው ስለሆነ፤ ትግሉን ወደ ህዝቡ ለማውረድና ከቢሮ ለማውጣት በነበረው ትንቅንቅ ላይ እውቀቱን፣ ገንዘቡንና ጊዜውን ያለ ምንም ስስት ሲሰጥ ስላስተዋልኩ፤ በላይ ፍቃዱ የሚታወቀው ሀሳብ በማመንጨትና ያ ሀሳብም ተግባራዊ እንዲሆን ሳይደክም በመስራት ስለሆነ፤ ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት›› የሚለው ወሳኝ ህዝባዊ ንቅናቄ ስያሜ በበላይ በኩል የቀረበ እንደነበር ስለማውቅ እንዲሁም በላይ ፈቃዱ ፓርቲያችን የማተሚያ ማሽን ሊኖረው ይገባል የሚል ሃሳብ በማቅረብና በመተግበር ውጤት ያሳየም በመሆኑና በአጠቃላይ የጀርባ ሞተር ሆኖ የቆየ ውድ የአንድነት ልጅ ነው ብየ ስለማምን ለበላይ ድጋፌን እሰጣለሁ፡፡
ታዲያ ይህ ግልፅ እምነቴ በድብቅ ስሞች ስም ለማጉደፍ በሚሯሯጡ በገዥው ፓርቲ ምልምሎች በኩል የተቀነባበረ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲከፈትብኝ አድርጓል፡፡ ልብ በሉ ‹‹ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው›› ነውና በወሬኞች ላለመፈታት እንጠንቀቅ፡፡ ስም አጥፊዎቹ የአንድነት ልጆች ቢሆኑ ኖሮ እንደዘረዘሩት የሀሰት ውንጀላ አንድ ቀን አናድርም ነበር፡፡ የውሸት ስም መጠቀም ሳያስፈልጋቸው ቢፈልጉ ፕሬዘዳንቱ ጋ አሊያም የምክር ቤት ሰብሳቢው ጋ በማምጣት ባቀረቡ ነበር፡፡ አድናቆቴ ከፍ ይል የነበረውም ይህንን ማድረግ ቢችሉ ነበር፡፡ አሁንም እስከነፃነት ትግሉን እንቀጥላለን፡፡10150630_609195442498727_1046966781_n

Sunday, 27 July 2014

በላይ በላይ ለምን እንበል? – ከጥላዬ ታረቀኝ አለማየሁ

ኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራው ከሁለት ዓመታት የፖለቲካ እረፍት በኋላ የአንድነት ፓርቲ አመራር ሆነው እንዲሰየሙ ጥሪ ሲደረግላቸው ጥሪውን የተቀበሉት
‹‹ወጣቶችን ለአመራርነት ለማብቃት››
ከሚል ውስጣዊ ቅንነት ጋር እንደነበር መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ ኢንጂነሩ ከዶክተር ነጋሶ የተረከቡት ፓርቲ ከመኢአድ ጋር የጀመረውን የውህደት ድርድር በማስቀጠልና ተቃዋሚዎች እየተዋሃዱ አንድ አቢይ ተቃዋሚ ፓርቲ እንዲመሰርቱ በመርህ ደረጃ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡
በእኔ እምነት ኢንጂነሩ ፓርቲውን ለመምራት የቀረበላቸውን ጥያቄ የተቀበሉበት ተገቢነት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የደረሰበት ወቅት ከፊታቸው ተደቅኗል፡፡ኢንጂነሩን ለመረከብ አዲስ ፊት የሆነውና በብዙ የአንድነት እንቅስቃሴዎች የጀርባ አጥንትና ሞተር ሆኖ የቆየው በላይ ፈቃዱ ራሱን ዕጩ በማድረግ አቅርቧል፡፡
አንድነትን የአዛውንቶች ክበብ አድርገው ለሚመለከቱ የበላይ ለፕሬዘዳንትነት ራሱን በዕጩነት ማቅረብ አንድነትን የአዛውንቶች ክበብ በማድረግ ይተቹት ለነበሩ ሁሉ ፓርቲው አዲስ ጉልበት እንዳለውና መካን አለመሆኑን ያሳይበታል፡፡ከበላይ በወጣትነት የዕድሜ ክልል ከመገኘት በተጨማሪ አንድነት ወጣት ሲል ዕድሜ ላይ ብቻ የተሰፋ አለመሆኑን ወጣትነት ለአንድነት ከአዲስ የትግል መንፈስ፣ከአዲስ አስተሳሰብና ፖለቲካው ከሚፈልገው ዘመናዊነት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ለማሳየት በላይ ፈቃዱ ትክክለኛው ማሳያ ይሆንለታል፡፡
ከቀጣዩ ዓመት ምርጫ አንጻር ቀጣዩ ዓመት አገር አቀፍ ምርጫ የሚከናወንበት መሆኑም ለሚፈጠረው ውህድ ፓርቲ ትልቅ የፈተና እና የትግል ጊዜ ይሆናል፡፡በዚህ ወቅት አባላት ከምርጫው ጋር የተያያዘ አጠራጣሪ ተሞክሮ የሌለው መሪ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡በዚህ ረገድ አንድነት ላወጣው የስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት ከፍተኛ አስተዋእጾ ያበረከተው በላይ ውህዱ ፓርቲ ሊከተለው በሚገባው የትግል ስትራቴጂ ዙሪያ በተመሳሳይ መልኩ እምቅ የፖለቲካ አቅሙን በማውጣት አገልግሎቱን ሊያበረክት ይችላል፡፡
በላይ ለመኢአድ አባላት አዲስ መሆኑ ኢንጂነር ግዛቸው ከመኢአድ የወጡ በመሆናቸውም በእርሳቸው አመራርነት ዙሪያ በመኢአድ ውስጥ ጥያቄና ተቃውሞ የሚኖራቸው ሰዎች አይኖሩም በማለት መገመት የዋህነት ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡በላይ ፈቃዱን የመኢአድ አባላትና አመራሮች የሚያውቁት ከውህደት ኮሚቴው ጋር በቅርበት ሲሰራ በመሆኑ ለእርሱ ድምጽ የሚሰጡበት ዕድል እንደሚኖር መገመት አያዳግትም፡፡
ከሌሎች ፓርቲዎች አንጻርሰማያዊ ፓርቲ እንዲመሰረት ገፊ ምክንያት የሆኑ ሰበዞች የሚመዘዙትና ማጠንጠኛ የሆኑት ኢንጂነር ግዛቸው ናቸው፡፡ሰማያዊ ሲመሰረት የእኛ ጥያቄ የመርህ ይከበር እንጂ ፓርቲ የመመስረት አይደለም በማለትም ከሰማያዊ መስራቾች ተርታ ራሳቸውን ያወጡ አባላትም ግዛቸው ተመልሰው መንበሩን በመረከባቸው ደስተኞች አይመስሉም፡፡እነዚህን ሀይሎች በውህደትና በእርቅ ወደ ፓርቲው ለመመለስ አልያም በአብሮነት ለመስራት ከበላይ የተሻለ ስለመገኘቱ ጥርጣሬ አለኝ፡፡
በእነዚህና በሌላ ወቅት ለውይይት በማቀርባቸው ነጥቦች የተነሳ አንድነቶች ድምጻቸውን በዕጩነት ከቀረቡት ለአንዱ ከመስጠታቸው በፊት ደግመው ደጋግመው እንዲያስቡበትና ውስጣቸውን እንዲያደምጡበት እጠይቃለሁ::10523227_758965607495524_448766099872658266_n

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በ1966ቱ አብዮት – ከሮበሌ አባቢያ

ታሪክማ ሊረሳ አይገባም
ታህሣሥ 7 ቀን 1966 ዓ.ም የነጌሌ ጦር አባሎች ለአዛዦቻቸው ላለመታዘዝ ወሰኑ። የምድር ጦር አዛዥ የነበሩት ሌተና ጄኔራል ድረሴ ዱባለ አማፅያኑን እንዲያረጋጉ በታዘዙት መሠረት የመንግሥት ልዑካን ይዘው ታህሣሥ 23ቀን 1966 ዓ.ም ነጌሌ ጦር ሠፈር ገብተው ሠራዊቱን ሲያነጋግሩ የተጠበቀውን መልስ ስላልሰጡ እርሳቸውም ከነተከታዮቻቸው ታገቱ፡፡ በ27/4/66 በአየር ኤታማጆር ሹም በጄኔራል አበራ ወልደማርያም የሚመራ የዓፄው ልዑካን ቡድን ወደ ነጌሌ ተልኮ በመደራደር፣ ታጋቾችን ሊያሰፈታ ቻለ። ነገር ግን ያድማው መነሻ ኢኮኖሚ-ተኮር ቢመስልም፣ አንደምታው በሌሎችም የጦር ኃይሎች ካምፖችም ውስጥ በመዛመቱ ምክንያት፣ መለዮ ለባሹ ለአብዮት ፍንዳታ አጋር ኃይል እንደሚሆን መሠረታዊ ለውጥ ለሚፈልጉ ተራማጅ ኃይሎች የምሥራች ሆኖ በግልፅ ይታይ ነበር።
የነጌለው አድማ የፖለቲካ አጀንዳ ይዞ ደብረ ዘይት የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ወደሚገኝበት ብቅ አለና የጎጃሙን ተወላጅ ማስተር ቴክኒሺያን ግርማ ዘለቀን እና በሕቡእ አብረው የተደራጁትን እነ ሲኒየር ቴክኒሽያን አበበ አረጋን፣ እንዲሁም ከጎረቤት የአየር ወለድ ጦር የተባበሩለትን ባለሌላ ማእረጎችን አገኛቸው። እነርሱም ታሪክ ለመሥራት ለአብዮታዊ ተግባር ተነሱ! በዚህ ጽሁፍ ውስጥ  ዘርዘር አድርጌ እንደምገልጸው፣ ጀግናው ግርማ ዘለቀ ከፍተኛ መኮንኖችን አግቶ የአየር ኃይሉን ከተቆጣጠረ በሗላ ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር በስልክ በቀጥታ ፖለቲካዊ ድርድር ጀመረና አስደናቂ ወጤት አስገኘ። ባላሌላ ማዕረጎች (non-commissioned officers)፣ አየር ኃይልን የሚያክል አግራዊ ተቁአም ተቆጣጥረው የፖለቲካ ለውጥ ሲያስገኙ በየትም ተነግሮ አያወቅም።
የ“እኛና አብዮቱ” ደራሲ ጠቅላይ ምኒስትር ፍቅረስላሴ ወግደርስ የአየር ኃይል መኮንን ስለነበሩ  ይህን ምዕራፍ በመጽሐፈቸው ለምን እንዳላካተቱት በመገረም ለጊዜው በጥያቄ ልለፈው።
ወደሚቀጥለው አርዕስት ከመሸጋገሬ በፊት፣ በሙስና ያልተበከሉ የወያኔ የመከላከያ፣ የደህንነተና የበላይ ከበርቴ አለቆቻቸውን በቀጥር ስር በማወወል የጀገናውን ግርማየ ዘለቀን ምሳሌ በመከተል ሰላማዊ ለውጥ ለማምጣት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እዲያደርጉ መማፀን ከዓላማዬ ውስጥ አንዱ ነው።
ስለዚች ጽሑፍ ዓላማ ጥቂት ልዘርዘር
አብዮቱ በየካቲት ወር 1966 ዓ.ም (18/6/66) ሲፈነዳ፣ ለብዙሀኑ ብሩህ ተስፋ  የፈነጠቀ መስሎ ታይቶ ነበር። ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ደም ያላፋሰሰ ሰላማዊ ትግል ሂደቱ፣ “ኢትዮጵያ ትቅደም፣ ያለምንም ደም” በሚል መፈክር ዙሪያ ሕዝቡን አሰልፎ እንደ ነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።
በ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት በቀጥታ የተሳተፍነውና በውስጡም ስንጓዝ ያጋጠሙንን ተግደሮቶችና የተከሰቱትን ሁነቶች ለታሪክ ጸሐፊዎች በማስረጃ ማቆየት የዜግነት ሞራላዊ ግዴታ ነው። እግዚአብሔር ረዢም እድሜ ሰጥቶኝ እስከ አሁን ስለአደረሰኝ በአብዮቱ ሂደት ወቅትና በፊት በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ላይ በሀላፊነት ላይ ተመድቤ ሳገለግል፣ ካካበትኩት የሥራ ልምድና በዚያም ሳቢያ በእጄ የገቡትን ሰነዶችና የመዘገብኳቸውን የግል ማስታወሻዎች በመመርኮዝ፣ በኔ አስተያየት ወቅታዊ ናት ብዬ ያመንኩባትን፣ ይህችን አጭር ጽሑፍ ለአንባቢ አቅርቤያለሁ።
ስለሆነም፣
  • በ1966ቱ አብዮት መዳራሻና ዋዜማ የዓፄው መንግሥት ወታደሮችና የፖሊስ ሠራዊት ወገናዊነታቸውን ለሕዝብ በማሰየት ዘውዳዊውን አገዛዝ በመገርሰስ ያስመዘገቡትን አኩሪ ታሪክ፣ የወያኔም የመከላከያ ሠራዊት፣ የፈፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ ደህንነት ተቋም አባላት በበኩላቸው በአርአያነት እንዲከተሉ በአጽንኦት መምከር አንዱ ዋና ዓላማዬ ነው።
  • የዛሬው የኢትዮጵያ ትውልድ፣ ከ1996 ጀምሮ ላለፉት 40 ዓመታት በእናት ሀገራችንና በህዝቦቿ ላይ ያደረሰው ውድቀት እንዳይደገም ከታሪክ በትክክል ተገንዘቦ ላንዴና ለመጨረሻ የሚደረገውን የነጻነት ዘመቻ እንዲቀላቀል አሳስባለሁ።
  • ጀግናው ማስተር ግርማ ዘለቀ እና ቆራጥ የትግል ጓደኞቹ እንደነ ሲኒየር ቴክኒሽያን አበበ አረጋ፣ ማስተር ቴክኒሽያን አየለ ኃይሌ የመሳሰሉትን ይዞና የአየር ወለድ መለዮ ለባሾችን አሰተባብሮ፣ ከሁለቱም ወገን ከፍተኛ መኮንኖችን አግቶ፣ አብዮታዊ የፖለቲካ ጥያቄ ለአፄው መንግሥት ስላቀረበ፣ የ ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ኃብተወልድ ካቤኔ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ የስንብት ደብዳቤ ለዓፄው አቅርቦ ደም ሳይፋሰስ በሰላም መሰናበቱንና በልጅ እንዳልካቸው ካቢኔ መተካቱን ላንባብያን ሳስታውስ፣ ምትክ የማይገኝላቸው ጠቅላይ ምኒስትር አክሊሉ ላሳዩት አርቆ አስተዋይነትና የፖለቲካ ብስለት አድናቆቴን እየገለጽኩ ነው።
በ1966ቱ አብዮት የኔን ተሞክሮ በተመለከተ በተለይ ለታሪክ ጸሐፈት የሚሆን አንድ መጽሐፍ ለማዘጋጀት ማቀዴን በዚህ አጋጣሚ እገልጻለሁ። ምክንያቱም፣ ጠቅላይ መምሪያው የሚገኝበት ግዙፍ የደብረ ዘይት አየር ኃይል ጣቢያ፦
  • ምሁራን ከአዲስ አበባና ካካባቢዋ እንዲሁም ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ፣ ከአፈሪካና ከእስያ እየመጡ ፣ የተወያዩበት፣ ያስተማሩበት፤
  • ፖሊሲና ፕላን የሚዘጋጅበት፤የአብዮቱን ፍንዳታ ተከትሎ ከባድ የውሳኔ ሀሳቦች የፈለቁበት፤
  • የአብዮቱን ፍንዳታ ተከትሎ ልዩ ልዩ የፖለቲካ ድርጅቶች አባሎቻቸውን በሕቡእ ለመመልመል የተረባረቡበት፤
  • የአየር የአየር ኃይል ሠራዊት ተሰብስቦ የዘውድ ሥርዓትም ሆነ የወታደራዊ መንግሥት በፍፁም ስለማንፈልግ፣ ሕዘባዊ መንግሥት እንዲቋቋም የውሳኔ ሃሰብ የሰጠበት፤
  • የዳበረ ዘመናዊ ቤተ መጻሕፍት የተከማቹበት፤
  • ዘመናዊ ላቦራቶሪዎችና የጥገና ወረክሾፖች የሚገኙበት፣
  • ለ34 ለዩ ልዩ ሙያዎች የሥልጠና ፋሲሊቲ የተዘጋጀበት፤
  • የንጉሠ ነገሥቱ የከፋፍለህ ግዛው ሥርዓት ተንኮል የተጋለጠባት፤
ስፍራ ነው። በእጩ መኮንንነት ተምሬ የተመረቅሁበት፣ ያስተማርኩበት እስካ ከፍተኛ ደረጃ አዛዥነት የሠራሁበት አመቺ ስፍራ እንደመሆኑ፣ መረጃዎችን ማግኘት ቀላል ስለሆነልኝ መጽሐፉን ለማዘጋጀት በእግዚአብሔር ፍቃድ ሥራዬ እንደማይከብደኝ አምናለሁ።



ከአብዮት ፍንዳታ እስከ ወታደራዊ ደርግ ምሥረታ
አብዮቱ ሊከሰት መዳረሻ ላይ ሕዝባዊው ንቅናቄ እየጎለበተ በመሄዱ መንግሥት ተጨነቀ። ሁኔታውን ለማቀዘቀዝ የአድማ መሪዎች ከጦሩ ውስጥ ጃንሆይ ፊት ቀርበው ይቅርታ እንዲለምኑ መንግሥት መላ መታ። የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንደሚባለው!

ሴራው ግን አልሰራም። ከአየር ኃይል ከኔ ጭምር በርካታ መኮንኖችና ባለሌላ ማዕረጎች፣ እስከዛሬ ግልጽ በልሆነልኝ መመዛኛ ተመርጠን ኢዩቤልዩ ቤተመንግሥት ሄደን ለግርማዊነታቸው ታማኝነታችንን እንድንገልፅና በየቦታው የተፈጠረውን አለመረጋጋት እንድናወግዝ የተሰጠንን መመሪያ ለመተግበር፣ በአውቶቡስ ተሳፍረን ወደ አዲሰ አበባ (ሸገር) ጉዞ ጀመርን። ተልዕኳችን ለሚዲያ ፍጆታ የታለመ ተንኮል በመሆኑና እኛ መጠቀሚያ በመደረጋችን ነገሩ በጣም አናደደን። ወደ አዲስ አበባ እሩ መንገድ እንደተጓዝን፣ በታቀደው ጊዜ ቤተ መንግሥት ላለመድረስ፣ እቃ ረስተናል፣ ዩኒፎርም መቀየር አለብን በሚል ሰበብ ሹፌሩ ወደ ደብረዘይት መኮንንኖች ሠፈር እንዲመለስ በፈጠርነው ዘዴ ጊዜ ለማባከን ተቻለ። ዘግይተን ከቤተመንግሥቱ ስንደረስ፣ አዛዣችን ሜጀር ጄኔራል አበራ ወልደማርያም በንዴት ጦፈው ዋናው በር ላይ ጠበቁን። ሌሎች ሰዓታቸውን ጠብቀው የመጡት የምድር ጦር፣ የብሔራዊ ጦር፣ እና የፖሊስ ሠራዊት ተወካዮች የተፈለገውን የታማኝነትና የአድመኞችን ኩነና መግለጫ ካሰሙ በሗላ ዓፄው ስለአሰናበቷቸው፣ አዛዣችን ምርጫ ስላልነበራቸው በብስጭት ተቆጥተው ወደ ቤተመንግሥቱ ግቢ ሳንገባ ከውጪው አሰናበቱን።

የተፈለገውን ታማኝነት ባላመግለፃችን ረክተን ተመልሰን ደብረ ዘይት ከተማ ስንደርስ፣ ያልጠበቅነው ሁኔታ አጋጠመን። የአየር ኃይልና የአየር ወለድ መለዮ ያጠለቁ ባለሌላ ማዕረጎችና ወታደሮች ተሰባጥረው ባንክ ቤቱን አዘግተው ጥበቃውን ተቆጣጥረውታል። ትላልቅ ሱቆች ተዘግተዋል። ወደቤቴ ሄጄ ምሳዬን ከበላሁ በሗላ በግል መኪናዬ ወደቢሮዬ ሄድኩ።
ማስተር ቴክኒሽያን ግርማ ዘለቀ፣ የአየር ኃይል መሣሪያ ግምጃ ቤት ሀላፊ እንደመሆኑ የመጋዘኑን በር ከፍቶ በውስጡ የሚገኙትን የነብስ ወከፍ መሣሪየዎች ለባለሌላ ማዕረጎች (ቴክኒሽያኖች) ካስታጠቀ በሗላ፣ በርሱ መሪነት በሕቡእ ይንቀሳቀስ የነበረው ቡድን ይፋ ወጣና ደብረ ዘይት የምንገኝ የንጉሠ ነገሥቱ አየር ኃይል ከፍተኛ የአመራር ባለሥልጣናት ታግተን በተለያዩ ስፍራዎች የካቲት 18 ቀን 1966 ዓ.ም ታጎርን፡፡ የጦር ሠፈሩም ባሳሪዎቻችን ቁጥጥር ስር ዋለ። ከሻለቃ ማዕረግ በታች ያሉ መኮንንኖች ያልታገቱ ቢሆንም ምንም ዓይነት መሣሪያ ሳይታጠቁ በግቢው (ካምፕ) ውስጥና ውጪ ይንቀሳቀሱ ነበር።

ከላይ ከተጠቀሰው እገታ በሗላ፣ አጋቾች ዐቢይ የፖለቲካ ለውጥ እንዲደረግ በርካታ ጥያቄዎችን ለመንግሥት አቀረቡ። በዚህ ሂደት ውስጥ ማስተር ቴክኒሽያን ግርማ አልፎ አልፎ ከግርማዊነታቸው ጋር በስልክ እየተገናኘ ለሚያቀረቡለት ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ይደራደር ነበር። ለምሳሌ እናንተ በአድማ ላይ እያላችሁ ሱማሊያ የኢትዮጵያን ድምበር አልፋ ብትወር ምን ይደረጋል ብለው ጃንሆይ ሲጠይቁት፣ አድማችንን በቅጽበት አቁመን ወራሪዉን በመግረፍ ይህንን የጋለ ቁጣችንን በጠላት ላይ እናበርዳለን ሲል ማስተር ቴክኒሽያን ግርማ ዘለቀ እንደመለሰላቸው ከእገታ በሰላም ከተለቀቅን በሗላ ለማወቅ ችያለሁ። እውነትም ማ/ቴክኒሽያን ግርማ እንዳለው፤ አብራሪዎች እና ቴክኒሲያኖች ስለአልታገቱ ተዘጋጅተው በተጠንቀቅ ላይ ስለነበሩ ተዋጊ አውሮፕላኖች ከደብረ ዘይት፣ ከድሬዳዋና ከአስመራ አየር ጣቢያዎች በመነሳት፣ ከሶሰተኛው ክፍለ ጦር ጋር በመተባበር ባጭር ጊዜ ውስጥ ውጊያ ለመግጠምና ጠላትን ለማዳሸቅ ይቻል ነበር።

በቁጥጥር ስር የዋልነው ከፍተኛ መኮንኖች በታሰርን በሶስተኛወ ቀን ከያለንበት ተወስደን በባለ ሌላ ማእረጎች ክበብ ምግብ ቤት ምሳ ከበላን በሗላ በአቅራቢያው ከሚገኝ አንድ ሰፊ አዳራሽ ውስጥ እንድንሰበሰብ ተደረገ። ሁለት ባለሌላ ማዕረግ ቴክኒሽያኖች፣ አንዱ ሽጉጥ ሌላው ኦቶማቲክ (ኡዚ) የያዘ ከፊታችን ቆሙ። ዙሪያውን ስመለከት ጥቁር ቱታ የለበሱ ፊታቸው ላይ ቁጣ የሚታይባችው ኦቶማቲክ መሳሪያ የታጠቁ ቴክኒሲያኖች ቆመዋል። ሽጉጥ የያዘው ቴክኒሽያን፣ እምባ እየተናነቀው አስተምራችሁ አሳደጋችሁናል፣ በማህበራዊ ኑሮም ተሳስረናል፣ አበልጆችም የሆን አለን በማለት እርምጃ ለመውሰድ የተገደዱበትን በመግለፅ ላይ እያለ ንግግሩን ሳይጨርስ፣ ከአጠገቡ የቆመው ጓደኛው ከመቅጽበት ሽጉጡን ከጁ ነጠቀውና ድራማው አበቃ። የገረመኝ ነገር ይህ ሁሉ ሲሆን ታጋች መኮንኖች ሁኔታውን ከቁብ አልቆጠነውም፡፡

ድራማው ቢያበቃም እስከዛሬ ያልተመለሱ ጥያቄዎችን አጭሮ አልፏል። ዕውን ሊረሽኑን ኖሯል? ወይስ መንግሥት የአጋቾችን የፖለቲካ ጥያቄ በአስቸኳይ እንዲመልስ ለማስገደድ? የክብር ዘበኛ አዛዠ ሌተና ጄኔራል አበበ ገመዳ የአየር ኃይልን ጦር ሠፈር በመድፍ ኢላማ ወስጥ አስገብቼዋለሁና ጃንሆይ ከፈቀዱልኝ ልምታው ብለው ፈቃድ ጠይቀው ስለተነፈጉ፣ አጋቾቻችን ሕይዎት ለማጥፋት እርምጃ ከመወሰድ ተቆጥበው ይሆን?

ጃንሆይ ምህረት የማድረጋቸውን ዜና ለማሰማት፣ ምክትል የእልፍኝ አስከልካያቸው ሜጀር ጄኔራል አሰፋ ለማ፣ የመጡ መሆኑን አጋቾቻችን አበሰሩን። ከዚያም ከአየር ኃይል ካምፕ ውጪ ጋራ በሩ ተብሎ በሚጠራው ተራራ አቅጣጫ በሚገኝ ጥቅጥቅ ባለ ቁጥቋጦ በተከበበ ገላጣ ሜዳ ላይ ታጋጆች ከፍተኛ የአየር ኃይል መኮንንኖች ብቻ እንድንኮለኮል ተደረገ። ቀደም ሲል ከኛ ጋር ታግተው የነበሩት የአየር ወለድ ጥቂት መኮንንኖች አልነበሩም። ለምን እንደሆነ እስከ አሁን ይገርመኛል።
ምን ሊመጣ ነው ብለን ስንጠባበቅ፣ የአየር ወለድ አዛዥ ኮሎኔል የዓለምዘውድ ተሰማ፣ በጥይት የተሞላውን ዝናር በወገቡ ዙሪያና ከጀርባው በትከሻው ላይ እስከ ጉልበቱ ድረስ አንዠርንጎ መትረየሱን አንግቦ ከጥቂት አጃቢዎቹ ጋር ከቁጥቋጦ ውስጥ ወጥቶ ኩስትር ብሎ ከታጋቾች ፊት ለፊት ቆመ። ነገሩ ያልጠበቅነው እንደመሆኑ ይህ ወራሪ ከጎረቤታቸን በማን ታዞ ነው የመጣብን ሳንል አልቀረንም።
የኮሎኔል የዓለም ዘውድ ወገናዊነት ከማን ጋር እንደሆነ ገና ንግግሩን ሲጀምር ግልፅ ሆነ። ግርማዊነታቸው ይቅርታ ያደረጉልን መሆኑን አበሰረን። ለሠራዊቱም በወር ሰባት (7) ብር ደሞዝ በዓፄው መልካም ፍቃድና ትእዛዝ ለመከላከያ ሠራዊት የተጨመረ መሆኑን አስታወቀን። ዝምታን ያዘለ ተቃውሞ ለጥቂት ጊዜ ሠፈነ። ከዚያ እጄን አወጣሁና ለመሆኑ ደሀው ገበሬ ከየት አምጥቶ ነው የተባለውን የደሞዝ ጭማሪ የሚከፈለን ብዬ ላነሳሁት ጥያቄ መልሱ በደፈናው ገንዘቡ አለ ከየትም ይገኛል ሆነ። ያሳፍራል! ቀጥሎም ከታገትነው ውስጥ አንዱ ኮሎኔል (ጌታሁን እጀጉ) እኛ ታሳሪ፣ እናንተ አሳሪና መሐሪ የተሆነበት ምክንያት እንቆቅልሽ እንደሆነበት አምርሮ ተናገረ። ለዚህ ጠንካራ ተቃውሞ ኮሎኔል የዘውድዓለም ምላሽ አልሰጠም፤ ታጋቾች ኮሎኔሉን በትዝብትና በንቀት ዓይን ይመለከቱት ነበር። ስብሰባውም በዚህ አበቃና ወደ ሌላ ቦታ ተወሰድን። ምንስ አጥፍተን ነው የጃንሆይ ‘ምህረት’ በአየር ወለድ አዛዠ የሚበሰርልን የሚለው ጥያቄ እስከዘሬ ድረስ በአዕመሮዬ ውስጥ ይመላለሳል።
ከኮሎኔል የዓለምዘውድ አሳፋሪ ድራማ ተላቀን ወደ ካምፓችን እንድንመለስ ተደረገና በአየር ኃይል ሠልጣኞች ክበብ አዳራሽ ውስጥ ተሰበሰብን። መልከ መልካሙ አጅሬ ግርማ ዘለቀ ብቅ ብሎ እፊታችን ቆመ። ማራኪው ቁማናው እንዳለ ሆኖ የሚያማምሩት ትላልቅ ዓይኖቹ እንቅልፍ ከማጣት ምክንያት ይመስለኛል ቀልተዋል። ግርማ፣ ከፊትለፊቱ ለተቀመጥነው ከሻለቃ እስከ ብ/ጄኔራል ማዕረግ ላይ ለምንገኝ ከፍተኛ መኮንኖች፣ ስለታሰርንበት ምክንያት እጅግ የሚመስጥ አጭር ንግግር አደረገ። ከአንድ መሪ የሚጠበቅ በሳልና ድንቅ ንግግሩንም፣ “እኛ በያዘችሁት ሥልጣን ስሩበት ብለን ተነሳን እንጂ ልንነጥቃችሁ አይደለም” በማለት ዘግቶ በሰላም አሰናበተን። ጥሪውና መልእክቱ ወቅታዊውን ሁኔታ ያካተቱ ጥርት ያሉ በመሆናቸው፣ ታጋቾች ትንፍሽ ሳንል አንዳች ጥያቄም ሆነ አስተያየት ሳንሰጥ ወደየቤታችን ሄድን። ተዳክሞ የነበረው የመንግሥት አስተዳደር ባስከተለው በደል ተነሳስተው፣ የምናዛቸው ባለሌላ ማዕረጎች የፖለቲካ ለውጥ ጥያቄ እስኪያነሱ ድረስ እኛስ ከፍተኛ መኮንኖች ምን እንጠብቅ ነበር? በበኩሌ መንፈሳዊ ቅናት ተሰምቶኝ እንደነበር አልክድም። ለውጡንም ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ ከልብ ለመደገፍ ወሰንኩ።
መሪ ይወለዳል ወይስ በሥልጠና ይታነፃል? በኔ እምነት ግርማ ዘለቀ ከመሪነት ባሕርዩ ጋር የተወለደ ነው። በየካቲት 1966 አብዮት ያሳየው አመራረና ብስለት ካስገኘው ውጤት ጋር ሲገመገም፣ የመንግሥት ካቤኔ በሰላም ሥልጣኑን ሲለቅ በኢትዮያ ታሪክ የመጀመሪያው ነው።ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየ ዐቢይ ሰላማዊ ለውጥ ነው ለማለት እደፍራለሁ። ለዚህም ድንቅ ክንውን ማስተር ቴከኒሽን ግርማና አብዮታዊ ግብረ-አበሮቹ የሚመሰገኑ ናቸው። ለዚህ አንፀባራቂ ድል፣ ታሪክ ክሬዲቱን  ለግርማና ለትግል ጓደኞቹ እንደሚሰጥ ጽኑ ተስፋ አለኝ።
የካቲት 20 ቀን 1966 ዓ.ም፣ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ኃብተወልድ ካቢኔ የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ለንጉሠ ነገሥቱ  በይፋ ያቀረበው ጥያቄ ከፀደቀ በሗላ፣ የዘውድ ምክር ቤት ሌ/ጄኔራል ዐቢይ አበበ እንዲተኩ ቢያሳሰብም እርሳቸው ፈቃደኛ ሁነው ባለመገኘታቸው፣ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን ተሹመው የአክሊሉ ካቢኔ በሰላም ሊተካ ቻለ። የቀድሞው ካቢኔ በሰላም ከሥልጣን መውረድ በምእራባውያን ዲፐሎማቶች ዘንድ እንደ ሰላማዊና ደም ያላፋሰሰ ለውጥ የተወደሰና የተደነቀ መሆኑን አንድ የፈረንሳይ ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ ለሥራ ጉዳይ ደብረ ዘይት መጥተው ስለነበር እግረመንገዳቸውን ቢሮዬ ጎራ ብለው እንደነገሩኝ አስታውሳለሁ። ምን ጊዜም ምትክ የማይገኝላቸው፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተወልድ፣ ደም እንዳይፋሰስ በማሰብ ላሳዩት በሳል አመራርና ሥልጣን ለመልቀቅ ላደረጉት ውሳኔ የላቀ ምሥጋና ይገባቸዋል እላለሁ።

ከእገታ ከተለቀቅን በሗላ፣ ሥነሥርዓትና ወታደራዊ ዲሲፕሊን በማስፈን አመራር መስጠት አንገብጋቢ ጥያቄ ሆነ። የዓፄው ሥርዓት የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲውን መተግበር ቀጥሎበታል። ስለሆነም ከጎረቤታችን ከአየር ወለድ ጦር ጋር መቃቃር ቀጥሏል። ሕዝባዊ እንቅስቃሴውም እያየለ ቀጥሏል። ስለዚህ ተወዳጁ አዛዣችን ብ/ጄኔራል አሰፋ ገብረእግዚ ሠራዊቱን  ሰበስበው ምን መደረግ እንዳለብት በእሳቸው መሪነት ሰፊ ውይይት ተካሄደ። እጄን አወጣሁና፣ የሀገር መውደድ የሚለካው በክንዳችን ላይ በለጠፍነው ወይም በትከሻችን ላይ በተሸከምነው ማዕረግ ሳይሆን ከእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ከሚመነጭ ፍቅር ነውና፣ ሕዝባዊ እንቅስቃሴውን በሕቡዕ የምትመሩት ባለሌላ ማዕረጎች በዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ ተመካክራችሁበት አቋማችሁን በፍጥነት ወስናችሁ ውጤቱን ለአዛዣችን አስታውቁ ብዬ ሀሳብ ሰጠሁ። ታዳሚው ባንድ ድምፅ በሀሳቡ ተስማማና ያንኑ ሌሊት መልካም ዜና የሚያበስር ወረቀት ተበትኖ አደረ። ሙሉ ወታደራዊ ዲሲፕሊን ሰፍኖ፣ አዛዥና ታዛዠ ተከባበሮ፣ ሠራዊቱ በአንድነት የአየር ኃይሉን ግዳጅ በስነሥርዓት እንዲወጣ በተበተነው ወረቀት ውስጥ መጻፉ በእረግጥም አስደሰታች ነበር። መለዮ ለባሹ የተነሳለትን አብዮታዊ ዓላማ ሳይዘነጋ፣ እንደተለመደው ጢሙን ተላጭቶ፣ አጎፍሮ የነበረውን ፀጉሩን አሳጥሮ ተስተካክሎ፣ እና ንፁህ የደንብ ልብሱን ለብሶ ግዳጁን ለመወጣት ዝግጁነቱነን በተግባር አረጋገጠ።

ወደ ሌላ አርዕስት ከመሸጋገሬ በፊት ከእገታ ከወጣን በሗላ ስለተወዳጀሁት ጀግና ስለ ግርማ ዘለቀ ጥቂት ልበል።
ከእገታ ከወጣን በሗላ ግርማ ዘለቀ ልክ የታገትን እለት ማታ መኖሬያ ቤቴ ድረስ መጥቶ ቤተሰቤን  ለሠፈሩ ጥበቃ እንደተደረገ አረጋግጦላቸው እንደነበር ስለተነገረኝ አድመኞቹ በኔ ላይ ምንም ቅሬታ እንዳልነበራቸው ተሰማኝና ወዳጅነታችን ቀጠለ።
የደርግ አመራር ብቃት ማነስና የሚከተለው የሶሽሊሰት ፍልስፍና ግርማን አላስደሰተውም፡፡ ፍልስፍናው፣ ኢትዮጵያ ለምትገኝበት የፊዉዳል ሥርዓት ፈፅሞ አይሠራም እያለ አጥብቆ ይከራር ስለነበር ከትግል ጓደኞቹም ጋር ሳይቀር ከሶሽያሊስት ርዕዮት አቀንቃኞች ጋር ልዩነት ተፈጠረ።
ደርግ ግርማን የማረሚያ ቤት ሀላፊ አድርጎ በመሾም ከፖለቲካ አርቆት ነበር። አጅሬ ግን ስድቡን አልተቀበለውም፤ ወደ ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ሄዶ ከፀረ-ደርግ ሐይሎች ጋር ለመቀላቀል ሲጓዝ ጎጃም ውስጥ ዳንግላ ሲደርስ ላስቆሙት ወታደሮች እጁን ላለመስጠት በመታኮስ ገሎ በተኩሱ ልውውጥ  እሱም ሞተ። በኔ እምነት፣ አትዮጵያም ጀግና ልጇን አጣች!!!
ፋሺስትን-አርዕድ ሸጋው አርበኛ የብቸናው ተወላጅ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አራዳ ጨርቅ ተራ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ ሲሰቀል፣ አንቺ ኢትዮጵያ ወንድ አይብቀልብሽ ብሎ መራገሙ ይታወቃል። የጎጃሙን ተወላጅ ጀግናውን ግርማ ዘለቀን ያ እርግማን ደርሶበት ይሆን? ጀግኖችን ከማክበሬ የተነሳ ደጃች በላይ ዘለቀን በተለይ በይፋ በጣም ስለማደንቅ፣ ባለቤቴ የፖለቲካ ሰለባ ይሆናል እያለች ትጨነቅ ነበር። ግርማ ዘለቀ ሲሞት እጅግ በጣም አዘንኩ።

ወያኔን በለስ ቀንቶት፣ በአሜሪካ ሁለንታዊ አጋዥነት፣ በጋዳፊ የጦር መሣሪያዎችን በገፍ አስታጣቂነት፣ በዓረብ ሀገሮች አመርቂ ገንዘብ ለጋሽነት፣ በመንግሥቱ ኃይለማርያም ኮብላይነት ታግዞ እናት ኢትዮጵያን ላለፉት 23 ዓመታት ለመቆጣጠርና በታሪኳ ተመጣጣኝ የማይገኝላቸው ዘግናኝ ሰቆቃዎችን በሕዝቦቿ ላይ በጭካኔ ሊፈፅም ቻለ። ይህን በተመለከተ፣ ሰኔ አንድ ቀን 2006 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ከተማ የተደረገው ጀግንነትና ፖለቲካዊ ብስለትን የተላበሰ አፍቃሬ-ለውጥ ደማቅ ሰልፍ፣ ለጎጃም ሕዝብ ያለኝን አክብሮት አሻቅቦታል። ጀግናው ግርማ ዘለቀና፣ በወያኔ ፓርላማ በተቃዋሚነት ተሰይሞ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሲሟገት የነበረው አርበኛው ታላቅ ወንደሙ አድማሴ ዘለቀ (እስር ቤት ተዋወቅነናል)፣ ሁለቱም ካሉበት ሆነው ደማቁን ሰልፈ ሲመለከቱ ከፍተኛ ኩራት እንደሚሰማቸው አይጠረጠርም
ማጠቃለያ
የወያኔ መከላከያና የፀጥታ ሠራዊት፣ የማስተር ቴክኒሽያን ግርማ ዘለቀን ምሳሌ ተከትሎ፣ በሙስና የተጨማለቁትንና በቁልፍ የአዛዥነት ቦታ ላይ የተመደቡትን የአንድ አናሳ ብሄረሰብ ከበርቴ ጄኔራሎችንና ኮሎኔሎችን በቁጥጥሩ ስር በማዋል፣ ወገናዊነቱን ግፍ ለደረሰበት የኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳየት፣ ታሪክ የመሥራት እድል ሳያመልጠው በፍጥነት ቆራጥ እርምጃ መውሰድ የሚያስመሰግነው ይሆናል።
የክቡር አክሊሉ ኃብተወልድን ምሳሌ በመከተል፣ ክርስቲያኑ የኢሀዴግ ጠቅላይ ሚ/ር፣ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በሕዝባዊ አመፅ የሚጥለቀለቁበትን አይቀሬውን ቀን በማሳብ፣ ሕይዎት ሳይጠፋ፣ ደም ሳይፈስ፣ እና ንብረት ሳይባክን ከተቃዋሚዎች ጋር ቢደራደሩ፣ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን አለምንም ቅድመ ሁኔታ ቢፈቱና የፖለቲካውን ምህዳር ቢያሰፉ፣ ከአስከፊ ውርደት ይድናሉ። ኢትዮጵያ ሀገራችንን ግን መለኮታዊ ጥበቃ ከውድቀት ያድናታል።
ወያኔ ላለፉት 23 ዓመታት ሲግተን የነበረው የግፍ ጽዋ፣ በቆራጡ አርበኛ በአንዳረጋቸው ፅጌ ታፍኖ መታሰር ሞልቶ መፍሰስ ጀምሯልና የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንግዲህ ትግዕግሥቱ ተሟጦ አልቋል።ሳይዘገይ መታረም ምርጫው የእሀዴግ ብቻ ነው!!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
rababya@gmail.com

A Call For Justice: Dimtsachin Yisema Washington D.C.

July 27, 2014
TPLF/EPRDF the Ethiopian regime terrorizing it's own people
The Ethiopian-American Muslim community in the Washington Metropolitan area is once again appealing to anybody who cares to listen about the gross human rights violation being committed by the ruthless ethnic based minority government of Ethiopia. We have been raising our voice for the last several years to draw the rest of the world’s attention to the atrocities committed by the Ethiopian government against its own people.
International and Regional Human Rights Watchdogs such as Amnesty International and Human Rights Watch including NGOs and semi-governmental organizations have not only continuously condemned the Ethiopian government’s wholesale Universal Human Rights transgressions, they have also documented it for history. Unfortunately, our plea has so far been ignored by those we trusted the most to stand on the side of justice and liberty. As a result, the dictators in Addis Ababa have been emboldened to continue on their repression in a much wider scale. The Western donor countries, specially, the Obama Administration and the British government who are responsible for most of the foreign aid money Ethiopia receives have so far conveniently opted to look the other way while the minority ruling clique is running a system not that much different from that of North Korea. Are we Ethiopians any less human beings than the people of Ukraine who within minutes of their crises got the undivided attention of the West? How is history going to judge the West – the bastion of democracy – for propping up a dictatorship that has jailed the most journalists in the world, religious leaders and conscientious objectors? We know we are living in a very dangerous world that is infested with terrorism. Why is it not obvious for the West allying with a dictatorship that is terrorizing its own people defeats the purpose of the “War on Terror”? We know nations big and small are driven by their interests, but standing on the side of democracy, justice and rule of law must be unconditional. This is what the West has abdicated from for the last 23 years by standing on the side of the rogue regime in Ethiopia. Is the West really at peace with itself while the so called ‘significant ally’ in the “War on Terror” is terrorizing its own people?
Three years ago, Ethiopian Muslims embarked on a peaceful protest every Friday within the confines of their Mosques after the government closed the only Islamic Higher Education Institute in the country, and unabashedly in contravention to the Constitution of the country imported and imposed on them by diktat the unorthodox Ahbashi ideology. In an earnest attempt to seek redress and stop the interference in their religious affairs, Ethiopian Muslims gathered and elected an Arbitration Committee that started negotiating with the government.
Unfortunately, the government was not moved and convinced. Instead, it tried to use the mediation process to divide the Muslim community, further exacerbating the situation. Needless to say the government’s crackdown that followed resulted in numerous deaths, countless injuries, and arbitrary detentions. As part of the crackdown, about two years ago, the government arrested all the members of the Arbitration Committee and charged them with ‘Treason, Terrorism, and Attempting to Impose the Sharia Law in the country’. These Muslim Community leaders and thousands of others are still languishing in the notorious prisons across the country and being subjected to a vast array of inhumane treatment with no relief in sight. Undoubtedly, the country has been converted into a roofless giant prison.
Today, the scale of the oppression has widened. Muslim students have been banned from praying on college campuses. Several hundred female Muslim students have been expelled from colleges and universities for refusing to comply with the ‘No Hijab’ rules. Hundreds of students have been arrested for standing their grounds facing miscellaneous trumped up charges in kangaroo courts that serve only the twisted political agenda of the government.
Today, the majority of the Mosques in Ethiopia are headed by the ruling party cadres masquerading as true Muslims. Praying is restricted to neighborhood Mosques and IDs are checked at entrances by security agents. Today, it is becoming so difficult to be a Muslim in Ethiopia that Muslim religious leaders and scholars, and the youth are fleeing the country in droves as do followers of other faiths. Even other countries are not safe havens anymore. Recently, Ethiopian security agents abducted three leaders of opposition groups from Yemen and Kenya with the help of corrupt officials in these countries.
On July 18, 2014, while Ethiopian Muslims were conducting their Friday congregational prayer at the Anwar Mosque in the Capital City, they were attacked without any provocation by the much dreaded riot Police armed with gears from the West. As a result, a young man was killed, hundreds were injured and several unaccounted for. Thousands: male, female, old and young were rounded up and transported to a designated location where they were subjected to further beating. Hijabs were forcefully snatched off females’ faces just to humiliate them. A wounded man was dragged out of his doctor’s care and thrown into jail with a bullet still lodged in his back. We want the world to know that such acts of terror are repeated across the country on regular bases. How long does the West stay comfortable looking the other way and giving deaf ears to the plight of Ethiopian Muslims? Back in 1991, the ruling clique negotiated its way to power with the help of the US and the British Administrations. We believe, these two donor countries are responsible more than any other country and have the moral obligation and the leverage to force the dictators in Addis Ababa to submit to the will of the people and restore rule of law in the country before it is too late and the country succumbs into complete chaos.
Dimtsachin Yisema Washington D.C.

ነቀዝ የወጋው ሰብልና ሙስና የነገሰበት ሃገር አንድ ናቸው። – Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ሕዝብ፤ ሙስና እየነዳ ላመጣው ግፍ ለዋጋ ንረት፣ ለኑሮ ውድነት፣ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ተዳርጓል፡፡ ሙስና ከስልጣን ጋር ተጋብቶ እንደ ሸረሪት ድር ተወሳስቧል፡፡
ሙስና በኢትዮጵያ ውስጥ ተስፋፍቶ መንግስታዊ ሽብርተኝነትን አማክሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሕዝብ ዋይታ፣ ለቅሶ ለመሆኑ በቅቷል፡፡ ቢሮክራሲው በሙስና ተዘፍቆ ለስራ ሂደቶች ማነቆ ሆኗል፣ የልማት እንቅስቃሴዎች በመንግስት ሹመኞች ሙስና ተሰነካክለዋል፣ ይህ ነው ለማለት በሚያዳግት ደረጃ ሙስናን ታኮ ግለኝነት ተንሰራፍቷል፣ ስግብግብነት፣ አልጠግብ ባይነትና ማህበራዊ ቀውሶች መገለጫዎቻችን ሆነዋል፡፡ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የመንግስት ለውጥን ተከትሎ የኢትዮጵያ እስር ቤቶችን የሚጨናነቁት በደረቅ ወንጀለኞችና በፖለቲካ እስረኞች ከመሆን ይልቅ በሙስና በተጨማለቁ የመንግስት ሹመኞች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የሃይማኖት መሪዎችና ነጋዴዎች እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፡፡
የመንግስት ሹመኞችና ባለሟሎቹ የሙስናን በሽታውን ወደ ሕዝብ ነዝተውታል፡፡ ነጋዴው ማህበረሰብ እንደወትሮው ወጭ ገቢውን የሚያሰላው ከቀጥተኛ ወጭው ጋር ያተያያዘውን ግዢና ግብር ብቻ አይደለም፡፡ የቀን ጅብ ለሆኑ ሙሰኞች የሚሰጠውን ኮሚሽንና ውጣ ወረዱን ጭምር ነው። ………… ሕዝቡ የኑሮ ውድነት ከበደኝ! የእቃ ዋጋ ንረት አስመረረኝ! ግፍ በዛብኝ! ሸምቶ መቃመስ አቃኝ የሚል ምሬት ሲያሰማ.. ሹመኞች አፍ ለማስያዝንና ለማሸማቀቅ ይሽቀዳደማሉ፡፡ “በገበያ ስርዓት ነው የምንመራው የሚችል ይገዛል፡፡ ያልቻለ አይገዛም” ይባላል፡፡ ገፋ ሲልም “አጭበርባሪ ነጋዴ ስናሳድድ አንገኝም!” የሚል ማበረታቻ አከል መልስ ለሕዝቡ ይሰጣል፡፡
የተረጋጋ የነበረውን የግብይት ስርዓት ያለበቂ መነሻና ጥናት የዋጋ ጣራ በማወጅ፣ ውቅያኖሱን ደብድቦ አሳውን የሚረብሽ ፖሊሲ ይዘረጋል፡፡ አለመረጋጋቱን ታኮ ነጋዴው እጥረትን፣ የጥራት ችግርን፣ ቅሸባን፣ ሚዛን ማጓደልን አይነተኛ የስራውና የትርፉ መሰረት ያደርገዋል፡፡ ሕዝብ፤ ሙስና እየነዳ ላመጣው ግፍ ለዋጋ ንረት፣ ለኑሮ ውድነት፣ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ተዳርጓል፡፡
ዛሬ በኢትየጵያ ውስጥ ቁሳዊ ሙስና እጅና እግር አውጥቶ በሕዝብ ሃብት ላይ እየተጫወተ ይገኛል፡፡ ሃምሳም ስልሳም ሚሊዮን ብር እንደ ቀልድ ከመንግስት ካዝና ሲጠፋ መስማትና እነ እገሌና እነ እንቶኔ ተጠርጥረው ስለተያዙ የተዘረፈውን ለማስመለስ ጥረት ላይ ነን ማለት የተለመደ ሆኗል፡፡ ዘራፊው መጀመርያ ወንጀሉን ያምናል፡፡ ቀጥሎ ከዘረፋው ምንዳ ውስጥ ፍርፋሪ ቆንጥሮ በመስጠት ፣ አምስትና አስር ዓመት ይፈረድበታል፡፡ ለአንድ አመት አስር ሚሊዮን ነው! ምን ችግር አለው! ለጥቆም ደግሞ በአመክሮ ወይም በምህረት መፈታት አለ፡፡
እንዲህ እየተደጋገፉና እየተመቻቹ የሚሄዱ የስልጣንና የጥቂት ነጋዴዎች ሙሰኝነት ስር እየሰደደ ባህል ሆኖዋል፤ መስራትና ማጭበርበር ልዩነታቸው እየጠፋ ነው፡፡ በይና አስበይ በአንድ ቦይ እየፈሰሱ ማን ማንን ይገስጻል፡፡ የሕግ ውክልና የተሰጠው ሹመኛና ሙሰኛ ነጋዴ የሙስናው ፍሬ እኩል ተቋዳሽ ከሆኑ ሕግ ማስከበርም ሆነ ማክበር ፈጽሞ ያዳግታል፡፡ሙሰኛ ነጋዴውም ዋጋ ለማናርና ለመቆለል ምክንያትም ሆነ ስጋት የለውም፡፡ በአቦ በስላሴ እያማካኙ ቀን በቀን ዋጋ መቆለል ነው፡፡ ሙስና ከስልጣን ጋር ተጋብቶ እንደ ሸረሪት ድር ተወሳስቧል፡፡ ለማን አቤት ይባላል! ማንስ ያዳምጣል! መፍትሔስ ከወዴት ይገኛል? ማለት ውሎ አድሮ ቀመሩ “ሙስናን ማጋለጥ ለመላላጥ” ወደ ሚል ከባድ ፍርሃት እንዳይለወጥ በቅጡ ማሰብ የግድ የሚልበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ #ምንሊክሳልሳዊ