ዛሬ እየሰፋ እየገዘፈና ጉልበት እያገኘ የመጣው ህዝባዊ እንቢታ ከአረቡ አገሩ ህዝባዊ አልገዛም ባይነት የጀመረ ይመስለኛል። ያኔ ከዚህ ስርአት በዚህም መንገድ መገላገልም ይቻላል ለካ? የሚለው እሰቦት በአይምሮው ያልዞረ ኢትዬጵያዊ ነበር ለማለት አይቻልም። የስርአቱም ደጋፊዎችም ቢሆኑ በግልባጩ እንቅልፍ ያጡበት ጉዳይ ነበር። አልገዛም ባይነቱ በኛ አገር ይሄ- ያ ይጎድለዋል። ይህ አደጋ አለው። በዚህ አንመሳሰልም ይሉ የነበሩትም ቢሆን ግምት ውስጥ አስገብተው አስበውበት ስለነበር ነው። ሀላፊነት ወስደው ይሰሩበት የጀመሩ ስብቦች እርግፍ አድርገው ቢተውትም። ድርጅቶች የስትራተጂ ለውጥ ቢያደርጉና ትኩረታቸው ወደሌላ ቢያዘነብልም ሂደቱ የሚገታ አልሆነም። የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ትግል በኛ አገር ተጨባጭ ሁናቴ ህዝባዊ እንቢተኝነት ማድረግ እንደሚቻል ያስረገጠ ሆነ። አሁን ያለበትን ደረጃ የበዛነው እጃችንን አጣምረን እያየነው ቢሆንም ነፃ የሚያወጣን ትግል ነው። አገዛዙ እንደስርአት መቀጠል የማይችልበት ደረጃ ደርሷል።ጊዜው እንደ አንድ አገር ህዘብ ከዚህ ዘረኛ፤ አድሏዊ ፤ ጨፍጫፊና የደናቁርት ስርአት መገላገል እንፈልጋለን አንፈልገም? የሚለውን ጥያቄ የሚያስነሳ ሆኗል።
መንገድ አለመዝጋት ከዘጋችሁ መልሶ ህዘቡ በደቦ ወጥቶ ካልሆነ በወታደር ሀይል ሊከፍተው የማይችል አድርጋችሁ ዝጉ። ሁሉም ያስፋልት መንገድ ላይ ከክምር ላይ ክምር ብቻ እስከጭራሹ ሊነዳበትና ሊፀዳ የማይቻል ማድረግ ያስፈልጋል። በየተወሰነ እርቀት ተቆፍሮ ጉርጓድ ማበጀቱም ጥሩ ነው። ማፍረሻው ከተገኘ ድልድዬችንም አፍርሱ። ትግሬ ወያኔዎች በቀጣይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ለማድረግ የሚያስችላቸውን ፖለቲካ እየሰሩ ነው። አንዳንድ ለለውጥ ቆመናል የሚሉም የድርሻቸውን እገዛ እያደረጉም ነው። ጫጩት ፊት ፈንግል እንደማይወራ ጠፍቶ ግን አይደለም። ለማንኛውም ዝም ብለህ ተጨፍጨፍ የሚል ህግ የለም። ትግልም አይደለም። እራስህን በሁሉም መንገድ ተከላከል። የሚከፋቸውና ፖለቲካ ሊሰሩበት የሚሞክሩ እንደሚኖሩ ይታወቃል። ስህተት ጥበቃ ለጉድ አቆብቅበዋል። ያ ችግራቸው ነው። ተገዳላይ ሆይ ትክክልና አግባብነት ያሌለውን የግድ መደረግ ካለበት ትለያለህ። “የሚካሄደው ትግል ነው”። የሚቻልህን አይደለም ከሚቻልህም በላይ ጥንቃቄዎችን በያዝከው መንገድ ማድረጉን ቀጥል አለቀ።
መንገዱ ይዘጋ ያኔ ሊገድል ባገሬው የተበተነው ዳቦ በታንክ ይቀርብለት እንደው እናያለን። ለማንኛውም ከመዓከሉ ተቆርጠው የሚቀሩ ወታደሮች የህዝብን ትግል መቀላቀል መፈለጋቸው ስለማይቀር ጥሪም ማድረግ ግንኙነት መፍጠርና፤ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ያስፈልጋል። ትግሉን የተመለከተውን በዚህ ልዝጋው የኦሮሞን ህዘብ ከመፍራትም ሆነ ከመጥላት ብቻ በየትኛውም ሰበብ ይሁን ይህን ትግል ከዳር ሆነን ባንመለከተው ኖሮ በዚህ ሳምንት ውስጥ ይህን ስርአት ተገላግለን ነበር። ይሄኔ ነፃ ህዝቦች ነበርን።
ጥያቄ 1. አሁን ኦሮሚያ ውስጥ እየሆነ ያለው ምንድን ነው?።
ሀ. ግርግር ለ. ግጭት ሐ. ስሜታዊነት መ. መልሱ ከነዚህ ውስጥ አንዱም አይደለም።
ሁላችንም ቢገባን ይህ ህዝብ ለኢትዬጵያዊነት የከፈለው መሰዋትነት ለሮሞነቱ ከከፈለው መሰዋትነት እጅጉኑ የበዛ ነው። ድሮም ቢሆን እንዳአገርና ህዝብ የማይታለፍ የሚመስል ችግር ውስጥ በተገባና ባጋጠመ ጊዜ ሁሉ ሊመዘን የማይችል መሰዋትነትን ከፍሎ አሻግሯል። ኢትዬጵያዊነትን አስቀጥሏል።የዛሬውም ከዛ የተለየ አይደለም። ኢትዬጵያ ትኖራለች። ሊያውም ዲሞርራሲያዊት፤ የዜጎች መብት የሚከበርባት፤ እኩልነት የሰፈነባትና የበለፀገች ሆና። ለዚህ ባህሉ፤ አናኗሩ፤ በሰከነ ሁኔታ መነጋገርና ማሰብ የሚችል መሆኑና አናሳ አለመሆኑ ተጨምሮበት ዛሬ ላይ ሆኖ በልበ ሙሉነት ይህን ለመናገር ያስደፍራል።
እንግዳ የሆነብንና አልመቸን ያለው ይህ ህዘብ ሁሉ ነገር ክሽፈት እየሆነ ስለተቸገረ መዘወርያው ላይ የሚገባውን ቦታ ማግኘት ወሳኝ መፍትሄ አድርጎ መውሰድ ነው። የሚገባውን ድርሻ ይዥ ወሳኝ በሆነ ሁኔታ በአገራዊ ጉዳይ ላይ አስተዋፆ ካላደረኩ ከዚህ የቁልቁለት መንገድ መውጣት አይቻልም ሲል አጥብቆ ማመኑ ነው። እዛች አገር ላይ የተንጋደደው ሚዛኑ ይስተካከል ብሎ በመጮህ ብቻ ሊስተካከል እንደማይችል ማወቁ ነው። ይህ ፍላጎቱና ድምዳሜው ትግሉን በኦሮሞነትም በኢትዬጵያዊነትም እንዲያካሂድ ግድ ማለቱ የፈጠረው ብዥታ ነው። በእርግጥ ይህ ህዝብ ከኢትዬጵያዊነት ጋር ያለውን ቁርኝት ሙሉ በሙሉ አውጥቶ በማየት ረገድ አንዳንድ የኦሮሞ ምሁራኖች ጋርም ስህተቱም ብዥታውም አለ። ለዚህ ገፊ የሆነው ምክንያት ይህን ህዝብ ጠልቆ ካለማወቅና ስር ከሰደደ ጥላቻ የሚዥጎደጎደው የዳቦ ስም ብዛትና ስድብ ነው። ዘረኛ፤ ጠባብ፤ ጎጠኛ፤ ሰውነት ደረጃ ያልደረሰ አውሬ…… ማቆሚያ የለውም። ያም ሆነ ይህ ግን በመጨረሻ ዲሞክራሲያዊት የሆነች ኢትዬጵያ ነው የምትኖረን። በነፃነት መምከርና ውሳኔ ላይ ሲመጣ የተንዘላዘለውን ሀሳብ እንደሚገርዘው ጥርጥር የለኝም።
የዶ/ር ብርሀኑን ንግግር ደጋግሜ አዳምጬዋለው። የኦሮሞን ህዝብ ትግል በሚመለከት የተናገረው ጠቅለል አድርጌ የተረዳሁት እየሞቱ ነው እዘኑላቸው። ግን ? በሚል አይነት ነው። “አይታችሗቸዋል” እያለ ሲያወራ ጭቃ እያቦኩ እቃቃ ስለሚጫወቱ የኬንያ ህፃናት የሚያወራም መስሎ ተሰምቶኛል። “ስለማንነትና ዲሞክራሲ ግንባታ” የተናገረው አዳራሽ ሙሉ ጭብጨባ ስለተቸረው፤ ካዛም በሗላ ብዙ ዶ/ሮች ድንቅ ትክክል የሆነ ንግግር ስላሉት ትክክል ነው ብለን እንውሰደው። ለኔ ግን ገና አልገባኝም። እንዲገባኝ ማንነት ማለት ምንድን ነው። ብዙ ማንነት ነው ያለው ስለየትኛው ማንነት ነው?። ማንነት ተፈጥሯዊ ነው ፈልገን የምንይዘው ነው?። ማንነት ላይ ያልተመሰረተ ፖለቲካ ማካሄድ ይቻላል ወይ?። ዲሞክራሲ በሰፈነባቸው አገሮች ማንነት የለም ወይ?። ማንነት ለዲሞክራሲ ግንባታ እንቅፋት የሚሆነው እንዴት ነው?። ንግግሩ ላይ ለዚህ ድምዳሜው አስረጅ አድርጎ ያቀረባቸውን አስረጆች ተያያዥነት አላቸው የላቸውም?። ብዙ ብዙ ጥያቄ አጭሮብኛል። በመጨረሻ የምደርስበት ድምዳሜ ዶ/ር ብርሀኑ ያለው ሊሆንም ላይሆንም ይችላል።
ለሁኑ አሁን ባለው ያገራችን ተጨባጭ እውነታ ትክክለኛ መስሎ የሚታየኝ ግልፅ አድርጌ ላስቀምጥ። የማንነት በዋናነት የኦሮሞ ህዝብ የማንነት ፖለቲካ ኢትዬጵያን በቀጥታ ዲሞክራሲያዊት የሚያደርግ ነው። እንደውም ከዚህ ውጪ ኢትዬጵያ ዲሞክራሲያዊ ልትሆን የምትችልበት እድል ዚሮ ነው። እንዴት? የሚለውን ከፈለጉ ዶ/ር ብርሀኑን ጨምሮ ሌሎችም እንደኔ ጥያቄዎችን አውጥተው ተመራምረው ስህተተኛ ያድርጉኝ። እንደውም ይህን የተረዱ ምሁራን ኦሮሞ ፖለቲካው ላይ ተፅኖ አድራጊ ከሚሆን ከሚል ነው ለኢትዬጵያ በእርግጥ ዲሞክራሲ ያስፈልጋታል ወይ? በማለት ፈራ ተባ እያሉ ጥያቄውን ማንሳት የጀመሩት። እይታዬን ከበድ ላድረገውና በድጋሚ በመሬት ላይ ካለው ተጨባጭ እውነታ በቀጣይ ለስልጣን እራሳቸውን ከሚያዘጋጁት ውስጥ ከኦሮሞ ብሄርተኞች ውጪ ያሉት በሙሉ ዲሞክራሲያዊ ሊሆኑ አይደለም እስከዛሬ ከነበሩን አንባገነኖች የከፉ ጨፍጫፊ አንባገነን ሳይሆኑ ስልጣን ላይ አንድ አመት መዝለቅ አይችሉም።
እንግዲህ ዲሞክራሲ ሰላማዊ የበለፀገች ኢትዮጵያ እንድትኖር ካለው ወሳኝነት አኳያ በእርግጥ ማነው ለዚህች አገር አንድነት አደጋ ሊሆን የሚችለው የሚለውን ጥያቄ ሁሉ ያስነሳብኛል። እኔም አገር እንዲኖረኝ እፈልጋለዋ።
ኦቦ ጀዋር አትቸኩል። ብዙ እየሰራህና ትክክለኛነት እያለህ ስህተት ታበዛለህ። የምን ጠላትነት ነው የምታወራው። ጠላትነት የለም። የማንስማማበት ጉዳይ አለ ምን አለ። እውነቱን ልንግረህ ያንን ትውልድ መሰልከኝ። ለነገሩ አንተም አፍሮ ታበጥራለህ መሰለኝ።
አቶ ግርም ካሳ የምን መጨራረስ ነው የምታወራው። ደሮም ሰላማዊም ታጋይም እንዳልሆንክ ጠርጥሬያለው። ሰላማዊ መጨራረስ ነው በለን ደግሞ። መጋኛ መንዘላዘያህን ይጨርሰው ሌላ ምን እላለው። እሱም እኔም ስለማናነበው ቢሞትም ዝም ብለህ ለመልስ ዜናዊ ግልፅ ደብዳቤ ፃፍ። ላስታውስህ አምሳ አንደኛ ግልፅ ደብዳቤ ላይ ነበር ያቆምከው።
ብሄራዊ ጭቆና ያብቃ።
ዳዊት ዳባ
No comments:
Post a Comment