Monday, 22 February 2016

የካቲት 12, 1929 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሃዘን ሞልቶ የፈሰሰበት ቀን (አብራሃም ለቤዛ)

Home » ጦማሮች፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም... » የካቲት 12, 1929 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሃዘን ሞልቶ የፈሰሰበት ቀን (አብራሃም ለቤዛ)

የካቲት 12, 1929 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሃዘን ሞልቶ የፈሰሰበት ቀን (አብራሃም ለቤዛ)

Yekatit 12 Square, Addis Ababa, Ethiopia
አብራሃም ለቤዛ
ፋሺሰት ጣሊያን ከ40 ዓመት በኋላ የአድዋን ድል ለመበቀል አትዮጵያን ወሮ ፤ በንጉሱ ፊት አውራሪነት የተመራው ጦራችን በአቅም ማነስና በአንዳንድ ባንዳዎች (ከE.B.C. የተዋስሆት ቃል ነች) ጭምር የፋሺስት ጦር ታግዞ በማይጨው ጦርነት ሺንፈት ቢጠናቀቅም ነገር ግን ፋሺስት በወረራ በቆየባቸዉ አምስት ዓመታት አንድም ቀን ኢትዮጵያን በሰላም አልገዛም፡፡
አርበኞች በዱር በገደል እራሳቸውን እያደራጁ በደፈጣ አደጋ እየጣሉበት የእግር እሾክ የሆኑበት ሲሆን ፋሺሰቱም በመርህ ደረጃ በያዘው የዘረኝበት አባዜው የአገሬውን ህዝብ የሰዓት እላፊ በማወጅ እንዲም እንደ አፓርታይዱ የደቡብ አፍሪካ ስርዓት ለወራሪው ዜጎች ብቻ የተፈቀደ መኖሪያ ሰፈር በመገንባት ፤ ጣሊያን ሰፈር መጥቀስ ይቻላል ፡፡ በተጨማሪም አገሬው ብቻ የሚገበያይበትን የገበያ ቦታ በመከለል በዘረኛ ፖሊሲው ይታወቃል፡፡ የዛሬ መርካቶ ገበያ አገሬው ከነጭ ወራሪዎች እንዳይገናኝ ተብሎ የተሰራ የገበያ ቦታ ነው፡፡
የፋሺስት ዘረኛ ፖሊሲ የከፋፍለህ ግዛ መርሁን በሚገባ ተጠቅሞል፡፡ በወራራ ወቅት ያጋጠመውን የኢትዮጵያ አርበኞች ከባድ ምከታ ለመከፈፋፈል ይመቸው ዘንድ ለሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ከአማራ ጭቆና ነጻ ላወጣህ ነው የሚል ከፍተኛ የሆነ የፕሮፓጋንዳ ስራ ሰርቶል፡፡ ምን ይህ ብቻ፤ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን የሃይማኖት ነጻነት የላችሁም እና እኔን ፋሺስቱን ብትቀበሉኙ ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት የበላይነትን ለእናንተ እሰጣለሁ በማለት ኢትዮጵያዊያንን በማበጣበጥ ወረራዉን የተሳካ ለማድረገወ ከንቱ ሙከራ አድርጎል፡፡ ታላቁ የአንዋር መስጊድ በጣሊያን ወረራ ወቅት የፋሺስጥ ጣሊያን የተንኮል ፕሮጀክት አካል ቢሆንም ፋሺስት ከኢትዮጵያ ሲወጣ የመስጊዱ ግንባታ ያላለቀ ቢሆንም ነገር ግን ንጉስ አጼ ሃይለስላሴ አስተዋይነት በእቴጌ መነን የበላይ ጠባቂነት የመስጊዱ ስራ እንዲጠናቀቅ ተደርጎል፡፡
ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ከወረራ በኋላ የምስራቅ አፍሪካ ግዛቱን በስድስት ግዛቶች ከፋፍሎ ሲያስተዳድረ የተጠቀመው ከዘረኛ ፖሊሲዉ የሚቀዳዉን የቋንቋ አካለል ሲሆን በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ኮርጆ እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ ወያኔ የኮረጀው የቋንቋ አካለሉን ብቻ ሳይሆን የአማራ ግዛትን በአንድ ወይም በሌላ መንገድ መቦጠጥን ነው፡፡ በዚህ ሰሞን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ያነሳዉ የማንነት ጥያቄ ፍትሃዊ እና የወያኔ ህገመንግስት የሚደግፈው ቢሆንም፤ በአምስት አመት የፋሺስት ወረራ ዓመታት ብቻ አካባቢው ጎንደር ባለው የፋሺስት ግዛት እንደራሴ እንዲተዳደር ስላልተፈለገ አስመራ ባለው እንደራሴ ስር ኤርትራንና ትግራይን በሚያጠቃልለው ግዛት ስር እንዲሆን ተደረጎል፡፡
በፋሺስት ጣሊያን የወረራ ዓመታት ስድስቱ የምስራቅ አፍሪካ ግዛቶች 1. ኤርትራ እና ትግራይ (አስመራ ላይ) 2› አምሃራ (ጎንደር ላይ) 3. ኦሮሞና ሲዳማ (ጅማ ላይ) 5. ሀረር (ሀረር ላይ) 6. ኦጋዴንን ጨምሮ ሶማሊያ (ሞቃዲሾ ላይ) ነበር፡፡
በኤርትራ ትውልድ ሃገራቸው እና በኢትዮጵያ ላይ ፋሺስት ጣሊያን እየተከተለ ያለው የዘረኝነት ፖሊሲ ስላንገሸገሻቸው አብራሃም ደቦጭ፤ ሞገስ አስገዶም እና ስምኦን አደፍርስ የተባሉ ትውልደ ኤርትራዊ ኢትዮጵያዊያን በግራዚያኒ የኔፕልስ ልኡል ልጅ የልደት በዓል ለማክበር በእለቱም ቸርነቱን ለማሳየት በአዲስ አበባ ለሚገኙ ደሃዎችንና አካል ጉዳተኞችን ምጽዋት ለመስጠት በተዘጋጀበት ሰዓት የእጅ ቦምባቸውን በወርወር ከፍተኛ መቁሰል አደጋ አድርሰውበታል፡፡
ጣሊያን ወትሮም ፋሺስት ወራሪ ሃይል ነው እና የቦምብ አደጋውን ለመበቀል የተሰማሩ የፋሺስት ወታደሮች በእለቱ በእንግድነት የተሰበሰቡት ኢትዮጵያዊያንን ፤ ደሃዎችንና አካልጉዳኞችን ጨምሮ የአዲስ አበባን ህዝብ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ጨምጭፎል፡፡ የታሪክ ድርሳናት እንደሚያመለክቱት በዚህ ጭፍጨፋ ሰላሳ ሺ (30000) ኢትዮጵያዊያን ተጨፍጭፈዎል፡፡ ህጻናት ሴቶች ሳይቀር የተጨፈቸፉ ሲሆን የፋሺሰት ወታደሮች የኢትዮጵያዊያንን ጎጆዎች በማቀጠል ፤ ከእሳት ለማምለጥ የሚሞክራዉን እንደ አዳኝ ግዳይ ጥለዋል፡፡
የዛሬ 79 ዓመት ፤ የካቲት 12 1929 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሃዘን ሞልቶ የፈሰሰበት ቀን ሲሆን ይህን ቀን ስናስታዉስ መስዎት ለከፈሉት ውድ ኢትዮጵያዊያን ምስጋና እያቀረብን ነገር ግን አሁን ወያኔ/ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ምድር ፈልቆ በዘረኛ ፖሊሲዉ ህዝብን ከህዝብ ፤ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጨውን ፤ የመብት ጥያቄ የሚያቀርቡ የህብተሰብ ክፍሎች ላይ የሚያደርሰውን ጭፍጨፋ በመታገል መሆን አለበት፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች፡፡

No comments:

Post a Comment