(ዘ-ሐበሻ) በነቀምት ከተማ የአጋዚ ሰራዊት ለ3 ተከታታይ ቀናት በሕዝብ ላይ እየተኮሰ ነው:: እንደ ምንጮቻችን ገለጻ በዛሬው ዕለት በከተማው የሚሰማው የጥይት ጩኸት በርትቷል:: በዚህም ከተማዋ እጅጉን ታምሳለች::
በነቀምት ከትናንት ምሽት ጀምሮ በአጋዚ ሰራዊት በተተኮሰባቸው ጥይት በርካታ ወጣቶች የቆሰሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል የስድስቱ ማንነት ታውቋል:: 2 ሰዎችም እንደሞቱ እየተነገረ ሲሆን ዘ-ሐበሻ ይህን ለማረጋገጥ እየጣረች ነው::
በቀለም ወለጋም እንዲሁ መረር ያለ ተቃውሞ እየተደረገ ሲሆን ሕዝቡ ዱላ በመያዝ አደባባይ በመውጣት እየተቃወመ ይገኛል:: በተለይም በቀለም ወለጋ ሕዝቡ ስለነፃነት እየጠየቀ ሕወሓት አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ በመጠየቅ ላይ ይገኛል::
በምስራቅ በምስራቅ ሐረርጌ ቃንጫ ከተማ ባለው ተቃውሞ ሕዝቡ መንገዶችን ሁሉ በድንጋይ እና በእንጨቶች በመዘጋጋት በአካባቢው የሚደረግን የመንገድ ትራንፖስርት አግዷል:: የአጋዚ ሠራዊት ድንጋይ እና እንጨት ማፈሻ መሣሪያዎችን በመጠቀም መንገዶችን ለመክፈት ቢሞክርም ሰልፈኞቹ በድጋሚ በመዘጋጋት እንደገና ተቃውሟቸውን ቀጥለዋል::
No comments:
Post a Comment